ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ: ፓትርያርኩ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ሲሉ መዋቅራዊ አሠራርን በእጅጉ የሚፃረረውን አካሔዳቸውን እንዲያጤኑ አሳሰቧቸው፤ ቋሚ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን መመሪያ ተፈጻሚነት አግዷል

 • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ፓትርያርኩ ትላንት ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሕግ አግባብ ውጭ ለሾሟቸው ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች የምደባ ደብዳቤ እንደማይጽፉ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ አስታውቀዋል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ፤ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አስተያየታቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ አዝዟቸዋል፡፡
 • አሠራሩ፣ ምርጫው እና መመሪያው ተቀባይነት የሚኖረው ሥራ አስኪያጆቹ ‹‹በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ተመርጠው ቀርበው ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር በአንድነት የጋራ ስምምነት ተደርሶበት በፓትርያርኩ ሲሾሙ ነው፡፡››

*        *        *

His Grace Abune Kelemntos

 • ‹‹ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ለፓትርያርክ ተጠሪ ኾኖ አያውቅም፤ ሊኾንም አይችልም፤ የሕግ ድጋፍ ስለሌለው፡፡ ይህ ያልተለመደ የሥራ ሒደት ብቻ ሳይኾን ከሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቃለ ዐዋዲው እና ከአገሪቱ የሕግ አሠራር ጭምር ውጭ ኾኖ ተመልክቸዋለኹ፡፡››
 • ‹‹የሥራ አስኪያጅ ምርጫው እና የተሰጠው መመሪያ ከትዝብት ላይ የሚጥል መኾኑን ተረድተውልን ለቤተ ክርስቲያን ሰላማዊ አሠራርና ለኹላችንም ሰላም ሲባል ውሳኔዎን እንደገና እንዲያጤኑት እያሳሰብኹ በተሰጠው መመሪያ እንዲኹም በሥራ አስኪያጅ ምርጫ የማልስማማና ለማስተናገድ የምቸገር መኾኔን ለቅዱስነትዎ ሳቀርብ በታላቅ ትሕትና ነው፡፡››

/ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፤ የከምባታ ሐዲያና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ለፓትርያርኩ ከጻፉትና ለቅዱስ ሲኖዶስ በግልባጭ ከአሳወቁበት ደብዳቤ/

Advertisements

18 thoughts on “ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ: ፓትርያርኩ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ሲሉ መዋቅራዊ አሠራርን በእጅጉ የሚፃረረውን አካሔዳቸውን እንዲያጤኑ አሳሰቧቸው፤ ቋሚ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን መመሪያ ተፈጻሚነት አግዷል

 1. 12162129mk21 March 20, 2015 at 5:23 pm Reply

  enes balsasat patriyariku lay tinat bikahed emertalhu, ene enja…. yasasbegnal… esachew lay yalew yesew chana bcha aymeslegnim, erasachew b/k/n lay yemiadersut bedel ale mesel . so, ebakachu ersachew yemistekakelubet or yemiwegdubet menged binor emertalehu!!!!! gn lehulum egziyabher zim aylm !!!!

 2. yemane March 20, 2015 at 9:18 pm Reply

  እግዚአብሔር ይባርካችሁ ጥሩ ነገር አሰማችሁን የተቻኰለ እና ቅዱስ ሲኖዶሱ ያልመከረበት አሰራር መልካም መስሎ አይታየኝም እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ከፈተና ይጠብቅልን።

 3. yemane March 20, 2015 at 9:29 pm Reply

  ጥሩ ነገር አሰማችሁን በሆነው ነገር አዝነን ነበር አባቶቻችን በርትተዋል። አሁን አምላካችን ለአባቶቻችን ፅናቱን ይስጣቸው።

 4. Anonymous March 20, 2015 at 11:54 pm Reply

  ፓትርያርኩ የሃሳብ እንዲሁም የካድሬነት እና የዘረኝነት ዝሙት ላይ ናቸው

 5. Anonymous March 21, 2015 at 6:48 pm Reply

  zendro manen yetamenal

 6. Anonymous March 22, 2015 at 1:00 am Reply

  Egziabher betekiristianachinin yitebik, lenendezih aynetoch tenkara abatoch tsinat yistilin.

 7. Anonymous March 22, 2015 at 6:34 am Reply

  ተሀድሶ መናፍቅ + ጸረ-ተዋህዶ ‹‹ካድሬ›› + ሙዳይ ምጽዋት ገልባጭ ሙሰኛ = የቤተክርስቲያን የጥፋት ህብረት

  የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች
  ውጤት ነው!!
  “ክፉዎች ሠራተኞችን እወቁባቸው” !!
  ስለ ጽዮን ዝም አልልም ስለ ኢየሩሳሌም ጽጥ አልልም ኢሳ. 62፣1

 8. Anonymous March 23, 2015 at 6:27 am Reply

  ጥፋቱ የፓትርያርኩ ነው፡፡ከላይ አቡነ ማቴዎስን፣ከታች በልዩ ሀገረ ስብከታቸው አቡነ ቀሌምንጦስን ሲያስቀምጡ በነዋሪው አካባቢያዊነት ደንብ መሰረት የአንድ መንደር ሰዎችን በላያቸው ላይ አንግሠው ራሳቸውን ከጨዋታ ውጭ እያደረጉ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባ ነበር፡፡አቡነ ማቴዎስ የፓትርያርኩን ደብዳቤ አልመራም ካሉ፣አቡነ ቀሌምንጦስም ደብዳቤዎትን አልቀበልም ካሉ ድርጊቱ መፈንቀለ – ፓትርያርክ ሆነ ማለት ነው፡፡በሌሎች አህጉረ – ስብከቶች ያን ያህል የማይደረገውን የቋሚ ሲኖዶስ ጣልቃ ገብነት በፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት ላይ ለማስተግበር በተደጋጋሚ የሚካሄደው ሙከራም የፓትርያርኩን ሥልጣን ሆን ብሎ የማሳነስ ዘመቻው አካል ነው፡፡ዘመቻው አዝማቾች ተመድበውለት በእቅድና በዐላማ የሚመራ ሲሆን ውስጡ ሲገለጥ ትርጓሜው ዘረኝነት ሆኖ ይገኛል፡፡ሽፋኑ ግን የቤተክርስቲያን ቅናት ነው፡፡

  • Anonymous April 19, 2016 at 6:24 am Reply

   min lemalet tasibo yihon?

 9. Anonymous March 23, 2015 at 8:06 am Reply

  ቅዱስ ፓትርያርኩ መንፈሳዊነት ቢኖራቸውም በዙሪያቸው ባሉ ጋሬጣዎች መሥራት የሚፈልጉትን በተግባር ማሳየት ተስኗቸዋል። ኑረዲን ኤልያስ ከትናንት እስከ ዛሬ በቤተክርስቲያን የሚፈጽመው ችግር እስካልተፈታ ድረስ የሚሰራው ስራ ትርጉም አልባ ይሆናል።አሁን ደግሞ በቤተክህነቱ የየደረሰውን ስራ ልጠቁማችሁ።አባ ቃለ ጽድቅየተባለውን መነኩሴ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እያለን በደንብ አድርጌ አውቀዋለሁ። በመናፍቅነቱ ወደር የማይገኝለት ሰው ነው። ከዚያ ከወጣ በኋላ አሰላ ኘድኀኔዓለም ተመድቦ ነበር። ነገር ግን ኑፋቄያዊ ትምህርቱን ለማስተላለፍ ቢሞክርም ምእመናን ያን ማድረግ ባለመቻሉ ብዙም አልቀጠለበትም። ከአሰላ በኋላ ወደ ምድረ አሜሪካ ሄደ። በዚያም ስደተኛ ሲኖዶስ ነኝ ብሎ እራሱን ካየነው አካል ጋር ሲያጫፍር ኖረ። ቢሆንም ስደተኛው ሲኖዶስ የለየለት መናፍቅ መሆኑን ተገንዝቦ በውግዘት እንዲለይ አደረገው።ትናንት የካዳትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ደግሞ ሊወጋት ለኑረዲን ኤልያስ ባጎረሰው እንጣጥ ዶላር ተመልሶ በጠቅላይ ቤተክህነት የውጭ ጉዳይ ጽ/ ቤት ተመድቧል። የዚህ ሁሉ ታሪካዊ ስህተት ምክንያቱ ኑረዲን ነህና ነገ ምትከፍለውን እዳ ያከብድብሃል። ስህተትህን አሁንም ገፋህበት። ቅዱስ ፓትርያርኩ የዋህ ቅን እና መንፈሳዊ አባት ናቸው። አንተ ነህ ቅዱስነታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት እና ከህዝብ ጋር እያጋጨህ ለመጠላት ያበቃሃቸው። ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንዲሉ አሁን ደግሞ ካድሬውን የማመን መናፍቁ አእመረን በታላቁ ሐገረ ስብከት ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጅ አድርገህ በማሾም ፓትርያርኩን ለተለመደው ስህተት አበቃሃቸው።ኑረዲን መቼም ቢሆን ልብ አትገዛም። ቃለጽድቅም ተልእኮህ ነውና ኑፋቄህን አትተውም። ስለዚህ ምእመናን ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንፀልይ የመናፍቃንን ድብቅ ሴራ እናጋልጥ። እኔም ስለ አአባ ቃለ ጽድቅ ያለኝን መረጃ በቅርቡ እለቃለሁ። በመሆኑም ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።

  • Anonymous April 18, 2016 at 1:36 pm Reply

   የቀደመ ማንነታቸውን ከፎቶ ጋር አስደግፈህ ሁሎችንም ፖስት ብታደርግ ብዙ ታተርፋለህ ግፋበት፡፡

 10. hiruyye March 23, 2015 at 8:23 am Reply

  ቅዱስ ፓትርያርኩ መንፈሳዊነት ቢኖራቸውም በዙሪያቸው ባሉ ጋሬጣዎች መሥራት የሚፈልጉትን በተግባር ማሳየት ተስኗቸዋል። ኑረዲን ኤልያስ ከትናንት እስከ ዛሬ በቤተክርስቲያን የሚፈጽመው ችግር እስካልተፈታ ድረስ የሚሰራው ስራ ትርጉም አልባ ይሆናል።አሁን ደግሞ በቤተክህነቱ የየደረሰውን ስራ ልጠቁማችሁ።አባ ቃለ ጽድቅየተባለውን መነኩሴ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እያለን በደንብ አድርጌ አውቀዋለሁ። በመናፍቅነቱ ወደር የማይገኝለት ሰው ነው። ከዚያ ከወጣ በኋላ አሰላ ኘድኀኔዓለም ተመድቦ ነበር። ነገር ግን ኑፋቄያዊ ትምህርቱን ለማስተላለፍ ቢሞክርም ምእመናን ያን ማድረግ ባለመቻሉ ብዙም አልቀጠለበትም። ከአሰላ በኋላ ወደ ምድረ አሜሪካ ሄደ። በዚያም ስደተኛ ሲኖዶስ ነኝ ብሎ እራሱን ካየነው አካል ጋር ሲያጫፍር ኖረ። ቢሆንም ስደተኛው ሲኖዶስ የለየለት መናፍቅ መሆኑን ተገንዝቦ በውግዘት እንዲለይ አደረገው።ትናንት የካዳትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ደግሞ ሊወጋት ለኑረዲን ኤልያስ ባጎረሰው እንጣጥ ዶላር ተመልሶ በጠቅላይ ቤተክህነት የውጭ ጉዳይ ጽ/ ቤት ተመድቧል። የዚህ ሁሉ ታሪካዊ ስህተት ምክንያቱ ኑረዲን ነህና ነገ ምትከፍለውን እዳ ያከብድብሃል። ስህተትህን አሁንም ገፋህበት። ቅዱስ ፓትርያርኩ የዋህ ቅን እና መንፈሳዊ አባት ናቸው። አንተ ነህ ቅዱስነታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት እና ከህዝብ ጋር እያጋጨህ ለመጠላት ያበቃሃቸው። ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንዲሉ አሁን ደግሞ ካድሬውን የማመን መናፍቁ አእመረን በታላቁ ሐገረ ስብከት ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጅ አድርገህ በማሾም ፓትርያርኩን ለተለመደው ስህተት አበቃሃቸው።ኑረዲን መቼም ቢሆን ልብ አትገዛም። ቃለጽድቅም ተልእኮህ ነውና ኑፋቄህን አትተውም። ስለዚህ ምእመናን ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንፀልይ የመናፍቃንን ድብቅ ሴራ እናጋልጥ። እኔም ስለ አአባ ቃለ ጽድቅ ያለኝን መረጃ በቅርቡ እለቃለሁ። በመሆኑም ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።

  • Anonymous March 23, 2015 at 2:36 pm Reply

   ትችት አይከፋም፡፡መዐርጉን ማጣጣል ግን ተገቢ አይደለም፡፡ “ንቡረ – ዕድ”ን “ኑረዲን” ማለት ሰውየውን ሳይሆን መዐርጉን ማሳነስ ነው፡፡ሰውየውና መዐርጉ ይለያያሉ፡፡መንግሥቱ ኃይለማርያምን ለመተቸት ኮሎኔል የሚለውን ማዕረግ ማሽሟጠጥ አስፈላጊ አይደለም፡፡ጳጳሱን ለመውቀስ ጵጵስናን አናጥላላም፡፡አናፌዝበትም፡፡ይህም እንደዛው፡፡ንቡረ – ዕድ ትልቅ መዐርግ ነው፡፡አክሱም ጽዮንና አዲስዓለም ማርያም ብቻ የሚሰጥ፡፡እና እባካችሁ እንደግ፡፡ትችታችንን ክርስቲያናዊ እናድርገው፡፡መዐርገ ክሕነትንና የተቀብዖ/የሹመት መዐርጋትን ሳናንኳስስ ልንወቅስ የምንፈልገውን ሰው መውቀስ ይቻላል፡፡አንውረድ፡፡

 11. Anonymous March 23, 2015 at 8:28 am Reply

  OUR FATHERS PLEASE BE TRUE RELEGUUOUS THE FOLLOWERS ARE BECOMING BETTER THAN YOU.

 12. Anonymous March 24, 2015 at 4:35 am Reply

  ኑረዲን ሊባል አይገባም ላልከው አስተያየት ሰጭ አንድ ነገር ላስታውስህ ተመልሼ መጣሁ። ንቡረዕድ ማለት ኑረዲን ማለት ነው ተብሎ ቢሆን እንዳልከው ስለ ተቀብኦ ስሙ አብረን ጥብቅና በቆምን ነበር። ጃንሆይ የሚባል አንድ ውሻ ነበር አሉ።የሰፈሩሰው ጃንሆይ ብሎ ሲጠራው እየሮጠ ከተፍ ይላል። ሂድ ሲሉትም ይመለሳል። ብቻ ውሻው ጃን ሆይ የሚለውን ስም ስለለመደው ለሰዎች ይላላካል።ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጃንሆይ ሞተ። አንድ ቀን የጃንሆይን መሞት ያልሰሙ ሽማግሌ ጃንሆይን ካየሁት ቆየሁ።የት ሄዶ ይሆን? ብለው ሲጠይቁ አንድ ሰው ቀረብ ብሎ ጃን ሆይ እኮ ከሞተ ከረመ ብሎ ለሽማግሌው ነገራቸው። ሽማግሌውም አይ ድሮም ስሙ ከብዶት ነበር አሉ ይባላል።ንቡረዕድ የሚለው የሹመት ስምም ታላቅ እና ክቡር መሆኑን እናውቃለን። አክሱም አና አዲስዓለምንም እናከብራለን።ግን የአክሱምን እና የአዲስ ዓለም ታሪክ እንዲነቀፍ ሁለንተናዊ ደኅንነታቸውም እንዳይጠበቅ የካህናት ኑሮ እንዳይሻሻል የቤተክርስቲያን መዋቅር እንዳይከበር በብልሹ አሠራሩ የሚያውከው ኤልያስ ኑረዲን ቢባል ያንስበታል እንጂ አይበዛበትም። እርሱ ማለት እኮ ሟች ሚስቱ ከፀነሰች እንደምትሞትሐኪም ነግሮት እያለ እንድትወልድ በማስገደድ የልጆቹን እናት ለሞት የዳረገ ጨካኝ ሰው ነው። እርሶ ማለት እኮ በልዩ መርሐ ግብር ከፕሮቴስታንት ድርጅት… በቃ ተወው የሚታወቀው ሁሉ አይፃፍም ። ዳኛ ሲኖረን ንጀሉን እናቀርባለን።ስለዚህ ወንድሜ አንተም ኑረዲን እና ንቡረዕድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጠይቀህ ተረዳ። እባካችሁ አንውረድ ላልከው ወርደህ የተፈጠፈጥከው ራስህ ነህ። ከመፃፍህ በፊት ደህና ደህና ጽሁፎችን አንብበህ ቅረብ።ለቤተክርስቲያን እንጂ የግለሰቦች ጠበቃ አትሁን።ቸር እንሰንብት።

  • Anonymous March 24, 2015 at 8:13 am Reply

   ጀግናየ ጊዜ ካለህ ከንቡረዕድ ጸዋትወ ዜማ፣ከመጋቤ ብሉይ አእመረ ደግሞ ቅኔ እና ትርጓሜ መጻሕፍትን ቀጽል፡፡እንደማይሕ አያዩሕም፡፡ስለማትታይ፡፡ቢያዩሕም አያዩሕም ጊዜ ስለሌላቸው፡፡አስተምሩኝ ካልክ ግን ግዴታቸው ነው፡፡ሊቃውንቱ ያልተቀረጸ መቅረጽ ግዴታቸው ነው፡፡ይሕ ሁሉ መንዛዛት የሚመጣው ካለማወቅ ነውና ያወቁትን ላላወቁት ማሳወቅ ግዴታቸው ነው፡፡አንተ የመማር ግዴታ እንዳለብህ ሁሉ እነሱም የማስተማር ግዴታ አለባቸው፡፡ግዴታ!!እርሳስህን ቀርጸሕ ና!!ትማራለህ!! “ሀለሐ…ወደረ፣ሎሃ…ጻፈ”፣ “የግሥ አርእስት ስምንት ናቸው እነሱም፡- ቀተለ፣ቀደሰ፣ደንገጸ፣ማኅረከ፣ባረከ፣ሴሰየ፣ክህለ፣ጦመረ” እያልክ አእመረ ጋር ቀጽለህ ስታበቃ በልክህ የኢሳይያስን ትርጓሜ ያስኬድልህና ኤልያስ ደግሞ በፈንታው “ቀዳሚ ዜማ….” ብለህ የቁም ዜማውን ከነዝማሜውና ይትበሃሉ እንድትዘልቅ ይረዳሃል!!ና ትማራለህ!!ነዐ ቅረብ ጽሙእ!!ሌለችም ካላችሁ ኑ…ዘፈተወ ይስተይ…ከእውቀት አፍላጋት!!በመነቋቆር ከመደንቆር፣ሳያመልጡ ጠጡ!!

   • ኅይለ ግብርኤል March 24, 2015 at 8:22 pm

    ሂድ ወደዚያ መናፍቅ ካድሬ የሰይጣን ተላላኪ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: