ሰበር ዜና – የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ተጠያቂው ሊቅና ኹለገቡ ባለሞያ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ዐረፉ

Lique Kahinat Kinfe Gabriel Altaye

የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን (Liturgical Theology) ተጠያቂው ሊቅ÷ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ

ከግማሽ ምእት ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንንና አገራችን ኢትዮጵያን በክህነት፣ በሊቅነት፣ በመምህርነት፣ በአስተዳደር እና በጸሐፊነት ሞያቸው በብቃትና በትጋት ሲያገለግሉ የኖሩት ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ዐረፉ፡፡

የሊቁ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል ሞተ ዕረፍት የተሰማው÷ ዛሬ፣ እሑድ ታኅሣሥ ፲፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ ቀበና መካነ ሕይወት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ከሚገኘው መኖርያ ቤታቸው ነው፡፡

በመኖርያ ቤታቸው÷ በቤተ ሰዎቻቸውና በወዳጆቻቸው መካከል ያረፉት ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል፣ ከግማሽ ምእት ዓመት በላይ በበርካታ ዘርፎችና በተለያዩ የሓላፊነት ደረጃዎች ሲሠሩ ከኖሩበት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከነበረባቸው ከፍተኛ የደም ግፊትና የነርቭ ሕመም ጋራ በተያያዘ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር በጡረታ የተገለሉ ቢኾንም በመምሪያ ደረጃ የሊቃውንት ጉባኤ አባልነታቸው አገልግሎታቸውን ቀጥለው ቆይተዋል፡፡

ከዘመናችን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መካከል ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል በልዩነት የሚታወቁትና የሚታወሱት÷ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን (Liturgical Theology) ራሱን ችሎ የቆመ የትምህርት ዘርፍ (discipline) ኾኖ ጎልቶ እንዲወጣና በሥርዐተ ትምህርትም መርሐ ትምህርት ተቀርፆለት እንዲታወቅ÷ በምሁራን አነጋገር የራሱ ጉባኤ እና ወንበር እንዲኖረው÷ ባደረጉበት ጥረታቸውና ድካማቸው ነው፡፡

ለዚኽም በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በተለያዩ መጻሕፍት የሚገኙትን የአምልኮ መፈጸሚያ ሥርዓታት በተመጠኑ ገጾች በማስተጋባት ለጥናት እንዲመች አድርገው ያዘጋጁበት ‹‹ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን›› የተሰኘው ዝነኛው መጽሐፋቸው በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡

ባለፉት ዐሥርት ዓመታት፣ በቴዎሎጂ ኮሌጆቻችን፣ በካህናት ማሠልጠኛዎቻችንና በሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን ጸሎተ ቅዳሴውንና ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ጨምሮ ተግባራዊውን ትምህርተ መለኰት (Practical Theology) ለማስተማር በመመሪያነትና ማጣቀሻነት እያገለገለ የሚገኘው ይኸው የሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል ‹‹ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን›› መጽሐፍ ዛሬም በተደጋጋሚ የመታተም ዕድል ማግኘቱም ከፍተኛ ጠቀሜታውን ያሳያል፡፡

ሊቁ መጽሐፉን ከማዘጋጀት ባሻገር በመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን (በቅድስት ሥላሴ፣ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ) በከፍተኛ ደረጃ እንዲኹም በበርካታ መድረኮች ብዙ ሺሕ ምእመናንን ለዓመታት አስተምረውበታል፤ ሳይፋልስ ተጠብቆ እንዲኖርም ሳያሰልሱ መክረውበታል፡፡ በዚኹ መጽሐፍና ከሌሎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋራ በየጊዜው ባዘጋጇቸው በርካታ ጽሑፎቻቸው ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ለመበረዝ በኅቡእም በገሐድም የሚያሤሩ አላውያንና መናፍቃንን ሞግተውበታል፤ ገሥጸውበታል፡፡

የቤተ ክርስቲያናችንን አስተዳደር የሚመራው ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደ ተቋም መደራጀት በጀመረባቸው ዓመታት አገልግሎታቸውን የወጠኑት ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል÷ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን ‹‹በእሑድ ትምህርት ቤት›› በየአጥቢያው አሰባስቦ በማስተማር ሰንበት ት/ቤቶች አኹን በሚገኙበት መልክ እንዲቋቋሙ የማድረጉን ጅምር ከወሰዱት፣ ስብከተ ወንጌልን በተለያዩ የብዙኃን መገናኛዎች (በጽሕፈትም በቃለ ስብከትም) በማስፋፋት ከሚታወቁት መምህራን ተርታ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የቀሳውስትና የመምህራን ማሠልጠኛ በተለይም በቅኔ፣ በአቋቋም እና በመጻሕፍተ ሊቃውንት በጉባኤ ያካበቱትን ሞያቸውን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በጀመሩት አገልግሎታቸው በብዙ አትርፈውበታል፡፡ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅን በምክትል ዲንነት መርተዋል፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የአስተዳደር መምሪያ፣ የካህናት አስተዳደር(መጋቤ ካህናት)፣ የገንዘብና ንብረት አስተዳደር እንዲኹም የቁጥጥር አገልግሎት መምሪያዎች በሓላፊነት በዋናና በምክትል ሓላፊነት እየተመደቡ በምስጉንነት ሠርተዋል፡፡

በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ተጠያቂነታቸውና ጠበቃነታቸው እንደ ዓምድ የሚታዩት ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል፣ በመድረክ ትምህርትና በቢሮ ሓላፊነት ብቻ ሳይወሰኑ በቤተ መቅደሱና በቅኔ ማሕሌቱ ክህነታዊ አገልግሎት ሕመማቸውን ታግሠው ጭምር እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው የጸኑ ብርቱ አባት ነበሩ፡፡

ይህ ዜና በሚጠናቀርበት ሰዓት የሚወጡት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ የሊቁ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ የቀብር ሥነ ሥርዐት ነገ፣ ታኅሣሥ ፳ ከቀኑ በ9፡00 ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ሰባክያነ ወንጌል እና በአባትነት ትጋት ሲያገለግሏቸው የኖሩት ምእመናን ልጆቻቸውና ወዳጆቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጦአል፡፡

የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የአባታችንን ነፍስ ያሳርፍልን፤ ከማኅበረ ቅዱሳን ይደምርልን፡፡

Advertisements

24 thoughts on “ሰበር ዜና – የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ተጠያቂው ሊቅና ኹለገቡ ባለሞያ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ዐረፉ

 1. Anonymous December 28, 2014 at 10:29 pm Reply

  እስከ ዘሬ ድረስ መልካም ነገር ታቀርቡ ነበረ ዛሬ ግን በቀረበው ነገር አዝኛለሁ እናንተስ ለሁሉም ለማሳወቅ መዘገባችሁ ትክክል ነው እኔ ግን ሐራ ተዋህዶን ዛሬ መክፈትና ማንበብ አልነበረብኝም ደግሞም ሐራን ማንበቤ መልካም ነው ግን የመረጥኩት ሰዓት ከቤተ ክርስቲያን ተመልሼ ነው ሐራ ተዋሕዶን ስከፍት ግን የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያስተማሩኝን መምህር ሞት ( እረፍት ) ሰማሁ ሊቀ ካህናት የደም ብዛትና የነርብ በሽታ እንዳለባቸው አላውቅም ነበረ እኔ የማውቀወ የእውቀት ብዛት እንዳለባቸው ነው እንጂ የደም ብዛት አላውቅም መምህሬ አባቴ መካሪዬ አስተማሪዬ ምሳሌዬ ናቸው በረከታቸው ይደርብን ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል የእርሶን ሞት በዚህ ሰምቼ ኃዘኔን በዚህ ለይ በመገለጤ በራሴ ዕድል አዝናለሁ በኔ ልብ ተቀርፀው ይኖራሉና አይሞቱብኝም አዎ ፈጣሪም ደህና ደህናውን ሰው መሰብሰብ ከጀመረ ቆይቷልና መኖሪያዎት ከነርሱ ጋር ስለሆነ በዚህ እጽናናለሁ ለቤተ ከርስቲያን መሰል ይፍጠርላት

  • Anonymous December 29, 2014 at 9:19 am Reply

   Bete krstian talak sew atach.yabatachnin nefs kemahibere kidusan ydemrlin.

  • Anonymous February 26, 2015 at 6:53 pm Reply

   ትክክል ድሮም መልካም ሰው አይቀመጥም

 2. Anonymous December 29, 2014 at 4:32 am Reply

  talak lik abatachin nefeson kene abreham yisahak ategeb yanurelen

 3. Anonymous December 29, 2014 at 5:35 am Reply

  ye abatachinin nefs yimarilin

 4. Anonymous December 29, 2014 at 5:48 am Reply

  Abatachin nefson egziabiher bene abreham,bene yisehak bene yaikob ategeb yaskemitilin!

 5. Anonymous December 29, 2014 at 9:25 am Reply

  የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የአባታችንን ነፍስ ያሳርፍልን

 6. Anonymous December 29, 2014 at 10:06 am Reply

  So so sad now a days it becomes difficult to hear or read a blessing news about our church & our beloved father who serves God for z last 50 years finally rest.R.I .P.

 7. Anonymous December 29, 2014 at 10:31 am Reply

  weleta melash yargen nefse yekebelelene

 8. Anonymous December 29, 2014 at 10:39 am Reply

  የአባታችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን፡፡ አባታችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ሀብት ነበሩ እንደርሳቸው የሚመክር የሚዘክር የሚገስጽ የሚያስተምር እግዚአብሔር ያስነሳልን አያሳጣን አሜን፡፡

 9. Henos December 29, 2014 at 10:48 am Reply

  R.I.P!

 10. ነንድወሰን ተበጀ December 29, 2014 at 2:05 pm Reply

  የሚያሳዝን ነገር ነው፤ የዳዊት ድንከን ባዶዋን ቀረች!!!!!

  • Yaekob Tsegazeab December 30, 2014 at 11:04 am Reply

   ኢትሕዝን ወልድየ፣ ሀሎ ዘይሰመይ ካልእ ህየንቴሁ። እስመ እግዚአብሔር የአምር ዘአንተ ትብዬ፣

 11. Anonymous December 29, 2014 at 2:41 pm Reply

  ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር
  በእውነት የተሰማኝን መግለጽ አልችልም። እኝህን የመሰሉ መጽሐፍ ጽፈው በጉባኤ ተገኝተው ከሚመክሩ የሚያስተምህሩ አባትን መለየት እጅግ ከባድ ነው። እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ቀኝ ያኑርልን። ለእኛም መካሪ አስተማሪ አባት ይስጠን።

 12. Anonymous December 30, 2014 at 1:00 pm Reply

  ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር!!!

 13. Abraham Ta December 30, 2014 at 7:55 pm Reply

  I am very sad to read this condolence, Liqe Kahnat Kinfe gebreal altaye was my father and his children my brothers,
  I miss you two times being far away from Abo Church in Addis Ababa.

  I am very sad,
  May greet my father as well he is also in heaven
  Rest in peace

 14. Anonymous December 31, 2014 at 3:52 am Reply

  it is hard to accept the dearest person in your life is gone away from your life. Abatachin you were among the dearest and knowledgeable fathers that I know since I was in Jimma for my undergraduate, in Addis Ababa for Masters degree and now too abroad for ma PhD. your preaching and blessings will remain with me and all of us. If it was possible to exchange life for life, I would love to change mine for you to keep our church from the problems from the insiders what they called them selves ”tehadeso” and the outsiders those protesters and all other challenges.
  Besewu Hager ye abaten erfet mesemat kebad new le eersewos wodemibeletbewot hedu egnanes leman tilwen hedu????????

  I hope your prayer will remain with us always

 15. anonyms December 31, 2014 at 3:54 am Reply

  it is hard to accept the dearest person in your life is gone away from your life. Abatachin you were among the dearest and knowledgeable fathers that I know since I was in Jimma for my undergraduate, in Addis Ababa for Masters degree and now too abroad for ma PhD. your preaching and blessings will remain with me and all of us. If it was possible to exchange life for life, I would love to change mine for you to keep our church from the problems from the insiders what they called them selves ”tehadeso” and the outsiders those protesters and all other challenges.
  Besewu Hager ye abaten erfet mesemat kebad new le eersewos wodemibeletbewot hedu egnanes leman tilwen hedu????????

  I hope your prayer will remain with us always

 16. Anonymous December 31, 2014 at 5:48 am Reply

  amen nebisachewin yemarilin

 17. abebech December 31, 2014 at 7:11 am Reply

  እግዚአብሔር ነፍስዎን በገነት ያሳርፍልን አባታችን ሐዘኔን ልገልጽ አልችልም እግዚአብሔር ተተኪ አባት አያሳጣን

 18. tayu tilahun December 31, 2014 at 4:54 pm Reply

  እግዚአብሔር ነፍሳቸውንከቅዱሳን ጋር ይደምርልን

 19. tibebu alene January 1, 2015 at 6:06 am Reply

  ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር
  በእውነት የተሰማኝን መግለጽ አልችልም። እኝህን የመሰሉ መጽሐፍ ጽፈው በጉባኤ ተገኝተው ከሚመክሩ የሚያስተምህሩ አባትን መለየት እጅግ ከባድ ነው። እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ቀኝ ያኑርልን። ለእኛም መካሪ አስተማሪ አባት ይስጠን።

 20. Daneil Reta January 3, 2015 at 3:00 pm Reply

  May God accept our father soul!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: