ቋሚ ሲኖዶስ: ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዘመናዊው የኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት እንዲተከል ወሰነ፤ ለተቋማዊ ለውጥ ባለተስፋዎች የምሥራች፣ ለአማሳኝ ተቃዋሚዎች ኀፍረትና መርዶ ነው!!

Head of EOTC Patriarchate

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት

 • ትክክለኛ የቋሚና አላቂ ንብረት ምዝገባና አስተዳደር፣ ተቀባይነት ያለውና እምነት የሚጣልበት የገንዘብ ገቢና ወጪ እንቅስቃሴ፣ ግልጽና ወጥነት ያለው የግዥ አፈጻጸም፣ ብቁ የቁጥጥር ሥርዐት ባለመዘርጋቱ የቤተ ክርስቲያናችን ጥቅል ሀብት አይታወቅም፡፡
 • በማንኛውም ሕጋዊናመናዊ የሒሳብ ምርመራ አሠራር እጅግ ኋላ ቀር በኾነው በነጠላ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ እና በሞዴላሞዴሎች አሠራር በሚልዮን ብሮች የሚገመት የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ እና ንብረት ከብኩንነት፣ ከመዘረፍ እና ከመጭበርበር ለማዳን አልተቻለም፡፡
 • በጠቅላይ ቤተ ክህነታችን ሦስት የበጀት ዓመታት ላይ የተካሔደው የውጭ ኦዲት÷ አጠቃላይ የፋይናንስ እንቅስቃሴያችንና የንብረት አስተዳደራችን በዘመናዊው የሒሳብ ምርመራ ስልት ሕጋዊ ተቀባይነት የሌለውና ሞያዊ አስተያየት ለመስጠት የማያስችል (Disclaimer of Opinion report) እንደኾነ አረጋግጧል፡፡

double_entry_accounting00

 • የቤተ ክርስቲያናችንን የገንዘብ ዝውውሮች ወጥነትና ተቀባይነት ባላቸው የፋይናንስ ደንቦችና መመሪያዎች ለመመዝገብ፣ በዚኹ ላይ በመመሥረትም ተአማኒ የኾኑና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጡ ፋይናንስ ነክ መረጃዎችንና ሪፖርቶችን በወቅቱ ለማቅረብ ያስችላል የተባለው የኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት፣ ሀብታችንን በአግባቡ በማስተዳደር ዋናውን ሐዋርያዊ ተልእኳችንን የምናጠናክርበት አቅም እንደሚፈጥርልን ታምኖበታል፡፡
 • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የቋሚ ሲኖዶሱን የፋይናንስ ፖሊሲ ውሳኔ ለመተግበር በሚያከናውነው ነባሩን የሰው ኃይል ቅድሚያ ሰጥቶ የማብቃት ቅድመ ዝግጅት፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው የተመረጡ ሠራተኞች የአጭር ጊዜ የፒችትሪ ሥልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ላይ እንዳለ ተጠቁሟል፡፡
 • ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተጠንቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ይኹንታና የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበትና የብዙኃን ካህናትንና ምእመናንን ተቀባይነት ያረጋገጠው የሒሳብ አያያዝ ፖሊሲና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ÷ በኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት ላይ ተመሥርቶ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እንደሚዘረጋ ለሚጠበቀው ዘመናዊና ወቅቱን የዋጀ የፋይናንስ አስተዳደር ቃለ ዐዋዲ ዝግጅት ደልዳላ መሠረት እንደሚጥል ተመልክቷል፡፡
 • በቅዱስ ሲኖዶስ የግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ለኹለተኛ ጊዜ በተገመገመውና ለትግበራ አመቺ የሚኾንበትን የመጨረሻ መልክ ይዞ እንዲዘጋጅ አቅጣጫ በተሰጠበት የቤተ ክርስቲያናችን መሪ ዕቅድ፣ ‹‹በመልካም አስተዳደርና በፍትሕ አሰጣጥ የመልካም አርኣያነት ግዴታን መወጣት›› ከቤተ ክርስቲያናችን ዘጠኝ የአገልግሎት አፈጻጸም ዕሴቶችና መርሖዎች (values and principles) አንዱ ኾኖ ተቀምጧል፡፡
 • ይኸው የመልካም አርኣያነት ዕሴትና መርሕ ግዘፍ ነስቶ መልክ አግኝቶ ይገለጽ ዘንድ፣ ቤተ ክርስቲያን የመንግሥተ እግዚአብሔር መሠረታዊ ተልእኮዋን ለመፈጸምና ለማፋጠን በመሣርያነት የምትጠቀምባቸው ተቋማዊ አደረጃጀቶቿ÷ ከሙስናና ወገንተኝነት የጸዱ፣ ፍትሐዊና በኹለንተናዊ መልካቸው ለዓለም ተቋማት የመልካም ምሳሌ መነሻና መድረሻ ኾነው ዘወትር እየተሻሻሉና እየዘመኑ መሔድ ይገባቸዋል፡፡ ለዚኽም ቋሚ ሲኖዶስ የፖሊሲ ውሳኔ የሰጠበት ዘመናዊው የኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት ጉልሕ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

የዜናውን ተጨማሪ መረጃዎች ይከታተሉ፡፡

Advertisements

6 thoughts on “ቋሚ ሲኖዶስ: ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዘመናዊው የኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት እንዲተከል ወሰነ፤ ለተቋማዊ ለውጥ ባለተስፋዎች የምሥራች፣ ለአማሳኝ ተቃዋሚዎች ኀፍረትና መርዶ ነው!!

 1. kuba Adugna September 23, 2014 at 12:27 pm Reply

  waaw congra.

 2. Anonymous September 23, 2014 at 2:34 pm Reply

  your style of presentation in spirit of hate turns the big news in to ‘yesefer bishishik’. please behave in a decent orthodox christian manner leaving the divisive kind of approach within the church administration. any way,welcome back.

 3. Anonymous September 25, 2014 at 5:57 am Reply

  Commenting the way of writing is not bad, even good for better communication, I agree in this fact. However, the most and crucial target should not be jumped. You leave no comment on the decision made by the Standing Synod, why????? You must answer for your self. welcome back!!!
  As to me, it is the will and hands of God to do so. We members and bodies of the church are very pleased of the decision.

  Abatochachinin ahunim yabertalin !!!!! Yebete kristianen tinsaei yasayen !!!!!!!!!

  Haile S. Ze Debre Berhan

 4. Anonymous September 25, 2014 at 6:34 am Reply

  ewenet kehone

 5. Anonymous September 26, 2014 at 7:26 am Reply

  Amnen ennikebel, yideregilin zendei entseliy, hule teteratari anihun !!!!!!

  Mewesenachew berasu melikt alew !!!!!!

  Gashaw ke kality

 6. Anonymous October 8, 2014 at 10:13 am Reply

  Oh thank you God . ye gahaneb dejochin degimo terarigo we de metubet endemiketachewu ergitegna nen. entsina enitsely
  .

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: