ቅዱስ ሲኖዶስ: ‹‹እነማን ናቸው ከጀርባዎ ያሉት?›› ሲል ፓትርያርኩን ጠየቃቸው፤ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተጠሪነት አንቀጽ ላይ የተጀመረው ውይይት በመካረር አደረ

Holy Synod in session

 • አቡነ ማትያስ÷ የሊቃነ ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ተጠሪነት ለፓትርያርኩ በማድረግ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት የኾነውን የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይነት በፓትርያርኩ የበላይነት ለመተካት ከምልአተ ጉባኤው ጋራ መሟገታቸውን አጠናክረው ውለዋል፡፡
 • የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ያላትን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን፣ በፓትርያርኩ ዐምባገነናዊ አመራር ሰጪነት በመርገጥ በስም እንጂ በግብር የሥልጣን ልዕልና የሌለው ሲኖዶስ ለመፍጠር እየተጣጣሩ ነው፡፡
 • ቤተ ክርስቲያን አንድነትን በሚጠይቅና ከፍተኛ የጥንቃቄ ርምጃዎችን በሚሻ የህልውና ጥያቄ ላይ እንዳለች ያጤኑ የምልአተ ጉባኤው አባላት፣ ፓትርያርኩ የልዩነት ነጥቦችን በማክረር ቤተ ክርስቲያኗን ለኹለት ለመክፈል ላደፈጡ ኃይሎች መሣርያ ሊኾኑ እንደሚችሉ ተገንዝበዋል፡፡
 • ‹‹ቅዱስነትዎ በጣም ተቀይረዋል፤ እነማን ናቸው ከጀርባዎ ያሉት?›› ሲልም ጠቅላላውን ጉዳይ በጥልቅ አስተውሎት በመመርመር በቤተ ክርስቲያኗ እና በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ብቻ አጠንጥኖ መሥራት እንደሚገባ አጽንፆት ሰጥቶበታል፡፡  
 • ልዩነት በተያዘባቸው የመነጋገርያ ነጥቦች ላይ ከሌላ አካል የተመከሩበት የሚመስለውን ብቻ እየተናገሩ አቋማቸውን ከማክረር በቀር ማብራራትና መተንተን በእጅጉ እንደተሳናቸው የተነገረባቸው ርእሰ መንበሩ፣ ‹‹የነበረው ሕግ እንዳይሠራ የማሻሻያ ረቂቁም እንዳይጸድቅ›› የሚመስል ‹‹ሲኖዶሱን የመበተን›› አዝማሚያ እያሳዩ እንደመጡ ተስተውሏል፡፡

*              *             *

 • በሥራ ላይ የሚገኘው የ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያን÷ ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት ፓትርያርክ፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት የሚያደርጉት ዓቢይ ጉባኤ እንደኾነ ይገልጻል፡፡ በአኹኑ የማሻሻያ ረቂቅም ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት ‹‹ቅዱስ ፓትርያርክ፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት የሚገኙበት ዐቢይ ጉባኤ ኾኖ ከፍተኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ፣ ሕግ አውጭና አስተዳደራዊ አካል ነው፡፡›› ይላል፡፡
 • ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ እያንዳንዱ ሊቀ ጳጳስና ኤጲስ ቆጶስ(ጳጳስ) ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ እንደኾነ ‹‹የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት›› በሚለው የማሻሻያ ረቂቁ አንቀጽ ፰(፪) ተቀምጧል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አበው (አበ ብዙኃን) የኾነው ፓትርያርኩ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤንና የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን በሊቀ መንበርነት(በርእሰ መንበርነት) ይመራል፡፡ ይኸውም ለመላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ‹‹የበላይ ጠባቂ፣ ለአንድነትዋና ለአስተዳደርዋ ከፍተኛ ሓላፊና ባለሙሉ ሥልጣን›› በመኾኑ እንደኾነ በሰበካ ጉባኤው ቃለ ዐዋዲ ደንብ አንቀጽ ፶፪(፩) ሰፍሯል፡፡
 • ይህም ሲባል ጠቅላላው የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ከፖፑ ሥልጣን በላይ ነው የሚለውን መነሣሣት (anti-papal concilliarism) በመቃወም፣ ፖፑ ‹‹የማይሳሳት የክርስቶስ እንደራሴና የአብያተ ክርስቲያናት ኹሉ የበላይ›› አድርጋ የፖፑን የሥልጣን የበላይነት (Primacy) በቫቲካን የመጀመሪያው ጉባኤ እንዳጸደቀችው የሮም ካቶሊክ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ከፍተኛ የሥልጣን ባለቤት በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውና የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያንን በበላይነት የመምራት፤ የማስተዳደር፤ የመጠበቅ፤ ፍትሕ መንፈሳዊ በሚፈቅደው መሠረት ሕጎችን፣ ደንቦችንና ልዩ ልዩ መመሪያዎችን የማውጣት፣ የማሻሻል፣ የመሻር የዳኝነት ሥልጣን አለው፡፡ ቤተ ክርስቲያንንና የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ነው፡፡
 • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ሕገ ቤተ ክርስቲያን አተረጓጎም፣ ‹‹የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር›› ሲባል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል የኾነውን በየደረጃው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ቅዱስ ፓትርያርክ፣ ቋሚ ሲኖዶስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሥልጣንና ተግባር፣ አሠራርና ዓላማ ለቤተ ክርስቲያን ዓላማዎች ማስፈጸሚያ፣ አስተዳደራዊ መዋቅሮችና ተቋማት ማቋቋሚያና ማሠርያ መመሪያ የሚሰጥበት ነው፡፡
 • ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን አካላትና የቤተ ክርስቲያንን አጠቃላይ ስብሰባ (አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ) በሰብሳቢነት ይምራ እንጂ በዐበይት ጉዳዮች ላይ ኹሉ ሲሠራ በቅዱስ ሲኖዶሱ ማስወሰን ይኖርበታል፡፡ በፊርማው የሚያስተላልፋቸው ሕጎች፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎች ኹሉ በቅዱስ ሲኖዶሱ የወጡ መኾን አለባቸው፡፡ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ከመጠበቅና ከማስጠበቅ ሓላፊነቱ ጎን ለጎን ቅዱስ ሲኖዶሱ ያወጣቸው ሕጎች፣ ያስተላለፋቸው መመሪያዎችና ውሳኔዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይነት(ልዕልና) የማስከበር ከፍተኛ ሓላፊነት አለበት፡፡

‹‹እነማን ናቸው ከጀርባዎ ያሉት?›› …

Zekarias Addis a day light robberየአማሳኞች ዋነኛ ቡድን መሪ የኾነው ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ÷ ትላንት ተሲዓት ስብሰባው በድንገት ከተቋረጠ በኋላ ምሽት ላይ ፓትርያርኩን አግኝተዋቸው እንደነበር ተናገረ፡፡ እንደ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ አነጋገር፣ ፓትርያርኩ ከስብሰባው የወጡት ተብረክርከው ነበር፡፡ ‹‹ለማይኾን ነገር አሠቃያችኁኝ›› ብለው እንዳማረሯቸውም አልሸሸገም፡፡ ‹‹የወሰዱት አቋም ታሪካዊ ነው፤ በተለይ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ›› በማለት ‹‹መብረክረክ›› ሲል የገለጸውን አካላዊና ሥነ ልቡናዊ ቁመናቸውን ‹‹ሲያክሟቸው እንዳመሹ›› የጠቀሰው ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ፣ መንግሥት የማኅበሩ ገንዘብ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ማእከላዊ ካዝና መግባቱን እንደሚፈልግና በጉዳዩ የጀመሩትን ጠንክረው እንዲገፉበት አበረታተናቸው ደስ ተሰኝተዋል ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት በማድረግም በፀረ ተቋማዊ ለውጥ እና በፀረ ማኅበረ ቅዱሳን ቅስቀሳቸው ሆ ብለው አልነሣ ያሏቸውንና ‹‹በሸዋ ጳጳሳት በተለይ በአቡነ ማቴዎስ ይመካሉ›› ያሏቸውን የገዳማትና የአድባራት አለቆች ‹ከአዲስ አበባ ለማንኮታኮት›› ማቀዳቸውን ገልጧል – ‹‹እያንዳንዱ ጳጳስ ተሸማቅቆ እንዲሔድ እናደርጋለን፤ ማኅበረ ቅዱሳን የሸዋ ስብስብ ነው፤ ነገ ጠዋት የሸዋ አለቃ ከያለበት ደብር ሲጠፋ የምትገቡበት እናንተ ናችኹ፡፡››

Advertisements

27 thoughts on “ቅዱስ ሲኖዶስ: ‹‹እነማን ናቸው ከጀርባዎ ያሉት?›› ሲል ፓትርያርኩን ጠየቃቸው፤ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተጠሪነት አንቀጽ ላይ የተጀመረው ውይይት በመካረር አደረ

 1. Mastewal October 29, 2014 at 11:46 pm Reply

  pls eliminate the last sentence…. yeshewa, yetigre … is not christianawi at all. PLEASE in the name of God … stop disseminating hate

  I’ve sadly seen in it everywhere, but I am incredibly disappointed to read it in this blog..

  Don’t split our Fathers by their tribes…. Wherever they come from they are our Fathers
  Bemeskelu And honenal eko

  • Senait October 30, 2014 at 11:30 am Reply

   I agree with Mastewal, plz eliminate the last paragraph

 2. Getinet Seifu October 30, 2014 at 1:35 am Reply

  Egziabiher Iyine libonachew letawere Iyine libonachewun Yabralachew.
  Melkamun hulu le kidist betekiristiyanachin lemiyasibu idmeyachewun
  yarzimilin!

 3. Anonymous October 30, 2014 at 2:08 am Reply

  what are you talking about? Are you telling us the bishops and archbishops are not subjected to the holy patriarch? are you all foolish enough? according to the spiritual law of the Orthodox Church and holy canon laws of the Orthodox Church each bishops and archbishops subject to the Patriarch. but our bishops and archbishops stand together against this. because they do not want to follow the right way of the Church laws. let me tell you this, in order to the save our church, we have to stand with the right one. the patriarch is hundred present right. he is straggling for the true church not for himself like others.
  I can say, our Lord Jesus Christ, hears the prayer of our fathers who are praying day and night . the dirty management of the our Church must be cleaned and enough is enough.
  we have to stand together for the truth.

  • Anonymous October 30, 2014 at 8:01 am Reply

   dedeb neh you are very very stupid

  • Natnael lulie (@ylulie4) October 30, 2014 at 7:24 pm Reply

   100 present 😀 percent lemalet new?Limatawi neger neh!!!

  • unknown October 31, 2014 at 5:36 am Reply

   I disagree with mastewal. this meeting is not about Christianity. it is about what we have seen. and what we have seen is very bad. nothing to do with Christianity. so we need to know who is who. what ever the work he use people have the right to know what is going on over there. the patriarch have a target which is given by Antichrists. we have seen that he has a lot of weakness. if he say that why do you try to eliminate and hide his word? it should not be edited. we need uncut new. then we decide. other wise you can spent your time with ETV. that is all. do not discourage the blogger.

 4. Anonymous October 30, 2014 at 4:21 am Reply

  Balege neh eshi kahnun ante tilaleh. Minale tiwlidun abatochun tesadabi bataregut

 5. Anonymous October 30, 2014 at 5:38 am Reply

  besimet enji beewket yetedegefe tsehuf bihon rasen yasmeseginal anbabin yanitsal ok. gin yemitayew abzagnawin simetawinet newuna bitasebibet!!!!! be orthodox kehone patriyarich yesinodos texeri new be catholik kehone degmo sinodos ye popu texeri new leyeten benayew melkam new yehe tefalese malet orthodox yekatolikin structure teketelech malet new. endih kehone degmo bezu yemifales menfesawina metsehaf kidusawi sreat ale

 6. Anonymous October 30, 2014 at 6:33 am Reply

  ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስን ከማንም በላይ የማኅበረቅዱሳን አባላት ያውቁታል(አንተ የምለው በጥቂቱ ስለማውቀው ነው)፡፡በተለይ ጅጅጋና ሐረር ስ/አስኪያጅ እያለ ለአመታት ከማኅበሩ ጎን ቆሞ ተሐድሶዎችን በመዋጋት ከፊት ለመሰለፍ አላመነታም፡፡እውነት እናንተ ኦርቶዶክሳውያን ከሆናችሁ፣እውነት እናንተ ማዕተብ ባንገታችሁ ካለ ግዴለም ጠይቁ፡፡የሐረር ማዕከል የማኅበረቅዱሳን አባላትን ጠይቁ፡፡አሁን እየሰራ ያለውን ለማወቅም ሲ ኤም ሲ ሚካኤልን ሂዳችሁ ጎብኙ፡፡ሸዋ-ትግራይ የሚለውን አቁሳይ አካሄድ ወደ ምዕመኑ ከመዝራታችሁ በፊት ግለሰቡ ባስተዳደራቸው አሕጉረ ስብከቶች ውስጥም ሆነ አድባራት የነበሩ የሸዋ ሰዎች ስላሉ እነሱን ጠይቁ፡፡
  አውቃለሁ ይሄን ጽሑፍ አታወጡትም፡፡ግን እባካችሁ ስለፈጠራችሁ ካሕኑ ከዚህ በፊትም እንደነበረው እንደባህርይው ይይዘዋል፡፡ጸቡንም እርቁንም እነሱ ያውቁበታል፡፡እናንተ ግን ነገሩን እያራገባችሁ የዋሑን ምዕመን እንዳትከፍሉት፡፡ስለፈጠራችሑ፡፡ስለ ቤ/ክ አምላክ፡፡
  ሊቀ ትጉሃን ላይ የሚወራው የሙስና ሐሜት እውነት ከሆነ ማስረጃ ቀርቦ ማስረጃው ላይ እሱም መከላከያውን እንዲያቀርብ ተፈቅዶለት በሕግ በሥርዓቱ ይዳኛል፡፡ዘወትር አብሮን ነው፡፡ከሀገር አልወጣ፡፡ምነው ወንድሞቼ የእርስ በርሱ ሳያንሰን ለሕዝብ ሚተርፍ ጥላቻ ውስጥ የምትከቱን፡፡እውነት አይምሰላችሁ፡፡አባቶች ዛሬ እንዲህ ቢጨቃጨቁ ነገ መልሰው ይገጥማሉ፡፡ይሄ ሲሆን ብዙ ጊዜ አይተናል፡፡ጥላቻው ወደ ሕዝብ ሲወርድ ግን መልካም አይደለም፡፡ስለፈጠራችሁ እንዲህ አይነት አንባቢን የሚያንጽ ሳይሆን የሚያናውጽ ዘገባ አታቅርቡ፡፡እንጎዳባችኋለን፡፡ይቺን አስተያየት እንድታወጧት በወላዲተ አምላክ ሥም እማጸናለሁ፡፡

 7. men elalhu October 30, 2014 at 6:44 am Reply

  sel kedumt abatoch endanenager afe tyezal Geta hoy engedhi men enelalen

 8. Anonymous October 30, 2014 at 6:52 am Reply

  Ibakachu yebetekrstiyanuan sirat yematawku menafikan ijachihun sebsibu.Manim Patriyark.Abune Pawulosin chemiro ine kesinodosu belay lihun weyim mehon yigebagnal alalum .

 9. Meseret Beyene October 30, 2014 at 7:21 am Reply

  Wondime, begna be Orthodox malya lelela lemechawot asbeh kehone ayichalim b/c Our church have a lot of good players inside.Therefor,we couldn’t need any support.You said that close your eye and let us cheat u. It is impossible.Doron seyatalilua…..

  • Abebe October 30, 2014 at 6:35 pm Reply

   Betekerestianachen menfesawi heywet yalew sew enji techawach tefelgal beye alamnem. Be emnet hulum yechalal. Chewata le mengest ena le alem new.

 10. DS October 30, 2014 at 8:01 am Reply

  @3rd comment
  Friend you are writing only your emotion. Yes according to the catholic tradition, the POPE is the supreme. but according to ours it is the holy synod above every one. So how on earth can our patriarch be right? He is backed by Woyane as was ever. He is fighting to safe guard the political territory of EPRDF. He has dropped every spiritual responsibility. He is destructing the church from the inside. He is aganist the holy sprit and Holy synod. He will be aganist the whole christians. Chriastians will at the end fail to follow him

 11. Anonymous October 30, 2014 at 8:30 am Reply

  ‹‹እነማን ናቸው ከጀርባዎ ያሉት?››

 12. Anonymous October 30, 2014 at 8:33 am Reply

  Ay mahibere seytan kemechew zorachuhibachew patriarkun sitamokashuachew alneber ende????? Demo bemin tegenagnachu ?weretegnoch.

 13. Tassew Tsehaye Reda October 30, 2014 at 8:46 am Reply

  «ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።
  ኢዮስጦስም የሚሉትን በርስያን የተባለውን ዮሴፍንና ማትያስን ሁለቱን አቆሙ።
  ሲጸልዩም። የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ፥ ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው አሉ።
  ዕጣም ተጣጣሉላቸው፥ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀና ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ።»
  (የሐዋርያት ሥራ 1 :21-26 )
  እንግድህ ቤተክርስትያናችን ሐዋርያዊት ናት እንላለን ግን የኛ የሊቀ ጳጳ አመራረጥ ግን ከሐዋርያት በፍጹም የራቀ እና የእግዚአብሔር ፍቃድ ሳይሆን የሰው ፍቃድ ያመዘነበት ምርጫ ነው የምንፈጽመው ለምን እንደ ሐዋርያት «የመረጥኸውን ከእነዚህ አንዱን ሹመው» አንልም?

 14. ተስፋዬ October 30, 2014 at 9:36 am Reply

  ሌላው ጠቅላያችን ለመሆን ያሰቡ ይመስላሉ !ያደረባቸው አጋንንት በፆምና በፀሎት እንጂ ከ ካድሬና ከመናፍቃን ጋር በመዋል አይለቃቸውም !!

 15. Abebe October 30, 2014 at 11:19 am Reply

  Mahberu be betekerestian akal west new belew asrat endemikebelu, ke gebi gubaewoch le hentsa le methaf eyetebale bezu genzeb endemisebeseb, lenedayan eyetebale dabo tesebsebo tesheto gebi gubaeyat bemahberu yetekemetebachwen eda kenedayan aff eyewesedu lemahberu endemiasgebu, mahberu lay comment yesete agelgay hulu bederesebet hulu endisaded meleekt endemitelalefbet, senbet temhert betochena sebeka gubaeyat bemahberu abalat teyzew yemahberun akuam becha endiaramedu mikarenew hulu endisaded endemidereg, ye senbet temehrt betoch yemahberu methafat endishetu leoch methaf azegajoch endayshetlachew gefit endemidereg, papasat mercha lay mahberu degafiwochu becha endimeretu endemirawet, abatochen des endalew kefena zek argo menagerm endale, ena lelochem endemihonu enew rase aychalew…..helinaye aykebelewem…..this is not christianity…..mahberu tefetnoal…..hulachenem entselyelet….Melkamun menged hulu endiyezem emegnalew….etselyalew….Amlakachen Egziabher kekfu neger hulu yetebkew. Amen….menem bihon melkam asbo tenesto neber….ahun gen aktacha melewet ameta. Kahun behuala mahberu menenem selegenzeb lemewkes moral yelewem. Yasaznal. Mahberu genzebun kesete yetefal yemil emnet yelelew astesaseb kegenebam tesastoal. Yemahberu minafek agelglot yeneberew dero genzeb saynorew neber. Ahunem Emnetachenen begenzeb sayhon befeteren lay enadreg. Yeh neger hulu Egziabher endalew yehonal. Abune Matiasem hone amasagne metloachew eyalut yalewena enante eyastegabachu yalachut fetsemo endemileyay mawek kelal new. Tebareku new melew ene….bereket nachehu….asadaj nachehuna benante bereket yegenal. LEMIREGMACHU MERKU, LEMIASADEDACHU TSELEYU, YEMITELUACHEHUN WEDEDU …..Amlakachen Egziabher betsedkna beneseha kesu gar endedenor hulachenenem yerdan. Amen.

 16. Anonymous October 30, 2014 at 1:08 pm Reply

  betame

 17. Anonymous October 30, 2014 at 1:23 pm Reply

  Dear readers first and foremost please know what is the real agenda of the patriarch. His holiness is clean from any ethnic thinking, from any theft and other immoral and corruption seen in some bishops. And his integrity will be a good opportunity for the church. From his deep love of the church he boldly says no more theft, corruption in the church, Whether it is done by bishop, management or association like mahber kdusan. This is the real agenda of the patriarch. But some bishops and mahbre kdusan stand against of it? all of us we should questioned them why they are against of it, and why they up and down to favor disorder in our church. Please move, give your voice to have corruption free church. It is a golden time to clean the church we shouldn’t miss it. Try to know the truth by asking again and again, don’t give a chance to those who work to make us blind.

 18. Anonymous October 31, 2014 at 1:37 am Reply

  ይሄ ዌብሳይት የፖለቲካ ነው የሃይማኖት ለምን ሰዎችን ትከፋፍላላቹ ከናንተ በረሶ የሰውን ጉድፍ ካልነቀስኩ ትላላቹ መች የራሳቹን ጉድፍ ነቀሳቹ ማህበርን እንደግፋለን ብላቹ ቤተክርስቲያን አትናዱ

 19. elias October 31, 2014 at 3:30 am Reply

  by z way beminim melekiya and sew bichawin tikikil ayihonim!! hulum papasat and ayinet aquam lemin liyizu chalu? hulum legenizeb yaderu nachew? yemayimesil neger new tewededem tetelam patriyariku ke sinodosu gar mesimamat alebachew that is!!

 20. Fikremariam Wodajo October 31, 2014 at 8:29 am Reply

  ተሀድሶዎች የሰራችሁት መዋቅርና የምክር መንገድ አላዋጣም፡፡ እውነት አሸንፋለች፡፡ ገና ገና……

 21. Anonymous May 28, 2016 at 1:52 am Reply

  ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ጥሩ አይደላችሁም በቀድም ስብሰባችሁ የተናገሩት የማህበረ ቅዱሳንን ህልውና ለማደብዘዝ ከመንግስት አካላት ጋር ሆነው መከራ አድርሰውብናል በዚህ ይብቃዎት አያጭበርብሩ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: