ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾኑ

abune-qelemntos2

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፤ የከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ የበላይ ሓላፊ

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ፣ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ዐሥረኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ መደበ፡፡

ብፁዕነታቸው፣ ትላንት በተጠናቀቀው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ፣ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ኾኖ በተደነገገው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ በምልአተ ጉባኤው የተመደቡት ከርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቀረበው ጥቆማ ነው፡፡

ምደባው አስመራጭ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሦስት ዕጩዎች ከተለዩ በኋላ በዕጣ እንዲከናወን ታስቦ እንደነበር ተገልጧል፡፡ ይኹንና የፓትርያርኩን ጥቆማ መነሻ በማድረግ እንዲወሰን የተደረገው፣ የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ የኾነው አዲስ አበባ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት በመኾኑ ጥቆማውም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እንዲሰጥ ምልአተ ጉባኤው ከተስማማበት በኋላ ነው፡፡

በኤጲስ ቆጶስነት ከመሾማቸው በፊት የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጸባቴ እንዲኹም የጥንታዊው ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አለቃ የነበሩት ብፁዕነታቸው፣ በነሐሴ ወር ፲፱፻፺፯ ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ ከተሾሙ በኋላ በምሥራቅ ሐረርጌና በወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ያገለገሉ ሲኾን በአኹኑ ወቅት የከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከትን እየመሩ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያን በበላይ ሓላፊነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ 

A.A Diosces Head Office

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሀገሪቱ ርእሰ ከተማ ስለኾነና ከሌሎች አህጉረ ስብከት የሚለይባቸው ልዩ ኹኔታዎች በመኖራቸው እኒኽን ከግምት ያስገባ የተለየ አወቃቀርና የፐርሰንት አከፋፈል ሥርዐት እንደሚኖረው በተሻሻለው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ሰፍሯል፡፡

በሀገረ ስብከቱ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚሾሙት በሕጉ÷ ስለ ትምህርት ዝግጅት፣ የአገልግሎት ልምድ፣ ግብረ ገብነት፣ የካህናትና ምእመናን አመኔታና ተቀባይነት የተዘረዘሩ የብቃት መስፈርቶች በሊቀ ጳጳሱ ሰብሳቢነት በሚመራው በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ተመርጠው የምርጫው ውጤት ለቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ መኾኑ ተደንግጓል፡፡

ከ160 በላይ ገዳማትና አድባራት የሚገኙበት አዲስ አበባ፣ በአራት አህጉረ ስብከት ተከፍሎ ከነበረበት ወደ አንድ ሀገረ ስብከት ከተመለሰበት የግንቦት ፳፻፭ ዓ.ም. ውሳኔ በኋላ፣ በሰባት ክፍላተ ከተማ በማዋቀርና የሥራ ክፍፍል በማድረግ በበጀት ዘመኑ በርካታ ሥራዎች እንደተከናወኑበት በ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የቀረበው የሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ 

እንደ ሪፖርቱ÷ በሀገረ ስብከቱና በክፍላተ ከተማ ጽ/ቤቶች አስተባባሪነት በቅርብ የሚገናኙ ገዳማትና አድባራት በአንድ ላይ በመቀናጀት ልዩ የአንድነት የስብከተ ወንጌል ጉባኤያት በሰፊው ተካሒደዋል፡፡ በተለያዩ ገዳማትና አድባራት የአብነት መምህራን ተመድበው ደቀ መዛሙርት እንዲያወጡ ሰፊ ሥራ ተሠርቷል፤ ጥሩ ውጤትም ተገኝቷል፡፡ የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚከበሩ በዓላት ላይ በመገኘት ከፍተኛ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

በተለያየ ምክንያት ከሥራቸው ተፈናቅለው የነበሩ ከሰማኒያ በላይ የቤተ ክርስቲያን መምህራን፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ በማስወሰንና ጉዳያቸውን የሚያጠና ከሀገረ ስብከቱ እንዲኹም የክፍላተ ከተማ ሥራ አስኪያጆች የተካተቱበት የጥናት ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ሥራ እንዲመለሱ መደረጋቸው ተዘግቧል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ከፍተኛ ችግር የሚያጋጥም ቢኾንም በሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ክትትል የተለያዩ የመንግሥት አካላትን በማሳመን ስምንት አብያተ ክርስቲያን ተተክለዋል፡፡

ሀገረ ስብከቱ፣ ከከተማው አስተዳደር ቦታ በሊዝ ወይም በነፃ በመጠየቅ ኹለገብ ሕንፃ ለመሥራት አልያም በቀድሞው የሀገረ ስብከቱ ሕንፃ ላይ በአካባቢው የግንባታ ደረጃ (ስታንዳርድ) መሠረት ባለሰባት ፎቅ ኹለገብ ሕንፃ ለመሥራት ዕቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ መኾኑን በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

በ፳፻፮ ዓ.ም. በጀት ዓመት ሀገረ ስብከቱ 445‚596‚486.80 ጠቅላላ ገቢ ያገኘ ሲኾን ከዚኽ ውስጥ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድርሻ (65 በመቶ) የኾነውን ከኃምሳ ሚልዮን ብር በላይ /50‚236‚305.27/ ገቢ አድርጓል፡፡ ይህም ከአምናው ፈሰስ ጋራ ሲነጻጸር ከአምስት ሚልዮን ብር በላይ ብልጫ እንደተመዘገበበት ተመልክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከዓመት ዓመት ከፍተኛ የገቢ ዕድገት እንዳስመዘገበና አስተዳደራዊ አሠራሩም እንደተሻሻለ በሪፖርቱ መሰማቱ የሚያበረታታ ነው፡፡ እንደ አዲስ አበባ ተጨባጭ ኹኔታ ሲታይ ገዳማቱና አድባራቱ ከፍተኛ የሀብት ክምችት ያለባቸው የብዙ ባለሀብትና ንብረት ባለቤቶች ከመኾናቸው የተነሣ በቃለ ዐዋዲው ሕግና መመሪያ ተደግፎ በታማኝነት ከልብ ከተሠራ በኹሉም የሥራ ዘርፍ ተኣምር መፍጠር እንደሚቻል ይታመናል፡፡

ይኹን እንጂ ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ጀምሮ በገዳማትና አድባራት በተደጋጋሚ እንደታዩ በሪፖርቶች ለተገለጹት፡-

 • ከሙስና ጋራ የተያያዘ የሥራ አለመቀላጠፍና የመልካም አስተዳደር ዕጦት
 • በጎሳ ላይ ያተኮረ የቅጥር፣ የዕድገትና የዝውውር አፈጻጸም ችግር
 • የሰበካ ጉባኤ በቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ መሠረት አለመደራጀት
 • የአባላት አስተዋፅኦ በትክክል አለመክፈል
 • የገንዘብና ንብረት አያያዝን ለማጎልበት የተላለፈውን መመሪያ በአግባቡ ተግባራዊ አለማድረግ
 • የሒሳብ ምርመራን በጊዜውና በትክክል አለማከናወን
 • የፐርሰንት ገቢውም በየደረጃው በቅጽ ተሞልቶ በጊዜው አለመቅረብ

እና የመሳሰሉት አሳሳቢ ችግሮች የማያዳግም ሥር ነቀል መፍትሔ እንዲሰጣቸው በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ደረጃ በተደጋጋሚ ሲጠየቅ ቆይቷል፡፡

ለተቋማዊ ችግሮቹ የማያዳግም ሥር ነቀል መፍትሔ ለማስገኘት፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ ይኹንታና አቅጣጫ የተሰጠበትና የማኅበረ ካህናቱን፣ ማኅበረ ምእመናኑንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ድጋፍ ያረጋገጠው የመዋቅር፣ የአደረጃጀትና የአሠራር ጥናት በቋሚ ሲኖዶስ እየታየ ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ የተላለፈበት ቢኾንም መለካውያን አማሳኞችና አድርባይ ፖሊቲከኞች ልዩ ጽ/ቤቱን ተቆጣጥረው በፈጠሩት ሳንክ ትግበራው በእጅጉ ዘግይቶ ይገኛል፡፡

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊነታቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተቋቋመው የሀገር አቀፍ አንድነት ጉባኤ የወጣው የአምስት ዓመት ስትራተጅያዊ ዕቅድ ጸድቆ ወደ ትግበራ እንዲገባ በማድረግ ባላቸው አባታዊ የአመራር ልምድ ተጠቅመው÷ በቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተዘጋጀውና በካህናቱ፣ ሊቃውንቱ፣ ሠራተኞቹና ምእመናኑ ‹‹የቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ ብሥራት›› የተባለውን የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ወደ ትግበራ ምዕራፍ በማሸጋገር አዲስ አበባ የአህጉረ ስብከቱ ኹሉ ሞዴል ኾኖ የሚታይበትን የተቋማዊ ለውጥ ጥናት እንደሚያሳኩና ብዙ ክፍተቶችን እንደሚሞሉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ለብፁዕነታቸው ውጤታማ የሥራ ዘመን እንመኝላቸዋለን፡፡

15 thoughts on “ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾኑ

 1. Anonymous October 31, 2014 at 3:00 pm Reply

  HaHaHa…..MK Alekelat…

  ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ EPRDF member nachew Sitilu neber ayidele ende be patriarch mircha gizie???

  This is an excellent calculation from patriarch side. MK totally excluded from Addis Ababa Diocese and we know that there are excellent and strong leaders in Sunday school department. I think you better confess in stead of fighting with true servants of Christ. Anyway, please be fast to transfer your bunch of millions to the EOTC account and the church will use it to start the newly designed construction around ARAT kilo. Of course, the church should ensure that our clergies in the monasteries and rural churches are free of poverty and…

  Our church lives more than 2000 years without MK and its mafia Shewa group. This is good enough that the Addis Ababa diocese archbishop is from SNNPR and he General manager is from OROMIA…Hello MK tell us now…..I love the calculation….

  May God protect our church from MK evil work!

  Betgilu Ashenef

  • Anonymous October 31, 2014 at 5:19 pm Reply

   Please z one who comment above r u sure u r talking about z church in a spiritual way what does it mean when u r saying z bishop is from south & z general manager is from oromia. I think u r motivated not from z perspective spirituality rather from z ethinicity angel so ur basic reason u hate mk is not for z sake of z church.may God protect his church from such kind of evil thoughts & bring love upon us.amen.

 2. Anonymous October 31, 2014 at 4:41 pm Reply

  “አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል” አይደል የሚባለው እስከነተረቱ።
  ልጅ “በትግሉ አሸናፊ” መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ!!

 3. Anonymous October 31, 2014 at 5:37 pm Reply

  you have narrow mind. Am not a member of MK but Mk are talking about true organization structure in our church. even if am not a member I support their stand.

 4. Zewdneh October 31, 2014 at 5:46 pm Reply

  Ye MK neger betam asazagne eyehone new…hhhhhhhhh…..yasaznal….menew MK?….menew! yeh neber alamachen? Besinodos lay felach korach mehon….abatoch mehal gebto mebetbet….agelgayochen mebeten….enkerdadu sibal sentu sende tachede! hhhhhhhhhhh……ay MK!

  • Anonymous October 31, 2014 at 8:19 pm Reply

   You must be rent seeker. MK is the pillar of our church in the contemporary world. It is really a headache for tehadiso menafikan like you.

 5. elias techane October 31, 2014 at 6:14 pm Reply

  (even if i don’t believe in race) let me tell u betgilu abune kelemintos ye shewa nigus(balabat) nachew not SNNPR & general maneger,administration dept,low dept,sebeka gubae dept,plan dept,sun-day school dept,development dept,migbare senay dept,timirt dept…..are from shewa in addis ababa hagere sibket

 6. Anonymous October 31, 2014 at 6:48 pm Reply

  ashenafi you think backwardly. still think about racism wow I thought your kind of people extinct. you are a treasure.

 7. Sam October 31, 2014 at 7:39 pm Reply

  Thanks to God. This is a good move for our Church services, MK and Sunday School services. I know this father, has been working well with the young generation.

 8. Anonymous November 1, 2014 at 6:01 am Reply

  Hulum Negre Lebgo Neaw.God Yewodedewn Yadergal

 9. tsebay November 1, 2014 at 6:49 am Reply

  never give up for evil works GOD always with us and mk who is doing well for the growth of our church.

 10. ABI November 1, 2014 at 12:43 pm Reply

  Egziabher Yefekedew Yihonal

 11. ABI November 1, 2014 at 12:45 pm Reply

  Metshaf Kiduse Atsadebu Yilal, slezih Kumneger enawra enji gobez

 12. Anonymous November 22, 2014 at 8:27 am Reply

  ከዘረኝነት በሽታ መቼ ይሆን የምንላቀቀው;

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: