የ106 ዓመት አረጋዊው የብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሥርዐተ ቀብር ባረፉበት ዕለት ተፈጸመ፤ የሥርዐተ ቀብሩ መጣደፍ ‹‹ሸኚው ሸኚ ሲያጣ›› እስኪያሰኝ ድረስ አባቶችንና ምእመናንን አሳዝኗል

funeral of Abune Aregawi

 • ሥርዐተ ቀብሩ÷ በካቴድራሉ የብዙ አባቶችንና ታላላቅ ምእመናንን ሽኝት ሲያስተናብሩ ለኖሩት አረጋዊ ሊቀ ጳጳስ በማይመጥንና በተቻኮለ አኳኋን ለመከናወኑ ምክንያቱ ፓትርያርኩ ዛሬ ምሽት ወደ ግብጽ የሚያደርጉት ጉዞ ቢኾንም፣ የጉብኝት መርሐ ግብሩ ከደረሰብን ሐዘን አኳያ ሊጤን ይችል እንደነበር አብረው የሚጓዙ ብፁዓን አባቶች ጭምር በጸጸት ተናግረዋል፡፡
 • የሥርዐተ ቀብሩ አፈጻጸም፣ ይቅርና ለአረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ለአንድ ደግ ምእመን እንኳ የሚገባ እንዳልኾነ ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንና ከአበው ትውፊት አንጻር የሚመዝኑ አባቶችና ምእመናን፣ በወቅቱ ፓትርያርክ ዘመን የቤተ ክርስቲያናችን ክብርና ሞገስ እየተፈተነ ለሚገኝበት አስከፊ ኹኔታ አመላካች አድርገውታል፡፡
 • በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረት፣ አንድ ሊቀ ጳጳስ ከዓለም በሞት ሲለይ አስከሬኑ የሚያርፈው የኤጲስ ቆጶስ ተልእኮውን ሲፈጽም በኖረበት ሀገረ ስብከት ወይም በሥራ ቦታው ነው፡፡ ባረፈም ጊዜ ዜና ዕረፍቱ በብዙኃን መገናኛ ይነገራል፤ ሥርዐተ ቀብሩም ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሚገኙበት ይፈጸማል፤ በየሀገረ ስብከቱም ጸሎተ ፍትሐት ይደረግለታል፡፡

 *        *        *

ዜና ሕይወቱ ወዕረፍቱ ለብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ በ1901 ዓ.ም. በፀለምት /ሰሜን ጎንደር/ ተወልደው ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ትምህርት ቤት ገብተውንባብና ዳዊት እንዲኹም ፀዋትወ ዜማ አጠናቅቀው ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ግብጻዊ ማዕርገ ዲቁናና ማዕርገ ቅስና ተቀብለዋል፡፡

በዋልድባ አብረንታንት ገዳም ገብተው ለዘጠኝ ዓመታት ያኽል (ከ1933 – 1942 ዓ.ም.) ሥርዓተ ገዳሙን ከአጠኑና በግብዝና ከአገለገሉ በኋላ በዚኹ ገዳም ዕርገ ምንኵስናን ተቀብለዋል፡፡ ትምህርታቸውን በመቀጠል በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በሚገኘው በደብረ ዓባይ ገዳም የደብረ ዓባይ መዝገበ ቅዳሴ ዜማ ተምረው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡

በ1943 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ፈቃድና ትእዛዝ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትን እንዲያገለግሉ ተልከው ለአራት ዓመታት ያኽል አገልግለዋል፡፡ አኹንም በቅዱስ ፓትርያርኩ ፈቃድ ወደ ግብጽ ሔደው ለ16 ዓመታት ያኽል ነገረ መለኰትን በዓረብኛ ቋንቋ አጥንተው ተመርቀዋል፡፡

funeral of Aba Aregawi

ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ በሱዳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በሓላፊነት ለማገልገል ተልከው ለስድስት ዓመታት ያኽል በአስተዳዳሪነት ሠርተዋል፡፡ በዚኹ ሓላፊነት ሳሉም በ1968 ዓ.ም. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ኹነው በተሾሙ ጊዜ በሱዳን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ወክለው በመምጣት ለበዓሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡

በ1972 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በቅዱስ ፓትርያርኩ ፈቃድ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት በመኾን አገልግለዋል፡፡

በጥቅምት ወር 1983 ዓ.ም. በሱዳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ኾነው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አንብሮተ እድ ተሹመዋል፡፡

ከመጋቢት 1985 ዓ.ም. ጀምሮ የኢሉባቦርና የጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው ለአንድ ዓመት ያኽል ሠርተዋል፡፡

ከየካቲት 1986 ዓ.ም. ጀምሮ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳምና ት/ቤት የበላይ ሓላፊ ኾነው አገልግለዋል፡፡

ከሐምሌ 1986 ዓ.ም. ጀምሮ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው አገልግለዋል፡፡

ከግንቦት 1992 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ሓላፊ ኾነው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡

funeral of Aba Aregawi03

ፎቶ: ማኅበረ ቅዱሳን

መጨረሻም በዚኹ ሓላፊነት ላይ ሳሉ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በተወለዱ በ106 ዓመታቸው ከዚኽ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል፡፡

burial of Aba Aregawi00
የቀብራቸው ሥነ ሥርዓትም በዚኹ ዕለት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሉበት፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሐቱ ከተከናወነ በኋላ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

ልዑል እግዚአብሔር የብፁዕ አቡነ አረጋዊን ነፍስ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን ሰጥቶ በአብርሃም በይሥሐቅ በያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን፤ በማለት እንሰናበታቸዋለን፡፡
Advertisements

14 thoughts on “የ106 ዓመት አረጋዊው የብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሥርዐተ ቀብር ባረፉበት ዕለት ተፈጸመ፤ የሥርዐተ ቀብሩ መጣደፍ ‹‹ሸኚው ሸኚ ሲያጣ›› እስኪያሰኝ ድረስ አባቶችንና ምእመናንን አሳዝኗል

 1. Anonymous January 10, 2015 at 6:08 am Reply

  ኦ ጻድቅ አባ አረጋዊ ንብር በማዕከሌነ
  ስዓል ወጸልይ ሀበ ማርያም እምነ

 2. Anonymous January 10, 2015 at 8:08 am Reply

  ልዑል እግዚአብሔር የብፁዕ አቡነ አረጋዊን ነፍስ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን ሰጥቶ በአብርሃም በይሥሐቅ በያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን

  • Anonymous January 11, 2015 at 8:57 pm Reply

   Breketachew yideresen amen!

 3. Anonymous January 10, 2015 at 11:08 am Reply

  Leoule Egezabhier yeabatchen yebtsu Abune Argawie nefse be Genet yanurelen

 4. Anonymous January 10, 2015 at 7:41 pm Reply

  Amen nefsachiwen begent ysarflen behulam bemneget semaye

 5. Anonymous January 11, 2015 at 6:45 pm Reply

  የ ብዙሃን አባት ሆነው ሳለ እንደዚህ መሆኑ በጣም የሚያሳዘን ነው::እግዚአብሔር ነፍሳችውን በአብርሃም በያቆብ አጠገብ ያኑርልን ::

 6. Anonymous January 12, 2015 at 12:03 pm Reply

  ለታላቁ አባታችን ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዕረፍተ ነፍስን ይስጥልን፡፡እግዚኦ አእርፍ ነፍሰ አቡነ አረጋዊ፡፡
  እናንተ ግን ከፈተናውና ከመከራው ሳይቀር ለማትረፍ አትሞክሩ፡፡ቤተክርስቲያኒቱ አባታችን ከተቆለፈባቸው ማረፊያ ቤት ሰብራ በማውጣት አስፈላጊውን የሕክምና ክትትል እንዲያገኙ ለቀናት ተከታትላ ከአስር በላይ ሊቃነ ጳጳሳት፣ቅዱስ ፓትርያርኩ፣የተቅላይ ቤተክሕነት የመምሪያ ኃላፊዎች፣አለቆችና የቢሮ ሰራተኞች፣ሊቃውንትና ካሕናት እንዲሁም ምዕመናን በተገኙበት አሸኛኘት ተደርጓል፡፡የምትጮኹት ፓትርያርኩን ለማሳቀል እንጅ ለአቡነ አረጋዊ ቀብር ገዷችሁ አይደለም፡፡ለአባቶቻችን ከገደዳችሁ ሁሌ ሐሜት መጻፉን አርግባችሁ በቁማቸውም አስተዋውቁን፡፡ዝምብሎ በየለቅሶው ማዳመቅ አይደለም፡፡በቁማቸው አትገዝግዟቸው ባይሆን አግዟቸው፡፡ምነው የአባቶቻችን አምላክ ለእናንተ ልብ አልሰጥ አለ፡፡አወካችሁን፡፡

  • Anonymous January 14, 2015 at 4:20 am Reply

   አንተ ደሞ የማ ቱልቱላ ነህ?ምን ይህንን ልትክድ ነው እንዴ ወሽካታ መናፈቅ ጎጠኛ !!

   • Anonymous January 23, 2015 at 4:01 am

    beka hasabihin yeteqaweme hulu menafiq gotegna new malet new ere gobez rega enibel
    ere tewu behuwala matefiyaw endayatren ere enichachal

 7. Anonymous January 12, 2015 at 2:12 pm Reply

  e/her nefsachewn begenet yanurilin

 8. Anonymous January 12, 2015 at 6:28 pm Reply

  nebesachewun beselam yasarefelen abatie

 9. Anonymous January 14, 2015 at 7:27 pm Reply

  Bereketiwo le Zelalem ayileyen; Abat Abat Abat………………

 10. Anonymous January 24, 2015 at 7:23 pm Reply

  Esachaw besue nnachawe wayolachawe lakarute. Nafsachawen yemarelene labatachen

 11. bittukan mammo January 22, 2016 at 7:41 am Reply

  ኦ አምላኬ ሆይ አባቶችን አታሳጣን እኛ ደካሞችና እንደ ነፋስ በየአቅጣቻዉ የምንነፍስ ትዉልድ እኮነን እባክህ ጥሩ አባቶችን አቆይልን ሆድ ባሰኝ ኡፍፍ—————————-

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: