ሰበር ዜና – ‹‹አቦይ ስብሐት ጎበዝ ነኽ አለኝ›› ያሉት ፓትርያርኩ የማኅበራትን ተጠሪነትና የገንዘብ እንቅስቃሴ በሚመለከተው የሕጉ ረቂቅ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ተፋጠው ዋሉ

Aba Mathiasoo

ርእሰ መንበሩ ስለማኅበራት በያዙት አቋም ከምልአተ ጉባኤው ስብሰባ በፊት ‹ከአ/አ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች› ጋራ ብዙ ሲሠሩበትና ሲደክሙበት የሰነበቱ መኾኑን ‹‹ስንት የደከምኹበት ነው፤ በቀላሉ የምተወው አይደለም›› በማለት ፍርጥም ብለዋል፡፡

 • ፓትርያርኩ የማኅበራት ገንዘብ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ገቢ ኾኖ በማእከል ካልተመራ በሚል ከማኅበራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጋራ የሚቃረን ግትር አቋም ይዘው ውለዋል፡፡
 • አቋማቸው ተቀባይነት ካላገኘ ስብሰባውን ለመምራት እንደሚቸገሩ በመግለጽ ምልአተ ጉባኤን ለማስገደድ ያደረጉት ሙከራ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጽኑ አቋም ሳቢያ አልተሳካላቸውም፡፡
 • ጉዳዩ ‹‹ከአዲስ አበባ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋራ ብዙ የሠራኹበትና የደከምኩበት ነው፤ በቀላሉ የምተወው አይደለም›› በሚል ከአክራሪነት ጋራ የተገናኘ ጽሑፍ ሲያነቡ ውለዋል፡፡
 • ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ‹አቦይ› ስብሐት ተናገረኝ እንዳሉት፣ ‹‹አንተ ጎበዝ ነኽ፤ ጽናት አለኽ፤ እንዲኽ ዐይነት ፓትርያርክ አይተን አናውቅም፡፡››

ከተጀመረ ስድስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ በዛሬ፣ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ሙሉ ቀን ውሎው፣ የ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያን ለማሻሻል በቀረበውና የልዩነት አቋም በተያዘባቸው የረቂቁ አንቀጾች ላይ ጠንካራ ውይይት ሲያደርግ አምሽቷል፡፡

የማሻሻያ ረቂቁ፣ ባለፈው ዓመት ግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብስባ ወቅት አንቀጽ በአንቀጽ ከተወያየበት በኋላ ተጨማሪ እርማትና ማስተካከያ አድርጎ ለአኹኑ ምልአተ ጉባኤ እንዲያደርስ የሠየመው ስድስት አባላት ያሉት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሊቃውንትና የምሁራን ኮሚቴ ያቀረበው ነው፡፡

የማሻሻያ ረቂቁንና በኮሚቴው አባላት መካከል የልዩነት አቋም የተያዘበትን ቃለ ጉባኤ ባለፈው ቅዳሜ ከቀትር በፊት ውሎው የተናበበው ምልአተ ጉባኤው፣ ለዛሬ ባሳደረው መሠረት ነው ፓትርያርኩ በአንድ በኩል፣ መላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሌላ በኩል ፍጥጫ የተቀላቀለበት ውይይት ሲያካሒዱበት የዋሉት፡፡

የልዩነት አቋሞች የተያዘባቸው ነጥቦች፡-

 • የሊቃነ ጳጳሳትን ተጠሪነት(ዝውውር እና ምደባ)
 • የማኅበራትን ተጠሪነትና የገንዘብ እንቅሰቃሴ ማእከላዊነት
 • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አመራር የተመለከቱት ይገኙበታል፡፡

ከስድስት የኮሚቴው አባላት መካከል በሦስቱም ነጥቦች ላይ የልዩነት አቋማቸውን በቃለ ጉባኤው ያስመዘገቡት የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ናቸው፡፡ ልዩ ጸሐፊው ከአምስቱ የኮሚቴው አባላት ተለይተው በያዙት አቋም÷ የሊቃነ ጳጳሳቱንና የማኅበራትን ተጠሪነት ለቅዱስ ሲኖዶሱ የሚያደርጉት የረቂቁ አንቀጾች ለፓትርያርኩ ይኹን በሚል እንዲተኩ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት እንደኾነና በሊቀ ጳጳስ ሳይኾን በፓትርያርኩ እንደሚመራ የሚገልጽ በረቂቁ ያልነበረ አንቀጽ በግልጽ እንዲቀመጥ ተከራክረዋል፡፡ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስም በዛሬው የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ የያዙት አቋም ይኸው የልዩ ጸሐፊው ክርክር በሌላ መጽሔት የታየበት፤ ከልዩ ጸሐፊው ጋራም አንድና ያው እንደነበር ተገልጧል፡፡

የኮሚቴው አብላጫ ማለትም አምስቱም አባላት የተስማሙበትና ከርእሰ መንበሩ አቡነ ማትያስ በቀር በመላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የተያዘው አቋም ደግሞ÷ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እያንዳንዱ ሊቀ ጳጳስ፣ ጳጳስና ኤጲስ ቆጶስ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲኾን፤ ሊቃነ ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትን በየሀገረ ስብከቱና በተለያዩ የሥራ ክፍሎች የመመደብ፣ በበቂ ምክንያት የማዘዋወር ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ እንደኾነ አጥብቆ የሚሟገት ነው፡፡

His Grace Abune Natnael

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሊቀ ጳጳስ

በሥራ ላይ የሚገኘው የ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያንም ይኹን ቀደም ሲል በጥቅምት ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. እና በሚያዝያ ፲፱፻፹፰ ዓ.ም. ጸድቀው ያገለገሉት ሕገጋተ ቤተ ክርስቲያን በዚኽ ረገድ ልዩነት የማይታይባቸው ሲኾን ይኸውም ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በዛሬው ስብሰባ እንደገለጹት÷ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የኾኑትን ሊቃነ ጳጳሳት የደረጃ እኩልነት፣ የመንፈሳዊ ተልእኮ ምደባና ብቃት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አባልነታቸው ሊያገኙት የሚገባውን ክብርና እምነት የሚያጠይቅ ድንጋጌ በመኾኑ ነው፡፡ ቀኖናው በእኛ ብቻ ሳይኾን በሌሎችም አኃት አብያተ ክርስቲያናት የሚሠራበት በመኾኑ በቤተ ክርስቲያናችንም ተጠብቆ ሊሠራበት እንደሚገባ ተገልጧል፡፡

ስለ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አመራር በሥራ ላይ በሚገኘው የ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያን÷ ‹‹እያንዳንዱ ሀገረ ስብከት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ በተሾመ ሊቀ ጳጳስ ወይም ጳጳስ ወይም ኤጲስ ቆጶስ ይመራል›› ተብሎ የተደነገገ ሲኾን ሕጉን መሠረት አድርጎ በ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የወጣው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ቃለ ዐዋዲ ደንብም ይህንኑ የሚያጸና ነው፡፡ የአሁኑ የማሻሻያ ረቂቅም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሀገሪቱ ርእሰ ከተማ ስለኾነና ከሌሎች አህጉረ ስብከት የሚለይባቸው ልዩ ኾኔታዎች እንዳሉና እነዚኽን ኹኔታዎች ከግምት ያስገባ የተለየ አወቃቀርና የፈሰስ አከፋፈል ሥርዐት እንደሚኖረው ቢያሰፍርም በአንቀጽ ፵፫ ንኡስ ቁጥር ፪ ‹‹ከአዲስ አበባ ጀምሮ እያንዳንዱ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ በተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ሊቀ ጳጳስ ይመራል›› ነው የሚለው፡፡

ከስድስቱ የኮሚቴው አባላት አምስቱ፣ በምልአተ ጉባኤውም መላው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይህንኑ የሊቀ ጳጳስ(ጳጳስ) አመራር የደገፉ ሲኾን ‹‹የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት›› ተብሎ በግልጽ ካልተደነገገ በሚል የተለየ አቋም የያዙት ደግሞ ርእሰ መንበሩ አባ ማትያስ ከኮሚቴው አባላትም ልዩ ጸሐፊው ንቡረ እድ ኤልያስ ብቻ ናቸው፡፡

በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ዋና ጸሐፊነታቸው የሀገረ ስብከቱን ገዳማትና አድባራት ቅጥር፣ ዕድገትና ዝውውር ወትሮም በተካኑበት የአማሳኞች ሰንሰለት የሚቆጣጠሩት ንቡረ እዱ፣ በፓትርያርኩ ዘንድ ስለምን ይህ አቋም እንዲያዝ እንዳደረጉ ግልጽ ነው – ልዩ ጸሐፊው ‹‹የልማት/ልማታዊ ጉብኝት›› በሚሉትና አጥቢያዎቹ ‹‹የኮቴ›› እያሉ በሚሣለቁበት የዘረፋ አሠራር እግራቸው በረገጠው ደብር ኹሉ በትንሹ ከ25‚000 ያላነሰ ብር የሚቀበሉበትና የከበሩበት ነውና! አዲስ አበባን የተጧጧፈች የሙስና ገበያ አድርገው የአብያተ ክርስቲያናቱ ቅጽሮች ሳይቀሩ እየተሸነሸኑ ከአንድም የአራት ይዞታዎች ባለቤት የኾኑበት ነውና! በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት አላግባብ የሚዘረፍበት፣ ሕጋዊና መንፈሳዊ አስተዳደር እየተጓደለ ጎጠኝነትና አድልዎ፣ ሁከትና ብጥብጥ ነግሦበት የነበረው የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር አምሳል ናቸውና!

ማኅበራትን በተመለከተ የረቂቁ አንቀጽ ፯ ንኡስ አንቀጽ ፳፬÷ ‹‹በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ አገልግሎት ለማበርከት ለሚቋቋሙ ማኅበራት ዕውቅና ይሰጣል፤ የማኅበራቱን መተዳደርያ ደንብ መርምሮ ያጸድቃል፤ ያሻሽላል፤ አስፈላጊ ኾኖ ሲያገኘውም ማኅበራቱን ያግዳል፤ ይሰርዛል›› በማለት ሓላፊነቱንና ተግባሩን የሚሰጠው ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ይኸው አቋም በማሻሻያ ረቂቁ ላይ ተጨማሪ እርማትና ማስተካከያ አድርገው እንዲያቀርቡ ከተሠየሙት የኮሚቴው አባላት አምስቱ የተስማሙበት ሲኾን ከፓትርያርኩ በስተቀር መላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም አቋማቸውን ያሳረፉበት ነው፡፡

ይኹንና ‹‹የኮሚቴው አባላት ማኅበራት ለፓትርያርኩ ተጠሪ እንዲኾኑ 5 ለ1 በኾኑ ልዩነት ተስማምተዋል›› የሚል ከተነበበው ቃለ ጉባኤ የተለየና የተሳሳተ መረጃ ጭምር በንቡረ እዱ የተነገራቸው ርእሰ መንበሩ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው፣ የማኅበራት ተጠሪነት ለፓትርያርኩ ይኹን ከማለት አልፈው የማኅበራት ጠቅላላ ገንዘብ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ገቢ ተደርጎ በበጀት እየተፈቀደ የሚያገለግሉበትን ማእከላዊ አሠራር በአቋም አክርረው አስተጋብተዋል፤ ‹‹አቋሜ ይኸው ነው፤ የምትቀበሉ ከኾነ ተቀበሉ›› በሚል ለውይይት በማይመች የስብሰባ አመራርም ምልአተ ጉባኤውን ሲያደክሙት ውለዋል፡፡

ለአገልግሎት በበጎ ፈቃድ የተሰባሰቡ የማኅበራት አባላት የገንዘብ አስተዋፅኦ ለመንበረ ፓትርያርኩ ገቢ እየተደረገ በማእከላዊነት ይንቀሳቀስ ማለት ከማኅበር ሕገ ተፈጥሮ አንፃር የማያስኬድ መኾኑን የገለጹት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ በአህጉረ ስብከትና በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ደረጃ እንኳ የሚጠየቀው ፈሰስ እንጂ ጠቅላላ ገንዘብ አለመኾኑን በመጥቀስ አስረድተዋቸዋል፤ ተገቢው አካሔድም በማኅበራት ምንነትና አስፈላጊነት ላይ መተማመን፣ የሚቋቋሙበትንና የሚያሠራቸውን ሕግ ማውጣት፣ ከተፈቀደው አገልግሎታቸው ጋራ በተገናኘ የገንዘብ አጠቃቀማቸውንና የንብረት አያያዛቸውን አግባብነትና ባለቤትነት በሚገባ ለማወቅና በጥብቅ ለመቆጣጠር የሚያስችል ሕግ መደንገግና አሠራሩን መዘርጋት መኾኑን ለፓትርያርኩ ለማስጨበጥም ሲጥሩ ውለዋል፡፡

ከቀትር በፊት በነበረው የስብሰባ ውሎ ‹‹አቋሜ ይኸው ነው፤ የምትቀበሉ ከኾነ ተቀበሉ›› ሲሉ ያረፈዱት ፓትርያርኩ ‹‹ይህንኑ አቋሜን የማትቀበሉ ከኾነ ስብሰባውን ለመምራት እቸገራለኹ›› በማለታቸው ምልአተ ጉባኤው የከረረውን ለማለዘብ የምሳ ዕረፍት አድርጎ ለመመለስ ተነሥቷል፡፡ ከቀትር በኋላ ስብሰባው ሲጀመር ‹‹ስብሰባውን ለመምራት እቸገራለኹ›› ያሉትን ቀይረው ‹‹አቋሜን ካልተቀበላችኹ ወደ ሌላው አጀንዳ እንቀጥል›› ቢሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ አጀንዳው የብዙኃኑን አቋም ይዞ መቋጨት እንደሚገባው በማሳሰብ ምልአተ ጉባኤው በጉዳዩ ላይ ውይይቱን መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጦላቸዋል፡፡ ማኅበራት ብለው ሲናገሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ማለታቸው ከኾነም የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ረቂቅ በአጀንዳነት የተያዘ በመኾኑ ራሱን ችሎ በስፍራውና በጊዜው መነጋገር እንደሚገባ ሊያግባቧቸው ሞክረዋል፡፡

ፓትርያርክ አባ ማትያስ ግን ይባሳችኹ ብለው፣ በማኅበራት ዙሪያ የያዙት አቋም ከምልአተ ጉባኤው ስብሰባ በፊት ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ጋራ ብዙ ሲሠሩበትና ሲደክሙበት የሰነበቱበት መኾኑን በመግለጽ ‹‹ስንት የደከምኹበት ነው፤ በቀላሉ የምተወው አይደለም›› በማለት ፍርጥም ብለዋል፤ ከዚኽም አልፎ በልዩ ጸሐፊው ንቡረ እድ ኤልያስ እንደተረቀቀ የተዘገበውን ማኅበራትን ከአክራሪነትና አሸባሪነት ጋራ የሚያቆራኝ ጽሑፍ እያነበቡና ጠቅሰው እየተናገሩ ምልአተ ጉባኤውን በርእሰ መንበር ከሚመራ አባት በማይጠበቅ አኳኋን ለመረዳትም ለማስረዳትም የሚያዳግትና ሒደቱን ቅርቃር ውስጥ የሚከት አካሔድ በመከተላቸው የዕለቱ ውሎ ያለአንዳች ውሳኔ ለመቋጨት እንደበቃ ተገልጧል፡፡

በምልአተ ጉባኤው የዛሬው ውሎ፣ የልዩ ጸሐፊው የልዩነት ነጥቦች ሳይጨመሩና ሳይቀነሱ የፓትርያርኩም አቋሞች ኾነው መንጸባረቃቸው፣ አቡነ ማትያስ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑንና የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን ሥልጣንና ተግባር እየጣሱ ለፈጸሟቸው ስሕተቶች በቀጣይም ለሚይዟቸው አቋሞችና ለሚከተሉት አካሔዶች የክፋቱ ሥርና የመለካዊ ምክሩ መተላለፊያ ማን እንደኾነ በማያሻማ ኹኔታ ቁልጭ አድርጎ ለምልአተ ጉባኤው አባላት እንዳሳየ ታምኖበታል፡፡

የልዩ ጸሐፊው ንቡረ እድ ኤልያስ መለካዊ ግብር፣ ርእሰ መንበሩ የሚያስተጋቧቸው ፀረ – ቅዱስ ሲኖዶስና ፀረ – ሕገ ቤተ ክርስቲያን የክፋትና የተሳሳቱ አቋሞች ምንጭና መተላለፊያ በመኾን ብቻ የሚገለጽ አይደለም፡፡ ፓትርያርኩ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከከፈቱት ዘመቻ በስተጀርባ አለ ተብሎ እንዲታሰብ የተፈለገውን ኃይል ለማሳሰብና የብፁዓን አባቶችን አቋም ያላላል የተባለ የሥነ ልቡና ጨዎት ዐይነት ነገርም አለበት፡፡

ይህንኑም ፓትርያርኩ ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጆሮ እንዲደርስ አድርገው እንዳስወሩት፣ ሰሞኑን በአንድ ምሽት ከአቶ ስብሐት ነጋ ጋራ ራት አብረው ተመግበዋል፡፡ በዚኹ የራት መርሐ ግብር ታዲያ አቡነ ማትያስ ‹አቦይ› ስብሐት ተናገረኝ እንዳሉት፣ ‹‹አንተ ጎበዝ ነኽ፤ ጽናት አለኽ፤ እንዲኽ ዐይነት ፓትርያርክ አይተን አናውቅም፡፡›› በርግጥ አቶ ስብሐት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ‹‹አይረቡም›› ብለው መዝለፋቸውን፤ ማኅበሩንም ‹‹የፖሊቲካ መድረክነት ይታይበታል›› ብለው መፈረጃቸውን ባለመዘንጋት የራሳቸው አቋምና ፍላጎት እንደሚኖራቸው ባንስተውም ይቺ የራት መርሐ ግብር ጨዎት መላ ግን ብዙዎችን ፈገግ ሳታሰኝ አልቀረችም፡፡

የኾነው ኹኖ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አተረጓጎም፣ የሊቃነ ጳጳሳትን ተጠሪነት ከምደባቸውና ዝውውራቸው ጋራ እንዳያሻማ አድርጎ በግልጽ መደንገግ÷ የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልና በፓትርያርኩ ዐምባገነናዊ አመራር ሰጪነት ለመተካት የታሰበውን አካሔድ በማምከን ሥልጣኑንና ተግባሩን ማስከበር መኾኑ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ዘንድ በቂ ግንዛቤ ተይዞበታል፤ በምልአተ ጉባኤው የአጀንዳ ማርቀቅና ማጽደቅ ወቅት እንደተነገረውም ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ የሕዝብ ጥያቄ ኾኗልና›› ማኅበረ ቅዱሳንን ይኹን ሌሎች ማኅበራትን በሒደት አዳክሞ የሚያፈራርስ ሳይኾን ትክክለኛ ሚናቸውን የተገነዘበና በጥንካሬ ለማሠራት የሚያስችል ሕግና መተዳደርያ ደንብ እንደሚወጣ ተስፋ ይደረጋል፤ በመኾኑም የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ነገም ቀጥሎ ይውላል…..

Advertisements

29 thoughts on “ሰበር ዜና – ‹‹አቦይ ስብሐት ጎበዝ ነኽ አለኝ›› ያሉት ፓትርያርኩ የማኅበራትን ተጠሪነትና የገንዘብ እንቅስቃሴ በሚመለከተው የሕጉ ረቂቅ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ተፋጠው ዋሉ

 1. Anonymous October 27, 2014 at 7:44 pm Reply

  egeziabher yihechin betekeresetiyan eneditebekat stelot enadereg bewenet yewechiwen senewaga mesekelun yizew qalun yekadu yehayimanot meri lene nachew beye mekebl kebedognal ebakachiw eneseley lebona yisetachew

 2. Nigat October 27, 2014 at 8:25 pm Reply

  ehhh egnih sewiye ahunis kerefugn. Fetari yiker yebelegn. Yehinina gena legena abat nachew biye ye Fetariyen bet siakoshishu zim malet yemichil almeselegnim. Beka libalu yigebal. Lenegeru esachew gena be atsew gize ye Tigray church emeseritalehu bilew sidolitu yeneberu nachew eko. Gize yesetew kil endilu honena—

  • Anonymous October 28, 2014 at 3:21 am Reply

   I am wondering what they are doing. I never disappointed with my church leaders like this. Please, do what God told you. Don’t do what makes people happy. Ask God before any decisions. That is how our holy father told us. I wish holy Spirit will be with you.

 3. Anonymous October 27, 2014 at 10:10 pm Reply

  This is for Nigat/

  May the Angle of the Almighty God pay you back according to your evil word. you have to think before you speak and you have to also learn about Ethiopia and Ethiopians. there is not Ethiopia without Tigray and the foundation of our religion, knowledge, civilization, language and a good heritage is Tigray. if you are Ethiopian, you have to respect the people of Tigray because without Tigray there is no Ethiopia and without Ethiopia there is not Tigray/. but you have to understand this, I am not saying the rest people of Ethiopia are not Ethiopians. yes. truly they are respected Ethiopians. I strongly believe that there are very respected people as the people of Tigray please think before you speack.
  .

  • Anonymous October 28, 2014 at 11:40 am Reply

   ብሄርተኝነት፣ጠበብተኝነት፣ ዘረኝነት፣ አክራሪነት ይለዋል ይህንን ነው። አቦይ ስብሃት መዋጋት ካለበት ይህን ነው። የማያገባው ቦታ ከሚገባ።

 4. Birhan Asfaw October 28, 2014 at 2:36 am Reply

  Amlak hoy hizbhn tebk ketkulawochim adinachew

 5. ግእዝ በመሥመር-ላይ October 28, 2014 at 3:49 am Reply

  ይቺን ድንቅ ቤተ ክርስቲያን አከርካሪዋን ለመስበር ቆርጠው ተነሥተው በግላጭ እየተራወጡ ባሉት በቀንደኛ ጠላቶቿ በነአቦይ ስብሐት በነአባይ ፀሐየ መጫኛነት የሚለኳት ብቻ ሳይኾኑ፤ ያስለኳትም አጫፋሪዎች (እነ-ማቅ ጭምር)–ሲኾን በወዲሁም አለዚያ ግን በወዲያው–ከተጠያቂነት አያመልጡም!

  • kibur October 28, 2014 at 8:58 pm Reply

   MIN NEKAH DEHNA SEW ALNEBERKIM? ene sawikeh endih alneberkim ahunim akuawamihin astekakil simihen alawetam astemrehegnalna. MK min aderege.

 6. Anonymous October 28, 2014 at 7:18 am Reply

  Zim belo wede fetari metseley new. His Holiness Aba matias seems doing the Gov. assignment not his own. Lehulachinim libona yisten!!!

 7. Anonymous October 28, 2014 at 7:59 am Reply

  የሐራ አቀራረብ ተቆርቋሪነቱ ሳያንሰው ዘለፋ ማብዛቱ አያስደስትም፡፡ ጉዳዩን ሁሉ በውስጥ አስተዳደር ሊከሰትና በውይይት ሊፈታ የሚችል አድርጎ ሳይሆን በድንበር እንደተፋጠጡ ጠላቶች መተያየቱ ጥሩ ስሜት አይሰጥም፡፡ አንባቢያችሁን ወደ ስሜታዊነት ሳይሆን ወደ ምክንያታዊነት የሚመራ አቀራረብ ቢኖራችሁ ጥቅሙ ለሁሉም ነው፡፡ይኸንን የምለው የሰሞኑ አያያዛችሁ የተጋነነ ሆኖ ስለተሰማኝ ነው፡፡
  አፀደ ማርያም

  • Senait October 28, 2014 at 12:10 pm Reply

   አፀደ ማርያም: well said sister, GBU

 8. Anonymous October 28, 2014 at 9:36 am Reply

  ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን ጥያቄ የሕዝብ ጥያቄ ኾኗል››ና….so, it will b resolved through a referendum. That is your last resort. I will never believe MK .Its leaders themselves r not free of corruption,racism…..bla bla.Please, don’t manipulate us in the name of innocent laitiys. Most of u r defeated returnees of Blante, who tasted z fist of Woyane in the battle ground.Try it!!U will pay a lot for ur chauvinist led tribalism.We saw how far u go 2 demoralize those Tigrian origin monks while most of ur allies r indulging with corruption. Any way, go ahead ,soon u will see GEMENA of ur allies, if u r lucky 2 escape Kaliti.If u rn.t ready to b fair, we shall spread it in any available media indiscriminately.
  wait!! wait a little!!NO MORE patient 4 ur hate driven propaganda against selected ethnicity!!

  • Anonymous October 28, 2014 at 11:32 am Reply

   ከላይ ለፃፍከው/ሽው/ ስለማህበሩ የምታውቀው ሳይኖርህ/ሽ/ ዝምብለህ/ሽ/ አፍህን/ሽ/ ለማይገባ ንግግር አትክፈት/ች/። ስለማህበሩ ምንም እውቀት እንደሌለህና በመሰለህ/ሽ/ እንደፃፍክ/ሽ/ ካሰፈርከው/ሽ/ ፅሁፍ በቀላሉ መረዳት ስለተቻለ ነው። ወይ ደግሞ የሌላ እምነት ተከታይ ሆነህ/ሽ/ የማህበሩ በጎ ምግባር ለኣላማህ/ሽ/ እንቅፋት ሆኖብህ/ሽ/ ይሆናል። ወይ ደግሞ በእምነት ውስጥ እያለህ/ሽ/ ማህበሩን ለማጥፋት ቀን ከሌት እየጣሩ አልሳካ ያላቸው እያወቁ ልቦናቸውን ለክፉ መንፈስ ያስማረኩ አምላክ ለመረጣቸው ቅዱስ ስራ ያልታደሉ ኣባቶች ቢጤ ትሆናለህ/ሽ/። ፈጣሪ አይነልቦናህን/ሽ/ ያብራልህ/ሽ/።

  • Anonymous October 28, 2014 at 11:52 am Reply

   Who are you? Who mentioned an ethnic group? Don’t waste your time to connect everything to ethnicity. This is your and your master’s usual code of game to divide the people of this country. You don’t like to see us united. On the other side, it seems that kaliti is your source of power. But here, none is concerned about your agenda. The agenda is about the church not about the bread of this earth. I think you know all of MK members make their bread elsewhere. They instead contribute at least 2% of their monthly income to the church.

 9. G/Hawariyat October 28, 2014 at 10:33 am Reply

  @ግእዝ በመሥመር-ላይ
  “እነ ማቅ ጭምር” ሲባል ምን ማለት ነዉ፡፡
  ለቤተ-ክርስቲያን እንደነሱ ያሰበና የሚዳሰስ አገልግሎት የለገሰ ማን አለ?
  ከቅዱሳን አባቶች ቀጥሎ ለዚች ቤተ ክርስቲያን ማን አላት? ሌሎቻችን’ኮ ከማሰብና
  ከማዉራት የዘለለ ፋይዳ አልሰራንላትም የሰራ እንኳ ቢኖር ጠጠር ቢያክል እንጂ

  • ግእዝ በመሥመር-ላይ October 29, 2014 at 4:47 am Reply

   ያለፉት የቻሉትን ያኽል አጥፍተው ዐለፉ፤ አኹን ደግሞ ሌላ አጥፊ ፓትርያርክ ብሎ እስንጥር ላይ ከማስቀመጥ መንበሩ ተደላድሎ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ይቅደምና እግዜር የፈቀደው ይሾም ብንል፤ የለም እኛ እግዜርን ሳይኾን እነአባይ ፀሐየን መስማት ይሻለናል ብለው ፈቃደ ዐላውያኑን ከፈጸሙ በዃላ፤ “የእግዚአብሔር ፈቃድ” ነው ተቀበሉ በማለት በቴሌቫንጄሊዝማቸው ሳይቀር “ትንቢት” እያጣቀሱ ሲወተውቱን የተሰማንን ስሜት እንዲኽ ገልጠን ነበር፦

   http://www.geezonline.org/2013/05/blog-post.html

   የሚያዋጣው ጥፋትን ማመን እንጂ ማድበስበስ አልነበረም። ወዳጄ፦ አኹንም የምሰጋው የተባለው ተብሎ የኾነው ኾኖ መልሰው እጫማ ሥር ይወድቁና የተወሰኑ ቆራጥ ወንድሞችና እኅቶችን በተናጠል እንዳያስጠቁ ነው!

   • Anonymous October 29, 2014 at 8:47 am

    ከጾምና ጸሎት ዉጪ ምን ማድረግ ይቻላል? ቀጣዩ አማራጭ እኮ ጦርነት ነዉ፡፡ ይህን መምረጥ ይቻላል?

 10. Anonymous October 28, 2014 at 11:22 am Reply

  ‹‹አንተ ጎበዝ ነኽ፤ ጽናት አለኽ፤ እንዲኽ ዐይነት ፓትርያርክ አይተን አናውቅም፡፡›› እውነት ነው፡፡ቤተ ክርስቲያን እንዲህ አይነት አባት ገጥሟት አያውቅም፡፡ወደፊትም እንዳይገጥማት እንጸልያለን፡፡ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡

 11. Anonymous October 28, 2014 at 11:25 am Reply

  ከላይ ለፃፍከው/ሽው/ ስለማህበሩ የምታውቀው ሳይኖርህ/ሽ/ ዝምብለህ/ሽ/ አፍህን/ሽ/ ለማይገባ ንግግር አትክፈት/ች/። ስለማህበሩ ምንም እውቀት እንደሌለህና በመሰለህ/ሽ/ እንደፃፍክ/ሽ/ ካሰፈርከው/ሽ/ ፅሁፍ በቀላሉ መረዳት ስለተቻለ ነው። ወይ ደግሞ የሌላ እምነት ተከታይ ሆነህ/ሽ/ የማህበሩ በጎ ምግባር ለኣላማህ/ሽ/ እንቅፋት ሆኖብህ/ሽ/ ይሆናል። ወይ ደግሞ በእምነት ውስጥ እያለህ/ሽ/ ማህበሩን ለማጥፋት ቀን ከሌት እየጣሩ አልሳካ ያላቸው እያወቁ ልቦናቸውን ለክፉ መንፈስ ያስማረኩ አምላክ ለመረጣቸው ቅዱስ ስራ ያልታደሉ ኣባቶች ቢጤ ትሆናለህ/ሽ/። ፈጣሪ አይነልቦናህን/ሽ/ ያብራልህ/ሽ/።

 12. Anonymous October 28, 2014 at 1:07 pm Reply

  አንተ ጎበዝ ነኽ፤ ጽናት አለኽ፤ እንዲኽ ዐይነት ፓትርያርክ አይተን አናውቅም፡፡›› እውነት ነው፡፡ቤተ ክርስቲያን እንዲህ አይነት አባት ገጥሟት አያውቅም፡፡ወደፊትም እንዳይገጥማት እንጸልያለን፡፡ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡

 13. Anonymous October 28, 2014 at 1:21 pm Reply

  why you make it a political matter and pro to racism?! I think you are the one who play behind these so called priests and fathers. Any one with God will not have a fear for your such shame full thinking. Do not think with gun.

 14. Tewahedo October 28, 2014 at 1:28 pm Reply

  ማፈሪያ ማቲያስ ድሮስ ከወያኔ ዝርያ ምን ጥሩ ነገር ሊገኝ?

 15. Tewahedo October 28, 2014 at 1:44 pm Reply

  Aba Matiyas = Protestant and Jihadist

 16. Anonymous October 28, 2014 at 1:58 pm Reply

  @ግእዝ በመስመር ላይ
  ጠርጠር ከገንፎ ውስጥ አለ ስንጥርን ብሒል ለጠጥከው፣ትንሽ ይደብራል።
  አንተም በበኩልህ ማኅበሩ ላይ ሌላ ጫና ስትፈጥርበት አይከብድም?
  ከፊት የገጠመውን ችግር ይፍታ ወይስ ሌላ ትችት ያስተናግድ?
  አንባቢም ድንግርግር እንደሚል ባይዘነጋ ወይስ መደናገሩ ይፈለጋል?

  • ግእዝ በመሥመር-ላይ October 29, 2014 at 4:56 am Reply

   እነ አትንኩን… አኹን ስለድብርት ይወራል? አዎ ከፊት የገጠመውን ችግር ጫማ ስሞ እንዲፈታ የሚያሳስብ መካሪ እንጂ፤ ካለፈው ጥፋት በመማር የሚገባውን ለማድረግ ቆርጦ እንዲነሣ የሚያበረታታ እንደማይፈለግ ሳውቀው እንዲያው በከንቱ እደክማለኍ። ግን ምን ላድርግ እናቲቱ የጋራችን ናትና፤ የሷን ጉዳት ዝም ብሎ ማየቱ አላስችል ቢለኝ ነው…

 17. fita October 28, 2014 at 7:02 pm Reply

  የሲኦል ደጆች አይችሏም!! የተባለች ቅድስት ቤተክርስቲያን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች፡፡ የአውሬውና የተከታዮቹ ሴራ ግን በቅዱሳኑ ጸሎትና ጥበቃ ይከሽፋል፡

 18. Alebel Atalel October 29, 2014 at 6:41 am Reply

  minem sayawuqu asteyayet mestet badonet new. yemayechalew degemo begiziabeher yichalal. lemlekam sera hulegizem yemayanqlafa dabilose selal yestekaklal atidengitu.

 19. Anonymous October 29, 2014 at 1:17 pm Reply

  ሌላ ምንም አማራጭ የለም። ይህ ፈተና ከፆምና ከፀሎት በቀር አይፈታም ሁሉም የተዋህዶ ልጅ በአንድ ልብ ሁኖ ፈጣሪውን ከመጠየቅ መቦዘን የለበትም። በጎ ነገርን እያወቀ የማይሰራት ኃጢያት ይሆንበታል ተብሎ በቅዱስ መፅሐፍ እንደተፃፈው ሁላችንም ለአባቶቻችን እና ለሁሉም የኦርቶዶክስ ልጆች አፅናኝ መንፈስ ቅዱስ ይላክልን፣ ድንግል ወላዲት አምላክ ለአባታችን አቡነ ማትያስ የሰሎሞንን ጥበብ ትስጣታቸው፣ መልካሙን ያሰማን ቸር ወሬ ያሰማን ጉባኤው በሰላም ያፈፅምልን። ማህበራችን ማህበረ ቅዱሳንን እና አገልጋዮቹ እግዝአብሄር አምላክ በአገልግሎት ያፅናልን፣ እስከ መጨረሻ የሚፀና እርሱ ይድናል ማቴ 24-13 ይላልና ቅዱስ መፅሐፍ። ለበመጨረሻ አንድ ነገር ልበል በማህበረ ቅዱሳን አባላት እጅ ሽጉጥ ሳይሆን ዳዊት፣ ፀናፅል፣ ከበሮ ፣እንዚራ፣ በገና ነው የሚገኘው። ሰለዚህ “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” እንደሚባለው ሆኖ ታየቶኛል። ለማንኛውም ለወንደሞቻችን ወልድ ማደሪያው ትሆን ዘንድ የመረጣት፣ የያቆብ መሳላል፣ የኖህ መርከብ፣ በቅድስት ኤልሳቤጥና በገናናው መልአክ በቅዱስ ገብርኤል በአንድ አይነት ምስጋና የተመሰገነች፣ የአብርሃም ድንኳን፣ የአሚናዳስ ሰረገላ፣ የሙሴ ደመና፣የመላእክት እህት፣የነብያት ትንቢት፣ የደናግል መመኪያቸው ሰአሊተ ምህረት ድንግል ወለድተ አምላክ ምልጃና ፀሎት ከእናንተና ከሁላችን ህዝበ ክርስትያን ጋር ለዘላለም ይኑር።
  አንቺ ነሽ ተስፋው ለአዳም ክዳነ ምህረት
  በተሰደደ ግዜ ከገነት። እያል ሁላችንም የአባቶቻችን ጉባኤ እስኪያለቅ ድርስ በፆምና በፆሎት እናሰባቸው። የእዝአብሔር ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን።

 20. Anonymous October 30, 2014 at 9:47 am Reply

  menu nw seber zena yehonw terki merki hula…………….

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: