የዐድዋው ዘማች የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር: አለቃው ቀንደኛው አማሳኝ ኃይሌ ኣብርሃ ባነገሠው ሙስናና ዓምባገነናዊ አስተዳደር ተቸግሯል

 • በጨረታ የተሰጠ የብር 61 ሚ. ሕንፃ በዲዛይን ክለሳ ስም ያለጨረታ ብር 175 ሚ. ተደርጓል
 • ሢሦ ለማይሞላ ሥራ የተፈጸመው ከብር 25 ሚ. በላይ ክፍያ እንዲመረመር ተጠይቋል
 • ሊቀ ጳጳሱ ያልፈቀዱት የብር 40 ሚልዮን የኪራይ ውል ከንግድ ባንክ ጋራ ተፈጽሟል
 • ከባንኩ የተለቀቀው ብር 14 ሚ. ያህል ገንዘብ በሕገ ወጥ ክፍያ እንዳይባክን ተሰግቷል
 • ያለውድድር በተሠራ ፕላን ከብር 12 ሚ. በላይ የተገመተ ሕንፃ ያለጨረታ ሊሰጥ ነው
 • ለካህናቱ የተደረገው የብር 250 ጭማሪ ሀ/ስብከቱ ያላጸደቀው ‹‹መደለያ›› ነው ተብሏል

*        *        *

 • አለቃው ‹‹ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው›› በሚል ማናለብኝነት ከተጠያቂነት ውጭ ኾኗል
 • ችግሩን ለሀገረ ስብከቱ ያጋለጡት የደብሩ ዋና ተቆጣጣሪ ከሥራና ከደመወዝ ታግደዋል
 • ነጻ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የልማት ኮሚቴው ባለሞያዎች በአለቃው ተመርረው ተበትነዋል
 • ሰ/ት/ቤቱ ለኮርስ ከሚያሠራው ሕንፃ ለንግድ ቤት ልቀቁ በሚል ጫና እያደረገበት ነው
 • የፓትርያርኩን ሲኖዶሳዊ ውሳኔ እግድ የተቃወሙ አመራሮችን አንለቃችኹም ብሏል

*        *        *

 • ‹‹ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው፤ ማንም ምንም አያመጣም፤ አላርፍ ካልክ ከገጸ ምድር አጠፋሃለኹ፡፡››

/የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ አስተዳዳሪ መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ ሕገ ወጥ አካሔዱን በአስተሳሰብና በአሠራር የሚቃወሙ አገልጋዮችንና ምእመናንን በማሸማቀቅ የሚታወቅበት የዛቻና ማስፈራሪያ ቃል/

/ምንጭ፡- አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፯፻፹፱ የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም./

St.-Georges-Cathedral-Addis-Ababa

ታሪካዊው የዐድዋ ዘማችና ባለድል ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚገኝበት የመናገሻ ገነተ ጽጌ ደብር

ዐድዋን ጨምሮ በተለያዩ ጦርነቶች በመዝመትና በነገሥታት መናገሻነቱ የሚታወቀው ታሪካዊው የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ባለዕዳ በሚያደርግና አገሪቱን በሚጎዳ ከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና የመልካም አስተዳደር ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

ደብሩ በራስ አገዝ ልማት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የጠቀሱ የደብሩ ሠራተኞችና ምእመናን በሰነድና በቃል ባቀረቧቸው አስረጅዎች፣ ‹‹በልማቱ በማመካኘት የሚታየው የሥራ ሒደት መልሶ ልማቱን የሚያኮላሽና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው፤›› ብለዋል፡፡

በተለይም ከ፳፻፮ ዓ.ም. መጀመሪያ አንሥቶ በደብሩ አስተዳደሪ መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ የሚፈጸሙት የመዋቅር ጥሰትና መመሪያን ያልጠበቁ ግለሰባዊ አሠራሮች በመባባስ ላይ እንዳሉ ነው ያስረዱት፡፡ ለዚኽም ከሕንፃ ግንባታና የኪራይ ውሎች ሕጋዊነት፣ ከኪራይ ገቢ አሰባሰብና ከወጪዎች አግባብነት አኳያ የደብሩ ገንዘብ አላግባብ እንዲባክን ተደርጓል ያሉባቸውን ጉዳዮች በማሳያነት አቅርበዋል፡፡

ደብሩ ‹‹ዳዊት ወንድሙ›› በተባለ የሕንፃ ሥራ ተቋራጭ በማሠራት ላይ የሚገኘው ባለአራት ፎቅ የንግድ ማዕከል ሕንፃ፣ በሰኔ ወር ፳፻፬ ዓ.ም. በውስን ጨረታ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት በሰበካ ጉባኤውና በልማት ኮሚቴው ጥምር የጋራ ስብሰባ ለአሸናፊው ድርጅት የተወሰነና የኮንትራት ውሉም በብር 61‚234‚885.02 ጠቅላላ ወጪ የተፈጸመ እንደነበር ተገልጧል፤ አማካሪ ድርጅቱ የተቀጠረውም በግልጽ አሠራር ተለይቶ ሲኾን በግንባታው ሒደትና በክፍያዎች አፈጻጸም የልማት ኮሚቴው ቴክኒክ ክፍል ሞያዊ ይኹንታና ማረጋገጫ በመስጠት ልማቱን ለማገዝ ጥረት አድርጎ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ውሉ እንደ ቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ በማዕከል (በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት) ተፈቅዶ ግንባታው እየተካሔደ ባለበት ኹኔታ፣ የደብሩ አስተዳደር በዲዛይን ክለሳ ሰበብ የግንባታ ዋጋውን ከዕጥፍ በላይ በማናር የሥራ ውሉን መቀየሩ ተመልክቷል፡፡ አልፋ አማካሪ መሐንዲሶች የተሰኘውን የቀድሞውን አማካሪ መሐንዲስ በማሰናበት ‹‹የዲዛይን ክለሳና ተያያዥ ሰነዶች ፍተሻ በማስፈለጉ›› በሚል ዳንኤል አሰፋ ፕራክቲሲንግ አርክቴክቸር የተባለ አማካሪ ያለምንም ግልጽ መመዘኛና ውድድር በጥር ወር መጀመሪያ ላይ ቀጥሯል፡፡ ከደብሩ ዋና ጸሐፊ ጋራ ባለው ግለሰባዊ ትውውቅ የመጣው አማካሪ መሐንዲስ ያለውድድር ለሠራው የፕላን ማሻሻያ ብር 80‚500 የተከፈለ ሲኾን የግንባታ ወጪውም ከብር 175 ሚልዮን በላይ እንዲንር መደረጉ ታውቋል፡፡

የኮንስትራክሽንን ሕጉን በመጣስ ያለጨረታ የተሰጠው ‹‹የፕላን ማሻሻያ›› እና የቃለ ዐዋዲውን ድንጋጌ በመተላለፍ ሀገረ ስብከቱ ባልፈቀደው ‹‹የተከለሰ ዲዛይን›› መቀጠሉ የተገለጸው ግንባታ፣ በአነስተኛ ግምት ከብር 80 ሚልዮን ያላነሰ የወጪ ልዩነት ቢታይበትም እንደማሻሻያ የተጨመሩት የአሳንሰርና የኤሌክትሪክ ዝርጋታዎች የተጠቀሰውን ወጪ ምክንያታዊ ለማድረግ እንደማይበቁ ተገልጧል፡፡ ሕንፃው ከጠቅላላ ሥራው ከሢሦ ባልበለጠበት በአኹኑ ደረጃው እንዲከፈል የታዘዘው ወጪ ከብር 25‚536‚438.98 በላይ መድረሱ፣ ሥራው በማዕከል ከተፈቀደው ውጭና በተለየ ውል እየተካሔደ መኾኑን እንደሚያረጋግጥ በአስረጅነት ተጠቅሷል፤ የልማት ኮሚቴው ቴክኒክ ክፍል የግንባታ ጥራት ምስክርነት ያልተደመጠበትና የጋራ ውሳኔና ስምምነት ያላረፈበት በመኾኑም ለተቋራጩ ሲፈጸም የቆየው ክፍያ አግባብነት በገለልተኛ አማካሪ መረጋገጥ እንደሚገባው ተጠይቋል፡፡

በዲዛይን ክለሳ ስም ከ175 ሚልዮን በላይ የናረው የግንባታ ወጪ በተጋነነ ዋጋ በሚፈጸሙ የሥራ ውሎች አላግባብ እንዲባክን እየተደረገ ስላለው የደብሩ ገንዘብ ኹነኛ መገለጫና አስቸኳይ እርምት የሚያስፈልገው ነው የሚሉት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ደብሩን በጎበኙበት ጥር ወር አጋማሽ ግንባታው የሚጨርሰው ጠቅላላ ወጪ እንደኾነ ተደርጎ በሪፖርት እስከ መገለጽ መድረሱ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ ከሕንፃ ግንባታው በተጨማሪ በዕድሳትም ስም ወጪ የተደረገው እስከ ብር 60‚000 ከፍተኛ ገንዘብ ተገቢው የደረሰኝ ማስረጃ ሳይቀርብ እንዲወራረድ አስገዳጅ ትእዛዝ በአስተዳደሪው እንደሚሰጥ በአቤቱታ አቅራቢዎቹ ተብራርቷል፡፡

የደብሩ ይዞታዎች በኾኑ ኹለት ሕንፃዎች ላይ ቅርንጫፎችን ለመክፈት የደብሩ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ጋራ ያደረገው የኪራይ ውል የቃለ ዐዋዲውን ድንጋጌ የጣሰና ‹‹ሀገረ ስብከቱ ምን አገባው›› በሚል የተፈጸመ እንደኾነ ነው የደብሩ ሠራተኞች የሚያስረዱት፡፡ የደብሩ አስተዳደር መስከረም ፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከዲስትሪክቱ ጋራ በፈጸመው የዐሥር ዓመት የኪራይ ውልየአቡነ ጴጥሮስ ቅርንጫፍ እና መሀል ፒያሳ ቅርንጫፍ ለመክፈት ብር 12 ሚልዮንና ብር 28 ሚልዮን በድምሩ ብር 40 ሚልዮን እንዲከፈለው መስማማቱ ታውቋል፡፡

አስተዳደሩ በውሉ መሠረት የኪራይ ክፍያው እንዲለቀቅለት ባንኩን የጠየቀ ከመኾኑም በላይ ስለቅድመ ክፍያው አፈጻጸም በጻፈው ደብዳቤ መሠረት እስከ አኹን ከብር 14 ሚልዮን ያላነሰ በቁጠባ ሒሳቡ ገቢ እንደተደረገለት ነው የተጠቆመው፡፡ በቃለ ዐዋዲው አንቀጽ 12(8) መሠረት፣ በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሳይፈቅዱና መመሪያ ሳይሰጡበት በተፈጸመው ውል የተገኘው ከፍተኛ ግምት ያለው የኪራይ ገንዘብ፣ መመሪያን ባልጠበቁ ከፍተኛ ክፍያዎች ሊባክን እንደሚችል አቤቱታ አቅራቢዎቹ ስጋት አላቸው፡፡

በዚህ ረገድ ለተቋራጭ መሐንዲሱና ለአማካሪው በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ብር ወጪ እየተደረገ መሰጠቱ የሚመለከታቸውን የሥራ ሓላፊዎች ማስጨነቁን ሠራተኞቹ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ተቋራጭ መሐንዲሱ ብድር ጠይቀዋል›› በሚል አራት ሚልዮን ብር በብድር መሰጠቱ በምሳሌነት ተወስቷል፡፡ ብድሩ ‹‹ለሥራው በጊዜ መፋጠን አስተዋፅኦ ስላለው›› በሚል የተፈቀደ ቢኾንም እንዲከፈል የታዘዘው ገንዘብ የሚመለስበት ዝርዝር ኹኔታ ሳይብራራና የሚመለከታቸው ክፍሎች ሐሳብ ሳይካተትበት እንደኾነ ተገልጧል፡፡

ለልማት መዋል የሚገባው የደብሩ ገንዘብ በብድር መልክ የተሰጠው ባለዕዳው ተቋራጭ፣ ደብሩ ከሚያከራያቸው ቤቶችና ቦታዎች ላይ ለጋራዥና ለመጋዘን ከተከራየበት ጊዜ ጀምሮ ከብር 420‚000 በላይ የኪራይ ውዝፍ ያለበትና ዕዳውን እንዲከፍል በተደጋጋሚ ቢጠይቅም በአስተዳደሩ በኩል የማስፈጸም ዳተኝነት መታየቱ ተዘግቧል፡፡ ይብሱኑ ተቋራጩ ከደብሩ በስተምሥራቅ በብር 12 ሚልዮን ብር ወጪ ይገነባል ለተባለው ሕንፃ ያለውድድር ለሠራው ፕላን ብር 35‚000 ተከፍሎታል፤ ፕላኑ በገለልተኛ ባለሞያ ባልተገመገመበትና የግንባታ ወጪ ዝርዝር ባልቀረበበት ኹኔታም የተባለውን ባለኹለት ፎቅ ሕንፃ እንዲሠራ ያለጨረታ የሥራ ውል ለመስጠት መታሰቡ ስጋታቸውን ከፍ እንዳደረገው ሠራተኞቹ አስረድተዋል፤ ባለዕዳነቱ ከመንግሥት ቫትም ጭምር እንደኾነ ነው አክለው የሚናገሩት፡፡

መዋቅራዊ አሠራርንና የሌሎችን የሥራ ሓላፊነት በማናለብኝነት በመጣስ እየተፈጸመ ነው በተባለው የገንዘብ ብክነትና የመልካም አስተዳደር ችግር ዋነኛ ተጠያቂ የተደረገው የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ፣ የቢሮ ሠራተኞችንና ባለሞያዎችን ለየብቻቸው በጽ/ቤት እየጠራ በዛቻ ቃል በማስፈራራትና በማሸማቀቅ በዋናነት ተጠቅሷል፡፡ የኃይሌ ኣብርሃ አስተዳደር በደብሩ ስለሚፈጽመው ከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና የአስተዳደር በደል ተደጋጋሚ መግለጫ ቢያቀርቡም ተቀባይነት ያጡት የደብሩ ዋና ተቆጣጣሪ አቤቱታቸውን ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሀገረ ስብከቱ ለፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ማቅረባቸውን ተከትሎ ከየካቲት ፰ ቀን ጀምሮ ከሥራቸውና ከደመወዛቸው በግፍ መታገዳቸው ታውቋል፡፡

‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ በእጄ ናቸው፤ ማንም ምንም አያመጣም፤ በሰላም አብሮኝ የማይሠራ ካለ ከገጸ ምድር አጠፋዋለኹ›› የሚሉ ኃይለ ቃሎችን በየስብሰባውና በየመድረኩ በመናገር ሐሳብ በነጻነት እንዳይራመድ ምክንያት በመኾኑ ከመስከረም ወር ወዲኽ ሞያዊ አስተዋፅኦዋቸውን ለደብሩ ልማት ዐሥራት ለማድረግ የተሰባሰቡት የልማት ኮሚቴው ቴክኒክ ቡድን ብዙኃን አባላት በዘለፋው ተመርረው መበተናቸውና የቀሩትም በጥቅም የተሳሰሩቱ መኾናቸው ተገልጧል፡፡ ከጥር ወር ጀምሮ ሀገረ ስብከቱ ሳያጸድቀው በገዛ ፈቃዱ ለካህናቱ ብር 250 ጭማሪ ማድረጉ ‹‹በይሉኝታ መያዣና መደለያ›› ነው ተብሏል፡፡

the heavily corrupt Haile Abreha

ጥብቅ አለቃ ኾኖ የአስተዳደር ሥራ ከጀመረበት ኩርፎ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንሥቶ እስከ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድረስ÷ በልማታዊ አባት ስም የቤተ ክርስቲያንን ሀብት በኪራይ አሳልፎ በመስጠትና ካባ ደንጊያ ሳይቀር በመሸጥ ራሱን የሲኖ ትራክና የልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ ቤቶችና ቦታዎች ባለጸጋ ያደረገው ቀንደኛው አማሳኝ ኃይሌ ኣብርሃ

ማንአለብኝ ባዩ ኃይሌ ኣብርሃ፣ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት በአባላቱ አስተዋፅኦና በልመና ለሚያሠራው ሕንፃም ምሕረት የለውም፡፡ በቦታ መጣበብ መርሐ ግብሮቹ እየተስተጓጎሉ የተቸገረው ሰንበት ት/ቤቱ÷ ለኮርስ(ሥልጠና)፣ ለቤተ መጻሕፍትና ለስብከተ ወንጌል አዳራሽ ዐቅዶ በደብሩ ሰሜናዊ ምዕራብ ከሚያሠራው ሕንፃ ወለሉን ለንግድ ቤት ኪራይ ካለቀቃችኹልን በሚል ማስገደጃ ጨርሶ ለመንጠቅ በማሰቡ ከአመራሩና አባላቱ ጋራ ፍጥጫ ውስጥ ገብቷል፡፡ ‹‹ምእመናን ናችኹ፤ አያገባችኹም ልንላቸው ይገባል›› ለሚለው ኃይሌ ኣብርሃ እንደኾን የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ‹‹ደግሶ ከማብላትና ጠላ ከማጠጣት›› እንደማያልፍ በራሱ አንደበት በይፋ ተነግሯል!! /መስከረም ፳፯ ቀን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ፣ ጥቅምት ፱ ቀን በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ የተናገረውን ከቪዲዮው ይመልከቱ/

አቤቱታ አቅራቢ ሠራተኞቹና ምእመናኑ በመጨረሻም፣ የሕዝብ ሀብት የኾነችው ቤተ ክርስቲያን ‹‹በልማት እየተመካኘ ተገቢ ባልኾነ የሥራ ሒደት በዕዳ እንዳትዘፈቅ፣ የሠራተኛው የሥራ ዋስትና አደጋ ላይ እንዳይወድቅ›› አሳስበዋል፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም ጥንታዊውንና ታሪካዊውን ደብር የሚታደግ ፈጣንና ፍትሐዊ ውሳኔ እንዲሰጥም ተማፅነዋል፡፡

ከመስከረም ወር ፳፻፯ ዓ.ም. ጀምሮ ደብሩን በዓምባገነንነት ማስተዳደር ላይ የሚገኘው መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ ሠራተኞችና ምእመናን በሰነድና በቃል ማብራሪያ አስደግፈው ስለሚያነሷቸው አቤቱታዎች የበኩሉን ምላሽ እንዲሰጥ በስልክ ለመጠየቅ እንደተሞከረ ተመልክቷል፡፡ ይኹንና ‹‹የምእመናን አቤቱታ እንድትቀበሉና ይህን ጉዳይ እንድትመረምሩ ሥልጣን የሰጣችኹ ማን ነው?›› በማለት የመለሰ ሲኾን፣ በአካል ካልኾነ በቀር በስልክ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመኾኑን ቢገልጽም ቀጠሮ እንዲይዝ ሲጠየቅ ግን ስልኩን በጠያቂዎቹ ጆሮ ላይ መዝጋቱ ነው የተዘገበው፡፡

ቤተ ክርስቲያንን በግብረ ሙስና በማዋረድና አባቶችን በመዝለፍ ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከተወሰነባቸው አማሳኞች ቀንደኛው ኃይሌ ኣብርሃ፣ ፓትርያርኩ አፈጻጸሙ እንዲታገድ በማድረጋቸው የታሪካዊውን ካቴድራል ሀብት ያለተጠያቂነት መመዝበሩን ተያይዞታል፡፡ ከዚኽም አልፎ የአ/አበባ ሀ/ስብከትና የሀ/ስብከቱ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የካቲት ፰ ቀን ከ160 የሰንበት ት/ቤት አመራሮች ጋራ ባካሔዱት ውይይት የፓትርያርኩን እገድ በመቃወማቸው ‹‹እንከሣችኋለን፤ አንለቃችኹም›› እያለ በመዛት ላይ ይገኛል – ከተጠያቂነት ውጭ በዓምባገነንነትና ምዝበራ ጎዳና የቀጠለው ኃይሌ ኣብርሃ!

*        *        *

ItaloAbyssinianWarpainting ከነገ በስቲያ ለ፻፲፱ኛ ጊዜ የሚከበረው የዐድዋ ድል በዓል በብሔራዊ ደረጃ መከበር የጀመረው በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደኾነ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ ዐድዋን ጨምሮ በማይጨውና በሰገሌ ጦርነት የዘመተው ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጣው ከአምቦ አካባቢ ልዩ ስሙ ዱላ ቆሪቻ ከሚባል ቦታ ነው፡፡ አንድ አርሶ አደር በስፍራው ሲያርስ አይቶ ለዐፄ ምኒልክ አስረክቧል፡፡ ታቦቱ ለተወሰነ ጊዜ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከተቀመጠ በኋላ ሐምሌ ፳፫ ቀን ፲፰፻፸፯ ዓ.ም. ወደ ገነተ ጽጌ መጥቷል፡፡

Emye Minilikዐፄ ምኒልክ ወደ ዐድዋ ሲዘምቱ መጀመሪያ ወደዚኽ ቤተ ክርስቲያን መጥተው ጸሎት አድርሰው በድል ቢመለሱ ዋናውን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ሊያሠሩ ስእለት ተስለው ነበር፡፡ ከዐድዋ መልስ ዐሥር ዓመታት ቆይተው የካቲት ፳፫ ቀን ፲፱፻ ዓ.ም. ዐፄ ምኒልክ፣ መኳንንቱና ሕዝቡ በተሰበሰበበት በግብፃዊው ጳጳስ በአቡነ ማቴዎስ መሠረቱ ተጣለ፡፡

ሥራውን ለማፋጠን ዐጤ ምኒልክ የጢስ ባቡር ከአውሮፓ አስመጥተው ነበር፡፡ የደብሩ መገንቢያ ድንጋይ የተመላለሰው የሰርኪስ ባቡር በሚባለው ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ በኾነው በዚኽ መኪና ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ አርኪቴክት አርፋኒዲስ የተባለ ግሪካዊ ሲኾን መሐንዲሱ ደግሞ ሙሴ ካስታኛ የተባለ ጣልያናዊ ነበር፡፡ የግንባታው ወጪ በአብዛኛው የተሸፈነው በመንግሥት ወጪ ነው፡፡ ዐፄ ምኒልክ 40‚000 ብር አዋጥተዋል፡፡ ደንጊያው ከኮተቤ፣ ቀበናና አምቦ፤ ጉልላቱ የተሠራበት ብረት ደግሞ ከፈረንሳይ የመጣ ነው፡፡

ፋሽስት ኢጣልያ በአምስት ዓመት ወረራው ወቅት ቤተ ክርስቲያያኑን የሚያፈርስበት ምክንያት ሲፈልግ ቆይቶ፣ ግራዝያኒ ላይ ቦምብ መወርወሩን ሰበብ በማድረግ ‹‹የአርበኞች መደበቂያ ነው›› በማለት ሕንፃውን ጋዝ አፍስሶ ለማቃጠል ቢሞክርም ሕንፃው ከመሠረቱ አልፈረሰም ነበር፡፡ ከውጫዊ ክፍሉ ይልቅ የተጎዳው ውስጣዊ ክፍሉ ነበር፡፡ ግምጃ ቤቱና መጻሕፍቱ ሲቃጠሉ ሥዕላቱም ተቃጥለዋል፡፡ የመቅደሱን ግድግዳም ጥቁር ቀለም ቀብቶት ነበር፡፡ ከፊሉ ካህናት ሲታረዱ ከፊሎቹም ወደ ሞቃዲሾ ተወስደዋል፤ የተቀሩትም ተሰደዋል፡፡ ታቦቱ ግን መምህር ወልደ ዮሐንስ በተባሉ ካህን አማካይነት ራስ አበበ ወልደ አረጋይ ወደ ነበሩበት ሰሜን ሸዋ ጎሽ ባዶ ዐፄ ዋሻ ማርያም በድብቅ ስለወሰዱት አልተገኘም፡፡ የተመለሰው ከድል በኋላ ግንቦት ፳፫ ቀን ፲፱፻፴፬ ዓ.ም. ነው፡፡

ፋሽስት ኢጣልያ ጥቁር ቀለም የቀባው የመቅደሱ ግድግዳ ሙሉ በሙሉ የለቀቀው የዐፄ ኃይለ ሥላሴ ፳፭ኛ የዘውድ ኢዮቤልዩ በዓል ሲከበር በተደረገ ዕድሳት ነው፡፡ የመጀመሪያውን ሥዕል የሣሉት አለቃ ኅሩይ ሲኾኑ የአኹኑን የሣሉት ደግሞ ሠዓሊ እም አእላፍና የተከበሩ የዓለም ሎሬዬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ናቸው፡፡

addis-ababa-st-georges-cathedral-entoto-maryam-church-35-638

ሥርዐተ ንግሥ

ዛሬ ያለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት የካቲት ፳፫ ቀን ፲፱፻፬ ዓ.ም ቢከበርም ሥራውን ያስፈጸሙት የዐፄ ምኒልክ ልጅ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ናቸው፡፡ በዚኹ ታላቅና ታሪካዊ ደብር በ፲፱፻፱ ዓ.ም. ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ወለተ ምኒልክ፣ በ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘውድ ጭነውበታል፡፡ ገዳሙ 467 ጋሻ መሬት ነበረው፡፡ ከዚኽ መካከል አብዛኛው በንጉሠ ነገሥት ዐፄ ምኒልክ የተሰጠ ነው፡፡ /ዲ.ን ዳንኤል ክብረት፤ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች፣ ፲፱፻፺፱ ዓ.ም./

Advertisements

10 thoughts on “የዐድዋው ዘማች የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር: አለቃው ቀንደኛው አማሳኝ ኃይሌ ኣብርሃ ባነገሠው ሙስናና ዓምባገነናዊ አስተዳደር ተቸግሯል

 1. Lishan March 1, 2015 at 7:34 pm Reply

  This report is unidirectional targeting a single person. Make it bidirectional.

  • melaku March 2, 2015 at 11:25 am Reply

   Before criticizing the report read it carefully! The person is not willing to talk with the Reporter!!! so, what is the mistake of the reporter. He did what he could.

   • Lishan March 4, 2015 at 6:53 pm

    How could the priest be able to talk with the reporter knowing that he going to write against him no matter what. Its ADDIS ADMAS’s reporter. If the priest wasnt able to talk it was possible to interview the Hagere Sibket head officials. The report says things are not going according to the he Hagere Sebket’s laws. It was also possible to interview other church officials. Such a thing is a national crime and if it was true for sure government Akabi Heg won’t be scielent. The megazine is not metioning the individuals giving the report. Its only targering a single person saying people said this and that. From a journalist’s point of view, its a little ….

 2. Anonymous March 2, 2015 at 11:19 am Reply

  Thank you very much for your information! keep on disposing corrupter!!!!

 3. melaku March 2, 2015 at 11:22 am Reply

  It is great! keep on disposing Corrupters!!!

 4. Anonymous March 3, 2015 at 11:09 am Reply

  “ከመስከረም ወር ጀምሮ-ከመስከረም ወር ጀምሮ” ማለት አበዛችሁሳ!!መልአከ መንክራት በመስከረሙ አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ በገሀድ ማኅበረቅዱሳንን ከተጋፈጡበት ጀምሮ እንዲሁም ቀደም ሲል የነበረውን የመዋቅራዊ ጥናት ይዘትና አካሄድ ፊትለፊት በመቃወማቸው ገና ብዙ እንደምታሳድዷቸው ገምተናል፡፡እናንተ እንደምትሉት “የሰራ ይፈተናል” እንላለን፡፡እሳቸው ይስሩ፣እናንተ አውሩ፡፡አዲስ ዓድማስም እንጀራ ነውና ይህን ሽጦ ይብላ፡፡
  የግንባታ ዲዛይን ሲከለስ የውል ጊዜና የግንባታ ዋጋም አብሮ እንደሚከለስ የታወቀና የተረዳ ስለሆነ፣በግንባታ ህጉ መሰረት ለተቋራጩ በቂ የቅድመ – ክፍያ ማስያዣ (Advance payment guarantee) እንዲያቀርብ በማድረግ የቅድመ – ክፍያ ገንዘብ (Advance payment) ከቀጣሪው ስለሚለቀቅ፣ተከራይ ተብሎ የተጠቀሰው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መንግሥታዊ አካል በመሆኑ ውሉ ከሕግ ውጭ ግለሰብን ለመጥቀም ታሳቢ ተደርጎ ይጻፋል ተብሎ ስለማይገመት፣ከልማት ገቢዎች ካሕናትን መደጎም ከአራዳ ጊዮርጊስ በፊት በቅ/ራጉኤልና በመካኒሳ ሚካኤል በመሳሰሉ አድባራትም ስለሚሰራበት፣የግንባታውን ሂደት የሚቆጣጠረው አማካሪ መሐንዲስ ተጠሪነቱ ለደብሩ ሰበካ ጉባኤ እንደመሆኑ መጠን ስለጉዳዩ ማብራሪያ የመስጠት ኃላፊነትና ሥልጣን ያለው እሱው በመሆኑ ጋዜጣው ርእስ ለማጮህ ከመንደርደር ከሚመለከታቸው ሰ/ጉባኤ አባላትና የአ/አ/ሀ/ስብከት ማብራሪያ መጠየቅ ይገባው የነበረ በመሆኑ፣ቁጥጥሩ በቂ ማስረጃ ካለው አሁንም ቢሆን ሁሉም የሕግ በሮች ክፍት ስለሆኑ፣አዲስ ዓድማስ ከነጻ ጋዜጣነቱ ይልቅ ራሱን በዳኝነት መንበር አስቀምጦ “አማሳኝ” ገለመሌ እያለ እነ ሃይሌ አብርሃን ማሳደዱን ላለፉት 12 ወራት እንደ መደበኛ ስራው ስለያዘው፣ሰ/ት/ቤትን ከአለቆችና ከቅ/ፓትርያርኩ በማቃቃር አባትን ከልጅ ለማለያየት የምትደረገዋን ድኩም አሻጥር ስለምናውቃት፣ወዘተ፣ወዘተ፣ወዘተ…..ሺህ ጋዜጣና ብሎግ ወሬ ቢያነፍስና ቢያናፍስ አይሞቅ አይበርደን፡፡
  ጎበዝ የሆነና በማዕተቡ የተማመነ ፊትለፊት ይምጣ!!አድባራትን ባማሩ ህንጻዎችና ልማቶች የዋጀውን ሰው ልቀቁት!!ይስራበት!!ብትችሉ ልክ እንደ በጎ አድራጊዎቹ ተባበሩት፡፡ካልቻላችሁ ዝም በሉ፡፡አታደናቅፉት፡፡እሱ ይችላል!!አሳይቶናል!!ማኅበራችንን ለምን አነሳ በላችሁ በቁጩ አታንቆጫቁጩ፡፡እናንተ የኤ ቢ ሲዲ ግርፍ ዲያቆናት የምትፈልጉት እንደፈለጋችሁ የምትጭኑትና በቡራኬ ብቻ የተወሰነ የቦዘ አሻንጉሊት አለቃ ነው፡፡ኃይሌ አብርሃ ደግሞ እንደሱ አይነት አለቃ አይደለም፡፡አይሰማችሁም!!ቡድንተኞችና ቂመኞች ናችሁና ገና ከዚህ የበለጠ እንደምታሳድዱትና በሕይወቱ እስከመምጣት ድረስ እንደምትሄዱ አምና ታሕሳስ 9 ቀን 2006 ዓ.ም ባደረግነው የጠ/ቤ/ክሕነት ምክክር ወቅት ገልጾልናል፡፡ስለዚህ እሱ ይሄ አይገርመውም፡፡እኛም እንደዛው፡፡አላለሙም ትላላችሁ፣ሲለማ ተቋራጩንና አማካሪውን ጭምር ታሳድዳላችሁ፣ሲከራይ የእኛ ደጋፊ ያልሆነ ሰው ለምን አከራይቶና ተከራይቶ ትላላችሁ፡፡የእናንተ ህንጻ በየትኛው ቃለዓዋዲ መነሻነት እንደተሰራና እንደተከራየ ከነገቢ መጠኑ ሳይታወቅ ስለ አራዳ ለማውራት የሞራል ብቃት የላችሁም፡፡
  አንተ እና አንቱ እያልኩ መቀላቀሌ ስለምወደው ነው፡፡በርታልኝ ሃይሌ!!የአጥቢያህን ምዕመን ስማ እነዚህን ግን ተዋቸው፡፡ጥላቻን ሃይማኖቱ ካደረገ ጋር ምን አደረቀህ!!ተዋቸው!!

 5. Anonymous March 3, 2015 at 1:39 pm Reply

  ahun Yemetachehut asetdadrun lmwekse becha ayedelem Yebetekeresetiyan lemate endayekahede new.bewenet betsafachehut neger eregetegnoche nachehu? harawoche esekezare senanbachehu koyetenal.bebezu negeroche senedeset neber. melake menekeratene agegnen belachehu baletchebete mereja ke Addis admas gar aberachehu ye KIduse Giworgisen selamna edegte tenqefalachu belen anegmetem. manegnaweme sew weyem tquam yemiflegwene mereja hedo matarate yichelal. 1 sera sisera 50 enekafat masekemet agebabe ayedelem./

 6. ze genete tsige March 9, 2015 at 10:00 am Reply

  እንደ መግቢያ
  የብሎጋችሁን ስያሜና ስእል ዐይተን ለቤተ ክርስቲያን የምትቖሙ መስሎን እንከተላችሁ(follow & like እናደርጋችሁ) ነበር፡፡ ነገር ግን እያደር እንደጠበቅናችሁ አልሆናችሁም፡፡ በመሆኑም አውቃችሁም ሆነ በስህተት ከገባችሁበት የአፍራሽነት ሳጥን ውጡና ገንቢ ሚና ላይ ተሰማሩ ለማለት በሌላው አቅጣጫ ላሉትም አስተያየት ቢጤ ለመስጠት ይህችን ጦማር ለመጻፍ ተነሳሳሑ ፤
  እንደማታወጡልኝ በመጠራጠር ልተወው ባስብም ቢያንስ አዘጋጁ ያነባታል ብዮ በስስ ብዜት (softcopy) ለእናንተ ፤ በጠንካራ ብዜት (hardcopy) ለገነተ ጽጌ ሰዎች ጽሑፌን ላደርሳችሁ ወደድኩ፡፡
  ለመሆኑ ሐራዎቹ (ጭፍሮቹ) ፡- ጭፍራነታችሁ ለማን ነው ? የብዙዎቻችን (ቢያንስ እኔና በእኔ አካባቢ ያሉ አንባቢዎቻችሁ) ጭፍራነታችሁ ለማኅበር እና ለአንድ አካባቢ ሰው ነው ወይስ ለተዋህዶ ? ማለት ከጀመርን ሰንብተናል፡፡ ይህን ያስባለኝ ጡመራችሁ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚደግፉና የሚፈሩ ሁሉ የብዕራችሁ ብጹዓን ናቸው፡፡ ማኅበሩን በምክንያትም ሆነ በአጋጣሚ የሚያነሱ ደግሞ ያለ ምሕረት በብእር ቢላዋ ይዘለዘላሉ፡፡ ለሞራል ኪሳራና ለሃሜት እንዲጋለጡ ይደረጋል፡፡ ለምሳሌ፡- አባ ቀሌምንጦስ ካድሬ የተባሉት ከማኅበሩ አቋም በተጻራሪ ሲቆሙ ነው፡፡ የእናንተን አጀንዳ ሲፈጽሙ ደግሞ ብጽእ አባታችን ይባላሉ፡፡ ፓትርያርክ ማቲያስ ቢሮአቸውን የማ.ቅ. ቅርንጫፍ ሲያደርጉ ቅዱስ ናቸው ፣ በማኅበሩ መሪዎች ውሸትና ግብዝነት ሲማረሩ ለምታውቁላቸው የንጽሕና ሕይወት ሳትጠነቀቁ ትሳደባላችሁ፡፡ በሃይማኖትና በሙስና ያለው ዘገባም ይሄው ነው፡፡ ከዚህ የሚብሰውና የማን ጭፍራ የሚያስብለን ደግሞ አቅም ያላቸውና የአንድ አካባቢ ተወላጆች ላይ ማተኮራችሁ ነው፡፡ ለመሆኑ በአዲስ አባባ ካሉት አድባራትና ገዳማት ውስጥ ግልጽ ዝርፊያ የሚካሄድባቸውንና በብዙ ሰዎች አስተያየት “የእናንተ” ሰፈር ተወላጆች የሚዘርፉዋቸውን ለምን አታነሱም ? ይህንን ጥያቄዬን እኔው በእርግጠኛነት መመለስ ባይኖርብኝም በብዙዎች ስሜት ግን መረጃ አጥሮአችሁ ሳይሆን የዓላማ ጉዳይ ሆኖባችሁ እንደሆነ ተገምታችኋል፡፡ ይሄ ደግሞ ለብሔር ፖለቲካ እንኳን ስለማይመጥን ፖለቲከኞቹም እየተውት ያለ አካሄድ ነው፡፡
  ወደ ወቅታዊውና ዋናው ጉዳይ ወደ መልአከ መንክራት ኃይሌ ጉዳይ ልመለስ፡-
  1. መልአከ መንክራት ኃይሌን እስካሁን በምትከሱዋቸው ልክ ፍርድ ቤት ያለቋማችኋቸው አዝናችሁ ሳይሆን ለፍርድ ቤት የሚበቃ መረጃ ስለሌላችሁ ነው፡፡ አንዳንዴ ወንጀለኛም መረጃ ያጠፋልና እንዲያ ነው ብለን በጭፍን ብንገምት እንኩዋን ፤ መረጃ ሳይኖር ፣ ተደብቆ ፣ ስም እያጠፉ ፤ መጻፍ የተዋህዶ ሐራነት የሚጠይቀውን መንፈሳዊ ማንነት አያሙዋላም ፤ በተቃራኒው በማኅበሩና በሌሎች ላይ መረጃ እና የብዙዎች ቅሬታ እያለም ባልተሟላ መረጃ ሰበብ ትታችሁታል፡፡ ታዲያ ለምን እነ ኃይሌ ላይ ብቻ ቀሰራችሁ፡፡ መልሱን ለእናንተ ልተወው ……….
  2. እኒህ አባት ያላቸውን መልካም ነገሮችስ ለምን በክፉው መሸፈን ፈለጋችሁ፡፡ በእርሳቸው አስተዳደር እና አስተባባሪነት ከኩርፉ ጊዮርጊስ እስከ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲናት የታነጹት ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት ፣ የንግድና የአገልግሎት ሕንጻዎች እና ሌሎች የልማት ሥራዎች በግልጽ የሚታዩ ናቸው፡፡ በስብከት በመዝሙር እና በማኅሌት ፍቅራቸ ው በአገልጋዮቹ ዘንድ የሚታወቀውን የመልአከ መንክራት ኃይሌን ስብእናስ አላያችሁትም ወይስ እናንተ የቁጥጥር ሰነድ ስትደልዙ ለአገልግሎት ጊዜ አልነበራችሁም፡፡ ከብሎጋችሁ አንድ ነገር ላስታውስ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ሲነሳ ድክመት ቢኖርበትም ይህንን እና ያንን ሰርቷል ስትሉን በጸጋ ተቀብለናል፡፡ ታዲያ ለእነ ኀይሌስ ይህንን ዐይናችሁ እንዳያይ ብዕራችሁም እንዳይጽፍ ምን ያዘው፡፡ መልሱን አሁንም ከእናንተ እጠብቃለሁ፡፡
  መልአከ መንክራት እና መሰል የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የወደቀባችሁ አባቶችና ወንድሞች በሙሉ ፡-
  1. ከምትታሙበት እየተጠነቀቃችሁ ከመንፈሳዊው አገልግሎትና ከልማቱ እያበዛቹ በርቱልን ነገ ታሪክና እግዚአብሔር ይመልሳሉ ፣ በአደባባይ የማያወሩ ብዙዎች እንዳሉና፡- በጸሎት በአርምሞና በስሜት እንደሚደግፉዋችሁ አትርሱ፡፡
  2. የመሪ ብቃት የሚታየው በእሳት ሲፈተን ነው፡፡ እነዚህን አጋጣሚዎች የአበው እና እማትን የእምነት ፣ የትእግስትና ጽናት ሕይወትን ለማሳየትና የተሻለ ስራ ለመስራት ተጠቀሙበት ስል በልጅነት አቅሜ እመክርለሁ፡፡
  3. በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት ፣ በምክንያትና በጥናት የተመሰረቱ፡- ሃሳቦች ፣ ድርጊቶችና ውይይቶችን አዘጋጁልን ፤ እነዚህን ዝግጅቶችም በጽሑፍ በጉባዔና በዘመኑ ትሩፋቶች አዳርሱን፡፡ የማኅበሩን መንፈሳዊ ዓላማ ትተው ስህተቱን በስሜት የሚደግፉትን ነጻ የምታወጡዋቸው በዚህ መንገድ ነው፡፡
  በመጨረሻ ፡- ሐራዎችም ሆናችሁ በአስተያየትና ትችት (comment) የምትሳተፉ ፣ በደረቅና እርጥብ ዝርፊያ የተሰማራቹሁትንም ሆነ ራሴኑ የነቢዩን ቃለ ትንቢት በማስታወስ ላጠቃልል፡-`መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፥ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!` ኢሳይ.10፡1-2

 7. Anonymous March 14, 2015 at 2:13 pm Reply

  ወይ እናንተ የደብሩ ሰላም ልማት ፍቅርና አንድነት በዚህ የሚደናቀፍ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችሁዋል እኛ እንሰራለን፡፡ እናንተ አውሩ ከዓመት ወይም ከሁለት ዓመት በሁዋላ በውጤት እንገናኛለን፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: