ሰበር ዜና – የቅ/ሲኖዶሱን ልዕልናና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መፃረራቸውን የቀጠሉት አቡነ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› አሉት – ‹‹አባ ማትያስ አላበደም፤ በዚኽ መግለጫ እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ›› ሲሉም በማኅበሩ ላይ የጥፋት መልእክታቸውን ዐዋጁበት!

 • ጥቂት አማሳኞች በማንጨብጨብ ሲከተሏቸው፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጨምሮ ብዙኃን ጉባኤተኞች በድንጋጤና በተደምሞ አዳምጠዋቸዋል፡፡ ፓትርያርኩ በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እንዳሉም አመላካች ኾኗል፡፡
 • ማኅበረ ቅዱሳን÷ በጉባኤያት፣ በኅትመትና በኤሌክትሮኒክስ የስብከተ ወንጌል ስርጭት፣ በቅዱሳት መካናት ልማት፣ በአብነት ት/ቤቶችና በካህናት ማሠልጠኛዎች ድጎማና ሞያዊ እገዛዎች ያከናወናቸው ተግባራት በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት በስፋት ተዳስሰዋል፤ ጉባኤተኞች ማኅበሩ ላስመዘገባቸው የሥራ ፍሬዎች ደማቅ ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡

his-hholiness00 ዛሬ፣ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብሰባ አዳራሽ በተጀመረው ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ላይ የጉባኤ መክፈቻ ቃለ በረከት እንዲሰጡ የተጋበዙት ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› በማለት ‹‹በቁጥጥር ሥር እንዲውል›› ቅስቀሳ እንዳካሔዱበት ተሰማ፡፡

ፓትርያርኩ የጉባኤ መክፈቻ ‹ቃለ በረከታቸው› ማሳረጊያ ላደረጉት ቅስቀሳ መሰል ንግግራቸው መግቢያ ያደረጉት፣ ‹‹ስለ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ ልገልጽ እፈልጋለኹ፤ ይህ ጉባኤ በዓመት አንዴ የሚገኝ ነው፤ ዕድሉ እንዲያመልጠኝ አልፈልግም፤›› በሚል ቃለ አጽንዖት ነበር፡፡

ከዚያም ‹‹ቤተ ክርስቲያናችን በቅኝ ገዥዎች ተይዛለች›› ካሉ በኋላ ‹‹ቅኝ ገዥው ማን ነው?›› ሲሉ ጠይቁ፡፡ ምላሹን ራሳቸው ሲሰጡ፣ ‹‹ኹላችኁም የምታውቁት አንድ ማኅበር ነው›› ሲሉ ጠቆሙ፡፡ ‹‹በምን?›› ሲሉ ዳግመኛ ጠየቁና ‹‹በገንዘብ፤ በራስዋ ገንዘብ፤ ይኼን እንድታውቁ እፈልጋለኹ›› ሲሉ መለሱ፤ ‹‹እኔ ይኽን ጉዳይ ከራሴ አወርዳለኹ፤ የቤተ ክርስቲያናችን ገንዘቧ፣ ክብሯ ተወስዷል፤›› በማለትም አስረገጡ፡፡

በአምናው ዓመታዊ ስብሰባ፣ ‹‹ማኅበሩ በቁጥጥር ሥር እንዲውል›› አጠቃላይ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፎ ነበር ያሉት ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ ‹‹ገንዘቡ፣ ንብረቱ በቁጥጥር ሥር እንዲውል የወሰናችኁት አንድም አልተፈጸመም፤ እነርሱም ፈቃደኛ አልኾኑም፤ ማን ጠይቆ?›› ሲሉ ኹኔታው ከአቅማቸው በላይ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

አስከትለውም ‹‹ቤተ ክርስቲያን ከቅኝ ተገዥነት ትውጣ፤ ካህናቱ ከመከራ ይውጡ›› በማለት መልእክታቸውን በማንኛውም ቦታ እንደሚያስተላልፉ ከተናገሩ በኋላ፣ በሓላፊነት የተቀመጡት ‹‹ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ፤ አንዷን ቅድስት፣ ኦርቶዶክሳዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ልመራ እንጂ ኹለት ቤተ ክርስቲያን የለችም፤›› ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ ነው፤›› ባሉት ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የጥፋት መልእክታቸውን ያስተላለፉት በሚከተለው መልክ ነበር፡-

‹‹እኔ ብቻዬን የምሠራው ነገር የለም፤ በዚኽ መግለጫ እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ፤ አባ ማትያስ አላበደም፤ መልእክቴን እያስተላለፍኹ ነው ያለኹት፤ መልእክቴን ተቀበሉ ብዬ እማፀናችኋለኹ፡፡››

የፓትርያርኩ አቋም ብዙም ያልተጠበቀ አልነበረም፡፡ ይኹንና የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ከተቀመጡበት አካባቢ ጥቂት አማሳኞች ቢያንጨበጭቡላቸውም በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በጉባኤተኞች ላይ ሰፍኖ ይታይ በነበረው መደመምና ድንጋጤ የተዋጠ እንደነበር ተገልጧል፡፡ ‹‹የመልካም አስተዳደር አስተሳሰብን ማበልጸግ›› በሚል ሰበብ መስከረም ፳፯ ቀን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ፣ መስከረም ፳፱ ቀን በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በማኅበረ ቅዱሳንና በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ላይ ከርእሱ በመውጣት በከፈቱት ዘመቻብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁንና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጨምሮ ከቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ ሓላፊዎችና በብዙኃን መገናኛ አውታሮች ከተስተጋባው የብዙኃን አገልጋዮችና ምእመናን ብርቱ ተቃውሞ የተነሣ በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እንዳሉ አመላካች ተደርጎም ተወስዷል፡፡

የጉባኤተኞችን ቀልብና ስሜት ለመግዛት የተጠቀሙበት ቅስቀሳ ‹‹ከልጆቹ ጋራ እልክ መጋባታቸውን›› ያሳያል ያሉ አንዳንድ ተሳታፊዎች፣ አባ ማትያስ በፕትርክና በተሾሙበት ቀን አበ ብዙኃን ለመኾን ቃል የገቡበትን መሐላ በግላጭና በተደጋጋሚ ከመጣስ በላይ እብደት ባለመኖሩ በተጣለባቸው ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊነትና አባትነት ጉዳዩን በጥሞናና በተረጋጋ መንፈስ ሊመለከቱት እንደሚገባ ያሳስባሉ፡፡ የአጠቃላይ ጉባኤው መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ካህናት በጸሎተ ወንጌል ሲከፈት ፓትርያርኩ በንባብ ያሰሙት ቃልም ‹‹ወንድምኽ ቢበድልኽ ምከረው፣ ይቅር በለው›› (ማቴ. ፲፰÷፲፭) የሚል ነበር – የማኅበረ አመራር ከፓትርያርኩ ጋራ የውይይት መርሐ ግብር እንዲያዝለት በተደጋጋሚ ባመለከተበት ኹኔታ ቀርቦ የተጠየቀበትና ምላሹ ተሰምቶ ጥፋተኝነቱ የተረጋገጠበት በደሉ ባይታወቅም!

MK on the 33rd gen assembly of Sebeka Gubae

(ፎቶ: ማኅበረ ቅዱሳን)

አባ ማትያስ የጠቀሱት ‹‹ገንዘብና የንብረት ቁጥጥር›› ጉዳይ በተመለከተ አጠቃላይ ጉባኤው ባለፈው ዓመታዊ ስብሰባው ያወጣው የጋራ ያአቋም መግለጫው፣ ‹‹እየተሠራበት ያለውን የገቢና የወጪ ሒሳብ በቤቱ የቁጥጥር አገልግሎት እያስመረመረ፣ በቤቱ ሞዴላሞዴሎች እየተገለገለ ማእከልንም በመጠበቅ አገልግሎቱን እንዲቀጥል›› ያስገነዘበበት ነበር፡፡

ማእከላዊነትን ጠብቆ ከማገልገል አንጻር፣ ማኅበሩ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ተሻሽሎ በጸደቀለት መተዳደርያ ደንቡ መሠረት ከዋናው ማእከል አንሥቶ በየአህጉረ ስብከቱ በዘረጋው መዋቅሩ ከየአህጉረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ በመመካከርና መመሪያ በመቀበል የቤተ ክርስቲያንን ኹለንተናዊ አገልግሎት የሚደግፉ ተግባራትን እያከናወነ እንዳለ ገልጧል፡፡ በየጊዜው የአገልግሎት ዕቅዱን በማሳወቅ በየስድስት ወሩ የአገልግሎት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸምና የሒሳብ ሪፖርት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ያቀርባል፤ ተገቢውን መመሪያም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ይቀበላል፡፡

የገቢና የወጪ ሒሳብ እንቅስቃሴውን ስለመቆጣጠርም፣ ሒሳቡን በየጊዜው በውስጥ ኦዲተር እያስመረመረ ቆይቶ በየዓመቱ ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባለው ሕጋዊ የውጭ ኦዲተር አስመርምሮ ለሚመለከታቸው የቤተ ክህነት አካላት እያቀረበ የሚሰጠውን መመሪያ ተከትሎ አገልግሎቱን በማከናወን ፳፫ ዓመታትን ማስቆጠሩን ገልጧል፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት የማኅበሩን የገቢና ወጪ እንቅስቃሴ መቆጣጠር በፈለገበት ጊዜ ኹሉ ማኅበሩ በውስጥ ይኹን በውጭ ኦዲተር ያስመረመረውን ሒሳብ ማየት አልያም በማንኛውም ጊዜ በራሱ ኦዲተሮች ወይም የውጭ ኦዲተሮች አወዳድሮ በመመደብ ማስመርመር እንደሚችል አበክሮ የገለጸው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ስንኳን የራሱን የሒሳብ አያያዝ ቀርቶ የቤተ ክርስቲያናችን የሒሳብ አሠራር በሙሉ ዘመናዊና ለኦዲት የሚመች እንዲኾን የሚያግዝ ማኅበር መኾኑን አረጋግጧል፡፡

ይኹንና የማኅበሩ የሒሳብ አሠራር ዘመናዊና በሕግ ተቀባይነት ያለው የኹለትዮሽ የሒሳብ አመዘጋገብ ሥርዐት(double entry accounting system) የሚከተል በመኾኑ፤ እጅግ ኋላ ቀር፣ በዘመናዊ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐትም ተቀባይነት እንደሌለው ቋሚ ሲኖዶስና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ሰሞኑን በቀረበላቸው የሦስት የበጀት ዓመታት የውጭ ኦዲት ምርመራ ሪፖርት አጋጣሚ ያመኑበትን የቤተ ክህነቱን የነጠላ የሒሳብ አመዘጋገብ ሥርዐት(single entry accounting system) ለመከተል እንደሚቸግረው በተደጋጋሚ አስተያየቱን አቅርቧል፡

በተመሳሳይ አኳኋን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የገንዘብና ንብረት ገቢና ወጪ መመዝገቢያ ሰነዶች (ሞዴላሞዴሎች) ሥራ ላይ ማዋል የማኅበሩን የሒሳብ አሠራር ወደ ኋላ የሚጎትት እንደኾነ ነው የገለጸው፡፡ ማንኛውም ሕጋዊና ዘመናዊ የሒሳብ ምርመራ(ኦዲት) አሠራር በተለይም የውጭ ኦዲት የኹለትዮሽ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐትን ተግባራዊነት በተሻሻለ ደረጃ የሚጠይቅ በመኾኑና በዚኽ የኦዲት ሥርዐት የቤተ ክህነቱ ሞዴላሞዴሎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ሞያዊ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

እስከ አኹን ባለው አሠራርና እውነታ ሞዴላሞዴሎቹን መጠቀም የቤተ ክርስቲያናችንን ገንዘብ፣ ሀብትና ንብረት ከብኩንነት፣ ከመዘረፍና ከመጭበርበር ማዳን እንዳልተቻለ ጥናታዊ ሪፖርቶች ያመለክታሉ፡፡ የሞዴላሞዴል አሠራር (የነጠላ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ) ማንኛውንም ወጪ(ቋሚ ዕቃም ቢኾን) በወጪነት የሚመዘግብ እንጂ አንድ ተቋም ስላለው ሀብት በአግባቡ የሚያሳይ አይደለም፡፡ የፓትርያርኩንም ኾነ የቱኪና ጯኺ አማሳኞች የ‹‹ተቆጣጠሩት›› ዐዋጅ የሚረዳና ጥያቄያቸውን የሚመልስም አይደለም፡፡

በርግጥም ጥያቄው የማኅበሩን የገንዘብና ንብረት እንቅስቃሴ በአግባቡ ለመቆጣጠርና ተቋማዊ ለውጡን እንደ ጥርስና ከንፈር ተደጋግፎ የማራመድ ከኾነ፣ በማንኛውም የዘርፉን ሞያ በሚረዳ ወገን ዘንድ ተቀባይነት ያለው የመፍትሔ ሐሳብ በማኅበሩ ቀርቧል፡፡ ይኸውም ቁጥጥሩ፡- የማኅበር ሕገ ተፈጥሮን የተገነዘበ፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሕግንና የቁጥጥር መርሕን የጠበቀ፣ ለቁጥጥር አመቺ የኾነና በሕግም ተቀባይነት ያላቸውን ዘመናዊ መንገዶች በመከተል ላይ ያተኩራል፡፡

ከማኅበር ሕገ ተፈጥሮ አኳያ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክህነት በሚመደብ በጀት እንደሚተዳደሩት መምሪያዎች ወይም ድርጅቶች ሳይኾን በበጎ ፈቃድ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ አባቶችን በፍቅር ለመታዘዝና ለማገዝ የተሰባሰቡ አባላቱ ያቋቋሙት ራሱን የቻለ የቤተ ክርስቲያን አጋዥና ድጋፍ ሰጭ አካል በመኾኑ በአባላቱ መዋጮና በበጎ አድራጊዎች ርዳታ/ድጋፍ ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ የማኅበሩን ሒሳብ ሊያንቀሳቅስና ንብረቱን ሊያስተዳድር የሚችለው ጠቅላላ ጉባኤው የመረጠው የማኅበሩ አባልና አካል የኾነ ብቻ ነው፡፡

ተቆጣጣሪው አካል በዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴው ውስጥ ከገባ ዓለም አቀፍ የቁጥጥር መርሕን ይጥሳል፡፡ ይኹንና ተቆጣጣሪው አካል ቁጥጥሩን ሊያጠብቁለት የሚችሉ ሥርዐቶችን መዘርጋትና ተግባራቱን በአግባቡ መከታተል ብቻ የማኅበሩን አገልግሎት፣ የገንዘብና ንብረት እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ያስችለዋል፡፡

በአግባቡ ከተደራጀ ተቆጣጣሪ አካል የሚጠበቁት እኒኽ የሥርዐት ዝርጋታዎችና ክትትሎችም፡-

 • የኦዲት ሥራን ማሠራትና ከውጤቱ ተነሥቶ ተገቢውን አስተያየትና መመሪያ መስጠት፤
 • ዕቅዶችንና ሪፖርቶችን በመገምገም አስተያየት መስጠት፤
 • የገንዘብና ንብረት የገቢና የወጪ ሰነዶች ኅትመት በተቆጣጣሪነት መፍቀድ፤
 • የባንክ ሒሳብ እንዲከፈት ማኅበሩ ሲጠይቅ ለባንክ ማሳወቅ፤
 • የባንክ ፈራሚዎችን ስም ማኅበሩ ሲያቀርብ ለባንክ ማሳወቅ፤
 • በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤያት ላይ እየተገኙ ሐሳብን መስጠት… የመሳሰሉት ናቸው፡፡

በማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ መሠረት ማኅበሩ አገልግሎቱን የሚያቆመው፣ ትክክለኛነቱ በቅ/ሲኖዶስ በተረጋገጠ የጠቅላላ አባላቱ ውሳኔ አልያም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ ሲኾን ያፈራው የማይንቀሳቀስ፣ ተንቀሳቃሽ የኾነና ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ንብረትነቱና ሀብትነቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደኾነ ሰፍሯል፡፡ ማኅበሩ ከሚከተለው የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት አኳያ የንብረት መሸጥና መለወጥ፣ ቱኪዎቹ እንደሚሉት ‹‹ማሸሽ›› ሳይኾን፤ በአጠቃላይ ንብረቱ ላይ የሚያመጣው ለውጥም የለም፤ የሚጨምረውና የሚቀንሰው ነገር በግልጽ በሚረዳ መንገድ በአሠራሩ የሚታይ ነውና፡፡፡፡

በአጠቃላይ የማኅበረ ቅዱሳን የማገልገል አቅም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አካል በታመነበትና የሚገኝበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን፣ ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ዕድገት የሚጠቅም፣ የላቀና የተሻለ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለማበርከት የሚያስችለው መዋቅራዊ አደረጃጀትና ምቹ ኹኔታ እንዲፈጠርለት እየተጠየቀ ባለበት ወቅት፣ የፓትርያርክ አባ ማትያስ ቅኝ ገዥ ነውአጥፉት ቅስቀሳ በእጅጉ አሳዛኝና በብርቱ ሊታሰብበት የሚያስፈልግ ነው፡፡

ደጉ ነገር! በዛሬው የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ በስፋት የተደመጠው የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አጠቃላይ ሪፖርት፣ ይህን በአማሳኞች፣ ጎጠኞች፣ አድርብዬ ፖሊቲከኞችና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ግንባር ቀደም መሪዎች ክፉ ምክር የተፈጠረ እልከኝነትና ምናልባትም የውጭ ኃይልን አጀንዳ በሌላ ገጽታ የሚገፋ የውክልና ጫና የወለደው ክሥ ከንቱ የሚያደርግ መኾኑ ነው፡፡

ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በጥቅልና በዝርዝር ያቀረቧቸው የማኅበሩ የሥራ ፍሬዎች፣ አባ ማትያስ ማኅበሩን በቅኝ ገዥነት እንደወረፉት ሳይኾን፤ ለታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት መጠበቅ፤ ለትምህርተ ሃይማኖቷ፣ ሥርዐተ እምነቷና ክርስቲያናዊ ትውፊቷ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሳይበረዝና ሳይከለስ መተላለፍ ትጉህ ዘኢይነውም ኾኖ ጥብቅና መቆሙን ነው፡፡

ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ ልዩ ጽ/ቤት በተዘረጋው የአማሳኞች፣ ጎጠኞችና አድርብዬ ፖሊቲከኞች የሙስና ኤምፓየር የቤተ ክርስቲያንን ‹‹ክብሯንና ገንዘቧን በቅኝ ገዥነት የወሰደ›› ሳይኾን፤ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታኹን ሙጬ የዘንድሮውን የአህጉረ ስብከት ውጤታማነት በገለጹበት ቋንቋ ‹‹የቤተ ክርስቲያናችን ምጣኔ ሀብት በዓለት ላይ የተመሠረተ ይኾን ዘንድ›› የአባላቱንና የበጎ አድራጊ ምእመናንን ጉልበት፣ ሞያና ገንዘብ አስተባብሮ ስኬታማ የልማት ሥራ የሠራ መኾኑን ነው፡፡

‹‹ካህናቱን ለጭቆናና ለመከራ ቀንበር የዳረገ›› ሳይኾን ከማንኛውም ክፍያ ነፃ በኾነና ያለስስት በልግስና በሚናኘው ሞያዊ አበርክቶው፣ ለተቀደሰው የክህነት ሞያቸው መከበርና ለኑሯቸው መመቻቸት የተጠበበና ከአማሳኞች፣ ጎጠኞችና ዐምባገነኖች ጋራ በየመድረኩ ፊት ለፊት የተሟገተ መኾኑን ነው፡፡

ፓትርያርኩም ኾነ መላው ኦርቶዶክሳዊ የሚጨነቅለት የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር መቀነስ አሳስቦት፣ በንግግር ብዛት ሳይኾን በተግባር፣ ሚልዮኖችና መቶ ሺሕዎች የቃለ እግዚአብሔርን ማዕድ በሚቋደሱባቸው ሐዋርያዊ ጉዞዎችና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዙ አውታሮች ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋቱንና ማጠናከሩን ነው፡፡

Advertisements

39 thoughts on “ሰበር ዜና – የቅ/ሲኖዶሱን ልዕልናና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መፃረራቸውን የቀጠሉት አቡነ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› አሉት – ‹‹አባ ማትያስ አላበደም፤ በዚኽ መግለጫ እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ›› ሲሉም በማኅበሩ ላይ የጥፋት መልእክታቸውን ዐዋጁበት!

 1. Anonymous October 15, 2014 at 12:11 pm Reply

  Ahunis beza ye ethiopia ortodox tewahdo b/n patriyarik woynis ye tehadiso menafkan petriyarik new ye mengist …… Min eyaderegu new????

 2. Anonymous October 15, 2014 at 1:26 pm Reply

  ብራቮ ፓትርያርክ ማትያስ ‘’ታሪክ ከመዘከር ታሪክ ወደ መስራት ስለተሸጋገሩ
  ‘’ታሪክ ከመዘከር ታሪክ ወደ መስራት ተሸጋግረናል’’!!
  ይህንን ኃይለ ቃል/መፈክር/ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ ለሥራ ወደ አንድ መሥሪያ ቤት ደርሼ ስወጣ የግቢ መውጫ በር አጠገብ ካለው የማስታወቂያ ሰሌዳ ውስጥ በደንብ እንዲታይ ጠቋሚ አጅ ምልክት ተደርጐበት ጐላ ብሎ የተጻፈው ዓይኔን ሳበው እግሬንም መንገዱን ወደ ቀኝ አስቀየረው፡፡ ጠጋ ብዬ አነበብኩት ጽሑፉ ደመቅ ብሎ በሁለት ቃለ አጋኖ ታጅቦ ታሪክ ከመዘከር ታሪክ ወደ መስራት ተሸጋግረናል!! ይላል፡፡ ቆም ብዬ የሚዘከረውን ታሪክ የሚያሰረሳ የሰሩት ታሪክ ምን ይሆን? ይሄን ያሉበት ምክንያትስ እያልኩ መ/ቤቱን ዓይኔ የደረሰበት ድረስ ዙሪያ ገባውን አማተርኩ….መልስ አላገኘሁም???? ሌላም ጥያቄ ድቅን አለብኝ..ታሪክ መዘከሩን ያቆማል እንዴ? የአንድ መጽሐፍ መቅድም ላይ ያነበብኩት … ‘’ታሪክ የሌለው ሕዝብ ታሪካዊ ሥራ ለመስራት አይጓጓም’’፡፡ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡ የተለያዩ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎችን በኀሊናዬ እያመላለስኩ ሳሰላስል በሃሳብ ከተጓዝኩበት እህት ምን ረስተሽ ነው የሚለው የጥበቃው ጥያቄ ወደ ቆምኩበት ቦታ መለሰኝ፡፡
  ስለተጸፈው ኃየለ ቃል ትንሽም ቢሆን ከመ/ቤቱ ሠዎች ማወቅ አለብኝ ብዬ ወደ መረጃ ኦፊሰሩ ተመለስኩ ከ5 በላይ ባለጉዳዮች ይጠብቁት ስለነበር እኔም ሌላ የምሄድበት ቦታ ስለነበር ለጥያቄዬ መልስ ሳላገኝ ቃሉን በአእምሮዬ እያመላለስኩ ወጥቼ ሄድኩ፡፡

  የወጣሁበትን ሥራ ጨርሼ ለምሳ ወደ ቤቴ ስገባ ከምሳ በፊት የእለቱን ዜና ለማየት ላኘቶፔን ከፍቼ ሳይ የመጀመሪያው መስመር ላይ የወዳጆቼን የ Hara Ze Tewahido ሰበር ዜና ላይ ዓይኔ አረፈ ፈጠን ብዬ ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› አሉ የሚለውን ሳነብ …አራት ሰዓት ላይ ያየሁትና መልስ ያጣሁለት ኃይለ ቃል አሁን መልስ አገኘሁለት
  …የእግዚአብሔር ወዳጆችን የቤ/ክ ልጆችን የሚያሳድደውን አውሬ ጉዳይ አስፈጻሚ ነበሩ፡፡ አሁን በራስ አገዝ ወደ ፈጻሚነት ተሸጋግረዋል፡፡
  ብራቮ ፓትርያርክ ማትያስ ‘’ታሪክ ከመዘከር ታሪክ ወደ መስራት ስለተሸጋገሩ

  • Anonymous October 15, 2014 at 2:20 pm Reply

   how stupid are you? “hod amlaku, musegna”

 3. Anonymous October 15, 2014 at 1:38 pm Reply

  be shumet qedus yehonu be tegebare gen ….. yehonut aba matiyas, TENA YESTLIGN.

  • Anonymous October 15, 2014 at 4:27 pm Reply

   besim kidus yehne betegbar gin yerekese mahiber aymeslihim

   • Anonymous October 24, 2014 at 4:49 am

    mahiberu alrekesem, yerekeskew antew neh. stupid

 4. tekle giorgis October 15, 2014 at 1:38 pm Reply

  Pop Matias if u rely on a person who have a gun our church rely on AMANUEL.May you can change your church by changing ur words remember death and life in the power of ur tongue. DM

  • Anonymous October 21, 2014 at 4:03 am Reply

   Please try to contemplate before u forward ur comment. U have been saying for years that abune /pop/ poul as having a gun but he had never shoot up on somebody rather than shooting evil spirit via his prayer. He has now passed away. U r repeating same words for pop mathias and u will never see targeting people using this physical gun rather than
   targeting sin like his anccesters. So My advise for u is don’t think that every body
   believes on the power of gun as most of us
   are not from the group where u arise from.

 5. Anonymous October 15, 2014 at 1:53 pm Reply

  Be sem kidus be tegebar gin ……. Aba Matiyas, Ye betekerestian Amlak TENA YESTLIGN

 6. Anonymous October 15, 2014 at 2:23 pm Reply

  የተሾሙለትን ዐላማ ከግቡ ለማድረስ እየሠሩ ያሉትን “እንዲኽ አሉ፤ እንዲያ አደረጉ” እያሉ ማብጠልጠል አንዳች ፋይዳ የለውም። ምንም ቢዘገይ፤ አኹን ዐላማቸው ዐላማችን፥ ምኞታቸው ምኞታችን እንዳልኾነ ከተረዳን፤ ቀሪው ነገር “ሺ ሞታቸው” ወይ ማተባችንን እያስበጠሰ ሲኦል አለዚያም አንገታችንን እያስቀነጠሰ መቃብር ሳያወርደን፤ ማድረግ የሚገባንን ማድረግ ነው። ርግጥ በመካከላችን የተሰገሰጉት የሺሞታቸው ተካፋዮች ለዚህ እንቅፋት ለመኾን ቆርጠው መነሣታቸው አይቀርም። ይነሧ! እንዲያውም ይነሡና እንያቸው… በከንቱ ጊዜ አናጥፋ!

 7. Anonymous October 15, 2014 at 4:59 pm Reply

  MK your time of repentance is now. the church is begging you more than 9 years You have time to return to church with full your heart, stop playing with a sharp knife which is the word of God. MK! you have to obey the fathers of the church and please remember what you have been doing for the last 22 years. you shed blood of many scholars and brothers .
  let me ask you MK! whom you want to hear or listen? begging you! please repent from your sin and clean yourself.
  we pray for you.
  May the Almighty God opens your internal hear to hear His voice and He may opens your internal eye to see His divine word.

 8. Anonymous October 15, 2014 at 5:25 pm Reply

  E.r melkamun hulu yadirgilin.Amen

 9. G/Silassie October 15, 2014 at 7:21 pm Reply

  ወንድሞቼ፣ ከክርስቶስ ወገን ከሆን መገፋፋቱን ትተን በፍቅር መነጋገሩ ይበጃል፡፡ ሁሉም ኃላፊ ነው፡፡ በረከታቸው ይድረሰንና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በብዙ መንገድ ተወቀሱ፣ በብዙ መንገድ ተመሰገኑ፡፡ ይሄ ጤናማ የሆነ የአስተዳደር ጉዞ ነው፡፡ በእኔ አመለካከት ማኅበረ ቅደሳንን ከመቆጣጠር አኳያ ከአሁኑ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በብዙ መንገድ ይሻላሉ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ማኅበረ ቅዱሳንን በቅርበት ያውቁታል፡፡ የሚያከናውናቸውን መንፈሳዊ አገልግሎቶች በአካል በመገኘት አበረታተዋል፡፡ በአንድ ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ላይ “ፈተና በበዛባችሁ መጠን ትጠነክራላችሁ፣ ብዙ ቢወራባችሁም በጎ ሥራችሁ ግን ሕያው ምስክር ይሆናችኋል፣ ሥትሰሩ ግን ከአባቶቻችሁ ጋር እየተመካከራችሁ ሥሩ፣ ወዘተ” እያሉ አባታዊ ምክር ሲሰጡ በአካል ተገኝቼ ሰምቻቸዋለሁ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ማኅበሩን በጥርጣሬ ቢመለከቱትም ከመውቀስና ታረሙ ከማለት ውጪ በገሃድ አሳልፎ መስጠት ዓላማቸው እንዳልነበረ በብዙ መንገድ መታዘብ ይቻላል፡፡ ከመንግስት በኩል የሚመጣባቸውን ጫና በብልጠት የተወጡ አባት ነበሩ ብየ መመስከር እችላለሁ፡፡ የአሁኑ አባታችን ግን አስቀድሞ በተሞሉት የጥላቻ አመለካከት ምክንያት ማኅበሩን ቀርበው እንዳይመለከቱና ድክመቱንና ጥንካሬውን እንዳይመለከቱ አድርጓቸዋል፡፡ ይሄ አመለካከት በማንኛውም ሰው ላይ የሚንጸባረቅ ጠባይ ሲሆን ይሄንን አመለካከት ለመቀየር ብዙ መስዋዕትነት ይጠይቃል፡፡ ያም ሆነ ይህ በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ ላይ ያልተመሰረተ ውሳኔ በሳይንሱም ሆነ በመንፈሳዊ አመራር የተሳሳተና ወደአልተፈለገ አቅጣጫ የሚያመራ አካሄድ ነው፡፡ አስታውሳለሁ ለፓትርያርክነት በተመረጡበት ቀን መግለጫ ሲሰጡ ትኩረት ሰጥተው ከተናገሯቸው ጉዳዮች አንዱና ዋናው ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ተገዢ መሆን እንደሚገባ ነበር፡፡ ይሄንን በአደባባይ የተናገሩትን አዋጅ ራሳቸውም ለመተግበር ተቸግረዋል፡፡ ይሄ ደግሞ የአመራር ክህሎት እንደሌላቸውና በመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን በራሳቸው ፈቃድ ለመጓዝ ቆርጠው የተነሱ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ ከአሁን በኋላ ደግሞ ይሄን አመለካከት እንደማይቀይሩትና እስከ ረፍታቸው ድረስ እንደሚቀጥሉበት ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እንደ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ነጭ ልብስ አለብስም ከሚሉ ይልቅ ነጭ ልብስ ለብሰው ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተገዢ ቢሆኑ የተሻለ ነበር፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጣብቂኝ ውስጥ የገባበት ወቅት አሁን ይመስለኛል፡፡ ቅዱስ ሲኖዱሱን በበላይነት የሚያስተባብሩት አባት ከሲኖዶሱ አፈንግጠው በራሳቸው መንገድ ከተጓዙ፣ ፈቃደ እግዚአብሔርን ሳይሆን የግለሰቦችን ፍላጎት ለማስፈጸም ከተነሱ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመተንበይ ነብይ መሆን አያስፈልግም፡፡
  እግዚአብሔር አምላካችን ለሁላችንም አስተዋይ ልቡና ይስጠን!!!

 10. Anonymous October 16, 2014 at 2:08 am Reply

  mastewaln yisten

 11. Teshome Aregu Gebeyehu October 16, 2014 at 7:53 am Reply

  ግን ለምን!!!

 12. A/Silassie October 16, 2014 at 9:40 am Reply

  Bezih ye kefa wekit erasin megizat ena tsento megegnet yasifeligal. Endene ginzabe, diabilos andand abatoch be kefetut kedada sholko menber patriarc kitsir gibi zew bilo gebitoal. Kirstiayanoch hulu; beteley le ewinet yekomachihu kidusan abatoch; madalat yelelebet, manim lishirew yemachil, kemeta ende siyifin ena esat yemiyatefa firdun endiset wede balebetu wede serwait geta Egziabher enichuh.

  Ene yemiferaw ke 2 amet befit yetederegew teamir ahunim endayidegem new.

 13. Amsalu G/kidan October 16, 2014 at 10:27 am Reply

  አባ ማትያስ ሆይ! እርማት አለዎት ያሰስተካክሉ? ቤተክርስቲያንን የሚመራና የመምራት ሥልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ እንጅ እርስዎ አይደሉም፡፡ ሕግጋተ ቤተክርስቲያን እንደደነገጉት እርስዎ ከሲኖዶሱ በታች እንጅ በላይ አይደሉምነና፡፡ እርስዎ ተጠሪነትዎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው እንጅ ቅዱስ ሲኖዶስ አይደለም ለእርስዎ ተጠሪ የሆነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ደግሞ ተጠሪነቱ ለመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ይሄንን አያውቁም? ነው ወይስ እየሸፈጡ ነው? የእርስዎ ሥራ ማስተባበር ነው ይሄንን ሊያውቁ ይገባል፡፡ እባክዎን ሕገ ቤተክርስቲያንን ያክብሩልን? ሕገ ቤተክርስቲያንን ሳያከብሩ ለቤተክርስቲያን እሠራለሁ ማለትዎ ለማስመሰልም እንኳን ቢሆን አልመሰለልዎትም፡፡ እርስዎ እያሉን እንዳሉት በእርግጥም ካላበዱ እንግዲያውስ ይሄንን በማድረግ ጤነኛነትዎን ያረጋግጡልን፡፡
  እርስዎ ቢናገሩ ገንዘብ አጫፋሪዎችዎ ቢናገሩ ገንዘብ፡፡ ምን ዓይነቱ በቃኝን የማያውቀው የማይጠረቃው የፍቅረ ነዋይ ጋኔን ነው ያደረባቹህ በመድኃኔዓለም? አንዳች የሚከሱበት ነገር ቢያጡ “ቅኝ ገዥ” ብለው ሳያፍሩ ምን ይሉኛል ይታዘቡኛል ሳይሉ የተጫኑትን እንደወረደ ተፉብን፡፡ ታዲያ በግልጽ እኔ የወያኔ ካድሬ እንጅ የቤተክርስቲያን አባት፣ የወያኔ አገልጋይ እንጅ የእግዚአብሔር አገልጋይ አይደለሁም ይበሉና? መቸም እናንተን መክሮ ዘክሮ ሰው ማድረግ ማለት ሰይጣንን ወደ መልአክነት እንደመቀየር ያህል የማይቻል ነውና ቤተክርስቲያንን ከማጥፋታቹህ በፊት እናንተን ያጠፋቹህ ዘንድ ጸሎቴ ነው፡፡

 14. Anonymous October 16, 2014 at 11:50 am Reply

  አቡነ ማትያስ፡ ቤ/ክ የተዋረደችዉ እርስዎን መከታ ባደረጉ በላተገኞች እንጂ በማበረ ቅዱሳን አይደለም ከፈጣሪዎ ተጣልተው እገኛንም አታጣሉን ማህበሩማ የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት በማስከፈት የክርስቲያኖችን እንባ እያበስ ነው አያ ጅቦ ሳታመካገኝ ብላገኝ እንዳለው የተጫኑትን ጭነት ሳያመካገኙ ያራግፉ

 15. YETEWAHIDO LIGI October 16, 2014 at 12:06 pm Reply

  OH MY GOD! HOW CAN PEOPLE FORGET ABOUT THE GREAT EVENT THAT HAPPEND ON AUGUST 2012. LET ME TELL YOU ONE THING; GOD IS VERY PATIENT, BUT IF YOU PERSIST ON YOUR WRONG ACTION PURPOSLY, HE WILL PANISH YOU BADLY.

 16. Anonymous October 16, 2014 at 1:20 pm Reply

  Ehhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhhh!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

 17. gebre yohanse October 16, 2014 at 2:07 pm Reply

  Abetu ye kidusan Amilak mahberachinin tebikilin

 18. Hiwot Mekuria October 16, 2014 at 2:41 pm Reply

  Egziabehare maheberune ytebekewal yekedusanu kemeneme belay yakeberate he emebetachen stelute melgawa yetebekewal

 19. ማማዬ የማርያም ልጅ October 16, 2014 at 5:40 pm Reply

  እግዚአብሔር ይባርካችሁ
  አሁንም ስለቤተክርስቲያናችን አንድነት በርታችሁ ስሩ
  ማሕበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላፀጋፀጋና በረከት ያብዛላችሁ

 20. Kurabachew Desta October 17, 2014 at 5:02 pm Reply

  don’t worry GOD is always with US!

 21. Anonymous October 18, 2014 at 9:13 am Reply

  ayyyyyyyyyyyyyyyyyyy yetignaw papas yihon simesegen yemisemaw be EGIZABIHER hayil new yalechiw betekiristian eniji be papasu weyim bemahibere kudisan wey be sewu hayil bihon tefitalech bewich yeminorut hizibachin enikan tikit eyalu eko anid mehon akitiwachewal man anid siyaregachew taye ke abatoch esike mahibere kudusan dires min seru?

 22. Anonymous October 18, 2014 at 12:49 pm Reply

  EGZIAO MAHARENE CHIRISTOS!!!

 23. […] ምንጭ፡ ሃራ ዘተዋህዶ […]

 24. […] ምንጭ፡ ሃራ ዘተዋህዶ […]

 25. Anonymous October 20, 2014 at 1:48 pm Reply

  abate skeda aydres..

 26. Anonymous October 21, 2014 at 8:22 am Reply

  ye kidusan amlak hulunim yimeleketal !

 27. assfa October 21, 2014 at 10:38 am Reply

  Egzibher mastewalun yisten

 28. ተተ October 21, 2014 at 2:33 pm Reply

  በህግ አልገዛ ያለው አጠቃላይ የቤተክህነቱ አሳተዳደር እንጂ የማህበረ ቅዱሳን አገልግሎት አይደለም። ማ.ቅ. በቤተክህነቱ የእዝ ሰንሰለት ውስጥ ለመግባት በመጀመሪያ ቤተክህነቱን እንደትኋን ከሚበሏት ካህን ወይም አገልጋይ እና ከማንም በላይ ለቤተክርስትያን ተቆርቋሪ ነን ባዮች ለማፅዳት ቁልፍ የሆነ የአሰራር ስርአት መዘርጋት አለበት፤ የማ.ቅ.አብይ አላማ ይህ ነው። አእምሮ እና ማስተዋል ያለው ሁሉ ይህን ያውቃል። ምእመኑ ሳይተርፈው ቤተክርስቲያኔን ላሳድግ፤ ሃይማኖቴ ትጠንክር ብሎ የሚለግሰውን ከኪሳቸው እንዳይወጣ የበግ ለምድ በመልበስ ቤተክርስትያኒቱ ውስጥ በመሰግሰግ የቤተክርስቲያኗን እድገት ወደታች፤ ምእመኑን ወደ እናት ቤተክርስትያን ከመሰብሰብ ይልቅ በክፉ ምግባራቸው መበተን፤ ወንጌል በመናፍቃን እና በተሃድሶዎች በየቤተክርስቲያኒቱ እንዲሰበክ ማድረግ፤ በየቤተክርስትያኑ ፍቅር እንዲጠፋ ማድረግ፤ የቤተክርስትያን ቅርስ እንዲዘረፍ ማድረግ፤ ምእመኑ የሃይማኖቱን ትሩፋት ጠብቆ እንዳይሄድ የሚያደርጉ እና አትስረቅ እያሉ የሚሰርቁ፤ አታመንዝር እያሉ የሚያመነዝሩ፤ አትሳደብ እያሉ የሚሳደቡ፤ ማ.ቅ.ንን ቢወነጅሉ አይፈረድባቸውም። ምክንያቱም አምላክ የሰጣቸውን ሓዋሪያዊ ተልእኮ ለስጋዊ ጥቅም በመሸጥ ባለፉበት፣ ባልደከሙበት የቤተክርስትያኒቱ ሃብት የቅንጦት ኑሮ ላይ ስላሉ የማ.ቅ.ጉዳይ የእግር እሾህ ቢሆንባቸው አይገርምም ። ይህ ድሮም ይታወቃል እሰከ ዛሬም መቆየታቸው አይዞኣችሁ ግፉበት የሚላቸው ጠፍቶ እንጂ። ታድያ ለፍጥረቱ የሚያስብ እግዚኣብሄር ማረፊያ ቢያጣ ለነዚህ ልጆች ጸጋውን አብዝቶ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ የወጣቱ ተረካቢ ማጣት፤ የምእመኑ ከቤተክርስትያን መራቅ እና ወንጌል መራብ የቤተክርስትያን ቅርስ መጥፋት፤ ቢያሳስባቸው ወደ ኣባቶች ቢጮሁ ሰሚ ማጣታቸው፤ እንቅልፍ ሳያምራቸው ከደምወዛቸው ቆርሰው ፈጣሪ በሰጣቸው እውቀት ካለዋጋ እንዲያገለግሉ አምላክ መረጣቸው። ስለዚህ ከኣባቶች የሚጠበቀው የስራቸውን ፍሬ አይተው ልጆቼ በርቱ እናንተም አግዙን እኛም እንርዳችሁ የኛ ተተኪዎች እናንተ ናችሁ ማለት ነበር እግዜር ልቦና ቢሰጣቸው። አሁንም እዝነ ልቦናቸውን ያብራላቸው! የንስሃ እድሜ ይስጣቸው! ማ.ቅ. ገንዘብ ቢሰበስብ የወደቁትን ኣነሳበት፤ ወንጌል አስተማረበት ፤ ምእመኑን ወደ እናት ቤተክርስትያን መለሰበት፤ ቤተክርስትያን አነፀበት፤ የተበተኑትን ሰበሰበበት፤ ቅርስ አኖረበት እንጂ የውሃ ጠብታ ወደ ጉሮሮው ኣላከበትም!!! ኣላማውም ስላልሆነ።

 29. alemihun October 22, 2014 at 1:47 pm Reply

  This is really shocking, Abun Mathias has gone wrong way. since, mahebere kidusan working in the expandation of Gospel for people in different remote places and countries, bring people together for developing the church of orthodox. so, please think by stopping
  .

 30. melkam October 23, 2014 at 5:45 am Reply

  ene yemlewu neger yelegnm gin hulunm yemiyawuk yeserawit geta egiziabher hulun yimermir.

 31. Anonymous February 16, 2016 at 6:18 am Reply

  • እኔ የምለው ለመሆኑ አባ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያ ለአለም እያስተዋዋቀ ያለው እንዲሁም እየጠፋ ያለውን የአብነት ትምህርት እያስፋፋ ያለው ማን ነው? ማህበረ ቅዱሳን አይደለም እንዴ፡፡
  • በየ ዮንቨርስቲዎች የሚገቡ ተማሪዎችን እውነተኛውን የእግዚአብሄር ቃል ተምረው አውቀው እንዲወጡ እያደረገ ያለውስ ? ማህበረ ቅዱሳራ አይደለም እንዴ፡፡
  • ለሲኖዲዎስ ግን ይህ አልታየም ያሳዝናል ፡፡
  • ለመሆኑ ምንድን ነው የሚያዮት አባቶች ያልሆነ ስህተት ሲሳሳቱ ካላዩ ካላረሙ ፣ካልገሰፁ
  • አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የእየ አድባንቱ አስተዳዳሬዎች ሲዘርፋ ፣ ሲያጭበረብሩ ፣ በቆብላይ በምልኩስና ላይ የማይገባ ተግባራ ሲፈፅሙ ያልታያቸው ከመሬት በመነሳት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በከፍተኛ አገልግሎት ላይ ያለውን የማህበረ ቅዱሳን መክሰስ መሳደብ እስክሞት ድረስ አለቅም ተገቢ አይደለም ፡1
  • ወንድሞች እህቶች “ እስከሞት ድረስ የተመንክ ሁን የህይወትን አክሊልንም ትጐናፀፋለህ “ ይላል ስለዚህ መፈተን መልካም ስለሆነ ጠንክሩ በርቱ እውነት እና ንጋት እያደር ይወጣል ነው ፡፡

 32. Lemma Banch February 16, 2016 at 7:38 am Reply

  • እኔ የምለው ለመሆኑ አባ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያ ለአለም እያስተዋዋቀ ያለው እንዲሁም እየጠፋ ያለውን የአብነት ትምህርት እያስፋፋ ያለው ማን ነው? ማህበረ ቅዱሳን አይደለም እንዴ፡፡
  • በየ ዮንቨርስቲዎች የሚገቡ ተማሪዎችን እውነተኛውን የእግዚአብሄር ቃል ተምረው አውቀው እንዲወጡ እያደረገ ያለውስ ? ማህበረ ቅዱሳራ አይደለም እንዴ፡፡
  • ለሲኖዲዎስ ግን ይህ አልታየም ያሳዝናል ፡፡
  • ለመሆኑ ምንድን ነው የሚያዮት አባቶች ያልሆነ ስህተት ሲሳሳቱ ካላዩ ካላረሙ ፣ካልገሰፁ
  • አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የእየ አድባንቱ አስተዳዳሬዎች ሲዘርፋ ፣ ሲያጭበረብሩ ፣ በቆብላይ በምልኩስና ላይ የማይገባ ተግባራ ሲፈፅሙ ያልታያቸው ከመሬት በመነሳት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በከፍተኛ አገልግሎት ላይ ያለውን የማህበረ ቅዱሳን መክሰስ መሳደብ እስክሞት ድረስ አለቅም ተገቢ አይደለም ፡1
  • ወንድሞች እህቶች “ እስከሞት ድረስ የተመንክ ሁን የህይወትን አክሊልንም ትጐናፀፋለህ “ ይላል ስለዚህ መፈተን መልካም ስለሆነ ጠንክሩ በርቱ እውነት እና ንጋት እያደር ይወጣል ነው ፡፡

 33. Anonymous March 12, 2016 at 7:21 am Reply

  YsYexan mahebre ,Yexfate mahebre enji mzgate albte abatachene bertuegeziyabeher krso 0gare yehune amen enwdotalne

 34. Anonymous March 28, 2016 at 11:42 am Reply

  እግዚአብሔር ይህችን ንፅህት እምነታችንን ይጠብቅልን

 35. […] ጉባኤ 33ኛው ዓመታዊ ስብሰባ መክፈቻ ‘ቃለ ምዕዳናቸው’፥ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ማኅበር ቅኝ እንደተገዛች በመግለጽ ቅ… ይህን ይመስል ነበር፤ ጥቅምት 6 ቀን በሚጀምረው የዘንድሮው […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: