እነዶ/ር ሺፈራው ማኅበረ ቅዱሳንን የሚወነጅሉበት የአክራሪነት ክሥ ወደ ‹‹የጎዳና ላይ ነውጥ ማነሣሣት›› ተጠናከረ

sendek newspaper sene 04 2006 E.C000

ይህ የዛሬ ረቡዕ፣ ሰኔ ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ሰንደቅ ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘገባ ነው፡፡ ዘገባው÷ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሚያዝያ ወር ፳፻፮ ዓ.ም ‹‹አክራሪዎች/ጽንፈኞች በተሳሳተ መንገድ ሃይማኖታዊ ይኹንታን ለማግኘት በሕዝባችን ውስጥ የሚያነሷቸው የማደናገርያ መልእክቶችና ማብራሪያቸው› በሚል ርእስ ባዘጋጀውና በቅርቡ በአዳማ ከተማ ለሚዲያ ባለሞያዎች በሰጠው ሥልጠና ላይ ተመሥርቶ የቀረበ ነው፡፡

ሰነዱ፣ ሚኒስቴሩ በመጋቢት ወር አጋማሽ ማኅበረ ቅዱሳንን አስመልክቶ በሚዲያዎች ከተላለፉት ዘገባዎችና ከቀረቡት ጽሑፎች በመነሣት በከፍተኛ ሓላፊዎች የተመራ ግምገማ ካደረገ በኋላ ‹‹በማኅበሩ የመሸገ አክራሪ ኃይል እንዳለ የተያዘውን አቋም በማጽናት ማኅበሩን ግን ለማፍረስ የተደረገ እንቅስቃሴ እንደሌለ ማብራራት›› በሚል የተሰጠው አቅጣጫ የተካተተበት እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡ማኅበሩ ውስጥ በመሸጉ የፖሊቲካ ዓላማ ባላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ‹‹አሉባልታ ይነዛሉ፤ ሕዝቡን ያደናግራሉ›› የተባሉት የኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ከአጀንዳው አኳያ ቅድሚያውንና የበላይነቱን የያዙበት ኹኔታ ከግምገማው አነጋጋሪ ነጥቦች አንዱ እንደነበር ታውቋል፡፡

በሰነዱ፣ የበላይነት የተያዘባቸውን መረጃዎች በበቂ ለማስተባበል አልያም በወረዳና በክፍላተ ከተሞች ደረጃ የግንባሩ አደረጃጀቶች በተሳተፉበትና በቅርቡ በተካሔደው ማኅበረሰብ አቀፍ ውይይት ፍረጃውና ትንታኔው ለአመራሩና አባሉ እንኳ አሳማኝ ያልኾነ የአክራሪነት ክሥ በማኅበሩ ላይ የቀረበበት ኹኔታ በማንኛውም መገለጫው ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርግ አቀራረብ አለመታየቱ በሥልጠናው ተሳታፊዎች ተገልጧል፡፡

‹‹የጎዳና ላይ ነውጥ ለማነሣሣት ሁከትና ብጥብጥ የሚሰብኩና የሁከትና ብጥብጥ መንገድን የሚቀይሱ›› ግለሰቦችና ቡድኖች በማኅበሩ ጥላ ሥር መሸሸጋቸውንና በማኅበሩ መወገዝ እንዳለባቸው የሚገልጽ የተጠናከረ ክሥ የቀረበበት ሰነዱ፣ ‹‹የመንግሥት ፍላጎት ማኅበሩ ከእኒህ አካላት ራሱን እንዲያጸዳ ነው፤›› ብሏል፡፡ ‹‹ማኅበሩን ለማዳከምና ለማፍረስ መንግሥት እንደሚንቀሳቀስ ተደርጎ የሚቀርበው አሉባልታ ቀድሞ በማስጠንቀቅ ከተጠያቂነትና ከሕግ የበላይነት አሠራር ለማምለጥ ይጠቅመናል የሚል ስልት ከኾነ የተሳሳተ አመለካከት ይኾናል፤›› ሲልም አሳስቧል፡፡

 • በኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች በቀረቡ ዘገባዎችና ጽሑፎች ላይ ተመሥርቶ በሚ/ር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው በተመራው የሚኒስቴሩ ግምገማ፣ የተላለፉት መረጃዎች ሐሰት እንደሌለባቸውና እነዶ/ር ሺፈራው በፀረ አክራሪነት ትግሉ አያያዝ ላይ ድክመት እንዳለባቸው ማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡
 • የግንባሩ አመራሮችና አባላት ጭምር የተቃወሙት የእነዶ/ር ሺፈራው ማኅበሩን በማዳከም ቤተ ክርስቲያንን የማቀጨጭ የአክራሪነት ፍረጃና መፍቀረ ፕሮቴስታንታዊ ብሎግ መር ትንታኔ የግንባሩን ድርጅታዊ መዋቅር ለማይቀለበስ አደጋ ሊያጋልጠው እንደሚችል ግንዛቤ ተወስዷል፡፡
 • ‹‹ከማኅበሩ ጋራ የተጀመረው ውይይት መቋረጡ ተገቢ አልነበረም፤ በውይይት ይዘን መሔድ ነበረብን፡፡›› /ግምገማው ያመለከተው ድክመት/
 • የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ አስገዳጅ ኹኔታ በመፍጠርና በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ለሚያካሒዱት ዘመቻ ‹‹በቅርብ ክትትል እገዛ እንደሚደረግላቸው›› በዶ/ር ሺፈራው እንደተገለጸላቸው ተናግረዋል – ‹‹አንዳንዶቹን ጳጳሳት አስቀድመን አስጠርተን አስወርድንባቸው፤ አባ እስጢፋኖስ ራሳቸው ተነሥተው ለቅቄአለኹ እንዲሉ አስደረግናቸው፤ ታዲያ ፓትርያርኩ እስከ ጥቅምት ሲኖዶስ ድረስ ሥራ አስኪያጅ [የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት] ኹነኝ ብለው አላስቀምጠኝ አሉ፤ ዶ/ር ሺፈራው በቅርብ ክትትል ጥበቃ የሚደረግልህ ወዳጃችን ነኽ አለኝ፤ ማኅበረ ቅዱሳንም ሐዘን ላይ ነው፤ ሕንፃው ንብረታችን ነው፤ ልቀቁልን ብለን እሪ ልንል ነው፤ መንግሥትም በትኑ ብሎ ለአመራሩ መመሪያ ይሰጠዋል፡፡››

/የአማሳኞቹ ቀንደኛ አስተባባሪ የኾነው ‹ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ
ከተናገረው/

 • ‹‹ከዚኽ በፊት ተደፍቀው የነበሩ ሃይማኖቶች የተረጋገጠላቸውን መብት ከሕገ መንግሥታዊ መርሖ ባፈነገጠ መልኩ በመጠቀም ሌላ ገጽታ ያለው የተዛባ የሃይማኖቶች ግንኙነት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ግለሰቦች፣ በፌዴራል ሥርዓቱ የተረጋገጠውን የሃይማኖት እኩልነት ምቹ ኹኔታ በመጠቀም ራሳቸው የሚከተሉት እምነት የበላይነት እንዲኖረው በስፋት ሲረባረቡ ይገኛሉ፡፡››

ዶ/ር ኃይለ ሚካኤል አበራ ‹‹አዲሲቷ ኢትዮጵያና የሃይማኖት
ብዝኃነት አያያዝ›› በሚል ርእስ ካቀረቡት ጽሑፍ የተወሰደ ነው፡፡
ዶ/ር ሺፈራውና የመሰሏቸው የመንግሥት ሥልጣንን በመጠቀም
ፕሮቴስታንታቲዝምን ለሚያደላድሉበት የሸፍጥ ቁመና በገላጭነት ቀርቧል፡፡

 • ‹‹መንግሥት በሃይማኖት ነክ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች የሚሠሩ ባለሥልጣናቱን ሚዛናዊነት በቅርበትና በየጊዜው መከታተልና መፈተሽ ይኖርበታል፤ አለበለዚያ አደጋው ለራሱ ነው፡፡›

/ከጥር ፳ – ፳፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በደሳለኝ ሆቴል የኢትዮጵያ
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠርቶት በነበረውና በዶ/ር ሺፈራው
በተመራው ውይይት በታየው የተሳትፎ ዕድል አሰጣጥ ግልጽ አድልዎ
ሳቢያ መድረኩን ጥለው የወጡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት
ጽ/ቤት ከፍተኛ ሓላፊዎች ከሰጡት አስተያየት/

Advertisements

26 thoughts on “እነዶ/ር ሺፈራው ማኅበረ ቅዱሳንን የሚወነጅሉበት የአክራሪነት ክሥ ወደ ‹‹የጎዳና ላይ ነውጥ ማነሣሣት›› ተጠናከረ

 1. Anonymous June 11, 2014 at 2:34 pm Reply

  ኩልክሙ መወድስ

  ማእረረ ሰላማ ስርናይ ፡ቃለ-ተዋህዶ፡ እፎኑ ፈድፈዱ ፡ወበዝኁ ጸላዕትኪ፤
  እለ ይትሜነዩ ወትረ፡ ከመ ያጥፍዑኪ፤
  ውስቴትኪ፡ ዕፄ-ተሐድሶ ፡እስመ ወጽአ ፡ብኪ፤
  ወወጠነ አማስኖ፡ እንዘኬ ይመትር፡ ምሥጢራተ ወንጌል ሥረወኪ፤
  ሦክሂ አማሌቃዊ፡ እንተ በቆለ ድኅሬኪ፤
  ሠጠጠ ወረገዘ ፡ ምዕመናነ አቁፅለኪ፤
  ወዝንቱሰ ይትርፍ ፡ እንተ በሙስና የአኪ፤
  መንግሥተ ብሔር በረደ-ጊሜ፡ ያንሶሱ በላዕሌኪ፤
  እስመ ከመ ሃሎ ኢዖቀ ፡ እም አምላከ ራማ ኃይልኪ፤
  መንግሥተ ብሔር በረደ-ጊሜ፡ ያንሶሱ በላዕሌኪ፡፡

  ጎጃሜው ከጎጃም

  • Annonyname June 12, 2014 at 8:20 am Reply

   ዲንቅ ነው አየው ይበሉ!!!!!

  • weg June 14, 2014 at 1:38 pm Reply

   Gojamew, translation please; I am lazy didn’t learn Geez. The only Geez I know is Abunezebesemayat.

   • Anonymous June 15, 2014 at 2:11 pm

    Dear weg, this is:
    ትርጉም፡
    የሠላማ( ከሣቴ ብርሃን) አዝመራ የሆንሽ የተዋህዶ ቃል / ስንዴ ሆይ! ያጠፉሽ ዘንድ ሁል ጊዜ የሚመኙ ጠላቶችሽ ምንኛ ፈጽመው በዙ ?
    ከውስጥሽ ተሐድሶ / ትል ወጥቶብሻልና፡፡ የወንጌል ምሥጢራት/ ስሮችሽንም በመቁረጥ ማጥፋት ጀመረ፡፡
    ካንቺ በኋላ የበቀለ አማሌቃዊ / እሾህም ፣ ምዕመናን / ቅጠሎችሽን ፈጽሞ ቆረጠ፡፡
    ይህም ይቅርና በጥፋት ከዚህ የባሰ የጉም በረዶ/ ያገር መንግስት በበላይሽ ይመላለሳል፡፡
    ኃይልሽ ከሰማይ አምላክ እንደሆነ( እንዳለ) አላወቀምና፡፡

    ምስጢር፡
    አገር ሰላም ብሎ ገበሬ ስንዴ ይዘራል፡፡ አንዳንዴ ግን የስንዴዋ ጠላት ይበዛባታል፡፡ መሬት ለመሬት እየሄደ ስሮቿን የሚበጣጥስ ወጥቶ የማይታይ ትል ያጋጥማታል፡፡ ሌላ ደግሞ ከበቀለች በኋላ የሚበቅል እሾህ ቅጠሎቿን እየበጣጠሰ እንዳታፈራ ያደርጋታል፡፡
    ይህ ሁሉ ሳያንሳት ደግሞ በረዶ የተሸከመ ደመና እየዞረ ልደመስስሽ ነው እያለ ያሰጋታል፡፡
    ነገር ግን ተፈጥሮን የሚቆጣጠር አምላክ ስላለ ከሁሉም አድኖ ለፍሬ ያበቃታል፡፡

    ይኸውልህ የኛ ተዋህዶም እነ አባ ሠላማን የመሰሉ ቅዱሳን አስተምረው፡ መሰረተ ጽኑ ሥርዓት ሰርተውልን ቢያልፉ፣ ከራሷ ጉያ የወጡት እናድሳት እያሉ በስውር አስተምህሮዋን እየቀየሩ ማር በመርዝ ቀላቅለው ማቅረብ ጀመሩ፡፡
    አማሌቃዊያንም እንደ እንግዳ አክብራ ብትቀበላቸው፡ ውለታው በሰይፍ ልጆቿን መቁረጥ ሆነ፡፡ ይህ እያለ ደግሞ ዘመናዊ ትምህርት ተማርኩ የሚለው” እግዚአብሔር የለም” እያለ ይፈላሰፍ የነበረው ቀርቶ ማኅበረ ቅዱሳን ዘመናዊውን ወጣት ሃይማኖቱን ጠብቆ እንዲኖር፣ ለሀገር ተቆርቋሪ ጥሩ ዜጋ እንዲሆን ቢያደርግ መንግስት “አሸባሪ ነው” አለ ሲባል እንሰማለን፡፡ ይህ እንግዲህ እንደ በረዶው ማናዣበብ ነው፡፡ ነገር ግን ኃይሏ ከእግዚአብሔር ስለሆነ ጠላቶቿ ይጠፋሉ እንጂ አትጠፋም፡ እልሃለሁ፡፡የአባቶቻቸን አምላክ ከኛ ጋር ይሁን አሜን፡፡

 2. Anonymous June 11, 2014 at 3:24 pm Reply

  Really…..I think there is misleading when it comes to the government of Ethiopia. Isn’t true the constitution of Ethiopia says every criticize can participate in any political party? If so why such accusation on those religious organization? There is fact we should know about this religious organization they are not political organization. However, it doesn’t mean some of the member of aren’t participate in Ethiopian politics outside the church…period!!! Just like some people who support the current government there is also some who oppose but this takes place outside the church. There is no way someone brings their political ideology and preaches in the church and neither Mehaber kidusan nor the Ethiopian Orthodox Church would allow it. So hands off may be you should remove your KADREA from the church. I’m sure the Ethiopian Orthodox Church better of your involvement.

 3. aynalem June 11, 2014 at 5:24 pm Reply

  Tehadso protestantawi nufaqe eyalachihu dofter shiferawun ena protestantochin setesedbu men yadreg?seltanun teteqme remeje mewsed alebegn yale yimeslal

 4. Anonymous June 11, 2014 at 5:28 pm Reply

  እስቲ ንገሩኝ በፖለቲካ ሽፋን የሐይማኖታቸውን ተልዕኮ የሚፈጽሙትስ ምይ ይባሉ? በጣም ያሳዝናል ከምር፦ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ99% በላይ ህዝባችን ሀይማኖተኛ ነው፥ ስለዚህ ሁሉም ሰው ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ የለበትም ማለት ነው። በነገራችን ላይ ባደጉት ሀገሮች አለመደገፍም ፖለቲካኛነት ነው። አሁን እንግዲህ ሊሉን የፈለጉት የፓርቲ ፖለቲካ ከሆነ፥ ማኅበሩ ማንም ሳይነግረው አስቀድሞ አመራሮቹና ሥራ አስፈጻሚዎቹ በፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ እንዳይሳተፉ ደንብ አውጥቶ ተፈጻሚነቱን እያረጋገጠ ነው። እስቲ ንገሩኝ በፖለቲካ ሽፋን የሐይማኖታቸውን ተልዕኮ የሚፈጽሙትስ ምይ ይባሉ? ይህ ሁሉ በውነት ለሀገር ታስቦ ሳይሆን በማኅበሩ ላይ ከውጭ የሚመጣውን ተልዕኮ (ተዋህዶ ሀይማኖት እንድትጠፋ በሚጥሩ፣ አገርን ማዳከም በሚፈልጉ፣ ግብረ ሰዶማዊነትን ለማስፋፋት ሌት ተቀን በሚሰሩ፣ የአገራችን ባህል እንዲጠፋና እንደሌሎቹ አፍሪካ አገራት እንዲመስል ወዘተ) ለማስፈጸም ካልሆነ ሌላ ፋይዳ የለውም። ከ1000000 በላይ የተማረ ሰው አእምሮ ማሰርም ሆነ መበተን አይቻልም፥ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቶ ያሸነፈ ማነው? ጨረስኩ ይኸው ነው:- እስቲ ንገሩኝ በፖለቲካ ሽፋን የሐይማኖታቸውን ተልዕኮ የሚፈጽሙትስ ምይ ይባሉ?

 5. Anonymous June 11, 2014 at 8:51 pm Reply

  ቤተክርስቲያንን የ መናፍቅ መፈንጫ ለማድረግ አባ ማትያስም ቆርጠው የተነሱ ይመስላል ::

 6. Anonymous June 11, 2014 at 9:12 pm Reply

  peace of our Lord be with ,wayanna afread the Young ethiopan realigious groüp mk the waynyana members wants to distroy achurch they eat 20 yeare the resourse of the church what they Need they want to swallow the mk and other members this is my massage but tell to aba mattias and his Dogs stop barking to the church of Christ we never afriad you all do you know aba pouöos and maleas are died we will see what can you do.

 7. Anonymous June 12, 2014 at 2:25 am Reply

   እስቲ ንገሩኝ በፖለቲካ ሽፋን የሐይማኖታቸውን ተልዕኮ የሚፈጽሙትስ ምይ ይባሉ? በጣም ያሳዝናል ከምር፦ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ99% በላይ ህዝባችን ሀይማኖተኛ ነው፥ ስለዚህ ሁሉም ሰው ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ የለበትም ማለት ነው። በነገራችን ላይ ባደጉት ሀገሮች አለመደገፍም ፖለቲካኛነት ነው። አሁን እንግዲህ ሊሉን የፈለጉት የፓርቲ ፖለቲካ ከሆነ፥ ማኅበሩ ማንም ሳይነግረው አስቀድሞ አመራሮቹና ሥራ አስፈጻሚዎቹ በፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ እንዳይሳተፉ ደንብ አውጥቶ ተፈጻሚነቱን እያረጋገጠ ነው። እስቲ ንገሩኝ በፖለቲካ ሽፋን የሐይማኖታቸውን ተልዕኮ የሚፈጽሙትስ ምይ ይባሉ? ይህ ሁሉ በውነት ለሀገር ታስቦ ሳይሆን በማኅበሩ ላይ ከውጭ የሚመጣውን ተልዕኮ (ተዋህዶ ሀይማኖት እንድትጠፋ በሚጥሩ፣ አገርን ማዳከም በሚፈልጉ፣ ግብረ ሰዶማዊነትን ለማስፋፋት ሌት ተቀን በሚሰሩ፣ የአገራችን ባህል እንዲጠፋና እንደሌሎቹ አፍሪካ አገራት እንዲመስል ወዘተ) ለማስፈጸም ካልሆነ ሌላ ፋይዳ የለውም። ከ1000000 በላይ የተማረ ሰው አእምሮ ማሰርም ሆነ መበተን አይቻልም፥ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቶ ያሸነፈ ማነው? ጨረስኩ ይኸው ነው:- እስቲ ንገሩኝ በፖለቲካ ሽፋን የሐይማኖታቸውን ተልዕኮ የሚፈጽሙትስ ምይ ይባሉ?

 8. Tiblest June 12, 2014 at 4:35 am Reply

  kewist honew betekristianin eyeshetuwat ekonew enante

 9. Anonymous June 12, 2014 at 7:18 am Reply

  ክሦስት ወር በፊት ተዘጋጀ ለተባለው …. እንደ ሦስት አመት ጊዜ ተቆጥሮና ጊዜው እንዳለፈበት አድርጎ ዶ/ር ሸፈራውንና መሰሎቻቸውን እንዲረጋጉ ማድረግ እንጂ፤ አሊያ…. ወይ ፍንክች ለዚህ አደባባይ ማን ሊሰለፍ? መናቅ ነው ወንድም እህቶቼ
  ..
  እንደው በሞትኩት ግን …. ፕሮቴስታንት ሆኖ ኢሕዴግን የመረጠ ይጠፋል? አሳምሮ ጠ/ሚርም የሕዝብ ተወካይም እስከመሆን..
  እንደው በሞትኩት …. ፕሮቴስታንት ሆኖ ተቃዋሚ ፓርቲን የሚመርጥ ይጠፋል?
  እሺ፤
  እንደው… እንደው በሞትኩት ….. ያ ሁሉ ተጋዳይ ሆኖ የገባው “አገልጋይ” ተመልሶ/ ‘አፍርሶ’ ገበሬ ሆነ ነው የምትሉኝ? በውጭስ ያሉ አባሎች/ ድጋፊዎች አገልጋዮች በህይወት አይኖሩም? (ሆድ ሲያውቅ..)!@#4
  ….እንደው ለመሆኑ ነፍሳቸውን ይማርና… ለአቶ መለስ ህልፈት ‘ለቅሶ’ ያልተከለከልኩት/ ከለልንው
  የሌላ ተቃዋሚ ቢሞትስ? (ግን አያድርገው፤ ‘በጥቁር ሊስት’?)
  ግን በሞተ ብቻ አላማስልና፤ በድጋፍ (ፖለቲካ ነውና) መልክ የግድ አቶ ‘ኢሕዲግን/ መንግስትን’ ብቻ መደገፍና፤ መምረጥ፤ መሰለፍ አለብኝ? ፕሮቴስታንት ሆንኩ ማኅበረ ቅዱሳን፤
  አንድ ቁም ነገር፤
  ኢትዮጵያዊው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ግን ‘ተመካኝቶ አይበላም’ ። (ማጣቀሻ፡ ዮዲት ጉዲት፤ ግራኝ፤የጣልያን ወረራ .. ከሁሉ ደግሞ በዚሁ ዘመን ያለን ራሳችን)

  /ዶ/ተሩንና መሳዮቹን እግዚአብሔር ቸርና ቅን ያሳስባቸው፤ ያመላክታቸው

 10. Anonymous June 12, 2014 at 12:45 pm Reply

  It is better not to give them any bit of attention. Just focus on the service you begin with. Don’t think for a second… God has a way out.

 11. Geremew Tadesse June 12, 2014 at 2:04 pm Reply

  yasazinal mahibere kidusan yepoletica sewoch mesheshegiya yemihon ayimesilegnim.

 12. M.E June 12, 2014 at 2:06 pm Reply

  እስቲ ንገሩኝ በፖለቲካ ሽፋን የሐይማኖታቸውን ተልዕኮ የሚፈጽሙትስ ምይ ይባሉ? በጣም ያሳዝናል ከምር፦ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ99% በላይ ህዝባችን ሀይማኖተኛ ነው፥ ስለዚህ ሁሉም ሰው ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ የለበትም ማለት ነው። በነገራችን ላይ ባደጉት ሀገሮች አለመደገፍም ፖለቲካኛነት ነው። አሁን እንግዲህ ሊሉን የፈለጉት የፓርቲ ፖለቲካ ከሆነ፥ ማኅበሩ ማንም ሳይነግረው አስቀድሞ አመራሮቹና ሥራ አስፈጻሚዎቹ በፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ እንዳይሳተፉ ደንብ አውጥቶ ተፈጻሚነቱን እያረጋገጠ ነው። እስቲ ንገሩኝ በፖለቲካ ሽፋን የሐይማኖታቸውን ተልዕኮ የሚፈጽሙትስ ምይ ይባሉ? ይህ ሁሉ በውነት ለሀገር ታስቦ ሳይሆን በማኅበሩ ላይ ከውጭ የሚመጣውን ተልዕኮ (ተዋህዶ ሀይማኖት እንድትጠፋ በሚጥሩ፣ አገርን ማዳከም በሚፈልጉ፣ ግብረ ሰዶማዊነትን ለማስፋፋት ሌት ተቀን በሚሰሩ፣ የአገራችን ባህል እንዲጠፋና እንደሌሎቹ አፍሪካ አገራት እንዲመስል ወዘተ) ለማስፈጸም ካልሆነ ሌላ ፋይዳ የለውም። ከ1000000 በላይ የተማረ ሰው አእምሮ ማሰርም ሆነ መበተን አይቻልም፥ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቶ ያሸነፈ ማነው? ጨረስኩ ይኸው ነው:- እስቲ ንገሩኝ በፖለቲካ ሽፋን የሐይማኖታቸውን ተልዕኮ የሚፈጽሙትስ ምይ ይባሉ?

 13. Mesfin Dubale June 13, 2014 at 11:09 am Reply

  መፅሐፍ ቅዱስም ሆነ ሊሎች የታሪክ መፃኅፍት እንደሚያስረዱን የሀይማኖት መሪ /እዉነተኛ የበጎች እረኛ/ እዉነትን ገፍትረዉ- ከሀሰት አብረዉ- አገልጋዮችን አስወንጅለዉ- አጥፊዎችን ሾመዉ- ቢተ/ክርስቲያንን ለመከራ ምዕመናንን ለክፍፍል ሀገርንም ለዉርደት… ወዘተ አልዳረጉም!!! አሁን ግን ሁሉ ነገር በተቃራኒ እየሆነ ነዉ ያለዉ፤ ልኡል እግዚአብሂር ግን ፍርዱን በጊዚዉ ይሰጣ ለ ል ፡፡

 14. Elias June 13, 2014 at 1:37 pm Reply

  አብርሃ ህወሃት እኮ የእንጀራ አባትህ ሆነ ምን አለ ስለነገዋ ኢ/ያ ምን አይነት ስርአት ያስፈልጋታል በምን ሂደት ነዉ ስርአቱ የሚዘረጋዉ ፣የሚያስፈልጉት መህበራዊ፤ኢኮኖሚያዊ ፤ባህላዊ ፤ህጋዊ መሰረቶች ምንድናቸዉ የሚለዉን ለመተንተን ብትሞክር 7/24 ስለህወሃት ማዉራት የምንመኘዉን ስርአት ሊያመጣልን አይችልም

 15. Yebel June 13, 2014 at 1:38 pm Reply

  መንፈሳዊ ማህበር እንደሞሆኑ መጠን መከራና ተግዳሮት ሲደርሰበት መንፈሳዊ ምላሽ ነዉ መስጠት ያለበት ሃዋርያቶች መከራና ስደት ሲደርስባቸዉ መንፈሳዊ ምላሽ ነዉ የሰጡት እሱም ፀሎትና በክርስቶስ ስም መከራዉን መቀበል ነበር ማህበረ ቅዱሳን ግን አላማዉ መንፈሳዊ ያለመሆኑ የሚታወቀዉ መንግስት ክስ ሲያቀርብበት ወደ ግል ሚዲያ በመሄድ ማስፈራራትና አመፅን መጥራትና እንዲሁም ባለዉ መዋቅርና የአባላት ብዛት መታበይን እንደ ቁልፍ ስትራቴጂ ነዉ የሚከተለዉ ስለዚህ ማህበረ ቅዱሳን ሳይሆን መባል ያለበት ማሀበረ ፖሎቲከኞች ነዉ ፡፡፡፡፡ አሁን የተሸፈነበት እርቃን እየወጣ ነዉ አባቱ ዲያብሎስ ሊያድነዉ አይችልም

  • Anonymous June 14, 2014 at 6:51 am Reply

   Can you give us a single word that can justify your saying, that MK run to private medias????
   No, you couldn’t. Read recently published <>. The stand of MK could not be found in any where, except its own legal medias, officially and publicly given talks. Otherwise, people like you and me as an individual are doing our business. This is the fact. Even in this message, you throw one stone to hurt MK, is it not? my dear

  • Anonymous June 14, 2014 at 2:44 pm Reply

   አንተ ካድሬ ወያኔ አርፈህ አትቀመጥም ተስፋ ቢስ

 16. Anonymous June 14, 2014 at 6:40 am Reply

  አድማው ውስጥ ወልደ ማርያም አለበትን ?
  ‹‹ አንድ ሰው መልካም ነው ያለውንና ለመሠረታዊ ለውጥ ይበጃል ያለውን ሲሰራ ከቅርብ ያሉ ጥቅማችንን ሊነካብን ነው ያሉት ለካ አድመውበታል፡፡ እርሱ እንኳን ይህን የሚሰማበት ለመብሉም ፋታ አልነበረውምና አላወቀም፡፡
  ታዲያ ለዚህ ትጉህ ሰው ዘመድና ወዳጅ ነን ያሉ ሰዎች የአድመኞቹን ክፋትና ማምረር አወቁና ለወዳጃቸው ‹ አንተዬ፣ አንተ ዝም ብለህ ሥራ ሥራህን ስትል እነ እገሌ አድመውብሃል፡፡ አድማቸው ደግሞ ክፉ ነውና አርፈህ ተቀመጥ › አሉት፡፡
  እሱም እንደ ሥጋ ባህርይ ደንገጥ ቢልም፤ ደግሞ እንደ ተላበሰው ጽኑ መንፈሰ እግዚአብሔር ጠንከር አለና ስለ ሃሳባቸው አመሰገነና አንድ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
  ጥያቄ፡- ‹‹ ለመሆኑ አድማው ውስጥ ወልደ ማርያም አለበት እንዴ ? ›› አላቸው፡፡
  እነርሱም አድማው ውስጥ ያሉትን ሁሉ ቆጠሩና እንዲህ ሲሉ መለሱለት
  መልስ፡- ‹‹ እንደውም፤ አድመኞቹ ውስጥ ወልደ ማርያም የለም ›› አሉት ፡፡
  እርሱም ‹‹ ወልደ ማርያም ከሌለበት እንኳን ተውት፤ አድማው ይፈርሳል፡፡ ›› ብሏቸው ሥራውን ቀጠለ፡፡
  እናተዬ በቤ/ክ ላይ ብዙ አድመኞች ለብዙ ዘመናት አሲረዋል፡፡ የቤ/ክ አካል በሆነው በማኅበረ ቅዱሳን ላይም ከውስጥም ከውጭም ብዙ አድመኞች አሉ፡፡ በተለያየ ሽፋን ቢመጡም ጭምብሉ ሲገለጥ ግን ሁሉም ያው የአንድ ምንጭ አድመኞች ናቸው፡፡

  አድማው ውስጥ ወልደ አብ ፣ ወልደ ማርያም መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ካለበት ብቻ አድማውና ፈተናው ለጥፋት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ጥያቄው አድማው ውስጥ ወልደማርያም አለበትን ? ከእኛ ምን በደል አለ ይሀን፡፡
  ተስፋ አለኝ ዘ ደብረ ብርሃን

 17. weg June 14, 2014 at 1:32 pm Reply

  “አድማው ውስጥ ወልደ ማርያም አለበትን ?”
  Thank you. Let God do his job, God is always with the true side.

 18. kk June 16, 2014 at 8:41 am Reply

  @Gojamew, thank you very much … please keep posting this kind of well matured ‘kine’ in every forums and blogs possible. God bless you!!

 19. weg June 17, 2014 at 2:20 am Reply

  Thank you Anonymous June 15, 2014 at 2:11 pm.

 20. anonymous June 17, 2014 at 9:43 am Reply

  እንዴት ነው ነገሩ፤ዶፍተር ተብየው ተልኮውን ለማሳካት እየደከመ ነው።አውቀንብሀል ልንለው ይገባል።የመንግሥትን ሥልጣን ተገን አድርጎ ኦርቶዶክስን እያሸበረ ነው።በሥልጣኑም እየባለገ ሙሥና እየሠራበት ነው።ዋ

 21. Birhan Asfaw June 18, 2014 at 7:16 pm Reply

  Egziabher yetekelewn manm ayneqilew.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: