ቅ/ሲኖዶስ: ለአማሳኞቹ ቀኖናዊ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ወሰነ፤ ፓትርያርኩ ‹‹ልዩ ጸሐፊዬን ከምታነሡ እኔን አውርዱኝ፤ ጥዬ እሔዳለኹ፤ ገዳሜ እገባለኹ›› ሲሉ ለንቡረ እድ ኤልያስ ተከላከሉ

 • ውሳኔው በዋናነት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስንና መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃን ይመለከታል
 • በቀጣይ ክትትልና ቁጥጥር በተቀጡበት ድርጊታቸው ከተገኙ ክህነታቸው እንዲያዝ ተወስኗል
 • ፓትርያርኩ ‹‹አጀንዳው መያዙን አላውቅም›› በሚል ውይይት እንዳይካሔድ ተቃውመው ነበር

*          *         *

 • ‹‹እምነት አለው ለማለት ይከብዳል፤ የሙስና አባትና የሰላም ጠንቅ ነው፤›› የተባሉት ንቡረ እድ ኤልያስ የነበሩትም ያሉትም ፓትርያርኮች ችግር ዋነኛ መንሥኤ እንደኾኑ ተሠምሮበታል
 • በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መሾም የበሸቁትና በቀኖናዊ ውሳኔው የተደናገጡት እነሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ ‹‹ይኼ ይዞ ሟች፤ለሸዋ አሳልፎ ሰጠን›› እያሉ ፓትርያርኩን ሲዘልፏቸው ዋሉ

*           *         *

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ፣ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ዐሥረኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ‹‹በሌብነት ላይ ተሠማርተው ቤተ ክርስቲያኗን እያወደሙ ነው›› ባላቸው ኹለት የአማሳኙ ቡድን መሪዎችና ግብረ አበሮቻቸው ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

the heavily corrupt Lique Tiguhan Zekarias Haddis

የሲ.ኤም.ሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ በሚገኙ ገዳማትና አድባራት ስለሚታየው የመልካም አስተዳደር ችግር የተወያየው ምልአተ ጉባኤው÷ ‹‹ቤተ ክርስቲያኗን አዋርደዋል›› ባላቸው የአማሳኞች መሪዎች ላይ ባሳለፈው ውሳኔ፣ ቀኖናዊ ቅጣት እንዲፈጸምባቸውና ከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡

the heavily corrupt Melake Genet haile abreha

የደብረ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ

ቀኖናዊ ቅጣቱና ከባድ ማስጠንቀቂያው በተለይ የአማሳኞቹን ቡድን እንቅስቃሴ በመደገፍ፣ በማስተባበርና በመምራት ተጠቃሽ በኾኑት የሲ.ኤም.ሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ እና የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ ላይ ተፈጻሚ እንደሚኾን ታውቋል፡፡

Nebured Elias Abreha, special secretary of the patriarch Aba Mathias

የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ

ኹለቱን የአማሳኞች መሪዎች እንደ አቀባባይ ደላሎች በመጠቀም ቀድሞም የነበራቸውን የምዝበራ ሰንሰለት አጠናክረው በቀጠሉት የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጉዳይ ምልአተ ጉባኤው የተነጋገረ ቢኾንም ፓትርያርኩ ‹‹የእኔ የግሌ ጸሐፊ ነው›› በሚል ተከላክለውለታል፡፡

‹‹እርሱን ብታነሡ ጦር ያማዝዛል›› በማለት ብፁዓን አባቶችን ፈገግ ያሰኙት ፓትርያርኩ፣ ልዩ ጸሐፊአቸው ከሓላፊነት ከሚነሡ ይልቅ የእርሳቸው ከፓትርያርክነት መውረድ እንደሚቀል ሲገልጹ ‹‹እኔም አብሬ ልነሣ›› በማለት የምልአተ ጉባኤውን አባላት አስደምመዋል፡፡

ንቡረ እዱ ‹‹እምነት አለው፤ የሃይማኖት ሰው ነው ለማለት ያዳግታል›› ያሉት የምልአተ ጉባኤው አባላት÷ በ፳፻፩ ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲከበር፣ ዐምባገነናዊና ቤተሰባዊ አስተዳደር እንዲወገድ በተንቀሳቀሱ ብፁዓን አባቶች ላይ ከተካሔደው እንግልት ጀርባም እንደነበሩ ተወስቷል፡፡ የልዩ ጽሕፈት ቤታቸውን አወቃቀር መነሻ በማድረግም ንቡረ እድ ኤልያስ÷ ‹‹የሙስና አባትና የቤተ ክህነቱ የሰላም ጠንቅ›› እንደኾኑ የተሠመረበት ከመኾኑም ባሻገር የነበሩት ፓትርያርክና የቅዱስነታቸውም ችግር ዋነኛ መንሥኤ እንደኾኑ በመጥቀስ ከመቀጣት መታለፍ እንደሌለባቸው የብዙኃኑ አቋም ተይዞባቸው ነበር፡፡

ፓትርያርኩ ‹‹የእኔ የግሌ ጸሐፊ ነው፤ እንደዛ ከኾነ እኔም አብሬ ልነሣ፤ መነኵሴ ነኝ፤ ገዳም የኖርኹ ሰው ነኝ፤ ገዳሜ እገባለኹ፤›› ከማለት በቀር ይህንኑ የብዙኃኑን ብፁዓን አባቶች አስተያየትና የጥፋተኝነት ብያኔ ማስተባበል አልተቻላቸውም፡፡ በመጨረሻም ‹‹ማንኛውም ነገር ላይ እንዳይገባ አደርጋለኹ፤ እመክረዋለኹ፤አስተካክለዋለኹ›› የሚል ሓላፊነት በመውሰዳቸው ለጊዜው ሊታለፍ እንደቻለ ተገልጧል፡፡

ርእሰ መንበሩ ‹‹አጀንዳው መኖሩን አላውቅም›› በሚል በሀገረ ስብከቱ የአስተዳደርና የሰላም ችግሮች ላይ ውይይት መካሔዱን ቢቃወሙም አጀንዳው ተይዞ በተላለፈው ውሳኔ ግን በተለይ ኹለቱንም የአማሳኞች መሪዎች ይግባኝ ከማይጠየቅበት የቅዱስ ሲኖዶሱ ብያኔና ፍርድ ማዳን አልተቻላቸውም፡፡

የሙስናው አበጋዞች በመጨረሻ ማስጠንቀቂያና ለጥፋታቸው በሚመጥን ቀኖናዊ ቅጣት እንዲታለፉ የተደረገው ተጨርሰው እንዲጠረጉ የፍርድ ሐሳብ ከቀረበ በኋላ ነው፡፡ ግለሰቦቹ በውሳኔው የመታረማቸው ጉዳይ በቀጣይ ክትትልና ቁጥጥር የሚታይ ሲኾን በተቀጡበት፣ የቤተ ክርስቲያንን ሰላም በአማሳኝነትና በአድመኝነት የማወክ ድርጊት ተመልሰው ከተገኙ፣ ክህነታቸው እንዲያዝ ምልአተ ጉባኤው ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ውሳኔውንና ትእዛዙን በመመሪያ የማስተላለፍና ተከታትሎ የማስፈጸም ሓላፊነትም ከፓትርያርኩ የሚጀምር ሲኾን መላው ኦርቶዶክሳውያንም በጥብቅ የሚከታተሉት ጉዳይ ይኾናል፡፡


            መልእክት በሲኖዶሳዊ ችሎት ለተቀጣችኹ የአማሳኞች መሪዎች

በ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በራሳችኹ ቃል ከፍ ባለ ድምፅ እንደተናገራችኹት፣ ‹‹የመጀመሪያ ጥያቄአችኹ በቅዱስ ሲኖዶስ እና በቅዱስ አባታችን እንመራ ነው›› ብላችኋል፡፡ ‹‹አማሳኞች ኾነን ከተገኘንም ከቤተ ክርስቲያን መውጣት ነው ያለብን›› ስትሉ በአጠቃላይ ጉባኤው ፊት አረጋግጣችኋል፡፡

እነኾ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውና የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የኾነው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመከረበት መሠረት ግብራችኹ ሌብነትና ይኸውም ቤተ ክርስቲያኗን እያዋረደ እንደኾነ ተረጋግጦ የጥፋተኝነት ብያኔ ተሰጥቶባችኋል፤ የቅጣት ውሳኔም ተላልፎባችኋል፡፡ ይህ ብያኔና ውሳኔም ይግባኝ የለውምና ከመፈጸም በመለስ በኃይልና በጩኸት ወይም እንደ ትሮጃን ፈረስ የሌላ ተልእኮ ሰገባና ሠረገላ ኾኖ በሽፋንነት በመላላክ ለመቀልበስ የሚመች አይደለም፡፡ በተለይ ደግሞ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ ‹‹መንጃ ፈቃድ የሌለው ሹፌር፤ ታርጋ የሌለው መኪና፤ ፊርማ የሌለው ደብዳቤ ነውና ተቀባይነት የለውም›› እንዳሉት ዋዘኛ አይደለም፤ ለአንድ ኦርቶዶክሳዊ ካህንና ምእመን በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ እንዲኽ ከመባል በላይ የበደለኝነት ማረጋገጫ የለምና!

ስለዚኽ ያላችኁ አማራጭ ስሕተታችኹን አምናችኹ ‹‹በፌስታል ሙዝና ብርቱካን የሚደለሉ፤ ቆባቸውን አስረክበው ከማኅበሩ ይቀላቀሉ›› እያላችኹ ያሳዘናችኋቸውን ብፁዓን አባቶችና ያስቆጣችኁትን አገልጋይና ምእመን ይቅርታ ጠይቃችኹ በበጎ ሥራ መካስ ነው፡፡ ከዚኽ ውጭ እምቢ ብላችኹ በአማሳኝነትና አድመኝነት ድርጊታችኹ ብትቀጥሉ ‹‹ክህነታችኹን ይዘናል ብትሉ ምን እናመጣለን?›› በማለት ሊከተል የሚችለውን የቅዱስ ሲኖዶሱን ርምጃ ራሳችኹም ቀድማችኹ አመልክታችኋልና የባሰ ፍርድና ቅጣት እንደሚጠብቃችኹ በእናንተም ዘንድ የተገለጠ ነው፡፡ የቅዱሳን አምላክ ቀናውን ያመለክታችኹ ዘንድ ልባዊ ጸሎታችን ነው፡፡


 

Advertisements

30 thoughts on “ቅ/ሲኖዶስ: ለአማሳኞቹ ቀኖናዊ ቅጣትና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ወሰነ፤ ፓትርያርኩ ‹‹ልዩ ጸሐፊዬን ከምታነሡ እኔን አውርዱኝ፤ ጥዬ እሔዳለኹ፤ ገዳሜ እገባለኹ›› ሲሉ ለንቡረ እድ ኤልያስ ተከላከሉ

 1. Anonymous October 31, 2014 at 9:55 pm Reply

  http://www.addisababa.eotc.org.et/site/en/news
  የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት 33ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ባለ 21 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

  ፫.፲፱.የማኅበራትን እንቅስቃሴ በተመለከተ
  ከቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ አግኝተውም ሆነ ፈቃድ ሳይኖራቸው በተለያየ መልኩ ተደራጅተው በማገልገል ላይ ያሉ ማኅበራት ለቤተ ክርስቲያን እድገትና ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት የራሳቸው ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ችግሮች እየተፈጠሩና የቤተ ክርስቲያን ሰላም እየደፈረሰ ይገኛል፤ የዚህ ዐይነት ችግሮችን ለማስቀረት እንዲቻል ቅዱስ ሲኖዶስ በጥልቀት መርምሮ አስፈላጊ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጉባኤው እየጠየቀ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነውን ውሳኔ በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅሮች ውስጥ ለማስፈጸም ሁላችንም ዝግጁዎች መሆናችንን በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናረጋግጣለን፡፡

  ፫.፳. ይህ የ፴፫ተኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ያወጣው አቋምና የሰጣቸው የውሳኔ አሳቦች በቅዱስ ሲኖዶደስ ጸድቀው ለሁሉም አህጉረ ስብከት ከተላኩ በኋላ የውሳኔው አፈጻጸም በሚቀጥለው ዓመት ፴፬ኛው አጠቃይ ስብሰባ እንዲገመገም ይደረግ ዘንድ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

 2. ተስፋዬ October 31, 2014 at 9:59 pm Reply

  ‘ንቡረ እድ’ ኤልያስ አብርሃ ‘ሊቀ ትጉሃን’ ዘካርያስ ሐዲስ ‘መልአከ ገነት’ ኃይሌ ኣብርሃን የለየላቸው መናፈቃን ለመሆናቸው እን ዲሁም የቤተክርስቲያን የጀርባ ቅማል መሆናቸውን አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው

 3. Anonymous November 1, 2014 at 1:20 am Reply

  egzabhare yeyelachu

 4. tekalign November 1, 2014 at 4:16 am Reply

  ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች መሰብሰቢያ ነችና ሻጪ ለዋጭ የክርስቶስ የ
  ፍርዱ አለንጋ ሳይወርድ ባቸው ንስዐ ግቡ፡፡ወይም ቦታው እዚህ ስላልሆነ ቦታው ን ፈልጉ፡፡

 5. Anonymous November 1, 2014 at 6:50 am Reply

  እኛም ተደምመናል!!!!!

 6. ታምሩ November 1, 2014 at 7:44 am Reply

  ንቡረ-ዕድ ኤልያሥ መነሣት ከፓትርያርኩ መነሣት ከበለጠና ጦር ካማዘዘ ሥማቸው ነገረ-ዕድ ኤልያስ ይባል። የመከላከያ ጄኔራል ነው እንዴ ሰውየው?

  • Anonymous November 2, 2014 at 4:11 am Reply

   የመከላከያ ጄኔራል ነው እንዴ ሰውየው? funny

  • Selam November 5, 2014 at 7:45 pm Reply

   sewoch abdenal ende…endet mastewal akaten…lene lezi miadersachew tefatachew aytayegnem….patryarkun eske mot yetenagerut Kes men tewesenebachew….enih abatoch endih aladeregum….ewnet yesema becha endalu new makew

 7. Anonymous November 1, 2014 at 7:53 am Reply

  እኔን ሁል ጊዜ የሚገርመኝ እነዚህ ለእርድ የቀረበ ሰንጋ በሬ የሚመሳስሉት የአድባራት አስተዳዳሪዎች በጾም በጸሎት ተወስነው የሚኖሩ ካህናት ናቸው ወይስ የስጋ ቤት ነጋዴዎች ናቸው?

 8. kich dumchi November 1, 2014 at 7:56 am Reply

  እኔን ሁል ጊዜ የሚገርመኝ እነዚህ ለእርድ የቀረበ ሰንጋ በሬ የሚመሳስሉት የአድባራት አስተዳዳሪዎች በጾም በጸሎት ተወስነው የሚኖሩ ካህናት ናቸው ወይስ የስጋ ቤት ነጋዴዎች ናቸው?

 9. ተስፋዬ November 1, 2014 at 5:30 pm Reply

  ጉድ ሳይታይ መስከረም አየተባም የምባለው ደረሰ !!!ለእርድ የቀረቡ ሰንጋዎች ነው ያለከው ?ጥሩ ተመልካች ነህ ::በፀሎት ከመወሰን ይልቅ በ ምንፈቅናና ጮማ በመቁረጥ ግዜአቸውን ያጠፋሉ ::ቤተክርስቲያንን ያደማሉ ::

 10. aaaaa November 1, 2014 at 5:35 pm Reply

  Ysigabet kualja korachoch enji

 11. aaaaa November 1, 2014 at 5:36 pm Reply

  baladelebut balgezut kbete laye yemichkinu

  • Selam November 5, 2014 at 7:46 pm Reply

   CHEKAGNE SEW NEH

 12. G/HAWARYAT November 1, 2014 at 6:20 pm Reply

  እግዚአብሄር ይመስገን!!! በእዉነት መንፈስ ቅዱስ አባቶችን ስራ አሰራ!!!

 13. Anonymous November 1, 2014 at 7:31 pm Reply

  Lehulum gize alew… Yebezuwoch enba feseso aykerem. 1ken Egziabher yabesewal. Lenesum lebona yesetachew….

 14. Anonymous November 2, 2014 at 4:25 am Reply

  Yekidusan Amlak yihichin bete kiristian mechem Aytewatim, minim enkuan yeresual lijoch meslew yemiakosluat hodachew amlakachew yehonu meri tebiyewoch bigedaderuatim

 15. Admas Keadmas November 2, 2014 at 5:05 pm Reply

  ለምን «ፓትርያርኩ»ከሕዝብ ይልቅ ለአንድ ሰው አደሉ? በትክክል ጥፋተኛ ሁነው ከተገኙ ፀሃፊው ከስልጣናቸው ቢወርዱ ምናለበት? ሞት አልተፈረደባቸው። «ፓትርያርኩ» ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከአማኙ ሕዝብ ይልቅ የፀሃፊው በስራው ለይ መቆየት ይበልጥባቸዋል ማለት ነው?

  • Anonymous November 5, 2014 at 7:47 pm Reply

   «ፓትርያርኩ» ewnet new yetenagerut

 16. Tassew Tsehaye Reda November 3, 2014 at 8:46 am Reply

  ለምን «ፓትርያርኩ»ከሕዝብ ይልቅ ለአንድ ሰው አደሉ? በትክክል ጥፋተኛ ሁነው ከተገኙ ፀሃፊው ከስልጣናቸው ቢወርዱ ምናለበት? ሞት አልተፈረደባቸው። «ፓትርያርኩ» ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከአማኙ ሕዝብ ይልቅ የፀሃፊው በስራው ለይ መቆየት ይበልጥባቸዋል ማለት ነው?እኔ በአድማሰ ሓሳብ እስማማለሁ! ግን አባታችን ምን ነካቸው? ይህ ሰውየ ለወደፍቱስ ከላይ ሁኖ ቤተክርስቲያን የማያውክበት ምን ዋስትና አለው? ኧረ ይህ ነገር የጤና አይመስልም!

 17. Tatek November 4, 2014 at 5:32 am Reply

  በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መሾም የበሸቁትና በቀኖናዊ ውሳኔው የተደናገጡት እነሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ ‹‹ይኼ ይዞ ሟች፤ለሸዋ አሳልፎ ሰጠን›› እያሉ ፓትርያርኩን ሲዘልፏቸው ዋሉ

 18. w/Maryam November 4, 2014 at 8:35 am Reply

  yigermal…mastewaln yisten, enersunm libonachewn be tihtna melso yebedelutn hizbe mie”men endiksu yadrig

 19. Tiruwork Abera November 4, 2014 at 9:50 am Reply

  የቅዱሳን አምላክ አሁንም የቀሩትን እንዲሁ አንጠርጥሮ ያውጣቸው የቤተክርስቲያን ሰዎች ሆነው ቤተክርስቲያንን የሚቦጠቡጡ፣ ቤተክርስቲያንን የሚከፋፍሉ፣ ከቤተክርስቲያንና ከምዕመናን ይልቅ ለግል ጥቅማቸው የሚሮጡትን አሁንም የቀሩትን እንዲሁ እግዚአብሔር ያጋልጣቸው፣ እግዚአብሔር አይቸኩልም ዘግይቶ እንዲህ ያወጣል! አሁንም ለቀሩት ንፁሀን የቤተክርስቲያን አባቶቻችንን ያጽናቸው፣ ያበርታቸው፣ እድሜና ጤና ይስጥልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን፣ ተዋህዶ ሀይማኖታችንን ከውስጥም ከውጭም ጠላት ይጠብቅልን ሁላችንንም በጤና በሰላም ያኑረን በፍቅር በአንድነት ያጽናን!!! አሁንም ተግታችሁ ፀልዩ!!!

  • Anonymous November 5, 2014 at 7:52 pm Reply

   eski kedmia yerasachenen hatiat neseha abat gar heden anterteren enawta….egna nen yeselassen akal behariat menbotebut.

 20. markose mesele November 4, 2014 at 12:08 pm Reply

  eresu gena bezu neger yametal ….yeteregem

 21. Anonymous November 5, 2014 at 8:49 am Reply

  በአባቶች ላይ አድሮ እዉነትን የገለጠ አምላክ ይክበር ይመስገን፤ አሜነን!!!

 22. Anonymous November 5, 2014 at 7:50 pm Reply

  ye kahnatu tefat altayegnem….ewnet new yetenagerut. Mahberu sent tefat eyalebet begulbet new endayketa yehonew. Hager bawekew tsehay bemokew guday mekeraker ayasfelgem. ene «ፓትርያርኩ» behon…mot yetemegnelegnem kes aswegez neber….gen «ፓትርያርኩ» tagash nachewena zem belewal.

  • g/silasie w/amanuel November 18, 2014 at 8:50 am Reply

   Ante Neger ed Elias neh? leba, kehadi.

 23. hiwot November 6, 2014 at 7:58 am Reply

  በእዉት አምላክ በአእገግዘዚአበብሀሄረር ደሰስ በለሎኘኛለል

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: