ሰበር ዜና: አጠቃላይ ጉባኤውን ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን አቋም ለማስያዝ ፓትርያርኩና ጥቂት አማሳኞች በዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ ጫናቸውን አጠናክረዋል

Zekarias Addis a day light robber

የጫናው ዋነኛ አስተባባሪ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ፤ የአጠቃላይ ጉባኤው ተሳትፏችኹ የታዛቢነት ብቻ ነው! ‹‹የቅዱስ ፓትርያርኩ መብት ተጥሷል›› እያላችኹ ጉባኤተኛው ውድቅ ባደረገው የቅስቀሳ አጀንዳ ማኅበረ ቅዱሳንን ለማስወገዝ ‹‹መድረክ ይከፈትልን›› በሚል በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ የምታደርጉት ግፊት ሀገረ ስብከቱን ይኹን የሀገረ ስብከቱን ገዳማትና አድባራት አይወክልም!

 • አማሳኞቹ በአጠቃላይ ጉባኤው የሚሳተፉት በታዛቢነት ብቻ ኾኖ ሳለ ‹‹መድረኩ ለምን አይለቀቅልንም›› በሚሉ የጽሑፍ መልእክቶች ግፊት የውይይት መርሐ ግብሩን ተጠቅመው የፓትርያርኩን ‹‹የቅኝ ገዥ ነው!›› ቅስቀሳ ለማጠናከርና ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን መግለጫ እንዲወጣ በዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ የሚያካሒዱት በዛቻና ማስፈራሪያ የታገዘ ጫና እንደማይወክላቸው የአዲስ አበባ ልኡካን እየገለጹ ነው፡፡
 • ‹‹ሰሞኑን መቅሠፍት አለ›› በሚል ከንቱ ማስፈራሪያ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ በተለያየ መንገድ ጫና ከመፍጠር አልፈው አካላዊ ጥቃት ለማድረስም እየተሰናዱ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡ የአማሳኞች እንቅስቃሴ አይወክለንም ያሉት ተሳታፊ ጉባኤተኞችና ብዙኃኑ የአ/አ ገዳማትና አድባራት ልኡካን ለአጸፋ እንቅስቃሴ እየተዘጋጁ መኾኑ ተጠቅሷል፡፡
  ???????????????????????????????

  ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ

  ???????????????????????????????

  የ፴፫ኛው የመ/ፓ/አጠ/ሰ/ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ተሳታፊ የአህጉረ ስብከት ሓላፊዎች

  ???????????????????????????????

  የዓመታዊው ስብሰባ የአህጉረ ስብከት ልኡካን በከፊል

 • የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች በሪፖርታቸው፣ ማኅበረ ቅዱሳን÷ በተለይ በጠረፋማ አህጉረ ስብከት አዲስ አማንያንን አስጠምቆ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ባደረገበትና የምእመናንን ቁጥር በጨመረበት፤ በተለያዩ ቋንቋዎች የተተኪ መምህራንና ካህናት ሥልጠና ባካሔደበት፤ የአብነት የአዳሪ ት/ቤቶችን እንዲኹም የዘመናዊ ት/ቤቶችን ግንባታ በጀት መድቦ የዲዛይንና ክትትል ሥራ በሠራበትና የግንባታቸውን ጠቅላላ ወጪ በሸፈነበት፤ በቅዱሳት መካናት የልማት ፕሮጀክቶች ቀረፃና በሕግ የማማከር አገልግሎት በሰጠበት፤ በ341 የመንግሥትና የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባደራጃቸው ግቢ ጉባኤያት 200,000 ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን በትምህርተ ሃይማኖት ባሠለጠነበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከፍተኛ ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡
 • በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አጠቃላይ ሪፖርትና በአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ሪፖርት ስለማኅበረ ቅዱሳን ኹለንተናዊ አገልግሎት በአጽንዖት በተጠቀሰው ከፍተኛ ዕውቅናና ብዙኃን ጉባኤተኞች ለዕውቅናው በሰጡት ደማቅ ድጋፍ÷ ‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ ነው›› ክሣቸው በተጨባጭ የተስተባበለባቸውና የ‹‹ተቆጣጠሩት›› ቅስቀሳቸው ውድቅ የተደረገባቸው ርእሰ መንበሩ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ በዓመታዊ ጉባኤው መክፈቻ ዕለት ጫማቸውን ትተው በባዶ እግራቸው ከአዳራሹ እስከ መውጣት ድረስ ስሜታዊ እንደነበሩ ተስተውሏል፡፡ በአኳኋናቸው ያዘኑት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ‹‹ብክይዎ እለ ታፈቅርዎ ለአባ ማትያስ›› በሚል ‹‹አላበድኹም›› ስላሉት ፓትርያርክ እያዘከሩ ነው፡፡
Nebured Elias Abreha, special secretary of the patriarch Aba Mathias

የፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ

 • ዛሬ እንደሚጠናቀቅ በሚጠበቀው የአጠቃላይ ጉባኤው የስብሰባ መርሐ ግብር፣ ፓትርያርኩ በመክፈቻ ቃለ በረከታቸው በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያሰሙትንና ብዙኃን ጉባኤተኞች ለማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት አስተዋፅኦ በሰጡት ደማቅ ድጋፍ የተስተባበለባቸውን ‹‹የቅኝ ገዥ ነው›› ቅስቀሳ የሚያጠናክር ንግግር በልዩ ጸሐፊያቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ መረቀቁ ተሰምቷል፡፡
 • በኹሉም የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ሪፖርት፣ ለማኅበረ ቅዱሳን ኹለንተናዊ የድጋፍ አገልግሎት ከፍተኛ ዕውቅና በተሰጠበትና ይህም በጉባኤተኞች ደማቅ ድጋፍ በተረጋገጠበት እንዲኹም በማኅበሩ ላይ አንዳችም ተቃውሞ ባልተሰማበት ኹኔታ፣ አጠቃላይ ጉባኤው ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን አቋም እንዲይዝና በጋራ መግለጫው እንዲያካትት ጥቂት አማሳኞች የሚያደርጉት ጫና ፓትርያርኩን የበለጠ ከማዋረድ ያለፈ ፋይዳ እንደማይኖረው ታምኖበታል፡፡
Advertisements

25 thoughts on “ሰበር ዜና: አጠቃላይ ጉባኤውን ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን አቋም ለማስያዝ ፓትርያርኩና ጥቂት አማሳኞች በዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ ጫናቸውን አጠናክረዋል

 1. fikadu tilahun October 18, 2014 at 4:27 am Reply

  enidi sinihon eniberetalen kidus paulos neger hulu keego naw ayidel yalew

 2. fikadu tilahun October 18, 2014 at 4:29 am Reply

  እንደ ሃሳቡ ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ሮሜ 8÷28 የሚለው

  • Anonymous October 18, 2014 at 2:40 pm Reply

   Yes Yes Yes !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

 3. Anonymous October 18, 2014 at 7:38 am Reply

  Ye Mahebere Kidusan Menor Le Ethiopa ye poletics meregagat endehum le baed Hymanot Mesffat Ras mitat yehone beteley betely Ortodocs Tewahdo Endetabeb Hizebu Hagerun Endetebk Yaderge ye Egziabher Setota new.

 4. zakios October 18, 2014 at 11:44 am Reply

  1.በዚህ ጉባዔ እንደ ኦርቶዶክሰ አማኝ ቤተክርስቲያኗ እየተመራቸ የአለችው በግብዞች: በሆዳሞች መሆኑን ያመለክተል፡፡
  2. ልብ ብሎ ለጠስተዋቸው የፓትርያረኩ ንግግር ከእሳቸው የመጣ ሳይሆን የተጫኑትን እንደማራግፍ ያሰቋጥራል፡፡ ከዚሀ ለመረዳት የሚቻለው የአመራር ብቃታው ምን ያህል የወረደ መሆኑን ያመላክተል፡፡
  3. ሁለት ቤተከርሰቲያን የለም ሲሉ በምሬት ተናግረዋል ፡፡ እራሳቸው ሌላ ጽሐፈት ቤት ከፍተው የለም እንዴ ? ሁለት የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አሥኪያጅ እኮ ነ ው የአለው፡፡ ለአመራር አሥቸጋሪ ሆኖ የሚመጣው ከዚህ ነው ፡፡ይልቅስ ከሲኖዶሱ ጋራ አመራር ቢያዳብሩ ይሻላል፡፡
  4. ማኀበረ ቅዱሳን ቀጥ የአለና ተጠያቀነት የአለው መመሪያ ሊወጣላቸው ይገባል፡፡ ፓትርያረኩ የአነሱት ከተጋነነው ውጭ ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው በሥራ አመራር ሊገደብ ይገባዋል፡፡
  4. የቤተክርስቲያኗ የሒሳብ አሠራር ዘመናዊ መደረጉ የሚደነቅ እንጅ ክፋት የለውም ፡፡ እንዲያውም ተአማኒነትን ያመጣል፡፡ ብዙ ጊዜ የቤተክርስቲያኗ የችግሩ ምንጭ ይህው ነዉ ፡፡ የማልሰማማው በተከርሲቲያኗን ማዘመን በሚለው ነው፡፡ ትውፌቷ ሳይቀነሰ ፣ሰይዛነፍ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ የሊቃውንቷች ገባዔ በቋሚነት ሊኖራት ይገባል፡፡ ይልቅስ ብፁዓን አባቶች ቢተጉ ይሻላል፡፡

 5. Anonymous October 18, 2014 at 4:09 pm Reply

  MR. malet Tsere orthodox nachew, ager ena hizb endikefafel yemifelgu yediablos melktegnoch nachew, slezih hulachihu tetenkeku endayastachhu, minim ayawkum.

 6. ተስፋዬ October 18, 2014 at 7:04 pm Reply

  ምድረ መናፈቅ ና ዘረኛ ቢራወጥ ምን ያመጣል ?ከዘርና ከ ሙሰኝነት ሳይወጡ ሰውን መክሰስ ምን ያደረጋል?
  ክህነታቸውን አላግባብ የሚጠቀሙ መጨረሻችው ምን እንደሆነ ይታወቃል !!!ያው ምንፍቅና ነው

 7. Anonymous October 18, 2014 at 7:29 pm Reply

  Abyss: Teklu Abate
  “ፓትርያርክ ብፁዕ አባ ማትያስና ተግዳሮቶቻቸው ”

  ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከተሾሙ እነሆ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው አራት ወራት ገደማ ይቀራቸዋል:: ቅድመና ድኅረ ሹመታቸውን ተከትሎ የውይይትና የክርክር መድረኮች በኢትዮጵያም በውጭውም ዓለም ተከፍተው ነበር:: የአምስተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ ሞት አንዳች ለውጥ ለቤተ ክርስቲያኗ ያመጣ ይሆናል ብለው የገመቱና የተመኙ ብዙዎች ነበሩ:: ሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ሊያወርዱ እንደሚችሉ ተተነተነ:: ዳሩ ግን የእርቁ ሂደት ሳያልቅ ምርጫ ተደረገና ብፁዕ አቡነ ማትያስ በወሳኝ ድምጽ እንዳሸነፉ ተነገረ:: መንግስት ከነበሩበት አስመጥቶ እንዳሾማቸው:: እርሳቸውም ነጭ ልብስ እንደማይለብሱና የቅንጦት ኑሮ እንደሚጸየፉ: ቤተ ክርስቲያን ያጣችውን ክብርና ተሰሚነት እንደሚመልሱ ተናገሩ:: «ይህን ማን አየው» በሚል ተስፋ አዲሱ ፓትርያርክ የለውጥ ሐዋርያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቅር እያላቸውም ቢሆን የገመቱ ነበሩ::

  የጎላ ነገር ሳይሰራ እነሆ ሁለተኛ በዓለ ሲመታቸውን ሊያከብሩ ነው:: ከቀድሞው ፓትርያርክ ጋር አንጻራዊ በሆነ መልኩ ሲወዳደሩ አቡነ ማትያስ ብዙም የመድረክ ሰው አይመስሉም:: በተለያዩ ጉባዔያትና መገኛ ብዙሃንም የአቡነ ጳውሎስን ያህል ጎልተው አልወጡም:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ድምጻቸውና ያሉበት ሁኔታ እየተሰማ የመጣ ይመስላል:: በሆነ ወቅት ላይ በመንግስት ካድሬዎች ለሰዓታት እንደታሰሩና እንግልትም እንደደረሰባቸው ሲነገር ነበር (ይህ እውነት መሆኑን ያጣራ አካል ግን የለም):: የእስራታቸው ዜና ከተሰማ ጀምሮ ግን በንግግራቸው ጠንከር ያሉና የፖለቲካ ቃና ያላቸው አቋሞችን ማስተላለፍ የጀመሩ ይመስላል:: በተለይ ከመስከረም ወር 2007 የመጨረሻ ሳምንት ጀምሮ ጠንከር ያሉ ጉዳዮችን ጠንከር ባሉ አነጋገሮች ማቅረብ ጀምረዋል::

  የብፁዕነታቸውን የአመራር ክህሎቶችና ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ቅርብ ጊዜ በተደረጉና በመደረግ ላይ ባሉ የቤተ ክርስቲያኗ ጉባዔያት ላይ ፓትርያርኩ ያቀረቧቸው ንግግሮች ዋና የመረጃ ምንጭ ናቸው:: አንደኛው መስከረም ፳፯ ቀን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ፣ መስከረም ፳፱ ቀን ደግሞ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሃፊዎች የታደሙበት ጉባዔ ነው:: የዚህ ጉባዔ መሪ ቃል ‹‹በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመልካም አስተዳደር አስተሳሰብን ማበልጸግ›› የሚል ሲሆነ ብፁዕነታቸው የመክፈቻ ንግግር በጽሁፍ አቅርበዋል:: ሁለተኛው የመረጃ ምንጭ ደግሞ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብሰባ አዳራሽ በተጀመረው ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ላይ ፓትርያርኩ የተናገሩት ነው:: ከነዚህ ንግግሮች ቢያንስ ቀጥለው ያሉትን ጉዳዮች መረዳት ይቻላል:: ከቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አስተዳደር አካላት ጋር አለመናበብ
  የአምስተኛው ፓትርያርክ አንዱና ትልቁ ችግራቸው በየደረጃው ካሉ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር አካላት ጋር ተናቦ: ተቻችሎና ተስማምቶ አለመስራት ነበር:: የስብሰባ አጀንዳ ከመምረጥ ጀምሮ ውሳኔዎችን እስከማሳለፍና እስከማስፈጸም ባሉ
  ሂደቶች ቅዱስ ሲኖዶስን ይገዳደሩት ነበር:: በሚያሳድሩት ቀጥታዊና ሥልታዊ ጫና ሲኖዶሱ ጥርስ የሌለው አንበሳ መስሎ እስከመታየት ደርሶ ነበር:: እንደምንም ተብሎ የተላለፉ ውሳኔዎች ሳይፈጸሙ የራሳቸው ህይወት ተፈጸመ::

  ስድስተኛውም ፓትርያርክ ገና ከጠዋቱ «ብቸኛ ሆኛለሁ» ማለት ጀምረዋል:: እርሳቸው ብቻቸውን እንደሆኑና ሃሳባቸውን የሚሰማ የበላይ አካል እንደሌለ በመረዳታቸው በአጥቢያ ደረጃ ካሉ አለቃዎች ጋር «ዝቅ» ብለው መወያየት እንዳስገደዳቸው በመስከረሙ ጉባዔ አሳውቀዋል:: በንግግራቸውም የደብርና የገዳማት አለቆች ከጎናቸው እንዲቆሙ ተማጽነዋል:: በአጥቢያ ደረጃ ካሉ አመራሮች ጋር መወያየቱ በራሱ ችግር የለውም:: ችግሩ የበላዩ አመራሮች ወይም ቅዱስ ሲኖዶስ በሥራቸው እንዳልተባበራቸው በስሞታ መልክ ለበታች አካላት መቅረቡ ነው:: ይህ ጉዳይ በተለያዩ እርከኖች ያሉ የቤተ ክርስቲያኗ አካላት ላይ አላስፈላጊ ጥርጣሬ ከመፍጥሩም በላይ ሥራን ይበድላል:: ይህንንም በተመለከተ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አሥኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የሰጡት መልስ ተጠቃሽ ነው:: ፓትርያርኩ የጠሩት ስብሰባ ግልጽነት የጎደለውና ወቅታዊ ጉዳዮችንም የተመለከተ እንዳልሆነ ብፁዕነታቸው ተናግረዋል:: እንግዲህ ከጠቅላይ ቤተ ክህነትና ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅናና ይሁንታ ውጭ የሚደረግ ስብሰባና የሚተላለፍ ውሳኔ እንዴት ውጤት ይኖረዋል? በአምስተኛው ፓትርያርክ ዘመን ቅዱስ ሲኖዶስ ያጣውን የመወሰንና የማስፈጸም አቅም ከማራዘም ውጭ ሌላ ምን ፋይዳ አለው? ይህ ተናቦ አለመስራት የቤተ ክርስቲያኗን ሰላምና አንድነት ይፈታተናል:: ቤተ ክርስቲያን የምትፈልገው የአንድ ሰው ወይም አካል ገናናነትን ሳይሆን ተስማምቶና ተቻችሎ ከሁሉም አካላት ጋር መስራትን ነውና ብፁዕነታቸው ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በክብር እንዲሰሩ ክርስትናው ያስገድዳል:: ወሳኝ የሆኑትን ጉዳዮች ትቶ በጥቃቅን ነገሮች ላይ ማተኮር ፓትርያርኩ መስከረም ፳፯ ቀን ጉባዔውን ሲከፍቱ ቀጥለው የተዘረዘሩትን አንገብጋቢ የሆኑ የቤተ ክርስቲያኗን ችግሮችን ዘርዝረዋል  የምእመናን በቁጥር መቀነስ  የቤተ ክርስቲያን ሃብት መቀነስና አብያተ ክርስቲያናት መዘጋት  የቤተ ክርስቲያን እሴቶች ለኢትዮጵያ የሚያበረክቱት ጠቀሜታ መቀነስ  መዋቅር ዘርግተው ለራሳቸው ጥቅም የሚሯሯጡ ሃላፊዎች መበራከት  ከቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እጅግ የላቀ መንፈሳዊ ተግባር መጥፋት  በቤተ ክርስቲያን ስም የሚደራጁ ማኅበራትና ግለሰቦች መዋቅርን አለመከተል  ማኅበራትና ግለሰቦች ንብረት ማፍራት ላይ መጠመድና አባቶችን መከፋፈል
  በእውነቱ ከሆነ እነዚህ ጉዳዮች እጅግ አሳሳቢዎች ናቸው.: ቶሎ መፍትሄ ካልተሰጣቸው ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር የተጣለባትን አደራ በተገቢው መጠን ልትወጣ አትችልም:: ዳሩ ግን ከጊዜና ከአቅም ውሱንነት የተነሳ እንዲሁም ከመረጃና ማስረጃ እጥረት የተነሳ ሁሉም ችግሮች በአንድ ጊዜ እኩል ትኩረት አያገኙም:: ለአጀንዳዎች ቅደም ተከተል ሰጥቶ መወያየት የሚያስፈልገውም ለዚህ ነው:: አስተዋይና አዋቂ መሪ የሚያስፈልገውም ለዚህ ነው:: ጥሩ መሪ ሁሉንም ችግሮች የሚፈታ ማለት ሳይሆን ወሳኝና አንገብጋቢ የሆኑትን ለይቶ በማውጣት መፍትሄ የሚሰጥ ማለት ነው:: ፓትርያርኩ ችግሮችን ቢዘረዝሩም ካለው ጊዜ አንጻር ትኩረት ሊሰጧቸው የሚገቡ ጉዳዮች መለየት ነበረባቸው:: የምእመናን ቁጥር መቀነስና የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት እንዲሁም የሙስና መስፋፋት ከማኅበራት ጥቃቅን ችግሮች ጋር እንዴት እኩል ይታያል?

  የሚገርመው ግን ረጅም ጊዜ የወሰዱ ጠንካራ ንግግሮች የተካሄዱት ከማኅበራትም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ብቻ ነበር:: የተወሰኑ የደብር አለቆች (አብዛኛው ችግር ከነሱ ሥራ ጋር እንደሚያያዝ ስላወቁ) የተወረወረውን ‘ጦር’ አቅጣጫ ቀየሩለት::
  ፓትርያርኩም ጉባዔው በማስተዋልና በመንፈሳዊነት መወያየት እንደሚያስፈልግ ከማሳሰብ ይልቅ ለጀሮ በሚሰቀጥጡ ስድብ ነክ ንግግሮች የተደሰቱ መስለው ታይተዋል:: መሪ የሌለው ስብሰባ ሆኖ የተነሳበትን «አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ» መሪ ቃል ሳይመራበት ቀረ:: የአቋም መግለጫ የወጣው ቤተ ክርስቲያኒቷን እያንገላታት ስላለው ስለሙስናና አድሎአዊ አሠራር ወይም ስለምእመናን መባዘንና አብያተ ክርስቲያናት መዘጋት ሳይሆን ስለአንድ ማኅበር ‘ሃብታም’ መሆን ነው:: በመሆኑም የእለቱ ጉባዔ መነሻውና መድረሻው ያልተጣጣሙ ሆነው ቀርቷል:: ይህም ከአመራር ብቃት ማነስ ወይም ከልዩ ዓላማ መኖር ጋር ሊያያዝ ይችላል:: ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉባዔያት የሚጠሩትና የሚመሩት እንዲህ ከሆነ እጅግ አሳዛኝና ፈታኝም ነው:: ብፁዕነታቸው ትልቁን ጉዳይ ከትንሹ ለይተው ካላወያዩና ከሚመለካተቸው አካላት ጋር አብረው ካልሰሩ የራሳቸውን ወይም የሌሎችን አካላት ፍላጎት ከመከተል የሚያግዳቸው አይኖርም:: ስሜትን መሠረት ያደረጉ ስሜት ቀስቃሽ ንግግሮች ንዴትን: ብስጭትን: ቅሬታን: ተስፋ መቁረጥን: ድካምን: ደስታን ወይም ስኬትን መነሻ ያደረገ ንግግር ሁሉ ስሜታዊ ነው:: አይደለም በመንፈሳዊ ህይወት በዓለማዊ አሠራርም ስሜታዊነት ጥቅም የለውም:: ጥሩ መሪ ማለትም ስሜትን ተቆጣጥሮ ሠራተኞችን ወይም አገልጋዮችን በማስተባበር ዓላማን ማሳካት የሚችል ነው:: ቅዱስ ፓትርያርኩ በልምድ ማጣትም ሆነ በብሶት ወይም በሌላ ምክንያት ስሜትን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ንግግሮችን ከላይ በተጠቀሱት ታላላቅ ጉባዔያት ደጋግመው ተናግረዋል:: ለምሳሌ ያህል ቀጥለው የተዘረዘሩት የፓትርያርኩ ንግግሮች አብይ ናቸው

   የሚሰማኝ ስላጣሁ ከበታች የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ጋር መወያየት አስፈለገኝ ወደፊትም ዓመቱን ሙሉ አደርገዋለሁ  ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ ነው የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ሃብት ቀምቷል  ይህ ማኅበር በቁጥጥር ሥር እንዲውል አሳስባለሁ  እኔ ይኽን ጉዳይ ከራሴ አወርዳለኹ፤ የቤተ ክርስቲያናችን ገንዘቧ፣ ክብሯ ተወስዷል  ቤተ ክርስቲያን ከቅኝ ተገዥነት ትውጣ፤ ካህናቱ ከመከራ ይውጡ  ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ፤ አንዷን ቅድስት፣ ኦርቶዶክሳዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ልመራ እንጂ ኹለት ቤተ ክርስቲያን የለችም  እኔ ብቻዬን የምሠራው ነገር የለም፤ በዚኽ መግለጫ እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ  በህግና በሥርዓት የማይመራ ማኅበር አሸባሪ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው  አባ ማትያስ አላበደም፤ መልእክቴን እያስተላለፍኹ ነው ያለኹት፤ መልእክቴን በጸጋ ተቀበሉ ብዬ እማፀናችኋለኹ
  እዚህ ላይ መነሳት የሚገባው ነገር ቢኖር ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት ከባድ ንግግሮች የቀረበ መረጃም ሆነ ማስረጃ አለመኖሩ ነው:: እንዴትና በምን ሁኔታና ምክንያት ነው ጠቅላይ ቤተ ክህነትና ቅዱስ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን ሃሳብ የማይጋሩ? ማኅበሩስ የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ሃብት የቀማው እንዴት ነው? ካህናትንስ እንዴትና በምን ሥልጣን ነው በገዥነት የያዛቸው? ለነዚህና ለሌሎችም ትችቶች መረጃም ሆነ ማስረጃ አልቀረበባቸውም:: ይህ ሆኖ ሳለ እንዴት ተደርጎ ነው የፓትርያርኩ ፍላጎት የሚፈጸመው? «ሃሳቤን በጸጋ ተቀበሉት» ማለታቸውም መረጃና ማስረጃ እንደሌላቸው ጠቋሚ ነው:: አሳማኝ መረጃና ማስረጃ ካለ መለማመጥም ሆነ መለመን አያስፈልግም:: ሁሉም አካል ለእውነት ተገዥ መሆን አለበትና:: የቀረቡት ንግግሮች መሠረታቸው በውል ባይታወቅም ከስሜት ግን የጸዱ አይደሉም:: ስሜት ደግሞ አይደለም ለፓትርያርክ
  ለተራ ክርስቲያንም የተመቸ ወይም የሚጠበቅ አይደለም:: ስሜት የጎበኛቸው ንግግሮች የሰውን እንጅ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለማያስቀድሙ በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች መካከል ክፍፍልን ያመጣሉ:: እልህን ከዚያም ቂምን ከዚያም መጠቃቃትን ይጋብዛሉና::

  ማጠቃለያ
  ከንግግራቸው እንደምንረዳው ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር መልካም ግንኙነት እንደሌላቸውና በዚህም የተነሳ መንፈሳቸው እንደተረበሸ ነው:: በዚህ ሁኔታ ያለ መሪ አይደለም አዲስ ውጤት ሊያመጣ ያለውን ሊንድ ይችላል:: ብፁዕነታቸው በተመረጡበት ወቅት ቤተ ክርስቲያኒቷ ያጣችውን ክብርና አንድነት እንዲሁም ተሰሚነት ለመመለስ ከሁሉም አካላት ጋር እንደሚሰሩ ቃል ገብተው ነበር:: ይህ ግን እስካሁን ሲደረግ ወይም ለመደረግ ሲሞከር አልታየም:: ይባስ ብሎ ጉባዔያት መረጃና ማስረጃ የሌላቸው ተራ ሊባሉ የሚችሉ ክሶችን በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ:: ከጥቂት ታዳሚዎች በስተቀር አብዛኞቹ ግራ ከመጋባትና ከመለያየት ባለፈ እየቀረቡ ባሉ ንግግሮች ተጠቃሚዎች ሊሆኑ አይችሉም:: ይህም የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልግሎት በእጅጉ ይጎዳል::
  ይቅር የማይሉና እርቅን የማያውቁ ባለሥልጣናት እንዴት ወንጌልን ሊሰብኩ ይችላሉ? ያጠፋ አካል ካለ ጥፋቱ በተጨባጭ ተነግሮት ይመከራል: አስተዳደራዊ ርምጃ ይወሰዳል እንጅ በመድረክ የስድብ ናዳ ይወረድበታል? የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዴት ይካሄድበታል? ከላይ ያሉት አባቶች በእንደዚህ ያሉ ነገሮች የሚጠመዱ ከሆነ ምእመናን ማንን አርአያ ሊያደርጉ ይችላሉ??? ምናልባትም የምእመናን ቁጥር መቀነስ አንዱና ትልቁ ምክንያት ይህ የበላይ አካላት አላስፈላጊ ግብግብ ይመስለኛል:: ብፁዕነታቸው ለራሳቸውና ለንግግራቸው ይበልጥ በመጠንቀቅ የአባትነት ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል:: የይቅርታ: የእርቅ: የአንድነትና የሰላም አርአያ ሆነው መቀጠል ይጠበቅባቸዋል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን የሚፈልጉት ፍጹም መንፈሳዊ አባት እንጅ በሥልጣኑና በኃይሉ የሚመካ መሪ አይደለም::

 8. Anonymous October 18, 2014 at 8:02 pm Reply

  “..አጠቃላይ ጉባኤው ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን አቋም እንዲይዝና በጋራ መግለጫው እንዲያካትት ጥቂት አማሳኞች የሚያደርጉት ጫና ፓትርያርኩን የበለጠ ከማዋረድ ያለፈ ፋይዳ እንደማይኖረው ታምኖበታል፡፡” የሚለዉ የዚህ ዜና መደምደሚያ በምንም መልኩ አይዋጥልኝም።.እኔ ስለሚባለዉ ማኅበር የማዉቀዉ ባይኖርም እነዚህ “ጥቂት አማሳኞች” ይህንን አደረጉ ማለት በራሱ የሚያሳየዉ ቤተክርስቲያኒቱ በመስቀልኛ መንገድ ላይ መሆኗን ነዉ። ዓለማዊዉ ኃይል “የ’እምነት አባቶችን” መግዛት ከቻለ እምነቱ ጥያቄ ዉስጥ ገባ ማለት ነዉ። ተስፋ የማደርገዉ በ’እምነታቸዉ የፀኑት ሁሉ ፈጣሪያቸዉን በፀሎትና በፆም እየለመኑ ችግሩን በሰላም በመፍታት ቤተክርስቲያኒቱ ተግባሪዋን በሰላም እንደምትቀጥል ነዉ።

  • Anonymous October 21, 2014 at 8:27 am Reply

   Abatachin politica temoletewal,huletun wodo ayihonem andun yimeretu,politica or haymanot
   hayimanotachin basawekin mahiber kidusan lay lemen mangoragore? sigemer yemengist meliketegna nachewu!

 9. Kebede October 18, 2014 at 9:12 pm Reply

  እውነተኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝና አስመሳይ ነጋዴው ፥ ማለት ስንዴውና እንክርዳዱ የሚለይበት ወቅት ላይ ስለሆን፥ በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለን የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ከስንዴው ጋር ቁመን እንክርዳዱን መታገል አለብን። አምላካችን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና በደሙ የመሠረታትን ቅድስት ወአሐቲ ቤተ ክርስትያን ይጠብቅልን። ለክብሯና ለአንድነቷ የቆሙትን ልጆቿን ፈተናውን ሁሉ ለማለፍ በጽናት ያቁምልን። ዓሜን።

 10. Mesele Nigatu Deko October 18, 2014 at 9:12 pm Reply

  let us see the truth together

 11. Anonymous October 18, 2014 at 9:24 pm Reply

  በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ቀራንዮ መድኃኔዓለም አለቅነት ተሾመው የሄዱትን አባት ካህናቱ አስቸገሯቸው፡፡ ለጥቂት ጊዜ የተላኩበትን ሊሠሩ ሞከሩ ግን አልሆነም፡፡ በመጨረሻም ለንጉሡ እንዲቀይሯቸው አመለከቱ፡፡ ንጉሡም ምነው ምን ገጠመህ? ቢሏቸው ‹‹ካህናቱም ካህናቱ፣ ቀራንዮም ቀራንዮ፣ መድኃኔዓለምም መድኃኔዓለም›› አሉ ይባላል፡፡ Source: Daniel Kibret’s views

 12. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነው October 19, 2014 at 9:38 am Reply

  The trial of mahibere kidusan

  http://www.youtube.com/watch?v=jejc0VNegi8 (ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ – )

  http://www.youtube.com/watch?v=A6bpGTYobug (ይኼኛው ግለሰብ ጤነኛም አይመስል – የወያኔ ካድሬ እንጂ)

 13. Anonymous October 19, 2014 at 10:57 am Reply

  ‹‹ እግር ካመመ በክረንች ወይም በመኪና መሄድ ይቻላል ጭንቅላት ካመመስ…..?? ምህረቱ ከላይ ይላክልን የማህበራችንንም አፅራር ያስትግስልን !!ማህበረ ቅዱሳን አይዙዋችሁ ስራችሁም በይበልጥ ቀጥሉበት ፀሎትን ማዘውተር ግድ ይለናልና››

 14. tadu October 20, 2014 at 1:46 pm Reply

  የተዋህዶ ልጆች ማ.ቅ አይዞኣችሁ ልጆቼ። እናንተ መንፈስ ቅዱስ ባቀበላችሁ ብዙ ታውቃላችሁ። ይህች ምድር ለኣምላክዋም ፈተና ነበረች እና በእሱ ሃይል ፅኑ! ፍዳው የሚብሰው እያወቁ ላላወቁ ነው። ሁላችንንም ከዚህ አይነቱ ማስተዋል ማጣት ወይም ትንቢት መፈፀሚያ መሆን ያድነን!!

 15. tadu October 20, 2014 at 2:14 pm Reply

  ዋ! ምድረ ሆዳም እና የቤተክርስትያን ደም መጣጭ ሁላ ከማ.ቅዱሳን ሳይሆን ከፈጣሪህ እንደተጣላህ የምታስተውልበት አእምሮህን እንዳጣህ እወቅ!!

 16. tadu October 20, 2014 at 2:19 pm Reply

  በጣም የሚያሳዝነው እና ክብራቸውን የገፈፈው ነገር ቢኖር በንግግራቸው ሁሉ ያንገበገባቸው የገንዘቡ ኪሳቸው አለመግባት እንጂ የቤተክርስትያኒቱ አገልግሎት ጉዳይ አለመሆኑ ነው።

 17. Anonymous October 21, 2014 at 6:41 am Reply

  አንደኛ ቅዱስ ፓትርያርኩ ማህበሩ በህግ አልሄድ አለ፣ የሚጠይቀውም ጠፋ፣ ወደ ህግ ይግባ፣ ገንዘብ የሚሰበስብበትም ደረሰኝ እንደ ሌሎቹ ማህበራት /ደጆችሽ አይዘጉ/ አይነት በቤተ ክርስቲያኒቷ ይሁን ነው ያሉት እንጂ ይፈረስ የሚል ቃል ከአንደበታቸው አልወጣም፡፡ ይህ ማለት ግን ባህበሩ እዲፈርስ የሚፈልጉ ወገኖች የሉም ማለት ግን አይደለም፡፡
  እንደው እውነት እንነጋር ከተባለ 20 ዓመት ሙሉ ራሱን ሲያደራጅ እንጂ ቤተ ክርስቲያንን መቸ አደራጀ? ምን አልባት መቸ አሰሩትና ምናምን ሊባል ይችላል እስኪ የትኛ ሰ/ት/ቤትን አደራጀ፣ ወደ ራሱ ሥራ አቀረበ /መጽሔት ህትመት፣ ስብከተ ወንጌል…/ ዘወትር ማህበሩ ሲያደርግ የነበረው ሁሉንም ሰ/ት/ቤቶች በአባላቱ ለመሙላትና ለመቆጣጠር እንዲሁም የእርሱ ተላላኪ እንጂ እርሱን እንዳይሆኑ ነበር ሲሰራ የነበረው፡፡ ደግሞስ ዓላማው ጥቅም ካልሆነ ለምን ተቋማቱን በአክስዮን ስም አዞረ/ለምሳሌ አቡነ ጎርጎዮስ ት/ቤቱን፣ ሐይመት የባልትና ውጤቶች… ወዘተ/
  ስለዚህ አሁንም ቅዱስ ፓትርያርኩ እንዳሉት በህግ ይገዛ፣ የቤ/ክ ደረሰኝን ይጠቀም፣ ሰ/ት/ቤቶች የማህበሩን ሥራ እዲሰሩ ሳይሆን የራሳቸውን ሥራ እዲሰሩ ያግዝ ፡፡ ይፍረስ የሚለው አይሆንም፣ አይፈርስምም

 18. Anonymous October 21, 2014 at 10:50 am Reply

  amets eyekesekesachu new libel betekiristanun lemafires enidezih yale zena ena were lemnim ayibejim

 19. abebech October 21, 2014 at 1:33 pm Reply

  እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን ማስተዋልን ይስጠን ዋናው ማስተዋል ነው

 20. abebech October 21, 2014 at 1:45 pm Reply

  ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ…በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል ትን.ዕንባ.3፡17-19″

  በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ 22 ዓመታት ተጉዟል፡፡

  ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡
  ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

  ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ወዳጆች አፈራ? ጠላቶችስ ለምን ተነሡበት?
  ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ፈቅዶ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ ወጣቶችን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርታቸው ጎን ለጎን በየአካባቢው ወደሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሔደው መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲማሩ በማድረግ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁና ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው እንዲያገለግሉ በማድረግ፤ በተጨማሪም ወጣቱ ሀገሩንና ሕዝቦቿን አክባሪ፣ በሥነ ምግባር የታነጸ እንዲሆን በማስቻሉ ብዙ ወዳጆችን አግኝቷል፡፡

  ከዚህም ሌላ የመናፍቃኑንና ቤተ ክርስቲያኒቱን እናድሳለን ብለው የተነሡትን የመናፍቃኑ ተላላኪ ቡድኖችን ሴራና የአክራሪ እስልምናውን እንቅስቃሴ በመረጃ አስደግፎ በማጋለጡ፣ ከክፉ ትምህርታቸው መመለስ ያልፈለጉ የተሐድሶ ቡድን አባላት ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ ስለተወሰነባቸው እና ሌሎችንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግሮች እየተከታተለ ለዕድገቷና ለብልጽግናዋ በመሥራቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆችን አፍርቷል፡፡

 21. Anonymous October 21, 2014 at 2:26 pm Reply

  በህግ አልገዛ ያለው አጠቃላይ የቤተክህነቱ አሳተዳደር እንጂ የማህበረ ቅዱሳን አገልግሎት አይደለም። ማ.ቅ. በቤተክህነቱ የእዝ ሰንሰለት ውስጥ ለመግባት በመጀመሪያ ቤተክህነቱን እንደትኋን ከሚበሏት ካህን ወይም አገልጋይ እና ከማንም በላይ ለቤተክርስትያን ተቆርቋሪ ነን ባዮች ለማፅዳት ቁልፍ የሆነ የአሰራር ስርአት መዘርጋት አለበት፤ የማ.ቅ.አብይ አላማ ይህ ነው። አእምሮ እና ማስተዋል ያለው ሁሉ ይህን ያውቃል። ምእመኑ ሳይተርፈው ቤተክርስቲያኔን ላሳድግ፤ ሃይማኖቴ ትጠንክር ብሎ የሚለግሰውን ከኪሳቸው እንዳይወጣ የበግ ለምድ በመልበስ ቤተክርስትያኒቱ ውስጥ በመሰግሰግ የቤተክርስቲያኗን እድገት ወደታች፤ ምእመኑን ወደ እናት ቤተክርስትያን ከመሰብሰብ ይልቅ በክፉ ምግባራቸው መበተን፤ ወንጌል በመናፍቃን እና በተሃድሶዎች በየቤተክርስቲያኒቱ እንዲሰበክ ማድረግ፤ በየቤተክርስትያኑ ፍቅር እንዲጠፋ ማድረግ፤ የቤተክርስትያን ቅርስ እንዲዘረፍ ማድረግ፤ ምእመኑ የሃይማኖቱን ትሩፋት ጠብቆ እንዳይሄድ የሚያደርጉ እና አትስረቅ እያሉ የሚሰርቁ፤ አታመንዝር እያሉ የሚያመነዝሩ፤ አትሳደብ እያሉ የሚሳደቡ፤ ማ.ቅ.ንን ቢወነጅሉ አይፈረድባቸውም። ምክንያቱም አምላክ የሰጣቸውን ሓዋሪያዊ ተልእኮ ለስጋዊ ጥቅም በመሸጥ ባለፉበት፣ ባልደከሙበት የቤተክርስትያኒቱ ሃብት የቅንጦት ኑሮ ላይ ስላሉ የማ.ቅ.ጉዳይ የእግር እሾህ ቢሆንባቸው አይገርምም ። ይህ ድሮም ይታወቃል እሰከ ዛሬም መቆየታቸው አይዞኣችሁ ግፉበት የሚላቸው ጠፍቶ እንጂ። ታድያ ለፍጥረቱ የሚያስብ እግዚኣብሄር ማረፊያ ቢያጣ ለነዚህ ልጆች ጸጋውን አብዝቶ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ የወጣቱ ተረካቢ ማጣት፤ የምእመኑ ከቤተክርስትያን መራቅ እና ወንጌል መራብ የቤተክርስትያን ቅርስ መጥፋት፤ ቢያሳስባቸው ወደ ኣባቶች ቢጮሁ ሰሚ ማጣታቸው፤ እንቅልፍ ሳያምራቸው ከደምወዛቸው ቆርሰው ፈጣሪ በሰጣቸው እውቀት ካለዋጋ እንዲያገለግሉ አምላክ መረጣቸው። ስለዚህ ከኣባቶች የሚጠበቀው የስራቸውን ፍሬ አይተው ልጆቼ በርቱ እናንተም አግዙን እኛም እንርዳችሁ የኛ ተተኪዎች እናንተ ናችሁ ማለት ነበር እግዜር ልቦና ቢሰጣቸው። አሁንም እዝነ ልቦናቸውን ያብራላቸው! የንስሃ እድሜ ይስጣቸው! ማ.ቅ. ገንዘብ ቢሰበስብ የወደቁትን ኣነሳበት፤ ወንጌል አስተማረበት ፤ ምእመኑን ወደ እናት ቤተክርስትያን መለሰበት፤ ቤተክርስትያን አነፀበት፤ የተበተኑትን ሰበሰበበት፤ ቅርስ አኖረበት እንጂ የውሃ ጠብታ ወደ ጉሮሮው ኣላከበትም!!! ኣላማውም ስላልሆነ።

 22. Nigatu Deko December 13, 2015 at 1:09 pm Reply

  Pleas let us pray as uor …

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: