ቅ/ሲኖዶስ: በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ የተሐድሶ መናፍቃን ፈተናና በጋምቤላ የጸጥታ ችግሮች ጉዳይ ውሳኔ አሳለፈ

በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ የተሐድሶ መናፍቃን (አላውያን) ድርጅቶችና ግለሰቦች አስተዳደራዊ ችግርንና ጎሳዊ ርእዮታዊ ጥላቻን ሰበብ በማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንን ከሕዝቡ ነጥሎ ለማዳከም በኅቡእ እና በገሃድ የሚያራምዱትን ክሕደት በትምህርት ማረም እንዲኹም የመከፋፈልና የጥላቻ ዘመቻቸውን ማጋለጥ ጠንካራ የጋራ መግባባትና አቋም ተይዞበታል፡፡

በምልመላና ቅበላ ክፍተት ሳቢያ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን የትምህርት ተቋማት ሰርገው ገብተው እንጀራዋን እየበሉ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅ ድርጅቶች እንደሚሠሩ የተጠረጠሩ ተቋማቱንና ብዙኃን ደቀ መዛሙርቱን የማይወክሉ ግለሰቦች ጉዳይ ተጣርቶ ለውሳኔ የሚቀርብበት አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

his-holiness-abune-henok-nashhvi

ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፤ የምዕራብ ወለጋና አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (ፎቶ: ናሽቪል ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት)

በተለይ በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ አህጉረ ስብከት ብሔራዊት፣ ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የኾነችውን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነትን ‹‹የምኒልክ ሃይማኖት›› እያሉ የአንድ አካባቢ በማድረግ ሕዝቡን ለሚከፋፍሉ የተሐድሶ አላውያንና የጎሰኝነት ርእዮታዊ ጥላቻ አራማጆች ምላሽ የሚሰጥ እና ምእመኑን በእምነቱና በአንድነቱ የሚያጸና መጠነ ሰፊ ስምሪት ይካሔዳል፡፡

በምዕራብ ወለጋና አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ የሚመራ ሀገር አቀፍ ትብብር ይቋቋማል፤ በአህጉረ ስብከቱ በጥቂት አባወራዎች የሚጠበቁ የገጠር አብያተ ክርስቲያንይረዱበታል፤ ምእመኑን በቋንቋው የሚያስተምሩ ሰባክያነ ወንጌል ይመደባሉ፤ መጻሕፍትና በራሪ ወረቀቶች ይዘጋጃሉ፡፡

his grace abune filpos, archbishop of Illubabor and Gambela

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ፤ የጋምቤላ እና ኢሉባቦር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

በጋምቤላ ካህናትና ማእመናን ለኅልፈተ ሕይወት በተዳረጉበትና በእርስ በርስ ግጭት ለተጎዱ ኹሉም ወገኖች ጸሎት የምታደርግበትንና የሰላም መልእክቷን የምታደርስበትንከኑሯቸው ለተፈናቀሉትም ድጋፍ የምታደርግበትን የማስተባበር ሥራ ትሠራለች፡፡

ቤተ ክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠረታት በምድር ያለች መንግሥተ እግዚአብሔር እንደመኾኗ መጠን ስለ ሀገርና ስለ ሰላም ትጸልያለች፡፡ ሕዝቦች በፍቅር፣ በሰላምና በአንድነት እንዲኖሩና ወደተሻለ የኑሮ ደረጃ እንዲደርሱ በተለይም የድኾች ወገኖች ችግር እንዲቃለል ከበጎ አድራጊዎች ጋራ በመተባበር ያልተቆጠበ ጥረት ታደርጋለች፡፡ በሰዎች መካከል የሚፈጠር የእርስ በርስ አለመግባባትና ግጭት እንዲኹም በሕዝቦች መካከል ጦርነት እንዳይኖር የማስተማርና የማስታረቅ ሓላፊነት አለባት፡፡ በአጠቃላይ በምትመራበት ሕግ መሠረት÷ የሀገር ሰላም፣ አንድነትና ዕድገት፤ የወገን ነፃነትና ብልጽግና፤ ለሰው ልጆች እኩልነትና ፍትሕ ርትዕ እንዲሰፍን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተልእኮዋን ታከናውናለች፡፡

Advertisements

7 thoughts on “ቅ/ሲኖዶስ: በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ የተሐድሶ መናፍቃን ፈተናና በጋምቤላ የጸጥታ ችግሮች ጉዳይ ውሳኔ አሳለፈ

 1. Abebe November 4, 2014 at 10:45 am Reply

  you don’t have a chance to manuver in the name of religion in Wollega. Of course Orthodox and the green, yellow and red colored flag are brought to the Oromo people by Menilik

  • ቢቂላ November 4, 2014 at 4:46 pm Reply

   ወዳጄ አበበ በመጀመሪያ ደረጃ በዛ ዘመን ኖረህ እንኳን ቢሆን እውነቱን ትረዳ ነበረ ነገር ግን አልኖርክም ሌላው ይቅር ቅርሻትህን ከማግሳትህ በፊት አስብ ፥ታሪክን አገላብጥ፥ የዛሬ ባለግዜዎች የሚነፉትን ቱልቱላ ትተህ ሀገራችን ኢትዮጵያ ማን ነበረች የሚለውን መርምር ::የጥላቻ መንፈስህን አስወግድ ፥እኔ ከአያቴ ከዛሬ ሃያ በፊት ብዙ ነገር በቃል ተነግሮኛል(ያረፈው በ መቶ አስራ ሁለት ዓመቱ ነው) አንተና መሰሎች የምትነግሩኝን አይደለም የነገረኝ::

  • Kestedemena November 4, 2014 at 9:49 pm Reply

   On this century, when I heard such primitive and bull thinking, my heart feel with pain and sickness. Our people were living and sharing goods and bad things for centuries, they can also share religion, culture, flag and …. What’s wrong with that? Please the so called nationalist, don’t be a narrow minded one, think widely and globally. How can you dare to represent million people with your bullshit thinking? Land is belongs to GOD, don’t be proud with the soil, that is not yours and you will be part of that tomorrow. Those illiterate and sick minded person are always thinking and sinking wrongly. My friend, how can you speak about the case of 150 years as if you were the man of that time? Please don’t float with fabricated stupid politics that will not be bread for you, it will be stone for you, you will be hammered by that. Please don’t be like a camel as for how many years are you raided by the stupid one? wake up like human being. I just consider such thinking as a none sense, rotten mind like you don’t care and respect others, you are a narrow minded and short sighted one. Wish your ill heart to be shower with peace, love, respect, tolerance, forgiveness and healthy thinking. Please don’t vomit your toxic words in a blessed areas.

  • Anonymous November 7, 2014 at 1:25 pm Reply

   መናፍቅ ወይም ተሃድሶ መሆንህን ካመንክ ሌላውን ለማሳደድ አትሂድ ነው የተባለከው። የሚገባህ ከሆነ! ያልተፃፈውን አታንብብ ።
   ታሪክ ብታውቅ ጥቅሙ ለራስህ፣ ባታውቅ ጉዳቱ ለራስህ፣ ሰለእርሱ ማንም አያገባውም። ግን ምንም እምነት ይኑርህ በድንበርህ ኑር! ቅድስት ተዋህዶ ቤተክርስትያን ልጆችዋን ለመንጠቅ የሚመጣባትን የምንም አይነት እምነት ተከታይ ነኝ ባይ ድንበሩን እስከዘለለ ድረስ ዝም ብላ አታይም። ጦር ጋሻ ባትመዝም የመንፈስ ጠላቶቿን በወንጌል ትዋጋለች። ይህ የሚኒሊክ ጉዳይ አይደለም የፈጣሪ እና የፍጥረቱ ጉዳይ ነው እና ከመናገርህ በፊት ጭንቅላትህ ያስብ።

 2. Anonymous November 4, 2014 at 1:59 pm Reply

  please read history!don’t be narrow minded. How could you get to the truth with hatred heart? jibbi minilik dhugaa sijalaa dhoksee akka hin hafne lapheekee baniitii dhugaa barbaadi.

 3. Anonymous November 4, 2014 at 2:27 pm Reply

  @ Abebe; Simply Racist!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: