ሰበር ዜና – በዝቋላ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ

zequulla

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ከተማ በሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ መቀስቀሱን የገዳሙ መነኰሳት እየተናገሩ ነው፡፡

ከጠዋቱ 2፡00 ገደማ የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎው የጀመረው ወንበር ማርያም እየተባለ በሚጠራው በገዳሙ ሰሜናዊ አቅጣጫ ነው፡፡

ይህ አቅጣጫ፣ የገዳሙ ሞፈር ቤት የሚገኝበት መውጫ መንገድ ሲኾን በአኹኑ ሰዓት በበርካታ ቦታዎች ጭስ እንደሚታይ በመነኰሳቱ ተገልጧል፡፡

የቃጠሎው መንሥኤ በውል ባይታወቅም እሳቱ በአካባቢው ባለው ከባድ የነፋስ ኃይል ወደ ገዳሙ መውጫና በገዳሙ ዙሪያ እንዳይስፋፋ ተሰግቷል፡፡

ziquwala_17የአቅራቢያው ነዋሪ ኅብረተሰብ በጥሩንባ በተላለፈው የድረሱልን ጥሪ የተሰባሰበ ሲኾን ወደ ወረዳው ጽ/ቤትም ተደውሎ የአስተዳደሩ አባሎችና የፖሊስ ኃይል በስፍራው መድረሳቸው ተገልጧል፡፡ ‹‹ቃጠሎውን በቅጠልና በአፈር ለመከላከልና መዛመቱን ለመቀነስ የነፋሱን ጋብ ማለት እየተጠባበቅን ነው ብለዋል፤›› አንድ የገዳሙ መነኰስ፡፡

በጥንታዊውና ታሪካዊው ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ ሲደርስ የአኹኑ የመጀመሪያ አይደለም፡፡ መጋቢት ፲ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. በደረሰው የእሳት ቃጠሎ እንደ አርዘ ሊባኖስና የሐበሻ ጥድ ያሉት አገር በቀል ዛፎች በስፋት ወድመዋል፡፡ መጋቢት ፰ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. የተቀሰቀሰው ቃጠሎ ደግሞ ተኣምራዊና ግራ አጋቢ ጠባይዕ የታየበት ነበር፡፡ በምሥራቃዊ አቅጣጫ በሚገኘው የመንግሥት ደን ውስጥ ተከሥቶ በአንድ ገጽ ኃይሉ ሲቀንስ በሌላ አቅጣጫ እየተዛመተ ገዳሙን ጨርሶ ለማጥፋት በተቃረበበት ኹኔታ ከአዲስ አበባ፣ ከቢሾፍቱና ከአዳማ በተመሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ በጎ አድራጊ ምእመናንና አካላት መተባበር እንዲኹም በመከላከያና በፖሊስ ኃይሎች እገዛ መገታቱ የሚታወስ ነው፡፡

በመጪው መጋቢት ወር መጨረሻ በገዳሙ የጠበል – ሐይቅ የኢሬቻን በዓል ለማክበርና በደብረ ዝቋላ የአባ ገዳ ሐውልት ለመትከል በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ መታቀዱንና በመንግሥት ብዙኃን መገናኛ መገለጹን ተከትሎ ቤተ ክርስቲያናችን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በኩል ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር በጻፈችው ደብዳቤ ተቃውሞዋን በማሰማት ላይ እንዳለች ይታወቃል፡፡DSC_0642[1]ጥንታዊውና ታሪካዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዛሬ በሚታወቅበት ቦታ ላይ ከተገደመ ከ700 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ በገዳ ደጅ ጠኚውን፣ አፈር ጠባቂውንና የአብነት ትምህርት መምህራንና ደቀ መዛሙርትን ሳይጨምር እስከ 350 መነኰሳትና መነኰሳዪያት እንደሚገኙበት ተዘግቧል፡፡

 

Advertisements

9 thoughts on “ሰበር ዜና – በዝቋላ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ

 1. NETSANET March 3, 2015 at 2:28 pm Reply

  እኔ ምንም ሊገባኝ አልቻለም ምን አርጉ ነው እቺን ሃገር ወዴት እየወሰዷት ነው እነዚ በዚ ሙስሊሙን በዚ አብያተ ክርስቲያንን በዚ የ ሃገሪቱን ቅርስ በዚ የህዝቡን ንብረት በዚህ ብሄር ከብህሄር እያነጣጠሉ ምን ሊያደርጓት ነው ሃገሬን በጣም ያስፈራል እንጃ ጌታ ብቻ ከመካከላችን ክፉ ሃሳብ ያላቸውን ሳይዘገይ ይንቀልልን እንጂ ጣጣቸው አይለቀንም

 2. Anonymous March 3, 2015 at 6:49 pm Reply

  Egzabhar yawiqal lehulum ngr

 3. endalke chane March 3, 2015 at 6:54 pm Reply

  እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ጸሉት ኀይሉን ይግለጥ

 4. kidane negash March 3, 2015 at 7:45 pm Reply

  አቤቱ የሆነብንን አስብ

 5. Anonymous March 4, 2015 at 7:22 am Reply

  Mene eyhone nwe yilwe ho amelika ante tiwkileke ethoipiane anthe tebkite

 6. gezu March 4, 2015 at 7:31 am Reply

  abetu ante atitewen ende cherinetih yene geta

 7. abosent March 5, 2015 at 7:19 am Reply

  wedajoch hoy tselot hylen tadrgalch selzih entsely
  menm men biyadergo bit kerstiyan heyaw nat egna gen endanwdk entenkeke

 8. Ewunetu March 5, 2015 at 8:22 am Reply

  God is faithful to his people. He (God) knows the source of everything happening in the universe. His judgement is perfectly right. He does not pay evil for evil but mercy over his own followers. So we have to not say nothing evil to anybody who did wrong things.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: