የኢሬቻ በዓል በደብረ ዝቋላ እንደሚከበር የተላለፈው ዘገባ ማስተባበያ እንዲሰጥበት ተወሰነ

debra zeq

 • ለአፈጻጸሙ የወረዳው እና የዞኑ አስተዳደር ባለሥልጣናት ሓላፊነት ወስደዋል
 • ከመጋቢት ፭ ክብረ በዓል በፊት ማስተባበያው እንዲተላለፍ ከስምምነት ተደርሷል
 • ከኹሉም አካላት የተውጣጣ የሽማግሌዎች ኮሚቴ የችግሩን ቆስቋሾች ያጣራል
 • በክብረ በዓሉ ቀን የተጠናከረ ጥበቃ እንዲደረግ መመሪያ ተሰጥቷል

* * *

 • ‹‹ለእኛ ዐዲስ ነገር ነው፤ እዚኽ ቦታ ኢሬቻ የለም፤ በአራት ወይም በስምንት ዓመት አንዴ ዝናም እምቢ እንዳይለን ገዳሙን አስፈቅደን ከምንፈጽመው ሥርዐት ውጭ በተነገረው መልኩ የሚከበር በዓል የለም፡፡ ያስተላለፉት መጠየቅ አለባቸው፡፡››

/የአባ ገዳ ተወካዮች/

 • ‹‹ኅብረተሰቡን ከእኛ ጋራ ሊያጣሉ የሚፈልጉ ግለሰብ አመራሮች አሉ፡፡… ለተላለፈው መልእክት ሓላፊነት የሚወስድ አካል ካልተገኘ፣ የመጋቢት ፭ ክብረ በዓል ከመድረሱ በፊት በስሕተት የተላለፈ መኾኑ ይገለጽልን፡፡››

/የገዳሙ አስተዳደር/

 • ‹‹እናንተ ሰላም ፍጠሩ፤ [በክብረ በዓሉ] ከተለመደው ውጭ አንዳችም የሚደረግ አይኖርም፤ ጥበቃውም እንዲጠናከር ይደረጋል፤ የተላለፈውን ዘገባ አጣርተን በኦሮምኛ እና በአማርኛ ማስተባበያ እንዲሰጥበት እናደርጋለን፡፡››

/የዞን የአስተዳደርና ጸጥታ ሓላፊዎች/

Advertisements

7 thoughts on “የኢሬቻ በዓል በደብረ ዝቋላ እንደሚከበር የተላለፈው ዘገባ ማስተባበያ እንዲሰጥበት ተወሰነ

 1. Anonymous March 9, 2015 at 11:31 pm Reply

  የወያኔን መጨረሻ መድኃንያለም ያሳየናል መታገስና ለ ሃይማኖታችን ዘብ መቆም ብቻ ነው ከኛ የሚጠበቀው::

 2. Fikremariam mersha March 10, 2015 at 6:02 am Reply

  እግዚአብሔር ይጠብቀን… እንኯን ሳምንት ያለፈው እሣት ይቅርና በሁለት ሰዓት ውስጥ ስንት ነገር ያቃጥል ይሆን?

 3. WULETAW March 10, 2015 at 12:48 pm Reply

  ይህ እንዳይሆን ለጣሩ ሁሉ ምስጋና ይድረሳቸው፡፡በተለይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በመናበብ ጉዳዩን በተቋማዊ መንገድ ለመፍታት የሄዱበት የሰከነ ጥረት የሚያስመሰግን ነው፡፡ደስ ብሎናል፡፡ሀገራችን ሰፊ ናት፡፡ሁሉም ልቡ በፈቀደለት መጠን የእኔ ነው የሚለውን እምነት በመተሳሰብ ለማስኬድ ከፈለገ ከቶም የቦታ ጥበት አይገጥመውም፡፡ስለዚህ ተከባብረንና አንዱ አንዱን ሳያስከፋ የየራሱን እምነት በግልና በቡድን እንዲከተል ለተቋማቱ የጸኑ ይዞታዎች መከበር-መከባበር መስራት የሁላችንም ድርሻ ነው፡፡
  ደግሜ ደጋግሜ በሂደቱ ገንቢ ሚና የተጫወቱ የቤተክርስቲያኒቱን ማኅበረ – ምዕመናን እና መንግሥታዊ አካላት ለማመሰገን አልሰንፍም፡፡ሲያስከፉን የምንወቅሰውን ያህል በጎ ሲሰሩ ደግሞ እውቅና ብንሰጣቸው ውለታው ለራሳችን ነው፡፡መውቀስ ብቻ አያንጽም፡፡ደግ-ደጉን ስናይ እንመርቅ፡፡እግዚአብሔር ያክብራችሁ፡፡አባታችንም ረጅም እድሜ ከጤና ጋር አድሎዎት ኦርቶዶክሳዊውን መንጋ ለመጠበቅ ብርታቱን ይስጥዎት፡፡
  ስለ ሁሉም አምላከ ቅዱሳን የተመሰገነ ይሁን፡፡የቅድስት ቤተክርስቲያንን ክፉዋን አያሰማን፡፡አሜን፡፡

 4. Anonymous March 11, 2015 at 5:24 pm Reply

  ይህ ብዙም አይደንቅም ለፈተና የባሰ ይመጣል
  ለሀይማኖታችን ከፀሎት ጋር በርትቶ መቆም

  ይህ አሸባሪ ግን በቅርቡ የእጁ አያጣውም ምናለ በሉኝ ፡ ;

 5. Elias Kassahun March 12, 2015 at 1:17 pm Reply

  እኔ የሚገርመኝ ምን አስፈልጎ ነው በየ 4 ወይም በየ 8 አመቱ ዝናብ ሲጠፋ ለመለመን ጠይቀን አስፈቅደን
  የምናደርገው የሚባለው፡፡ ዝናብ ከጠፋ ቤተክርስቲያንዋ በቦታዋ ትጸልይላችሁዋለች እንጂ ማንም በቦታዋ
  አይጸልይም፡፡ እናንተም በሰው ቦታ ማድረግ ለምን አስፈለገ አሁንም አልሸሹም ዞር አሉ ነው የገዳው ስርአት
  አራማጅ የተናገሩት፡፡ ከፈለጋችሁ ኦዳ ነቤ አለ እዛ ሄደው የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ፡፡ ዝቁዋላ ምን
  እንደፈለጋችሁ አሁንም ግልጥ ነገር የለም፡፡ የተዳፈነ እሳት ነው የሆነው፡፡ ነገ አውቀው ይጠይቁና ክልላችን ነው
  ውጡ ይመጣል፡፡ ሁሉም የገዳ ሰዎች እችን ቤተክርስቲያን እንደማጋፉዋት እርግጠኛ ነኝ ይቀበሩባታልና፡፡ እምነትዋን
  ተቀብለው ዝናብ ሲጠፋ ጸሎት ታድርግልን እንደማለት በራሳችን አካሄድ እንሄዳለን ካሉ ግን በጣም ችግር ነው
  የሚሆነው፡፡ የትኛውም የቤተክርስቲያንዋ አማኝ ነኝ የሚል ሁሉ የቤተክርስቲያንዋን የበላይነት ተቀብሎ ሊታዘዛት
  ይገባል፡፡

 6. senu August 24, 2016 at 12:35 am Reply

  Erecha mindinew ?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: