ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ አገዱ

 • በአድባራት አለቆች ላይ የተላለፈው ውሳኔ ‹‹ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነው››/ፓትርያርኩ/
 • ‹‹ቤተ ክርስቲያናችን በቂ ሕገጋት አሏት፤ማእከሉ ተጠብቆ ሊሠራባቸው ይገባል፤››/ቅ.ሲኖዶስ/
 • ልዩ እና አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ስለ መጥራት ምክክር መደረጉ ተጠቁሟል

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፸፱፤ ታኅሣሥ ፲፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

addis admasየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ‹‹በቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና በሰጠችው ማኅበር ላይ ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ባላቸው በአንዳንድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት አስተዳዳሪዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አፈጻጸም ‹‹ሕገ መንግሥቱንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር ነው›› በሚል በፓትርያርኩ መታገዱ ተገለጸ፡፡

ፓትርያርኩ ኅዳር 30 ቀን በቁጥር ል/ጽ/126/300/2007 ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ ‹‹አፈጻጸሙ እንዲቆይ›› በማለት ያገዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተካሔዱ ጉባኤዎች÷ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል፤ ይህም አነጋገር ጉባኤውን ቅር አሰኝቷል፤›› ያላቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ቀርበው ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው በአንድ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በመንበረ ፓትርያርክና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሾች በተካሔዱት ስብሰባዎች የቀረቡት ሐሳቦች ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን መልካም አስተዳደርና ወቅታዊ ችግሮች›› የተመለከቱ የጉባኤተኞች አስተያየቶችና ሐሳቦች እንደነበሩ ያስታወሱት ፓትርያርኩ፣ በአጀንዳውና በተከፈተው ውይይት ተሰብሳቢዎቹ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን በግልጽ መናገራቸውና ከዚኽ በመነሣት አሉ ተብለው የታመነባቸው ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ‹‹በዓለም አቀፍ ደረጃም ኾነ በሀገራችን ለሕዝብ የተፈቀደ ዴሞክራሲያዊ መብት መኾኑ የሚያጠያይቅ አይኾንም›› ብለዋል፡፡ በስብሰባዎቹ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን በግልጽ ያቀረቡ ሰዎችን መገሠጽና መውቀስም ‹‹ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ይመስላል›› ሲሉ ነው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ አፈጻጸም እንዲቆይ ያስታወቁት፡፡

ጉባኤዎቹ በቤተ ክርስቲያን ጠሪነት የተካሔዱ እንደነበሩና ተሰብሳቢዎቹም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት፣ አገልጋዮችና ሠራተኞች መኾናቸውን ፓትርያርኩ ጠቅሰው÷ የጎደለው እንዲሟላ የጠመመው እንዲቃና ያላቸውን አስተያየት በማቅረባቸው ተግሣጽና ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ቅዱስ ሲኖዶሱ ያሳለፈው ውሳኔ ‹‹የስብስባ ነፃነትንና መብትን ነፍጎ ሐቁ እንዳይነገር›› የሚከለክልና ውጤቱም‹ጊዜ ያለፈበትን አፈና በማንገሥ ችግሮች ካሉበት ተባብሰው እንዲቀጥሉ ማድረግ ነው›› ብለዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ‹‹የዳኅፀ ልሳን ወለምታ አጋጥሞም ከኾነ በወቅቱ ማብራሪያና ማስተካከያ ይሰጥበታል እንጂ እንደ ከባድ ጥፋት ተቆጥሮ ሰዎች ሊገሠጹበትና ሊወቀሱበት አይገባም፤ ሕግም አይፈቅድም፤›› ሲሉ ገልጸዋል – በደብዳቤአቸው፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ያላቸው አንዳንድ የአድባራት አስተዳዳሪዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ቀርበው ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው ያሳለፈው ውሳኔ ‹‹ሕግንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር›› ብቻ ሳይኾን ‹‹ትልቁን ጉባኤ በታሪክና በሕግ ዐዋቂዎች ዘንድ ግምት ውስጥ የሚጥለው እንዳይኾን›› ያስጠነቀቁት ፓትርያርኩ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ ዳግመኛ በጥልቀትና ከሕግ አንጻር ፈትሾ ሊያጤነው ስለሚገባ አፈጻጸሙ እንዲቆይ እንዲደረግ ለመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡


ቅዱስ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤ ስብሰባው ውሳኔውን ያሳለፈው በሙሉ ድምፅ ተስማምቶ እንደኾነ ውሳኔው የሰፈረበትና በቁጥር 83/187/2007 በቀን 8/3/2007 ዓ.ም. ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በተጻፈ ሸኚ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የተላከው የጥቅምት 21 ቀን ቃለ ጉባኤው ያስረዳል፡፡ በጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የሚመራው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በዚኹ መነሻነት ውሳኔው ተግባራዊ እንዲደረግ በቁጥር 1374/11/19/2007 በቀን 18/3/2007 ዓ.ም. በአድራሻ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ቢያስታውቅም አፈጻጸሙ በፓትርያርኩ መታገዱ ታውቋል፡፡ በቃለ ጉባኤው የሰፈረው የምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ ሙሉ ቃል የሚከተለው ነው፤

‹‹ቤተ ክርስቲያናችን በቂ ሕገጋት አሏት፡፡ እነዚኽ ሕገጋት ማእከሉ ተጠብቆ ሊሠራባቸው ይገባል በማለት ጉባኤው በሰፊው ተወያይቶ፣ በቃለ ዐዋዲው ሕግና ደንብ መሠረት በደረጃው ማለትም ውሳኔ የተሰጠው ከኾነ በይግባኝ ታይቶ መምጣትና ይህን ተከትሎ መሠራት እንዳለበት አምኖበታል፡፡ እንዲኹም ቀደም ሲል በጠቅላይ ቤተ ክህነትም ኾነ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በተደረጉ ጉባኤያት አንዳንድ የደብር አስተዳዳሪዎች ተገቢ ያልኾነ ቃል ስለተናገሩና ይህ አነጋገር ጉባኤውን ቅር ያሰኘው በመኾኑ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ቀርበው ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው ሲል ምልአተ ጉባኤው በአንድ ድምፅ ተስማምቶ ወስኗል፡፡››


‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› የተባሉት የአድባራት አስተዳዳሪዎች በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙና አዲስ አበባም የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ቢኾንም ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ኹሉ የበላይ አካል በኾነው በቅዱስ ሲኖዶስ የወጡ ሕጎችን፣ የተላለፉ መመሪያዎችንና የተሰጡ ውሳኔዎችን ለሚመለከታቸው አካላት በፊርማቸው ከማስተላለፍ ጀምሮ በተግባር ላይ መዋላቸውን የመከታተልና የመቆጣጠር ሓላፊነቶች ያሉባቸው በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሙሉ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈውን ውሳኔ አፈጻጸም የማገድ ሥልጣን እንደሌላቸው ተገልጧል፡፡ እንደ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋጌ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጽ/ቤትም ተጠሪነት ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በመኾኑ የቅዱስ ሲኖዶሱን መመሪያዎችና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕገጋት መፈጸምና ማስፈጸም እንደሚጠበቅበት ተመልክቷል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ በራስዋ ሕግና ሥርዐት የምትመራበት የበላይ ሕግ÷ ሕገ ቤተ ክርስቲያን እንደኾነና በሕጉ መሠረት የምታስተዳድራቸውን ካህናትና ምእመናን የምትቆጣጠርበት፣ ለሚፈጸሙ ጥፋቶችና በደሎችም የቅጣትና የእርምት ርምጃ የምትወስድበት ደረጃውን የተከተለ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ የዳኝነት ሥልጣን እንዳላት ተጠቅሷል፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ የዳኝነት ሥልጣንም በቅዱስ ሲኖዶስ የሚወሰኑ ውሳኔዎች የመጨረሻ ውሳኔዎች እንደኾኑ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ሰፍሯል፡፡ በፓትርያርኩ ደብዳቤ ‹በቤተ ክርስቲያን ጠሪነት የተሰበሰቡ ናቸው› በተባሉት ጉባኤያት የቀረቡት ሐሳቦችና አስተያየቶች በቃለ ዐዋዲው ሕግና ደንብ መሠረት ደረጃቸውን ጠብቀው ያልቀረቡ መኾናቸውን የተቸው ቅዱስ ሲኖዶሱም ‹‹ቤተ ክርስቲያናችን በቂ ሕገጋት አሏት፤ እነዚኽ ሕገጋት ማእከሉ ተጠብቆ ሊሠራባቸው ይገባል፤›› በማለት በውሳኔ ቃለ ጉባኤው አሳስቦ ነበር፡፡

የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ የማስፈጸምና አፈጻጸሙን የመከታተል ሓላፊነት ያለባቸው ብፁዕ ዋና ጸሐፊው፣ ፓትርያርኩ አፈጻጸሙ እንዲቆይ ያስታወቁበት ደብዳቤ በጽ/ቤቱ በኩል በግልባጭ የደረሳቸው ሲኾን በቋሚ ሲኖዶስ አባላትና በአንዳንድ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድም በፓትርያርኩ የሕገ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ጉዳይ ልዩ እና አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ስለመጥራት ምክክር መደረጉ ተጠቁሟል፡፡

corrupts and day light robbersለቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መነሻ ከኾኑት ጉባኤያት በተለይም መስከረም ፳፯ ቀን ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ›› በሚል ርእስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ በፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ የተመራውና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች የተካፈሉበት ስብሰባ ተጠቅሷል፡፡

ተሰባሳቢዎቹ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ጠቃሚ ነው ብላ ላመነችበት አገልግሎቱ ዕውቅና ሰጥታ በተለያዩ አግባቦች የምትቆጣጠረውን ማኅበር÷ ‹‹ፈጣሪ የለም ይላል፤ አሸባሪና አክራሪ ነው፤›› እያሉ ከዓለም አቀፍ ጽንፈኞች ጋራ እያስተካከሉ መወንጀላቸው አግባብነት እንደሌለው በግልጽ ያስቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ የማኅበሩ አባላት የቤተ ክርስቲያን ልጆች፣ ኹለንተናዊ አገልግሎቱም ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ እንደኾነ አረጋግጦ ሊያሠራው በሚያስችል ሕግ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው በውሳኔው አስታውቋል፡፡

ውይይቱ በሒደቱ ከተያዘለት ርእስ በጠበበና ይልቁንም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ አነጣጥረው ይሰነዘሩ በነበሩ አስተያየቶች የተመላ እንደነበር የሚገልጹ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ የመድረኩ አያያዝ አስቀድሞ ለተቆረጠ አጀንዳ ሕጋዊ ልባስ ለመስጠትና በአድማው ለተለዩ ሰዎች ብቻ የተፈቀደ እንጂ ፓትርያርኩ እንዳሉት ሐቁ የተገለጸበትና ነፃ እንዳልነበር ተናግረዋል፡፡ ‹‹ቆራጣ ደብዳቤ ይበቃዋል፤ ከመንግሥት ጋራ በመተባበር እስከ ጫፍ አድርሱልን፤ በቶሎ ቁረጡት›› ማለት፤ ሊቃነ ጳጳሳቱንም ‹‹ከፈለጉ ቆባቸውን አስቀምጠው ወደዚያው ይግቡ›› እያሉ ማቃለላቸውና መዝለፋቸውስ በምን መመዘኛ ነው ዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ የሚኾነው በማለት ተሳታፊዎቹ ይጠይቃሉ፡፡

ፓትርያርኩ በተሾሙበት ቀን በፈጸሙት ቃለ መሐላ፣ የኹሉም አባት(አበ ብዙኃን) ኾነው ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ጠብቀው ያለአድልዎ መምራት ሲገባቸው፣ ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱን ቅር የሚያሰኝ ያልተገባ ቃል ተናግረዋል›› የተባሉት የአድባራት አስተዳዳሪዎች ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው ምልዓተ ጉባኤው በአንድ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈውን ውሳኔ አፈጻጸም በሌላቸው ሥልጣን ማገዳቸው÷ በቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አመራር፣ በካህናቱና በምእመናኑ ዘንድ መንፈሳዊ አባትነታቸውንና ታማኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው እንደሚኾን አሳስበዋል፡፡

ፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን በመጣስና የቅዱስ ሲኖዶሱን ሥልጣን በመፃረር የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ አፈጻጸም ያገዱበት ደብዳቤpat ab mathias banned holy synod decision pat ab mathias banned holy synod decision02

 

 

Advertisements

19 thoughts on “ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ አገዱ

 1. Anonymous December 20, 2014 at 8:48 pm Reply

  Abune Matias gobez nachew. Enkuanem be video askeretsut. Papasat kobachewen askemtew yehidu mahberum yekortena yetal yale menem yelem. Be adebabay lemen yewashal? Egziabher betekerestianen yetebekelen. Betam yasaznal.

 2. […] Source:: haratewahido […]

 3. Bisrat December 20, 2014 at 9:57 pm Reply

  Enante tsehaftena ferisawyan efugnetoch……biketuachew erasachew sebseba tertew ketuachew belachu tamuachewalachu….bayketuachew lemen alketuachewem belachu tamalachu. Kefu nachehu !

 4. Ameha December 20, 2014 at 10:07 pm Reply

  The letter seems right. Abune Matias is right, I say.

 5. Abel December 20, 2014 at 10:16 pm Reply

  Hara Tewahedo….and all other blogs…………EGZIABHER YEKER YEBELACHU. EGZIABHER YEKER YEBELACHU. EGZIABHER YEKER YEBELACHU. Yemetaderguten atawkumena EGZIABHER YEKER YEBELACHU.

 6. Wolde-Tinsaie December 21, 2014 at 8:15 am Reply

  “የዘፈን ዳር ዳሩ እስክሳ ነዉ”ይባላል፡፡
  ምንድን ነዉ ነገሩ? ሰዉየዉ. . .፤ እንዴት ነዉ አካሄዱ? ዉሳኔዉ ሲወሰን በቦታዉ አልነበሩምን?
  ቤተክርስቲያናችን መፅሀፍ ቅዱሳዊ የሆነ የራሰዋ ስርትና ህግ አላት፡፡ ይህም ዓለም ዲሞክራሲ ከሚለዉ በላይ የሆነ ነዉ፡፡ የቤተክርስቲያኒቱን ህግ መፃረር ምን ማለት ነዉ? ይህ ነገሮች በጣም እየተበላሹ እንደሆነ ምልክት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ነገ ግብረ ሶዶም ዲሞክራሲያዊ መብት ነዉ ሊባል ነዉ፡፡ ያ ማለት መፅሃፍ ቅዱስ ስህተት ነዉ ብሎ ማሰብና ማስፈፀም ነዉ፡፡ አካሄዳቸው ወዴት ነዉ?
  እግዚአብሄር ይርዳን ክፉውን ያርቅልን!
  የእዉነት አምላክ በቸርነቱ ምህረቱንና ሰላሙን ይስጠን! የአብርሃም አምላክ የቅዱሳን ሃዋርት አምላክ የፃድቃንም አምላክ ከክፉው ያንጻን በዕምነታችን ያጽናን አሜን!

 7. Amsalu g/kidan December 21, 2014 at 8:39 am Reply

  አቦይ ማትያስ ኧረ አባክዎን እንዴ! ቤተክርስቲያን እኮ የምትተዳደረው በሰማያዊው ሕግ በሕገ እግዚአብሔር እንጅ በምድራዊውና የሰይጣን መልእክተኛ በሆነው በወያኔ ሕግ አይደለም! ሲጀመር የሲኖዶስን ውሳኔ ሊያግዱ የሚችሉበት ሥልጣን እኮ የለዎትም፤ ይሄ ሕገ ወጥነት ውንብድና አልበዛብዎትም? ነው ወይስ ባለፈው አብጃለሁ በጤናየ አይደለም ብለው ነበር አሁንም ጤናዎ አልተመለሰም? ጌቶችዎ እኮ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ብለዋል ታዲያ እርስዎ ቤተክርስቲያንን በወያኔ ሕግ አሥተዳድራለሁ የሚሉት ከየት አምጥተው ነው?

 8. Zekarias Micahel December 21, 2014 at 4:53 pm Reply

  abatochachn aetdaferu

 9. Anonymous December 21, 2014 at 5:05 pm Reply

  “የዘፈን ዳር ዳሩ እስክሳ ነዉ”ይባላል፡፡
  ምንድን ነዉ ነገሩ? ሰዉየዉ. . .፤ እንዴት ነዉ አካሄዱ? ዉሳኔዉ ሲወሰን በቦታዉ አልነበሩምን?
  ቤተክርስቲያናችን መፅሀፍ ቅዱሳዊ የሆነ የራሰዋ ስርትና ህግ አላት፡፡ ይህም ዓለም ዲሞክራሲ ከሚለዉ በላይ የሆነ ነዉ፡፡ የቤተክርስቲያኒቱን ህግ መፃረር ምን ማለት ነዉ? ይህ ነገሮች በጣም እየተበላሹ እንደሆነ ምልክት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ነገ ግብረ ሶዶም ዲሞክራሲያዊ መብት ነዉ ሊባል ነዉ፡፡ ያ ማለት መፅሃፍ ቅዱስ ስህተት ነዉ ብሎ ማሰብና ማስፈፀም ነዉ፡፡ አካሄዳቸው ወዴት ነዉ?
  እግዚአብሄር ይርዳን ክፉውን ያርቅልን!
  የእዉነት አምላክ በቸርነቱ ምህረቱንና ሰላሙን ይስጠን! የአብርሃም አምላክ የቅዱሳን ሃዋርት አምላክ የፃድቃንም አምላክ ከክፉው ያንጻን በዕምነታችን ያጽናን አሜን!

 10. Anonymous December 22, 2014 at 4:19 am Reply

  Ark bishop Matyas where you go? you have to think every things beside of you ? please don’t guided by some one . you have to walk your selves. it is the above written letters not yours ;that is the stolen people idea. don’t follow them otherwise we will know the way to remove you within your wyane .you know ? you proud is weyane . ta Kare

 11. Anonymous December 22, 2014 at 7:20 am Reply

  gudi sayisama ayikerim yebetekiristiann wusane yesewu mebti yemenekanewu kalun lene nistiros, lene ariyos,lene mekdeniyos…..mebti enyikomu ferahu!!!geta hoy yehen kemayat na kemesimat sewuren

 12. ሙሉጌታ December 22, 2014 at 5:17 pm Reply

  በተልዕኮ የተናገሩት ስለነበረ ላኪዎቻቸው ኃላፊነቱን ወሰዱ ማለት ነው። ፓትርያርኩ ስለሰብዓዊ መብትና ስለ ሕገ መንግሥት መብት ያወቁት ከዛ ከተበላሸ ስብሰባ በኋላ መሆኑ ነው እንደ እንደርሱ ከሆነ መልካም ነገር ግን ክፉዎች ሰውን ለመወንጀልና ለመግደል መብታቸውን ሳይሆን ጊዜ የሰጣቸውን ባለጊዜነት ተጠቀሙና ያሰቡት ሳይሳካ ቀርቶ በተራቸው ተዋራጅና ተጠያቂ ሲሆኑ ደግሞ መብት ሕገ መንግሥት ጅኒ ጃንካ ይላሉ። ጊዜ የሰጠው ቅል አሉ። እንዚህ ጳጳሳት ቢሰርቁ አይጣየቁ፣ ቢዋሹ አይፈተሹ፣ ቢቀሙ ለፍርድ አይቆሙ፣ ቢወሰልቱ በጉባኤ አይረቱ ሆነኮ ነገሩ። መቼ ይሆን ተጠያቂነት በሃገራችን ሰፍኖ የምናየው።

 13. Anonymous December 22, 2014 at 10:46 pm Reply

  ጽ/ቤቱን ወያኔ፤ የሚጨማለቅበት ስለሆነ ብዙም አይደንቅም …
  ግን “አባቶች” ስለ ሕገ-መንግስት፤ ዴሞክራሲና ግለሰባዊ መብት ሲሰብኩ ማየት ያሳዝናል… መዝቀጥ!
  ለሁሉም ግን ጊዜ አለ!!

  ሳሙኤል/ ቴክሳስ

 14. shambel December 23, 2014 at 9:55 am Reply

  አቡነ ማትያስ እንደዚህ ሊጽፉ አይችሉም፤፤አማርኛን በሚገባ አስተካክለዉ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ሰዉዬ እንዲህ ከቶዉኑ ለጽፉ አይችሉም፤፤ስለ ህገ መንግስትስ ተምረዋል ማለት ነዉ?; ከሆኔስ መቼ?;
  ቤተክርስቲያንን በምድራዊ ህግ ለመግዛት የሚያስብ ፓትሪያርክ፤፤ ለፈደራል ጉዳዮች ግልባጭ ማድረጉሳ?

  የፈደራል ጉዳዮችስ ደብዳቤዉ እንደደረሳቸዉ ምን አሉዋት? ጎበዝ አሉዋት? ቡራኬዋ ይድረሰን አሉዋት? ስልጣንዋን ከፈለጉ አዋ ለእነሱ መስራት ነዉ የሚያዋጣዋት፡፡

  • Anonymous February 16, 2017 at 6:20 am Reply

   Ehmmm

 15. fokariwu December 23, 2014 at 10:01 am Reply

  አቡነ ማትያስ እንደዚህ ሊጽፉ አይችሉም፤፤አማርኛን በሚገባ አስተካክለዉ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ሰዉዬ እንዲህ ከቶዉኑ ለጽፉ አይችሉም፤፤ስለ ህገ መንግስትስ ተምረዋል ማለት ነዉ?; ከሆኔስ መቼ?;
  ቤተክርስቲያንን በምድራዊ ህግ ለመግዛት የሚያስብ ፓትሪያርክ፤፤ ለፈደራል ጉዳዮች ግልባጭ ማድረጉሳ?

  የፈደራል ጉዳዮችስ ደብዳቤዉ እንደደረሳቸዉ ምን አሉዋት? ጎበዝ አሉዋት? ቡራኬዋ ይድረሰን አሉዋት? ስልጣንዋን ከፈለጉ አዋ ለእነሱ መስራት ነዉ የሚያዋጣዋት፡፡

 16. Getu Bekele December 23, 2014 at 11:24 pm Reply

  Kidusnetachew yewesedut ye ermt rimga abatawi ena ye betkrstian aderan bagenazebe melku new; Btsuan abatochm ye kedmo wsaneyachewn dagm bemayet ye kdusnetachewn wsane endemiatsenut tesfa alegn. Bemtshf kidus endmnmeleketew Egziabher Israelyawyanin.ynenewe hizbin liyatefa kewesene behuala eko melso mrowachewal; Kdusnetachew le menfes lijochachew bemaseb endybetenu besachew mikrna amerar litebku mewsenachew abatawiu gdetachewn kemewetat ye meneche silehone likeberu enji litechu aygebam.kdusneto Ye Ethiopia Amlake regme edmen ke tenana ke selam gar ystot. Akbariwo Lijo Dn. Getu Bekele Ze kefa we Bonga

 17. rabise December 27, 2014 at 1:14 pm Reply

  በመንበረ ፓትርያርኩ ቅ/ማርያም ገዳም በሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ መመዝበሩ ተገለጸ፡፡

  ********
  ቤተክርስቲያን በፓትሪያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በሚመራ የሙስና ሰንሰለት በጠራራ ጸሐይ እየተዘረፈች ነው፡፡

  ********
  በምዝበራው ላይ አንዳንድ የመንግስት የደህንነት አካላት እጅ እንዳለበት በሰፊው እየተገለጸ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ፡-
  – በቅድስት ልደታ (ሜክሲኮ) ፡- ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ተመዝብሯል፣ በቅዱስ ዑራኤል (ካዛንችስ) ፡- በብስራተ ገብርኤል (ሳርቤት)፣ በግቢ ቅዱስ ገብርኤል (አራት ኪሎ)፣ በሳእሊተ ምህረት (ሲኤምሲ)፣ በቅዱስ ተክለሀይማኖት (መርካቶ)፣ በቅዱስ ሚካኤል (አዲሱ ሚካኤል አቶቢስ ተራ) … በድሬደዋ ቅዱስ ገብርኤል፣ እና በሌሎችም አድራራትና ገዳማት በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠ ከፍተኛ የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት መዘረፉን ምዕመናን፣ ካህናትና ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት በተለይመ ብጽዕ አቡነ እስጢፋኖስ መግለጻቸውና ከሀገረ ስብከቱ በፓትሪያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በሙስና ቡድን አደራጅነት መነሳታቸው የሚታወቅ ነው፤ እንዲሁም ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዲስ የለውጥና የአሰራር ስትራቴጂ ዕቅድ ተጠንቶ በስራ ላይ እንዳይውል “በፓትርያርኩ”፣ በንቡረ ዕድ ኤልያስና “አባ” ሰረቀ…የሙስና አንጃ መደናቀፉ የሚታውቅ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በፓትሪያርኩ ቀጥታ ተጠሪነት የሚተዳደረውና የሙስና አማሳኞች መንበር በሆነው የአራት ኪሎ ቅድስተ ማርያም ገዳም በብዙ ሚሊዮኖች ብር የሚገመት የቤ/ክ ሀብትና ንብረት መመዝበሩ ተረጋግጧል፡፡
  የገዳሟ የገንዘብ አያያዝና የንብረት አጠቃቀም በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር ታዝዟል፤ የሥራ ዘመኑ ያለፈው ሰበካ ጉባኤ ለገዳሙ ልማትና ለኦዲቱ ዕንቅፋት ሆኗል ተብሏል፡፡
  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ የፓትሪያርኮች መንበር (መንበረ ፕትርክና) በሆነችው ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብና ንብረት በአስተዳደር ኃላፊዎችና ሠራተኞች መመዝበሩን ማህበረ ካህናቱ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ የቤተክርስቲያ ሀብትና ንብረት ዝርፊያ ይቁም በሚሉ አገልጋይ ካህናቱና ዳያቆናቱ ላይ እናንተ “ማህበረ ቅዱሳንና ግንቦት ሳባት ናችሁ፣ የግንቦቱን የመንግስት ምርጫውን ለማወክ ትንቀሳቀሳላችሁ፣ ወደ ሌላ ደብር እናዛውራችኅለን፤” በሚል ከሚያደርሱባቸው ዛቻና ማስፈራራት እንዲቆጠቡ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋል፡፡
  ስለዚህ ሁላችንም ስለ እምነቶ ኃላፊነታችን እንድንወጣ የቤተክርስቲያን አምላክ ይርዳን፡፡

 18. Anonymous December 27, 2014 at 10:31 pm Reply

  I say for all who writing thir comment, respect our fathers. But, tell their weak sides based on
  administration. they have enough knowledge. the question is where and to whom they use their knowledge? we gonna ask our patriarch:
  -Abune Puwulos flight ROME for funeral of pope PUL ,Jima christian Mrtires at these time
  before his flight but until his death he never said any thing.Instead he preaching about DEMOCRACY and HIV
  -waldiba monks and Lands lutng by gov,t force abune paulos keep quite and his successor
  MATIAS TOO.WHEN CAN you Talk aout our church abune MAtias FOR THIS GOV,T?
  -Last week BAHREDARE CHRSTIANS MARTIRES for thir religion what have yuo said abut this?
  when our patriarch not standing for our religion depending to tewahido it,s qustionabel to say our father?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: