የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በፓትርያርኩ እና ጳጳሳቱ ፍጥጫ ተቋጨ

 • ጳጳሳት የፓትርያርኩን የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ቅድመ ኹኔታ አልተቀበሉትም
 • ‹‹ቅድመ ኹኔታው የማኅበሩን አገልግሎት የሚያቀጭጭ በሒደትም የሚያስቆም ነው፡፡›› /ታዛቢዎች/
 • ማኅበሩ የመተዳደርያ ደንቡ ማሻሻያ ረቂቅ እስኪጸድቅ በነባሩ ለመመራት ይገደዳል

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፶፤ ቅዳሜ ግንቦት ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

Holy Synod endingበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅን እንደ አንድ አጀንዳ የያዘው የዘንድሮው የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ከረቂቁ ጋራ በተያያዘ በፓትርያርኩ እና በሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል በተፈጠረ ፍጥጫ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

የፍጥጫው መንሥኤ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተሠየመው የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ አጥኚ ኮሚቴ ያዘጋጀው የማሻሻያ ረቂቅ በዝርዝር ከመታየቱ አስቀድሞ ፓትርያርኩ ለውይይቱ እንደ ቅድመ ኹኔታ ያቀረቧቸው ነጥቦች በአብዛኛው የምልዓተ ጉባኤው አባላት የገጠመው ተቃውሞ እንደኾነ የስብሰባው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የቅ/ሲኖዶሱን ስብሰባ በርእሰ ጉባኤነት የሚመሩት ፓትርያርኩ፣ በአጀንዳው ላይ የሚካሔደውን ውይይት ቀጣይነት ይወስናል በሚል ካቀረቧቸው ቅድመ ኹኔታዎች ውስጥ÷ ለአጥኚ ኮሚቴው መመሪያ የሰጡባቸው ‹‹ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች›› አንድም ሳይቀነሱ በደንቡ እንዲካተቱና ረቂቁ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ከጸደቀ በኋላ እንዲታይ የሚሉ እንደሚገኙበት ተመልክቷል፡፡

ፓትርያርኩ በቅድመ ኹኔታ አስቀምጠዋቸዋል በተባሉት ነጥቦች ስምምነት ላይ ከተደረሰ ስብሰባው ሊቀጥል እንደሚችል በመጥቀስ የምልዓተ ጉባኤውን ድጋፍ ኃይለ ቃልም ተማኅፅኖም በተቀላቀለበት አኳኋን መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡

Holy Synod Ginbot 2006

ፎቶ: ማኅበረ ቅዱሳን

ይኹንና የሚበዙት ሊቃነ ጳጳሳት በቀጥታ እንደተቃወሟቸው፣ የተቀሩትም ለፓትርያርኩ ድጋፍ ከመስጠት እንደተቆጠቡ ታውቋል፡፡ ፍጥጫው ቀጥሎ አቡነ ማትያስ ‹‹አቋሜ ይኽው ነው፤›› በሚል አጀንዳውን መዝጋታቸውን ሲያስታውቁም፣ ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ እንዲህ ተብሎ የሚተው አይደለም፤›› በሚል ከኹሉም ሊቃነ ጳጳሳት ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ምንጮቹ ይገልጻሉ፡፡

የቅ/ሲኖዶሱ መደበኛ ስብሰባ የሚካሔደው ምልዓተ ጉባኤው ከጅምሩ ተስማምቶ ባጸደቃቸው የመነጋገርያ አጀንዳዎች መሠረት እንደኾነ በሊቃነ ጳጳሳቱ ተቃውሞ ተጠቅሷል፡፡

የማኅበሩ የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ እንዲቀርብ ከሚጠበቅበት ከጥቅምት ፳፻፭ ዓ.ም. ጀምሮ* እየተንከባለለ ለኹለት ዓመታት መዘግየቱን ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰው፣ የተጓተተው አጀንዳ ‹‹የማኅበሩን አገልግሎት ያቀጭጫሉ፣ በሒደትም ያስቆማሉ›› በሚል በተተቹት የፓትርያርኩ ቅድመ ኹኔታዎች ሊዘጋ እንደማይችልና ተጨማሪ ጊዜ ሳይወስድ ቅ/ሲኖዶሱ ሊወያይበት እንደሚገባ በአጽንዖት በመናገራቸው፣ አጀንዳው መታየት በጀመረበት ቀን ሳይቋጭ ለቀጣዩ ቀን በይደር ተላልፏል፡፡

አጀንዳው ሰኞ፣ ግንቦት ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጥዋት መታየት ሲጀምር፣ አጥኚ ኮሚቴው በ37 አንቀጾችና በ34 ገጾች አሻሽሎ ያዘጋጀው የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብና የኮሚቴው ቃለ ጉባኤ በንባብ መሰማቱ ታውቋል፡፡ ፓትርያርኩ ‹‹ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች›› በሚል ራሱን በቻለ ርእስ በደንቡ እንዲካተት ለአጥኚ ኮሚቴው ጥብቅ መመሪያ የሰጡበት ባለ24 አንቀጽ ሰነድም አብሮ እንዲነበብላቸው የጠየቁበት ኹኔታም የመጀመሪያ ቀን የፍጥጫ መነሻ እንደነበር ተሰምቷል፡፡

በ24 አንቀጾችና በአምስት ገጾች የተዘረዘሩት የፓትርያርኩ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች÷ በአባላቱ በጎ ፈቃድ ተቋቁሞ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኘውን ማኅበር ከሕገ ተፈጥሮው ውጭ የሚያደርግ፣ በቅ/ሲኖዶሱ ፈቃድ ከሚመራበት ደንብ በተፃራሪ ተቋማዊ ህልውናውን፣ የአመራር ምርጫውን፣ የአባላት አያያዙንና የሥራ ቦታውን ለውጭ ተጽዕኖ አሳልፎ የሚሰጥና አጣብቂኝ ውስጥ የሚያስገባ፣ በአርኣያነት የሚጠቀሰውን የፋይናንስ አሠራሩን ወደ ኋላ የሚጎትት መኾኑን እንደተረዱ ያብራሩ አንድ የቅ/ሲኖዶሱ አባል፣ ‹‹ቀጣዩ ቀንም የከበደ ነገር ይዞ እንደሚመጣ ግልጽ ነበር፤›› ይላሉ፡፡

በይደር የተያዘው አጀንዳ በቀጣዩ ቀን ማክሰኞ ጥዋት ተጀምሮ ለግማሽ ቀን የቀጠለ ቢኾንም ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳቱ የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያውን ወደ ዝርዝሩ ገብቶ ለመመልከት የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዳልተቻላቸው ታውቋል፡፡

His Holiness Ab Mathias01 ‹‹ፓትርያርኩ በቅድመ ኹኔታ ያስቀመጧቸውን ነጥቦችና በአጀንዳው ቀጣይነት ላይ የያዙትን አቋም አልቀየሩም፤ ሊቃነ ጳጳሳቱም ባጸደቅነው አጀንዳ መሠረት ቅድሚያ ሰጥተን መነጋገር ያለብን የሠየምነው አጥኚ ኮሚቴ አዘጋጅቶ ባቀረበው ረቂቅ ላይ ነው፤ መካተት ያለበት ነገር ካለም ማኅበሩን በሚያሠራ መልኩ እያገናዘብን በሒደት እናየዋለን እንጂ አጀንዳው በቅድሚያ ኹኔታ መታሰር የለበትም በሚል በተለያዩ አግባቦች ለማስረዳት ጣሩ፤ በመጨረሻም ፓትርያርኩ ‹እንግዲያውስ ስብሰባውን ለመምራት አልችልም› በማለታቸው የስብሰባው መቋጫ ኾኗል፤›› ይላሉ – ሒደቱን ለአዲስ አድማስ የገለጹ የስብሰባው ምንጮች፡፡

የማኅበሩ ደንብ በመጀመሪያ ረድፍ ከሰፈሩት የቅ/ሲኖዶሱ መነጋገርያ ነጥቦች አንዱ እንደነበር ያስተዋሉ ሌሎች የስብሰባው ተከታታዮች በበኩላቸው፣ አጀንዳው ከቅደም ተከተሉ ወጥቶ እየተገፋ በመጨረሻ መነሣቱ በፓትርያርኩና በሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል ይህ ዓይነቱ አለመግባባት ሊነሣ እንደሚችል ጠቋሚ ነበር ብለዋል፡፡

ተከታታዮቹ አክለውም፣ ፓትርያርኩ ስብሰባውን ለመምራት ፈቃደኛ ባይኾኑም በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ በተደነገገው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት መሠረት፣ ምልዓተ ጉባኤው በማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያዎች ላይ የጀመረውን ውይይት ቀጥሎ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚችልባቸው አግባቦች እንደነበሩ ገልጸው፣ ቅ/ሲኖዶሱ በጋዜጣዊ መግለጫው፣ የመጨረሻው መነጋገርያው ባደረገው የማኅበሩ ደንብ ላይ ‹‹ውይይት ተደርጎበታል›› ከማለት በስተቀር አጀንዳውን ያለውሳኔ የቋጨበት አኳኋን ያልተለመደና አደናጋሪ ነው ብለዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በዘመኑ ጥበብ የሠለጠነውን ኦርቶዶክሳዊ ትውልድ አደራጅቶ ማንነቱን የሚያውቅበትንና በግብረ ገብ የሚታነፅበትን ትምህርተ ሃይማኖት ከማስተማር ባሻገር፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማት አገልግሎታቸውን በብቃት የሚወጡበትን ኹለገብ ሞያዊ ድጋፍ የመስጠት ሓላፊነት እንዳለበት በደንብ አጥኚ ኮሚቴው የማሻሻያ ረቂቅ ላይ መስፈሩ ተገልጧል፡፡

ይኹንና ‹‹ጥበቃና ጥንቃቄ›› በሚል ፓትርያርኩ እንደ መመሪያ ያቀረቧቸው ድንጋጌዎችና ግዴታዎች እንዲሁም ከልዩ ጽ/ቤታቸው ማኅበሩን አስመልክቶ በየጊዜው የሚወጡ መመሪያዎች የማኅበሩን አገልግሎት የማቀጨጭ በሒደትም አዳክሞ የማስቆም ውጤት ሊኖራቸው እንደሚችል የጉዳዩ ተከታታዮች ስጋታቸውን ያስረዳሉ፡፡

የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ፣ ቅ/ሲኖዶሱ የማኅበሩ ደንብ እንዲሻሻል ግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ባካሔደው ስብሰባ**÷ ማኅበሩ፣ ከጊዜው ጋራ የሚሔድ፣ አገልግሎቱና አደረጃጀቱ የደረሰበትን ስፋትና ዕድገት የሚመጥን፣ ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ልማት የሚጠቅም ድርጅታዊ መዋቅር እንደሚያስፈልገው ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት አምስት ሊቃነ ጳጳሳት፣ ገለልተኛ የሕግ ባለሞያዎችና የማኅበሩ አባላት በታከሉበት አጥኚ ኮሚቴ የጋራ ጥናት የተዘጋጀ መኾኑ ታውቋል፡፡

በግንቦት ወር ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. በበጎ ፈቃድ በተሰበሰቡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ማኅበረ ካህናት የተመሠረተው ማኅበሩ፤ እየተመራ የሚገኘው ቅ/ሲኖዶስ በሐምሌ ወር ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ አሻሽሎና በሙሉ ድምፅ አጽድቆ በሰጠው መተዳደርያ ደንብ ሲኾን ለአራተኛ ጊዜ የተሻሻለው ረቂቅ በወቅቱ ተመርምሮ ባለመጽደቁ በነባሩ ደንቡ እየተመራ ለመቀጠል እንደሚገደድ ተመልክቷል፡፡
******************

* እና **፡- ይህ ቃለ ጉባኤ፣ የማኅበረ ቅዱሳን የ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. መተዳደርያ ደንብ እንዲሻሻል የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ያሳለፈው ውሳኔ ነው፡፡ ቅ/ሲኖዶሱ በውሳኔው÷ የማኅበሩ ደንብ እንዲሻሻል ያስፈለገበትን ምክንያት፣ የሚሻሻልበትን አቅጣጫና ደንቡን ለማሻሻል የሠየማቸው የአጥኚ ኮሚቴው አባላት እነማንና ከየት እንደኾኑ በግልጽ አስቀምጧል፡፡

Holy Synod Ginbot 2004 E.C decision on amendments of MK000

Advertisements

27 thoughts on “የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በፓትርያርኩ እና ጳጳሳቱ ፍጥጫ ተቋጨ

 1. Birhan Asfaw May 31, 2014 at 6:33 pm Reply

  Amlake hoy ….abat siten

 2. Anonymous June 1, 2014 at 5:39 am Reply

  ‹ቅድመ ኹኔታው የማኅበሩን አገልግሎት የሚያቀጭጭ በሒደትም የሚያስቆም ነው፡፡››

 3. Anonymous June 1, 2014 at 5:53 am Reply

  እነ አባ ሰረቀና እነ ኤልያስ አብርሃ ከውጭ አካላት ጋር ሁነው ቤተክርስቲያንን እየመሩ ነው እንጂ በእውነት አሁን ኢትዮጵያ ፓትሪያሪክ አላት እንዴ. ግድ የለም ለሌባ እና ለተሃድሶ ቤተክርስቲናችንን አንሰጥም

 4. Anonymous June 1, 2014 at 5:53 am Reply

  amelake betekerestiyanachenene tebekelen

 5. Anonymous June 1, 2014 at 5:55 am Reply

  የሚያሳዝነው ፓትርያሪኩ እኮ መሰብሰብ እንኳን የሚፈልጉት ለቤተ ክርስቲያ ከሚያስልጓት አካላት ጋር ሳይሆን በየደብሩ እየዘረፉ ገንዘብ የሚያመጡላቸውን አስተዳዳሪዎች ነው እኮ…. የአዲስ አባባን ችግር ለመፍታት በተሰራው ሥራ ማንን አባረው ነው አሁን በቅዱስ ፓትርያሪኩ ጽ/ቤት ባለጉዳይ የሚያስተደናግዱኮ ዘራፊ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ናቸው….. ብቻ እኛ አሁን ለሁሉም ለእናት ለአባቶቻችን ለውንድም እሀቶቻችን በደንብ እየስረዳን ቤተ ክርስቲያንን ካላገዝን ወደፊት ምን ሊገጥመን እንደሚችል ማሳያ ነው……

 6. Anonymous June 1, 2014 at 11:30 am Reply

  TEHADSOWOCH YEMIMERACHEW PAPAS DEGMO METUBEN… LENTHELEY YEGEBANAL…..

 7. mesikelu June 1, 2014 at 11:50 am Reply

  people have to stop to donate for the church specially for those who are based in Addis ababa and Tigray, while it is very important have a paradigm shift and look after only the monasteries.this is one way to inflate woyanea sponsored gangsters in the Holy synod and undermined their influence…..Esikemeher Dires maletea newu.

 8. Anonymous June 1, 2014 at 2:34 pm Reply

  betekerstiyanachenen amlakachen egziabhere yetebekelen

 9. Anonymous June 1, 2014 at 2:34 pm Reply

  ወይ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደዚህ ቅጥረኛ የሆኑ አባቶች መፈንጫ ትሆነ… እባክህን አምላከችን እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ከውድቀት ጠብቅልን.

 10. Anonymous June 1, 2014 at 2:38 pm Reply

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነቷና ሥርዓቷ ሳይበረዝ ከትውልድ ትውልድ የሚሠራን ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲህ ከአንድ ፓትሪያሪክ ተቃውሞ ያመጣው የእሳቸው ሀሳብ ብቻ ሳይሆን የብዙዎች የውስጥም የውጭም እጆች ምን ያክል እንደበዛ ግልፅ ሁኖልናል ስለዚህ እያነመንዳንዳችን ስለ እምነታችን መነሳት፣ መበርታተና ማወቅ አለብን

 11. Anonymous June 1, 2014 at 5:43 pm Reply

  laderesachihun mereja egziabhier yistilin,ayzouchihu lenege nege erasu yichenekal.ketayun
  tiwlid egziabhier slemifelgew slenesu sibale yeteshalewin endemiaderg enamnalen.tesfa enadergalen!!!!!!!!!!!!

 12. sim June 1, 2014 at 6:05 pm Reply

  ተጠሪነታቸዉ ለቅዱስ ሲኖዶስ የሆኑት ፓትርያሪክ በአንባገነንነት የራሳቸዉን እና የላካቸዉን አካል አጀንዳ በግድ ተቀበሉ ብሎ ማስገደድ ምን የሚሉት መሪነት ነዉ፡፡ በአንባገነኖችስ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚደናቀፈዉ እስከመቸ ነዉ? አባቶቻችን ሆይ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት መንፈሳዊዉን ተጋድሎ ተጋደሉ፡፡ አቤቱ ለቤተክርስቲያን ቅን እና አርቆ አናቢ መሪን ስጥልን

 13. Asgedom June 1, 2014 at 7:49 pm Reply

  MIEMANAN TESEBASIBEN ENERSUN TILEN MEGENTEL NEW BETE KIHNETUN YITAKEFUT. AHUNIM PATRIARICH TEBIYEW KALTESTEKAKELU MEBITACHIN NEW BETEKIRSTIANUAN KEHULET KEFILEWATAL AHUNIM KESOST ENDITIKEFEL NEW AYDEL YEMIFELIGUT?

  • Anonymous June 2, 2014 at 1:50 pm Reply

   አንተ መናፈቅ አላማህ ምን እንደሆነ ያስታውቃል ወይ የወያኔ ካድሬ ወይ ደሞ ቤተክርስቲያንን ለመበተን ቆርጦ የተነሳ መናፍቅ
   አስመሳይ እዚህ ምን ትሰራለህ ?ለምን አዳራሽህ አትሄድም ?ወሽካታ መናፈቅ

 14. kuba Adugna June 2, 2014 at 6:43 am Reply

  Kidus Igiziabiher hulunim yawukawal

 15. Anonymous June 2, 2014 at 10:01 am Reply

  ትሻልን ልኬያት ትብስን አስገበኋት እንዲል በዚህ አይነት ከቤተክህነት ሰዎች የዓለማዊ ባለስልጣናት በጣም ይሻላሉ፡፡የተሃድሶ ተላላኪዎች፣ አስፈፃሚዎች ናቸው ፡፡ ወይ አይሰሩ ወይ አያሰሩ !! ለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!!!! አሜን!!!

 16. Anonymous June 2, 2014 at 11:09 am Reply

  ተጠሪነታቸዉ ለቅዱስ ሲኖዶስ የሆኑት ፓትርያሪክ በአንባገነንነት የራሳቸዉን እና የላካቸዉን አካል አጀንዳ በግድ ተቀበሉ ብሎ ማስገደድ ምን የሚሉት መሪነት ነዉ፡፡

 17. Anonymous June 2, 2014 at 11:14 am Reply

  የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አባት እስክሰጠን ሁላችንም ማህበራችንን እንጠብቅ ቤተ ክርስቲያናችንን አንርሳ

 18. AD June 2, 2014 at 11:15 am Reply

  የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አባት እስክሰጠን ሁላችንም ማህበራችንን እንጠብቅ ቤተ ክርስቲያናችንን አንርሳ

 19. Anonymous June 2, 2014 at 4:12 pm Reply

  ሀሰታም

 20. Anonymous June 3, 2014 at 3:39 pm Reply

  Mahebere Kidusan Y betekerestian Leje naw be abatoch tselote ena fikade betekerestianene endiyagelegele be kiduse sinodose fikade tesetote y teleayu y betekerestian agelegelotochene be melaw alem eyadarese yale y betekerestiane y kurete kene agelegaye tazash naw

 21. ንቁም በበኅላዌነ June 3, 2014 at 8:35 pm Reply

  የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የቅዳሴ ቤት በዓል ተከበረ

  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፐትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ቁጥራቸው ከሃያ ሰባት ያላነሰ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ በርካታ ማህበረ ምዕመናን በተገኙበት ቅዳሜ ግንቦት 23 ቀን 2006 ዓ.ም የቅዱስ ገብርኤል ፅላት ከነባሩ ቤተክርስቲያን በመውጣት በቅዱስ ፓትርያርክና በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ወደ አዲሱ ካቴድራል የገባ ሲሆን በዚህ ዕለት የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አጽም ቀደም ሲል ከበረበት ቦታ ተነስቶ ወደ አዲሱ ካቴድራል በመግባት የብፁዕነታቸው የፋልስተ አጽም በዓል ተከብሯል፡፡
  በማያያዝም ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ከማታው ዋዜማ ጀምሮ ሌሊቱን ሙሉ የማህሌቱና የቅዳሴው ሥርዓት ተከናውኖአል፡፡ ከዚያም በኋላ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት በቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በካህናትና በሰንበት ት/ቤቶች መዘምራን እና በበርካታ ሕዝብ ታጅቦ የኡደት ሥርዓት ተፈጽሟል፡፡
  በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከትለብሱ ኃይለ እምአርያም በሚል የመጽሐፍ ቃል ተነስተው፤ የዕለቱን በዓል፣ የጌታን ዕርገት እና የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የታሪክ ጎዞ በማውሳት ሰፋ ያለ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ ከዚያም የሚከተለውን ጉባኤው ቃና ቅኔ አበርክተዋል፤
  መርአተ አማኑኤል ቤቴል እንተ ቆምኪ በዘአማኑኤል ገቦ፣
  ሰርጎ አእዛንኪ እንቁ ወአጶሮግዮን ዘቦ፣
  ከዚያም በማያያዝ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ኃላፊ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ የተደረገላችሁ የመንግሥት መ/ቤቶች ተወካዮች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኃላፊዎች የጠቅላይ ቤተ ክህነት የልዩ ልዩ መምሪያ ኃላፊዎች፣ የሀገረ ስብከታችን ሠራተኞች፣ የወረዳዎች ሊቃነ ካህናት፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የአጥቢያዎች ሰራተኞች እና ምዕመናን በሙሉ በዚህ ታላቅ ሥራ ላይ የተሳተፋችሁ በዛሬው ዕለት የተገኛችሁ ሁሉ ለሼር ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤትና ሠራተኞች የዚህን ሕንጻ ቤተክርስቲያን የግንባታ ሥራ በመምራት የደከማችሁ የገዳሙ ማሕበረሰብ አባላት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረው የዚህ ታላቅ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በቸርነቱና በረድኤቱ ተፈጽሞ ለማየት ስላበቃን እንኳን ለዛሬው በዓል አደረሰን አደረሳችሁ፤
  እንደሚታወቀው ሁሉ ወደር የሌለው የእግዚአብሔር ቸርነት እየረዳን በርካታ አብያተ ክርስቲያናት እየታነጹ ናቸው፡፡ በየዘመናቱ የነበሩ እግዚአብሔርን የሚወዱ ለሥራው የተመረጡ ደጋጎች ሰዎች መሆናቸው ከቅዱሳት መጽሐፍት መረዳት ይቻላል፡፡ ልዑል እግዚአብሔር የፈቀደላቸው ሰዎች ሁሉ በየዘመናቸው የፈጸሙት ተጋድሎ በአስተማሩት ትምህርት እና በፈጸሙት በጎ ሥራ ሁሉ የሚነበቡ መጻሕፍት ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ አርአያነት እና ለምሳሌነት ለትውልድ የሚተላለፉ መንፈሳዊ ታሪክ ትተው ስላለፉ ገድላቸውና ሥራቸው ሲዘከር ይኖራል፡፡ ይህ ዛሬ የምንገኝበት የዘዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሰልጠኛ ተብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተው በ1959 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ አማካኝነት ሲሆን ለብዙ ጊዜያት አገልግሎት ከሰጠ በኋላ በደርግ ዘመነ መንግሥት በተፈጠረው የመንግስት ለውጥ ምክንያት ማሰልጠኛው ተዘግቶ እና የማሰልጠን ሥራውን አቋርጦ ለመሠረተ ትምህርት ጣቢያነት ውሎ ነበር፡፡
  ከዚህ በኋላ ዳግመኛ የተከፈተው በሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩት በታላቁ አባታችን በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድና ውሳኔ በ1971 ዓ.ም ነው፡፡ በቀጣዩ ዓመት በ1972 ዓ.ም በብፁዕነታቸው ተዘጋጅቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበው መተዳደሪያ ደንብ በጉባኤው ሙሉ ድምጽ ጸድቆ የዘዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና የካህናት ማሰልጠኛ ተብሎ እንዲጠራ መደረጉ ከመዛግብት ለመረዳት ተችሏል፡፡
  የካህናት ማሰልጠኛው መሥራች የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን ልንዘክራችው ከሚገቡት ባለ ታሪኮች አንዱ ናቸው፡፡ መካን ይቄድሶ ለሰብእ ወሰብእ ይቄድሶ ለመካን፡፡
  ሰው ቦታን ያከብራል፣ ቦታም ሰውን ያከብራል፤ እንደሚለው በእግዚአብሔር ፈቃድ በብፁዕነታቸው ጥረት የነበረውን ይህን ሥፍራ የወንጌል አገልጋዮች የእግዚአብሔር አርበኞች እንዲሆኑ የሚሰጡበትና በቃለ እግዚአብሔር የሚታይበትን መንፈሳዊ ት/ቤት ለመሆን በቅቷል፡፡ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት የተሰጠውን ትምህርት መተግባር ለመፈተን የሚአስችል ሕንጻ ቤተክርስቲያን አልነበረም አገልግሎቱ በዛፍ ሥር ይደረግ እንደነበር የስርክ ጸሎተ ምህላ፣ መሀረነ አብም፤ በዚሁ በቂ ባልሆነ ቦታ ይሠራ እንደነበር ይነገራል፡፡ ብፁዕነታቸው አገልግሎት የሚሰጥበት አነስተኛ መቃኞ እንዲሠራ ያደረጉ ሲሆን ሥራውም በየካቲት 1973 ዓ.ም ተጀምሮ በሶስት ወራት ውስጥ ተጠናቅቆ ግንቦት 19 ቀን 1973 ዓ.ም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል እንዲገባ ተደርጓል፡፡
  ይህ ቤተክርስቲያን ጠባብ ስለነበር እና ለቅኔ ማህሌት አገልግሎት የሚበቃ ሥፍራ ስላልነበረው እስከ ዛሬ ስንገለገልበት የነበረውን ያህል እንዲሰፋ የተደረገ ሲሆን ቤተክርስቲያኑ በአሁኑ ጊዜ አባቶች የሚስተናገዱበት ፅርሐ ጽዮን በ1973 ዓ.ም ስለተገነባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ገዳምና የካህናት ማሰልጠኛ ተብሎ ተባርኳል፡፡ በዚህ ዓመት የገዳሙ መተዳደሪያ ደንብ እንደገና ተሸሽሎ ጸድቋል።

  ገዳሙም እንደሌሎች የኢትዮጵያ ገዳማት የነግህ እና የሰርክ የማህበር ጸሎት የሚደርስበት፤ ሆኖ በሥርዓተ ገዳም እየተመራ እስከ ዛሬ ድረስ ዘልቋል፡፡ ይህ ገዳምና የካህናት ማሠልጠኛ ከራሱና ከሌሎቹ አህጉረ ስብከት ለስልጠና የሚላኩ ሰልጣኞችን መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርትና ሥርዓት የቤተክርስቲያን ሥርዓት በቤተክርስቲያን ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን እያገናዘቡ ትምህርት እንዲማሩና ለደረሱበት የአገልግሎት መስክ ለቤተ ክርስቲያን እንዲቆረቆሩና እውነተኛ ትምህርትን እንዲአስተምሩ መምህራንን አፍርቷል፡፡
  ከዚህ ሌላ ከመጀመሪያው ኮርስ ስልጠና በተጓዳኝ የአዳሪ ትምህርት ቤት በማቋቋም በአካባቢው እናት አባት የሌላቸውን ሕጻናትና ወጣቶች በመሰብሰብ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ትምህርት የአብነት ትምህርት እንዲማሩ ተደርጎአል፡፡ ከዚህ ጋር የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት እንዲኖራቸው እና በተግባርም የማስተማር ልምድ እንዲኖራቸው ለማድረግና ዘመናዊ ትምህርት እንዲማሩ በማድረግ ማሰልጠኛው ዛሬ በልዩ ልዩ ከፍተኛ ማዕረግ ላይ የሚገኙ ምሁራንን አፍርቷል፡፡ በዚህ መሠረት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሠልጠኛ ተምረው በአሁኑ ወቅት በሊቀ ጵጵስና ደረጃ ላይ የሚገኙ በርካታ ብፁዓን አባቶች ለማፍራት በቅቷል፡፡ ዛሬ በመካከላችን የማይገኙትን ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅን እና ብፁዕ አቡነ ይስሐቅን በገዳሙ ያስለፉትን የአገልግሎት እና መምህርነት ሥራ በማሰብ ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ በተጨማሪም ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች የሚማሩ ወጣቶች ወደ ገዳሙና ማሠልጠኛው ገብተው የክረምት የዕረፍት ጊዜአቸውን በትምህርት እና በስልጠና እንዲአሳልፉ ተደርጓል፡፡
  በዚህ የትምህርትና የሥልጠና መርሐ ግብር መሠረት ስለ ሃይማኖታቸው እና ስለ ቤተክርስቲያናቸው እንዲአውቁ የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውም ፈጽመው ከተመረቁ በኋላ በተሠማሩበት ሥራ የተዋሕዶ ሃይማኖታቸውን የመጠበቅ እና ሃይማኖታቸውን እንዲአገለግሉ ለማድረግ ተችሏል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም መነሻውና መሠረቱ ይህ ገዳም ነው፡፡ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ፍሬዎች ሊገኙ የቻሉት ገዳሙና ካህናት ማሰልጠኛው የመንፈሳዊ ዕውቀት መቅሰሚያ የገዳማዊ ሕይወት መገኛ የልማት እና የሥራ ባህል መማሪያ የቤተክርስቲያን መሠረት መጣያ አንድ ክርስቲያናዊ ቋንቋ የሚነገርበት ነው፡፡
  ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሰፊ ቤተክርስቲያን እንዲሠራ ምኞት ቢኖራቸውም ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም በማለዳው ክፍለ ዕለት በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥሪ ከመካከላችን ተለይተዋል፡፡ የታላቁ አባታችን ምኞት ውጥን እና ጅምር ሥራ ሁሉ ይህ ታላቅ ኃላፊነት ከወደቀባቸው እና ቀንበሩን በሚሸከሙበት አማካኝነት ሥራው ተጠናክሮ በተለመደው ሁኔታ እንደቀጠለ ነው፡፡ ለወደፊቱም እንደዚሁ ይቀጥላል፡፡ ከእነዚህ መካከል አዲስ የታነጹት የአብነት ትምህርት መማሪያ የተግባር ቤት፣ ቢሮ፣ የእንግዳ ማረፊያ፣ መጋዘኖች፣ የመጸዳጃ ቤት፣ የነባሮቹ ሕንጻዎች ዕድሳት ሊጣቀሱ ከሚችሉ ሥራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ዛሬ በዚህ ገዳም ለመሰብሰባችን ምክንያት የሆነው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘበኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጥቅምት 4 ቀን 1997 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ አስቀምጡ፡፡
  በመሆኑም ዛሬ ለመመረቅ በቃ፡፡ የዚህ ሕንጻ ምርቃት የገዳማችንን መስፋት የሚአበስር እና የታላቁ አባታችን የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምኞታቸውን መሳካት አመላካች ነው፡፡ ዛሬ ልጆቻቸው ሁሉ በዚሁ ተሰብስበን የምናከብረውን ደስታ በመካከላችን ተገኝተው ቢመለከቱ ኑሮ ምን ያህል ደስተኛ እንደሚሆኑ ሁላችንም እናምናለን፡፡ ቅዱስ ዳዊት የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለማነጽ ባሰበ ጊዜ በልጁ በሰሎሞን እንዲታነጽ እንዲፈቀድለት እና እንዲሠራው ሁሉ ታላቁ አባታችን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ያሰቡትን እና የተመኙትን ይህንን ሕንጻ ቤተክርስቲያን እኛ ልጆቻቸው እንደጀመርነው ሠርተን እንድንፈጽመው እና የዚህ መንፈሳዊ ታሪክ ባለቤቶች ለመሆን እንድንበቃ ያስቻለን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ በመሥራት የሚገኘው መንፈሳዊ በረከት የላቀ ስለሆነ የሰው ልጆች ከዚህ በረከት እንዳይጠቀሙ ጠላት ዲያብሎስ ልዩ ልዩ ፈተናዎችንና እንቅፋቶችን መፍጠሩ ባይቀርም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረው ሁሉ ሥራ ይፈጸማል፡፡
  ስለዚህ በልዑል እግዚአብሔር ቸርነት በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱሳን ተራዳኢነት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንደሚያዩት በቤተክርስቲያናችን ልጆች ጥረት ሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ተፈጽሞ እንሆ ለምረቃ በቅተናልና ደስ ይበላችሁ፤ ለዚህ ያደረሰን ቸሩ አምላካችን ይክበር ይመስገን፡፡ እንደቀደሙት አባቶቻችን እኛም ደግሞ በቀሪው ዘመናችን የእግዚአብሔር ቸርነት የሚነገርባቸው ቤተክርስቲያን የምትኮራባቸው ሀገር የምትከበርባቸው እና ለምሳሌነት ሊዘከሩ የሚችሉ መልካም ታሪኮችን ለትውልድ ለማስተላለፍ ታጥቀን መነሳት ይኖርብናል፤ በዚህ መልክ ልንሠራቸው ከሚገቡ የልማትና ማህበራዊ አገልግሎት መካከል ይህ የሰው አእምሮ የሚለማበት መንፈሳዊ ተቋም አንዱ ነው፡፡ በዚህ ታላቅ የደስታ ቀን ለዚህ ያበቃንን ፈጣሪያችንን እናመሰግነዋለን፤ በልዩ ልዩ መልክ የረዱንን ሁሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናመሰግናቸዋለን፤ በማለት ብፁዕነታቸው ሰፋ ያለ ሪፖርት አሰምተዋል፤ የብፁዕነታቸው ሪፖርት እንደተጠናቀቀ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲሳት መምህር የሚከተለውን ጉባኤ ቃና ቅኔ አበርክተዋል፡፡
  ጎርጎርዮስ ሊተ ገዳምከ ባሕረ ሰሊሆም ይእቲ፡፡
  አእይንተ ብርሃን ዘውስጥ ክልኤተ አምጣነ ረከብኩ ባቲ፡፡
  በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዓት አእይንቲክሙ እለ ርዕያ ወአእዛኒክሙ እለ ሰምአ በሚል ርዕስ ጅምረው የሚከተለውን አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
  ይህንን ጸጋ ያዩ አይኖቻችሁ የሰሙ ጆሮቻችሁ ንዑዳን ክቡራን ናቸው፡፡ ነቢያት ጌታ ይወርዳል፣ ይወለዳል፣ ይሞታል፣ ይነሳል እያሉ ትንቢት ሲናገሩ ቆይተው አረፍተ ዘመን ገትቶአቸው ትንቢታቸው በተፈጸመ ጊዜ በአካል ጌታን አላዩም፤ ነገር ግን ከእነርሱ በኋላ የተነሡ ሐዋርያት ናቸው፡፡

  ምንጭ: http://www.addisababa.eotc.org.et

 22. ንቁም በበኅላዌነ June 3, 2014 at 8:40 pm Reply

  “ማኅበረ ቅዱሳንም መነሻውና መሠረቱ ይህ ገዳም ነው፡፡ “

 23. Abunu June 4, 2014 at 3:38 am Reply

  “ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ” ይሉሃል ይሄ ነው::

  http://medhanialemeotcks.org/wp-content/uploads/2013/02/%E1%8C%AD%E1%8A%95%E1%8C%8B%E1%8D%8D-Final.pdf

 24. Anonymous June 4, 2014 at 7:26 pm Reply

  ብጹዕ አቡነ ቄርሎሰ አዲሱ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የደርግ የለውጥ ሐዋርያ ሆኖ ያገለገለ ነው አሁን ደግሞ ፈረንጅ ሀገር ሲቃርም ከርሞ ካባውን ገልብጦ ወያኔ ኢህአዴግ ሆኖ መጣና ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ ይህንንም በመቃወማችን ነበር በተለይ እኔን አንድ የወያኔ ባለስልጣን በፓትርያርኩ ምርጫ ሰሞን ስልክ ደውሎ አርፈህ ካልተቀመጥክ ምላስህን እቆርጠዋለሁ ብሎ ያስፈራራኝ አሁንም ማትያስ የወያኔ ስራ አስፈጻሚ በመሆን ማህበረ ቅዱሳንን የሚያሳድደውና ማህበራቸውን ለማፍረስ የሚቃትተው ብለው የተናገሩት እውነታቸው ነው ማለት ነው፡፡

 25. mesfin atnaf June 6, 2014 at 7:13 am Reply

  oh , getaye hoy antew fered

 26. daniel June 10, 2014 at 8:01 am Reply

  ተጠሪነታቸዉ ለቅዱስ ሲኖዶስ የሆኑት ፓትርያሪክ በአንባገነንነት የራሳቸዉን እና የላካቸዉን አካል አጀንዳ በግድ ተቀበሉ ብሎ ማስገደድ ምን የሚሉት መሪነት ነዉ፡፡ በአንባገነኖችስ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚደናቀፈዉ እስከመቸ ነዉ? አባቶቻችን ሆይ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት መንፈሳዊዉን ተጋድሎ ተጋደሉ፡፡ አቤቱ ለቤተክርስቲያን ቅን እና አርቆ አናቢ መሪን ስጥልን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: