የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልና በማጽናት ተጠናቀቀ፤ የፓትርያርኩ ምሬትና ብስጭት ያሳሰባቸው ብፁዓን አባቶች ሲያረጋጓቸው አመሹ

His Holiness Abune Mathias with thier Graces the Archbishops

 • ‹ከሕዝብ አጋጫችኹኝ፤ ከወንድሞቼ አንድነት ለያችኹኝ፤ ከነገራችኹኝ አንዱንም የተቀበለኝ የለም›› በሚል የተመረሩት አቡነ ማትያስ ምክራቸው ያልሠመረላቸውን ሦስት አማሳኝ አማካሪዎችን በከፍተኛ ድምፅ ‹‹ውጡልኝ›› በማለት ከፊታቸው አበረሯቸው፡፡
 • ከትላንትናው የስብሰባ ውሎ መጠናቀቅ በኋላ ፓትርያርኩ የነበሩበት የምሬትና የብስጭት ኹኔታ ተነግሯቸው ወደማረፊያቸው የተጠሩት በሹመት ቅድምና ያላቸው ብፁዓን አባቶች÷ አቡነ ማትያስ በተጠሪነት ጉዳይ የተሟገቱለት አቋም የቤተ ክርስቲያን እንዳልኾነ፣ ለአጭር ዕድሜ የኖረው የቤተ ክርስቲያን ሕግ መለወጥ እንደሌለበት ይልቁንም የአማሳኞችንና የባዕዳንን ምክር ከመስማትና ከመቀበል ተጠብቀው ትላንት ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋራ ኹነው የተከላከሉለትን ሕገ ቤተ ክርስቲያን ማስከበራቸውን ቢቀጥሉ በእርሳቸውና በአባቶች መካከል ያለው ውጥረት ሊረግብና ሊተራረቅ እንደሚችል አመልክተዋቸዋል፡፡
 • ፓትርያርኩ በትላትናው ምሽት አማሳኞቹን በብስጭትና በምሬትም ቢኾን ከአበረሯቸውና በብፁዓን አባቶች ምክር ከተጽናኑ በኋላ በዛሬው የምልአተ ጉባኤው ውሎ ስብሰባውን በተረጋጋና በመግባባት መንፈስ ሲመሩና ‹‹እናንተ ካላችኁት አልወጣም›› እያሉ በጋራ ሲወስኑ ውለዋል፡፡
 • የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይነት(ልዕልና) በማረጋገጥ በተጠናቀቀው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ አጀንዳ፣ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እያንዳንዱ ሊቀ ጳጳስና ኤጲስ ቆጶስ(ጳጳስ) ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶሱ እንደኾነ ጸንቷል፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ኾኖ ሲሠራበት የቆየው ልምድ በማሻሻያው ተካትቶ እንዲደነገግ ተወስኗል፡፡ በልዩነት ነጥቦቹ ላይ በተላለፉት ውሳኔዎች መሠረት ረቂቁ ተስተካክሎ ሲቀርብ በምልአተ ጉባኤው አባላት ፊርማ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል፡፡
 • በደቡብ አፍሪቃ በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብና በምእመናን መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት መፍትሔ ለመስጠት በቀረበው የአጣሪ ልኡክ ሪፖርት ላይ የመከረው ምልአተ ጉባኤው÷ ብፁዕነታቸው ለጊዜው መንበረ ጵጵስናቸውን በናይሮቢ አድርገው በኬንያ፣ በጅቡቲና በሱዳን ተወስነው እንዲሠሩ፤ በደቡብ አፍሪቃ ደግሞ አገልግሎቱ በአድባራት አለቆችና በሰባክያነ ወንጌል ላይ ተመሥርቶ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡ ምልአተ ጉባኤው በሰሜን አሜሪካ በሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ጉዳይ መምከር ጀምሯል፡፡
 • ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ራሱን የቻለ ሊቀ ጳጳስ ስለመመደብና በሀገረ ስብከቱ የተፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ በነገው ዕለት በመምከር ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡
Advertisements

26 thoughts on “የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልና በማጽናት ተጠናቀቀ፤ የፓትርያርኩ ምሬትና ብስጭት ያሳሰባቸው ብፁዓን አባቶች ሲያረጋጓቸው አመሹ

 1. Tenaw Aytegeb October 30, 2014 at 6:39 pm Reply

  E/r Yimesgen! Enanten/Hara tewahidowochi E/r yanurilin!

 2. Arega October 30, 2014 at 6:39 pm Reply

  Abune Matias Ken, yewahena ena deg abat nachew…….WEDEDKUACHEW. Be adebabay mister lay poletika aychawetum. Fit lefit new minagerut.

 3. Anonymous October 30, 2014 at 6:40 pm Reply

  Selam HT
  Please post your article and news in pdf form too so as to address the news to many users

  Thank you

 4. Serkalem October 30, 2014 at 6:41 pm Reply

  correct !!!

 5. Anonymous October 30, 2014 at 7:44 pm Reply

  Betu abatathen bimelesu tariken bemelekam bitefu yesalutale tarikawi Deneget kemeserat EGEZIABEHAIRE yetebeku

 6. Anonymous October 30, 2014 at 7:54 pm Reply

  Mente aseyo le EGEZIABHIERE …….

 7. Anonymous October 30, 2014 at 8:43 pm Reply

  who is that with bishops, please change these picture or cut out by animating,
  haw he stand with arch bishopes.

 8. Anonymous October 30, 2014 at 8:45 pm Reply

  Beka awerthe chresk weregna

 9. Bisrat October 30, 2014 at 9:55 pm Reply

  Thanks to the Almighty God: whose interference made everything as it should be.

 10. dawit October 31, 2014 at 3:40 am Reply

  ere yemenigist yaleh addis ababa hagere sibketin ato belay sheto cheresew tewu diresulet temarerin eko fitih tefa ebakachihu lemimeleketew nigerulin

 11. Teddy October 31, 2014 at 4:40 am Reply

  እነሆ መልካምን ዜና ነገራችሁን…..እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን….

 12. Anonymous October 31, 2014 at 4:53 am Reply

  wushet ayalkbachihum?
  Ewunt ena ngat eyadere yteral.

 13. Gebreyesus October 31, 2014 at 4:57 am Reply

  አባቶቸች እንደዚህ በአንድ ቆማችሁ ስትታዩ እንዴት ያስደስታል ፈጣሪ በመንፈስም አንድ ያድርጋችሁ፡፡ የሰይጣንን እና የ መለያየት መንፈስን ያርቅላችሁ፡፡ ነገር ግን ቤተክርስቲያን ሁሌም ቢሆን ከፈተና ተለይታ አታውቅም የፈጣሪ መንፈሳዊ ሃይል እና የ እመቤታችን ተራዳኢነት ስለማይለያት አንድም ቀን ወድቃ አታውቅም፡፡

  እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ይጠብቅ

 14. Ashenafi Mesele October 31, 2014 at 5:34 am Reply

  እግዝኣብሔር ይመስገን። ተሳሳትኩኝ፣ ይቅርታ መባባል ሲኖር ደስ ይላል እግዝኣብሔርም ደስ ይለዋል።

 15. Wolde-Tinsaie October 31, 2014 at 6:09 am Reply

  በነጻ አዕመሮም ስናስበው አንድ ሰው ከወሰነው ብዙሃን አባቶች መክረዉ የወሰኑት እንደሚበልጥ አያጠያይቅም፡፡
  እግዚአብሄር ይመስገን! በእልክና በጥላቻ ሳይሆን በማስተዋል፤ በጥበብና በፀሎት ከበረታን ሁሉም ነገር ለበጎ ነው፡፡ እስራኤልን በግብፅ አስጨንቆ ፈርኦንን በእልክ አጽንቶ እስከዘለዓለም የሚተረክ አሰደናቂ ታምር ተፈጸመላቻው፡፡አምላካችን በቸርነቱ ቤተክርስቲያንችን ያፅናልን፤ አንደ ሙሴ፤ ኤልያስ፤ ዮሀንስ የፀና ሲኖዶስ ያድርግልን፡፡ ነቀፋ የሌለባቸዉ አባቶች ይስጠን፡፡ አሜን!

 16. Tassew Tsehaye Reda October 31, 2014 at 6:32 am Reply

  ዋናው በሓሳብ መለያየት ሳይሆን በመጨረሻ አንድ መሆን ነው ዲያብሎስ በማደርያዎቹ እያደረ አባቶችን ለመለያየት ብጥርም ከነሱ ጋር ያለው መንፈስ ቅዱስ ሰለሆነ ያሸንፉታል

 17. Anonymous October 31, 2014 at 7:16 am Reply

  Egziabher Hayal Newu !!!!!! In any ways our worry was the UNITY and STRENGTH of the HOLLY SYNOD. We have heard this news, thanks to GOD!!!!!!!!
  Me and We true children of the Church MUST respect and implement what ever is decided by the Holly Synod!!!!!!!!

  Tesfa’legn Ze Debre Eba

 18. Barken October 31, 2014 at 8:36 am Reply

  ምነው? .. ‹‹በቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ ከቅዱስ ሲኖዶስ ይልቅ፣ ከብጹአን አባቶች ይልቅ ፣… እነዚህ የቀን ጅቦች፣ የአውሬው ተከታዮች … ዓላማዬን ስለሚያስፈጽሙልኝ ነው ከእነሱ ጋር አንድነቴ፣ ወዳጅነቴ፣ ህብረቴ … በአደባባይ ሲሉ ከርመው፤ አሁን ከሕዝብ አጋጫችኹኝ፤ ከወንድሞቼ አንድነት ለያችኹኝ፤ ከነገራችኹኝ (‹‹ከዓላማዬ››) አንዱንም የተቀበለኝ የለም… ምናምን፣ ምናምን … የሚሉት›› ምን ገጠማቸው? ጊዜ ለመግዛት ነው?››.. ይህ ተግባር ታሪክ በማይረሳው ማህደር ተመዝግቦ ለዘላለም ይኖራል፣ በሰማዩ በፍርድ አደባባይ የቅዱሳኑ አምላክ ለፍርድ ይገልጠዋል፡፡ ግን ቤተክርስቲያንን ለማሸነፍ አይቻልም ቤተክርስቱያን ሁል ጊዜ ትዋጋለች ተሸንፋ ግን አታውቅም ዲያብሎስ ዝናሩን አራገፈ ቀስቱን ጨረሰ…፡፡ ቤተክርስቲያንን ግን እስከ ዓለም ፍጻሜ ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች፡፡›› ምክንያቱም መሰረቷ ክርስቶስ ነውና፡፡

  • Anonymous October 31, 2014 at 12:23 pm Reply

   Yeh website milew tekekel lemehonu men maregagecha alachuna new metedesetut…..bebuden enji bemenfes atasbum ende

  • Anonymous November 4, 2014 at 1:52 pm Reply

   Ltftrw slme tmsgen mlte ytkmal

 19. rufael October 31, 2014 at 5:38 pm Reply

  I think this moment gave us insight about the entire situation with in the ethiopian orthodox church.
  Let narrow our differences and stand together. Because whether we believe or not the enemy will not get rest until what he wants to achieve.
  Get ready for new battle, pray and watch
  Servant’s of. ALMIGHTY GOD

 20. mekonnen tafesse October 31, 2014 at 8:41 pm Reply

  interesting!

 21. Kessis Gebrekrstos November 1, 2014 at 3:05 am Reply

  I raely surprised about the patriarchal imagination ……tshal fetch tbis ametehat ale yeagere sew.

 22. Anonymous November 1, 2014 at 6:00 am Reply

  temesgen

 23. Biruk November 1, 2014 at 9:09 am Reply

  TEMESGEN!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: