ማኅበረ ቅዱሳን: ፓትርያርኩ በመሯቸው ስብሰባዎች በሚካሔድበት የስም ማጥፋት ዘመቻ ቅሬታውን ገለጸ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጠው ጠየቀ

 • ኑፋቄያቸውና ሕገ ወጥ ጥቅማቸው እንዳይጋለጥ የሚሰጉ አካላት ያስተባበሩት ነው
 • የብፁዓን አባቶች ስም እየተጠቀሰ የወረደው የስድብ ናዳ በእጅጉ አሳዝኖናል
 • በፈቃዳችንና በነፃ የምንፈጽመውን የአገልግሎት መብታችንን የሚፃረር ነው
 • ግለሰቦቹ በስም ማጥፋት ዘመቻቸው ከቀጠሉ ማኅበሩ በሕግ ይጠይቃቸዋል

*               *               *

 • የስም ማጥፋት ድርጊቱን የፈጸሙበት ግለሰቦች÷ ራሳቸውን ደብቀው የምንፍቅና ዓላማን ያነገቡና ማኅበሩ ለዓላማቸው መሳካት ዕንቅፋት እንደኾነባቸው የሚያምኑ፤ የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመጠቀም የግል ሀብት የሚያካብቱና ማኅበሩ ሊያጋልጠን አልያም ምቹ ኹኔታ ፈጥሮልን የኖረውን የሒሳብና ሌሎች አሠራሮች ክፍተት ሊደፍንብን ይችላል በሚል የሚፈሩ፤ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር በተማረ ኃይል በመሙላት ቦታ ያሳጣናል በሚል የሚሰጉ፤ ማኅበሩን በመቃወም ማኅበሩን ከሚጠሉ አካላት ጥቅም ለማግኘት ወይም በተሳሳተ መረጃ የማኅበሩን አገልግሎት ጥቅም ባለመረዳት የሚቃወሙ ናቸው፡
 • ማኅበረ ቅዱሳን ዘመናዊና በሕግም ተቀባይነት ያለውን የኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት (double entry accounting system) የሚከተል በመኾኑ የቤተ ክህነቱን የነጠላ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት ለመከተል እንደተቸገረ በተደጋጋሚ አስረድቷል፡፡ ይኹንና የቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት ባስፈለገው ጊዜ ማኅበሩ በውስጥ ይኹን በውጭ ኦዲተር ያስመረመረውን ሒሳብ ማየት፣ በአካልም ተገኝቶ ማረጋገጥ እንደሚችል ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ማስታወቁን አውስቷል፡፡
 • ማኅበሩ በማንኛውም የፖሊቲካ አመለካከት ጣልቃ እንደማይገባና አገልግሎቱ ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ እንዳልኾነ አረጋግጦ፣ ማኅበሩ የፖሊቲካ ዓላማ እንዳለው ለተሰነዘረው ውንጀላ መረጃው ቀርቦ በሚመለከተው አካል ሊታይና ሊጣራ እየቻለ የማይመለከታቸው አካላት ከሜዳ ተነሥተው ስም ለማጥፋት ሊጠቀሙበት እንደማይገባ አሳስቧል፡፡ ማኅበሩ ‹‹አክራሪ ነው፤ አሸባሪ ነው›› ማለትም ‹‹ውንጀላን ከማዳመቅ ያላለፈ ፋይዳ የሌለው መሠረተ ቢስ ክሥ፤›› ነው፡
 • ማኅበሩ ‹‹ከምእመናን የዐሥራት በኵራት ገቢ ይሰበስባል›› በሚል በስብሰባዎቹ ላይ የተሰነዘረበትን ‹‹ስም ማጥፋት›› ፍጹም ሐሰት በማለት አጣጥሎታል፡፡ በሰጠው ምላሽም ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱን የሚያከናውነው ከአባላቱ ገቢ በሚሰበስበው የኹለት በመቶ ወርኃዊ አስተዋፅኦ እንደኾነ፣ ለቅዱሳት መካናትና ለስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራሞች ደግሞ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ከገባሬ ሠናይ ምእመናን ድጋፍ እንደሚያፈላልግ ገልጧል፡
 • ማንኛውም ግለሰብ ይኹን ኅብረተሰብ የራሱን እምነት ከማራመድ አልፎ በሌላው እምነት ጣልቃ መግባት ስለሌለበት፣ ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ጣልቃ ገብተው የሚያውኩትን የተሐድሶ መናፍቃን የመከላከልና ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ተልእኮዬን አጠናክሬ እቀጥላለኹ፤›› ብሏል፤ ‹‹እናቱን አውሬ ሲበላት ቆሞ የሚሥቅ ልጅ የለም›› ሲልም አቋሙን አስረግጧል፡
 • ፓትርያርኩ በሚጠሯቸው ስብሰባዎች የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ በተመሳሳይ መልኩ ከቀጠለ÷ ቤተ ክርስቲያንን እርስ በርሷ የማትናበብ፣ ማእከላዊ አሠራር የሌላት የሚያስመስልና ለአገልግሎቷ ዕንቅፋት የሚፈጥር በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን በጥንቃቄ መርምሮና አጣርቶ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠይቋል፡፡

(የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከዜናው ቀጥሎ ይመልከቱ)

*                 *                *

(ሰንደቅ፤ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

mahibere kidusan logoበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር አገልግሎቱን የሚፈጽመው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ፓትርያርኩ በተገኙባቸው ስብሰባዎችና ስለ ስብሰባዎቹ በሚዘግቡ ሚዲያዎች ላይ የማኅበሩ ስም እየተጠቀሰ የሚካሔድበትን የስም ማጥፋት ዘመቻ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት መጠየቁ ተገለጸ፡፡

ማኅበሩ ጥያቄውን ያቀረበው ‹‹በሚዲያና በተለያዩ ስብሰባዎች የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ አግባብ አለመኾኑን ስለመጠየቅ›› በሚል ጥቅምት ፩ ቀን በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በግልባጭ ደግሞ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመ/ፓ/ጠቅ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የቅሲኖዶስ አባላት ለኾኑት ለኹሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሰራጨው ደብዳቤ* ነው፡፡

ላለፉት 23 ዓመታት በቅዱስ ሲኖዶስ በወጣለትና በተፈቀደለት ሕግና ደንብ መሠረት በቤተ ክርስቲያን ሥር ተዋቅሮ ኹለንተናዊ አገልግሎቷን ለመደገፍና ለማጠናከር የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጸው ማኅበሩ÷ በማያውቀው፣ ጥፋትም ካለ ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና መልስ ባልሰጠበት ኹኔታ ፓትርያርኩ ባሉባቸውና በተለያዩ ጊዜያት በተጠሩ ስብሰባዎች የተፈጸምበት የስም ማጥፋት ዘመቻ መደጋገም ደብዳቤውን ለመጻፍ እንዳስገደደው ገልጧል፡፡

aba mathias opening the conf

‹‹ቅዱስነትዎም ይህ ኹሉ ሲኾን የማኅበሩን አመራር አካላት አንድም ቀን ጠርተው አለመጠየቅዎ እንደ ልጅነታችን አሳዝኖናል::›› (ማኅበረ ቅዱሳን)

ማኅበሩ በደብዳቤው፣ በየስብሰባዎቹ የሕዝብ መገናኛ አውታሮች እየተጠሩ በማኅበሩ አገልግሎት ምክንያት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የኾኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በስም እየተጠቀሱ ተራ የስድብ ናዳ እንደወረደባቸው ገልጦ፣ ‹‹የስም ማጥፋት ዘመቻው እኛንም ኾነ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶችንና ምእመናንን በእጅጉ አሳዝኖናል፤›› ብሏል፡፡ ስብሰባው የተቀረፀበትንና ‹‹አስነዋሪ›› ሲል የገለጸውን ቪዲዮ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሕጋዊ ድረ ገጽ ላይ በኢንተርኔት መለቀቁ፣ የቤተ ክርስቲያን አካላት ነን ከሚሉ ሰዎች የማይጠበቅና ‹‹ቤተ ክርስቲያንን ለጠላት መሳለቂያ ለማድረግ›› በጥፋት መልእክተኞች የተቀናበረ እንደኾነ አመልክቷል፡፡

ትውልዱ በእምነትና በዕውቀት ታንፆ በሞያው፣ በገንዘቡና በጉልበቱ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያገልግልና ሐዋርያዊ ተልእኮዋ እንዲፋጠን ማኅበሩ ያበረከተው አገልግሎትና ስኬት አኹን ላለበት ደረጃ የደረሰው በብፁዓን አባቶችና በሊቃውንት ምክርና ጸሎት ተደግፎ እንደኾነ ደብዳቤው አስታውሷል፡፡ የቤተ ክርስቲያን እምነቷና ሥርዓቷ ሳይበረዝና ሳይከለስ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ጥብቅና በመቆሙ፣ ከዚኽም አንጻር ‹‹አፅራረ ቤተ ክርስቲያን›› ናቸው ካላቸው አካላት የሚሰነዘሩ ‹‹የተሐድሶ ሽምቅ ደባዎች››ን ለቅዱስ ሲኖዶስ በማስረጃ አስደግፎ በማጋለጡና ማስረጃው ተጠንቶና ተረጋግጦ በውግዘት እንዲለዩ በማድረጉ ምክንያት በአገልግሎቱ ላይ ግልጽና ስውር ፈተናዎች እየተፈጠሩ መቆየታቸውን አስረድቷል፡፡

ማኅበሩ ‹‹አስነዋሪ›› ያለውና በተጠቀሰው መምሪያ ሕጋዊ ድረ ገጽ ላይ የተለቀቀው ቪዲዮ መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ›› በሚል ርእስ የተካሔደውን የግማሽ ቀን ስብሰባ የሚያሳይ መኾኑ ታውቋል፡፡ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ በጽሑፍ የተደገፈ ገለጻ የሰጡበትና በልዩ ጸሐፊያቸው የተመራው ይኸው ስብሰባ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች የተካፈሉበት ሲኾን የማኅበረ ቅዱሳንን ስም በመጥቀስ ማኅበሩ ‹‹ለአባቶች አይታዘዝም፤ መዋቅር ጠብቆ አይሠራም፤ ሒሳቡን አያስመረምርም፤ ዐሥራት ይሰበስባል፤ የፖሊቲካ ዓላማ አለው፤ አክራሪና አሸባሪ ነው…ወዘተ›› በሚሉ ሐሳቦች ዙሪያ ያተኮሩ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደተፈጸመበት ደብዳቤው ዘርዝሯል፡፡

Zekarias Addis a day light robber

ከጭናክሰን/ጅግጅጋ እስከ አዲስ አበባ በማፊያ ምግባሩ የታወቀው የአማሳኞች ፊታውራሪ ወሮበላው ዘካርያስ ሓዲስ

ማኅበሩ በስብሰባው ላይ ‹‹ስም ማጥፋት›› የተባለውን ድርጊት የፈጸሙበት ግለሰቦች ማንነት እንደየ     ምክንያታቸው ሊለያይ እንደሚችል በተለያዩ ጊዜያት ያካሔዳቸውን ጥናቶች መነሻ በማድረግ አመልክቷል፡፡ እኒኽም÷ ራሳቸውን ደብቀው የምንፍቅና ዓላማን ያነገቡና ማኅበሩ ለዓላማቸው መሳካት ዕንቅፋት እንደኾነባቸው የሚያምኑ፤ የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመጠቀም የግል ሀብት የሚያካብቱና ማኅበሩ ሊያጋልጠን አልያም ምቹ ኹኔታ ፈጥሮልን የኖረውን የሒሳብና ሌሎች አሠራሮች ክፍተት ሊደፍንብን ይችላል በሚል የሚፈሩ፤ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር በተማረ ኃይል በመሙላት ቦታ ያሳጣናል በሚል የሚሰጉ፤ ማኅበሩን በመቃወም ማኅበሩን ከሚጠሉ አካላት ጥቅም ለማግኘት ወይም በተሳሳተ መረጃ የማኅበሩን አገልግሎት ጥቅም ባለመረዳት የሚቃወሙ እንደኾኑ ነው ያስረዳው፡፡

የማኅበሩ አገልግሎት ችግር ይኖርበታል ተብሎ ቢታሰብ እንኳ ትክክለኛው አካሔድ ማኅበሩ በጉዳዩ ተጠርቶ፣ ተጠይቆና ችግሩ ተረጋግጦ እንዲያርም ማድረግ ነው ያለው ማኅበረ ቅዱሳን፣ የስብሰባው አካሔድ ‹‹ድብቅ ዓላማ አንግቦ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማደናቀፍ የተቀናጀ ሤራ ነው›› የሚያሰኝ ጥያቄ ሊያሥነሳ እንደሚችል ገልጧል፡፡ ‹‹ቅዱስነትዎም ይህ ኹሉ ሲኾን የማኅበሩን አመራር አካላት አንድም ቀን ጠርተው አለመጠየቅዎ እንደ ልጅነታችን አሳዝኖናል›› በማለትም ከስብሰባው ቀደም ሲል ከፓትርያርኩ ጋራ የውይይት መርሐ ግብር እንዲያዝለት በተደጋጋሚ ያቀረበው ጥያቄ** ተቀባይነት ባላገኘበት ኹኔታ መሠረት በሌላቸውና ከእውነትነት በራቁ የሐሰት ክሦች ‹‹የስም ማጥፋት ዘመቻ›› እንዲከፈትበት በመደረጉ ቅር መሰኘቱን አስታውቋል፡፡

በደብዳቤው እንደተብራራው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያኒቱን ኹለንተናዊ አገልግሎት የሚያበረክተው፣ ከዋናው ማእከል አንሥቶ በሀገር ውስጥና በውጭ አህጉረ ስብከት በተዘረጋው መዋቅሩ ሲኾን ይኸውም ከየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ በመመካከርና መመሪያ በመቀበል የሚከናወን ነው፡፡ በየጊዜው ዕቅዱን በማሳወቅ በየስድስት ወሩ የዕቅድ አፈጻጸምና የሒሳብ ሪፖርት ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያቀርባል፡፡ ሒሳቡን በየጊዜው በውስጥ ኦዲተር የሚያስመረምር ሲኾን በየዓመቱ ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባለው ሕጋዊ የውጭ ኦዲተር አስመርምሮ ለሚመለከታቸው የቤተ ክህነቱ አካላት እያቀረበ ይገኛል፡፡ በዚኽም ከየትኛውም አካል ጥያቄ፣ ነቀፌታ ይኹን እርማት ቀርቦበት ባያውቅም ባቀረባቸው ሪፖርቶች የሚሰጠውን መመሪያ ተከትሎ አገልግሎቱን እያከናወነ ኻያ ሦስተኛ ዓመቱን ማስቆጠሩን በደብዳቤው ተመልክቷል፡፡

ማኅበሩ ‹‹እንኳን የራሱን የሒሳብ አያያዝ የቤተ ክርስቲያንዋ የሒሳብ አሠራር በሙሉ ዘመናዊና ለኦዲት የሚመች እንዲኾን የሚያግዝ ነው፤›› ያለው ደብዳቤው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ዘመናዊና የኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት(double entry accounting system) የሚከተል በመኾኑ የቤተ ክህነቱን የነጠላ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት ለመከተል እንደተቸገረ አልሸሸገም፡፡ ይኹንና የቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት ባስፈለገው ጊዜ ማኅበሩ በውስጥ ይኹን በውጭ ኦዲተር ያስመረመረውን ሒሳብ ማየት፣ በአካልም ተገኝቶ ማረጋገጥ እንደሚችል ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ማስታወቁን አውስቷል፡፡ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ወዶ ፈቅዶ አባቶችን ለማገልገል፣ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በፈቃደኝነት ለመደገፍ የተቋቋመ በመኾኑ የመታዘዝ ይኹን በሞያ የተደገፍ የሒሳብ አያያዝ የመተግበር ችግር የለበትም፤›› በማለት ለመዋቅሩ ያለውን ታማኝነት አጽንቷል፡፡

ማኅበሩ ‹‹ከምእመናን የዐሥራት በኵራት ገቢ ይሰበስባል›› በሚል በስብሰባው ላይ የተሰነዘረበትን ‹‹ስም ማጥፋት›› ፍጹም ሐሰት በማለት አጣጥሎታል፡፡ በሰጠው ምላሽም ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱን የሚያከናውነው ከአባላቱ ገቢ በሚሰበስበው የኹለት በመቶ ወርኃዊ አስተዋፅኦ እንደኾነ፣ ለቅዱሳት መካናትና ለስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራሞች ደግሞ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ከገባሬ ሠናይ ምእመናን ድጋፍ እንደሚያፈላልግ ገልጧል፡፡ አገልግሎቱ የበጎ ፈቃድና የትሩፋት መኾኑን በተደጋጋሚ የገለጸው ማኅበሩ፣ ከአባላቱ የሚሰበሰበው የኹለት በመቶ ወርኃዊ አስተዋፅኦ፣ እያንዳንዳቸው ለየሰበካቸው የሚጠበቅባቸውን ዐሥራት ወይም የሰበካ ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ የሚያበረክቱት እንደኾነ አረጋግጧል፡፡

Mahibere Kidusan head office

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ሕንፃ

ማኅበሩ ረብ የለሽ ሲል ውድቅ ካደረጋቸው የአንዳንድ ተሰብሳቢዎች ክሦች ውስጥ፣ ግንባታውን የተጠናቀቀውንና የሚገለገልበትን የጽ/ቤት ሕንፃ የሚመለከት ይገኝበታል፡፡ ሕንፃው ያረፈበት ቦታ የተገዛው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የወቅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሰጡት ውክልና መኾኑን ማኅበሩ በደብዳቤው ገልጦ÷ አባላቱ የወር ደመወዛቸውን በተደጋጋሚ በማዋጣት የገነቡትን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ስም በሕግ ተመዝግቦ የሚገኘውንና በማኅበሩ የሒሳብ ሪፖርትም በቋሚ ንብረትነት ተይዞ በየወቅቱ የሚገለጸውን ሕንፃ አመራሩ ይኹን አባላቱ የመጠበቅና የመገልገል እንጂ ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ የመስጠት ይኹን የመሸጥ ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቋል፡፡

በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀውና እየተመራበት በሚገኘው መተዳደርያ ደንቡ መሠረት፣ ማኅበሩ በማንኛውም የፖሊቲካ አመለካከት ጣልቃ እንደማይገባና አገልግሎቱ ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ እንዳልኾነ አረጋግጦ፣ ማኅበሩ የፖሊቲካ ዓላማ እንዳለው ለተሰነዘረው ውንጀላ መረጃው ቀርቦ በሚመለከተው አካል ሊታይና ሊጣራ እየቻለ የማይመለከታቸው አካላት ከሜዳ ተነሥተው ስም ለማጥፋት ሊጠቀሙበት እንደማይገባ አሳስቧል፡፡ ማኅበሩ ‹‹አክራሪ ነው፤ አሸባሪ ነው›› ማለትም ‹‹ውንጀላን ከማዳመቅ ያላለፈ ፋይዳ የሌለው መሠረተ ቢስ ክሥ ነው፤›› ብሏል፡፡

ማንም ግለሰብ ይኹን ኅብረተሰብ የፈለገውን እምነት ሊከተል እንደሚችል እምነቱ እንዳለውና የማንንም ሰብአዊና ሕገ መንግሥታዊ መብት እንደማይነካ በአጽንዖት የገለጸው ማኅበሩ፣ ማንም የራሱን እምነት ከማራመድ አልፎ በሌላው እምነት ጣልቃ መግባት ስለሌለበት፣ ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ጣልቃ ገብተው የሚያውኩትን የተሐድሶ መናፍቃን የመከላከልና ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ተልእኮዬን አጠናክሬ እቀጥላለኹ፤›› ብሏል፤ ‹‹እናቱን አውሬ ሲበላት ቆሞ የሚሥቅ ልጅ የለም›› ሲልም አቋሙን አስረግጧል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተጣለባቸው ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊነትና አባትነት በማኅበሩ ላይ የሚካሔደውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በአጽንዖትና በተረጋጋ መንፈስ እንዲመለከቱ ማኅበረ ቅዱሳን በአቤቱታው ተማፅኗል፡፡ ግለሰቦቹን በሕግ ለመጠየቅ ሊገደድ እንደሚችል ያስታወቀው ማኅበሩ፣ ‹‹አስነዋሪና የቤተ ክርስቲያን ነን ከሚሉ አካላት የማይጠበቅ ነው›› ያለው ድርጊት ‹‹በቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን በፈቃዳችን ገንዘባችንን፣ ጉልበታችንንና ጊዜአችንን አስተባብረን የምናደርገውን ነፃና የፈቃድ አገልግሎት መብታችንን የሚፃረር ነው፤›› ሲል አስገንዝቧል፡፡ ኹኔታው በተመሳሳይ መልኩ ከቀጠለ÷ ቤተ ክርስቲያንን እርስ በርሷ የማትናበብ፣ ማእከላዊ አሠራር የሌላት የሚያስመስልና ለአገልግሎቷ ዕንቅፋት የሚፈጥር በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን በጥንቃቄ መርምሮና አጣርቶ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠይቋል፡፡

Advertisements

51 thoughts on “ማኅበረ ቅዱሳን: ፓትርያርኩ በመሯቸው ስብሰባዎች በሚካሔድበት የስም ማጥፋት ዘመቻ ቅሬታውን ገለጸ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጠው ጠየቀ

 1. Daniel October 16, 2014 at 6:47 am Reply

  ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ጣልቃ ገብተው የሚያውኩትን የተሐድሶ መናፍቃን የመከላከልና ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ተልእኮዬን አጠናክሬ እቀጥላለኹ፤›› ብሏል፤ ‹‹እናቱን አውሬ ሲበላት ቆሞ የሚሥቅ ልጅ የለም››
  ….
  ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተጣለባቸው ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊነትና አባትነት በማኅበሩ ላይ የሚካሔደውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በአጽንዖትና በተረጋጋ መንፈስ እንዲመለከቱ

  • Anonymous October 16, 2014 at 9:27 am Reply

   Egzabhar amlake ferdun yestachew

 2. Anonymous October 16, 2014 at 7:06 am Reply

  ከ400 በላይ ቅጥረኛ ሠራተኛ ይዞ በጎ ፈቃደኛ በነፃ አገልጋይ ማለት፣
  ከ65 በላይ የንግድ ድርጅት ከፍቶ ቅን፣ አሳቢ ተቆርቋሪ አገልገጋይ፣
  ከሚሊየኖች ገንዘብ በነጭ ወረቀት እየተቀበለ እና እየነገደ ሕግ አክባሪ በሲኖዶስ ሕግ ተዳዳሪ የሑሳብ ስሌት አዋቂ መሳይ
  ሊቃውንትንና እና አባቶችን እያሳደደ ተሳዳጅ መሳይ
  ስንቱን ሊቀጳጳስ ሲዘልፍ፣ ስንቱ አገልጋይ ሲሰድብ ቆይቶ ተሰደብኩ ማለት

  የምን ቀልድ

  የተሳደዱት፣ የተሰደቡት፣ የተነገደባቸው፣ እነማን እንደሆኑ አላወቀም

  • Anonymous October 16, 2014 at 7:00 pm Reply

   Who are you? You must be among corrupt priests or tehadiso or politically motivated group.am sure you will not undetstand all i am talking right now.your idea shows me how illerate you are.

  • Anonymous October 17, 2014 at 3:05 am Reply

   Egiziabiher amilak yikir yibelih

  • Anonymous October 17, 2014 at 9:15 am Reply

   አዎ በርግጥም አታውቅም:: ማወቅ ካለብህ እወቅ ባታውቀውም ግን ያንተ ጩኸት ከሩጫችን ሊገታን አይችለም::‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ጣልቃ ገብተው የሚያውኩትን የተሐድሶ መናፍቃን የመከላከልና ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ተልእኮዬን አጠናክሬ እቀጥላለኹ፤›› ብሏል፤ ‹‹እናቱን አውሬ ሲበላት ቆሞ የሚሥቅ ልጅ የለም›› :: ደስ የሚለው ነገር ግን የእውነተኛነት ማረጋገጫ የሆኑት ፈተናዎች በየጊዜው መጉረፋቸው ነው:: መልካም ይህን የምንቋቋምበት ደግሞ ሰማያዊ ኃይል አለን:: ወገኖቸ የሆናችሁ የማህበሩ አባላት ሆይ በዚህ ልንደሰት ይገባናልና ደስ ይበላችሁ:: ፈተናዎችን የምናልፍባቸውን መንገዶች ደግሞ በጋራ እንወያያለን ባለቤቱ ደግሞ ይመራናል “ሠለስቱ ምዕትን እንደረዳ” ይረዳናልና አትናደዱ አትጨነቁ ይህ ሰማያዊ ማህበር ነውና::

 3. Anonymous October 16, 2014 at 7:20 am Reply

  ወቅቱ የቤተክርስቲያን ጠላት የሆነው ዲያብሎስ ጥርሱን ያሾለበት በመሆኑ ሁላችንም በፀሎት እንትጋ

 4. Tiruwork Abera October 16, 2014 at 7:57 am Reply

  ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ጣልቃ ገብተው የሚያውኩትን የተሐድሶ መናፍቃን የመከላከልና ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ተልእኮዬን አጠናክሬ እቀጥላለኹ፤›› ብሏል፤ ‹‹እናቱን አውሬ ሲበላት ቆሞ የሚሥቅ ልጅ የለም›› ትልቅ አቋም ነው እውነትም ነው ለቤተክርስቲያን ያለችኋት የቤተክርስቲያን ምርጥ ልጆች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን በተረፈ ፀልዩ ለእነሱም እግዚአብሔር ማስተዋልና ልቦና ይስጣቸው አእምሯቸውን እንዲያውቁ ያድርግላቸው!!!

  • Anonymous November 21, 2014 at 7:57 am Reply

   Egzibaher asitewayi libi yisitachewu ayine libonachewuni yabiralachewu

 5. benti October 16, 2014 at 8:53 am Reply

  ከ400 በላይ ቅጥረኛ ሠራተኛ ይዞ በጎ ፈቃደኛ በነፃ አገልጋይ ማለት፣
  ከ65 በላይ የንግድ ድርጅት ከፍቶ ቅን፣ አሳቢ ተቆርቋሪ አገልገጋይ፣
  ከሚሊየኖች ገንዘብ በነጭ ወረቀት እየተቀበለ እና እየነገደ ሕግ አክባሪ በሲኖዶስ ሕግ ተዳዳሪ የሑሳብ ስሌት አዋቂ መሳይ
  ሊቃውንትንና እና አባቶችን እያሳደደ ተሳዳጅ መሳይ
  ስንቱን ሊቀጳጳስ ሲዘልፍ፣ ስንቱ አገልጋይ ሲሰድብ ቆይቶ ተሰደብኩ ማለት

  • Anonymous October 25, 2014 at 6:07 pm Reply

   ke ebab enqulal ergib ayfelefelim . yegahaneb dej. atilfa woym atlifi aysakam

 6. Anonymous October 16, 2014 at 9:28 am Reply

  Egzabhar amlake ferdun yestachew

 7. Anonymous October 16, 2014 at 9:28 am Reply

  እኛ አባታችንን በጥሞና በትህትና እንጠይቃልን፡፡ብጽዕ አባታችን የጥሞና ጊዜ ወስደው እየተናገሩት ያለውንና በቤተ ክርስቲያን ላይ ሊያደርሰ የሚችሉትን አደጋ እንዲያስቡበት እንፈልጋልን፡፡ ዘመኑም እርሳቸውም ያልፋሉ ነገር ግን መጪው ትውልድ የተጎሳቆለች ቤተ ክርስቲያን ሊያስረክቡት አይገባም፡፡ መሳሳት በዕርሳቸው አልተጀመረም መመለስ ግን ታላቅነት ነው፡፡ እኛ አባታችንን በጥሞና በትህትና እንጠይቃልን፡፡

 8. Anonymous October 16, 2014 at 9:59 am Reply

  አገልግሎታችሁ ሰማዊ ነዉና ይችን ቤተክርስቲያን በንጹህ ልቡ እግዚአብሄርንም በፍጹም የሚያመልክ ሁሉ ከናንተ ጋር ነዉ፤ አገልግሎታችሁ ከዘር፤ ከአክራሪነት፤ ከኃይል የጸዳ፤ የሩቅ አላማችሁ በሃይማኖትና ምግባር የታነጸ መልካም የኢትዮጵያና የሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም ዜጋ መፍጠር ነዉና የገዥዎች ገዥ፤ የንጉሶች ንጉስ፤ ለኃይለኞችም ኃልን የሚሰጥ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ነዉና ጽኑ እስከ ሞት ድረስ የታመናችሁ ሁኑ ተብለናልና፡፡ አዲስ ነገር የለም ይህ ሊሆን ግድ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር የገዥዎቻችንን አይነልቢና ያብራልን፤ አስተዋይ ልቦናም ይስጥልን፤ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንንም ያስታግስልን፡፡ እግዚብሔርኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

 9. Anonymous October 16, 2014 at 10:45 am Reply

  “ከጭናክሰን/ጅግጅጋ እስከ አዲስ አበባ በማፊያ ምግባሩ የታወቀው የአማሳኞች ፊታውራሪ ወሮበላው ዘካርያስ ሓዲስ” realy? yihe new kirstiyanawi anegager? besintu enzen be Egziabher!

  • Anonymous October 16, 2014 at 2:19 pm Reply

   you’re right bro. I support MK but these are the words that kill their good will. Please be respectful for church Fathers. You can’t tell/ask others to respect while you’re defaming Church fathers.

 10. Anonymous October 16, 2014 at 11:28 am Reply

  ማኅበረ ቅዱሳን በ2006 ዓ.ም ከ13,948,984.71 በላይ ወጪ በማድረግ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ደገፈ አትም ኢሜይል

  ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም.

  መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

  በ33ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ባቀረቡት ሪፖርትና በዐዋጅ ነጋሪ መጽሔት 6ኛ ዓመት ቁጥር 10 ጥቅምት 2007 ዓ.ም ላይ በተገለጸው ሪፖርት ውስጥ የማኅበረ ቅዱሳን የ2006 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ከነጻ ሞያ አገልግሎት ውጭ ከ13,948.984.7 /አሥራ ሦስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዐርባ ስምንት ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ዐራት ብር/ በላይ ወጪ በማድረግ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት መደገፉ ተገልጿል፡፡

  ዋና ዋና ድጋፍ ያደረገባቸው ሀገረ ስብከቶች

  ማኅበረ ቅዱሳን በበጀት ዓመቱ ለደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ለምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት፣ ለደብረ ከዋክብት ጉንዳጉንዶ ገዳም፣ ለሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ አቡነ ቶማስ ገዳም ለውኃ ታንከር፣ ለዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ለምዕመናን መቀመጫ ወንበር ለመግዛት ብር 8,139,847.36 /ስምንት ሚሊዮን አንድ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሺሕ ስምንት መቶ ዐርባ ሰባ ብር ከሠላሳ ዘጠኝ ሣንቲም ወጪ በማድረግ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ደግፏል፡፡

  በተጨማሪም በተለያዩ አህጉረ ስብከት ለሚገነቡ የአብነት ት/ቤቶችና የካህናት ማሠልጠኛዎች እንዲሁም ለአብነት መምህራንና ተማሪዎች ድጎማና አህጉረ ስብከት ለሚያካሒዷቸው ሥልጠናዎች መደጎሚያ፣ ለምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ግንባታ ብር 11,034,334.00/ አሥራ አንድ ሚሊየን ሠላሳ ዐራት ሺሕ ሦስት መቶ ሠላሳ አራት ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

  ማኅበሩ በሙያ ደረጃ ለ35 አብያተ ክርስቲያናት የዲዛይን ሥራ ከተለያዩ አህጉረ ስብከት ለመጡ 15 የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች የነጻ የሕግ ምክር አገልግሎት የሰጠ ሲሆን ከተለያዩ አህጉረ ስብከት ለተጠየቀ 10 የልማት ሥራዎች ፕሮጀክት ጥናት በነጻ ተጠንቶ ለጠያቂዎቹ ተሰጥቷል፡፡ በኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ አውታሮች አማካኝነት በሀገር ውስጥና በውጭው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ሰፊ ትምህርት የሰጠ ሲሆን 671,000.00 /ስድስት መቶ ሰባ አንድ ሺሕ/ ሐመርና ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በበጀት ዓመቱ አሰራጭቷል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም በአማርኛ፣ በእንግሊዘኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች በድረ ገጽ ትምህርታዊ ዝግጅቶች እንዲተላለፉ አድርጓል፡፡

  ማኅበሩ በበጀት ዓመቱ በ341 የመንግሥትና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚገኙ 200,000 /ሁለት መቶ ሺሕ/ ኦርቶዶክሳዊ ተማሪዎች ተከታታይ ኮርስ ሰጥቷቸዋል፡፡ በ226 በጀት ዓመትም 14,847,657.82 /አሥራ አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ ሰባ ሺሕ ስድስት መቶ ሃምሳ ሰባ ብር ከሰማንያ አራት ብር ከሰባ አንድ ሣንቲም ወጪ በማድረግ 848,675.11/ ስምንት መቶ አርባ ስምንት ሺሕ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ብር ከአሥራ አንድ ሣንቲም/ በልዩነት ተመዝግቧል፡፡

  ማኅበረ ቅዱሳን

  የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ሁለገብ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት በብር 4,599,645.00 /አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺሕ ስድስት መቶ ዐርባ አምስት ብር/ ወጪ እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡

  የደብረ ካስዋ ጉንዳጉንዶ ገዳም ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ዓዲግራት ከተላ ላይ በብር 2,614,431.36 /ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ አሥራ ዐራት ሺሕ ዐራት መቶ ሠላሳ አንድ ብር ከሰላሣ ስድስት ሣንቲም/ እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡

  ሰሜን ምዕራብ ትግራይ /ሽሬ/ አቡነ ቶማስ ገዳም 150 ሺሕ ሊትር ውኃ መያዝ የሚችል ውኃ ታንከር በብር 672,822.00 /ስድስት መቶ ሰባ ሁለት ሺሕ ስምንት መቶ ሃያ ሁለት ብር/ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

  ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የሞጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን 64 ተማሪዎችን መቀበልና ማስተናገድ የሚችል የአብነት ትምህርት መማሪያ እና ማደሪያ ከነሙሉ መገልገያው በብር 2,950,380.00 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሺሕ ሦስት መቶ ሰማንያ ብር/ ተሠርቶ እና ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

  በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት አርባ ምንጭ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን 100 ተማሪዎችን መቀበልና እና መያዝ የሚችል ማሰልጠኛ በብር 1,666,378.00 /አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ሺሕ ሦስት መቶ ሰባ ስምንት ብር/ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

  ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በጎንደር በዓታ የአቋቋም ትምህርት ቤት በብር 5,981,132.00 /አምስት ሚሊዮን ብር/ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

  በተለያዩ አህጉረ ስብከት 160 የአብነት ት/ቤቶች ለሚገኙ 171 የአብነት መምህራን እና 993 የአብነት ተማሪዎች ከ1,800,000.00 /አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሺሕ ብር/ በላይ ወጪ ለማዳን ድጎማ ተደርጓል፡፡

  ከተለያዩ አህጉረ ስብከት ለተጠየቁ የ35 አብያተ ክርስቲያናት የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ዲዛይን ሥራ በነጻ በመሥራት አብያተ ክርስቲያናቱ ሊያወጡ የነበረው ብር 840,000.00 /ስምንት መቶ ዐርባ ሺሕ ብር/ ወጪን ለማዳን ተችሏል፡፡

  ሀገር ውስጥ ባሉ የተለያዩ አህጉረ ስብከት ከ150 በላይ የሕዝብ ጉባኤያት እና በሰሜን አሜሪካ 5 የስብከተ ወንጌል ጉባኤያት ተደርጎ በርካታ ምእመናን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲያገኙ ሆኗል፡፡

  ከሚመለከታቸው አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ፈቃድና ከየአህጉረ ስብከት ጋር በመተባበር ለ10 ቀናት የቆየ ሐዋርያዊ ጉዞ ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ /አፋር፣ ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ድሬዳዋ እና ሶማሌ አህጉረ ስብከት/ ተደርጓል፡፡

  ስብከተ ወንጌል ያልተስፋፋባቸውን ጠረፋማ አካባቢዎች በመለየት እና ፕሮጀክት በመቅረጽ ስብከተ ወንጌል የማስፋፋት ሥራዎች እየተሠሩ ሲሆን በተሰጠው አገልግሎት ከአህጉረ ስብከት ጋር በመተባበር 4396 ምእመናን ተጠምቀው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ለመሆን በቅተዋል፡፡

  በሀገሪቱ ባሉት የመንግሥትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ላሉ ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ትውፊትና ነገረ ሃይማኖት ለማወቅ የሚያስችላቸውንና በሥራ ሲሠማሩ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል መነሻ የሚሆናቸውን ትምህርት በካሪኩለም በማካተት ተከታታይነት ያለው የኮርስ ትምህርት ተሰጥቷቸዋል፡

  • Anonymous October 16, 2014 at 12:41 pm Reply

   እግዚአብሔር ስራችሁ ይባርክ!!!

 11. hayeda21@gmail.com October 16, 2014 at 1:23 pm Reply

  mahibere kudusan always fight with church corrupter

 12. Anonymous October 16, 2014 at 1:48 pm Reply

  Egziabher amlak aglglotachihun yasfalachhu

 13. Senait Admasu October 16, 2014 at 3:17 pm Reply

  lemin min tesera bilen anayim?keminsadeb

 14. Adamu October 16, 2014 at 4:41 pm Reply

  እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን
  በሰማይ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ

 15. Anonymous October 16, 2014 at 4:59 pm Reply

  የማህበረ- ቅዱሳነን ስራ የተቀደሰ ነው ፣እግዚአብሄር ይጠብቅልን፡፡

 16. Girmachew October 17, 2014 at 1:09 am Reply

  Questions:
  1. are all this projects done by MK from the planing to execution including financing?
  2.if the answer for the above question is yes, Where is all this Money coming from?
  3. and in fact if MK is doing all this, isn’t it beyond its mandate to spend the church’s money to its preference and pushing the church’s administration aside?

  • Tershome October 17, 2014 at 8:24 pm Reply

   one thing u have to know is that MK has got the mandate from the Holy Synod. The source of the money is 2% contribution from its members and fund raising. Every spiritual associations do the same, i mean, they collect contributions. MK is not misusing the money rather the members even pay extra money voluntarily from their pocket. Please guys, don’t blame without knowing MK. You can come and see anytime. May God Bless MK and protect our church from protesters.

   • Anonymous October 25, 2014 at 6:19 pm

    ye guys do you know what you are talking about ? the money is not from the church it is from its members, i you from those who are embezzling the church’s money. your question is controversial. MK has done allot than what the churches does. question for you. do you love your country, your identity, your culture, and do you hate sin, corruption. this is the quality of all members of MK. If you don’t have and want to have all such come and become a member. God bless you.

 17. Arbagashaw Maru October 17, 2014 at 2:02 am Reply

  ቅድስት ድንግል ማሪያም ሆይ፡ ማህበረ ቅዱሳንን ጠብቂልን በምልጃሽ፡፡

 18. Anonymous October 17, 2014 at 6:16 am Reply

  Benti ena anonymous, ye mahibere kidusan neger selalegebachu ebakachu kereb belacheu lemeredat mokeru. Alemawok tefate ayedelem. Be alamam lemehed mawok yebejal.

 19. Anonymous October 17, 2014 at 6:50 am Reply

  እኛም አባታችንን በጥሞና በትህትና እንጠይቃልን፡፡ብጽዕ አባታችን የጥሞና ጊዜ ወስደው እየተናገሩት ያለውንና በቤተ ክርስቲያን ላይ ሊያደርሰ የሚችሉትን አደጋ እንዲያስቡበት እንፈልጋልን፡፡ ዘመኑም እርሳቸውም ያልፋሉ ነገር ግን መጪው ትውልድ የተጎሳቆለች ቤተ ክርስቲያን ሊያስረክቡት አይገባም፡፡ መሳሳት በዕርሳቸው አልተጀመረም መመለስ ግን ታላቅነት ነው፡፡ እኛ አባታችንን በጥሞና በትህትና እንጠይቃልን፡፡

 20. Anonymous October 17, 2014 at 8:06 am Reply

  Amlakachin kidus Egziabher yih agelgilot brasu yemeseretew silhone zim aylim.ytehadso menafikan werea ewnetun ygeletal

 21. Anonymous October 17, 2014 at 9:23 am Reply

  ተኩላን ካላባረሩት ውሻን ካልከለከሉት መንከሱን አይተውምና በርቱና ለቤተክርስቲያን ቁሙላት፣ማህበረ ቅዱሳን ባይኖር ወጣቱ የት ነበር?

 22. Anonymous October 17, 2014 at 9:57 am Reply

  Every thing is for good

 23. Anonymous October 17, 2014 at 12:51 pm Reply

  EOTC MK Yebetekirsitian Alegnita Mahiberachin Beljinetu Tamagn New .
  Bezih Aliteraterim.Amasagnoch lemasiredat Simokiru Be Kefaw Andebetachew Mehunu Yetereda
  new

 24. Anonymous October 17, 2014 at 12:52 pm Reply

  I know who is Mk No more talk.

 25. unkown October 17, 2014 at 12:57 pm Reply

  We know who are The corrupted none No more talk I know My MK

 26. Anonymous October 17, 2014 at 1:02 pm Reply

  የማህበረ- ቅዱሳን ስራ የተቀደሰ ነው ፣እግዚአብሄር ይጠብቅልን፡፡

 27. Anonymous October 17, 2014 at 3:57 pm Reply

  ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ…

  Share share share በማዱረግ መልክቱን እናስተላልፍ!!!!!
  ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ…፣ እንዲህ ቢሆንበት…፣ እንዲህ ቢደረግበት…፣ እያሉ ክፉ ክፉውን የሚመኙ፣ መፍረሱን የሚወዱ፣… ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይህን አካሄድ ለምን? ብለን እንድንጠራጠርና እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡

  ከዚህ በፊት በ2014 September ወር መጀመሪያ ላይ በእኛ ነሐሴ/2006 ዓ.ም መናፍቁ Addisalem Biruk፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ስሙን እንኳ እንደማይወደው በሚያመለክት ቃል፣ “ርኩሳን” ብሎ እየጠራ፤ ስለ ፓትርያርኩ ሲናገር፡-

  Addisalem Biruk፡- `…yegbriel seyf papsum be geta nachew mahbere rekusan awegzawal abytogawa zerfe kebde tezetaw anbesa begashaw ere sentu tensh betetages (Orthodoxin) enwersatalen yehe “mehbr” tensh enkfat hone enji` ማለቱን አስታውሳለሁ፡፡

  “እንቅፋት ሆነን እንጂ” የሚለውን ያዙልኝ፡፡

  ከዚህም በተጨማሪ መስከረም 27/2007 ዓ.ም ድረስ ተሰብስበው በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ሲያሴሩ የተገኙት፡፡ ከፓትርያርኩ ጋር ስለተሰበሰቡት የተሐድሶ አራማጆች አስቀደሞ የተሰጠው መረጃ ደግሞ እንዲህ ይል ነበር፡፡ ይህ መረጃ የተገኘው ከሙሉ ወንጌል አማኝ ከሆነች ሴት ሲሆን እንዲህ ብላ ነበር፡-

  “አንድ ከፍተኛ ሚስጥር … የኦርቶዶክስን ትልልቅ ስፍራ የያዙት ስብከተ ወንጌል ሃላፊዎችና ቅዱሳን አባቶች … ብትከሰሱም እኔ ጋ ነው የሚያመጡአችሁ ይላሉ፡፡. ወንጌል ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሮአል፡፡ ጨዋታው በናንተው ሜዳ ነው” ያለችው ተጠቃሽ ነው፡፡

  ከዚህ መረጃ ደግሞ፡-

  1. “ብትከሰሱም እኔ ጋ ነው የሚያመጡአችሁ” የሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ፡- ጳጳስ ወይም ፓትርያርክ እንደሚሆን ይገመታል፤
  2. “ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሮአል” የሚለው የልብ ልብ፣ ፕሮቴስታንቱ እያጠቃናችሁ ነው ማለታቸውን አመላካች ሲሆን፤
  3. “ጨዋታው በናንተው ሜዳ ነው” የሚለውን ስንመለከት እውነትም አሁን ደርሶብናል፣ እየተጫወቱብን ነው እንድል ያደርጋል፡፡

  እንድታስተውሉ የምፈልገው ይህንን ያሉት በተደጋጋሚ እንደሚናገሩት “ሙሉ ወንጌል ኑና ተሳተፉ” የሚሉ ስለሆኑ፤ ፕሮቴስታንት አስታጥቆ የላካቸው መሆኑን ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ፓትርያርኩ ይህንን ጉዳይ ሳያውቁ
  ማኅበሩ ይጥፋ…
  ማኅበሩ ይፍረስ…
  ማኅበሩ ይታገድ…ለሚላቸው የፕሮቴስታንት ሠራዊት ማንነት ሳያጠኑ እውነት ነው፣ አሸባሪ ነው፣ አሥራት በኩራት ይሰበስባል፣ ….ወዘተ ብለው ስለከሰሱአቸው፤ ቆብ አድርገዋልና ልጆቼ ናቸው፣ መስቀል ይዘዋልና ፕሮቴስታንት አይደሉም፤ ብለው ከሆነ፣ ያልጠበቁት እየተደረገ ነው፡፡ አውቀውም ከሆነ ከላይ የተላከ ስውር ጥይት እየተተኮሰብን፤ በግድ ተቀበሉ በማለት ተገድደን እየተደፈርን ነውና ውጊያው ከሕዝበ እግዚአብሔር ጋር ነው፡፡

  ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የመሰለው አንድ ምሳሌ ለዚህ ይስማማል፡-

  “ጥይት የመታው ሰው ተናድዶ፡- “ምነው እንዲህ ታበላሸኝ” ቢለው፤

  “እባክህ እኔ አይደለሁም፣ እኔ ተተኮስኩ እንጂ ተኳሹ ሌላ ነው፤ እኔ መልክተኛ ነኝ” አለው፡፡

  “ተኳሹ የት አለ?” ቢለው፤

  “እርሱማ አይታይም ተደብቆ ነው የሚተኩሰው፤ እርሱ ስለሚደበቅኮ ነው እኔ የመጣሁት” አለው ይባላል፡፡”

  አሁንም ፕሮቴስታንት ኃይልንና ሥልጣንን ተጠቀመው፤ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክህደታቸውን ለማስገባት፤ ጊዜው የእኛ፣ ባለጊዜ እኛ ነን፤ ቤተ ክርስቲያናችሁን፣ ቅርሳችሁን፣ ታሪካችሁን፣ …እንወርሳለን፡፡ ቅዳሴያችሁን በኪፖርድ ዘፈን ተክተን እንግታችኋለን፤ በዐውደ ምኅረታችሁ ቅዱሳንን ስናቃልላቸው ሳትወዱ በግዳችሁ ትሰሙናላችሁ፣ የወልቂጤው አገር እና የአዲስ አበባው የቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ አይበቃንም ሁሉንም እንይዛለን፣ በማለት ውጊያ ቢጀምሩ የማያቋርጥ እምባና ደም ይፈሳል፡፡

  ምሥጢሩ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት፣ የሒሳብን ሕግ የተማሩ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት የበሰሉ፣ ለዲቁና ለቅስና ማዕረግ የደረሱ፣ ቤተ ክርስቲያንዋን የመምራት አቅምን ለአባቶች እንደ ልጅነታቸው አሳብ የሚያቀርቡ ስለሆኑ፣ ለቤተ ክርስቲያንን እንደ እንጀራ ልጅ ከሩቅ ቆመው ሳይሆን፤ ቀርበው “አባቴ ከእርስዎ በላይ አላውቅም…እንዲህ ቢያደርጉ” እያሉ ዘመናዊ አካሄድን በቤተ ክርስቲያን የሚያሳዩ፤ እንዲሁም እንደ አማኝነታቸው በሰበካ ጉባኤ እና በሰ/ት/ቤቶች ታቅፈው፡- የፕሮቴስታንት ቅጥረኞችን ተከታትለው በፊልም ቀርጸው፣ ይሄ የተሐድሶ አባል ነው በማለት ለአባቶች ስለሚያጋልጡአቸው፤ የተሐድሶ ተኩላዎች፣ ሙዳየ ምጽዋቱን ሊመዘብሩ ሲሉ፤ ቁጥጥር ይደረግበት፣ ይህ አካሄድ ለሌብነት የተመቸ ነውና ይስተካከል፣…ወዘተ በማለት ስሕተት ስለሚያርሙ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ይፍረስ፣ በየሰበካ ጉባኤ ተሰግስገው እያወኩን ነውና ይውጡ፣… ማለትን እንደአማራጭ ይዘውት ሰምተናቸዋል፡፡

  ሌባ ሲሰርቅ የሚያየውን ይወዳል ብሎ ማመን ሞኝነት ነው፡፡

  ይሁን ተብሎ ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ…

  1. አባላቱ አይፈርሱም

  የተሐድሶ ለምድ ለብሰው ካህን መስለው ከፓትርያርኩ ጋር የተሰበሰቡት፣ ያላወቁት ወይም ልብ ያላሉት አንድ ነገር አለ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ከቤተ ክህነት ከፍ ብሎ ያለው ፎቅ ማለት አይደለም፣ የክርስቶስ ሕንፃ የሆኑ አማኝ ምእመናኑ ናቸው፡፡

  እነዚህ የማኅበሩ አባላት ሁሉ፡-

  በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሁሉ የሚገኙ፣
  የሰበካ ጉባኤ አባላት ሆነው የተመዘገቡ፣
  በየአቅጣጫው የተቋቋሙ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሁሉ አባል ሆነዋል፡፡

  ስለዚህ የተሐድሶ ተኩላዎች፣ ገንዘብ የሚገኝበትን ሕንፃ ቢረከቡ፣ ወይም ዶክመንቱን ሁሉ ሰብስበው ቢያቃጥሉ፣ የእግዚአብሔር ሕንፃ ምእመናኑን፣ ማለትም የማኀበረ ቅዱሳን አባል የነበሩትን፣ የክርስቶስ ልጆች ሰውነትን መረከብና ማፍረስ አይችሉም፡፡

  የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በአገሪቱ ሁሉ ባሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ታቅፈው፣ በየሰበካ ጉባኤያቱ ተመዝግበው፣ ወርኃዊ መዋጮም እየከፈሉ፣ በደረሰኝ ይሁን በማለት አሥራት በኩራትን በመክፈል ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ ናቸው፡፡

  ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ስላሉ፣ በየትኛውም ጉባኤ ያለውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ እንደገና መቅረጽ ይችላሉ፣ ለሕዝቡ ግንዛቤ መስጠት ይችላሉ፣ ሙዳየ ምጽዋቱን ሊዘረፍ ሲል፣ አጠገብ ናቸውና ይጮሃሉ፣ ተዘረፍክ ብለው ሌባን ይከላከላሉ፣ ንዋያተ ቅድሳትን ሊያቃጥሉ ቢሹ ሳይቃጠል በቅጠል…፣ የፕሮቴስታንት ስብከት ሲሰበክ የተቃውሞ ድምጽ በማሰማት ውጊያውን ይጀምራሉ፤ ….

  ስለዚህ የተሐድሶ መናፍቃን አይሆንላቸውም እንጂ፤ ቢሆን የተረከቡት አምስት ኪሎ ያለውን ሕንፃና ሊዘርፉት የፈለጉትን ገንዘብ እንጂ፣ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆኑትን አባላቱን መረከብና ማፍረስ አይችሉም አገልግሎታቸውን በየሰንበት ትምህርት ቤቱ ይቀጥላሉ፡፡

  ወይስ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን እና ሰበካ ጉባኤያቱን ሁሉ ልታፈርሱ ትችላላችሁን? ሁከት ካልፈለጋችሁ በቀር ይህንን ማድረግ አትችሉም፡፡

  አይሳካም እንጂ ሲኖዶሱ ይፍረስ ብሎ ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ…

  2. ሰ/ት/ቤቶች ውስጥ ያለው ሥራ አይፈርስም፡፡

  ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ እኔ ባለሁበት ሰ/ት/ቤት ብዙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት አሉ፡፡ እኒህ የዩኒቨርስቲ፣ የኮሌጅ፣ እና የሙያ ማሰልጠኛዎች ውስጥ ታቅፈው የተማሩ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች የነበሩ ሲሆኑ፣ ኋላም ሲመረቁ፣ የማኅበረ ቅዱሳንን ዋናውን ዓላማ በሰ/ት/ቤቶች ታቅፎ ማገልገልና ማጠናከር ስለሆነ፣ የአባልነት መዋጮ ለሰ/ት/ቤቶቹ ከሚያገኙት ደመወዝ በመክፈል፣ በጉልበት በመርዳት እና በሰ/ት/ቤቱ ውስጥ ያሉትንም ሕፃናትን በዓለማዊ ትምህርታቸው እንዳይጎዱ በማስጠናት አገልግሎታቸውን ይወጣሉ፡፡

  አይደረግም እንጂ የተሐድሶ ባለሥልጣናት፣ ሰ/ት/ቤት ውስጥ ያሉትንም የሚያባርሩ ከሆነ፣ ጠቡ ያን ጊዜ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ገንዘብ እንጂ እኛን በስብከት መርዳት አይሹም፣ ተሐድሶዎች ሕንፃ በሚከራይባቸው ቦታዎች ተመድበው፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን መቦጥቦጥ እንጂ ሰ/ት/ቤቶች ውስጥ ገብተው ሕፃናትን አይደግፉም፣ ሰ/ት/ቤቱ ውስጥ ገንዘብ ተሰብስቦአል ከተባሉ ደግሞ፣ ግማሹን አምጡ በማለት የማይደረግ ነው ቢሏቸው እናሽገዋለን ለአባት አትታዘዙምና በሚል የሚያውኩ መሆናቸው ገሃድ የወጣ ጉዳይ ነው፣ ብር የደም ሥር ነው ለእነርሱ፣ ለመስቀል በዓል እንኳ ትርኢት ልናሳይ ገንዘብ እንዲረዱን ቢጠየቁ መስሚያም የላቸው፣ ማፍረስ እንጂ መገንባት አይታያቸውማ!

  አይሆንም እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻው ቢቀማ በሰ/ት/ቤቶች ውስጥ ተደራጅቶ እንደገና ሥራውን ይቀጥላል፣ ምንም የምታመጡት ነገር እንደሌለ እዩ፡፡ ምናልባት ባለ ጊዜ ነን ብላችሁ፣ ሰ/ት/ቤቶችንም ካላፈረሳችሁ በቀር የሚቻል አይሆንላችሁም፡፡

  በሥልጣን ተጠቅማችሁ በግድ ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ…

  3. በየሰበካ ጉባኤ ውስጥ ያሉትን አባላት አይፈርሱም

  ቃለ ዓዋዲው በአካባቢ ካሉ ክርስቲያኖች ሰበካ ጉባኤ አባለት እንዲዋቀር ያዛል፡፡ የሰበካ ጉባኤ አባላት ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን አባል የሆኑትም ሁሉ፣ በትዳርም ሆነ ከቤተ ሰብዕ ጋር በመኖር በየአጥቢያው ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም በአማኝነታቸው የመመረጥ መብት አላቸው፡፡ እኛም እንመርጣቸዋለን፡፡

  ስለዚህ ከፓትርያርኩ ጋር ስትሰበሰቡ የሰማነው ንግግራችሁ ሁሉ፣ ትኩረት ያደረገው ገንዘብ ላይ ነው፣ ጭቃ ቤት ሠራን ተብለን በተሐድሶነት እየተጠረጠርን ነው ስትሉ ሰማናችሁ፤ ፎቅ ቤታችሁን፣ ጭቃ ስትሉት አለማፈራችሁ ትዝብት ውስጥ ከቶአችኋል፡፡

  ይሳካልናል ብላችሁ አምስት ኪሎ ያለውን ማኅበረ ቅዱሳን ይፍረስ ስትሉ፤ አባላቱ ግን በየሰበካ ጉባኤው ታቅፈው አሉ፣ ይኖራሉም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በየመንፈሳዊ ተቋማት ሁሉ አለ አይጠፋም እኮ! መንፈሳዊ ነገር ሊሠራ የተቋቋመ ነውና፡፡

  የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሆኑት ግንባራቸው ላይ “ማኅበረ ቅዱሳን ነን” የሚል ጽሑፍ አልተለጠፈባቸውም፡፡ ዓላማቸው ግን በአእምሮአቸው ውስጥ ተለጥፎ አለ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለሚመዘብሩ የተሐድሶ ሌቦች፣ መቅረጫቸው ቪዲዮ ቢታጣ፣ ጥርት ብሎ የሚቀርጸው ዓይናቸው፣ የተቀረጸውን የሚይይዘው ሚሞሪያቸው አእምሮአቸው ነው፡፡

  ታዲያ እንዴት ታባርሩአቸዋላችሁ? ሰበካ ጉባኤያቱን ሁሉ አፍርሳችሁ እናንተ ብቻ ልትመረጡበት ካልሆነ በቀር፣ መንፈሳዊ ተቋማቱን ልትበትኑት አትችሉም፡፡ ከዓይን አትሰወሩም፡፡ የምታደርጉ ከሆነ ግን፣ ልምድ ያለው የማኅበረ ቅዱሳን አሠራር፣ ስውር አሠራራችሁን ለሕዝብ ጆሮ ያደርስባችኋል ምን ይውጣችኋል???

  በፕሮቴስታንት ውስጥ ያላችሁ የተሐድሶ ደጋፊዎች ተሳክቶላችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ…

  በፕሮቴስታንት ውስጥ ያላችሁ የተሐድሶ ደጋፊዎች ተሳክቶላችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ…

  4. ቤተ ክርስቲያን ውስጥም ማኅበሩ ስለሚገኝ ማኅበረ ቅዱሳን አይፈርስም

  ማኅበረ ቅዱሳን በየሰንበት ት/ቤቶቹ ሁሉ እየተዘዋወረ አስቀድሞ ግንዛቤ ሰጥቶናል፡፡ መጽሐፍ አሳትሞ ስለ እናንተ ዓላማና አካሄድ አስቀድሞ አስነብቦናል፡፡ ስለዚህም ነው በየቤተ ክርስቲያኑ ተገኝቶ ግጻዌ በሚያዘው መሠረት የዕለቱ ወንጌል ካልተነበበ፣ ለምን ዛሬ የወንጌሉ ንባብ ተቀየረ? ብሎ ይጠይቃል፤ ተአምረ ማርያም ሳይነበብ ከቀረ፣ ማኅበረ ቅዱሳን እዚያው ቤተ ክርስቲያን ስለሚገኝ፣ ደባችሁን ይደርስበትና፣ ተአምረ ማርያም ይነበብ ብሎ በመጠየቅ ያስነብባል፣ በየዐውደ ምኅረቱም የሚሰጠው በግጻዌ መሠረት ወቅታዊ ትምህርት እንማር እንጂ ብሎ ይቆጣጠራል፣ አስተያየት ለሰብከተ ወንጌል ኃላፊው ይጽፋል፣ እምቢ ካለው ለሕዝቡ ግንዛቤ ይሰጣል፤ ለሌባውና ለተኩላው የተሐድሶ አራማጅ፣ አስቀድመን ታጥቀን እየጠበቅን ነውኮ! በየት በኩል ነው ዓላማችሁ የሚሳካው፤

  ሕንፃ ስትረከቡና ብር ገንዘብ ስትሉ፤ ያልተገነዘባችሁት እኛ በማኅበረ ቅዱሳን በሳል አመራሮች፣ ስለ እናንተ አስቀድመን መገንዘባችንን ነው፡፡

  የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሆይ! እነዚህ መጽናኛዎች ከጎናችሁ እንዳሉ ተረዱ፡-

  `ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል` (ያዕቆ 4:15)

  “እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ” (ሐዋ 18፡9)

  “ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል” (1ኛ ቆሮ 10:13)

  የሰላም አምላክ ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅ! የእመቤታችን ጸሎት አይለያችሁ!

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

 28. Anonymous October 17, 2014 at 4:09 pm Reply

  ke mihaberu befit enen

 29. Anonymous October 18, 2014 at 7:21 am Reply

  ማህበረ ቅዱሳን ማለት የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን የጀርባ አጥንት ነው፡፡ማህበሩ ከሊቃውንቱ ጋር በመመካከር
   የተዋህዶ ልጆች የሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግቢ ጉባኤ ውስጥ ታቅፈው ኃይማኖታዊ ስርአቱ የጠበቀ የቤተክርስትያን ት/ት በኮርስ መልክ እያስተማረ ኃይማኖታቸው እንድያጸኑና ከመናፍቃን ት/ት ራሳቸው እንዲጠብቁ የምያደርግ
   ኃይማኖታዊ ስርአቱ የጠበቀ የወንጌል ት/ት በጋዜጣ፤በመፅሔት በድምፅወምስል የምያስተምርና የምሰራጭ
   ገዳማትና አብነት ት/ት ቤ/ት የምያጠናክር
   በአጠቀላይ ተዋሕዶ ኃይማኖታችን ስርአቷና ትውፊቷ የምያስጠብቅ ማህበር ነው፡፡
  ታድያ ይህን ሁሉ ውንጀላ ለምን ይሆን?ድንግል ማርያም እውነቱን ትግለጥልን?!አፅራረ ቤተክርስትያን ታስታግስልን?! አሜን!!!!

 30. belaypawli October 18, 2014 at 7:23 am Reply

  ማህበረ ቅዱሳን ማለት የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን የጀርባ አጥንት ነው፡፡ማህበሩ ከሊቃውንቱ ጋር በመመካከር
   የተዋህዶ ልጆች የሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግቢ ጉባኤ ውስጥ ታቅፈው ኃይማኖታዊ ስርአቱ የጠበቀ የቤተክርስትያን ት/ት በኮርስ መልክ እያስተማረ ኃይማኖታቸው እንድያጸኑና ከመናፍቃን ት/ት ራሳቸው እንዲጠብቁ የምያደርግ
   ኃይማኖታዊ ስርአቱ የጠበቀ የወንጌል ት/ት በጋዜጣ፤በመፅሔት በድምፅወምስል የምያስተምርና የምሰራጭ
   ገዳማትና አብነት ት/ት ቤ/ት የምያጠናክር
   በአጠቀላይ ተዋሕዶ ኃይማኖታችን ስርአቷና ትውፊቷ የምያስጠብቅ ማህበር ነው፡፡
  ታድያ ይህን ሁሉ ውንጀላ ለምን ይሆን?ድንግል ማርያም እውነቱን ትግለጥልን?!አፅራረ ቤተክርስትያን ታስታግስልን?! አሜን!!!!

 31. አለም October 20, 2014 at 7:28 am Reply

  የማህበረ ቅዱሳን አባል ነን ብላችሁ እዚህ ብሎግ ላይ የምትጽፉ በጣም አዝኚ ነው ይህንን የጻፍሁት ምን አልባጽ ፖስት ካደረጋችሁት እኔ የምለው ለነገሩ የተማራችሁት ስድብ ነው እንዲ ለነገሩ ቃሉ ከልብ የተፈውን በአፍ እንደሚናገር የናግራል የተማራችሁትን ነው የምታሳዩት የእግዚአብሔርን ቃል ብትሞሉ ኑሮ ያንኑ ትናገሩ ነበር እናንትን በድብቅ ማህበሩ ያስማራችሁ ፖለቲካ ፣ ስርዓትና ወግ እንጂ የጌታን ቃል ሲጀመር እንሱም አያውቁት ከየት አመጥተው ያስተምራችኋል ፡፡ ለማንኛውም ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ይነሳ ጠላቶቹም ይበተኑ ነው የማለው የእግዚአብሔር ጠላት ሰይጣን ነው ግን የተጠቀመው እናንተን ነው ቃሉን በመሸፍን ክርስቶስን የመሸፍን ስራ እያሰራችሁ በክርስቶስ ትይዩ ቅዱስንን ወግንና ስርዓትን እንድታመልኩ መማድረግ ጌታ እናንተን ይወዳል ስለሁሉ ሞታልና ግን ጠላቱን ሰይጣንን ከተነሳ ይጥላዋል ስለዚህ እግዚአብሔር ተነስቷል ጠላቱን ሊጥል ስለዚህ ውድ የቤ/ክ ልጆች እንደቀደሞት ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች ለውነት ቁሙ ታሪክን በደንብ አንብቡ ከመጽሀፍ ቅድስም ጋር ታሪቁ ወደ እውነት ኑ፣ ንስሃ እንግባና ሁሉትን ለአንዱት ቤ/ክ እንስራ እኛ እዚህ እርስ በርስ ስንባላ ሙሲሊም መጥቶ ጉድ እንዳይፈላ እርስ በእርስ በፍቅር በመያያዝ የክርስቶስን እውነት በመግለጥ እርሲን መጠበቅ ይሻለናል፡፡ ማስተዋልን ይሰጥን

  • eshetu December 20, 2014 at 2:48 pm Reply

   አንቺ ማን ነሽ? ምን አልባት ኢየሱስ ክርስቶስ በ ስሜ ይመጣሉ ካላቸው ውስጥ አንዷ አንቺ ትሆኝ? አትድከሚ እውነት እምነትም ሆነ ታሪክ ከ እኛ ጋር ነው እንጂ ካንቺ እንዳልሆነ ስታውቂ አትቀባጥሪ:: ወዳጄ እውነት ካንቺ ጋር ቢሆን ኖሮ እማ አንቺና መሰሎችሽ ማኅበረ ቅዱሳንን በፕኦለቲካ ለመክሰስ ከመኳተን በምንፍቅና በከሰስሽው ነበር:: አሁንም እልሻለሁ በእምነትም ጉዳይ አንዲት እውነት ካንቺ ዘንድ ካለች ያለምንም ማቅማማት ማተቤን እበጥስልሻለሁ እና እስኪ እውነትሽን አስረጅኝ?

 32. Anonymous October 20, 2014 at 1:20 pm Reply

  ዋ! ምድረ ሆዳም እና የቤተክርስትያን ደም መጣጭ ሁላ ከማ.ቅዱሳን ሳይሆን ከፈጣሪህ እንደተጣላህ የምታስተውልበት አእምሮህን እንዳጣህ እወቅ!!

 33. yohaness wt October 21, 2014 at 5:02 pm Reply

  yihen yaderegew egziabher silehone kemahiberu belay yegziabhern aserar binadenk tiru naw bye amnalehu, silehulum neger egziabher yetemesegene yihun…..

 34. yohaness wt October 21, 2014 at 5:05 pm Reply

  እናቱን አውሬ ሲበላት ቆሞ የሚሥቅ ልጅ የለም›

 35. aaaa October 25, 2014 at 9:22 am Reply

  Abetu Gta hoy hizbehin aden tebqen

 36. Akele Getnet October 28, 2014 at 10:35 am Reply

  እግዚአብሔር ሆይ ቤተ-ክርስቲያናችንን ጠብቅ፣ምዕመኖቿንም አፅና፡፡

 37. GG March 26, 2016 at 3:53 pm Reply

  1ኛ ጢሞቲዎስ 1፡3_4
  ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፦ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሄር መጋቢነት አይጠቅምም።

  1ኛ ጢሞቲዎስ 4፡7
  ነገር ግን ለዚህ አለም ከሚመችና የዕሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሄርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።

  2ኛ ጢሞቲዎስ 4፡4
  እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፦ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ።

  ቲቶ 1፡13_14
  ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፦ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።

  2ኛ ጴጥሮስ 1፡16
  የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኋይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።

  የማርቆስ ወንጌል 16፡15
  እንዲህም አላቸው፦ ወደአለምሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።

  ሕዝቅኤል 34፡7
  ስለዚህ እረኞች ሆይ፦ የእግዚኣብሄርንቃል ስሙ።

 38. GG March 28, 2016 at 10:58 am Reply

  1ኛ ሳሙኤል 1፡5
  በውኑ የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሄር በሚቃጠልና በሚታረድ መስዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፦ መታዘዝ ከመስዋዕት፦ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።

  ቲቶ 3፡1_3
  ለገዦችና ለባለስልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፦ ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጁ ማንንም የማይሳደቡ የማይከራከሩ ገሮች ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ አሳስባቸው።

  ዕብራውያን 13፡17
  ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፦ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፦ ይህንኑ በደስታ እንጂ በሃዘን እንዳያደርጉት፦ ይህ የማይጥቅማችሁ ነበርና፦ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ።

  1ኛ ጴጥሮስ 4፡17
  ፍርድ ከእግዚአብሄር ቤት ተነስቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሄር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምንይሆን?

 39. Engidawork Dejene June 10, 2017 at 12:41 pm Reply

  ይገርማል በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ማህበረ ቅዱሳን በተክርስቲያንን ከታድሶወች የተለያዩ የጥፈት ሙከራወች ፡ የመንግስት አካል ነን ከሚሉ ግለሰቦች (ከመንግስት አላማ ዉጪ ከሆኑ) : የሀይማኖት አባትነን በማለት የበተክርስቲያኑዋን ንብረት, ቅርስ ሲያወድሙ ይከላከላል … ይህን ጥፋት የመከላከል መልካም ተግባር ማህበሩ እንዳያከናዉን የሚፈልጉ ግለሰቦችን ስንመለከት በአንድም በሌላም በጥፋት ለይ የተሰማሩ ናቸዉ … ምንም እንኩዋን የማህበሩ አባል ባልሆንም ተራ የሆንኩ እና ሀጢያተኛ ብሆንም በሚያደርጉት መልካም ተግባር ለሚደርስባቸዉ ሁሉ ከጎናቸዉ ሆናለዉ … ቅዱስ አባታችንን በብዙ ነገር አሳዝነዉናል

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: