ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ ለመመደብ ያቀረቡትን ጥያቄ ቅ/ሲኖዶሱ ውድቅ አደረገው – ‹‹ለምነው አብረውኝ ይሥሩ ያሏቸውን ሊቀ ጳጳስ በመገፍተር ኃይልዎን ማሳየትዎ እንዴት ነው የሚገፋው?››

 • በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚመራው በቅዱስ ሲኖዶስ በተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ሊቀ ጳጳስ እንጂ በፓትርያርኩ የምደባ ምክረ ሐሳብ አለመኾኑን በመጥቀስ ነው ጥያቄአቸው ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው፡፡
 • ከዚህም ባሻገር የብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከሓላፊነት መልቀቅ ምክንያታዊ ማብራሪያ እንደሚያስፈልገው ምልዓተ ጉባኤው ፓትርያርኩን በማሳሰቡ ለአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የሊቀ ጳጳስ ምደባ አልተደረገም፡፡
 • ምልዓተ ጉባኤው ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በሓላፊነታቸው እንዲቆዩ ለማግባባት ጥረት ያደረገ ቢኾንም ከአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱና ከፓትርያርኩ አላስፈላጊ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ጋራ በተያያዘ በተደጋጋሚ እያገረሸ በሽምግልና ሲፈታ የቆየው አለመግባባት እልባት ሊያገኝ አለመቻሉ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

Holy Synod08

 • የፓትርያርኩ አቋም ካሳዘናቸው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል የምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ በምልዓተ ጉባኤው መካከል ቆመው ሲናገሩ፡- ‹‹ገና አንድ ዓመት ሳይሞላዎት ለምነው አብረውኝ ይሥሩ ያሏቸውን ሊቀ ጳጳስ በመገፍተር ኃይልዎን ማሳየትዎ እንዴት ነው ሥራ ኾኖ የሚቀጥለው? ከወዲኹ እንዴት ነው የሚገፋው?›› ብለዋል፤ ንግግራቸውም እንደተፈጸመ የቅ/ሲኖዶሱ አባላት ባልተመለደ አኳኋን በጭብጨባ ድጋፋቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡
 • ከአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናት ዝግጅቱ ጋራ በተያያዘ በተፈጠሩ አለመግባባቶችና በተደረጉ ሽምግልናዎች መካከል ፓትርያርኩ ብፁዕነታቸውን ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን አባል ነዎት ወይ?›› ብለው እስከ መጠየቅ መድረሳቸው ተጠቁሟል፡፡
 • የአ/አ ሀ/ስብከት እስከ ጥቅምት ፳፻፯ ዓ.ም. የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ያለሊቀ ጳጳስ ሊቆይ ይችላል፤ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናቱ ከትግበራ እንደታገተ ነው፤ ለውጡን በመደገፍ የተንቀሳቀሱ አገልጋዮች ከአማሳኞች ኔትወርክ በቀል ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፡፡
 • በመጨረሻም የብፁዕነታቸውን ከሓላፊነት መልቀቅ÷ ከምልዓተ ጉባኤው ቁጥጥር ውጭ የኾኑት ፓትርያርኩ፣ ከሀ/ስብከቱ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች ጋራ የፈጠሩትን ቁርኝት በገሃድ ያረጋገጠ ኾኗል፡፡
 • በአማካሪነት ስም የፓትርያርኩን ልዩ ጽ/ቤት በተቆጣጠሩት የአማሳኞች አለቃ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ አማካይነት ፓትርያርኩን ያለቀጠሮ የማግኘት ልዩ መብት ያላቸው አማሳኞቹ፣ ‹‹ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ብቻ ሳይኾን ከቅ/ሲኖዶስ አባልነት እናወርዳቸዋለን፤ ወደ ጅማቸው እንመልሳቸዋለን›› እያሉ በፓትርያርኩ ፊት በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ላይ ሲዝቱ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል፡፡
Advertisements

22 thoughts on “ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ ለመመደብ ያቀረቡትን ጥያቄ ቅ/ሲኖዶሱ ውድቅ አደረገው – ‹‹ለምነው አብረውኝ ይሥሩ ያሏቸውን ሊቀ ጳጳስ በመገፍተር ኃይልዎን ማሳየትዎ እንዴት ነው የሚገፋው?››

 1. Anonymous May 28, 2014 at 7:19 am Reply

  እውነት እውነት ያልታደሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሳይሆኑ እኛ በጎቹ ነን፡፡ በቃ የክፋታችን ጽዋ ሞልቶ እግዚአብሔር ጠባቂ አልሰጣችሁም አለን፡፡ ደገኛ ሊቃነ ጳጳሳቱም ሰብሳቢ አባት (ቅዱስ ፓትርያርክ) አታገኙም ተባሉ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እንኳን እንደ ተራ ተርታ ስብሰባ ሳይጠናቀቅ ጭብጨባ አቋማቸውን የሚገልጹበት ሆነ፡፡
  አሁን በግል የምንበረታ ጥሩ ግን አባቶቻችን አባካችሁ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ ምዕመናን ልጆቻችሁን አሰልፋሁ ሱባኤ ግቡ፡፡ እንጩህ፡፡ በእንባችን እንታጠብ፡፡
  እግዝኦ እግዚኦ
  ተስፋ አለኝ ከመሃል አገር

 2. Anonymous May 28, 2014 at 7:20 am Reply

  እውነት እውነት ያልታደሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሳይሆኑ እኛ በጎቹ ነን፡፡
  በቃ የክፋታችን ጽዋ ሞልቶ እግዚአብሔር ጠባቂ አልሰጣችሁም አለን፡፡ ደገኛ ሊቃነ ጳጳሳቱም ሰብሳቢ አባት (ቅዱስ ፓትርያርክ) አታገኙም ተባሉ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እንኳን እንደ ተራ ተርታ ስብሰባ ሳይጠናቀቅ ተጠናቀቀ ተብሎ መግለጫ ተሰጠ፡፡ ጭብጨባ አቋማቸውን የሚገልጹበት ሆነ፡፡
  አሁን በግል የምንበረታ ጥሩ ግን አባቶቻችን አባካችሁ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ ምዕመናን ልጆቻችሁን አሰልፋሁ ሱባኤ ግቡ፡፡ እንጩህ፡፡ በእንባችን እንታጠብ፡፡
  እግዝኦ እግዚኦ
  ተስፋ አለኝ ከመሃል አገር

 3. አስካለ ዮሐንስ May 28, 2014 at 11:44 am Reply

  ” ዮሴፍን የማያውቅ ፈርኦን በመነሳቱ ምክንያት በእስራኤል
  ዘሥጋ ላይ መከራ አፀናባቸው።”
  እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ!

 4. Anonymous May 28, 2014 at 4:19 pm Reply

  የወያኔ ደባ መቼ ተጠናቀቀና ? ወያኔ ሾማቸው እሳቸው ደሞ በተራቸው ለተቀመጡበት ወንበር እንኩን የማያስቡ የኢየሱስ ክርስቶስ እንደራሴ መሆን እንዲህ ቀላል መስሏቸው አይደል በወያኔ የተሾሙት ወይ በራስ ከራሳቸው አልሆኑ

 5. mulugeta May 28, 2014 at 7:07 pm Reply

  I have no words to explain how the patriarch shifted away from the church interst. He is not abide by the fiduciary duty that the church expecting from him. I am not blaming others for his wicked performance. He him self should be responsible for yje mess. He promised to attract the fathers who weren’t sure that he fit for that place. They were right and he didn’t waste time to fullfill what he and his alike people like. They will have no rest till our church stop functining, however the promise by our Lord Eyesus Kirstos to our mother church that always kept her ftom such act by abune matyas and gis desiples of destruction. She will perfirm their funeral as she did to others 2ho work hard against her.

 6. Kebede May 28, 2014 at 7:29 pm Reply

  በግፈኞች እጅና በቃየልያኑ ‘ጳጳሳት’ ተባባሪነት የፈሰሰው የንፁሁ የብፁዕ ወቅዶስ አቡነ ቴዎፍሎስ-አቤል ደም መንበሩን ረግሞታል ልበል? በግፍ ከኢትዮጵያ እንዲሰደዱ የሆኑት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሀዘንና እልቅሶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አይደርስም ማለት ይቻላል ? ቅዱስ አባታችን በሕይዎት እያሉ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ ሌሎች 2 ‘አባቶች’ አንዱ ሲሞት ሁለተኛው በመተካት ፥የጦር መሳርያ ባላቸው ወገኖቻቸው ፈቅድና ምርጫ መንበሩ ላይ ሲቀመጡበት እየታየ ታድያ እንዴት ሁኖ ነው ”ሲኖዶሱ በመንፈስ ቅዱስ ነው የሚመራው ” ማለት የሚቻለው ? መነፈስ ቅዱስ የሚመራው ሲኖዶስ በአባላቱ መካከል ፍፁም የሆነ ፍቅርና አንድነት ይኖራል እንጅ መናናቅ፤ ዓለማዊ የሆነ የመንደርተኝነትና የዘረኛነት ስሜት በዚህ ሁኔታ ለዓለም ግልጽ ሁኖ አይታይም ነበር።

 7. Getachew Fetene May 28, 2014 at 9:24 pm Reply

  Our Patriarch may be misleaded. Let us pray for him.
  Corruption is becoming the identity of our church. This is really shame and difficult to accept.
  Our God bless our fathers, who understand this real problem and being one and standing for truth. I am proud of them.
  When I think those who are responsible to lead the church at the middle level are forgetting the power of our Lord. Most of them are guided by their fleshy mind. God will reveal the truth. He will punish those who ignored his power.
  Those who are at the leading position should not block us from looking our Lord. Let us think for this innocent peaple and poor but beatiful country.

 8. G/egezeabher May 29, 2014 at 5:15 am Reply

  yalitadelechi afisa lekemechi ,lela tegadalayi

 9. Anonymous May 29, 2014 at 9:05 am Reply

  የወያኔ ደባ መቼ ተጠናቀቀና ?

 10. Anonymous May 29, 2014 at 12:37 pm Reply

  Abetu yeker yebelen….

 11. ንቁ May 29, 2014 at 3:21 pm Reply

  ውድ ሐራውያን!

  እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በሰላም አደረሳችሁ።

  ” ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ፣ ዓይን ያለው ይመልከት፣ ልብ ያለው ያስተውል! ”

  ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በታሪኳ አይታው የማታውቀው አጣብቂኝ ውስጥ የገባችበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው ቢባል ማጋነን አይሆንብኝም። ይህ ማለት በየጊዜው ተነስተው የነበሩ ነገስታትና ያለፉት ሥርዓቶች ግፍ አልፈጸሙባትም ማለት ሳይሆን እንደዛሬው በውስጥም በውጭም በተደራጀና በተመጋገበ መንገድና ስልት መከራው አልጸናባትም ብዬ ለመከራከር እደፍራለሁ። ለምን በሉኝ?
  የቅድስት ቤተክርስቲያንን የቀድሞ ታሪኳን ለማጠየም፣ ውበቷን ለማስጠላትና ውለታዋን ለመናድና ለማፈራረስ የሚደረገው ዘመቻ የቤተክርስቲያኒቱን ከፍተኛውን የሥልጣን እርከን በመቆጣጠርና ያንኑም ሥልጣናቸውን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተሰለፉትንና ለቤተክርስቲያኒቱ የውስጥ እግር እሳት የሆኑባት አባቶችና አለቆችን ታስቦበትና በሚገባ የተጠና በሚመስል መልኩ ችግር ያለባቸውና የአንድ አካባቢ ሰዎች መሆናቸውን ስታዘብ ፍርሃት ያድርብኛል። ለምን የአንድ አካባቢ ሰዎች ሆኑ ሳይሆን የኔ ፍራቻ በአንድም ይሁን በሌላ እነዚህ ሰዎች በአብዛኛው የቤተክርስቲያኒቱ ተከታይ ዘንድ ጥሩ ስም የሌላቸው፣ በሙስና የተዘፈቁ፣ ለፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ መናፍቃን ሽፋን የሚሰጡና የግል ችግር ያለባቸው መሆኑ ላይ ነው። ምክንያቱም እንደዚህ ዓይነት ስብእና ያላቸውን ሰዎች ኮምፕሮማይዝ ወይም አስገድዶ ለቤተክርስቲያኒቱ ጠላት አድርጎ ማሰለፍ እጅግ ቀላል ስለሚሆን ነው።
  ለማሳያ ያህል: –
  1。በጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አሁን ደግሞ በአማካሪነት ስም
  የፓትርያርኩን ልዩ ጽ/ቤት የተቆጣጠሩት ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ፥
  2。በጠቅላይ ቤተክህነት የቀድሞው የካህናት መምሪያ ሃላፊ የአሁኑ የቤቶችና ሕንፃዎች አስመላሽ ኮሚቴ
  ሰብሳቢ መጋቤ ካህናት ኃይለሥላሴ ዘማርያም ( ይፋ ባልወጣ መልኩም ቢሆን የህወሓት አባልና ካድሬ)፥
  3。በጠቅላይ ቤተክህነት የቀድሞው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ የአሁኑ የስልጠና መምሪያ
  (በእርሳቸው አጠራር “የሊቃውንት መምሪያ”)ሃላፊ፥ ወ。ዘ。ተ。
  እነዚህ የጨለማው ቡድን አመራር አባላት ቤተክርስቲያኒቱን ከውጭ ሆኖ ከሚገፋው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችና የዚሁ እምነት ተከታይ በሆኑ ፖለቲከኞችና የኢህአዴግ አመራሮች ተዘጋጅቶ የቀረበላቸውን የተሳሳተ መረጃ ፓትርያርኩን ለማሳሳትና ጳጳሳቱን ለማስፈራራት ይጠቀሙበታል። በቅድስት ቤተክርስቲያናችን የአደረጃጀትና የአሰራር ለውጥ እንዳይተገበርና በኋላቀርና በዘመድ አዝማድ አሰራር እጅና እግሯ ታስሮ ምንም እንዳትቀሳቀስ በማድረግ ልጆቿን አስበርግጎ ከቅፅረ ቤተክርስቲያን ለማስኮብለል የማይፈጸም የተንኮል አሰራር የለም ማለት ይቻላል። ይህ ከውጭ ሆኖ የሚገፋው ሃይል የመንግስትን ሥልጣንና የግብር ከፋዩን ሀብትና ንብረት ተገን አድርጎ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የአደባባይ ምስጢር ነው።
  የዚህ ቡድን ቀንደኛ አመራሮች መመሪያ ሰጭ፣ መረጃ ሰብሳቢና ተንታኝ እንዲሁም እርምጃ ወሳጅ በመሆን በታቀደና በተቀነባበረ ዘዴ ቅድስት ቤተክርስቲያን የመከራው ዘመን እንዲጸናባት ሁሉንም ዓይነት አቅም እየተጠቀሙ ይገኛሉ።
  ለማሳያ ያህል:-

  1. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፥ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የኢህአዴግ ም/ቤት አባልና ሊቀመንበር፣ ብሔር-ወላይታ፣
  እምነት-ፕሮቴስታንት፣
  2. ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም፥ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትርና የኢህአዴግ ም/ቤት አባል፣ ብሔር-ወላይታ፣
  እምነት-ፕሮቴስታንት
  3. አቶ አሰፋ አብዩ ፥ የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተርና የኢህአዴግ ም/ቤት አባል፣ ብሔር-ሐዲያ፣
  እምነት -ፕሮቴስታንት
  4. አቶ ያሬድ ዘሪሁን፥ የውስጥ ደህንነት ዋና መምሪያ ዳይሬክተርና የኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬ፣ ብሔር-ሐዲያ
  እምነት -ፕሮቴስታንት ወ.ዘ.ተ.

  የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ወዴት ናችሁ?ወቅቱ እጅግ የከፋ ጊዜ ነው። እባካችሁ ኦርቶዶክሳውያን ይህንን የከፋ ችግር በማስተዋል እንመልከት! አካባቢያችንን በንቃት እንጠብቅ!ከቤተሰቦቻችን ጀምረን ለንስሐ አባቶቻችን፣ ለምንቀርባቸው ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እንዲጠነቀቁና ቤተክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ እናድርግ!

  በቸርነቱ አፅራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን፣ እኛንም ይጠብቀን።

 12. Anonymous May 30, 2014 at 9:35 am Reply

  ante weshetam MK

  • ንቁም በበሕላዌነ May 31, 2014 at 10:40 pm Reply

   “አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም” አሉ ፣አበው።

 13. Anonymous May 30, 2014 at 7:13 pm Reply

  yhe degemo ke Mk gare men agenagewe? wero bela!

 14. Anonymous May 31, 2014 at 1:45 pm Reply

  እነዚህ የጨለማው ቡድን አመራር አባላት ቤተክርስቲያኒቱን ከውጭ ሆኖ ከሚገፋው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችና የዚሁ እምነት ተከታይ በሆኑ ፖለቲከኞችና የኢህአዴግ አመራሮች ተዘጋጅቶ የቀረበላቸውን የተሳሳተ መረጃ ፓትርያርኩን ለማሳሳትና ጳጳሳቱን ለማስፈራራት ይጠቀሙበታል። በቅድስት ቤተክርስቲያናችን የአደረጃጀትና የአሰራር ለውጥ እንዳይተገበርና በኋላቀርና በዘመድ አዝማድ አሰራር እጅና እግሯ ታስሮ ምንም እንዳትቀሳቀስ በማድረግ ልጆቿን አስበርግጎ ከቅፅረ ቤተክርስቲያን ለማስኮብለል የማይፈጸም የተንኮል አሰራር የለም ማለት ይቻላል። ይህ ከውጭ ሆኖ የሚገፋው ሃይል የመንግስትን ሥልጣንና የግብር ከፋዩን ሀብትና ንብረት ተገን አድርጎ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የአደባባይ ምስጢር ነው።

 15. Anonymous May 31, 2014 at 1:47 pm Reply

  የዚህ ቡድን ቀንደኛ አመራሮች መመሪያ ሰጭ፣ መረጃ ሰብሳቢና ተንታኝ እንዲሁም እርምጃ ወሳጅ በመሆን በታቀደና በተቀነባበረ ዘዴ ቅድስት ቤተክርስቲያን የመከራው ዘመን እንዲጸናባት ሁሉንም ዓይነት አቅም እየተጠቀሙ ይገኛሉ።

 16. Anonymous May 31, 2014 at 1:47 pm Reply

  የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ወዴት ናችሁ?ወቅቱ እጅግ የከፋ ጊዜ ነው። እባካችሁ ኦርቶዶክሳውያን ይህንን የከፋ ችግር በማስተዋል እንመልከት! አካባቢያችንን በንቃት እንጠብቅ!ከቤተሰቦቻችን ጀምረን ለንስሐ አባቶቻችን፣ ለምንቀርባቸው ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እንዲጠነቀቁና ቤተክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ እናድርግ!

 17. Anonymous June 3, 2014 at 8:30 pm Reply

  ብጹዕ አቡነ ቄርሎሰ አዲሱ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የደርግ የለውጥ ሐዋርያ ሆኖ ያገለገለ ነው አሁን ደግሞ ፈረንጅ ሀገር ሲቃርም ከርሞ ካባውን ገልብጦ ወያኔ ኢህአዴግ ሆኖ መጣና ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ ይህንንም በመቃወማችን ነበር በተለይ እኔን በረከት ስምኦን የተባለው የወያኔ ባለስልጣን በፓትርያርኩ ምርጫ ሰሞን ስልክ ደውሎ አርፈህ ካልተቀመጥክ ምላስህን እቆርጠዋለሁ ብሎ ያስፈራራኝ አሁንም ማትያስ የወያኔ ስራ አስፈጻሚ በመሆን ማህበረ ቅዱሳንን የሚያሳድደው ና ማህበራቸውን ለማፍረስ የሚቃትተው ብለው የተናገሩት እውነታቸው ነው ማለት ነው፡፡

 18. Berhanu Melaku June 6, 2014 at 10:00 pm Reply

  ማ.ቅ ጠነከረ ማለት የፕሮቴስታንት እምነት ከኦርቶዶክስ እምነት ፈተና በዛበት ማለት ነው።
  የኦርቶዶክስ ልጆችን እያፋጁ እምነቷን ገፍትሮ ለመጣል የሚደረግ ሴራ ነው።
  ዛሬ የተያዘው ቅኔ “አማራ ኦረቶዶክስ ነው” ሳይሆን የሚል “ኦርቶዶክሰ አማራ ነው” የሚል ነው።
  በዚህም ሆነ በዚያ እምነታችንን አባቶቻችን ባቆዩት ትውፊት እንጠብቃለን !!!
  ኃይላችን አብ፣ ብርሃናችን ወልድ፣ መሪያችን መንፈስ ቅዱስ፣ አማላጃችን ድንግል ማርያም፣ ጀነራላችን ቅዱስ ገብርኤል፣ እና ተፋላሚያችን ቅዱስ ሚካኤል ናቸው፤ አንፈራም በእምነታችን ቀልድ የለም !!!

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር ።

 19. Fire Mariam June 9, 2014 at 9:05 am Reply

  Min aynet zemen lay deresin? Yetelat filatsa mechem betekiristianin tiluat ayawukim!!! silezih leabatochachinim Feriha Egziabherin Yasasbachew hulu bersu fekad endihon metsom mestelay bicha new yemiasfeligew enji fetenan meshesh kiristianawi sinemigbar aydelem

 20. Anonymous June 11, 2014 at 2:31 pm Reply

  really we have to pray a lot for this case. let our GOD with us for ever!!!!!

 21. Anonymous October 13, 2014 at 9:08 am Reply

  cher worei yaseman

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: