ፓትርያርኩ ከጥቂት አማሳኞች ምክር ይልቅ የብዙኃኑን ካህናትና ምእመናን ድምፅ ሰምተው ተገቢ ምላሽ እንዲሰጡ ተጠየቁ፤ ‹‹አለዚያ ውሳኔዎ ደብሩ በአንድ ዓመት ያገኘውን ሰላም ያውከዋል፤ እኛም ልጅ እርስዎም አባት አይኾኑንም››

St.Urael church bld complex

የደብረ ጽጌ ቅ/ዑራኤል ቤተ ክርስቲያንና ኹለገብ ሕንፃ

 

ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ በጉዳዩ ላይ እንደሚወያይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ትላንት ጥዋት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለተሰለፉ ከአንድ ሺሕ ለማያንሱ የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት፣ የካህናት፣ የሰንበት ት/ቤትና የምእመናን ተወካዮች አስታውቀዋል፤ የዛሬው የቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ የካህናቱንና ምእመናኑን ቀጣይ ርምጃ ይወስናል፡፡

 

 

 • ፓትርያርኩ በጥቂት አማሳኞች ምክር ላይ የተመሠረተ የሙስና ክሣቸውን በማስረጃ አስደግፈው እንዲገልጹላቸው የተማፀኗቸውን፤ ለአቤቱታ በሕዝብ ማመላሻ አውቶቡሶች፣ ታክሲዎችና የቤት መኪናዎች ተጓጉዞ የመጣውን ምእመንም በአባታዊ መልእክት እንዲያሰናብቱ የጠየቋቸውን አምስት ተወካዮች በግቢ ጥበቃ፣ በፖሊስና በጸጥታ ኃይል ለማስወጣት ትእዛዝ ሰጥተው ነበር፡
 • ፓትርያርኩ የደብሩን አስተዳዳሪ በሙሰኛነት በመክሠሥ የጠቀሱት ምክንያት፣ ሀገረ ስብከቱ የአስተዳዳሪውን ውጤታማ አመራር በመመስከር ካቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ጋራ መለያየቱና መፃረሩ፣ ጉዳዩ በርግጥም ቅን መነሻ የሌለውና በጥቅም ትስስር ላይ የተመሠረተ መኾኑን አጋልጧል፡፡
 • በፓትርያርኩ እንደ ሙስና የተጠቀሱት የገንዘብ ወጪዎች÷ በሀገረ ስብከቱ የታዘዙ፣ የሰበካ ጉባኤው ውሳኔ ዐርፎባቸው በሕጋዊ ሰነዶች የተደገፉና ፓትርያርኩም በቀጥታ የሚያውቋቸው እንደኾኑ ተመልክቷል፤ የፓትርያርኩን የቢሮ ዕቃዎች ለማሟላት ከደብሩ ወጪ የተደረገው አራት መቶ ሺሕ ብር ይገኝበታል፡፡
 • ከደብሩ ከ22 ሚልዮን ብር በመመዝበር የተጠረጠሩ አማሳኞች ተጋልጠው ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረጋቸውን ያስታወሱት የምእመናን ተወካዮቹ፣ ክሡ በአሳማኝ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ ከኾነ አስተዳዳሪው ከሓላፊነታቸው መነሣት ብቻ ሳይኾን በሕግ የማይጠየቁበት ምክንያት እንደሌለ ገልጸዋል፤ አካሔዱም በደብሩ ልማደኛ አማሳኞችና በሙስና ከተጨማለቁ በኋላ ያለተጠያቂነት በሚዘዋወሩ ሌሎች አለቆች ላይም ተፈጻሚ እንዲኾን ጠይቀዋል፡፡
 • ‹‹አለቃው ቅዱስ ናቸው ብለን አይደለም፤ ሊያጠፉ ይችላሉ፤ እስከ አኹን ከተመደቡት ግን እንደ እርሳቸው ያሉ አላየንም፤ ቆጠራው በይፋ ነው፤ የገባና የወጣውን ማንም በይፋ ያውቀዋል፤ ገቢው ኻያ ሚልዮን ብር ደርሷል፤ አገልግሎቱ ሥርዓት ይዟል፤ አገልጋዩ ቦታውን አግኝቷል፤ ሰዓታት ቆመው፣ ኪዳን አድርሰው፣ ቀድሰውና አቊርበው፣ ካህኑን ከምእመኑ አስማምተው ሕዝቡን አንድ አድርገው የሚመሩ እንደ እርሳቸው አይተንም አናውቅ፡፡››
 • ‹‹እስከ አኹን ገንዘባችን ተዘርፏል፤ እስከ አኹን ዑራኤል ተሽጧል፤ ከአኹን በኋላ አንድ ሌባ እዚያች ደጅ አይደርሳትም፤ ወጣቶች ቤተ ክርስቲያናችኹን አጥራችኹ ጠብቁ፡፡›› /የአካባቢውን ወጣቶች ያበረታቱ የአጥቢያው ተሰላፊ እናቶች/
Advertisements

3 thoughts on “ፓትርያርኩ ከጥቂት አማሳኞች ምክር ይልቅ የብዙኃኑን ካህናትና ምእመናን ድምፅ ሰምተው ተገቢ ምላሽ እንዲሰጡ ተጠየቁ፤ ‹‹አለዚያ ውሳኔዎ ደብሩ በአንድ ዓመት ያገኘውን ሰላም ያውከዋል፤ እኛም ልጅ እርስዎም አባት አይኾኑንም››

 1. Anonymous July 2, 2014 at 7:16 pm Reply

  amlak lebochen yastageselen

 2. Anonymous July 4, 2014 at 5:06 pm Reply

  Bewnet Egzyaber yefired

 3. Anonymous July 6, 2014 at 7:10 pm Reply

  ሸፍጠኞች ሁል ጊዜ የሚያሸንፉ ይመስላቸዋል ነገር ግን እግዚአብሔር ማሸነፍ አይችሉም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: