የባህልና ቱሪዝም ቢሮው መግለጫውን እንዲያርም ታዘዘ፤ ኢሬቻ በደብረ ዝቋላ አይከበርም

 • ፓትርያርኩ እና የመስተዳድሩ ፕሬዝዳንት በጉዳዩ ላይ መወያየታቸው ተጠቁሟል
 • ‹‹የኢሬቻ ቱሉ በዓል በክልል ደረጃ የት አካባቢ መከበር እንዳለበት ገና አልተወሰነም፡፡››
                                   (የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና የኦሮሞ አባ ገዳዎች ምክር ቤት)

zequullaየኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ ‹‹ኹለተኛው ዙር የኢሬቻ በዓል በዝቋላ ተራራና በአካባቢው ይከበራል›› በሚል በሬዲዮና በቴሌቪዥን ለአስተላለፈው መግለጫ እርምት እንዲያደርግ በክልላዊ መንግሥቱ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከድር መመሪያ እንደተሰጠው ተገለጸ፡፡

የርእሰ መስተዳድሩ መመሪያ የተሰጠው÷ የባህልና ቱሪዝም ቢሮው ከክልሉ የገዳ ሥርዐት ጽ/ቤት ጋራ በመኾን፣ በመጪው መጋቢት ፴ የገዳ ሥርዐት መታሰቢያ ሐውልት ተከላ እና የኢሬቻ በዓል በደብረ ዝቋላ የጠበል ሐይቅ ዙሪያ እንደሚከናወን መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በመንግሥታዊው ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን በኦሮምኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ያስተላለፈው መግለጫ ከቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር፣ አገልጋዮችና ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ነው፡፡

ziquwala_17የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በኢትዮጵያ ካሉት ጥንታውያንና ታሪካውያን ገዳማት አንዱ እንደኾነ የጠቀሰው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ መግለጫውን በመቃወም ጥር ፳፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር በጻፈው ደብዳቤ፣ በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተሰጠው መግለጫ በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የእምነት ነጻነት የሚጥስ በመኾኑ በመንግሥት የብዙኃን መገናኛ መተላለፉ ተገቢ እንዳልነበር ተችቷል፡፡

በመግለጫው ሳቢያ በመናንያን መነኰሳቱና በአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የተቀሰቀሰው ቁጣ ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ መንግሥት ለሚመለከተው ክፍል ተገቢውን መመሪያ እንዲሰጥ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የጠየቀበትን ሰፊ ዘገባ መነሻ ያደረገው የቅዱስ ሲኖዶሱ ጽ/ቤት፣ ችግር ከመፈጠሩ በፊት መግለጫው በተላለፈበት የመንግሥት ብዙኃን መገናኛ ማረሚያ እንዲሰጥበትም የመስተዳድሩን ፕሬዝዳንት አሳስቦ ነበር፡፡

የክልሉ ፕሬዝዳንት ስለ ጉዳዩ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ መነጋገራቸውን የጠቆሙት የዜናው ምንጮች፣ በንግግሩ ወቅት የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በዝቋላ ተራራና በአካባቢው የኢሬቻ በዓል እንደሚከበርና የገዳ ሥርዐት መታሰቢያ የማቆም ሥርዓት እንደሚከናወን በኦሮምኛና በአማርኛ ቋንቋዎች ለአስተላለፈው መግለጫ እርማት እንዲያደርግ በርእሰ መስተዳድሩ መመሪያ እንደተሰጠው ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እንደተገለጸላቸው አስታውቀዋል፡፡

የአባ ገዳ ተወካዮችን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የአስተዳደር፣ የባህልና ቱሪዝም፣ የፖሊስና የጸጥታ ዘርፍ ሓላፊዎች ከገዳሙ አስተዳደር ጋራ የካቲት 25 ቀን በገዳሙ ሞፈር ቤት እና የካቲት 30 ቀን ደግሞ በአዱላላ ወረዳ ጽ/ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ የመንግሥት ሥልጣንን ተገን በማድረግ እምነታቸውን ለመጥቀም የሚሠሩ ግለሰብ አመራሮች በተለይም ከመጋቢት ወር ፳፻፪ ዓ.ም. አንሥቶ ቦታቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስፈራራትና ዛቻ እያደረሱባቸው እንዳሉ በውይይቱ ወቅት የተናገሩት የገዳሙ ተወካዮች፣ አስተዳደሩ ይዞታቸውን የሚያስከብር የማያዳግም መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

በቢሮው መግለጫ የተፈለገው ገዳማውያኑን ከኅብረተሰቡ ጋራ ለማጋጨት ነው ያሉት የማኅበረ መነኰሳቱ ተወካዮች፣ ከመጋቢት ፭ ክብረ በዓል በፊት መግለጫው በስሕተት የተላለፈ መኾኑ ተጠቅሶ ማስተባበያ እንዲሰጥበት በአጽንዖት ጠይቀው ነበር፡፡ የሥርዐተ ገዳ ተወካዮች በበኩላቸው፣ ‹‹ዝናም እምቢ እንዳይለን በቤተሰብ ደረጃ ገዳሙን አስፈቅደን ከምንፈጽመው ሥርዓት›› ውጭ ደብረ ዝቋላ ይኹን የጠበል ሐይቁ የዋቄፈታ እምነት ተከታዮች በብዛት የሚሳተፉበት የኢሬቻ በዓል አከባበር ታሪክ እንደሌለው አስረድተዋል – ‹‹ለኛ ዐዲስ ነገር ነው፤ ከየት አምጥተው እንዳስተላለፉት አናውቅም፤ ያስተላለፉት መጠየቅ አለባቸው፡፡››

በውይይቱ ማጠቃለያ፣ ከመግለጫው ጋራ ግንኙነት ስለአላቸው አካላት አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ማስተባበያ እንደሚሰጥበትና ለአፈጻጸሙም ሓላፊነቱን እንደሚወስዱ በባለሥልጣናቱ መገለጹ ተመልክቶ ነበር፡፡ አንዱ በሌላው እምነት ጣልቃ ገብቶ ጫና የሚፈጥርበት አሠራር እንደማይኖር የተናገሩት ሓላፊዎቹ፣ በክብረ በዓሉ ከተለመደው የተለየ ክንዋኔ እንደማይፈጸምና የተጠናከረ ጥበቃ እንዲደረግ መመሪያ እንደተሰጠም ማስታወቃቸው ተዘግቧል፡፡

ደብረ ዝቋላ እና የጠበል ሐይቁ ከዛሬ 877 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይዞታነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ብርሃነ ረድኤቱን የሚገልጽበት ይኸው ጥንታዊ ገዳማችን፣ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለሀገር ሰላምና ደኅንነት የጸለዩበት፣ በየጊዜው ሕሙማን ጠበሉን በመጠጣትና በመጠመቅ የሚፈወሱበት፣ የጻድቁ ታቦት ከመንበረ ክብሩ ወጥቶና ተፈጥሯዊ የጠበል ሐይቁን ዑደት በማድረግ የሚከብርበት ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅዱስ መካናችን ነው፡፡

ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተወለዱት በግብጽ ንሂሳ በምትባል ቦታ ከአባታቸው ስምዖን ከእናታቸው አቅሌስያ ነው። በአጠቃላይ የኖሩበት ዕድሜ 562 ዘመን ሲኾን 300 ዓመቱን በግብጽ፣ 262 ዓመቱን በኢትዮጵያ (100 ዓመት በዝቋላ) በተጋድሎ ያሳለፉ ታላቅ አባት ናቸው።

ጻድቁ ዕድሜአቸው 300 ዓመት ሲኾን ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ እንደመጡ ወደ ሮሃ አምርተው ከቅዱስ ላልይበላ ጋራ ተገናኝተው ሥራውን ባርከውለታል፡፡ በመላዋ ኢትዮጵያ ተዘዋውረው ከማስተማራቸው ባሻገር የዝቋላንና የምድረ ከብድን ገዳማት መሥርተዋል፡፡ በአማራው አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ በትግራዩ ኣቡየ፣ በኦሮሞው እና በጉራጌው አቦ እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ ጻድቁ በዐረፉበት ወቅት በኢትዮጵያ የነበረው ንጉሥ ከ1414 – 1418 ዓ.ም. የነገሠው ሕዝብ ናኝ/ዐፄ እንድርያስ/ ነው፡፡ ኢትዮጵያም የዐሥራት አገራቸው ኾና በቃል ኪዳን ተሰጣቸዋለች። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዕረፍት በየዓመቱ መጋቢት ፭ ቀን በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል።

ገገገከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲኾን ከሰማይ ታላቅ የነጎድጓድ ድምፅ ተሰማ፤ ጌታችን መላእክትን አስከትሎ ወደ አባታችን ወረደ፤ ከሰማይ ወደ ምድር ሕብሩ አምሳያው ልዩ ልዩ የኾነ እንደ ፀሐይ እና እንደ ጨረቃ የሚያበራ እንደ ወንጪፍ ድንጋይ የሚወረወር ነበር፤ ከዚያ የነበሩ ኹሉ ፈሩ፤ ወደ ኋላም ሸሹ፤ ምድር ራደች፤ ተራሮች ኮረብቶች ተናወጡ፤ ብርቱ ጩኸት ንውጽውጽታ ኾነ።

‹‹ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰላም ላንተ ይኹን፤ እነኾ የማይታበል ቃል ኪዳን እገባልኃለኹ፤ ስምኽን የጠራውን መታሰቢያኽን ያደረገውን፤ ዕጣን ቋጥሮ ግብር ሰፍሮ መባ ይዞ ቤትኽ የመጣውን እምርልኃለኹ፤ አንተ ከገባኽበት ገነት መንግሥተ ሰማያት አገባዋለኹ፤›› አለው፡፡ አባታችንም ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ፣ የኢትዮጰያን ሕዝብ ማርልኝ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹እነኾ ምሬልኃለኹ፤ ዐሥራት በኩራት አድርጌም ሰጥቼሃለኹ፤ ከመጋቢት አምስት ቀን ጀምሮ ዝክርኽን ያድርጉ፤ በአማላጅነትኽም ይማጸኑ፤›› አለው። ከዚህ በኋላ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት የአባታችንን ነፍስ ሊቀበሉ ወረዱ፣ በታላቅ ምስጋናም ወደ ሰማይ አሳረጉት፤ ሥጋውንም ይዘውት ሔዱ፤ የት እንደተቀበረም እስከ አኹን አይታወቅም፡፡

እንደ ሐዋርያት የተኣምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጥቶት አጋንንትን ያወጣ ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ በትእዛዘ እግዚአብሔር በበርሓ ሲኖር ስድስት አንበሶችና ስድስት ነምሮች አብረውት ይኖሩ ነበር፡፡ የጻድቁ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ ይበዛል፤ ኢትዮጰያን አብዝቶ ይወዳታል፤ ምድራዊ ምግብ አልተመገበም፤ የእናቱን ጡት እንኳን አልጠባም፤ ልብስ፣ መጠለያ አልፈለገም፤ የክረምት ቁር የበጋ ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ፤ በዛሬዋ ቀን ሩጫውን ጨረሰ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን፤ እኛንም ከጻድቁ አባታችን በረከት ያሳትፈን። አሜን፡፡

************

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከኦሮሞ አባ ገዳዎች ምክር ቤት ጋራ በመኾን ትላንት መጋቢት ፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የሰጠውና ማምሻውን በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተላለፈው ዘገባ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

(ኢቢሲ፤ ሪፖርተር በላይ ሓድጎ፤ መጋቢት ፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

EBC logoየኦሮሞ ሕዝብ በዓመት ኹለት ጊዜ ከሚያከብራቸው በዓላት አንዱ የኾነው ኢሬቻ ቱሉ በዓል፣ በክልል ደረጃ የት አካባቢ መከበር እንዳለበት ገና አለመወሰኑ ተገለጸ፡፡

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ምክር ቤት ሰብሳቢና የቱለማ አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ እና የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ዘውዱ ማሞ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ በጋ ላይ ዝናም ሲጠፋ ሕዝቡ ወደ ተራራ በመውጣት ፈጣሪውን የሚለማመንበት የኢሬቻ ቱሉ በክልል ደረጃ የት መከበር እንዳለበት የሚወሰነው፣ የታሪክ ባለሞያዎች በሚሰጡት መረጃና በሕዝብ ፍላጎት መሠረት አባ ገዳዎችና የአገር ሽማግሌዎች በሚሰጡት ውሳኔ ነው፡፡

ክረምት በበጋ ሲተካ እንኳን ለብርሃን አበቃን በማለት ሕዝቡ ፈጣሪውን የሚያመሰገንበትና በውኃ ዳር የሚከበረው ኢሬቻ መልካ ደግሞ በአባ ገዳዎችና በአገር ሽማግሌዎች ውሳኔ መሠረት ከደርግ ሥርዐት ውድቀት በኋላ በየዓመቱ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ እየተከበረ መኾኑ ይታወቃል፡፡

Advertisements

10 thoughts on “የባህልና ቱሪዝም ቢሮው መግለጫውን እንዲያርም ታዘዘ፤ ኢሬቻ በደብረ ዝቋላ አይከበርም

 1. Anonymous March 13, 2015 at 2:14 pm Reply

  ፓትርያርኩ ሹመቱን ከሰጣቸው መንግስትና ካድሬዎች ጋራ ሲያሸቃብጡ እንዲሁም ተሐድሶ ቤተክርስያን ላይ እያደረሰ ያለውን አደጋና የተሃድሶ አቀንቃኞች የቤተክርስቲያን አባቶችን እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስን ሲሳደቡ(ቅ/ሲኖዶሱ ደግሞ ጊዜ ያለፈበትን አፈና አንጋሽ የተባለውን ልብ ይሏል)፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖና ሲሰጣቸው ፓትርያርኩ ራሳቸው በሕገመንግሥቱ የተሰጠ የኃይማኖትን መብት ይጥሳል ብለው ቀኖናው እንዳይፈፀምና ተሐድሶዎች ዛሬም እንዲፈነጩ ሲታገሉ ለተመለከተ ሰው አባ ማትያስ አላበደም ያሉትን አብዛኞቻችን እንዳልተቀበልነው እርግጠኛ ነኝ፡፡ ማስተዋል ቢኖራቸው በወቅቱ የተናገሩት ‘በሕገመንግሥቱ ምናም እያሉ የዘላበዱት ‘ያሳፍር ነበር፡፡ እንዲሁም ያሁኑን መዘዝ እንደሚያመጣ አያውቁም ማለት ይከብዳል:: የሌሎች እምነት ተከታዮች ቤተክርስቲያን ላይ ሲፈነጩ እንደደገፉ ዛሬም የእሬቻ በዓል ቢከበር ለምን ዝም አይሉም ነበረ? እሬቻ ይከበር ያለው መንግስት ቢሆንም የመንግስትን ጉዳይ አስፈፃሚ ካድሬ የቤተክህነት ሸማቂ ሰዎችም አይኖሩበትም ማለት ይከብዳል:: የሆነው ሆኖ ዛሬም ፓትርያርኩ ይህንን የሕገ መንግስት ወፈፌ ወሬ ትተው ስለሕገ ቤተክርስቲያን ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ቢያወሩ ይሻላቸዋል መካሪም ካለ ቢመከሩ ጥሩ ይመሰለኛል::

  የቤተክርስቲያን አምላክ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ሰላም ያድርግልን፤ እንዲሁም በስተርጅና ቤተ ክርስቲያንን ከማድማት እንዲቆጠቡ ልቦና ይስጥልኝ::

  • Anonymous March 16, 2015 at 8:23 am Reply

   የኛ ውድ የተዋሕዶ ተቆርቋሪ(Anonymous March 13, 2015 at 2:14 pm)፡-ተቆርቋሪነትህን አድንቀንልሃል!!ስማ!!ጸረ-ተሐድሶ ኮሚቴ የተቋቋመው በአባ ማትያስ አስተዳደር ዘመን መሆኑን አስተውል፣ፓትርያርኩ በወለጋ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን የደረሰባቸውን ግፍ ሲገልጹ “እውነት በወለጋ መንግሥት ያለ ይመስላል” ለማለት ድፍረት ነበራቸው፣የእሬቻን በዐል በዝቋላ መከበር ለመቃወም ወሬ በኢንተርኔት በማናፈስ ሳይሆን ቀጥታ ለሚመለከታቸው የክልል ርእሰ – መስተዳደር ለመጻፍ ቁርጠኝነት አላጡም፣በመጻፋቸውም ነው ኢቲቪ መግለጫ ለመስጠት የተገደደው፡፡ስለዚህ አጀንዳውን አትለጥጠው፡፡ብትችል ለድርጊታቸው እውቅና ስጥ ባትችል ዝም በል፡፡የቤተክሕነት ሰዎች በእሬቻ አከባበሩ ሳይኖሩበት አይቀርም እያልክ በግምታዊ ፍረጃ ራስህን አትጉዳ፡፡ፀጉርህን አትንጭ፡፡እንዳትበድል!!
   ስለ ሕገ – መንግሥቱ ጥራትና ጉድለት መበየን የፓትርያርኩ ተግባር አይደለም፡፡እንከን አለበት ካልክ የአንቀጹንና የንዑስ አንቀጹን ድክመቶች በዝርዝር ገልጸህ ጻፍበት፡፡በተለይ የኢኦተቤክንን ጥቅም ይጎዳል ብለህ የምትገምተውን አንቀጽ አብራርተህ ጻፍ፡፡ፓትርያርኩ ከመንግሥት በሚያገናኛቸው ጉዳይ ተባብረው ለመስራት ግን ያንተ ፈቃድ አስፈላጊያቸው አይመስለኝም፡፡እድሜያቸው እስካለ ድረስ ገና እንደሚሰሩ ማረጋገጫ እሰጥሀለሁ፡፡ምክንያቱም አባ ማትያስ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ናቸው፡፡መንግሥታችንም የኢትዮጵያ መንግሥት ነው፡፡የግብፅ አይደለም!!
   ቅ/ሲኖዶስ የፓትርያርኩ ውሳኔ ትክክል አይደለም ብሎ ካመነ ደብዳቤያቸውን በሚመጣው የግንቦት ቅ/ሲኖዶስ መርምሮ እርምት የመስጠት ሥልጣኑ በእጁ ነው፡፡ተሐድሶ በቤተክርስቲያን ፈነጨበት እያልክ ከጣራ በላይ ከመጮህ ጥቂት ማስረጃዎችን ብታቀርብልን ጥሩ ነው፡፡የአባ ማትያስ ፀረ – ተሐድሶ አቋም ከአሜሪካ እስከ ኢየሩሳሌም፣ከኢየሩሳሌም እስከ ኢትዮጵያ ጥርጣሬ ውስጥ ገብቶ አያውቅም፡፡ካስፈለገ በአሜሪካ ስቴቶች “ተዐቀቡኬ” በሚል ርእስ ያካሔዱዋቸውን ጉባኤያት ዝርዝር መረጃ እሰጥሀለሁ፡፡በጥንተ አብሶ የጠራ አቋም ይዘው የመጀመሪያ ሊባል የሚችለውን ውግዘት በነቀሲስ አስተርዐየ ፅጌ ላይ ያስተላለፉት እሳቸው ናቸው፡፡ለዚህ አይደል ቀሲስ አስተርዓየ በየፖለቲካ ገጸ-ድሩ ሲወነጅላቸው የሚውል፡፡የአባ ማትያስ ርቱዕ ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ አማኒነትን ጥያቄ ውስጥ ለመክተት መጣር ከንቱ መታተር!!የሐዲሳቱን ሊቅ በኑፋቄ መጠርጠር ከንቱ መታተር!!የጎንደሩ ሊቅ የየኔታ ዶ/ር አየለ ተማሪ ላይ የሐሜት ጣት መቀሰር ከንቱ መታተር!!አባ ማትያስ=ርቱዐ – ሃይማኖት!!
   በእኔ እይታ በእኒህ ርቱዕ ኦርቶዶክሳዊ አባት ላይ የሚሰነዘሩ ተቃውሞዎች አራት መነሻዎች አሉዋቸው፡፡አንደኛው ቤ/ክ ከዚህም በላይ በሁለንተናዊ መልኩ እንድትራመድና ሀገራዊ ሚናዋን በቅጡ እንድትወጣ ካለመ ቀናኢነት የሚነሳ ነው፡፡ይሄ ደስ ያሰኛል፡፡እነዚህን ወገኖች መስማትና ማሳተፍ ይገባል፡፡በአካሄድ ቢሳሳቱ እንኳ ስለቅንነታቸው ሊሰሙ ይገባል፡፡ሌሎቹ ግን ኢህአዴግንና ቤተክሕነትን ደርቦ ከሚያይ ፖለቲካዊ ፍረጃ፣ህወሀትንና ትግራይን ደርቦ ከሚያይ ፀረ-ትግራዋይነት ዘረኝነት የሚመነጭ ጥላቻ፣ፓትርያርኩ ማኅበረቅዱሳንን ለምን ተናገሩብን በሚል ከአንዳንድ አባላቱ ቡድንተኝነት የሚመነጩ አሉባልታዎች በመሆናቸው እንዳላዩ ማለፍ ነው፡፡ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች በእነሱ የፖለቲካ አቋም የተቃኘ ፓትርያርክ፣እነሱ ከተወለደበት አካባቢ የተወለደ ፓትርያርክ፣መዋቅሩን ለማኅበረቅዱሳን የበላይነትና ኢ-መዋቅራዊ አካሄድ የሚያመቻች ፓትርያርክ እስካልተሾመ ድረስ ጩኸታቸውን አያቆሙም፡፡ስለዚህ ጩዋሂዎቹን እንዳላዩ ማለፍ ነው፡፡ልብ ይስጣቸው እንዳንል አዋቂ አጥፊ ነን ለማለት ይዳዳቸዋል፡፡ያደረባቸው በጾምና ጸሎት ካልሆነ በቀር የሚለቅ አልመሰለኝም፡፡ከተቻለ ላለፉት 23 አመታት የተዋረሳቸው እንዲወጣ ቀኖና ይዘን እንጸልይላቸዋለን፡፡እስከዚያው ግን በጥላቻ ለታመሙት ወንድም እኅቶቻችን እግዚአብሔር ይማራቸው እንላለን፡፡
   ለአባታችን አቡነ ማትያስ ያለኝ ፍቅር የልብ ነው!!አኪዎስ-አኪዎስ-አኪዎስ!!ይደልዎ-ይደልዎ-ይደልዎ ብለን የመረጥናቸውን ቅ/ፓትርያርክ እንከተላለን!!ዛሬም ነገም!!ምክንያቱም ፓትርያርክ ናቸው!!ምክንያቱም ፕትርክና እንደፖለቲከኛ እንደፈለግን እያወረድን ሌላ በምትኩ የምንሾምበት መንበር አይደለም!!ምክንያቱም የፕትርክና መንበር የእድሜ ልክ ነው!!በመሆኑም ማገዝ እንጅ መገዝገዝ አዋጭ አይደለም!!

   • Anonymous March 17, 2015 at 1:01 am

    Wet awkwh mothal ahune man yemut ewnet tenagerkna etamenahu belh new esti julun yemichel Amlke yefredew

 2. Anonymous March 13, 2015 at 2:19 pm Reply

  ህገ መንግስቱ እኮ እብዶች ተሰብሰበው ጤነኛውን ለማሳበድ እንዲሁም የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት ቀደምት ስልጣኔ ለማውደም የሰሩት ነው የሚመሰለው

 3. Anonymous March 13, 2015 at 11:48 pm Reply

  1st and 2nd asteyayet yesetachut. Azenkulachu. Gen tenegna nachu? Hara tewahdo azegajoch enantes tenegna nachu? Be ergetegnet tsebel mibal neger ketetemekachu 10 amet alfoachuhal. Endewem tsebel matweduna metferu yemeslegnal. BE AKRABIACHU BALEW OR BEWEDEDACHUT BETE KERESTIAN TETEMEKU.

 4. Anonymous March 15, 2015 at 8:28 am Reply

  ……ተዘጋጅቼ ነበር ወደ ዝቋላ የተጓዝኩት፡፡ በዓሉን በሰላም አክብረን ተመልሰናል፡፡ የድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይሁን፡፡

  ዝናብ የሚዘንበው በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ ግንድ ቂቤ በመቀባት ወንዝ ዳር ቄጤማ በመበተን አይደለም፡፡

  • Gossa March 17, 2015 at 10:24 pm Reply

   የሐራ ዘ ተዋህዶ አድሚኖች …እኛ የምንሰጠውን አስተያየት በሎክ በማድረግ መፍትሄ የሚገኝ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል፡፡ ቅድም በጭቋላ (እናንተ ደብረ ዝቋላ በምትሉት) ሀይቅ ላይ የሁለተኛውን ዓመታዊ የኢሬቻ በዓል አከባበርን በተመለከተ በተነሳው አለመግባባት ይህ ሪፕላ እያደረኩለት የምገኘው ስሙን ያልገለጠ ኒዮ-ነፍጠኛ ወደ ኦሮሞ ህዝብ ለወረወረው የአሽሙር ስድብ መልስ ብሰጠው ብሎክ አድርጋችኋል፡፡ ለመሆኑ የኛን አስተያየት በሎክ በማድረግ መፍትሄ የሚገኝ መስሏችኋል???….እስቲ ይህ ግለሰብ የኦሮሞን ህዝብ ለመስደብ የሚናገረውን ተመልቱ …. “ዝናም የሚዘንበው …..ግንድ ቅቤ በመቀባት ወንዝ ዳር ቄጤማ ቄጤማ በመበተን አይደለም፡፡” ተዘጋጅቼም ነበር ብለሃል…ምን ለመሆን ነበር ባክህ???
   እኔ የኦሮቶዶክስ ክርስትናን ከቤተሰቤ የወረስኩት በመሆኑ አከብረዋለሁ፡፡ ሆኖም እንዲህ ዓይነት የአንድን ትልቅ ህዝብ ባህል ለማንቋሸሽ የሚወረወር ቃል ግን ያሳዝነኛል፡፡…..አሁን በዚህ በ21ኛው ክፍለዘመን ላለፉት 125 ዓመታት የአባቶቻችንና የአያቶቻችንን ባህል፤ቋንቋና ማንነት ለማጥፋት የሄዳችሁበት መንገድ አሁን የሚያስኬድ አይመስለኝም፡፡ በመሰረቱ አባቶቻችንና አያቶቻችን የኢሬቻን በዓል በዓመት ሁለት ግዜ ሲያከናውኑ የነበሩት ይህ ኒዮ-ነፍጠኛ በትምክህት ድንቁርና ተወጥሮ እንደተናገረው ….ግንድን፣ወንዝን ወይም ዛፍን ለማምለክ ሳይሆን … የዝናም፤የወራጅ ወንዞች፤የከብቶች፤ የአዝመራው፤ የሰው ልጆችና የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ለሆነ፤… በሰው ልጅ አይን ለማይታይ፤…በእጅ ለማይዳሰስ ዋቃ (ፈጣሪ) ነው፡፡ ዋቄፈታ ማለት ይህን ሀያል የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ (ዋቃን)ማምለክ ወይም ማመን ማለት ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በዋቃ ማመን የጀመረው እና ለዋቃ በዓመት 2 ጊዜ መስዋዕትን የማቅረብ ስረዓትን ዛሬ ሳይሆን የጀመረው ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ነው፡፡ ያኔ ከ4ኛው ክፍለ ዘመን በፊት፣ የናንተ ቅድም አያቶች … ኤደን ባህረሰላጤ ላይ በተከሰተ ችግር ጉዟቸውን አቋርጠው በድንገት ወደ ኢትዮጵያ በሽሽት ጎራ ባሉት ፤ ፍሪምናጦስ (በኋላ አባ ሰላማ በመባል የመጀመሪያ ፓትርያርክ የሆነው ማለት ነው) እና ኦዶስዮስ ከመጠመቃቸው በፊት ጨረቃና ክዋክብት ያመልኩ በነበረበት ዘመን…የኦሮሞ ህዝብ በገዳ ስርዓት የሚመራ፤ በዋቃ የሚያምን ፤ ልክ እንዳሁኑ ኢሬቻን በዓመት ሁለት ግዜ እያከናወነ ለፈጣሪው መስዋዕት የሚያቀርብ ስልጡን ህዝብ እንጂ…ይሄ ኒዮ-ነፍጠኛ እንደሚያስበው በግንድ ወይም በዛፍ የሚያመልክ ህዝብ አልነበረም…አይደለምም፡፡ ያለመታደል ሆኖ ከዛሬ 125 ዓመት ጀምሮ …ኦሮሞ ባህሉን ፤ ቋንቋውን ፤ማንነቱን ሰርዞ የናንተን ማንነት እንዲቀበል ቀላል የማይባል ዘመቻ እንደተከናወነበት ጥቂት የማይባሉ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ ከላይ እንደተባለው በገዳ ስርዓት ኦሮሞ በዓመት ሁለት የኢሬቻ በዓላት ያከናውናል፡፡ እነዚህም፤
   (1) የዓመቱን መጀመሪያ ኢሬቻ የሚያከናውነው ለምስጋና ነው፡፡ ምስጋና እና መስዋዕት ለዋቃ (ለፈጣሪ) ለማቅረብ! …..ከክረምቱ ወደ ፀደይ ወራቶች ላሻገራቸው…ከብቶቻቸውን፤ልጆቻቸውን እና እነርሱን በሰላምና በጤና ለጠበቀ፤ አዝመራቸውን ላሳመረ ወይም ላቃና ፈጣሪ (ዋቃ)!
   (2) ሁለተኛው ኢሬቻ ….ዝናብን እንዲያዘንብላቸው ለዋቃ ልመናና መስዋዕት የሚያቀርቡበት ነው፡፡
   እንግዲህ ይህንን የመሰለ ለብዙ ሺህ ዓመታት የቆየ የህዝብ ማንነት መገለጫ ባህልን ነው… አባቶቻችሁ እንዲጠፋ እና እንዲረሳ ካለፉት 125 ዓመታት ጀምረው ሲጥሩ የነበረው፡፡ የሚያሳዝነው ዛሬም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ጥቂት የማይባሉ የዚህ ትምክተኛ ግለሰብ አይነቶች መኖራቸው ነው፡፡

   • Kuba March 25, 2015 at 12:53 pm

    Gosa thaks Ialso shared ur Idea.

 5. Anonymous March 15, 2015 at 7:33 pm Reply

  Abatachin aba abune matias en hatiyategnaw tinish neger eleminiwotalehu. Adera behilmie Tsehay sitiwota bilew yetenagerut shumet endemishomu guadegnawe tergumewutal .yetesete tsega endeminesa yawukalu ersiwo tenkirew yikir yibelu yetezenagut neger kale zewor bilew yasibu. Ante atmekiregnim bilew endayilu lememker dingay yimekral. Yesew lij degimo kibur new. Lersiwe melkam ereft endihonliwe entseliyalen. Silezih tehadso beyet endale yiwoku yimkeru yemaymeles kale yitseliyu degimo kaltemelese yileyut mikniyatum leloch bogochin ke ijwe endayneteku. Amen yitseliyulign bereketwo yidresen amen

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: