ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ለመኾን እንደማይችሉ ያምናሉ

 • በአብዮቱ መባቻ ዓመታት ከደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት›› ጋራም በቁርኝት ሠርተዋል
 • ከደርግ ጋራ አብሮ በመሥራትና ደርግን በማውገዝ መካከል የሚታዩት የፓትርያርኩ የአቋም ጽንፎች ፀረ አማሳኝ መስሎ የአማሳኞች ከለላ ኾኖ የመገኘት ፍፃሜ ነው!!

(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፵፱፤ ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.)

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያኒቱና መሪዎቿ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ሊኾኑ እንደማይችሉና መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቷ የአስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ ቢገባ ሕገ መንግሥቱን እንደማይፃረር አቋም ይዘው መከራከራቸው ተገለጸ፡፡

የፓትርያርኩ አቋም የተንጸባረቀው፣ ከአንድ ሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶሱ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ለቀናት ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደነበር የስብሰባው የፋክት ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ለካህናት ስለተከለከሉ ተግባራት አስመልክቶ፣ ጳጳሳትና በቤተ ክርስቲያኒቱ በሓላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ካህናት ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ አባልነት ወይም አራማጅነት ነፃ መኾን እንደሚገባቸው ይደነግጋል፡፡

ስለ አንቀጹ አግባብነትና አስፈላጊነት በተሰጠ ማብራሪያ፣ ‹‹እስከመቼ ድረስ አንድ ላይ ተጣብቀን እንኖራለን፤ ሕገ መንግሥቱ እንደሚለው ነፃ መኾን አለብን፤ ነፃ መኾናችንን ለማረጋገጥ ጳጳሳትና በሓላፊነት ደረጃ ያሉ ካህናት ከፖሊቲካ እንቅስቃሴ አባልነትና አራማጅነት ነፃ እንዲኾኑ መከልከል አለብን፤›› መባሉ ተዘግቧል፡፡

ፓትርያርኩ አንቀጹን በመቃወም ‹‹ከመሐንዲስ፣ ከዶክተር ነፃ ልንኾን እንደማንችለው ከመንግሥት ጥገኝነትም ነፃ ልንኾን አንችልም፤›› የሚል አስተያየት መስጠታቸው ተዘግቧል፡፡ አያይዘውም በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ እንጂ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጣልቃ ቢገባ ድንጋጌውን እንደማይፃረር የሚያሰማ አቋም አራምደዋል ተብሏል፡፡

አቡነ ማትያስ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ የመጨረሻ ወሳኝና ላዕላይ የሥልጣን መዋቅር ከኾነው ከቅ/ሲኖዶሱና አባላቱ ይልቅ ከመንግሥት ጋራ አላቸው የሚባለው ያልተገራና ያልተገደበ ግንኙነት የሊቃነ ጳጳሳቱን ቁጣ ቀስቅሷል በተባለበት ኹኔታ ይህን አቋም ማራመዳቸው እያነጋገረ እንደሚገኝ ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Patriarch Abune Mathias formerly known as Aba Teklemariam with Dergue's Renewal committee membersሌሎች የፋክት ምንጮች በበኩላቸው፣ ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጋራ አላቸው በሚል በተቺዎቻቸው የሚጠቀሰው ልክ ያልኾነና ያልተገራ ግንኙነት ጵጵስና ከመሾማቸው አስቀድሞ የሦስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ በነበሩባቸው የአብዮቱ መባቻ ዓመታትም፣ የወቅቱን የሥርዓት ለውጥ በቤተ ክህነቱ ለማሥረጽና ተቃዋሚዎች (በተለይ ኢዲዩ) የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ ወደ ስሜን ኢትዮጵያ ተጉዘው የፈጸሙትን ተግባር በአስረጅነት ይጠቅሳሉ፡፡*

›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››
*YeTahisas Girgir ena Mezezuበግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ከ፲፱፻፵፰ – ፶፫ ዓ.ም. በአገር ግዛት ሚኒስቴር የሕዝብ ፀጥታ ጥበቃ መምሪያ ሓላፊ ሌተና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ልዩ ረዳት የነበሩት አቶ ብርሃኑ አስረስ ‹‹ማን ይናገር የነበረ… የታኅሣሥ ግርግርና መዘዙ›› በሚል ርእስ በቅርቡ ለኅትመት ባበቁት መጽሐፍ፣ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የፊት ስማቸው አባ ኃይለ ማርያም እንደነበር የጠቀሱት በስሕተት ይመስላል፡፡

በ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በወልቃይት፣ በፀገዴና በአርማጭሆ ቆላ ደርግን በመቃወም የተንቀሳቀሰውን የኢዲዩ ኃይል ለማቆምና ደገኛው ከቆለኛው ጋራ እንዳይተባበር ለመምከር በደርግ ተመልምለው ወደ በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ካቀኑት መካከል በወቅቱ አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት አኹን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አንዱ የቡድኑ አባል እንደነበሩ የመጽሐፉ አዘጋጅ ገልጸዋል፡፡

አባ ተክለ ማርያም በወቅቱ ‹‹የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አቡነ ቀሲስ፣ በኋላ አቡነ ማትያስ ናቸው›› የሚሉን ጸሐፊው፣ ከአባ ተክለ ማርያም ጋራ አለቃ ቀለመ ወርቅ(የቤተ ክህነት ደብተራ ይሏቸዋል) በቡድኑ ውስጥ የተካተቱት ‹‹ለሃይማኖት ነክ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደነበር›› አስፍረዋል፡፡

የሕዝብ ተሰሚነት አላቸው በሚል ከጠቅላይ ግዛቱ ሰባት አውራጃዎችና የጎንደርን ከተማ በመወከል ከተመረጡት መካከል በወቅቱ የደብረ ታቦር አውራጃ ተወካይ አቶ(በኋላ ሊቀ ማእምራንና ደርግ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር በኅብተረሰብ ተሳትፎ ላይ መመሥረት በሚል ሐዋርያዊ አገልግሎቷን በሶሻሊስታዊ መንፈስ ለመቃኘት ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ ጸሐፊ) አበባው ይግዛው አንዱ እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡

Patriarch Abune Mathias with renewal committeesከዘመቻው ጉዳይ ጋራ በተያያዘ ስብሰባ የተደረገው በጎንደርና ደብረ ታቦር ላይ ብቻ እንደነበር የሚገልጹት አቶ ብርሃኑ፣ ‹‹ኢዲዩ እየበረታ መጥቷል፤ እኛም በሰላም ተነጋግረን ደገኛውንና ቆለኛውን እንዳይተባበር ማድረግ አልቻልንም፤›› በማለት ዘመቻው ስኬታማ እንዳልነበር ጠቅሰዋል፤ አያይዘውም ‹‹ኹለቱ የሃይማኖት ሰዎች የተመለሱት አንድም አስተያየት ወይም ማብራሪያ ሳይሰጡ ነበር፤›› ብለዋል፡፡ (ገጽ 400 – 421)
***************************************************

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር ዶ/ር ውዱ ጣፈጠ ካሱ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ በሠሩት ጥናት፣ የሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ቀሲስ የነበሩት አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት (በኋላ ብፁዕ አቡነ ማትያስ) ደርግ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የለውጥ ጊዜያዊ ጉባኤ›› (the EOC provisional council or Renewal Council) በሚል ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ አባል የነበሩ ባይኾኑም የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ከነበሩት ዶ/ር ክነፈ ርግብ ዘለቀ ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው በነሐሴ ወር ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ምክትል ሊቀ መንበር ኮሎኔል አጥናፉ አባተ ቀጥተኛ መመሪያና ቁጥጥር የተቋቋመ ነበር፡፡ ከኹለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጋራ ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው ጊዜያዊ ጉባኤው፣ ቅዱስነታቸው በአራት መዋቅሮች(የፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት፣ የስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ፣ የውጭ ጉዳይና ልማት ኮሚሽን) የቤተ ክህነቱን አስተዳደር ለማጠናከር ያቋቋሙትን ኮሚቴ በመጋፋት ለውጥና መሻሻል ያመጣል ያለውን የራሱን ባለአምስት ኮሚቴዎች (የሕግና አስተዳደር፣ የስብከተ ወንጌልና ትምህርት፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ የታሪክና ባህል ጉዳዮች እና የአቤቱታ ሰሚ) መዋቅር ዘርግቷል፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው ጋራ ያልተግባቡትና የማሻሻያ መዋቅሩን ያልተቀበሉት ቅዱስነታቸው በወርኃ የካቲት ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. ጊዜያዊ ጉባኤው ለደርጉ ባቀረበው የክሥ ሪፖርት ‹‹ሲጠበቅ የቆየ ፍርድ›› በሚል ዐዋጅ ከመንበረ ፕትርክናው ተገፉ፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱና በጊዜያዊ ጉባኤው መካከል ሽኩቻ የተካሔደበት ቀጣዩ የፕትርክና ምርጫ በጊዜያዊ ጉባኤው በኩል ታጭተው የቀረቡትን ሐዋርያዊውን ባሕታዊ አባ መላኩ ወልደ ሚካኤል – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በመንበሩ ሠየመ፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫና ሹመት፣ በአህጉረ ስብከት ዝውውር እንዲሁም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሹመት በቀጥታ ይቆጣጠር የነበረ ከመኾኑም በላይ ከደርጉ ጋራ እጅና ጓንት ኾነው በአባልነት የሠሩ አባላቱ በዋና ሥራ አስኪያጅነትም ተቀምጠው ነበር፡፡ ጵጵስና እስኪሾሙ ድረስ የቅዱስነታቸው አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ የነበሩት አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት ጊዜያዊ የሃይማኖት ጉባኤው ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራት ብቻ ሳይኾን ወደ ስሜን ኢትዮጵያ ተነቃንቀው ስለ አብዮቱ ካስተማሩና የሥርዓት ለውጡን የሚቃወሙ እንደ ኢዲዩ ያሉ ኃይሎች የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ ከቀሰቀሱ የደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት› አንዱ ነበሩ፡፡

“Before his appointment as bishop, Matyas had been Abune Qasis of Patriarch Abune Takla-Haymanot. Though not a member of the provisional council, he had closely worked with Dr. Kenafe-Regeb Zallaqa, chairman of the council, and was mobilized to northern Ethiopia with members of the council to teach and explain about the revolution.”(WUDU TAFETE KASSU,PhD; THE ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH,THE ETHIOPIAN STATE AND THE ALEXANDRIAN SEE: INDIGENIZING THE EPISCOPACY AND FORGING NATIONAL IDENTITY,1926 – 1921; p.366)

Advertisements

15 thoughts on “ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ለመኾን እንደማይችሉ ያምናሉ

 1. Anonymous June 9, 2014 at 11:00 am Reply

  enihen tagaye new yebetekrstiyan meri yadereguachew…..

 2. Anonymous June 9, 2014 at 11:01 am Reply

  በንቃት መቆም ካልቻልን አኮ ዋጋ የለንም ቤተክርስቲያናችንን ማን እንደሚመራት ተመልከቱ..ሁላችንም ልን ነቃ ይገባናል

 3. Anonymous June 9, 2014 at 12:39 pm Reply

  ብጹዕ አቡነ ቄርሎሰ አዲሱ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የደርግ የለውጥ ሐዋርያ ሆኖ ያገለገለ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፈረንጅ ሀገር ሲቃርም ከርሞ ካባውን ገልብጦ ወያኔ ኢህአዴግ ሆኖ መጣና ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ፡፡ ይህንንም በመቃወማችን ነበር በተለይ እኔን በረከት ስምኦን የተባለው የወያኔ ባለስልጣን በፓትርያርኩ ምርጫ ሰሞን ስልክ ደውሎ አርፈህ ካልተቀመጥክ ምላስህን እቆርጠዋለሁ ብሎ ያስፈራራኝ፤ አሁንም ማትያስ የወያኔ ስራ አስፈጻሚ በመሆን ማህበረ ቅዱሳንን የሚያሳድደውና ማህበራቸውን ለማፍረስ የሚቃትተው ብለው የተናገሩት እውነታቸው ነው ማለት ነው፡፡

 4. Anonymous June 9, 2014 at 12:48 pm Reply

  አይ የማቅ አባለት ገና ብዙ ትላላቹ አቡነ መርቆርዮስ፤አባ ገብርኤል . . . የመሳሰሉትስ

  • Anonymous June 10, 2014 at 3:30 am Reply

   This is nothing to do with MK. MK is a 23 year old org the picture presented here is well over 40 years old, as Patriaric Mathias in his recent visit to Gondar said, “he was in the city the last time 42 or 43 years ago”

 5. Anonymous June 9, 2014 at 12:56 pm Reply

  ante degemo telalaki yehonk sew yehen guday degemo mk gar men agenagnew lela yemetelew atah malet new

 6. Anonymous June 9, 2014 at 1:00 pm Reply

  ጤነኛው ማነው ? ብዙ ጉድ አለ!!! ይህን ማለቴ ለአባ ማትያስ በመደገፍ አይደለም ግን በጥቅሉ ሲኖዶስ አለ ወይ የነአባ እንቶኔ ታሪክ የየአንዳዳቸው ምን ይመስላል ውስጡን ለቄስ በውስጥ በውጭ ያለው ዅሉ አንድ ነው ።
  ይህንን ነው የአባ ገሪማን ንባብ ይዛችሁ ይግባኝ የማይጠየቅበት ሲኖዶስ ያላችሁት ይገርማል እኛስ ይግባኝ ለክርስቶስ እንላለን እንደነ አባ ቀውስጦስ በስሜት ሳይኾን ከምር ዳኝነት ገንዘቡ ለኾነ ለርሱ እርሱም ይፈርዳል ።
  ስለዚህ ከመንደር ከሰፈር ከካድሬነት ከንግድ ……ከሌላም ከሌላም የነጻው ማነው ? እንደኔ ማንም!!!! አንዳድ አሉ የሚለውን ማዘናጊአ አቆዩትና ካለ እገሌ በሉ በግልጽ እንነጋገር ።
  በውነት ከምር ለቤተ ክርስቲያን ካሰባችሁ ሲኖዶስ እንዲኖራት ሥሩ እንሥራ ሌላ አማራጭ የለም ለኔ አሁን ያለንበት ጊዜ እስላሙ ግብጻዊ ጳጳስ ኾኖ በኢትዮጵያ ከነበረበት ጊዜ የከፋ ነው ። ብቻ የድንግል ልጅ ይታረቀን ማኅበረ ቅዱሳንስ የማን አቀንቃኝ ነበር በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በፊት ዛሬስ ማን ከማን ተሽሎ በምን መመዘኛ ነው አንዱን ወዶ አንዱን የጠላው ኹሉስ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምን ጠቀሟት ሸክምና መሰናክል ከመኾን በቀር አምላከ ቅዱሳን ፈታሔ በርት ኮናኔ በጽድቅ እርሱ ይፍረድ ።

  ኀጥኡን የሚያጸድቅና በጻድቁ ላይ የሚፈርድ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው።

  መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፲፭

 7. የቅርብ ታዛቢ የውነት አሽከር June 9, 2014 at 1:16 pm Reply

  ጤነኛው ማነው ? ብዙ ጉድ አለ !ይህን ማለቴ ለአባ ማትያስ በመደገፍ አይደለም ግን በጥቅሉ ሲኖዶስ አለ ወይ የነአባ እንቶኔ ታሪክ የየአንዳዳቸው ምን ይመስላል ውስጡን ለቄስ በውስጥ በውጭ ያለው ዅሉ አንድ ነው ።
  ይህንን ነው የአባ ገሪማን ንባብ ይዛችሁ ይግባኝ የማይጠየቅበት ሲኖዶስ ያላችሁት ይገርማል እኛስ ይግባኝ ለክርስቶስ እንላለን እንደነ አባ ቀውስጦስ በስሜት ሳይኾን ከምር ዳኝነት ገንዘቡ ለኾነ ለርሱ እርሱም ይፈርዳል ።
  ስለዚህ ከመንደር ከሰፈር ከካድሬነት ከንግድ ……ከሌላም ከሌላም የነጻው ማነው ? እንደኔ ማንም!!!! አንዳድ አሉ የሚለውን ማዘናጊአ አቆዩትና ካለ እገሌ በሉ በግልጽ እንነጋገር ።
  በውነት ከምር ለቤተ ክርስቲያን ካሰባችሁ ሲኖዶስ እንዲኖራት ሥሩ እንሥራ ሌላ አማራጭ የለም ለኔ አሁን ያለንበት ጊዜ እስላሙ ግብጻዊ ጳጳስ ኾኖ በኢትዮጵያ ከነበረበት ጊዜ የከፋ ነው ። ብቻ የድንግል ልጅ ይታረቀን ማኅበረ ቅዱሳንስ የማን አቀንቃኝ ነበር በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በፊት ዛሬስ ማን ከማን ተሽሎ በምን መመዘኛ ነው አንዱን ወዶ አንዱን የጠላው ኹሉስ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምን ጠቀሟት ሸክምና መሰናክል ከመኾን በቀር አምላከ ቅዱሳን ፈታሔ በርት ኮናኔ በጽድቅ እርሱ ይፍረድ ።

  ኀጥኡን የሚያጸድቅና በጻድቁ ላይ የሚፈርድ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው።

  መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፲፭

  • Anonymous June 12, 2014 at 7:18 am Reply

   what did u do on be half of ur self?

 8. Anonymous June 9, 2014 at 3:35 pm Reply

  Yemhren weysehalene

  lela men yebalal

 9. Kebede June 9, 2014 at 6:13 pm Reply

  እውነት ነው አባ ማትያስ የደርጉ የለውጥ ሐዋርያ ሁነው ሠርተዋል። እኔ የ17 ዓመት ወጣት ዲያቆን ሁኘ በጎንደር ክፍለ ሀገር ከመጣው የደርግ ለውጥ ሐዋርያ ልዑክ ጋር ሲንቀሳቀሱ አይቻቸው ነበር። ቀለመወርቅን እንዲያውም ኋላ የኢሕአፓ ስኳድ እንዳቆሰለው የሰማሁ መስሎኛል። አሜሪካን በነበሩበት ጊዜም ደርግ እስከሚወድቅ ድረስ እኔ የአትላንታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስትመሠረት ከመሥራቾቹ አንዱ ስለነብርኩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቀ ጳጳስ/አባት እንዲሆኑ ተከራክረው ካሳመኑት ግምባር ቀደሙ ሰው እኔ ነበርኩ። ወያኔ ሥልጣን ሲይዝ ግን ከዲሲ ወደ አትላንታ መጥተው የሥጋ ወንድሞቻቸው ሥልጣን ለመያዝ በመብቃታቸው የተሰማቸውን የደስታ መግለጫ በማቴዎስ ወንጌል ምትክ አነበቡልን። በዚያ ምክንያት ተለያየን። መሪገታ ሙሴ ብቻ አብሯቸው ቆመ። የብዙኀኑ አባት መሆናቸው ቀርቶ የጥቂቶቹ መሆንን መረጡ። በጣም ስናከብራቸውና ስንወዳቸው የነበርነው ልጆቻቸው ተቀየምናቸው።

 10. Anonymous June 10, 2014 at 3:42 am Reply

  ስለዚህ ከመንደር ከሰፈር ከካድሬነት ከንግድ ……ከሌላም ከሌላም የነጻው ማነው ? እንደኔ ማንም!!!! አንዳድ አሉ የሚለውን ማዘናጊአ አቆዩትና ካለ እገሌ በሉ በግልጽ እንነጋገር ።

 11. Anonymous June 10, 2014 at 1:23 pm Reply

  ይህ ብሎግ የማን ነው? እንዴት ነው ግኑኝነት የሌላቸው? ሌላው ጎንደር ለአባ መርቆርዮስና የመልአኩ ተፈራ ግኑኝነት ለምን አልተጠቀሰም? እንደሁም የመነኩሴው ስም የግድ የአባ ማትያስ መሆን አለበት ብላቹ ነው የቀየራቹት እንጂ ፀሐፊው አባ ኃ/ማርያም ነው ያለው መልክ መሰለና ለናንተ እንዲመች አስጠጋቹሁባቸው አይ ማቅ።

 12. Anonymous June 10, 2014 at 1:54 pm Reply

  ከደርግ ጋራ አብሮ በመሥራትና ደርግን በማውገዝ መካከል የሚታዩት የፓትርያርኩ የአቋም ጽንፎች ፀረ አማሳኝ መስሎ የአማሳኞች ከለላ ኾኖ የመገኘት ፍፃሜ ነው!!
  ዛሬም አልመሸም ድሮ የበደሏትን ዛሬም መበደል የለባቸውም እስትንፋሳቸው እስኪቅዋረጥ ድረስ ግን ቤተክርስቲያንን መበደል የግፍ ግፍ ነው ::አንዳንዴ እኮ ወያኔና ደርግ አይወዳደሩም ደርግ በጣም የተሻለ ነበር ቢያንስ እንዲህ ሀገርንና ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ጠላት አላደረገም ለማጥፋትም አልተነሳም ::ደርግ ሲመጣ ከደርግ ጋ ወያኔ ሲመጣ ከወያኔ ጋ ከሆኑ ነገ ሰይጣን አካል ኖሮት ስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጦ እኔ ሰይጣን ነኝ ቢላቸው ተባባሪነታቸውን ከማሳየት ወደ ኃላ የሚሉ አይመሰለኝም ::የሆነው ሆኖ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው ::

 13. Anonymous June 11, 2014 at 1:36 pm Reply

  ለምንድን ነው በትግራይ ተወላጆች ላይ ብቻ የምትዘምቱት ጉዳዮ ሃይማኖት ሣይሆን ዘር እንደሆነ ገባኝ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: