፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል

03

  • ሥራዎች የታቀዱ፣ የሚመዘኑና በተቋም ደረጃ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ እንዲኾኑ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል /የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት/

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብስባ ዛሬ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የስብሰባ አዳራሽ ይጀመራል፡፡

ዘንድሮ ለ፴፫ኛ ጊዜ የሚካሔደው ይኸው ዓመታዊ ስብሰባ፣ ከጥቅምት ፭ – ፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የሚቆይ ሲኾን ጉባኤውን በርእሰ መንበርነት የሚመሩትን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩንና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ከ50 አህጉረ ስብከት የተውጣጡ ከ800 ያላነሱ ልኡካን ይገኙበታል፡፡

የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ ከኾነው ከአዲስ አበባ፣ የሀገረ ስብከቱን ተወካዮች ጨምሮ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ምክትል የሰበካ ጉባኤ ሊቃነ መናብርት የሚገኙ ሲኾን ከእያንዳንዳንዱ አህጉረ ስብከት ደግሞ የሰበካ ጉባኤ፣ የስብከተ ወንጌል፣ የሰንበት ት/ቤት፣ የካህናት እና የምእመናን ተወካዮች የኾኑ ስድስት፣ ስድስት ልኡካን እንደሚሳተፉበት ታውቋል፡፡

His Grace Abune Mathewos gen manager of EOTC

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፤ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ

ዓመታዊ አጠቃላይ ጉባኤው በአራት የሥራ ቀናት ቆይታው፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የሚቀርበውንና ቤተ ክርስቲያናችን በመላዋ ኢትዮጵያና በውጭም አህጉረ ስብከት በዘረጋችው የሥራ መዋቅሯ ያከናወነችውን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የሥራ አፈጻጸም የሚዳስስ ሪፖርት ያዳምጣል፡፡ የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶችም በየአህጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጆች ቀርበው ይሰማሉ፡፡

በዘንድሮው አጠቃላይ ዓመታዊ ጉባኤ የሚቀርበው የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት፣ የእያንዳንዱ መምሪያና የልማት ተቋማት የ፳፻፮ ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም በአስተዳደር ጉባኤ ተገምግሞ ውጤቱ በተቋም ደረጃ ከተመዘነ በኋላ የሚቀርብ መኾኑ የሪፖርት አቀራረቡን ካለፉት ጉባኤያት የተለየ እንደሚያደርገው ተጠቅሷል፡፡

በቀጣይም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ የሚሠሩ ሥራዎች የታቀዱ፣ የሚገመገሙና በተቋም ደረጃ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ እንዲኾኑ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ እንዳለ በብፁዕነታቸው ሪፖርት መመልከቱ ተጠቁሟል፡፡

በዓመታዊ ስብሰባው አህጉረ ስብከት ላከናወኗቸው ተግባራት ዕውቅና ከመስጠት እንዲኹም በሥራ አፈጻጸማቸው ውጤታማ የኾኑትን በማወዳደር፣ በወድድሩ መካከል በሚፈጠረው የልማት አቅም ቤተ ክርስቲያናችንን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

አጠቃላይ ጉባኤው በስብሰባው ማጠናቀቂያ፣ ቤተ ክርስቲያናችን በሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያከናወነቻቸውን ዐበይት ተግባራትና ያስመዘገበቻቸውን ውጤቶች መሠረት በማድረግ ጥቅምት ፲፪ ቀን ለሚጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የውሳኔ ሐሳብና የአቋም መግለጫ እንደሚያወጣ ይጠበቃል፡፡

የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስን ሪፖርት ሙሉ ቃል በቀጣይ እናቀርባለን፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: