ቅዱስ ሲኖዶስ: የፓትርያርኩን የአጠቃላይ ጉባኤ የስብሰባ አመራር በመገምገም ለሥነ ሥርዐቱ መከበር ውሳኔና መመሪያ ሰጠ፤ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ላይ መወያየት ጀመረ

 • ምልአተ ጉባኤው በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የጋራ መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ ላይ መክሮ አጽድቋል፤ በሥራ ላይ እንዲውልም መመሪያ ሰጥቷል፡፡
 • ከአጠቃላይ ጉባኤው አጀንዳ ውጭ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ለማስወሰን ታቅዶ በፓትርያርኩ ግፊትና በአማሳኞች ውትወታ የተከፈተው መድረክ÷ ስብሰባው ‹‹ባለቤት የለውም ወይ?›› ያሰኘና የአጠቃላይ ጉባኤው ክብረ ሞገስ በርእሰ መንበሩ አመራርና የቀጥተኛ ተሳትፎ መብት በሌላቸው አማሳኞች ሥርዐት አልባነት የተጣሰበት እንደነበር ገምግሟል፡፡

  the heavily corrupt Haile Abreha barking on the multitude of the participants of the 33rd gen assembly

በ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ የመጨረሻው ቀን በነበረው የውይይት መርሐ ግብር ወቅት ነው፡፡ በእግራቸው አዳራሹን እየተመተሙ፣ በስኳር ማንኪያ ብርጭቆውን እያቅለጨለጩ አማሳኝነታቸውንና ኑፋቄአቸውን የሚያጋልጧቸውን ተሳታፊ ጉባኤተኞች ሊያሸማቅቁ ሞክረው ያልተሳካላቸው ጥቂት ኹከተኞች በፈጠሩላቸው ሙቀት የተበረታቱ የሚመስሉትና በታዛቢነት ብቻ መገኘት ያለባቸው የደብረ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ ሲናገሩ፣ ‹‹እኛ ታጥቀን ነው ያለነው›› አሉ፡፡ በነፃ መሬት ያካባቢ ምልሻ የነበሩበት ጊዜ ታወሳቸው መሰል?

ከሙስናው ‹ምቾት› ጋራ በየጅምናዚየሙ ዱብ ዱብ ማለታቸው እንኳ ባያስከፋም በንግግራቸው ይዘት ከርእሰ መንበሩ ጋራ አንድ ቃል በነበሩበት በዚያ መድረክ ‹‹ታጥቀናል›› ለማለት መድፈራቸው አሳፍሮናል፡፡ ድፍረቱም ቢኾንኮ ከዕውቀት የጸዳ ጩኸት ብቻ እንደኾነ ወዲያው ተገለጸ! ለነገሩ ‹‹ምንትስ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል›› አይደል የሚባለው! ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ‹‹ሲንግል ኢንትሪን እየተውኹ ወደ ደብል ኢንትሪ ለመግባት እየተንደረድርኹ ነው፤›› እያለ እንኳ ማኅበረ ቅዱሳንን÷ ‹‹እስኪ ምን ትኾናላችኹ፤ ወደ ሲንግል ኢንትሪ ኑ፤ ሲንግል ኢንትሪ ተጠቀሙ!›› ማለትዎ ትጥቅዎና አካላዊ ግንባታዎ ከሚያሰማዎ ጉልበተኝነት በቀር ከሌላ ከወዴት ይመነጫል? አባታዊነትም ሳይንሳዊነትም የራቀው ነውና!!

ያለመንፈሳዊና ትምህርታዊ ትጥቅ አባታዊነቱም ሳይንሳዊነቱም ከወዴት ይገኛል? ስለ እርስዎ አደገኛ አማሳኝነት በተደጋጋሚ መዘገቡን ራስዎን ‹‹ያለትራንስፖርት በዓለም እንደማስተዋወቅ›› ካስደስትዎ እንግዲያው፣ የአማሳኙ ቡድን ሎጅስትክ ኾነው ከሚበትኑት ብር ባሻገር የቤቶች፣ የሲኖ ትራክና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ባለንብረትነትዎ ሕጋዊነት ተሰፍሮ ተቆጥሮ እስኪረጋገጥ ድረስ ከዚኽ የተሻለ ማስተዋወቂያ አናገኝልዎትምና እናዝናለን፡፡


 •  በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የማሻሻያ ረቂቅ÷ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ተጠሪ የሚያደርገውንና የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይ አካልነት የሚያሳየውን አንቀጽ፣ ለፓትርያርኩ ለማድረግና በፓትርያርኩ ዐምባገነናዊ አመራር ሰጪነት ለመተካት በልዩ ጸሐፊያቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በኩል ሙከራ እየተደረገ ነው፡፡
 • በረቂቁ ላይ ተጨማሪ ማስተካከያ አድርጎ እንዲያቀርብ በምልአተ ጉባኤው በተሠየመው ኮሚቴ ውስጥ አንዱ አባል የኾኑት ልዩ ጸሐፊው÷ በማኅበራት ዕውቅና አሰጣጥ፣ የመተዳደርያ ደንብን በማጽደቅ፣ በማሻሻል፣ በመሰረዝና በማገድ አሠራር ተጠሪነታቸውን ለፓትርያርኩ በማድረግ ‹‹ማኅበራት አያስፈልጉም›› የሚለውን አቋማቸውን ገቢራዊ ለማድረግ እየጣሩ ነው፡፡
 • በተለያዩ አህጉረ ስብከት በቀደሙት ብፁዓን አባቶች ብርቱ ጥረት የተቋቋሙት የሕፃናት መርጃ ማእከላት፣ የማእከላቱን አስተዳደርና የቤተ ክርስቲያንን ተቋማዊ አሠራር በሚቃረኑ ደንቦችና መመሪያዎች የግለሰብ ሓላፊዎች መጠቀሚያ የኾኑበት፤ ቤተ ክርስቲያን በማታውቃቸው ውሎች መዘዝ ነባር ይዞታነታቸው ጥያቄ ውስጥ የወደቀበት ውዝግብ ተጣርቶ እንዲቀርብ ምልአተ ጉባኤው ትእዛዝ ሰጥቷል፤ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
 • ለሕፃናት ማሳረፊያ እንዲኾኑ በተሠሩ ቪላ እና ሰርቪስ ቤቶች ውስጥ ጠቅልለው ገብተው እየኖሩ የግል መኖርያ ቤታቸውን በከፍተኛ ዋጋ እንዳከራዩ የሚነገርባቸው የሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት ዋና ሓላፊ በቅዱስ ሲኖዶሱ ተጠርተው ተጠይቀዋል፡፡
 • የዕጓለማውታ ሕፃናቱን ጤንነት ለመከባከብ በክሊኒክ ደረጃ ተጀምሮ ወደ ጠቅላላ ሆስፒታል ያደገው የምግባረ ሠናይ አጠቃላይ ሆስፒታል ከውጭ የምግባረ ሠናይ ድርጅቶች ድጋፍ ተላቅቆ ራሱን ወደ ልማት ማእከልነት በመለወጥ በራሱ ገቢ ከመተዳደር አልፎ ዓመታዊ ገቢውን ወደ ስምንት ሚልዮን ብር ማድረሱ በድርጅቱ ሓላፊዎች ተገልጧል፡፡ ይኹንና ‹‹ተጠሪነቱ ለማን ነው? አናውቀውም›› የሚል ጥያቄ በፓትርያርኩ እንደቀረበበት ተሰምቷል፤ የመሬት ይዞታውም እየተገፋ ለግለሰቦች ጥቅም መዳረጉ የተነገረ ሲኾን ‹‹ኦዲትም አያውቀውም›› ተብሏል፡፡
Advertisements

4 thoughts on “ቅዱስ ሲኖዶስ: የፓትርያርኩን የአጠቃላይ ጉባኤ የስብሰባ አመራር በመገምገም ለሥነ ሥርዐቱ መከበር ውሳኔና መመሪያ ሰጠ፤ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ላይ መወያየት ጀመረ

 1. Anonymous October 28, 2014 at 12:32 pm Reply

  ግራ የሚገባኝ ነገር…..
  መጽሀፍ ቅዱስ ባገላብጥ ባገላብጥ የትኛውም ህትመት ላይ ኢየሱስ ሲሳደብ አላነበብኩም፡፡ እግዚአብሄር የሚገስጽ እንጂ የሚሳደብ አምላክ አይደለም፡፡ ይህን ያስተማረን ታላቁ መጽሀፍ መጽሀፍ ቅዱስ ነው፡፡ በአለማችን ያሉ የነበሩም ቅዱሳን ያስተማሩን ትህትና እና ፍቅርን እንጂ በየትኛውም የቅዱሳን ገድል ላይ ስድብ አልተጻፈም፡፡ በአለም ላይ ተጋድሎ ያደረጉ አባቶች የስድብ ቃል ትንፍሽ አላሉም ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ ታላቅ ክርስቲያናዊ ተግባር ከሆነ የዚህ ዘመን ትውልዶች ስድብ ከማን ተማርን; ስድብ የዲያቢሎስ ግብር እንጂ የመንፈስ ቅዱስ ባህሪ አይደለም፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ አሉባልተኝነት፤ጭፍን ጥላቻና አስነዋሪ ስድብ ከየት አመጣነው ስለክርስቶስ ፍቅር የሞቱ አባቶቻችንን እያነሳን በስማቸው እየማልንና እየተገዘትን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያን ስም እናቴ እናቴ እያልን እየጠራን ምን የሚያክል መስቀል በአንገታችን አንጠልጥለን አርብ እሮብን ጨምሮ አጽዋማትን እየጾምን በሞባይሎቻችን ሆድ የአለምን እርኩሰት ቀድተን በኤር ፎኖቻችን ስናዳምጥና ዘፈንና ዘፋኝነትን ስናደንቅ ውለን አድረን፡፡ በእግዚአብሄር አገልጋይ ንጹህ የዝማሬ መስዋት የምንዘባበት፤በእግዚአብሄር ንጹህ አገልጋዮች ካህናትና ዻዻሳት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እና ንቀት የምናሳይ እኛ ማነን የትኛው እየሱስ የትኛዋ ቤተክርስቲያን ይህንን እርኩሰት አስተምራናለች ለአይናችን ብሌን ያስጠላንን አገልጋይ ጅራትና ቀንድ እየቀጠልን ተኩላና ቀበሮ ስናደርገው እግዚአብሄር ስለአገልጋዮቹ የማይገደው ይመስለን ይሆን በፍጹም እግዚአብሄር ፍቅርም ተዋጊም ነው፡፡ ይታገሳል የዘገየ ቢመስልም በፍጥነት ይደርሳል፡፡ ትውልድ ልብ እንበል፡፡

 2. Endeshaw Aweke October 28, 2014 at 2:39 pm Reply

  Ergnachen ayanklafam aytegname teblo tetsfual,,,

 3. Anonymous October 28, 2014 at 3:39 pm Reply

  ebakachu sidib yibika, lebete krstian yemihonatn wusane e/r keegna belay yawkalena ,yilk le abatoch asteway libonan endisetlin tegten entsely….

 4. Anonymous October 29, 2014 at 10:38 am Reply

  በማቲዎስ ወንጌል የመጨረሻው ዘመን ምልክቶች ተብሎ ከተዘረዘሩት ውስጥ አውሬው/666/ በእምነት የበቁትን ሁሉ እስከማሳት ይደርሳል እና አትደነቁ ሲል ጊዜው ገና የሚሆን እና የበቁ የሃይማኖት ኣባቶችም ቢሆኑ እንዲህ አይን ኣሳውሮ በማያስት ጉዳይ ያስታቸዋል ብዬ ኣላስብም ነበር። እንዲህ ከሆነ በጣም ያስፈራል። ሰለሌላው ትቶ ፈጣሪ የአውሬውን መንፈስ በቸርነቱ ድል እንዲነሳልን ቀን ከሌት በፀሎት መማፀን ያሻል። ነግሦ የሚታየው ክፉ መንፈስ ወደ ሌሎቻችንም እንዳይዛመት ተግተን እንፀልይ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: