ሰበር ዜና – የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ከሓላፊነታቸው ተነሡ፤ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በፓትርያርኩ ብቸኛ ውሳኔ ተክተዋቸዋል

yemane zemnefes kidus

በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ተተኪ ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች ለቦታው በሚመጥን መልኩ በውድድር እንዲሾሙ እየጠየቁና የፓትርያርኩን ያልተመከረበት አካሔድ እየተቃወሙ ባሉበት ኹኔታ ‹‹ነባር የቤተ ክርስቲያኒቱ ሠራተኛ ካህንና በዘመኑ ዕውቀትና በአመራር ብቃት እጅግ ሞያ አላቸው›› በሚል በፓትርያርኩ ብቸኛ ውሳኔ የተሾሙት የአማሳኞች አጋር ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ

 • መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተመድበዋል
 • ብፁዕ ጠቅ/ሥራ አስኪያጁ ውሳኔውን በአስቸኳይ እንዲያስፈጽሙ በሹመት መመሪያ ታዝዘዋል
 • ሊቀ ማ/ን የማነ ሥራን በመበደል፣ አእመረ አሸብር በሃይማኖታቸው ርቱዕነት ነቀፌታ አለባቸው
 • የፓትርያርኩ አካሔድ በረዳት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበበት ነው
 • ቋሚ ሲኖዶስ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚነጋገርበት ይጠበቃል

*      *     *

 • ተተኪው ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ በወቅቱ በዋና ጸሐፊነት በሚሠሩበት በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር፣ ከመልካም አስተዳደርና ከገንዘብ ብክነት ጋራ ተያይዞ በቅርቡ ከተነሣው ተቃውሞና በነበሩባቸው አድባራት ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይልቅ ለግል ቢዝነሶቻቸው ቅድሚያ በመስጠት በሚገባ የሚታወቁ ናቸው፡፡
 • ፓትርያርኩ፣ በቁጥር ል/ጽ/301/10/2007 በቀን 10/07/07 ከልዩ ጽ/ቤታቸው ባወጡት ደብዳቤ፣ የሹመት መመሪያቸው ከዛሬ መጋቢት ፲ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲኾን አስታውቀዋል፤ በሀገረ ስብከቱ የሚደረገውን የክፍል ሓላፊዎች ምደባና ዝውውር ይኹንታና ፈቃድ በመስጠት ጭምር ይቆጣጠራሉ፡፡
 • ፓትርያርኩ ከረዳት ሊቀ ጳጳሳቸው ይልቅ ከልዩ ጸሐፊአቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋራ የመከሩበት ዓምባገነናዊ አካሔዳቸው፣ ከፀረ – ሕገ ቤተ ክርስቲያን እና ፀረ – የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔዎች አቋማቸው አንጻር በመጪው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚነሣባቸውን ብርቱ ጥያቄ ትኩረት የማስቀየስ አካል እንደኾነ እየተጠቆመ ነው፡፡
Advertisements

16 thoughts on “ሰበር ዜና – የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ከሓላፊነታቸው ተነሡ፤ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በፓትርያርኩ ብቸኛ ውሳኔ ተክተዋቸዋል

 1. Anonymous March 19, 2015 at 6:33 pm Reply

  “የፓርላማ ተመራጩ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ::“ ማለታችሁን ረስታችሁት ነው፡፡

 2. Anonymous March 19, 2015 at 7:51 pm Reply

  lemahberuns lebe Alban Belay mekonen zare gibate Mekir nw mak dilemma Belay lasagne meche new yemitomfew poletikegnoch nachihu

 3. zakios March 19, 2015 at 9:39 pm Reply

  የድሮዎቹ ጳጳሳት እንዲያው ፈሪሃ እግዚአብሔር ነበራቸው፡፡ የአሁኖቹ ደግሞ ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ ሆነው ቁጭ፡፡ የሚያስቡት በመንፈሰዊነት መሆኑ ቀርቶ በአለማዊነት ከሆነ ሰነበተ፡፡ ሊረዱት ያልቻሉት እንመራዋለን የሚሉት ምዕመን ከእነሱ በተሻለ ለእምነቱና ለቤተክርስቲያኗ ተቆርቋሪ መሆኑና ከካህናቱ ደግሞ በዕውቀትና ፈሪሃ እግዚአብሔር የአደረባቸው ባይኖሩ ኖሮ ጠፍተን ነበር፡፡
  ችግሩ እገሌ ተነስቶ እገሌ ተተካ ሣይሆን ቤተክርስቲያኗ መሠረታዊ ችግር ውስጥ ነው የአለችዉ፡ ይህ ደግሞ ሥር የሰደደ የቆየና ተወራራሽ በሆነ ችግር ተተብትባ ነው የአለችው፡፡

 4. ethiopia March 20, 2015 at 2:35 am Reply

  hulum neger yasaznal bicha egziabhier amlak lebietekrstianitu sewu ytallat

 5. Anonymous March 20, 2015 at 6:47 am Reply

  ለሁለንተናዊ ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ መቃናት ጥሩ አሠራርን የሚዘረጋ ዓይናማ መሪ ያስፈልጋል፡፡ ‹‹ዕውር ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ›› ማቴ 15፣13

  ቁመናው ዘለግ ያለውን፣ መልኩ ያማረውንና ናዝራዊ የሚመስለውን ሳይሆን ልቡ ንጽህ የሆነውን፣ ሀሳቡ የተቃናውን፣ ማግኘት የማይለውጠውን፣ ይቅርታ አድራጊውን፣ ለእውነት ተቆርቋሪውን፣ ተለሳልሶ የማይናደፈውን፣ እያገሣ የማያስደነብረውን፣ መሥዋዕት ሁኑልኝ ሳይሆን ልሁን የሚለውን ጥበብና ማስተዋልን የሚሻውን፣ በመከራ ተጠብሶ የበሰለውን፣ በፈተና ነጥሮ የወጣውን፣ የታናናሾቹን ታላቅነት የሚቀበለውን፣ ለቆዳው ሳይሆን ለቅንነቱ የሚጨነቀውን፣ ትዕሥትና ትሕትና የያዘውን መሪ በአሁኑ ሰዓት ቅድስት ቤተክርስቲያን ትሻለች፡፡

  በዚህ ወቅት በዝህች ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ በጎቼን ጠብቁ ተብለው በተሾሙ የመቅደሱ ኃላፊዎችና የመንጋው ጠባቂዎች በቤተክርስቲያን ላይ፣ በምዕመኑ ላይ፣ በሀገር በወገን ላይ እየተፈጸሙት ያለው ተግባርና ኃላፊነት ግን የአንድን መሪ ክህነታዊ ኃላፊነትን የሚገልጽ ሳይሆን ተግባርና ኃላፊነታቸውን የረሱ፣ ለሥጋዊ ኑሮአቸው ለዓለማዊ ስልጣናቸው ምቹነት የሚሮጥጡ፣ የተኩላዎች ሀሳብ ነው፡፡ ምክንያቱም፡-
  የመሪ ክህነታዊ ኃላፊነት ከራሱ ወይም ከሰው አሳብ ይልቅ የእግዚአብሔርን አሳብ ማገልገል ነው፡፡ ‹‹ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኃላ አንቃፋ›› እንዲል ሐዋ. 13፣36

  ***********************************

  ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ቀድሞ ወደ እዚህ ታላቅ የቅድስና ወንበር ሳይሾሙ የቤተክርስቲያንን ችግሮችና ውስጣዊ ተግዳሮቶች እየዘረዘሩ ብዙ መልካም መሳይ ቃላት ሲደረድሩ ነበር፡፡ ጥበበኛው ንጉሡ ሰለሞን ‹‹ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማርን ይንጠባበባልና፣ አፍዋም ከቅቤ የለሰለሰ ነውና›› ምሳሌ 5፣3 ያለው በወቅቱ በተግባር የሚታየውን የሚገልጽ ነው፡፡
  ዙፋን ገልብጠው ወደ ዙፋን የወጡ መሪዎች መነሻ ዓላማቸው የሀገር ንብረት ባክኗል፤ የሕዝብ መብት ተነፍጓል የሚል ነበር፡፡ ዙፋኑ ላይ ሲወጡ ግን እነርሱ እንደሚብሱ በታሪክ ሁሉ ታይቷል፡፡ ‹‹ከበሮ በሰው እጅ ያምር፣ ሲይዙት ያደናግር›› እንደሚባለው በሰው እጅ ያለን ኃላፊነት እኛ ብንይዘው የተሻለ እንደምንሠራበት ብናስብም ለእግዚአብሔር አሳብ ካልተገዘን ሥልጣኑ ራሱ ይገዛናል፡፡
  **********************************

  ይህች ቤተክርስቲያን አንድ ጊዜ ቅድስት ሆና የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶ አካል ሆና ታንጻለች፡፡ ቤተክርስቲያን ባለቤቷና መሥራቿ እግዚአብሔር ስለሆነ በየዘመኑ የሚነሳባትን ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሁሉ በድል ስትወጣ ቆይታለች፡፡ ለቀጣይም እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ጸንታ ትኖራለች፡፡ እንደ ዘመኑ የበጎቹ ጠባቂ እረኞች ተግባር ቢሆን ኖሮ በጎቹም የተኩላዎች ሲሳይ ሆነው በረቱ ባዶ በቀረ ነበር፡፡
  ይህቸ ቤተክርስቲያን ዓምዷ (ምሰሶዋ) የሆነው እውነትና ሀይማኖት ካልተጠበቀ ወይም ችላ ከተባለና እግዚአብሔር ከገለጠው እውነት ጋር በልማት ስም የቤተክርስቲያኒቷን ሀብትና ንብረት፣ ተልዕኮና አገልግሎት … እንሸቃቅጠው ከተባለ፤ ዘረኝነት፣ ስልጣን ወዳድነት፣ ፓለቲከኝነት ከተጸናወተን ቤተክርስቲያን ባሕርይዋ ስለማይፈቅድላት እንዲህ ያለውን ነገር መቀበል አትችልም፡፡ መሠረቷ እና ዓምዷ እውነት ብቻ ነውና፡፡
  ***********************************
  በዘመናችን የነበሩትን መንፈሳውያን እንዲሁም ዓለማውያን መሪዎችን አይተናቸዋል፡፡ በጊዜያቸው ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን የማገልገል ኃላፊነት በአግባቡ ሳይወጡ በማን አለብኝነት በምዕመኑ ላይ፣ በቤተክርስቲያን ላይ፣ በህዝብና በሀገር ላይ ብዙ ሮሮ፣ እንባ፣ ሀዘን፣ ለቅሶ፣ ግፍና መከራ አድርሰው አልፈዋል፡፡ ዛሬ ግን ሁሉም የሉም፡፡ ወደ ዕውነቱ ቦታ ሄደዋል፡፡ ስለዚህ እኛም የዘመኑ የወንበሩ ባለቤቶችም በጊዜያችን እንወቅበት፡፡ ‹‹ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት እንዴት መኖር እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድ፣ መሰረቱም የሕያ ው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ነው›› እንዲል 1ኛ ጢሞ 3፣15

 6. mr alemu March 20, 2015 at 7:19 am Reply

  this church should act internationally to reach those who r in need of gospel.we shouldnt be caught in this silly adminstrative issue.how we not learn from Egypt?

 7. Anonymous March 20, 2015 at 7:53 am Reply

  ይህ ሰው የትግርኛ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ዜና አንባቢ የነበረ ሰው ነበር አሁን ደግሞ ሊቀ ማእምራን ተብሎ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ተብሎ ተሾመ ይገርማል!!! ባለፈው ፓትርያርኩ በጠሩት ስብሰባ ላይም ማህበረ ቅዱሳን በአሜሪካ ሶስተኛ ሲኖዶስ ሊያቋቁም ነው በማለት በሀሰት ሲከስ የነበር ሰው ነው፡፡ አይ እናት ኢትዮጵያ መጨረሻሽ እንዴት ይሆን? ጥፋትሽን አያሳየን እግዚአብሔር ያስብሽ ፡፡ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ አካልህ የሆነችውን በደምህ የቀደስካትን እናታችን ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንችንን አትተዋት ያለእርስዋ ተስፋ የለንምና፡፡ ይህም እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደበደላችን አይሁን፡፡

 8. Anonymous March 20, 2015 at 7:57 am Reply

  ሐራ, በላይ ሲመዘብር ዝም ብለሽ ቃል ሳትተነፍሽ መሰንበትሽ ፌይር ነው ትያለሽ?

 9. እኛ የአጥቢያዎቹ March 20, 2015 at 8:15 am Reply

  ሊቀ – አእላፍ በተሾሙበት የመጀመሪያ ወራት መልካም አስተዳደር ለማስፈን፣የካሕናትንና ምዕመናንን እሮሮ ለመፍታት የሄዱበት መንገድ አስመስጋኝ ነበር፡፡ይህ አቋማቸው ሀ/ስብከቱን ያለ ጎላ ችግር ሊቀጳጳስ እንኳ ሳይኖር እንዲመሩ ያስቻለ ነበር፡፡የሕግ ባለሙያ መሆናቸው፣የልብ ቅንነት ያላቸው መሆናቸው፣የማመልከቻ አቀባበል ሥርዓቱን ለማስተካከል መጣራቸው የተሻለ የአስተዳደር ጭላንጭል መስጠቱ አይካድም፡፡ሆኖም ቆይቶ የቤተክሕነት ነባራዊ አዙሪት በሆነው የመማለጃ መቀበል እና የዘረኝነት ወጥመድ ስለመግባታቸው በሰፊው ታሙ፡፡በተለይ የተወሰኑ አካባቢ ካሕናት ተለይተው አድማ በሚመስል መልኩ በማን አለብኝ ባይ አለቆች ከስራ ሲፈናቀሉ፣የሥራ ደረጃቸው ዝቅ ሲደረግ፣ያልተገባ መቀጮና ማስጠንቀቂያ ሲደርሳቸው አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ተሳናቸው፡፡የምዕመኑ እሮሮ በረከተ፡፡ይሕ እሳቸው ያልፈቱት የቤት ስራ ለአቡነ ቀሌምንጦስም ተረፈ፡፡ዛሬም አልተቀረፈም፡፡
  እንግዲህ የአዲሶቹ ተሹዋሚዎቸ ፕሮፋይል ሲታይ፡- (1) ምንአልባት ከተወለድንበት አካባቢ የተነሳ ተለይተን እየተሳደድን ነው የሚሉ ወገኖችን ለማርገብ፣(2) በሀገረ – ስብከቱ መምሪያዎች ውስጥ ሚዛን አልባ የአንድ አካባቢ ተጽእኖ እየጎላ በመምጣቱ አዲስ አበባ ልዩ ሀ/ስብከታቸው የሆነው ፓትርያርኩ የሚሰጡት መምሪያ በብልሃት ወደጎን እየተደረገ ነቀፌታው ብቻ በየሚዲያው እየተረፋቸው ነው የሚለውን ዐደባባይ ያልወጣ ትችት ለማስወገድ፣(3) በነዋሪ ነባሪው የጥፋት መንገድ ካልገቡ በቀር አዳዲሶቹ ተሹዋሚዎች ያላቸው ዘመናዊና መንፈሳዊ የትምህርት ዝግጅትና ልምድ ለቦታው ብቁ የሚያደርጋቸው እንደሆነ አይቶ ለጊዜው የፓትርያርኩን ውሳኔ መቀበል ይቻላል፡፡
  አዳዲሶቹ ተሹዋሚዎች በአዲስ መንፈስና በፍትሐዊነት ለመስራት ቆርጠው ከተነሱ በፍቅረ – ነዋይ አንዳች ሐሜት ከማይነሳባቸው ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ጋር በመሆን ለሀ/ስብከቱ የተሻለ መስራት ይችላሉ፡፡ሆኖም ችግሩ ውስብስብ ነውና በአንድ ጊዜና በዘላቂነት ይፈቱታል ለማለት ያስቸግራል፡፡
  ለማንኛውም፡- ሊቀ – ማዕምራንና እና መጋቤ – ብሉይን ሹመት ያዳብር ብለናል!!መልካሙን ለማድረግ የቤተክርስቲያን አምላክ ጥበቡን ይግለጽላችሁ!!አባቶች “ኢትንዐዶ ለሰብእ ዘእንበለ – ትርአይ ተፍጻሜቱ…ሰውን ፍጻሜውን ሳታይ አታመስግነው” ይላሉና ቀድመን ውዳሴም ሆነ እርግማን አንሰነዝርባችሁም!!በበኩላችን ስላለፈው ሳይሆን ስላለውና ስለሚመጣው ማሰብን እንመርጣለንና የሚነሳባችሁን ሐሜት እየደጋገሙ የማሸማቀቅን አካሄድ ተከትለን አናነውራችሁም!!ብቻ ከእናንተ ብዙ እንደምንጠብቅ እንነግራችኋለን!!ከላይ የአባቶችን መመሪያ፣ከታች የምዕመኑና የካሕናትን የልብ ትርታ እያዳመጣችሁ ቤተክርስቲያንን ወደፍጹም አንድነት እንድትመልሱዋትና ፓ/ኩ በየመድረኩ ያለመታከት የሚሰብኩትን የተቃና አስተዳደር መፍጠር ገቢራዊ ለማድረግ አምላከ – ቅዱሳን እንዲራዳችሁ እንለምናለን!!

 10. Worku Adefris Wmariam March 20, 2015 at 9:35 am Reply

  ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ——–ጆሯ ችን ክፉ ነገር በመሰማት ተንበሸበሸ!!!!!

 11. ከኮሚቴው አባላት አንዱ March 20, 2015 at 12:17 pm Reply

  በስተመጨረሻም አዲስ አበባ ሀገረስብከት ከማኅበረቅዱሳን ቅኝ ግዛት ነጻ ወጣ፡፡ማኅበሩ ልኩን ዐወቀ፡፡የሐራ ዐይን ያወጣና በማኅበረቅዱሳን ሥም የተሸፈነ የሸዋ ወገንተኛነትና ጸረ ትግራይ-ጎጃም አቋም ተገለጠ፡፡የምናውቅስ ድሮም እናውቀዋለን፡፡የጎጃም ሰው ቀና ሲል በኑፋቄ ትከሳላችሁ፣የትግራይ ሰው ሲመጣ በፖለቲካ እያሳበባችህ ታሳድዳላችሁ፡፡ሀገረስብከቱ ዐይን ባወጣ መንገድ አንድ ብሔር ሲፈነጭበት ግን እንዳላየ ታልፋላችሁ፡፡ነቅተናል፡፡
  አሁን ሁሉም በተሰጠው ድርሻ ያገለግላል፡፡አቋማችንን በደንብ ተፈታትሸናል፡፡ተዋውቀናል፡፡ዐላማችን ድርሻ ይታወቅ እንጅ እከሌ ይጥፋ የሚል አልነበረም፡፡አይደለም፡፡አይሆንም፡፡የማናዘዝና የመናዘዝ ሥልጣን ባይኖራችሁም በምግባር እንደክም እንደሆነ እንጅ በፀናች ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነታችን አንዳች ሳንካ እንደሌለብን ተናግረናል፡፡ አልሰማችሁንም፡፡በየሚዲያው ወሬ ማራባቱ ይጠቅም መስሏችሁ ስማችንን ከነፎቶአችን በክፋት መንገድ አራባችሁ፡፡ለንግግራችን ጆሮ ነሳችሁን፡፡ከማኅበረቅዱሳን ገጸ-ድር እስከ ኢሳት በከፈታችሁት የወሬ ጦርነት ሳንፈልግ ጉዳዩን የአሸናፊና ተሸናፊ አደረጋችሁት፡፡እናም በደንብ ገሥጸን ስናበቃ ጥቂት ቀንደኞቻችሁን ለሕግ ልናቀርብ ስንል በጳጳሳት ሰናፊል ተደብቃችሁ አመለጣችሁ፡፡በነ አቡነ ቀውስ-ጦስ እና አቡነ አብርሃም አስተዋይ አካሄድ ከእልህ ጎዳናችን ተመለስን፡፡አሁንም ካላረፋችሁ እንመለስባችኋለን፡፡በድርሻችሁ ልክ አገልግሉ፡፡ወሬ ቀንሱ፡፡የጥቅምትና የግንቦት ቅዱስ ሲኖዶስ አጀንዳ ቀራጺ ለመሆን አትሞክሩ፡፡ያ ካልሆነ ግን ውርድ ከራሳችን፡፡በመዋቅር ሥር ከተሰጣችሁ ድርሻ እያለፋችሁ መመጻደቅና በየእለት ዕለቱ አሰራራችን ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጭ እንፈተፍታለን ካላችሁ ድጋሚ በእናንተ ጉዳይ አጀንዳ ይዘን አባቶቻችንን ስራ አናስፈታም፡፡ለእናንተ ሚኒስቴርና ኮሚሽነር የሚጠራ የለም፡፡ድሮም አልተጠራም፡፡ያልተገባ ግብራችሁን ዘርዝረን እጃችን ላይ ባለው ማኅተም መሸኚያ ደብዳቤ አድርገን ለአንድ ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ መጻፍ ነው፡፡በምክር ካልተመለሳችሁ በመከራ እንሞክራችኋለን፡፡የበዙ የዋሐን አባላቱንና ማኅበሩን ለማዳን ሲባል ጥቂት ባለ ስስ ነጠላ ረዋጺ/ተንቀዥቃዥ አመራሮችን በዚህ ጎዳና አደብ ማስገዛት ግድ ይሆናል፡፡አደብ ግዙ፡፡እንደመማጥ፡፡ስንመለከታችሁ የማኅበረቅዱሳንን አጀንዳ ተሸክሞ “አቤት ወዴት” የሚል ሰው ካልተሾመ በቀር እንቅልፍ የሚወስዳችሁ አይመስልም፡፡እሱ ለጊዜው የሚታሰብ አይደለም፡፡አሁን ባለው አያያዛችሁ ለዛ ደረጃ ገና አልደረሳችሁም፡፡ዓለማዊ የኤቢሲዲ ቀለምን መሸምደድ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊውን የገብር ኄር ተግባርና ቅንነትም ውረሱ፡፡በሚዲያ በተንጫጫ አይደለም፡፡በድምጽ ብዛት እውነት አትቆምም፡፡ተያይተናል፡፡ተፈታትሸናል፡፡እረፉ፡፡ካላረፋችሁ ለቤተክርስቲያን ሰላም ሲባል ጥቂቶቻችሁን በማረፊያ እንድታርፉ ለማድረግ እንንቀሳቀሳለን፡፡ዳግመኛ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን ትሆኑ እንደነበረው መረን እንድትለቁ አንፈቅድም፡፡ያ ዘመን አይደገምም፡፡እደግመዋለሁ፡፡ያ ዘመን አይደገምም፡፡ትመከራላችሁ ብለን 23 አመት ሥም ስታቦኩና ስትጋግሩ ታግሰናል፡፡ከአሁን በኋላ በፊት ለፊት ቅዱስ አባታችን እያላችሁ በጀርባ በየሚዲያው መረን በለቀቀ መልኩ ሥም እያጠፉ መኖር የሚቻል ከመሰላችሁ ግን………ሞክሩት!!ያን ጊዜ የቤተክሕነቱ የሕግ መምሪያ የፍትሑን ጎማ እንዲያሽከረክር እናዝዛለን፡፡አድራሻ የሌላቸውን ብሎጎች አድራሻ ያላቸው ጋዜጦችንና አማተር ጸሐፍትን ለፍርድ በማቅረብ እናስተምራቸዋለን፡፡ከ23 አመት መታገስ የአንድ ቀን የፍርድ ውሎ ሳይሻል ስለማይቀር፡፡

  • Anonymous March 21, 2015 at 5:54 am Reply

   are you sure you are one of the member?

 12. Anonymous March 20, 2015 at 2:48 pm Reply

  እረ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ተነስተዋል ብላችሁ የጻፋችሁ አካላት ጉዳዩን ብታጣሩ መልካም ነው እሳቸው መደበኛ ሥራቸውን እየሰሩ ነው የዋሉት እናም ጉዳዩ ይረጋገጥ

 13. yemane March 20, 2015 at 2:57 pm Reply

  ኧረ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ከሐላፊነታቸው ተነስተዋል የተባለው ይረጋገጥ ምክንያቱም እሳቸው ዛሬ እንኳን መደበኛ ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነው የዋሉት ስለዚህ እንደገና ይረጋገጥ።

 14. Anonymous March 22, 2015 at 6:37 am Reply

  ተሀድሶ መናፍቅ + ጸረ-ተዋህዶ ‹‹ካድሬ›› + ሙዳይ ምጽዋት ገልባጭ ሙሰኛ = የቤተክርስቲያን የጥፋት ህብረት

  የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች
  ውጤት ነው!!
  “ክፉዎች ሠራተኞችን እወቁባቸው” !!
  ስለ ጽዮን ዝም አልልም ስለ ኢየሩሳሌም ጽጥ አልልም ኢሳ. 62፣1

 15. Anonymous March 30, 2015 at 3:22 pm Reply

  ይህ ሰው እኮ ከዚህ ቀደም በኢቲቪ ጋዜጠኛ የነበረ ሰው ውሸትን ሲያሰራጭ የነበረ ሰው መሆኑ ይታወቅ፡፡ አሁንም ቢሆን በየት በኩል አድርጎ እዚህ እንደገባ ፈጣሪ ይወቀው፡፡ እግዚአብሄር ሀገራችንን ይጠብቃት፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: