የጅማ ዩኒቨርስቲ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎች ለመጾም ተቸግረዋል፤ ‹‹የአምልኮ፣ የአለባበስና የአመጋገብ መመሪያ›› አፈጻጸም እንደ ሓላፊዎች እምነት የሚወሰን ኾኗል

 • ‹‹መመሪያው በኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ላይ በማተኮር በአድሏዊነት ይፈጸማል›› /ተማሪዎቹ/
 • ‹‹መንግሥት ለሙስሊም ኾነ ለክርስቲያን ተማሪዎች በልዩ ኹኔታ ምግብ እንዲዘጋጅ ፈቅዷል›› /የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሚያዝያ ፳፻፮ ዓ.ም. የመመሪያው አጸፋዊ ማብራሪያ/
 • ‹‹ዩኒቨርስቲው ያወጣው መመሪያ ላይ እንዲህ የሚል የለም፤ ሴኩላሪዝም ባለበት ዩኒቨርስቲና በዩኒቨርስቲው የሴኔት ሕግ መሠረት የሰኔን ጾም ይኹን ሌላውን ጾም የማጾም ግዴታ የለብንም፤ ዩኒቨርስቲው የራሱ ፕሪንስፕልና መመሪያ አለው፡፡›› /በአድሏዊነት የሚከሰሱት የተማሪዎች ዲን አቶ እውነቱ ኃይሉ/

(ሰንደቅ፤ ፱ኛ ዓመት ቁጥር ፬፻፶፰፤ ረቡዕ ፲፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

በጅማ ዩኒቨርስቲ የተለያዩ ካምፓሶች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎች በሥርዓተ እምነታቸው የተደነገጉ የዐዋጅ አጽዋማትን በመጾም ክርስቲያናዊ ግዴታቸውን ለመወጣት መቸገራቸውንና የትምህርት ተቋማት የአምልኮ፣ የአለባበስና የአመጋገብ መመሪያውን በአድሏዊነት በሚያስፈጽሙ ግለሰብ ሓላፊዎች ምክንያት የእምነት ነጻነታቸው እየተረገጠ መኾኑን ለሰንደቅ ገለጹ፡፡

በጅማ ዩኒቨርስቲ የዋናው ግቢ፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ የግብርናና እንስሳት ካምፓሶችና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ለሰንደቅ እንደተናገሩት፣ ከሰኔ 2 ቀን 2006 ዓ.ም. አንሥቶ የተጀመረውን የሐዋርያት ጾም /በተለምዶ የሰኔ ጾም/ በተማሪዎች ዲኑ በኩል ‹‹የሰኔ ጾም የሚባል የምናውቀው ነገር የለም›› በመባላቸው ምክንያት ሥርዓተ እምነታቸውን ለመፈጸም እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡

ጾመ ሐዋርያት/የሰኔ ጾም/ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሰባት ዓመት ዕድሜ በላይ የሚገኙ ምእመናንዋ እንዲጾሟቸው ካዘዛቸው ሰባት የሕግ/የዐዋጅ/ አጽዋማት አንዱ ነው የሚሉት ተማሪዎቹ፣ የጾም ምግብ ባለመዘጋጀቱ ጾማቸውን ለማፍረስ የተገደዱ ተማሪዎች እንዳሉና የተቀሩትም በጾም ከዋሉ በኋላ ዳቦና ውኃ ከመቅመስ በቀር የሚመገቡት እንደሌላቸው በምሬት ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ኅብረት በጉዳዩ ላይ ከዲኑ ጋራ ያደረገው ውይይትም በዲኑ ‹‹ማንም የፈለገውን ቢል አይዘጋጅም›› በሚል የተለመደ ጥላቻ የተሞላበት ዕብሪትና የሚያራምዱት ፕሮቴስታንታዊ እምነት የተጫነው አቋም ሳቢያ ውጤት እንዳላመጣ ጠቅሰዋል፡፡

በአጽዋማት ወቅት የጿሚ ተማሪዎችን ብዛትና ስም ዝርዝር ለተማሪዎች ዲኑ በማስታወቅ የጾም ምግብ በቁጥራቸው ልክ እንደሚዘጋጅላቸው ያወሱት ተማሪዎቹ፣ ከመመገብ ታቅበው በሚቆዩበት ሰዓት የማይጠቀሙበትን ኮታቸውን ከካፊቴሪያው በማውጣት በሰዓታቸው መመገብ ይችሉ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ከ2004 ዓ.ም. ዐቢይ ጾም ጀምሮ ግን ጥዋት በቁርስ ሰዓት ከሚያወጡት አንድ ዳቦ በስተቀር ከሌሎች እምነት ተከታዮች በተለየ የካፊቴሪያውን አገልግሎት ማግኘትና በጀታቸውን በአግባቡ መጠቀም እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡

የአምልኮ፣ የአለባበስና የአመጋገብ መመሪያው፣ በግቢው ውስጥ ሃይማኖትን የሚገልጽ ነገር ለብሶ መግባት እንደማይቻል የሚያዝዘውን ብናከብርም ከሌሎች እምነት ተከታዮች በተለየ ትኩረት የግቢው የጸጥታ አካላት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎችን በማሸማቀቅ እናደርገዋለን የሚሉት ቁጥጥር አድሏዊነት የሚታይበትና ፍትሐዊነት የጎደለው መኾኑን ገልጸዋል፡፡ mk gibi gubae students00

[በቀዳም ስዑር ዕለት ተማሪዎቹ በራሳቸው ላይ ቄጤማ እንዳሰሩ ወደ ሲገቡ ቄጤማውን እንዲያስወግዱ ታዝዘዋል፤ የበዓለ ትንሣኤ ሌሊት ከቅዳሴ በኋላዳ ግቢው ሲመለሱ ለክብረ በዓሉ የለበሱትን ነጭ የሀገር ልብስ እንደለበሱ ወደ ግቢው እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡ በመመሪያው መሠረት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሔዱ የለበሱትን ነጠላ ከዩኒቨርስቲው ግቢ በር ላይ አጣጥፈው ይዘው የሚገቡ ቢኾንም ያጣጠፉትን ነጠላ በትክሻቸው ጣል አድርገው ከታዩ በጥበቃ አባላት አጸያፊ ኃይለ ቃል ይሰነዝርባቸዋል፡፡

በአንፃሩ በሌሎች እምነት ተከታዮች ላይ (ማንነትን በግልጽ አያሳውቅም በሚል ከሰላምና ደኅንነት አጠባበቅ አኳያ ተከልክሏል የተባለውን ኒቃብ በሚያደርጉ ሙስሊም ተማሪዎች ይኹን እምነት ገላጭ ጥቅሶች ያለባቸው ቲሸርቶችን በሚለብሱ ፕሮቴስታንት ተማሪዎች) ምንም ዓይነት ቁጥጥር ሲደረግ እንደማይታይ ተገልጧል፡፡ በአለባበስና ሥርዓተ አምልኮ ረገድ በአድሏዊነትና ፍትሐዊነት በጎደለው የተማሪዎች አያያዝ ከፕሮቴስታንቱ የተማሪዎች ዲን አቶ እውነቱ ኃይሉ በተጨማሪ ስማቸው የሚነሣው የዩኒቨርስቲው የጸጥታ ሓላፊ ኢንስፔክተር ካሊድ አባ ተማም ናቸው፡፡

በሥርዓተ አምልኮ ረገድም የእምነታቸውን ክብር ለማስጠበቅ ባለፈው ዓመት በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ባቀረቡ 15 ተማሪዎች ላይ ተደራራቢ ግፍ መፈጸሙ ተመልክቷል፡፡ ለተማሪዎቹ ሰላማዊ ጥያቄ ፖሊስ የኃይል ምላሽ ከመስጠቱም ባሻገር በዩኒቨርስቲው የሥነ ምግባር ደንብ ስም ጨርሶ ከትምህርት ገበታቸው የተባረሩ፣ ለአንድና ኹለት ዓመት የታገዱ፣ ማስጠንቀቂያ የተላለፈባቸውና ከትምህርት ገበታቸው ጨርሶ ከመባረር አልፎ በተደራቢነት በዞን ፍ/ቤት ደረጃ ተከሰው ለእስራት የተዳረጉ ተማሪዎችም እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡]

ሰንደቅ በጉዳዩ ላይ በስልክ ያነጋገራቸው የተማሪዎች ዲን አቶ እውነቱ ኃይሉ፣ ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግ ዐዋቃለኹ፤ ሴኩላሪዝም ባለበት ዩኒቨርስቲና በዩኒቨርስቲው የሴኔት ሕግ መሠረት የሰኔን ጾም ይኹን ሌላውን ጾም የማጾም ግዴታ የለብንም፤ ዩኒቨርስቲው የራሱ ፕሪንስፕልና መመሪያ አለው፤›› ብለዋል፡፡

በትምህርት ተቋማት እንዲተገበር በፌዴራል መንግሥት ደረጃ በወጣው የአምልኮ፣ የአለባበስና የአመጋገብ መመሪያ መንግሥት፣ ‹‹አቅም በፈቀደ መጠን ለክርስቲያንና ሙስሊም ተማሪዎች በተለየ ኹኔታ ምግብ እንዲዘጋጅ›› መግለጹን በመጥቀስ ዩኒቨርስቲው በመመሪያው መሠረት ለምን የተማሪዎቹን ጥያቁ እንደማያስተናግድ የተጠየቁት አቶ እውነቱ፣ ‹‹ዩኒቨርስቲው ያወጣው መመሪያ ላይ እንዲህ የሚል የለም፤›› በሚል የመመሪያውን ተግባራዊነት የሚቃወም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

መመሪያው በሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እየተተገበረ የጅማ ዩኒቨርስቲ የሴኔት መመሪያ መንግሥት ሴኩላሪዝምን አሰፍንበታለኹ ከሚለው መርሖ ልዩ ስለኾነበት ምክንያት ሲጠየቁም ‹‹እኔ ስለ ጅማ ዩኒቨርስቲ ብቻ ነው የማውቀው፤ ከተማሪዎች ጋራም ተወያይተናል፤ እዚያም የሚያደርስ አይመስለኝም፤ ወደፊትም እንወያያለን፤›› ብለዋል፡፡

[የአምልኮ፣ የአለባበስና የአመጋገብ መመሪያው ‹‹በምንም መልኩ የዜጎችን የእምነት ነጻነት አይጋፋም›› ይላል፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሚያዝያ ፳፻፮ ዓ.ም. ያዘጋጀውና ሰሞኑን ለሚዲያ አካላት ሥልጠና የሰጠበት ሰነድ፤ ምክንያቱንም ሲያብራራ ‹‹ከመመሪያው አንጻር የትምህርት ቤት ማኅበረሰብና ተማሪዎች ማንንም እስካላወኩ ድረስ ሥርዓተ እምነታቸውን በግላቸው ተግባራዊ ማድረግን ይፈቅዳል፤›› በማለት ያስረዳል፡፡

መመሪያው በትምህርት ተቋማት ውስጥ እንዳይደረግ የሚከለክለው፥ በቡድን መጸለይን፣ ከአለባበስ አንጻርም ‹‹ማንነትን በግልጽ ለመለየት የማያስችል›› አለባበስን ነው፡፡ ከአመጋገብ አኳያም ማንኛውም ተማሪ የሌላውን መብት እስካልተጋፋ ድረስ በግሉ ጸልዮ መመገብ ይችላል፤ አቅም በፈቀደ መጠንም መንግሥት ለክርስቲያኑ ኾነ ለሙስሊም ተማሪዎች በተለየ ኹኔታ ምግብ እንዲዘጋጅ መፍቀዱን ሰነዱ ይገልጻል፡፡

ታዲያ፥ በረመዳን ቁርሱም ምሳውም ራቱም ተደምሮ ምሽት ላይ ለሙስሊሙ ተማሪ የሚሰጥበት፣ ክርስቲያኑ ጿሚ ተማሪ ግን ጥዋት ላይ ባወጣት አንዲት ዳቦ ለኹለት ወር ሑዳዴ የሚቀጣበትና በጀቱን የሚዘረፍበት በደል አልበቃ ብሎ ‹‹ለሰኔ ጾም ጨርሶ የጾም ምግብ አናዘጋጅም፤ የሰኔንም ይኹን ሌላውን ጾም የማጾም ግዴታ የለብንም›› የሚለው የእነ እውነቱ ኃይሉ – ኢንስፔክተር ካሊድ አባ ተማም አድሏዊ አሠራር ከየት የመጣ ነው?]
*******************************************************

በበጀት ዓመቱ መንግሥትና ገዥው ግንባር፣ ‹‹በመዋቅራችንና በሕዝባችን ውስጥ ዘርፈ ብዙ ንቅናቄ በመፍጠር አክራሪነት የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማነቆ እንዳይኾን›› የሚል ዓላማ በመያዝ፡- የመንግሥት መዋቅር አመራርና ሲቪል ሰርቪሱ ኹሉንም ሃይማኖት በእኩልነት የማገልገል አመለካከትና ተግባር የመገንባት፤ ሃይማኖት ነክ መልካም አስተዳደርን በመንግሥት መዋቅሮች የማረጋገጥ፤ የአምልኮ፣ የአመጋገብና የአለባበስ መመሪያውን በትምህርት ተቋማት ተግባራዊ በማድረግ ‹‹ከሃይማኖት፣ ከባህልና ከፖሊቲካ ተጽዕኖ የተላቀቁ መኾናቸውን የማረጋገጥ›› ግቦችን አስቀምጠው ነበር፡፡

የሴኩላሪዝም መርሖና የሴኔት ሕግ በሽፋንነት የሚጠቀስበት የጅማ ዩኒቨርስቲው የእነ አቶ እውነቱ ኃይሉና ኢንስፔክተር ካሊድ አባ ተማም አሠራር ግን ለወጉም ቢኾን ከፌዴራል መንግሥቱ መመሪያ እንዲሁም ለበጀት ዓመቱ ከተቀመጠው ዓላማና ከተጣለው ግብ ጋራ የተግባባ አይመስልም፡፡

አለመግባባት ብቻ ሳይኾን እንደ ጅማ ዩኒቨርስቲው ኹሉ ስማቸው ባልተጠቀሱ ሌሎችም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሓላፊነታቸውን ተገን በሚያደርጉ ግለሰቦች በቤተ ክርስቲያናችንና በኦርቶዶክሳውያን ላይ ጥቃቱና ጫናው በርብርብ መልክ የሚፈጸም አስመስሎታል፡፡

የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ኅብረት የጿሚ ተማሪዎችን ጥያቄ ይዞ ከተማሪዎች ዲን ጋራ ቢነጋገርም የተሰጠው ምላሽ ‹‹ማንም የፈለገውን ቢል አይዘጋጅም›› የሚል በመኾኑ ከጿሚ ተማሪዎቹ ውስጥ በኢሕአዴግ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ተማሪዎች አቤቱታቸውን ለግንባሩ አባል ድርጅቶች ጽ/ቤቶቹ እስከ ማቅረብ ደርሰዋል፡፡ ‹‹ይህ ብጥብጥ ለመፍጠር የተፈለገበት ጉዳይ ስለኾነ ለበላይ እናመለክታለን፤›› ያሉት ጽ/ቤቶቹ የዩኒቨርስቲውን ሓላፊዎች ካነጋገሩ በኋላ ‹‹ከአቅማችን በላይ ነው›› ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

የኾነው ኾኖ ከዚህ ውጥረት ተጠቃሚው ማነው? ‹‹ሰላማዊ የመማር ማስተማር ተልእኮን ለማስፈጸም የተነደፈ ነው›› የተባለውን መመሪያ በመጣስ የእምነት ነጻነትን እየገደበ ያለውስ ማነው? ‹‹አክራሪዎችና ጽንፈኞች›› እያሉ ሌላውን ከማሳጣትና ‹‹ተመልሶ ባደረ ጥያቄ አንዳንድ የአፈጻጸም ችግሮችን እያጋነኑ ያደናግራሉ›› በሚል ከመክሠስ በፊት እንዲህ ያሉ ሓላፊዎችን ከመዋቅሩ በፍጥነት በማጽዳትና የተባለውን ‹‹የሴኩላሪዝምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ›› በአግባቡ መመለስ አይበጅም ወይ?

ከሚለፈፈው ‹‹የፀረ አክራሪነት ትግል›› አኳያ ለዓመቱ በተያዘው ዕቅድና በተጣሉት ግቦች መሠረት ፈጻሚ አካላት ሓላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ክትትልና ድጋፉ የግድ ሊደረግ ይገባል፡፡mk gibi gubae studentsበሌላ ገጹ ጉዳዩ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን በየሰበቡ አነሣስቶ ወደ ቀውስ በማስገባት በማኅበሩ ላይ ጠቅላላ ምት የማሳረፍ ፍላጎት እንዳለ ማሳበቁም አልቀረም፤ ማኅበሩ ግን አኹን በጅማ ማእከል የግቢ ጉባኤያት መዋቅሩ በኩል እንዳደረገው ሃይማኖታዊ መብታቸውን የሚጠይቁ የዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ አካልና የግቢ ጉባኤያቱ አባላት የኾኑ ተማሪዎችን በማረጋጋት ጥያቄያቸው ምላሽ እንዲያገኝ እየሠራ መኾኑ ነው የሚታወቀው፡፡

ማኅበሩ፡-

 • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በግቢ ጉባኤያት አደራጅቶና በቂ ዝግጅት አድርጎ ትውልዱ ከሃይማኖቱ እንዳይናወጽ፣ ከሥርዓተ እምነቱ እንዳይወጣ፣ ታሪኩንና ባህሉን እንዳይዘነጋ የማስተማር፤
 • ባለንበት ዘመን በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚካሔደውን የተቀናጀ የሃይማኖት ወረራ ለመከላከል ሃይማኖቱን የሚያውቅና የሚጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያኑን የሚከባከብና በቅንነት የሚያገለግል፣ ሀገሩን የሚወድ ግብረ ገብና ብቁ ዜጋ የማፍራት፤
 • በመንፈሳዊና በዘመኑ ትምህርት የበሰለው የኅብተረሰብ ክፍል በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥር ኾኖ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲፈጽምና የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ ሥርዓት ባለው መንገድ እንዲያበረክት በሚያስችል ኹኔታ የማደራጀትና ለተልእኮ የማዘጋጀት ሓላፊነት ያለበት ነውና!!
Advertisements

33 thoughts on “የጅማ ዩኒቨርስቲ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎች ለመጾም ተቸግረዋል፤ ‹‹የአምልኮ፣ የአለባበስና የአመጋገብ መመሪያ›› አፈጻጸም እንደ ሓላፊዎች እምነት የሚወሰን ኾኗል

 1. Anonymous June 19, 2014 at 12:33 pm Reply

  የፕሮቴስታንት መጫወቻ ሆነን መቅረታችን እጅግ ያሳዝናል፡፡ አሁንስ ትዕግስት አይሉ ምን ዝምታችን ገደቡን አልፎ እየሄደ ነው፡፡ ሞቶ ምድርን ያሟሸ የለም፡፡ ብንፈራውም አይቀርልንም፤ እንሞታለን ሞታችን ከንቱ እንዳይሆን ዋጋ ከፍለን ድምፃችንን እናሰማ፤ ሰው ባይሰማን የፈጠረን ቸል አይለንም፡፡ አሁንስ በዛዛዛዛዛ!!!!!! የጅማ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የሠለስቱ ደቂቅን ኣርኣያነት ተግባራዊ አድርጉ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡፡

  • Anonymous June 20, 2014 at 6:09 pm Reply

   Tew Tew ayhonim. Ende selesitu dekik lemehon ayzoh berta bay ayasfeligim. Yalibeselu wetatoch Tiyakeyachew tikikil bihonim mfetehew gin endih endalkew semaet hunu belo ayhonim. Egziabher mneged alew mfetehy yisetal. Alkisu, anbu yishalal

 2. nigus June 19, 2014 at 2:54 pm Reply

  be orthodox lay andm sew tatun endaysenezir!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  • Anonymous June 19, 2014 at 3:52 pm Reply

   EGZIABHER ytadegacihu wegenoche

 3. Neway kassahun June 19, 2014 at 3:54 pm Reply

  Yejimmanem gubae menekakat gemeru?

 4. Anonymous June 19, 2014 at 4:50 pm Reply

  wey jemma enedegen ensu men yadregu……

 5. Anonymous June 19, 2014 at 9:33 pm Reply

  Egziabher yrdan

 6. abebaw June 20, 2014 at 6:36 am Reply

  Tseliu

 7. Anonymous June 20, 2014 at 6:54 am Reply

  ክርስቲያኖች የጾም ምግብ ከተከለከሉ መናፍቅ ወይም ኢአማኒ የሚሆኑ መስሏቸው ከፈጣሪ ጋር ያለያዩን መስሏቸው ስለሆነ አትፍረዱባቸው ይህ የዲያብሎስ አስተሳሰብ ነው፡፡ ከዚሁ የምንረዳው ዲያብሎስ ክንዶቹን ሲያስተባብር ነው፡፡ የእውነተኛዋን ሃይማኖት ተከተታዮች በፈተና ለመጣል፡፡ ነገር ግን ዝናሩን ይጨርሳል እንጂ የድል ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ በቤተክርስቲያናችን የቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ታሪክ ከዚህ በላይ ብዙ ያስተምረናል፡፡ ከእነርሱ ይልቅ ከእኛ ጋር ያሉት ብዙዎች ናቸው ፡፡ ጸንታችሁ ቁሙ፡፡ ተግታችሁ ጸልዩ፡፡ ጠላት ሲበረታ በሃይማኖት የሚጸናው ህዝብ ይበዛል፡፡ ሰላማዊ ጥያቄ ብቻ አሰሙ፡፡ ፊት ለፊት አትጋፈጡ፡፡ አልሰማም ያለውን አካል ጊዜው ሲደርስ ፈጣሪ እንዲሰማ ያደርገዋል አሊያም ከቦታው ያነሳዋል፡፡ ይህ አዲስ ነገር አይደለም ፡፡ የፈጣሪ ቁጣ እንዲውርድ አትቸኩሉ ፡፡ ለፈጣሪ አሳስቡ እንጂ ራሳችሁን ከመጠን ያለፈ አታስጨንቁ፡፡ ማንም በምግብ ብቻ አይኖርም፡፡ ደግሞም ያጋጠማችሁን ጊዜያዊ ችግር ለአባቶች ንገሩ መፍትሔውን ከእነርሱ ታገኛላችሁ፡፡

 8. Anonymous June 20, 2014 at 7:49 am Reply

  አረ ግፍ ነው ወገን!!!

  እግዚአብሄር ስራዉን ይሰራል ከቶ ቸል አይለንም!!!

 9. ADDIS June 20, 2014 at 10:21 am Reply

  ejig betam yasazinal amlak yrdan

 10. Abebe Beyene June 20, 2014 at 10:39 am Reply

  . . . ግን ያሁኑ ይባስ እስከ 1991 ዓ.ም. ድረስ በጅማ ዩኑቨርስቲ ግብርና ፋኩሊቲ የዱሮው እርሻ ኮሌጅ የልደትና ትንሳኤ በዓልን በኮሌጁ ውስጥ መዝሙር አጥንተን፣ልዩ ልዮ መንፈሳዊ ዝግጅቶችን አድርገንና ጾመን ያጠራቀምንው የዳቦ ዱቄት፣ሰኳርና ማርማላታ በተማሪ ቁጥርና በቀናት ታስቦ ስለሚሰጠን ጸበል ጸድቅ (ዳቦ ኩኪስ ለስላሳ መጠጥ) በማዘጋጀት የሀገረ ሰብኩቱን ሊቀ ጳጳስ፣ የሰባቱ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች መምህራንናና የሁሉንም ሰ/ት/ቤት አባላት ጋብዘን በወቅቱ በአዲሱ ካፍቴሪያ በበዓሉ ምክንያት በልዩ መስተንግዶ የተዘጋጀውን ምሳችንን ከእንግዶቻችን ጋር ተጋርተን በመመገብ በዓሉን ከቀኑ 7፡00 እስከ 11፡00 እናከብር ነበር፡፡

  ታዲያ በዚንያ ወቅት የኛን አይተው የበዓል ማክበሪያ ዱቄት ሰኳርና ማርማላታ ይሰጠን ብለው ጠይቀው እነሱ እኮ ሲጾሙ ስላልተጠቀሙት ነው እናንተ ስትጾሙ መቼ አተረፋችሁ ተብለው ነገር ግን ነገሩ ኦርቶዶክስ ተማሪዎች የሚገባቸውን ስለሰጠን የመጣ የተቃውሞ ጥያቄ ነው ተብሎ ስለ ግቢው ለሰላም ሲባል ተሰጣቸውና በአል አከበሩ፡፡

  በማስከተል ሌሎቹ በ1991 ዓ.ም. የትንሳኤ በዓል ለማክበር የመስተንግዶ ሥራው ተጠናቆ አዳራሽ ለማስዋብ ዲኮር ተገዝቶ አገር ሰላም በማለት ስቅለትን በቤተክርስቲያን ስናከብር ውለን ስንመጣ ትንሳኤን በካፌ አታከብሩም ተባለ ለምን ሲባል ፕሮቴስታንቶች ፓስተር ጠርተናል እስፔስ ለቅዳሜ ማታ ይፈቀድልን ብለዋል ይህም ከእናንተ ስላዩ ነው ተባልን፡፡ በወቅቱ ታላቅ ጭንቅ ነበር ግን ያሁኑ ይባስ፡፡

  በወቅቱ ጉዳዩን የሚያስተባብሩት ታላላቅ ወንድሞች ቅድስ፣ዲ/ን ጊደይ እና ሌሎችም ነበሩና በትህትናና በትዕግስት የሚመለከተውን አካል ተማጽነውበ1991 ዓ.ም. ለመጨረሻ ጊዜ በዓል በግቢ አዳራሽ ተፈቅዶልን አከበርን፡፡ በሚቀጥለው ዓመት (1992 ዓ.ም) በግቢ ባልኖርም ለትንሳኤ በዓል ተገኝቼ በወቅቱ የነበሩ እህቶችና ወንድሞች ያዘጋጁትን ጸበል ጸድቅ በቤተክርስቲያን ወስደው በደብረ መዊዕ መድሐኔአለም ቤተ ክርስቲያን ትንሳኤ እንደተከበረ አስታውሳለሁ፡፡

  ታዲያ ነገሮች ከቀን ቀን እየተለወጡ መጡና ይህ መጥፎ ዜና ስሰማ ውስጤ አዝኖ ያሁኑ ይባስ አሰኘኝ፡፡ ሁሉ የሚቻለው አምላክ ለወንድሞቻችንና እህቶቻችን ብርታትን እንዲሰጣቸው ከልብ እመናለሁ፡፡

  ገ/ሥላሴ

   

 11. Anonymous June 20, 2014 at 10:47 am Reply

  NEGERU ENDIH NEW SEW BE EGZIABHER KAL CHIMIR ENGI BE MEBIL BICHA AYNORIM GIN YE TEWAHIDO LIJOCH HULACHINIM BINASIBIBET TIRU NEW

 12. Anonymous June 20, 2014 at 11:12 am Reply

  egziabher hulem kegna gar new aniferam tenkiru wedimoche ehitoche egziabher yatsnan

 13. Anonymous June 20, 2014 at 11:18 am Reply

  kegna gar yale kenesu gar yalehun yibelthal bertu ,tsinu eske fitsamehuwu

 14. sim June 20, 2014 at 11:30 am Reply

  ይህ በሀይማኖታችን ላይ የመጣ ችግር ነዉ እና አባቶች ሊቃነ ጳጰጳሳት ዝም ሊሉት አይገባም ከሚመለከተዉ አካል ጋር ተነጋግረዉ መፍትሔ ሊሰጠዉ ይገባል አትፁሙ ከማለት በላይ ምን ልንባል ነዉ የተሰጣችሁን አደራ ጠብቁ

 15. teame haile June 20, 2014 at 2:16 pm Reply

  tewahido malet fetenan malef ayadagitewm! egziabher talak new.

 16. Anonymous June 20, 2014 at 2:45 pm Reply

  Ere yemengest yale , eunetu na kalid yrasacheun mengest mesrteual ande belun……

 17. Anonymous June 20, 2014 at 4:51 pm Reply

  endezih andu fetena newu andu tigist andu endezih endezih eyalin beka ezih deresn nege ethiopian pente ena esilam yiwerisatal

 18. Anonymous June 21, 2014 at 8:41 am Reply

  endazhe mehone yelbatem 1 haymanoet equei new mne asflegea musilm orthodox yamhale enda

 19. Anonymous June 21, 2014 at 12:04 pm Reply

  ይህ በሀይማኖታችን ላይ የመጣ ችግር ነዉ እና አባቶች ሊቃነ ጳጰጳሳት ዝም ሊሉት አይገባም

 20. Anonymous June 21, 2014 at 1:45 pm Reply

  egiziabher amilak yitebikachihu

 21. Eden Mekbib June 21, 2014 at 2:49 pm Reply

  አይ ይች ምድር…………ግን ቤተክርስቲያን ሆይ ምነው መከራሽ በዛ? ምነው ረጋጭሽ በምድር ሁሉ መጥፋትሽን የሚሹ እንደ አሸን ፈለጉ?ወተት ከመስጠት ውጭ ምን ያጎደልሽባቸው ነገር አለ….ብቻ ግን ይዘገያል እንጂ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም
  በያለንበት ነቅተን መዘጋጀት በልዑል እግዚአብሂር ቸርነት በእመቢታችን ምልጃ በቅዱሳን ጥበቃና ፀሎት ታሪክ ይቀየራል….
  አለን ኡሌም በእግዚአብሔር አለን

 22. Anonymous June 21, 2014 at 3:34 pm Reply

  Is there any plan to visit S. Sudan refugees in Ethiopia? This is something the church needs to orginize real quick. No preaching or teaching. Just feed and let them drink the hungry and thristy, kiss their chucks, wash their legs, sit, talk, laught and cry with them. Then, when their suffering subsides, they will remember the blessings they received in Jesus name. They really need an honest help, not politically motivated one. They suffered way too long.

  • Anonymous June 21, 2014 at 5:53 pm Reply

   እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው

 23. Eden Mekbib June 21, 2014 at 5:43 pm Reply

  OH God May God be with them,If you can try to Contact D/K Daniel Kibret or Mahibere Kidusan ,Let me know if you need there phone or email address and i will try to get for you Please let me know..May God be with them !!!!!

 24. Misikir June 21, 2014 at 8:57 pm Reply

  Linega sil yichelmal

 25. Dawit June 22, 2014 at 6:49 pm Reply

  ለተዋሕዶ ክርስቲያኖች ብቻ ምግብ ማዘጋጀት የሚችል ወገን ፈልገው ማስተባበር ይኖርባቸዋል። እንዲያውም ኦርቶዶክሳውያን ወደ ካፊቴሪያው ሄደው ከመመገብ መቆጠብ፡ ነገ ሊመርዟቸው እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው! ጸረ-ተዋሕዶዎች ግን እራሳቸውን ለገሃነም እሳት በማዘጋጀት ላይ ናቸው ነው።

 26. Anonymous June 23, 2014 at 10:47 am Reply

  _______________መዝሙር፡51፡(52)።______________
  ለመዘምራን፡አለቃ፤ኤዶማዊው፡ዶይቅ፡መጥቶ፡ለሳኦል፦ዳዊት፡ወደአቢሜሌክ፡ቤት፡መጥቷል፡ብሎ፡በነገረው፡ጊዜ ፤የዳዊት፡ትምህርት።
  1፤ኀያል፡ሆይ፥በክፋት፡ለምን፡ትጓደዳለኽ፧ዅልጊዜስ፡በመተላለፍ፧
  2፤አንደበትኽ፡ኀጢአትን፡ያስባል፤እንደ፡ተሳለ፡ምላጭ፡ሽንገላን፡አደረግኽ።
  3፤ከመልካም፡ይልቅ፡ክፋትን፥ጽድቅንም፡ከመናገር፡ይልቅ፡ዐመፃን፡ወደድኽ።
  4፤የሚያጠፉ፡ቃልን፡ዅሉ፥የሽንገላ፡ምላስን፡ወደድኽ።
  5፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ያፈርስኻል፤ከቤትኽም፡ይነቅልኻል፥ያፈልስኻልም፥ሥርኽንም፡ከሕያዋን፡ ምድር።
  6፤ጻድቃን፡አይተው፡ይፈራሉ፤በርሱም፡ይሥቃሉ፥እንዲህም፡ይላሉ፦
  7፤እግዚአብሔርን፡ረዳቱ፡ያላደረገ፥በባለጠግነቱም፡ብዛት፡የታመነ፥በከንቱ፡ነገርም፡የበረታ፡ያ፡ሰው፡እንሆ ።
  8፤እኔስ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡እንደ፡ለመለመ፥እንደ፡ወይራ፡ዛፍ፡ነኝ፤ለዓለምና፡ለዘለዓለም፡በእግዚአብሔር ፡ምሕረት፡ታመንኹ።
  9፤አድርገኽልኛልና፥ለዘለዓለም፡አመሰግንኻለኹ፥በቅዱሳንኽም፡ዘንድ፡መልካም፡ነውና፥ስምኽን፡ተስፋ፡አደርጋ

 27. Ermias June 23, 2014 at 10:48 am Reply

  _______________መዝሙር፡51፡(52)።______________
  ለመዘምራን፡አለቃ፤ኤዶማዊው፡ዶይቅ፡መጥቶ፡ለሳኦል፦ዳዊት፡ወደአቢሜሌክ፡ቤት፡መጥቷል፡ብሎ፡በነገረው፡ጊዜ ፤የዳዊት፡ትምህርት።
  1፤ኀያል፡ሆይ፥በክፋት፡ለምን፡ትጓደዳለኽ፧ዅልጊዜስ፡በመተላለፍ፧
  2፤አንደበትኽ፡ኀጢአትን፡ያስባል፤እንደ፡ተሳለ፡ምላጭ፡ሽንገላን፡አደረግኽ።
  3፤ከመልካም፡ይልቅ፡ክፋትን፥ጽድቅንም፡ከመናገር፡ይልቅ፡ዐመፃን፡ወደድኽ።
  4፤የሚያጠፉ፡ቃልን፡ዅሉ፥የሽንገላ፡ምላስን፡ወደድኽ።
  5፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ያፈርስኻል፤ከቤትኽም፡ይነቅልኻል፥ያፈልስኻልም፥ሥርኽንም፡ከሕያዋን፡ ምድር።
  6፤ጻድቃን፡አይተው፡ይፈራሉ፤በርሱም፡ይሥቃሉ፥እንዲህም፡ይላሉ፦
  7፤እግዚአብሔርን፡ረዳቱ፡ያላደረገ፥በባለጠግነቱም፡ብዛት፡የታመነ፥በከንቱ፡ነገርም፡የበረታ፡ያ፡ሰው፡እንሆ ።
  8፤እኔስ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡እንደ፡ለመለመ፥እንደ፡ወይራ፡ዛፍ፡ነኝ፤ለዓለምና፡ለዘለዓለም፡በእግዚአብሔር ፡ምሕረት፡ታመንኹ።
  9፤አድርገኽልኛልና፥ለዘለዓለም፡አመሰግንኻለኹ፥በቅዱሳንኽም፡ዘንድ፡መልካም፡ነውና፥ስምኽን፡ተስፋ፡አደርጋ

 28. Anonymous June 26, 2014 at 12:21 pm Reply

  ክርስቲያናዊ ስርዓት የዲያቢሎስና የተከታይ ጀሌዎቹ የዘወትር ጭንቀትና ስቃይ እንደሆነ መረዳት ይገባናል፡፡ለምን ይህንን አደረጉ ማለት አይገባንም ምክንያቱም የሚያሰማራቸው ሰይጣን እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደለም፡፡ለዚህም ያባታቸውን የሰይጣንን ግብር ለመፈፀም ይፋጠናሉ፡፡ በይሁዳ መልዕክት ላይ እንደተፃፈው እነርሱ አስቀደወመው ለዚህ የተመረጡ /የተመደቡ/ ናቸውና፡፡፡፡እኛ ግን እንደ ዲያቢሎስ ልጆች በስጋዊ አስተሳሰብ መጓዝ አይገባንም፡፡ከአምላካችን የተማርነው እኮ ሰይፍህን ወደ አፎቱ መልሰው የሚል ቃልን ነው፡፡ይልቅ ወደፈተና እንዳንገባ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡አሁን ነው በፍቅር የማሸነፍ ክርስቲያናዊ ስራችንን መስራት የሚገባን፡፡ፈተናችን እዚህ ላይ ነውና፡፡ እባካችሁ ፈተናን አንጥላ የብርታታችን ምንጭ ነውና ነገር ግን ፈተናውን የማልፍበት ልቦናና ሀይል ስጠኝ ብለን እንማፀን፡፡ አንዳንዴም ፈተና ለቅጣት ይመጣልና ወደራሳችን እናስብ ሀጥያታችንን እንመልከት ፈጥነንም ወደ ንሰሀ እንቅረብ ያኔ የሰይጣን ሀይል እንደጉም በኖ ይጠፋል፡፡አሁንስ በዛብን፤ ትዕግስታችን አለቀ፤በቃን፤ሰማዕት እንሁን…..ወዘተ የክርስቲያን አመለካከት ሳይሆን ክርስትናን ያልተረዱ ሰዎች አስተሳሰብ ነው፡፡

 29. Anonymous June 26, 2014 at 10:45 pm Reply

  egziabher zimitaw legizew new .

 30. Anonymous July 9, 2014 at 6:20 pm Reply

  Hulachinm tegten entseliy EGZIABHER srawn yiseral.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: