ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ: ማኅበረ ቅዱሳን እየተመራበት ባለው መተዳደርያ ደንቡ እስከ መጪው ግንቦት እየሠራ እንዲቆይ ወሰነ፤ የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ በአዲስ መልክ ተሻሽሎ ይዘጋጃል

mahibere kidusan logo

 • የመተዳደርያ ደንቡን ማሻሻያ ረቂቅ ለግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አዘጋጅቶ የሚያቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
 • ማኅበሩ በጊዜአዊነት በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ለመምሪያው የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ተጠሪ ኾኖ አገልግሎቱን በመፈጸም ይቆያል፡፡
 • ጠቅላይ ቤቴ ክህነቱ ዘመናዊውን የኹለትዮሽ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐት መከተሉ ማኅበሩ ከፋይናንስ ሥርዐቱ ጋራ የሚጣጣሙ የሒሳብ ሰነዶችን ለመጠቀም ያስችለዋል፡፡
 • የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት መመዘኛ ሕግ ጸደቀ፤ በመጪው ግንቦት የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንደሚፈጸም ተጠቁሟል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ፣ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ዐሥራ አንደኛ ቀን ውሎው፣ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅና ከአገልግሎቱ ጋራ በተያያዘ ስለተፈጠሩ ችግሮች ከተወያየ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡

በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ እንደተመለከተው÷ የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ አገልግሎቱ ከደረሰበት ዕድገትና ከወቅቱ ኹኔታ አንፃር እንዲሻሻል በተላለፈው ውሳኔ መሠረት ደንቡን አጥንቶ የሚያሻሽል በኹለት ብፁዓን አባቶች የሚመራና አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ሠይሟል፡፡

የአጥኚ ኮሚቴውን የደንብ ማሻሻል ሥራ እንዲመሩ የተመደቡት ኹለቱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት÷ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስና የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳዳርና ልማት ድርጅት የበላይ ሓላፊ፤ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ናቸው፡፡ ከኹለቱ ብፁዓን አባቶች ጋራ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመደቡ ሦስት አባላት እንደሚኖሩ ታውቋል፡፡

አኹን የማኅበሩን መተዳዳርያ ደንብ ስለማሻሻል የተሠየመው አካል ለኹለተኛ ጊዜ የተቋቋመ ሲኾን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ባሳለፈው ውሳኔ÷ ድርጅታዊ መተዳደርያ ደንቡን አጥንተው እንዲያቀርቡ አምስት ብፁዓን አባቶችን፣ የሕግ ባለሞያዎችንና የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን ያካተተው ዐሥራ አንድ አባላት ያሉት ኮሚቴ የመጀመሪያው ነበር፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ በቀደመው የግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. ውሳኔው መሠረት፣ የተሻሻለው ደንብ ረቂቅ ለጥቅምት ፳፻፭ ዓ.ም. መቅረብ ሲገባው ዘግይቶ በ37 አንቀጾችና በ33 ገጾች ተጠናቅቆ ላለፈው ዓመት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንዲጸድቅ በአጀንዳነት ተይዞ ነበር፡፡ ይኹንና አጥኚ ኮሚቴው ሥራውን ካጠናቀቀ በኋላ በፓትርያርኩ በኩል የረቂቁ አንድ አንቀጽ ኾኖ ሳይጨመርና ሳይቀነስ እንዳለ እንዲገባ ለኮሚቴው ሰብሳቢ በአድራሻ ያስተላለፉትና ‹‹የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከወሰነው ውሳኔ ጋራ የማይሔድ ነው›› የተባለው 24 ነጥብ መመሪያ በፓትርያርኩና በኮሚቴው አባላት እንዲኹም በፓትርያርኩና በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል ልዩነት በመፍጠሩ ያለውሳኔ አድሮ ነበር፡፡ ለወራት የተደከመበት የማኅበሩ የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ ሳይጸድቅ ሌላ አጥኚ ኮሚቴ ለኹለተኛ ጊዜ እንዲሠየም ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያትም ከዚኹ ልዩነት ጋራ የተያያዘ እንደኾነ ተገምቷል፡፡

የልዩነቱ ዋነኛ መንሥኤ የኾነው በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሞዴላሞዴሎች መጠቀምን በመሠረቱ ማኅበሩ የተቀበለው ቢኾንም ሐሳቡ የማኅበሩን የገንዘብና የንብረት እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እስከኾነ ድረስ ለውሳኔው አተገባበር የጠቅላይ ቤተ ክህነታችን የሞዴላሞዴል አሠራር(የነጠላ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ) ከማኅበሩ የኹለትዮሽ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዓት ጋራ የተጣጣመ እንዲኾን ማኅበሩ ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጽ/ቤትና ከቁጥጥር አገልግሎት መምሪያው ጋራ ሲነጋገርበት ቆይቷል፡፡

ይኹንና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሦስት የበጀት ዓመታቱን በውጭ ኦዲተር ካስመረመረ በኋላ በተያዘው የ፳፻፯ ዓ.ም. በጀት ዓመት፣ እጅግ ኋላ ቀርና በዘመናዊ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐት ተቀባይነት የሌለውን የነጠላ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ በመተው የኹለትዮሽ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐት ለመከተል በመወሰኑ÷ ማኅበሩ በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት፣ ከፋይናንስ ሥርዐቱ ጋራ የተጣጣሙና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈቃድና ዕውቅና ያላቸው የገንዘብና የንብረት ገቢና ወጭ ሰነዶችን ለመጠቀም ምቹ ኹኔታ እንደሚፈጥርለት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት መምሪያም ፈቃድና ዕውቅና በሰጣቸው ሰነዶች ብዛትና የኅትመት ቁጥር ላይ ተመሥርቶ የሒሳብ ምርመራ(ኦዲት) አሠራሩን በተሻሻለ ደረጃ ለማካሔድ እንደሚያስችለው ተጠቁሟል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚኹ ጋራ በተያያዘ በዛሬው ዕለት ባስተላለፈው ውሳኔው፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን፣ መተዳደርያ ደንቡ በመጪው የግንቦት ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተሻሽሎ እስኪዘጋጅ ድረስ አኹን እየተመራበት ባለው መተዳደርያ ደንቡ እየተገለገለ እንዲቆይ ወስኗል፡፡

Mahibere Kidusan denb

የማኅበሩ የወቅቱ መተዳደርያ ደንብ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሐምሌ ፲ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ለሦስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የጸደቀ ነው፡፡ በብፁዓን አባቶች እርማት ተሰጥቶበትና ተስተካክሎ ምልአተ ጉባኤው በሙሉ ድምፅ ያሳለፈው ይኸው 43 አንቀጾች ያሉት ባለ36 ገጽ መተዳደርያ ደንብ÷ ማኅበረ ቅዱሳን ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ድረስ የተፈቀደለትንና የተወሰነለትን አገልግሎቱን የሚያቀናጅበትን፣ የሚመራበትንና የሚያስተባብርበትን መዋቅር ለመዘርጋት ያስቻለው ነው፡፡


ለማገልገልና ለመጽደቅ ነው የመጣነው፤ ከቤተ ክርስቲያናችን አልወጣንም፤ ልንወጣም አልመጣንም
???????????????????????????????

ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም፤ በመ/ፓ/አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ፴፫ኛው ዓመታዊ ስብሰባ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ

…በለሰለሰ አንደበት፣ ፍጹም በኾነ መንፈሳዊ ስሜት፣ ለዚኽ ጉባኤ አክብሮት በተመላበት አቋም ሐሳቤን ለመግለጽ እፈልጋለኹ፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን የተመሠረተው በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ነው፡፡ እኛ ያደግነው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ያሳደጉን ብፁዓን አባቶቻችን በዚኽ ጉባኤ አሉ፡፡ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት ውስጥ አድገን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ስንገባ በውጭ የማርክሲስት ሌኒንስት ፍልስፍና ወጣቱን ግራ እያጋባና ቤተ ክርስቲያንን እየተፈታተነ ነበር፡፡ በግቢ ውስጥ ደግሞ መናፍቃን የዋሁን ኦርቶዶክሳዊ እየተፈታተኑና እየነጠቁ ነበር፡፡ በእነዚኽ ፈተናዎች የቤተ ክርስቲያን ቅንዓት አቃጥሎን፣ አንገብግቦን እንዴት እንሰባሰብ፤ እንዴት ቤተ ክርስቲያናችንን እናገልግል፤ ምን እናድርግ ብለን ተሰበሰብን እንጂ በማኅበር ፍቅር አይደለም፡፡

እንዴት እናገልግል ብለን የመጣነውም ወደ አባቶቻችን ነው፤ ወደ ሌላ ወደየትም አልሔድንም፡፡ ወደ አባቶቻችን መጥተን÷ እንዴት እናገልግል፣ ሕግ ስጡን፤ መመሪያ ስጡን፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እቀፉን፤ ምከሩን አስተምሩን፤ በዚኽ ሒዱ በሉን ብለን ነው የቀረብነው፡፡ በዚኽ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ፣ እነዚኽ ልጆች በዚኽ በዚኽ ቢያገለግሉ ቤተ ክርስቲያንን ይጠቅማሉ ብሎ ሕግ ሰጠን፡፡ እኛ፣ መቼም ምንጊዜም፤ ዛሬም ወደፊትም ከቤተ ክርስቲያናችን ውጭ አልወጣንም፤ አንወጣም፤ ልንወጣም አልመጣንም፡፡ ስለዚኽ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሰጠን ሕግ ነው እያገለገልን ያለነው፡፡

ማኅበሩ ዕቅዱንና የአገልግሎት አፈጻጸሙን በየስድስት ወሩ ቀደም ሲል ለሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ፣ አኹን ለብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ያቀርባል፤ በየዓመቱ ደግሞ የሒሳብ አሠራሩን የውስጥ ኦዲተር አለው፤ በዚያ ያሠራል፤ የበለጠ ደግሞ በሕግ ተቀባይነትና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባላቸው ኦዲተሮች ኦዲት አስደርጎ ሪፖርቱን ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ያቀርባል፡፡

ባለፈው ጊዜ፣ ይህ የተከበረ ጉባኤ ተወያይቶ የወሰደው አቋም አለ፤ ማኅበረ ቅዱሳን በሞዴል መጠቀም አለበት የሚል አቅጣጫ ሰጥቶ ነበር፡፡ አጠቃላይ ጉባኤው እንዳበቃ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ደብዳቤ ጽፈውልናል፡፡ እኛም በተሰጠው አቅጣጫ ለመሥራት ፈቃደኞች መኾናችንን ገልጸናል፤ ነገር ግን የሒሳብ አሠራር ስለኾነ፣ የአሠራር ሒደት ስለኾነ ውሳኔው እንዴት እንደሚተገበር መመሪያ ይሰጠን ብለን ለብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ደብዳቤ ጽፈናል፡፡

ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትጠቀመው የነጠላ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ነው፤ ማኅበሩ የሚጠቀመው የኹለትዮሽ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐት ነው፤ ስለዚኽ ይህን የሚያስታርቅ ጥናት ይደረግና እንዴት እንደምንሠራ መመሪያ ይሰጠን ብለን ጠይቀናል፡፡ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁም ጥያቄአችንን ተቀብለው መመሪያ ሰጥተውናል፤ መመሪያውንም ተቀብለናል እንጂ አንታዘዝም አላልንም፡፡

ቅዱስ አባታችን÷ በእግዚአብሔር ፊትና በዚኽ ታላቅ ጉባኤ ፊት እውነት ነው የምናገረው፤ እኛ እናከብርዎታለን፤ አባታችን ነዎት፤ ለቅዱስ ሲኖዶሱም ለቅዱስነትዎም በአጠቃላይ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች ክብር አለን፡፡ ለማገልገል፣ ለመጽደቅ ነው የመጣነው እንጂ እያንዳንዳችን የራሳችን ኑሮ አለን፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በአወጣልን ሕግ፣ በሚሰጠን መመሪያ እየሠራን ነው ያለነው፤ ወደፊትም መታረም፣ መሻሻል አለባቸው በሚባሉ ነገሮች ላይ ተስማምተን፣ ታግዘን እናገለግላለን፡፡ 

እኛ የቤተ ክርስቲያን ችግርም አይደለንም፤ የማኅበሩ አባላት ‹‹ግንብ እየገነቡ ነው፤ ሀብት እያሸሹና እየተካፈሉ ነው፤›› የተባለው ነገር ይጣራ፤ መረጃው ይቅረብ፤ እንዲኽ ተብለን የተከሠሥነው እውነት ከኾነ እኛ ፍርድ መቀበል እንፈልጋለን፤ እንዲኽ ያሉትንም በሕግ  እንጠይቃለን፡፡ ፍርድ ይታይልን!! /የማኅበሩ ተወካይ በአጠቃላይ ጉባኤው ላይ ‹‹እስኪ ማኅበሩም በአንደበቱ ይናገር›› ሲሉ ባገኙት ጠባብ ዕድል ከተናገሩት/


በቅዱስ ሲኖዶስ የግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ውሳኔ÷ ማኅበሩ አኹን እየተመራበት ያለው ደንብ ተጠንቶ እስኪሻሻል ድረስ ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተለይቶ ተጠሪነቱ ለብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ኾኖ እንዲሠራ በተወሰነው መሠረት፡- የዓመት ዕቅዶቹን በዓመቱ መጀመሪያ እያሳወቀ፤ በየስድስት ወሩ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶቹን፣ በየዓመቱ መጨረሻ ደግሞ የሒሳብ ሪፖርቱንና ዓመታዊ የሒሳብ ምርመራ(የኦዲት) ሪፖርቱን እያቀረበ፤ በአእምሯዊ፣ ሞያዊና ፋይናንሳዊ አበርክቶው ከመምሪያዎችና ድርጅቶች ጋራ በትብብር እየሠራ በአጠቃላይ ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አመራር እየተቀበለ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ይኸው የአገልግሎት ግንኙነት በአህጉረ ስብከት ደረጃ ከማእከላት ጋራ፣ በወረዳ ቤተ ክህነትና በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ደረጃ ከወረዳ ማእከላት ጋራ ቀጥሎ እየተፈጸመ ይገኛል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የዛሬው ውሳኔ ማኅበሩ ለብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ ከነበረበት በጊዜያዊነትም ቢኾን ወደ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሚመልሰው ነው፡፡ ‹‹የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሊኾን አይገባውም›› የሚል የመሥራች ብፁዓን አባቶቹን መሠረተ ሐሳብ ያጸናው ማኅበሩ፣ ለጊዜውም ቢኾን ወደ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ቢመለስም ከአባላቱ ተዋፅኦ፣ ዕድሜና የአገልግሎት አድማስ አኳያ ከጅምሩም መርጦ የገባበት የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር ነው፡፡ በመኾኑም በዋናነት ከመምሪያው የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ጋራ በአባትነትና ልጅነት መንፈስ እየታዘዘና መመሪያ እየተቀበለ በሚፈጽመው አገልግሎቱ ቀደም ሲል ከመምሪያው ሓላፊዎች ጋራ ተከሥቶ የነበረው አለመግባባት ችግር ይፈጥርበታል ተብሎ አይገመትም፡፡

የኾነው ኹኖ የደንብ አጥኚ ኮሚቴው ለኹለተኛ ጊዜ የተሠየመበት ምክንያት ምንም ይኹን ምን ሊተኮርበት የሚገባው መነሻ ጉዳይ÷ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ እንዲሻሻል አጥኚ ኮሚቴ የሠየመበት ውሳኔ መሠረተ ዓላማ ነው፡፡

በወቅቱ እንደተገለጸው ቅዱስ ሲኖዶስ መተዳደርያ ደንቡን እንዲሻሻል የወሰነበት መሠረተ ዓላማ፡-

 • ማኅበረ ቅዱሳን የመሥራት አቅሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ፣ በቤተ ክርስቲያናችንም እየሠራ ባለው ሥራ ኹሉ አብያተ ክርስቲያናትን፣ አድባራትንና ገዳማትን በስፋት እየጠቀመ ያለ በምሁራን የታቀፈ ኹለንተናዊ ዝግጅት ያለው ማኅበር ስለኾነና ብዙ የልማት ሥራዎችን በመሥራት ላይ የሚገኝ በመኾኑ እንደ ተቋሙ ስፋትና ዕድገት ደግሞ እንደ ጊዜው ኹኔታ ራሱን የቻለ ድርጅታዊ መዋቅር ሊዘጋጅለት እንደሚገባ በመታመኑ ነው፤
 • የማኅበሩን አገልግሎት የሚመጥንና ለወደፊቱም ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ዕድገት የሚጠቅም የላቀና የተሻለ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለማበርከት የሚያስችለው ራሱን የቻለ መዋቅራዊ አደረጃጀት እንዲዘጋጅለትና የማኅበሩን አገልግሎቶችና የወደፊት ኹኔታዎችንም ያገናዘበ የመተዳደርያ ደንብ ሊቀረጽለት እንደሚገባው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመታመኑ ነው፡፡

በአጠቃላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ እንዲሻሻል በተደጋጋሚ አጥኚ አካል መሠየሙ፣ ደንቡ እስኪሻሻልም ድረስ እየተገለገለበት ባለው መተዳደርያ ደንቡ እየተመራ እንዲቆይ መወሰኑ በወቅቱ ከተከፈተበት የአማሳኞች አስተባባሪዎች ዘመቻ አኳያ ቢያንስ ኹለት ዐበይት ፋይዳዎች እንዳሉት ይታመናል፡፡

የመጀመሪያው÷ አማሳኞቹ ማኅበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርምሮ የጸደቀና የተፈቀደ ሕግ እያለው እንደሌለው፣ እንዲያውም ማኅበሩ ሕግ መግባት እንደሚፈራ የሚለፍፉት ከእውነታው የተጣላ መሠረተ ቢስ ውንጀላ መኾኑ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ከጥንቱም ሕጋዊና በሕግ የኖረ ማኅበር ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳን ሕግን አልፈራም፤ ማኅበረ ቅዱሳን ሕግን አይፈራም፤ ሕግን የሚፈራ ማን ነው? ሕግን የሚፈራው ለሙስናና ጎጣዊ መሳሳብ በር የሚከፍተው አሠራር÷ በተቋማዊ ለውጥ እንዳይቀረፍ ሕገ ወጥ ግላዊና ቡድናዊ ጥቅሙን ለማስጠበቅ የሚላላጠው አድመኛውና አማሳኙ ቡድን ነው፡፡

ኹለተኛው÷ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስለማኅበሩ ተጠሪነት በሥራ ላይ በሚገኘው መተዳደርያ ደንቡና በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. ካሳለፈው ውሳኔው በተፃራሪ ለፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እንዲኾን ሕገ ወጥ መመሪያ በማውረድ መርሐ ግብሮቹ ሲስተጓጎሉ የቆየበት አሠራር እንዲታረምና እንዲስተካከል የሚያደርግ በመኾኑ ነው፡፡


 ‹‹የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሊኾን አይገባውም››

ziway abune gorgorios1…ማኅበራት ኹሉ አንድ ዓላማ ባላቸው አባላት ሱታፌ የሚመሩ በመኾኑ ወደ አንድ የተጠናከረ ማኅበር ማጠቃለል እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በብፁዕ አቡነ ገብርኤል መኖርያ ቤት በተደረገ ስብሰባም በአማራጭነት ከቀረቡት ማኅበረ ሐዋርያት፣ ማኅበረ አርድእት እና ማኅበረ ቅዱሳን የሚሉ ስያሜዎች መካከል፤ ከላይ የተጠቀሱት ማኅበራት ኹሉም የቅዱሳን መታሰቢያ በመኾናቸው የማኅበሩ ስያሜ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› እንዲኾን በብፁዕ አቡነ ገብርኤል የቀረበው ሐሳብ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› በመባል የተሰየመው ይህ ማኅበር አገልግሎቱን ማበርከት የሚችለው በየት መኾን እንዳለበት መወሰን ቀዳሚው ጉዳይ ነበር፡፡ በዚኽ ጉዳይ ላይ ለመወሰን ብዙ ጊዜ የወሰደ ውይይት ከተደረገ በኋላ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ‹‹የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሊኾን አይገባውም›› ያሉትን መሠረተ ሐሳብ በመያዝ፣ ማኅበሩ ማገልገል የሚገባው በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ በመጠቃለል የቤተ ክርስቲያኒቱ አካል በመኾን ነው፡፡ እንዲኹም በተለያዩ ምክንያቶች የማገልገል ነፃነት ላይገኝ ስለሚችል ከቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውጭ ቢኾን የተሻለ ሊኾን ይችላል፤ የሚሉ ሐሳቦች ቀረቡ፡፡ ከእነዚኽ ሐሳቦች አንዱን መቀበልና መወሰን የግድ ነበር፡፡

በዚኽ ረገድም እልኽ አስጨራሽ ውይይትና ምክክር ከተደረገ በኋላ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት፣ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ኾኖ ከማገልገል በቀር ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም አገልግሎት ለመፈጸምና መንፈሳዊ በረከት የሚገኝበት ሥራ ለመሥራት እንደማይቻል ከስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ ከዚኽ ስምምነት በፊት በኹለቱ ሐሳቦች ላይ የከረረ ውይይት በመደረጉና ለጊዜውም መስማማትም ባለመቻሉ ኹሉም ጸሎተ ማርያም አድርጎ እንዲመጣ በመወሰን በቀጠሮ ተለያይተው ነበር፡፡ በቀጠሮው ቀን ኹሉም በአንድ ሐሳብ ተስማምተው የተደረሰበት ኹኔታ የማይረሳ ነው፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎትም አስቸጋሪና አከራካሪ በኾኑ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት የሚደረስበት አሠራር ኾኖ ለመቀጠል በቅቷል፡፡

የማኅበሩ አገልግሎት በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ መኾን እንደሚገባው ከተወሰነ በኋላ ቀጥሎ የተነሣው ጉዳይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ከሚገኙት ልዩ ልዩ መምሪያዎች መካከል በየትኛው ሥር መዋቀር እንደሚገባው መለየት ነበር፡፡ ይህን ጥያቄ ለመመለስም የማኅበሩ አገልግሎት አድማስ፣ የአባላቱ ተዋጽኦ እና የአባላቱ ዕድሜ ኹኔታ…ወዘተ መጤን ነበረበት፡፡ በዚኽ አንጻርም አባላቱ የሚያገለግሉበት በሰንበት ት/ቤቶችም በመኾኑ አብዛኛዎቹ አባላቱም ወጣቶች በመኾናቸው፤ በአማራጭ ከታዩት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ እና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የቀረበ ኾኖ የተገኘው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ነበር፡፡ የማኅበሩ መዋቅርም በዚኽ መምሪያ ሥር እንዲኾን ተወሰነ፡፡

ይህ ውሳኔ በማኅበሩ የወቅቱ አመራር ይወሰን እንጂ መምሪያው ማኅበሩን ተቀብሎ በሥሩ ለማደራጀትና አገልግሎቱንም ስለመቀበሉ የተረጋገጠ ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚኽ የመምሪያውን ሓላፊዎች በማነጋገር ይህን ሐሳብ የማሳመንና የማስረዳት ሥራ ለመሥራት እንዲኹም ይኹንታቸውን ለማግኘት ጥረት ተጀመረ፡፡

በተለይ የወቅቱ የመምሪያው ሓላፊዎች የነበሩት መምህር ገበረ ሚካኤል ድፈር እና ሊቀ ትጉሃን ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ የተወሰኑ የማኅበሩን አባላት በሰንበት ት/ቤት እና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያውቋቸው ነበር፡፡ አባላቱም በአገልግሎት ላይ በመኾናቸው የመምሪያው ሓላፊዎች በየዓመቱ በየሰንበት ት/ቤቶቹ በሚደረገው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የጥምህርትና የምረቃ በዓል መርሐ ግብሮች ላይ እየተገኙ ያስተምሩ ነበር፡፡ በዚኽ የተነሣ የማኅበሩን አባላት ከዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና የካህናት ማሠልጠኛ ጋራ ያላቸውን ቁርኝት ከግምት በማስገባትና እነዚኽን በዘመኑ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል በቀና መንፈስና በመንፈሳዊ ስሜት የቀረቡትን ወጣቶች የወንጌል ኃይል፣ የተዋሕዶ ሃይማኖት ሠራዊት አድርጎ ማሰማራት ለቤተ ክርስቲያን የሚኖረውን መልካም አስተዋፅኦ በመገንዘብ ጥያቄአቸው አዎንታዊ ምላሽ አገኘ፡፡

በወቅቱ የመምሪያው ሓላፊ መምህር ገብረ ሚካኤል ድፈርና ምክትል ሓላፊው ሊቀ ትጉሃን ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ በቀናነትና በደስታ ሓላፊነት በመውሰድ ከማኅበሩ ጋራ ለቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ፈቀዱ፡፡ ይህ ምላሽ የተገኘበት ቀን በማኅበሩ የአገልግሎት ጉዞ ውስጥ የማይዘነጋ የማዕዝን ድንጋይ ኾኖ ሲታወስ የሚኖር ነው፡፡

/የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት፤ የማኅበረ ቅዱሳን አመሠራረት ታሪክ፤ መስከረም ፳፻፯ ዓ.ም./

Advertisements

23 thoughts on “ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ: ማኅበረ ቅዱሳን እየተመራበት ባለው መተዳደርያ ደንቡ እስከ መጪው ግንቦት እየሠራ እንዲቆይ ወሰነ፤ የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ በአዲስ መልክ ተሻሽሎ ይዘጋጃል

 1. Sam November 1, 2014 at 4:38 pm Reply

  This is a good news for the Church services in general and for MK and Sunday School in particular. Let us all work together for the better results.

 2. Anonymous November 1, 2014 at 5:49 pm Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን!

 3. zakios November 1, 2014 at 6:35 pm Reply

  ሁሉንም ማድረግ የሚችለው ኃያሉ እግዚአብሔር ሊቃነ ጳጳሳቱን ይርዳቸዉ፡፡ መሠረታዊዉ ነጥብ ግን ማሕበረነ ቅዱሳን አደረጃጀታቸውና አሠራራቸው ግልጽና ተጠያቂነት ሊኖረው ይገበል፡፡ ከምንም በላይ ሐይማኖታችን በበቁ አባቶች ልትመራ ይገባታል፡፡ የእሰካሀኑ አካሔድ በየፊናው የሚቋቋመው የሰንበት ፣የመዘምራን ሊታሰብ ይገባዋል፡፡

 4. Anonymous November 1, 2014 at 7:47 pm Reply

  egzabihergin enesigen

 5. Getasew November 2, 2014 at 12:19 am Reply

  Yitbarek EGZIABHER amlake abewine lezeabtsahane eskezatisiat.betekirstianachin tebiklin.we all tewahido belivers,pray!

 6. Anonymous November 2, 2014 at 2:03 am Reply

  Egziabher ymesgen mahiberachinin Egziabher yibarklin

 7. setargie asmare November 2, 2014 at 3:41 am Reply

  May god bless you all through your life.your spiritual service cannot measured by words.
  Simply god gives you his blessings.

 8. Anonymous November 2, 2014 at 6:57 am Reply

  የማህበረ ቅዱሳንን መልካም ስራና የቅድስት ቤተክርስቲያን አካል መሆኑን ለማታውቁ እስኪ ይህን ተመልከቱና እወቁ ማየት ማመን ነው ። እግዚአብሔር ቅድስት ቤተክርስቲያንና ማህበራችንን ከውስጥ ከውጭ መናፍቅ የማፍረስ ሴራ ይጠብቅልን አሜን

  • Anonymous November 2, 2014 at 4:13 pm Reply

   That was a false news. You will soon find out when the synod is over. For now dream on.

 9. Anonymous November 2, 2014 at 7:13 pm Reply

  Temesgen new lela min akim alegn,Betechristianachinin,mahiberachinin Egziabher yitebik

 10. Anonymous November 3, 2014 at 5:53 am Reply

  amen

 11. Anonymous November 3, 2014 at 5:58 am Reply

  EGZIABHER yimesgen

 12. anonymous November 3, 2014 at 8:19 am Reply

  Egziabhaire yemesgen abatochen yetebekelen eskemechereshawe yechen bete kirstyan enditebekute yadergelen,fetenawen yakelelachew hulachenem betselote enasebachew yale enesu menore le kerstiyan kebade selehone hulachenem mastewalune yesten

 13. Anonymous November 3, 2014 at 8:37 am Reply

  AMELAKE KIDUSANE YEHUNEN . Ewneten meyaze kemeneme belaye selhon ayaseframe.

 14. Anonymous November 3, 2014 at 11:34 am Reply

  amlak kidusan bate krstiyann yitebk

 15. Anonymous November 3, 2014 at 8:11 pm Reply

  ማህበ ረ ቅዱሳን ምእመናንን ሰብስበዋል፣ ለቤተ ክርስትያን ኣገልግለዋል፣ ቤተ ክርስትያንም በተለይ በውጭ ኣድንዋታል፣ በተለይ በገጠር ኣመርቂ ሰማያዊ ስራዎች ሰርተዋል። በተለይ በውጭ እነሱን የሚጠይቅ ያገልላሉ የሚባለው ቢታሰብበት። ኣክራሪዎች ናቸው የሚለውን ቢገመገም። ችሎታ ያለውና የሌለውን ኣቅፈው፤ በረጋ መንፈስ፤ ልበ ሰፊ ሁነው እንዲጋዙ ትምህርት ይሁኑባቸው።
  ወልደገብርኤል

 16. Mamush Solomon November 4, 2014 at 6:28 am Reply

  ለሁሉም ጊዜ አለዉ ! ዝም ብለን ሥራችንን እንስራ ክርስቲያን የሚኖረዉ ከፈተና ጋር በእርሱ ኃይልም እያሸነፈ ነዉና

 17. Anonymous November 4, 2014 at 7:40 am Reply

  egziabher hoy,srah grum new! fetena mannetn endigelt tadergaleh! misgana yidresh

 18. Anonymous November 4, 2014 at 12:45 pm Reply

  hulume zem belo yegzabhern nger yemlkte yefqdewn yadergle

 19. Anonymous November 4, 2014 at 12:51 pm Reply

  እግዚአብሔር አምላካችን አገልግሎታችንን ይባርክ፣ ማኅበራችንን ይጠብቅልን፣ አባቶቻችንን ያኑርልን አሜን።

 20. Muluwork Desta November 5, 2014 at 1:06 pm Reply

  እግዚአብሔር እንዲቀድም ካደረግን መንገዱ ሰላም ነው እግዚአብሔር ይመስገን!

 21. Anonymous November 10, 2014 at 1:31 pm Reply

  mesertachen kerestose newenahulume lederseben gedenew keresteyan hulu betelot tegu

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: