የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ በፓትርያርኩ መታገዱን ተቃወሙ

 • አማሳኞች ባለመገሠጻቸው ‹‹እነ እገሌ ምን ተደረጉ? እኛስ ምን እንኾናለን?›› በሚል በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ላይ እየዘበቱና ሀገረ ስብከቱን ለማወክ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
 • በሃይማኖት ሕጸጽ ስለሚጠረጠሩ ሰባክያንና ሥርዐት አልባ ዘማርያን የሚቀርቡ ማስረጃዎች ውሳኔ ሳያገኙ ምደባና ስምሪት መሰጠቱ ሰንበት ት/ቤቶችን እያዳከመ ነው፡፡
 • በአማሳኝ አለቆችና በሙዳይ ምጽዋት ገልባጮች ግርግር የውኃ ሽታ የኾነው የሀ/ስብከቱ ተቋማዊ ለውጥ ጥናት ለሰንበት ት/ቤቶች በሚያመች አኳኋን የሚተገበርበት ኹኔታ እንዲጤን ተጠይቋል፡፡
 • የአ/አ ሀ/ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ድረ ገጽ በቅርቡ ይፋ ይኾናል፤ ሊቀ መንበሩ ‹‹መንግሥት ከኛ ጋራ ነው›› በሚሉ ግለሰቦች ዛቻና ማስፈራራት እየተደረገባቸው ነው፡፡

*        *       *

 • ‹‹አባ እስጢፋኖስን ከአዲስ አበባ ያስነሣነው እኛ እንጂ ሲኖዶሱ አይደለም የሚሉ አማሳኞች በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት ባለመገሠጻቸው አኹንም ተከታዮቻቸውን ይዘው ብፁዕነትዎን ለማስነሣት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ እኛ እናስቀይራችኋለን፤ ዕድገት እናሰጣችኋለን፤ እናሾማችኋለን እያሉም ለሠራተኞች ይናገራሉ፤ የማይደግፏቸውን በገንዘብ ኃይል ከቦታቸው እንዲፈናቀሉና ያለፈቃዳቸው እንዲዛወሩ ያደርጓቸዋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ በእጃችን ናቸው የምንፈልገውን እናስፈጽማለን ስለሚሉ የሲኖዶሱ ልዕልና ጠፍቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ በግለሰቦች የምትመራ አስመስለዋታል፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ሰርቀው ባካበቱት ሀብት መልሰው እያወኳት ይገኛሉ፡፡ ይህም የወጣቱን የአገልግሎት ተነሣሽነት እየተጎዳ ነው፡፡›› /የካ፣ አራዳና ጉለሌ ክ/ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት/
 • ‹‹አማሳኝ አለቆችና አንዳንድ የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች ከመዋቅር ውጭ የአካባቢ ወጣቶችን እያደራጁ ከሰንበት ት/ቤቶች ጋራ በማጋጨትና በፖሊቲካ እየወነጀሉ ሕገ ወጥ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅና የኑፋቄ ዓላማቸውን ለማራመድ ይሠራሉ፤ በዐውደ ምሕረት ፀረ – ሰንበት ት/ቤት ቅስቀሳ ያካሒዳሉ፤ ሰንበት ት/ቤቶችን የሚደግፉ ካህናትን ያሸማቅቃሉ፤ ያዘዋውራሉ፤ ክህነት ያላቸው የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች ከመቅደስ ያባርራሉ፤ መምህራን የሚጋበዙት በዓላማና በጥቅም ትስስር ነው፤ ሕገ ወጥ አሠራራቸውን የሚቃወሙ በሰበካ ጉባኤያት የሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮችን ያግዳሉ፤ ለሰንበት ት/ቤቶች የሥራ ማስኬጃ በጀት አይመድቡም፤ ገቢ እንዳያገኙም ይከላከላሉ፤ ባዶ ይዞታዎችን ለመማርያ አዳራሽ ከመፍቀድ ይልቅ ለጋራዥ ማከራየትን ይመርጣሉ፡፡›› /ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት/
 • ‹‹እንደ ግርማ በቀለና አሸናፊ መኰንን ካሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወገዙ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ዓላውያን ጋራ የተሳሰሩና በሃይማኖት ሕጸጽ የሚጠረጠሩ ሕገ ወጥ ሰባክያንና ዘማርያን ግለሰቦችን ከአባልነት አግደን ርምጃውን ለብፁዕነትዎ ለማሳወቅ ተገደናል፡፡ በአንዳንድ ሓላፊዎች ግን ‹ተዉአቸው፤ ልጆቻችን ናቸው፤ አትንኳቸው› እየተባለ በሌሎች አጥቢያዎች ኑፋቄአቸውን እያስፋፉ ነው፤ ቤተ ክርስቲያናችን ዐውደ ምሕረትዋን አታዝበትም፡፡ የሰንበት ት/ቤቶች አንዱ ዓላማ አፅራረ ቤተ ክርስቲያንን መከላከል እስከኾነ ድረስ ለምንድን ነው ድብቅ ዓላማቸውን እንዲያራምዱና ቤተ ክርስቲያናችንን እንዲበጠብጡ የሚፈቀድላቸው? የምናቀርበው ማስረጃስ ስለምን ወቅታዊና ተገቢ ውሳኔ አያገኝም?›› /ቂርቆስ ልደታና አዲስ ከተማ ክፍላተ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት/
 • ‹‹ቤተ ክርስቲያን የሀብታምና የድኻ ተብላ የምትከፈልበት ዘመን መጥቷል፤ ከአለቆች ጋራ የተሳሰሩ ግለሰቦች በቦሌ መድኃኔዓለም፣ በገርጂ ጊዮርጊስና በሰሚት መድኃኔዓለም የባለጸጋ ልጆችን ከሌሎች አባላት ለይተው ብር እያስከፈሉ፣ የተለየ መጽሐፍና ያማረ ቦታ አዘጋጅተው ሰንበት ት/ቤቱ የማይቆጣጠረው ትምህርት ያስተምሯቸዋል፡፡ አካሔዱ እንዲመረመር ባመለከትነው መሠረት አጥኚ ቡድን በሀገረ ስብከቱ ተልኮ እግድ ተላልፎበታል፡፡ ይኹንና አስተዳዳሪው ማን እንደሚያስፈጽመው እናያለን በሚል የሀገረ ስብከቱን መመሪያ ለማስፈጸም ፈቃደኛ አልኾኑም፤ ይልቁንም በፌዴራል አስለቅምሃለኹ እያሉ የሰንበት ት/ቤት አመራሮች እስርና እንግልት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ነገ ደግሞ በቅዳሴው ልንለይ ነው ወይ?›› /የቦሌ ክ/ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት/

*        *        *

 • ‹‹የበዓል መዝሙር ከማቅረብ ውጭ እኛም እናንተም አልሠራንም፤ ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው እያለቀሱ የሚናገሩ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን በማየቴ ተስፋዬ ለምልሟል፤ አኹንም በየመድረኩ በሚቆሙ ተጠርጣሪ ሰባክያንና ዘማርያን ላይ ክትትሉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፤ እንዲህ አሉ ብላችኹ አትንገሩን፤ ያሉትን በማስረጃ አጠናክራችኹ አቅርቡልን፡፡››

/መ/ር ይቅርባይ እንዳለ፤ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ሓላፊ/

 • ‹‹የአማሳኞቹን እንቅስቃሴ ዐውቃለኹ፤ ጥቅማቸው እንዳይዘጋባቸው በሰው ሕይወት ከመምጣት ወደኋላ አይሉም፤ በእነርሱ ላይ የምናየው አባቶቻችን ያልነገሩንን ያላስተማሩንን ነገር ነው፤ ከአባቶቻችን የተማርነው በንጽሕና በቅድስና ኾኖ በማገልገል የሚገኘውን በረከት ነው፤ ከየአጥቢያው ስለተነሡት ችግሮችም መረጃዎች አሉን፤ ቤተ ክርስቲያን ሙስናን በመዋጋት ሓላፊነቷን ከመወጣት ወደኋላ አትልም፤ እኔም የመጣኹት ይህን ለማስፈጸም ነው፡፡ መሾምና መሻር የእናንተ ድርሻ ባይኾንም ስለ ቤተ ክርስቲያን ግን አያገባችኹም አይባልም፤ እንዲያውም የሰንበት ተማሪዎች ሐሳብ መጋቢዎች መኾን አለባችኹ፡፡ የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ እንደሚገባው አልሠራምና የድርሻውን ይወጣ፤ ሀገረ ስብከቱም ራሱን ይፈትሽ፡፡›

/ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፤ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊ/

*        *        *

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፬ ቁጥር ፯፻፹፰፤ ቅዳሜ የካቲት ፲፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

Sunday School student applausing his holiness anti-corruption effortየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅ/ሲኖዶስ፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያንን አዋርደዋል፤ አባቶችን ዘልፈዋል›› ያላቸው አማሳኝ አለቆች ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው ያሳለፈው ውሳኔ ‹‹ሕገ መንግሥቱንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር ነው›› በሚል በፓትርያርኩ ትእዛዝ መታገዱ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት ሰንበት ት/ቤቶች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፡፡

የአ/አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ባለፈው ሳምንት እሑድ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት አዳራሽ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባካሔደው የግማሽ ቀን ውይይት፣ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባው አማሳኝ አለቆች ተግሣጽና ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ያሳለፈው ውሳኔ ባለመፈጸሙ ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፋ ኹኔታ እየታወከችና እየተመዘበረች እንደምትገኝ በተሳታፊዎች ተገልጧል፡፡

ፓትርያርኩ ‹‹አፈጻጸሙ እንዲቆይ›› ያሳለፉትን እገዳ ተከትሎ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውሳኔውን ለማስፈጸም ባለመቻሉ፣ አማሳኝ አለቆች እንቅስቃሴያቸውን ለሚቃወሙ አገልጋዮች ስም እያወጡ በገንዘብ ኃይል ከሥራቸው እንዲፈናቀሉና ያለፈቃዳቸው እንዲዘዋወሩ፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የድርሻቸውን እንዳይወጡ ከመዋቅር ውጭ ባደራጇቸው አካላት እየከፋፈሉና ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ፣ ግንቦት ሰባት›› በሚል በፖለቲከኛነት እየወነጀሉ ከአገልግሎት በማገድ ለእስርና እንግልት እየዳረጓቸው እንደኾነ ተጠቅሷል፡፡

‹‹ፓትርያርኩ በእጃችን ናቸው፤ የምንፈልገውን እናስፈጽማለን›› በማለት ዕድገትና ሹመት ለማሰጠት እንደማይሳነው በመግለጽ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ እንዳለም ተጠቅሷል፡፡ የቡድኑ እንቅስቃሴ በዋናነት ‹‹ሊያሠሩን አልቻሉም›› ያላቸውን የወቅቱን የሀገረ ስብከቱን ረዳት ሊቀ ጳጳስ የሚወነጅል ሲኾን ከመጪው የግንቦት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በፊት ከሓላፊነታቸው የሚነሡበትን ተቃውሞ የማጠናከር ዓላማ እንዳለው ተመልክቷል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በአማሳኝ አለቆች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አለመፈጸሙ ‹‹እነ እገሌ ምን ኾኑ? እኛስ ምን እንኾናለን?›› በሚል እየተዘበተበትና ‹‹በእግሩ የመጣ በመኪና ይሔዳል›› በሚልም ለከፋ ሙስና በር መክፈቱ ተገልጧል፡፡

ለሀገረ ስብከቱ የታቀደው የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ በ‹‹አማሳኝ አለቆችና ቲፎዞዎቻቸው የውኃ ሽታ›› መኾኑን የገለጹት ተሳታፊዎቹ፣ ያለተጠያቂነት የሚፈጽሙት ቤተ ክርስቲያኒቱን የመለያየትና የመመዝበር ድርጊት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን የአገልግሎት ተነሣሽነት እየጎዳ ከመኾኑም በላይ ‹‹የቅዱስ ሲኖዶሱ ልዕልና ጠፍቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ በግለሰቦቹ እጅ ላይ ያለች አስመስሏታል›› ብለዋል፤ ‹‹ወዳልተፈለገ ነገርስ አያመራም ወይ?›› ሲሉም ውይይቱን ለሚመሩት በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስና የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሊቀ መንበር ቀሲስ ኄኖክ ዐሥራት ጥያቄአቸውን አቅርበዋል፡፡

‹‹በሃይማኖት ሕጸጽ የሚጠረጠሩ ሰባክያን ተመድበውብናል›› ያሉ የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስና የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ አድባራት ሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች በበኩላቸው፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዐውደ ምሕረት በዝማሬና በስብከተ ወንጌል የመሳተፍ መብታቸው አስተምህሮዋን በሚፃረሩ የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎችና ሕገ ወጥ ሰባክያን ስምሪት መታወኩን በምሬት ገልጸዋል፤ በሰሚት መድኃኔዓለም በግለሰቦች ፍላጎት የባለጸጋ ልጆች ከሌሎች አባላት ተለይተውና ለብቻ ተሰብስበው ሰንበት ት/ቤቱ ሊቆጣጠረው በማይችል መልኩ የሚማሩበትና ቤተ ክርስቲያኒቱን ‹‹የሀብታምና የድኃ›› ብሎ የመክፈል አሠራር መስተዋሉን አስረድተዋል፤ የሰንበት ት/ቤቱ አመራር ይህ ዐይነቱ አካሔድ እንዲታገድ በጠየቀው መሠረት በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የተላለፈው መመሪያ በደብሩ አስተዳደር ተቀባይነት ባለማግኘቱ የአመራር አባላቱ እስከ መታሰር መድረሳቸው በእንባ ተገልጧል፡፡

በውይይት መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ትምህርትና ቃለ ምዕዳን የሰጡት በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ ጉበኞች ፈጽሞ እንደማይተኙና እያደረጉ ስላሉት እንቅስቃሴ መረጃው እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ እንቅስቃሴአቸው የተደራጀና በከፍተኛ ገንዘብ የተደገፈ እንደኾነ ሊቀ ጳጳሱ ገልጸው፣ ‹‹ጥቅማቸው እንዳይዘጋ በሰው ሕይወትም ከመምጣት ወደኋላ አይሉም›› ብለዋል፡፡ ይኹንና ቤተ ክርስቲያን ከፓትርያርኩ አንሥቶ ሙስናን ለመዋጋት ወደኋላ እንደማትል ለተሳታፊዎች አረጋግጠዋል፡፡

his grace abune Kelemntos‹መሾምና መሻር የእናንተ ድርሻ ባይኾንም ስለ ቤተ ክርስቲያን ግን አይመለከታችኹም አይባልም፤ እንዲያውም የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች የአስተዳደሩ ሐሳብ መጋቢዎች ናቸው፤›› ያሉት ሊቀ ጳጳሱ፣ ወጣቱ በትጋትና በብልሃት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑን አጥር ኾኖ ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡ ከአየጥቢያው በተነሡት ችግሮች ዙሪያም የሚገባውን ያኽል አልሠራም ካሉት ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አንሥቶ ኹሉም ራሱን እንዲፈትሽና የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡ ውይይቱ ቀጣይነት እንደሚኖረው አቡነ ቀሌምንጦስ አስታውቀው፣ አማሳኞች የወጣቱን ጥያቄ ከመንገድ በማውጣት ከግንቦቱ ምርጫ ጋራ በተያያዘ ትንኮሳ ከመፍጠር ስለማይመለሱ በዜግነቱም በመንፈሳዊነቱም ጥያቄውን መዋቅር ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ በማቅረብ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ መክረዋል፡፡

ጠቅላላ ቁጥራቸው ከ760 በላይ የኾኑ የ160 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች አመራሮች፣ የሀገረ ስብከቱና የሰባቱም ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ሓላፊዎች፣ የሀገረ ስብከቱና የሰባቱም ክፍላተ ከተማ የሰንበት ት/ቤት አንድነት አመራሮች እንዲኹም ጥሪ የተደረገላቸው የአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተወካዮች በተገኙበት በዚኹ የውይይት መርሐ ግብር÷ ‹‹የወጣትነትን ሕይወት ለቤተ ክርስቲያን መቀደስ›› በሚል ርእስ በሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች ክፍል ሓላፊ መ/ር ደምስ አየለ የውይይት መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል፡፡ በጸደቀው የአምስት ዓመቱ የሰንበት ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ አንድነት ስትራተጂ ማህቀፍ የመንፈቅ ዓመቱ ዕቅድ ክንውን ከየክፍላተ ከተሞቹ ተጠቃለው በመጡ ሪፖርቶች መነሻነት ተገምግሟል፡፡

ሰንበት ት/ቤቶች ወጥ መተዳደርያ ደንብና ተመሳሳይ ሥርዐተ ትምህርት ይኖራቸው ዘንድ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት፣ 11‚200 አባላትን በጥራት ለማፍራት የተጣለው ግብ አፈጻጸም፣ ከመንፈሳውያን ማኅበራት ጋራ ግንኙነቶችን ለማሻሻል የተደረጉ ጥረቶች በግምገማው ተዳስሰዋል፡፡ በአጥቢያ አስተዳደርና በሰንበት ት/ቤቶች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት፣ በሥልጠናና የተለያዩ እገዛዎችን በመስጠት ለመፍታት የአንድነቱ አመራር የበኩሉን ሚና መጫወቱ ተጠቅሷል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ድረ ገጽ ግንባታ ተጠናቅቆ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲኾን ሰንበት ተማሪውም በሃይማኖት ሕጸጽ በሚጠረጠሩ ሰባክያንና ሥርዐት አልባ ዘማርያን ዙሪያ ተጨባጭ ማስረጃዎችን በቅዱስ ሲኖዶስ ለተቋቋመው አጣሪ አካል እንዲያቀርብ ጥሪ ተላልፏል፡፡

በተያያዘ ዜና÷ የውይይት መርሐ ግብሩን እንደ ስጋት ከሚመለከቱ አካላት እንደኾነ የተጠረጠረ ዛቻና ማስፈራሪያ በሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤት አንድነት አመራሮች ላይ እየተፈጸመ እንዳለ ተጠቁሟል፡፡ በዕለቱ ውይይቱን ሲመሩ የነበሩት የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሊቀ መንበር ቀሲስ ኄኖክ ዐሥራት ዛቻና ማስፈራሪያው ከደረሰባቸው አመራሮች አንዱ እንደኾኑ የጠቆሙት ምንጮቹ፣ ‹‹መንግሥት ከኛ ጋራ ነው፤ ቀባሪ ታጣለኽ፤ አንተን ለማጥፋት ጥቂት ገንዘብ ይበቃናል›› የሚሉ ግለሰቦች ለተከታታይ ቀናት በስልክ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳደረሱባቸው ገልጸዋል፡፡

Advertisements

19 thoughts on “የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ በፓትርያርኩ መታገዱን ተቃወሙ

 1. ቀፀላወርቅ ዓድማሱ February 23, 2015 at 7:37 am Reply

  ክስ ከማስረጃ ጋር ሲሆን ጥሩ ነው፡፡ራስን መመልከተም ሲታከልበት ደግሞ ይበልጥ ጥሩ ነው፡፡በዚህ ሪፖርት ላይ እንደማየው ሰንበት ት/ቤቶች በራሳቸው ያለባቸውን ውስጣዊ ችግር ለመዳሰስ እምብዛም አልተሞከረም፡፡እኔ እስከማውቀው ግን በቃለዓዋዲው ከተቀመጠው 30 አመት በላይ 40 አመት የደፈኑ ሰዎች ለረጅም ጊዜ አመራሩን የሙጥኝ ማለት፣ለጊዜው ልዘረዝራቸው የማልፈልጋቸው የሥነምግባር ችግሮች፣አድመኝነት፣ትዕቢት፣ራስን በንባብና በመንፈሳዊ ሕይወት ከማነጽ ይልቅ ይሄን ያህል አመት አገለገልኩ እያሉ በባዶ መኮፈስ፣ለካሕናት የሚገባውን አክብሮት አለመስጠት፣እኛ ያልነው ካልሆነ ማለት፣የሱቅ ኦዲትን አለማሳወቅ፣የሰንበት ት/ቤት አመራር በተወሰኑ ሰዎች በሞኖፖል መያዝ፣በካሕናት አለመግባባት ውስጥ አንዱን ግሩፕ ወግኖ ከሳሽ መሆን፣ሕዝቡ ከኛ ጋር ነው እያሉ ማስፈራራት፣ተተኪ አለማፍራት፣ጠባቂነት፣በአሉባልታ መነዳት፣ለሌላ አካል ተቀጽላ መሆን፣አልፎ አልፎ ቢሆንም በሙስና እና ዘረኝነት መሳተፍ፣የትብብር መንፈስ ከማዳበር ይልቅ ሁሉንም እኔ አውቃለሁ የሚል ገፊነት፣እርምትና ተግሳጽ ለመቀበል ፍጹም ፈቃደኝነት ማጣት፣ለራስ የተጋነነ ግምት መስጠት፣አለመግባባትን በተቻለ መጠን በውስጥ ለመፈታት ከመጣር ይልቅ ወደ ምዕመንና ወደ ሚዲያ ከዚያም ሀገረስብከት ይዞ መሮጥ፣ራሰን ለሚዲያ ተጽእኖ ማጋለጥ፣ተጠሪነትን ከአጥቢያ ደብር ይልቅ ለሌላ አካል ማድረግ፣በቂ መረጃ ሳይኖር አቋም መያዝ፣ያለማስረጃ መወንጀል፣ራስን ደሴት ማድረግ፣ለበላይ አካላት ውሳኔ ተገዥ አለመሆን፣ቃለዓዋዲውን ጠብቆ አለመጓዝ የመሳሰሉ ችግሮች ቢነሱና ውይይት ቢደረግባቸው ጥሩ ነው፡፡ራስን ሳይመለከቱ ሁልጊዜ ጣትን በመቀሰር ብቻ ችግር አይፈታም፡፡በስብሰባው የተነሱትንና መኖራቸው የማይካደውን የቤተክርስቲያን ወቅታዊ ችግሮች ለመፍታት ቅንነት ካለን እነዚህን ህጸጾች ከራሳችን ነቅሰን እንነሳ፡፡እኛም የችግሩ አካል ነን እንበል፡፡ሁላችንም በድለናል፡፡ማለባበስ ይቅር፡፡

  • በረከት February 24, 2015 at 3:11 pm Reply

   ቀፀላወርቅ ዓድማሱ – የተሰኙ አንድ አስተያየት ሰጪ ኮሶን በሙዝ ጠቅልሎ አይነት አስተያየት መስጠታቸው ይገርማል፡፡ ግን እስቲ አንድ ጥያቄ ይመልሱልኝ የግብጹ ቅዱስ አባትና ምዕመኖቻቸውን በፍቅር፣ በወንጌል፣ በፍጹም የጸሎት ህይወት ለብዙ ዘመናት ሲመሩ የነበሩት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ እኮ እስከ እረፍት ቀናቸው በሰ/ት/ቤት በመገኘት ያስተምሩ ነበር፡፡ መጀመሪያም መነሻቸውም እኮ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው፡፡ ታዲያ እኚህ ቅዱስ አባት እድሜ ለምን አልገደባቸውም? አስተያየት ሰጪው እኔ እስከማውቀው ካሉ ይሄንንስ አያውቁም፡፡ አይመስለኝም ኮሶን በሙዝ ጠቅልሎ ያልኩበት ምክንያት አንዱ ይህ ነው፡፡

   ሌላው ቀጸላወርቅ እኔ እስከማውቀው ግን በማለት ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት ዘሎ 40 ዓመት የሞላቸው በሰ/ት/ቤት የሙጥይ ብለዋል አሉ፡፡ ለመሆኑ በአስተዳደሯም ይሁን በአገልጋዮቿ ከእኛ ሲኖዶስ እና የአገልግሎት መዋቅር ተሽላ፤ በጅሀዲስቶች መሀል ተቀምጣ ምዕመኖቿን በታላቅ ፍቅርና አንድነት የምታገለግሎው የግብጻ ቅድስት ቤተክርስቲያን ማንኛውም ህጻን ሆነ ወጣት፣ አዛውንት ሆነ ጳጳስ አገልጋይና ምዕመን በዕለተ ሰንበት በሰ/ት/ቤት ማገልገል፣ ገብቶ መማር እንዳለበት ህግ አውጥታ እየተገበረች ያለችው፡፡ ለማንኛውም የቤተክርስቲያን ሹመት መነሻ የሚሆነው በሰ/ት/ቤት አልፎ በወጣትነቱ አርአያ ሊሆን የሚችል ተግባር የፈጸመ ኢጵስ ቆጶስ፣ ካህን፣ ዲያቆን፣ ምዕመን ብቻ ነው ለቀጣይ የቤተክርስቲያኒቱ ዕድገትና አገልግሎት የሚታጭ፣ የሚሾም፡፡ ሌሎችም አሃት አብያተክርስቲያናት በዚህ ዘርፍ ብዙ የላቀ ውጤት አስመዝግበው ይገኛል፡፡

   እስቲ ደግሞ የእኛኑ የቅርብ አባቶች ህይወት እናንሳ ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ለምን ከወጣቱ ትውልድ ጋር በህይወት ዘመናቸው እጅና ጓንት ሆነው ተጉዘው አለፉ፡፡ አሁንስ በህይወት የሚገኙት የሰሜን ሸዋ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤፍሬም ከህመማቸው ከአልጋ ተነስተው በዕለተ ሰንበት ሰ/ት/ቤት አግዳሚ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው የሚማሩት ሌሎችም ቀደምት ታላላቅ አባቶች አሁንም በዘመናችን ብዙ አባቶች አሉ ነገር ግን አገልግሎታቸው በዘመኑ ባሉ ጥቂት አጥፊዎች ተሸፍኖባቸው ነው እንጂ፡፡ ታዲያ በእኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ግን በሰ/ት/ቤት ጎልማሳ ሆኖ መታየት ልክ እንደ ህጻን ስራ የሚቆጠረው፣ በሰ/ት/ቤት የተማረ ሆኖ ማገልገል ልክ እንደ ማህይም ስራ የሚቆጠረው፡፡ ልክ እንደ ቀበሌ መታወቂያ የእድሜ እርከን ተዘጋጅቶለት ከ30 ከዘለለ ሰ/ት/ቤት መታየት የለበትም ብሎ የሚታወጀው፡፡ ለነገሩ ቃለ አዋዲውም ከወጣ ብዙ ዓመታትን አሳልፏል በአሁኑ ወቅት ያለውን ርዮተ ዓለም ለመሸፍን የሚችል ነገሮች እንደሚጎሉት እሙን ነው፤ መስተካከልም የሚገባው ነው፡፡

   ቤተክርስቲያኒቷ ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ለሆኑት ምዕመናን ልጆቿ የሚገለገሉበት የሚሰባሰቡበት እራሱን የቻለ ልዩ መርሀግብር አውጥታለች ወይ? No Answer! ሆኖም ግን አንድ አገልጋይ ዲያቆን፣ ሰባኪ፣ ካህን፣ ኢጵስ ቆጶስ፣ ጳጳስ ሆኖ ለመሾምና የቅድስት ቤተክርስቲያንን ተልዕኮ ለማሳካት ከተፈለገ በቅድሚያ ሰ/ት/ቤት ገብቶ የተማረ፣ አሁንም በማገልገል ላይ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል፡፡

   አስተያየት ሰጪው እንዳሉት ማለባበስ ይቅር ነውና፤ የወቅቱ አገልግሎት ዓላማው የወጣቱንና የምዕመኑን ህይወት በሥርዓት ቤ/ክ ከማነጽ ይልቅ ስጋዊ ጥቅምና ተልዕኮ ያነገበ ስለሆነ ለቤተክርስቲያኒቱ ተልዕኮ፣ ለወጣቱ ቦታ የለውም፣ ማለባበስ ይቅር ማለት ይህ ነው፡፡ እኔ ከታች አንድ አስተያየት ሰጪ በሰጡት በአብዛኛው ሀሳባቸው እስማማለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡

   • ቀፀላወርቅ ዓድማሱ February 25, 2015 at 8:21 am

    ወንድም በረከት ለገለጻህ አመሰግናለሁ፡፡ኮሶው በሙዝ ይጠቅለልም በማር ይለወስ ዋናው መፈወሱ ነው፡፡ማሻሩ፡፡የዘረዘርኩዋቸው ነገሮች ብዙ ሆነው ሳለ አንዷን ነቅሰህ በግብፅ ማንጸሪያነት ብዙ ስለተናገርክ ትንሽ ልናገር፡፡
    እስከማውቀው በግፅ ቤ/ክ እንደኛ የተራቀቀ ያሬዳዊ ዜማ የለም፡፡ቅኔያትና ትርጓሜ መጻሕፍትም ከእኛ ጋር ሲነጻጸር በጥብቀት መሰጠቱን እጠራጠራለሁ፡፡መዝገብ ቅዳሴያቸውም እንደኛ 14 ሳይሆን 3 ብቻ እንደሆነ አንብቤያለሁ፡፡ስለዚህ ለራሳችን የምንሰጠው ግምት ሊያንስ አይገባም፡፡የሥርዓት፣የትውፊት፣የበለጸገ የሥነ – ጽሑፍና የትርጓሜ – መጻሕፍት ክምችት ያላት የኢኦተቤክ ሃይማኖታዊ ወንድማማችነታችን ባይካድም የግብፅ ተውሶ አያስፈልጋትም፡፡ይሄን ያዝልኝ!!አእምሮህ በሚዲያ ጫጨታ አይታጠብ!!
    የእኛ ሰ/ት/ቤቶች አሁን ያላቸው አደረጃጀትና ሥርዓተ – ትምሕርት ጳጳስ ለማፍራት የሚያስችል ደረጃ ነው ማለት ራስን ማታለል ነው፡፡ከላይ እንዳልኩት የኢኦተቤክ ያላት ያሬዳዊ ዜማ፣ቅኔ፣ትርጓሜ እና ተዛማጅ የአብነት ትምህርቶች በሰንበት ት/ቤቶቻችን በተደራጀ መልኩ እንደማይሰጡ እናውቃለን፡፡እሱን ሀገራዊ እውቀት ሳይዙ ግብጽ-ግብጽ ማለት “አባቱን አያውቅ አያቱን ይናፍቅ” መሆን ነው፡፡አንንጠራራ፡፡ግብፅም ቢሆን እነ አቡነ ሺኖዳና አቡነ ታውድሮስ መነሻቸው ሰ/ት/ቤት ነው ቢባልም በእሱ ብቻ ጳጳስ ሆኑ ማለት አይደለም፡፡ለአመታት በቴዎሎጂ ኮሌጅ ታድመው፣በገዳማት የሚገባውን አገልግሎት ሰጥተው፣በአስተዳደሩ ተፈትነው አልፈው፣አባቶቻቸውን እንደኛ እያጣጣሉ ሳይሆን ውጫዊ ፈተናቸውን ለመቋቋም ሲሉ የውስጥ አስተዳደራዊ ጉዳያቸውን በውስጥ እየፈቱ ነው፡፡በቅዳሜና እሑድ ኮርስ ብቻ እኛ ጳጳስ ካልሆንን የኢኦተቤክ አስተዳደር አይዘምንም ማለት ጥራዝ – ነጠቅነት ነው፡፡ከግብፅ ውጡ!!አታሽቃብጡ!!
    የእድሜን ጉዳይ በሚመለከት በ1991 ዓ.ም ነው ቃለ – ዓዋዲው የጸደቀው፡፡ስለዚህ ያን ያህል ያረጀ ነው ማለት አይቻልምና የ30 አመት የሰ/ተማሪነት ገደቡ ሊጠበቅ ግድ ነው፡፡እንኳን ሰ/ተማሪነት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ዲቁናም የተለምዶ የእድሜ ገደብ አለው፡፡ጺምን አሸብቶ ዲያቆን መሰኘት አይቻልም፡፡ወይ መመንኮስ ወይ መቀሰስ ግድ ነው፡፡ቅዱስ ሲኖዶስ ሁኔታውን አመዛዝኖ በቃለ – ዓዋዲ ለሰ/ት/ቤት የተቀመጠው የእድሜ ገደብ 30 አመት ነው ካለ እስኪሻሻል ሕጉን ማክበር ግድ ነው፡፡ግብጽ፣ዝዋይ ብሎ ማመቻመች አይቻልም፡፡ለነገሩ ዝዋይ በቋሚነት የሰባክያን ማሰልጠኛ እንጅ የሰ/ት/ቤት ተቋም አልነበረም፡፡የአቡነ ጎርጎርዮስ ራእይም ቴዎሎጂና የአብነት ት/ቤት ተቀናጅቶ እንዲሰራ እንጅ በቅዳሜና እሑድ የትርፍ ጊዜ ኮርስ አመራር ማፍራት የሚል አይደለም፡፡የኢኦተቤክ ታሪክ በአባ ጎርጎርዮስ ገጽ-98 ተመልከት፡፡ሰ/ት/ቤት ወደ ማዕርገ – ጵጵስና የሚደረስበት መንገድ እንዲሆን ከተፈለገ አሁን ያለው የምግባር ችግር ይቀረፍ፣አብነት ት/ቤት በተጓዳኝ ይሰጥበት፣አደንባሽ አመራሩ ይፈተሸ፣በዋል ፈሰስ ካደረገው አሉባልተኝነትና አውቃለሁ ባይነት የወፈ – ገዝት መንገድ ይጽዳ፡፡ከግብጽ ወጣቶች እሱንም ኮርጁት፡፡ “የማይገረፍ ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል” እንዲሉ አባቶችን እና የበላይ አመራርን ብቻ በመዝለፍ በተቃኘው ሚዲያ አንድ ቃል ስለ ሰ/ት/ቤት ድክመት ሲነገር መንጫጫት ከንቱ ድካም ነው፡፡በተደረገ አገልግሎት፣በተጨመረ እውቀትና ትሕትና ጭምር እንጅ በእድሜ ዘመን ቆይታ ብቻ መኮፈስ አያዋጣም፡፡ስለሌሎች የቤ/ክ አካላት ነውር ብቻ በማውራት የራስን ነውር ማለባበስ ነውር ነው፡፡አሁንም እደግመዋለሁ፡፡ማለባበስ ይቅር!!ካስፈለገና ሐራተዋሕዶ ከፈቀደች በሰ/ት/ቤት አንድነት አመራሩ ውስጥ ስላሉ ግለሰቦች በረባ አገልግሎት ያልታጀበ እድሜና ዝርዝር የምግባር ችግርም መናገር ይቻላል፡፡ከ30 አመት በላይ ያላችሁ ወይ ጽዋ ማኅበር ማቋቋም ወይም ሰንበቴ መመስረት ነው፡፡የታዳጊዎችን እድል በአገልግሎት አመት ርዝመት እያመካኛችሁ ርስት አታድርጉት፡፡ተባብሮ፣ተፋቅሮና ተናቦ መስራቱንም እወቁበት፡፡መታበይ በዝቷል፡፡ተግሳጽ ተጠልቷል፡፡አባት ተንቋል፡፡ተፈታተሹ፡፡ማለባበስ ይቅር!!ደግሞም አስተውሉ!!ከሰ/ት/ቤት የወጡ ተሀድሶዎች የፕሮቴስታንት ኳየር እስከመሆን ሲደርሱ አይተናል፡፡በዚህም በገጠሪቷ ቤ/ክ ሰ/ትቤት ሲቋቋም ሕዝቡ ጴንጤ ሊያመጡብን ነው ያለበት ጊዜ መኖሩን እናውቃለን፡፡ይሄ ሁሉ መናፍቅ ሲወረን ሰ/ት/ቤቶችም ነበሩ፡፡ስለዚህ ካለው የቤ/ክ ድክመት ሁሉ ተካፋይ እንጅ ነጻ አይደላችሁም፡፡አትኮፈሱ፡፡መጀመሪያ ራሳችሁን አድኑ፡፡ፈትሹ፡፡አትሽሞንሞኑ፡፡ወጣቱ የተሰጠውን ድርሻ በአግባቡ ሳይወጣ ጣት መቀሰርንና ማመከኛትን ሙያ አድርጎታል፡፡ፈትሽ!!ተፈተሸ!!ስለተቋሙስ ሁሉም ምላሱ እስኪዝል እያወራ ነው፡፡ሰ/ት/ቤት ግን በአደንባሽ ወመሽ አመራሮቿ ትዕቢት ታጅራ ተለባብሳ እየደነበሸችና በአዳዲስ ማኅበራት ጥላ እየተዋጠች ነው፡፡ንቃ!!

  • በረከት February 26, 2015 at 9:23 am Reply

   አቶ ቀፀላወርቅ ለሰጡኝ ምላሽ እያመሰገንኩ እስቲ የእርሶ አስተያየትን መነሻ ሀሳብን ለአፍታ ቃኘት እናድርገው፤ ግን ሁሉንም ማየት ጊዜም ቦታም አይበቃም፡፡
   አቶ ቀፀላወርቅ ዓድማሱ በመጀመሪያ አስተያየቶ ሲጀምሩ ክስ ከማስረጃ ጋረ ቢሆን ጥሩ ነው፡፡ ብለዋል፡- በዚህ ሀሳብ ላይ ብቻ ገጽ ሊበቃው የማይችል ማስረጃዎችን በሰነድ፣ በድምጽ ወምስል ማቅረብ መዘርዘር ይቻል ነበር፡፡ የእምነታችን ጉዳይ ከሆነ ክስ ማንሳት አስፈላጊ ከሆነ እጅግ በጣም ትንሹ ኢምንት ጉዳይ ሊሆን ይችላለ፡፡ ከክስ አልፎ እራስን መሰዋትነት ለሚጠይቅ የእምነታችን የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ሁል ጊዜ ዝግጁ ነን፤ ወዳጄ ይሄን እንዲያውቁት፡፡ ይህንን ደግሞ ከቀደምት ቅዱሳን አባቶቻችን እና ከዘመናችን ወጣት ግብጻውያንም ተምረናል፤ ሰ/ት/ቤት አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጦ መማርን ብቻ አይደለም የተማርነው፤ የዕምነት ሰማዕትነት የሚናፈቅ እድል፣ የዕምነት ጽናት … መሆኑንም እንደ ቀደምት አባቶቻችን፤ የዘመኑ ግብጻውያንም በእድሜያችን አስተምረውናል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፡፡ ትውልድን ማነጽ ይህ ነው፡፡ እባኮን ሰ/ት/ቤት ገብቶ ከመማር የሚገኘው የጽድቅ አክሊል፤ እርሶ እንዳንቋሸሱት፣ ትውልዱ ይሰደድ እንዳሉት አይደለም፡፡ ይህ አለመሆኑን አቶ ቀፀላወርቅ ለሌሎቹም ቢያሳውቁ ጥሩ ነው፡፡ በየመንደራችን ስሙን፣ ስሟን ከአስካለ ማሪያም ወደ ከድጃ፣ … እየቀያየር የሚሰደድ ትውልድ የሚፈራው፣ ሀገሩን ወገኑን የሚክድ ትውልድ የሚፈጠረው እኮ ከህጻንነት ጀምሮ በአግባቡ በሰ/ት/ቤት ተኮትኩቶ አለማደግ ውጤት ነው፡፡
   ዋናው በምሰጠው አስተያየት ላይ እንዲታወቅልኝ የምፈልገው ጉዳይ ቤተክርስቲያናቸውን በፍጹም መታዘዝ፣ በታማኝነት፣ በፍቅር፣ በፈሪያ እግዚአብሔር የሚያገለግሉ፤ ለአባቶች፣ ለወጣቱ፣ ለምዕመኑ ቀናኢ የሆኑ፣… ብዙ አገልጋይ አባቶች፣ ቀሳውስት ፣… እንዳሉ ሁል ጊዜም አልዘነጋውም፤ የእነሱን መኖር ስናስብ በተቀራኒው አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ይህን ትውልድ በተኩላ ለማስበላት፣ የሚራወጡት የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ ተብዬዎችን እንዳናስባቸው፤ የቤተክርስቲያኒቷን ጉልላቷን ብቻ በማየት የክርስቶስ አካሉ የሆነቸውን ቤ/ክ በአይምሮዋችን እንድናስብ ያስገድደናል፣ በቤቱም እንድንጸና የነሱ ጸሎት፣ ምክር፣ ተግሳጽ፣ ወንጌል፣ ህይወት ሀይልና ብርታት ይሆነናል፡፡
   -ሰሞኑን አንድ አባት ምናሉ እነዚህ የዘመኑ ጆቢራዎች እኮ ስላልተመቻቸላቸው ነው እንጂ ጽላቱን ከቤ/ክ አውጥተው እንደሸጡት ህንጻ ቤተክርስቲየኒቱንም ለመሸት የአይመለሱም ነበር ያሉት፡፡ ለምን አልተመቻቸላቸውም ካሉ? ይሄ ወመሽ ቤተክርስቲያኒቱን የሙጥኝ ብሎ እንዴት ተችሎ፤ ከዚህ ያፈተለኩ የሸወዱት ግን ብዙ ህንጻ ቤተክርስቲያናትን፣ ጽላቱ፣ የእግዚአብሔር ቤት ሀብት ንብረት … ሆዳቸው አምላካቸው በሆኑ ተሸጧል፣ ተለውጧል፤ አዎ በትክክል፡፡ ምን ማስረጃ አለ ካሉ በአራቱም አቅጣጫ በአዲስ አበባ አጥቢያዎች በአሁኑ ሰዓት እየተፈጸመ ያለውን ሙስና፣ ፕሮቴስታንታዊ የአውደምህረቱ የክህደት ትምህርት፣… ከጥቂት አድባራትና ገዳማት ውጭ አብዛኞቹ ገዳማትና አድባራት ላይ ኃላፊ አገልጋይ ተብለው በተሰየሙ፣ ሰባኪ ወንጌል ተብለው በተሰየሙ ከላይ እስከ ታች ባሉ አካላት ክህደት፣ ሙስና ፣ ዝርፊያ፣ ሙዳይ ምጽዋት ዝርፊያ፣ የቤተክርስቲያን ህንጻዎቿን፣ መሬቷን፣ ሱቆቿን፣ ንዋያቷን ዝርፊያ ነው እየተፈጸመ እያየን ያለነው፡፡ ቀፀላወርቅም ይህን አላውቅም አላይሁም አልሰማሁም የሚሉ ከሆነ በጣም በእርግጠኝነት የምነግሮት እርሶም በዚህ ሴጣናዊ ተግባር ውስጥ ተሳታፊ ሳይሆኑ እንደማይቀር በድፍረት ልነግሮት እችላሁ፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡
   -አቶ ቀፀላወርቅ- ጽላቱን ከመንበሩ አውርዶ እየሸጠ ያለው ወጣቱ ነው ወይስ ምዕመኑ? ለዚህም ማስረጃ ይቅረብልኝ ካሉ? ቃሊቲ ወህኒ ብዙ ታራሚዎች ጋር ጎራ ይበሉ፣ ወይም ዘወትር በሰንበት ከሰ/ት/ቤት መልስ ፓሊስና ህብረተሰብ ፕሮግራም ይከታተሉ፡፡ ማለቴ ሰ/ት/ቤት ገብተው የሚማሩ ከሆነ ነው፡፡ ግን እርሶ በዕለተ ሰንበት ሰ/ት/ቤት አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጦ ለመማር አይመጥነኝም ብለው ካሰቡ እንኳን ለወመሹ የቲዎሎጂ ዕውቀቶን ቆመው ቢያስተምሩ ፣ ቢመክሩ፣ ቢዘምሩ ጥሩ ነው በሚል ነው፡፡ ኮሶን በሙዝ ጠቅልሎ ካልሆነ ብቻ፡፡
   -በአንድ ወቅት አንድ የፕሮቴስታንት መሪ እንዲህ ብለው የተናገሩት ታሪካዊ ገለጻ አለ፡- እኛ እኮ ላለፉት 10 እና 15 ዓመታት እምነታችንን በዚች ሀገር ላይ ማስፋፋት የቻልነው የራሳችንን የሀይማኖት ዶክትሪን በመስበክ ሳይሆን በኦርቶዶክስ አገልጋዮቿ ዘንድ የሚታየውን የከፋ የስነ ምግባር ጉድለት ነቅዘን በማውጣት፣ ለራሷ ለምዕመኖቿ በማሳወቅ፣ በመገልለጥ ነው! በደቦ ብዙ ተከታዮችን በአዳራሾቻችን የሞላነው ብለዋል፡፡ ለዚህስ የብልሹ ሥነ ምግባር ውጤት ክስ ማስረጃ ይሉ ይሆን? አቶ ቀፀላወርቅ? አዎ ማስረጃ ካሉ ግን፡- ለዚህ በሚሊዮን ለሚቆጠር ህይወት መጥፋት፣ ለትውልዱ በተኩላዎች መበላት ምክንያት ከሆኑት፣ በተግባር ተጠያቂ ሊሆኑ ከሚችሉት አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ከፈጸሙት ጋር አንዱ አርገው እራሶን ሊወቅሱ ይገባዎታል፡፡
   -አቶ ቀፀላወርቅ ዓድማሱ ታዲያ እርሶ እንዳሉት ወጣቱ ትውልድ ጥሩ ሥነ ምግባር ከየት አይቶ ይማር፤ አሁን እርሶ ማስረጃ ይቅረብልን ብለው ጠበቃ ከቆሙላቸው ወገኖች እኮ በተግባር መማር የሚችለው ክህደት፣ ሙስናን፣ ታጣቂነት፣ ዝርፊያ፣ አድመኝነት፣ ፍጹም ፕሮቴስታንታዊ የክህደት ትምህርት የሆኑ ተግባራት ነው መማር ማየት የሚችለው፡፡ ይህ ደግሞ የአውደምህረት ሚስጢር ነው፡፡
   – አቶ ቀፀላወርቅ በጣም የሚገርም አስተያየት ነው የሰጡት፣ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ በእውነት እላለው ፍጹም ከቤተክርስቲያን ተቆርቋሪነት ያፈነገጠ ሀሳብ ነው የሚያራምዱት፤ እርሶ ባነሷቸው እያንዳንዱ ቃላት፣ ሀረጋትና ገለጻዎች ላይ በጣም ሰፊ የሆነ ምላሽና ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል ግን ስንቱ ማንስት ይቻላል No time… No space …፡፡ የሰ/ት/ቤት ሱቆች ኦዲት አያውቃቸውም ብለዋል፤ ቆይ አቶ ቀፀላወርቅ ከተቋቋመ 60 ዓመት የሞላው ቤተክህነቱ ኦዲት ተደርጎ አያውቅም እኮ፡፡ በነገራችን ላይ ለዚን ያህል ዘመን ኦዲት ያልተደርገ ትልቅ የዓለማችን ተቋም ቢኖር የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቤተክህነት ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ፤ በዚህ ተግባሩ ደግሞ በጊነስ የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ መመዝገብ የሚገባው ልዩ ተቋም ነው፡፡ ፍጹም አንገት ያስደፋል፤ እስቲ በ100 ሚሊዮኖች የሚያንቀሳቅሱት የአዲስ አበባ አድባራት ኦዲት ያውቃቸዋል? አቶ ቀፀላወርቅ? በደጃቸው አላለፈም፡፡ በእነ እገሌ እጅ እኮ ነው በፎርጅድ መሀተም፣ ሞዶሌችና ሰነዶች የቤተክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት እየተዘረፈ ያለው፡፡ በቅርቡ እንኳን አንድ የቤተክህነት ልዑክ በተወሰኑት የአዲስ አበባ አጥቢያዎች ጉብኝት አድርጎ አቶ ቀፀላወርቅ ማስረጃ ይቅረብል ካሉት በላይ ቤ/ክ በጆቢራዎች በሙስና እየተመዘበረች እንደሆነ አልሰሙም፡፡ ታዲያ የሰ/ት/ቤቱ የመማሪያ መጽሀፍት እንዴት ኦዲት ይወቃቸው? ከየት ተምረው? ተጠያቂው ከልጁ በፊት አባቱ ነው እኮ፡፡ ግን አቶ ቀፀላ የሚሰጡት አስተያየት መነሻው ምን እንደሆነ ተረዱት? ለነገሩ በአስተያየቶ አገላለጽዎ ያሳሰቦ የመጽሀፍቶቹ ጉዳይ እንደማይሆን ፍጹም ግልጽ ነው፡፡ ትውልዱ ለምን ቤተክርስቲያን መጣ፣ ለምን በአውደ ምህረቱ ሞላ ነው እንዴ? ያስተውሉ!
   – አቶ ቀፀላወርቅ ዓድማሱ በሰጡት እያንዳንዱ አስተያየት ላይ ፍጹም ምክንያታዊ የሆነ በማስረጃ የሚገለጽ ምላሽ ላቀርብሎት እችላለሁ፤ ግን ጊዜም፣ ቦታም አይበቃም፡፡ ጥቅምም የለውም፡፡ ግን ከመነሻዬ ኮሶን በሙዝ ጠቅልሎ ላልኩት ከበቂ በላይ የሚሆን ነው፡፡
   ዋናው ነገር ግን ይህን ወጣት በተኩላዎች አስበልቶ፣ ከፕሮቴስታንት አዳራሽ አጉሮ ይህችን ቤተክርስቲያ ሸጦ ብሩን ለመከፋፈል ማሰብ፤ ፍጹም ቅዥት ነው፡፡ ስለዚህ የማይቻል ነገር አይቻልም፡፡ መሆን ያለበት ግን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ዶግማና ቀኖና ተገዝቶ ከሆድ አምላኩ ታቅቦ መማማር፣ መተራረም፣ መመካከር፣ አርአያ የሚሆን ተግባር ለወጣቱ ሰርቶ ማሳየት ነው፡፡ መፍትሄም የሚሆነው፡፡
   -አቶ ቀፀላወርቅ ዓድማሱ ለቀሪዎቾ አስተያየቶ ምላሽ ለመስጠ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም፣ … No time… No space … አመሰግናለሁ፡፡

   • Seifu February 28, 2015 at 3:03 pm

    Bere ! When the Jews crucified our lord Christ, their intention was not to respect the commandments of God or the laws of Moses. They simply hated him. His was accepted and his way of teaching was a little different. They hated him in all seance and they used all possible laws to prerequisite him. It is quite clear that the problems that you mentioned do exist in our church. Even worse than you mentioned. So far as I know, the priests that you hate, not the thieves but the the ones that spoke over the wrong acts of MK, are the one that are trying to solve these problems.

    As I know, it is these priests that support the campaign of our patriarch against corruption. U and ur friends are trying to take the credit of their job and use it against them selves. Simply bc they showed the good, as well as the bad sides of MK, the mahber who acts against the wills of the synod it self. How ? Well, i believe you know that the Holy Synod has decided several times for the MK to have his financial system audited by our church and not the company that MK choose it self. Come on! We’re all grown ups. We know the polythics and don’t try to fool us with senseless reasons. You are against the patriarch NOT because they are corrupt but because the patriarch and the priests you hate want everything corrected in all divisions. I.e. to correct the corruptions in church, in mahbere kidusan as well as in all civil society. U just hate them because they spoke about the + and – of MK. If you really were a true person, you would also write that MK is sharing the money collected by the name our church to its members in the name of axion. I wonder how much of the share the top officials are owning! U would also that MK refused several times to audit its money by the church, even if the synod decided a million times about it. By the way, MK gubo sysetem aykebelem kalk weshet new. There, at MK, i tell them in front trying to solve it all together, though they hate me for that.

    If u were a true person, you would write to do something about the MK priests and diakons who wished death to MY PATRIARCH, IN FRONT OF HIM ! If u were a true person, you would also write about MK, who refused to have its books audited by the church’s Likawent. If u were a true person, you would also write about MK who declares tehadso on everyone it hates mostly with no evidence. How about MK’s capitalist strategy in USA. Dont u think this also has to be checked. I my self has given ASRAT to MK. Now I regrate it ! Do u really know what really is going on there? I know ! We are all grown ups. Dont try to fool us with edited video and audio giving ur own interpretation. BZW, u would also say im tehadso simply bc I showed u ur week side. hahahahahaha, what’s wrong with you? Why dont you work together? Why dont u simply believe in a win win strategy?? U and I and every one is against the ones that steal money and the ones that are protestants, tehadso. From what I read of ur comment, u seem to be driven by hoaxes than absolute reasoning. Here is what is going on.

    Let’s say you, some Sunday schools are people “X”. Our patriarch and the priests that spoke the + and – of MK are people “Y”. The corrupt priests and other corrupts are people “Z”. What is happening is , “X” hates “Y”. So, “X” prosecutes, condemns everything of “Y” saying “Y” is the same as “Z”. “X” and “Y” are both trying to solve the problem of “Z”. “X” wants to take the credit of what ever “Y” did and want to blame “Y” for what ever things going wrong. What is best is if “X” and “Y” work together to solve the problems of “Z”. “X” are members and propaganda leaders of MK.

    I was like you and I know how it feels. I recommend u this. Go to “Y” and work with them for some time. They wont say no for sure. Hey! I know u all. I grew up with u and MK. I know the inside everything and dont just be driven by a hoax or fox, tehadso. Corruption is everywhere. Everyone has to work together to solve the problem. Dero dero zem belo sayastewel ye bahtawi kal eyesema mirebesh aschegari bezu neber. Ahun sayastewel endihu ye mahbere kidusan x y z calculation west yegebaw new miaschegrew.

    These days, im really happy that MK is not the government of ethiopia or our church. If they did this with what they now have, what would have they done if they were holding the military in their hands? Our church is built in martyr and not in war. St. Gorge was a soldier. He decided to be a martyr than general. Dont war. Work together for a better future.

    Let’s all be people of truth. Tell me my week points. I will correct. Listen to me when I tell u urs. Don’t just close ur ears bc u love MK so much. Don’t just rise on fathers. Work with them to make a difference. Be tsom seat yekertana erk yetasebal eji kalketachulen yebalal??? Men ale kalteketu kemetelu tesebsbachu betselyulachew. Lewt ayametam??? Listen to the following.

   • Seifu March 1, 2015 at 7:39 pm

    Echin yewedal ! Hara Tewahdo ! u’re editing my comment before posting. This is not fair. U re deleting and hiding serious evidences i mention. Either post everything or post nothing.

 2. Anonymous February 23, 2015 at 4:53 pm Reply

  ይህችን ቤተክርስቲያን ትውልድ አልባ ለማድረግ በታቀደው የተሀድሶ የአስርት ዓመታት እቅድ ለማስፈጸም ምን እየተደረገ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በጥቂቱ ለማሳያ ያህል፡-
  1ኛ. በሰንበት ት/ቤት የሚሰባሰቡ ወጣቶች ስራ ፈት እንደሆኑ እና የስነ ምግባር ችግሮች ከሌሎች ወጣቶች በተለየ መልኩ ጎልቶ የሚታይባች መሆኑን፤ በምንፍቅና እና በሙስና በተዘፈቁ ‹‹በአስተዳዳሪዎች››፣ ‹‹ጸሀፊዎች››፣‹‹ሰባኪያን›› …አማካኝነት ማስወራት፤ በየአውደ ምህረቱ መተቸት፡፡
  2ኛ. ሰ/ት/ቤቶች በቤተክርስቲያን አስተዳደራዊም ይሁን ልማታዊ አገልግሎቶች ላይ ምንም ግብአት እንደሌላቸው አድርጎ ማቅረብ፣ እንዲሁ ተሰባስቦ መዝሙር ከመዘመር ባለፈ በቤተክርስቲያን ውስጥ በተለይም በአስተዳደራዊ ዘርፉ ላይ እንደማይመለከታቸው አድርጎ ማቅረብና በአገልግሎቱም እንዳይሳተፉ እንቅፋቶችን መፍጠር፡፡
  3ኛ. በመመሪያው መሰረት ለሰ/ት/ቤቶች አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ለማሟላት እንቅፋት መፍጠር፣ ፍጹም ፈቃደኛ አለመሆን፤ በጥቂቱ የሚገለጹ የወቅቱ የሰ/ት/ቤቶች ተግዳሮቾች ናቸው፡፡
  *******************************
  በአሁን ወቅት ቤተክርስቲያኒቱን ትውልድ አልባ ለማድረግ ቀን ከሌት በመንደፋደፍ ላይ ከሚገኙት አካላት አንዱና ዋነኞቹ የቤተክህነቱ የበላይ አመራርና የውስጥ ጉዳይ አስፈጻሚ ግለሰቦች ውስጥ፡-
  -የቀድሞው የማደራጃ መምሪያ ኃላፊውና በምንፍቅና ምክንያት በሰ/ት/ቤቶቹ አንድነት ጉባኤ የዶሴ የማስረጃ ክስ አማካኝነት እንዲነሳ የተደረገው ‹‹አባ›› ሠረቀ እና
  -በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያኒቷ ባለቤት አልባ በሚመስል መልኩ ከአማሳኞችና ከጸረ-ተዋህዶ ካድሬዎች ጋር ህብረት ፈጥሮ እያመሳት የሚገኘው ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ ዋናዎቹ ናቸው፡፡
  *******************************
  ከላይ ከተጠቀሱት ግለሰቦች ጋር ግንባር ፈጥረው የቤተክርስቲያኒቱን ቀጣይ ተረካቢ ትውልድ በሰ/ት/ቤቶች እንዳይደራጅ፣ በቤተክርስቲያኒቷ የልማት አገልግሎት ላይ በአዲስ አበባና በሌሎች ሀገረ ስብከቶች እንዳይሳተፉ ከሚያደርጉ ቡድኖች ውስጥ፡-
  1ኛ. በተሀድሶ ምንፍቅ የሚጠረጠሩ በቤ/ክ ውስጥ የተሰገሰጉ ‹‹አገልጋይ›› ሰባኪያን ግለሰቦች …፣
  2ኛ. በከፍተኛ የሙስና እና የምዝበራ አዘቅጥ ውስጥ የሚገኙ የቤ/ክህነትና የአድባራት ‹‹ኃላፊዎች› ፣ ‹‹አስተዳዳሪዎች››፣ ‹‹ጸሀፊዎች››፣ ‹‹የሂሳብ ሹማምንት››፣ ‹‹የልማትና የሰበካ ጉባኤ አባላት›› … ዋናዎቹ ናቸው፡፡
  *******************************
  እነዚህ አካላት ይህን ተግባር ለምን ይፈጽማሉ?
  1ኛ. በቤተክርስቲያኒቷ ላይ እያጧጧፉ ያሉትን የዝርፊያ፣ የሙስና እና የህገ ወጥ ተግባራት ሰንሰለት እንዳይነካባቸው፤
  2ኛ. በተሀድሶ ምንፍቅና የውስጥና የውጭ ሴራ ቤተክርስቲያኒቷን ትውልድ አልባ በማድረግና ቤተክርስቲያኒቷን በመሰነጣጠቅና ለመከፋፈል ያለሙትን የዘመናት ህልም እውን ለማድረግ፤
  3ኛ. አንዳንድ ‹‹የመንግስት›› አካላት የቤ/ክ አስተዳደር መጠናከርን በተለይም የወጣቱ ትውልድ መደራጀትን እንደ ስጋት ስለሚመለከቱት፤ እና
  4ኛ. ኢትዮጵያን በግብረ ሰዶም … የኃጥያት እሳት ለማቃጠል እንቅፋት ከሆኑባቸው የወቅቱ የሀገሪቱ አካላት ውስጥ በዋናነት የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ማህበራት በመሆናቸው ነው፡፡
  *******************************
  ስለዚህ?

  በዕምነታቸው ምክንያት በአክራሪ ሙስሊሞች በሊቢያ በ21 ግብጻውያን የኦርቶዶክስ ወጣቶች ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝ ግፍበዘመናችን መመልከታች፤ ለእኛ ኢትዮጵያውያን የተዋህዶ ወጣቶች በአሁኑ ወቅቱ በሰንበት ት/ቤት ተደራጅቶ ቤተክርስቲያንን ለማገልገል፣ ለመገልገል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ከሚደርስብን ፈተና እና እንቅፋት አንጻር ገና ብዙ ይቀረናልና፡፡

  ስለዚህ፡- በህብረት በጾምና በጸሎት የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማሪያም ምልጃን፣ የቅዱሳኑን፣ የሰማዕታቱን፣ የአርድእቱን … ኃይል ምልጃና ብርታት፣ የቅዱሳን መላዕክቱን ጠብቆትና ተራዳይነት አጋዥ አድርገን ለአፍታ እንኳን ሳንዘናጋ፣ አንድነታችንን ከሚከፋፍል ሴራ! ‹/I› ተጠብቀን እንደ እርግብ የዋሀዎች እንደ እባብ ብልሆች ሆነን ጉዞአችንን አጠናክረን መቀጠል ይጠበቅብናል፡፡

  *******************************
  ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር!!!

  • ዘበነ February 25, 2015 at 2:16 pm Reply

   ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ ቤተክርስቲያኒቱ ላይ ትልቅ የመናፍቃንን አላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለ ቅጥረኛ መናፍቅ ነው።
   1,በቦሌ መድሀኒ ዓለም በህፃናት ላይ የምንፍቅና ኮርስ በመስጠት ብዙ የቦሌ ህፃናት ተበርዘዋል።
   2,አቃቂ መድሀኒአለም በዚህ አጀንዳው ተንቀሳቅሶ 156 የሰንበት ተማሪዎች ከሰንበት ት/ቤቱ ተባረው ወደ መናፍቅ አዳራሽ በእሱ መሪነት እንዲገቡ ተደርገዋል
   3,በሰሚት መድሀኒአለም የሰንበት ት/ቤትን የመከፋፈል ና የማዳከም አጀንዳ በዚሁ ቀ/ሰለሞን እየተፈፀመ ያለውን ያካባቢው ሰው ይፈረድ ሰ;ት/ቤቱ ተዘግቷል
   4,በቦሌ ሚካኤል የተሐድሶ እንቅስቃሴ ተግባራዊ ለማድረግ ከአለቃው ጋር በመሆን ለህፃናት ኮርስ እየሰጠ ይገኛል
   5,የንሰሀ ልጆቹን ፀሎት፣ፃም፣ስግደት አያስፈልግም።ለማርያም፣ለቅዱሳን ብዙም ቦታ አትስጧቸው ዋናው ኢየሱስ ነው። በሚል ያስተማረውን የንሰሀ ልጄ የሚላት ተከራክራው ሰሞኑን ልታጋልጠው ቤተክህነት ሄዳለች
   በአጠቃላይ ይህንን ተመልክቶ ስለቀሲስ ሰሎሞን በቤተክርስቲያን ውስጥ የመናፍቅነት ተልእኮ በቅርብ ቀን መፀሐፍ ተዘጋጅቷል ይጠብቁ

 3. Anonymous February 24, 2015 at 6:25 am Reply

  ሰንበት ትምሕርት ቤቶች
  *************************
  ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የከፋ እንቅስቃሴ ለሚያደርጉት የተሃድሶ ዓላማ አራማጆች በአንድም ይሁን በሌላ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት አቋም አልባ በመሆናቸው የተነሳ ለተሃድሶዎች መጠቀሚ እየሆኑ ነው….. ብዙዎቹ ሰንበት ት/ቤቶች ዛሬም ከተቀመጡበት ወንበር ሳይነሱ….. እንዳሉ( K constant ) ናቸው….. በቁማቸው ያንቀላፉ….. ዓላማ….. ግብ…. ራዕይ የሌላቸው ሰንበት ት/ቤቶች ከተኙበት የኮሚቴ ስራ መንቃት ስላልቻሉ ተሃድሶዎቹ እንደፈለጉ አውደምሕረቱን ይዘፍኑበታል…… ኃላፊነት የከበዳቸው…… መናገር ያስፈራቸው….. እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ የሚጎተቱ….. የኦርቶዶክስ ለዛው ጠፍቶበት በተሃድሶዎች እጅ ስለወደቀው አውደምሕረት የማይጨነቁ….. ማሕተቡን እንዳሰረ…. ነጠላውን እንዳጣፋ…. ለቤተክርስቲያን ጠላት እየሆናት ስላለው አካል የማይጨነቁ….. ነገር ግን ካሕናትን በሬ አርዶ ለማብላት….. ቢራ ከፍቶ ለማጠጣት የቸኮሉ…. መንፈሳዊ ስራ እና መንፈሳዊ ጥበብ….. ስጋዊ ስራ እና ስጋዊ ጥብብ የተደበላለቀባቸው…..

  ከመዝሙር ጥናት ውጪ ሰንበት ት/ቤታቸው ሌላ ግብ እና ተልዕኮ እንዳይኖረው ተደርገው ተጠፍጥፈው የተሰሩ ሰንበት ት/ቤቶች ለድክመታቸው ላልሰሩት ስራ በምክንያትና በሰበብ የታጠሩ ናቸው…… እልፍ አዕላፋት ምክንያት ያለመታከት የሚደረድሩ….. በየመታጠፊያው ሰበብ የሚያዥጎደጉዱ…… ሰበብ የማያጡ….. የተሰጡለትን ዓላማ የዘነጉ….. የተቀበሉትን ኃላፊነት የማያስተውሉ….. እንቅልፍ የከበደባቸው…. የእነርሱ ክልል (Boundary) እስካልተነካ ድረስ ቤተክርስቲያን ምንም ብትሆን….. ምንም የማይመስላቸው….. ቃለ አዋዲውን በሚገባ ያልተረዱ…… ቤተክርስቲያን በቃለ አዋዲው ላይ የሰጠቻቸውን ስልጣን አንዱንም እንኳን ለመጠቀም ፍላጎት የማያሳዩ…… ከሌላው አጥቢያ ተቀይሮ የመጣው መናፍቅ እና ተሃድሶ አቋም ስለሌላቸው ዘፍኖባቸው የሚሄዱ…… አሽላልቶባቸው እና አቅራርቶባቸው የሚሄዱ ሰንበት ት/ቤቶች……. ለምን ብለው እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነታቸው እንደ ተቋምነታቸው የማይጠይቁ በመሆናቸው የተነሳ ነው…… መጠየቅ ባለመቻላቸው በመላው የሀገራችን አቅጣጫ በምትገኘው ቤተክርስቲያን ለተጋረጠው የተሃድሶ እንቅስቃሴ በአንድም ይሁን በሌላ ደጋፊ ወደ መሆኑ ደረጃ እየተሸጋገሩ ነው

  ግርም እኮ ነው የሚለው …… መቼ ነው ተጀናጃኝ ሰንበት ት/ቤቶች…… የሚቅለሰለሱ ሰንበት ት/ቤቶች…. አቋም አልባ የሆኑ ሰንበት ት/ቤቶች….. እኔ ምን አገባኝ የሚሉ ሰንበት ት/ቤቶች በፀረ-ተሃድሶ እንቅስቃሴ ላይ ምክንያታዊ ድርሻ የሚይዙት መቼ ነው……… መቼ ነው ጠያቂ የሚሆኑት…… እንደ ተቋም ተሰሚ የሚሆኑት መቼ ነው……. ከእንቅልፋቸው የሚነቁት መቼ ነው

  ብዙዎቹ ሰንበት ት/ቤቶች ያሳዝናሉ …..ቆራጥ ባለመሆናቸው የተነሳ ስንት ነፍስ አስበሉ …ግብረ መልስ መስጠት ባለመቻላቸው ስንቱ ለቤተክርስቲያን ጠላት ሆነ ….. እኔኮ በጣም ግርም ነው የሚለኝ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት መጠራትና መመረጥ ፅንሰ ሃሳቡ ያልገባቸው…… በርናባስና ሳውልን ለጠራኋቸው ስራ ለዩልኝ የሚለውን አምላካዊ ቃል ያልተረዱ…… ቅዱስ እስጢፋኖስን ጨምሮ የሰባቱ ሰዎችን ለግልጋሎት መመረጥ ያልገባቸው…… እንደ ሮዴ የተንኳኳውን በር መክፈት ትተው እንዴት ይሄ ሊሆን ቻለ ብለው በመገረም የሚደነጋገሩ…… ነገም ከነገም ወዲያ የሚደነጋገሩ….. የቅድስት ቤተክርስቲያንን ክብር ለማስጠበቅ እና ክብሯ ለማስመለስ የተቀመጡ የማይመስላቸው….. ከኖሩበት ካደጉበት ነባራዊ ሁኔታ ወጥተው ተሃድሶ በቤተክርሰቲያን ላይ ሊያስከትል ያለው ችግር ያልተረዱ…… አሁንም እዛው በተኙበት ያንኮራፉ…… ምን ያሕል አባላችን ወደ ጉባዔያችን መጣ ብለው ቁጥር የሚመዘግቡ ….. ምን ያሕል አባላችን ግን በተሃድሶ እንቅስቃሴ ተነጠቀብን ብለው የማያስቡ…… ወይም እንዳያስቡ ተደርገው የተቀረፁ ሰንበት ት/ቤቶች ለመናፍቃን እና ለተሃድሶዎች በአንድም ይሁን በሌላ….. አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ደጋፊ ወደመሆን ደረጃ እየተሸጋገሩ ነው

  በመፃጉ ታሪክ ላይ ተመርኩዞ ቀድመሕ ግባ የሚል ስብከት ተሰብኮላቸው…… የተዘጋው በር ገርበብ ተደርጎ ተከፍቶላቸው….. የተደናገሩ….. የተሃድሶን ስራ እና ሴራ ዘወትር ስለሚሰሙት እንደ ተራ ነገር የሚቆጥሩት….. የሕንድ ቤተክርስቲን ለሁለት መከፈል ተረት ተረት የሚመስላቸው…… የአርመን ቤተከርስቲያን ለሶስት መከፈል ወግ የሚመስላቸው….. የሶርያ አብያተ ክርስቲያናት መፈራረስ የእርስ በእርስ ጦርነት ብቻ የሚመስላቸው…… በግብፅ ቤተክርስቲያን ላይ የተሞከረውን ሴራ ያልተረዱ …..ሰንበት ት/ቤቶች ዛሬም አቋም ወስዶ ለመቃወም ሲታትሩ አይታዩም……… ለምን ቢባል መልሱ ድንዛዜ ነው …. በየቀኑ ጉዳዩን ስለሚሰሙት ተለምዶአዊ ክስተት አድርገውታልና

  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምንም አትሆንም….. ብለው በተቀመጡበት ወንበር ላይ የሚያንኮራፉ ሰንበት ት/ቤቶች አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ለተሃድሶ እንቅስቃሴ ደጋፊ እየሆኑ ነው ….. አቋም በሌላቸው ሰንበት ትምሕርት ቤቶች ዙሪያ ተሃድሶዎቹ(መናፍቆቹ) በሚገባ አተኩረው ይሰራሉ…. እንደነዚሕ ያሉ ሰንበት ት/ቤቶች በሚገኙበት ቤተክርስቲያኖች ላይ የተሃድሶ ዓላማ አራማጆች አተኩረው ይሰራሉ….. በካሕናቱ በዲያቆናቱ ዙሪያ አተኩረው ይሰራሉ…..
  በሀዋሳ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የተከሰተው ችግር ሕልም የሚመስላቸው ባለ ሰመመኖች……ስለ ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን(አዲስ አባባ) ሁኔታ ማውራት የማይፈቅዱ……. የደብረ ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ችግር መክስተ ምስል (ፊልም) የሚመስላቸው….. ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ጓደኛ አድረጎ የሚሰብከውን ሰባኪ ከአውደምሕረት ጎትቶ ማውረድ ያቃታቸው ሰንበት ት/ቤቶች…….. ምንፍቅናው ሲታወቅበት የኦርቶዶክ ማልያ ለብሶ የሚሸልለውን ሰባኪ ከአውደምሕረቱ ላይ ማውረድ ካልተቻለ ምኑን የቤተክርስቲያን አካል ተኮነ…… በትሕትና በፍቅር በእምነት እና ቤተክርስቲያን በመጠበቅ መካከል ያለውን ልዩነትእና አንድነት አጥርቶ ማየት ያቻሉ ሰንበት ት/ቤቶች….. በጊዜ በመንቃት ካልቻሉ አደጋው የከፋ ነው የሚሆነው…… ሰንበት ትምሕርት ቤቶች እባካችሀን በ Logarithm Function ሊገለፅ የሚችል ምክንያት አትደርድሩ Parabolic (Downward and Upward) ዕቅድ አትንደፉ …..ቢጨመቁ የአንድን ሰው አማካይ የእውቀት ልኬት ለማይሞሉ ተሃድሶዎች በጣም ቀላል Linear Function ለመተግበር ዝግጁ ሁኑ…….. መቼም ሰው በእናንተ አቋም አልባነት ተቃጥሎ አይሞት ….. ምክንያት…. ምክንያት…. ምክንያት….. ምክንያት…… ምክንያት…… ምክንያት…… ምክንያት ………… ሲበዛም ይሰለቻል …..ሰበብ ….. ሰበብ…..ሰበብ…..ሰበብ…..ሰበብ……ሰበብ …….. ሲበዛም ይመራል

 4. Anonymous February 24, 2015 at 6:29 am Reply

  • nehmiashishay March 31, 2015 at 6:59 am Reply

   Anonymous February 24, 2015 at 6:29 am Reply

 5. Anonymous February 24, 2015 at 8:00 am Reply

  ራሳችሁን ፈትሹ፡፡ነጽሩ ነፍሰክሙ፡፡
  የተዘረዘሩት ሰዎች ሳይኖሩም በሰ/ት/ቤት ዙሪያ ችግር ነበር፡፡አባ ሰረቀ የማደራጃው መምሪያ ኃላፊ እያሉም ነበረ፡፡አሁንም አለ፡፡ችግሩ ግለሰባዊ አይደለም፡፡ተቋማዊ ነው፡፡የሚቀረፈውም እንደተቋም ሁሉም አንድ ልብ ሆኖ በቃለዓዋዲው በተሰጠው ድርሻ ልክ ሲንቀሳቀስ ነው፡፡በአሁን ሰዓት ሰ/ት/ቤት ማለት በቃለዓዋዲው በተቀመጠለት መብትና ግዴታ ሳይሆን በማኅበረቅዱሳን ቅኝት የሚነጉድ ተቀጽላ ተቋም ሆኗል፡፡ተጠሪነቱ ለስሙ ለአጥቢያ አድባራት ነው ይባል እንጅ በተግባር ተጠሪነቱ ለማኅበረቅዱሳን ከሆነ ሰነበተ፡፡ማኅበረቅዱሳን ደግሞ ውስጣዊ ችግሩን ሁሉ በተሐድሶና በአባ ሰረቀ እያሳበበ ማለባበሱን ከተያያዘው ድፍን 7 አመት ሞላው፡፡ባለፉት 7 አመታ በአምሳሉ ሲቀርጻቸው የቆዩት ሰ/ተማሪዎችም በዚሁ ጎዳና ጉዞ ጀምረዋል፡፡የራስን ድክመት አለመመልከት፡፡ጣትን መቀሰር፡፡ተሳዳቢነትንና ያላግባብ ፍረጃን እንደተቆርቋሪነት መቁጠር፡፡ከንቱ ጉዞ፡፡ተሐድሶንና ሙስናን እንዋጋ ካልን መጀመሪያ ራሳችንን እናንጻ፡፡ብዙ ሆነን በአንድ ድምጽ ስላወራን ብቻ ድክመታችን አይሸፈንም፡፡
  ራሳችሁን ፈትሹ፡፡ነጽሩ ነፍሰክሙ፡፡
  ቢደክምም የራሳችን ነውና ተቋሙን አክብረን በሕጉ እንመራ፡፡ከተመሰረተ 50 አመታትን የደፈነው፣በቃለዓዋዲው በግልጽ እውቅና የተሰጠው፣በሰበካ ጉባኤ ወኪል ያለውና በእያንዳንዱ የአጥቢያ ቤ/ክ በውሳኔ ሰጭነት የሚሳተፈው፣በማደራጃ መምሪያ ደረጃ በሊቀጳጳስ የሚመራው ሰ/ት/ቤት ራሱን እየፈተሸ ነጻነቱን አስከብሮ የሚቆም ተቋም መሆን ሲገባው ያለሕጉና ሥርዓቱ ራሱን ለ20 አመት ማኅበር ተቀጽላ አድርጎና የማኅበረቅዱሳን አጀንዳ ተሸካሚ ሆኖ እንጀፍ-እንጀፍ ማለቱ ደስ አይልም፡፡በራሳችሁ እግር ቁሙ፡፡ወመሽ አመራሮቻችሁን ፈትሹ፡፡አመራሩ የአረጋውያን ክበብ እየሆነ ነው፡፡አመራሩ በቆይታው የረባ መንፈሳዊ እውቀትን ሳይሆን የካሕናትን አድማ ተምሮ በዘመናዊ መልኩ ማስቀጠልን እንደሙያ የያዘ ነው፡፡እሱን ፈትሹት፡፡
  ራሳችሁን ፈትሹ፡፡ነጽሩ ነፍሰክሙ፡፡
  ማመከኛትን እንደስራ የያዘውን አመራራችሁን ፈትሹት፡፡እሱን ስትጨርሱ እጃችሁን ብትቀስሩ ያምርባችኋል፡፡የራስን ድክመት እያለባበሱ ዘወትር ጣት መቀሰር፣ካቻማሊ እየሞሉ ወደ ቤተክሕነት መሰለፍ፣በየግልጋዜጣውና ብሎጉ የራስን ነውር ሸፍኖ የሌላውን ማጉላት፣በቃ ለቤ/ክ የምናስብ እኛ ብቻ ነን እያሉ ራስን መስቀል፣አንዳች የረባ የቤ/ክ የጉባኤ ትምህርት ሳይቀስሙ 20 እና 30 አመት ያገለገልነው ሰ/ት/ቤት እያሉ አመራሩን የሙጥኝ ብሎ ተቋሙን ማደንበሽ አያዋጣም፡፡የተሐድሶ ኑፋቄ(በማ/ቅ ኤዲቶሪያል ቦርድ ምንፍቅና ነው የሚባለው፡፡ቃሉን ከየትኛው የግሥ አወራረድ እንዳገኙት አምላክ ይወቅ)የሚመከተውና ያለው ምዕመን በቅድስት ተዋሕዶ የሚጸናው በእውቀትና በምግባር እንጅ ዘወትር አንጋጦ አበሳን በማበስና በአሳዳጅነት መንፈስ አይደለም፡፡እሱ ጎዳና ለማኅበረቅዱሳንም አልጠቀመም፡፡
  ነጽሩ ነፍሰክሙ፤ወአንጽሑ ነፍስተክሙ፡፡ነፍሳችሁን ተመልከቱ፤ሰውነታችሁን ንጹህ አድርጉ፡፡ቅዳሴ እግዚእ ቁ 12፡፡

 6. ዘበነ February 24, 2015 at 1:23 pm Reply

  አዎ፣ ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ የሚያደርገው ያለ እንቅስቃሴ መፈተሽ አለበት! የማን ዓላማ ይዞ፣ የማን ቅጥረኛ ኾኖ ነው የሚንቀሳቀሰው?

 7. Anonymous February 24, 2015 at 1:24 pm Reply

  “……ሰንበት ት/ቤት ራሱን የቻለ ተቋም ነው ስለዚ ለሰንበት ት/ቤት ሌላ ማህበራት አያስፈልጉትም፡፡
  በመሠረቱ ማህበራት የተለያየ ታሪካዊ አነሳስ አላቸው፡፡ በመሆኑም ሰንበት ት/ቤቶች እየታደከሙ ማህበራት እየተስፋፉ ናቸው፡፡
  ማህበራት በሰንበት ት/ቤቶች ሥር ናቸው ተብሎ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወስኖአል፡፡ ማህበራት በሕግ ሥር ካልሆኑ ጉዳታቸው ሊአመዝን ይችላል፡፤ ሰንበት ት/ቤቶችን ለማጠናከር የማያቋርጥ ትግል እናደርጋለን፡፡ አንድነቱም ጠንክሮ ሊሠራ ይገባዋል መመሪያ እያራርቀንም ነገር ግን የተራራቅነው እኛው ራሳችን በፈጠርነው ችግር ነው፡፡
  በአድባራቱና በየገዳማቱ የነበሩትን ችግሮች አብዛኛዎቹን አስወግዶናል፡፡ ቀሪዎችንም ችግሮች ለመፍታት ጥናት እያደረግን ነው ያለነው፡፡
  ስለዚህ ወጣቶች በትዕግስት መጠበቅ አለባቸው ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ ብሎ እንዳስተማረን በጥበብና በየዋህነት ማገልገል አለብን ድርሻዎቻችንን አውቀን መስራት አለብን….”ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በዕለቱ ከተናገሩት
  ምንጭ፡- http://www.addisababa.eotc.org.et/site/

 8. sis February 24, 2015 at 3:12 pm Reply

  Yehe ye choma rasoch mesebsebya website new. Sorry to see u say that u re a Christian. Astesaseb betam yegolachual. Ene kentu sehon kenante awaki negne bayoch yeteshale asbalew. Kenante yeteshale ye menfesawinet meredat alegne !

 9. Meberat February 24, 2015 at 6:28 pm Reply

  ይህች ቤተክርስቲያን የምትመራው በራሷ አስተዳደር እንዳልሆነ ለማረጋገጥ እኮ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካል የሆነውን ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውን ውሳኔ እኮ በቦታው ጉባኤውን ሰብስበው የወሰኑትን ውሳኔ መልሰው ‹‹… ቅዱስ ሲኖዶሱ እኋላ ቀር፣ ጸረ-ዲሞክራሲ፣ ዘመን ያለፈበት … ተቋም ነው! ውሳኔዎቹም የዚህ ውጤቶች ናቸው፡፡ …›› ብለው ፓትሪያክ አባ ማትያስ እኮ በራሳቸው ደብዳቤና ፊርማ ለፌደራል ፓሊስ፣ ለፕሮቴስታቱ ሽፈራው ተክለማርያም (የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር) የከሰሱት፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ ይህች ተቋም እየተመራች ያለችው በሌላ አካል ስለመሆኑ የሰነድ ማስረጃ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ከዚስ የበለጠ የኃይማኖት ክህደት፣ አሪዮሳዊነት ሊኖር ይችላል?
  ቅዱስ ሲኖዶሱን እራሱ የጉባኤው ሰብሳቢ አባ ማቲያስ በደብዳቤ፣ በፊርማ፣ በማህተም ‹‹ … ጸረ-ዲሞክራሲ፣ እኋላ ቀር፣ ዘመን ያለፈበት … ›› ከማለት ያለፈ ምን ሊለው ይችላል፡፡ ለነገሩማ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ጉባኤ በኤልያስ አብርሃና መሰሎች ለማፍረስም በአባቶች መካከል ልዩነት ለመፍጠር … በቅርቡ ሰፊ ዝግጅት ተደርጎ እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው እኮ፡፡ ይህንን ሴራ እራሳቸው አባቶች በአውደ ምህረቱ እየተናገሩትና እየመሰከሩ እየሰማን ነው፡፡
  ‹‹… ቅዱስ ሲኖዶሱ እኋላ ቀር፣ ጸረ-ዲሞክራሲ፣ ዘመን ያለፈበት … ተቋም ነው! ውሳኔዎቹም የዚህ ውጤቶች ናቸው፡፡ …›› ሲባል እየሰማ፣ እያየ ዘማሪ ለመምሰል ዩኒፎርም ለብሶ አብሮ የሚያጫፍር … ሰንበት ተማሪ ወይስ መንገደኛ ወይስ ሙዳይ ምጽዋት ገልባጭ ወይስ … ???
  የኤልያስ አብርሃ የልብ ወዳጅና ጉዳይ አስፈጻሚው የፌደራል ጉዳዮች ሚስትሩ እኮ በመንግስትና በህዝብ ስልጣን ላይ ተቀምጦ 1200 ህዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽ ‹‹በኦርቶዶክሶች አንቀት ላይ የሚንጠለጠለው ገመድም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ይወልቃል! ይበጠሳል የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡›› ብሎ ሲያውጅ አልሰማንም? አላየንም? ይህ ግለሰብ እኮ የአባ ማትያስ፣ የኤልያስ አብርሃ፣ … የልብ ወዳጅ ነው እኮ፡፡ ቆይ አንገትህን በሰይፍ እስከሚቀላው ነው የምትጠብቀው ???
  እምነትም ተፈጥሮዋዊ ስሜትም አልባ ትወልድ!!!

 10. Seifu February 24, 2015 at 7:37 pm Reply

  This video exactly tells what is going on here.

  There are problems in our church yet, Things are not being corrected the right way but the catholic way. This for sure may make our church apologize in the future for making unchristian acts. I have a friend, he was so much pushed from sunday school simply bc he listened to Dn. Begashaw’s sibket. What happened next…hhhhhh….he was pushed to the alcohol house. He is a kind person. There are protestants, named tehadso, tehadiso means protestantism in any form. but pushing everyone that has the gut to speak over MK’s mistakes by naming tehadso is unchristan, unfair and simply un just. There is corruption, yet naming everyone who speaks against the shames of MK a corrupt is un christia, un fair and simply unjust. I know a women from MK with a budjet for spying over Begashaw and Mirtnesh. Her task is to collect every information for presicuting them. Luckily up to now they are clean. May God bring peact to our church. And, I cant see the big difference b/n Dn. Tizitaw’s and Dn. Tewodros’s mezmur. But who made the grouping?

  These zemarian are now separated bc of devil. We are choosing the solution in power but not in a speritual way. Its hard. I will never work with any one who hates my patriarch blessing the patriarch of Egypt. Before respecting my father, is it right to respect the father of my neighbour? I have to respect and love both. Who has trained sunday schools to stand against their own patriarch? What a generation?! What a sad story! What a sad story in ethiopia.! And u Hara tewahdo, living in usa and israel, troubling ethiopia…..hhhhhhh….may God give you a kind heart. The holy heart that knows how to correct problems. U make our church a war field. a place of war that a place of peace. U and the black and white MK. And now the sunday schools. I cant believe this. I really dont want to be like u. I will never send my future children to sunday school either. U are very unchristian. What makes u and the corrupt people different then. Sunday school steal’s by hiding money report from local church. MK steals by axion, hiding from church audit and many other that i dont want to mention now. every one is getting corrupt. U are all runing for ur own power. Ur own name. Rasachu be zemare semet kebero yezachu tezelalachu. Matwedut sew sizel denese telalachu. Mata be mahlet seat kahnat bezemare zema kebero yezew eyeteshkerekeru yezemralu, matwedut sew kebero yezo keteshkerekere denese, chefere telalachu. Kefu nachu, Kefu ! Kimegna demegna ! Rasachu bira tetetalachu. Matwedut sebaki bira tegabzo kayachu video tekertsalachu. Yasaznal……mastewalun yestachu. When u point one finger on some one, the other three are up on you. Im really sorry to see this from peaople who call them selves people of the church. Seberbari geez yezachu setesadebu atafrum.

 11. Seifu February 24, 2015 at 7:39 pm Reply

  O the video i attached was this about what is going on now.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: