በማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ረቂቅ የፓትርያርኩና የምልዓተ ጉባኤው ልዩነት ተካሯል፤ ለመሥራት ተቸግሬአለኹ ያሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከፓትርያርኩ ረዳት ሓላፊነት ለመልቀቅ ጠይቀዋል

Holy Synod in session

 • ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከጨለማው ቡድንና ፖለቲከኞች ጋራ የመከሩበትን የራሳቸው ያልኾነ የተልእኮ ሐሳብና አጀንዳ የተቃወሟቸውን የምልዓተ ጉባኤውን አባላት ‹‹በገንዘብ የተገዛችኹ›› እያሉ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችና በአማሳኞች መሠረተ ቢስ ክሥና ውንጀላ በመዝለፍ ቅዱስ ሲኖዶሱን ተዳፍረዋል፡፡
 • አቡነ ማትያስ ለአጥኚ ኮሚቴው የላኩት ባለ24 አናቅጽ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች ሳይቀነሱና ውይይት ሳይደረግባቸው በደንቡ ካልተካተቱና ረቂቁ በሌላ ኮሚቴ ዳግመኛ ካልታየ በሚል አጀንዳውን በራሳቸው አቋም ብቻ ለመቋጨት ያደረጉት ሙከራ፣ በፍጹም አንድነት በቆሙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተቃውሞ ውድቅ በመደረጉ በመተዳደርያ ደንቡ ማሻሻያ ላይ የሚደረገው የምልዓተ ጉባኤው ውይይት ይቀጥላል፡፡
 • ከድንጋጌዎችና ግዴታዎቹ መመሪያ ውስጥ፡- የማኅበሩ ፈቃድ በየዓመቱ እንዲታደስ፤ ማኅበሩ ከቅፅረ ቤተ ክርስቲያን ውጭ እንዳይሰበሰብና ቢሮ እንዳይከፍት፤ የሠራተኞቹ ቅጥርና ምደባ በመንበረ ፓትርያርኩ እንዲካሔድ፤ አባላቱ በግልም በቡድንም በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሥራ፣ በቀኖናዊ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌና በሰንበት ት/ቤቶች ጉዳይ እንዳይገቡ፤ የማኅበሩ አባላት በግል ለሚሠሩት ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና የሀገርን ሰላም የሚፃረር ድርጊት›› ማኅበሩ ሓላፊነት እንዲወስድ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
 • የአጥኚ ኮሚቴው አብላጫ አባላት፣ የፓትርያርኩን የድንጋጌዎችና ግዴታዎች መመሪያ ‹‹ከቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔና የደንብ ማሻሻያ አቅጣጫ ጋራ የማይሔድ›› በሚል ያልተቀበሉት ሲኾን ማኅበሩ በበኩሉ በተለይ በፈቃድ ዕድሳት ረገድ የተነሣው ሐሳብ ‹‹በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ በጸደቀ መተዳደርያ ደንብ የሚመራውን የማኅበሩን አገልግሎት ለማስቆም የሚደረግ አካሔድ ነው፤›› ብሏል፡
 • ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የመሥራት አቅሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ፣ በቤተ ክርስቲያናችንም እየሠራ ባለው ሥራ ኹሉ አብያተ ክርስቲያናትን፣ አድባራትንና ገዳማትን በስፋት እየጠቀመ ያለ፣ በምሁራን የታቀፈ ኹለንተናዊ ዝግጅት ያለው ማኅበር ስለኾነና ብዙ የልማት ሥራዎችን በመሥራት ላይ የሚገኝ በመኾኑ ራሱን የቻለ ድርጅታዊ መዋቅር ሊዘጋጅለት እንደሚገባ ታምኖበታል፡፡›› /የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አጥኚ ኮሚቴውን ባቋቋመበት የግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ምልዓተ ጉባኤው ያሳለፈው ውሳኔ/
 • ‹‹ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና እያደገ በመሔድ ላይ ለሚገኘው የማኅበሩ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የሚመጥንና ለወደፊቱም ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ዕድገት የሚጠቅም የላቀና የተሻለ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለማበርከት የሚያስችለው ራሱን የቻለ መዋቅራዊ አደረጃጀት ሊዘጋጅለትና የማኅበሩን አገልግሎቶችና የወደፊት ኹኔታዎች ያገናዘበ መተዳደርያ ደንብ ሊቀረፅለት ይገባል፡፡›› /የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. የምልዓተ ጉባኤ ውሳኔው ለአጥኚ ኮሚቴው የሰጠው የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ አቅጣጫ/

Holy Synod04

 • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሓላፊነታቸው በአርኣያነት የሚጠቀስ ጥረት ባደረጉበት የመዋቅር የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት ሳቢያ ከፓትርያርኩ ጋራ ውስብስብ ችግር ውስጥ እንደገቡና አብረው ለመሥራት እንደሚቸገሩ በምልዓተ ጉባኤው መካከል ቆመው የተናገሩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ‹‹አባቶቼ፣ አሰናብቱኝ›› ሲሉ ቅዱስ ሲኖዶሱን ጠይቀዋል፤ ምልዓተ ጉባኤው እንደሚነጋገርበት ይጠበቃል፡፡
 • ፓትርያርኩ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መልቀቂያ ያቀረቡበትን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የረዳት ሊቀ ጳጳስ ምደባ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ለመከፋፈል እየተጠቀሙበት እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡

Holy Synod07

 • የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ በቅርቡ ባረፉት ብፁዕ አቡነ ቶማስ ቦታ÷ ምዕራብ ጎጃም – ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከት÷ ተዛውረዋል፤ በምትካቸው የአኵስም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩትና የመንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ሰላማ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት መመደባቸው ተጠቁሟል፡፡
Advertisements

26 thoughts on “በማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ረቂቅ የፓትርያርኩና የምልዓተ ጉባኤው ልዩነት ተካሯል፤ ለመሥራት ተቸግሬአለኹ ያሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከፓትርያርኩ ረዳት ሓላፊነት ለመልቀቅ ጠይቀዋል

 1. Anonymous May 27, 2014 at 7:46 am Reply

  betekerstiyanachenen lemafrese yemisrute sera mene derja endederse new yemiyasayew egna betekerstiyananchenen anasdeferm. mk is always working for the protection and existence of our church —–

 2. Anonymous May 27, 2014 at 7:47 am Reply

  ቤተክርስቲናችንን ለማጥፋት ጳጳሱንና መሰሎቹን እየተጠቀሙባቸው ስለሆነ በቤተክርስቲን ቀልድ የለም ሁላችንም ዝም አንልም…

 3. Anonymous May 27, 2014 at 7:54 am Reply

  SEE OUR CHURCH IS GOING ON …….

 4. laekeselam May 27, 2014 at 8:20 am Reply

  MK EgziAbHer ale ayizogn musegnochin atlefu yikesesu.

 5. kuba Adugna May 27, 2014 at 8:45 am Reply

  Igiziabiher Mahibarun Yitabikilin

 6. Anonymous May 27, 2014 at 8:48 am Reply

  ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ግን ይደቃሉ፡፡ ሰውየው ምን ነካቸው? ከእግዚአብሔር ጋር የሚሠራውን መግፋት ከእግዚአብሔር ጋር መታገል መሆኑን አስተውለውት ይሆን? እንደ ያዕቆብ በፍቅር ካልሆን በቀር እግዚአብሔርን ታግሎ ያሸነፈ ማነው? እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው፡፡

 7. kebede May 27, 2014 at 8:59 am Reply

  God is from the beginning God He is unchangeable He was with early Church Fathers what about today? Why not? He is with our hero the honorable members of HOLY SYNOD. I read this in tear still we should pray. By the way MK PLANTED BY THE WILL OF GOD HIMSELF THEREFORE IT IS IMPOSSIBLE ON MK. THE PRAYER OF ALL SAINTS ARE WITH THEM. I profoundly admired about all the temptation arose in MK any way GOLD IS AFFIRMED ITS GOLDNESS AFTER COME OUT FROM THE FIRE. WE KNOW EVERY THING ALL THE FATHERS OF THE MONASTERY ARE WITH YOU INCLUDING THE HONORABLE HOLY SYNOD. OUR PATRIARCH BY HIS LACK OF MANAGEMENT UNKNOWINGLY IS LOADED BY OTHER THE SO CALLED ……….THE FOLLOWER OF PROTESTANT.

 8. melese Girma May 27, 2014 at 10:04 am Reply

  ጥሩ ነው ቀጥሉበት

 9. Anonymous May 27, 2014 at 10:30 am Reply

  Tegten enitseliy ebakachihu leamlakachin
  yemisanew yelm abatachinin wedemelikamuhadab endiyamtalin.

 10. Anonymous May 27, 2014 at 11:18 am Reply

  The thing we should do is crying for our selves, praying for our fathers to be one in any circumstances. Mk is only one wing of the church service, there are many that need strong stands of our fathers, too.

 11. Anonymous May 27, 2014 at 12:48 pm Reply

  ከሰዉ አስተሳሰብ በላይ እግዚአብሔር ያስባልና የእዉነተኛ አባቶችን ዉሳኔ በተስፋ እነጠብቃለን፡፡

 12. Anonymous May 27, 2014 at 12:52 pm Reply

  How could we design our strategy!? We are educated and we strong. The GOD of the world is with us! So what makes us dormant? Shall we keep silent while our religion is endangered by the enemy of our faith????????????????????????

 13. Anonymous May 27, 2014 at 1:43 pm Reply

  Bata.krestianacenan.entadagat

 14. Anonymous May 27, 2014 at 3:28 pm Reply

  please let us know more info as quick as possible. God is with us

 15. Anonymous May 27, 2014 at 7:41 pm Reply

  Gifu’omu igzio leile yigefu’uni

 16. Anonymous May 28, 2014 at 12:53 pm Reply

  Anonymous የባሰ አታምጣ የሚሉት አባቶቻችን ለካስ ወደው አይደለም ፤ አቅለው ብለው ቆለለው አሉ የባሰ አታምጣ

 17. KENANTE YEMIBELT HAILE KEGNA GAR ALE May 28, 2014 at 1:56 pm Reply

  YIHE KOM BILO MASSEBIN YITEYIKAL. YIHCHI AGER KEBAD NEGER EYAGATEMAT NWE. SEWOCHU LEMIN MASTEWAL ENDAKATACHEW ALIGEBANIM , YESEWU CHINKLAT MEYAZACHEWNM YATERATIRAL . HIDASIE EYETEBALE SINT NEGER LEMESRAT EYETASEBE NWU EYETEBALE ZEWTRE KEBERO YIMETAL BIYANSE YIH NEGER LIDENAKEF YICHLAL BILO MASSEB ENDET AKATACHEW , SEWOCH AYDELUM ENDIE ENDET EGIBT ENA SORIYA , LIBIYA ENDET MEMAR YAKTACHEWAL. HAGERIN YEMITEKIM , TWLIDEN YEMIYANITS MUSINAN YEMIKAWOM , HAGERAWI SIMET YALEWN ZEGA YEMIYAFERAN MAHIBER LEMAFRES ? MIN MALET NWU ? . SEWYEWUS MIN NEKACHEWU MOT AFAF LAY HONEW FETARIN AYFERUM ENDIE MIN ALE BEHIMANOTACHEW KOMEW YEHIWOTEN TSIWA BIKEBELU ENESU KASCHEGERUACHEW . ALBEZAM ENDIE ? EYETEMERAN YALENEW BE ETHIOPIYAWIYAN AYDELEM ENDIE ? MINDNEWU CHIGRACHEW KEN LITLEN YICHLAL BILEWU AYASIBUM ENDIE . NEFSE GEDAY NEGE TEYIZO LATEFAW NEBSI LITEYEK ENDEMICHIL BIYASIB NORO WHENI AYWORDIM NEBER . SADAM HUSSEN EKO KEBERO GUDGUAD WUST NWU YETEGEGNEWU , GADAFI , HUSMINOMUBAREK KENESU ENIMAR EBAKACHIHU ATINEKAKUN BESAT CHAWETA AYMERACHIHU .

 18. KENANTE YEMIBELT HAILE KEGNA GAR ALE May 28, 2014 at 2:04 pm Reply

  ABATOCH BETSINAT KOMACHIHU ATSNUN . YIHCH YEMENGISTESEMAYAT TSIWA NECH. TALAKUNA JEGNAW BITSUE ABATACHEN ABUNE PETROSEN ENASIBACHEWU. BESIGA LAY ENJI BENEFS LAY SILTAN YELELACHEWN HILEGNOCH ANIFRA . YEMIYASFERAN NEGER BINOR YIHN TEKETILO LIMETA YEMICHLEWN HAGERAWI KEWIS . LEMIN HIMANOT ZER GOSA POLETICA WETADER SIBIL BALESILTAN HABTAM DEHA WOND SET LIJ AWAKI SHIMAGILE WETAT AYLEYIM YIHNEN MASEB NWU YETESANACHEWU SEWOCHU.

 19. Anonymous May 28, 2014 at 4:01 pm Reply

  ከሰዉ አስተሳሰብ በላይ እግዚአብሔር ያስባልና የእዉነተኛ አባቶችን ዉሳኔ በተስፋ እነጠብቃለን፡፡

 20. Anonymous May 28, 2014 at 5:46 pm Reply

  It is time to awake from sleep and fight for her/his religion!!!!

 21. M.E May 28, 2014 at 5:48 pm Reply

  It is time for every christian to awake from sleep and fight for his region!!!!

 22. Berhanu Melaku June 6, 2014 at 10:46 pm Reply

  ማ.ቅ ጠነከረ ቤተ ክረስቲያናት ከዘመኑ ጋር ትውፊትን እያጣጣመችና ዘመን አመጣሽ ጠላቶቿን እየተከላከለች የሶስተኛ ሽህ አመቷን ጉዞ በቀጥታ መጔዝ ትችላለች ማለት ነው። እኔ የማ.ቅ አባል አይደለሁም፤ ነገር ግን ማ.ቅን የማውቀው በሥራው ነው።
  በዚህም በዚያም በኩል የሚሰማው ዜና ጥቅም የሚባል የሥጋ ፓራሳይት አባቶችን ቦርቡሮ ግብቶባቸዋል ነው። ለመነኩሴ ሃብት፣ሚስት፣ቤት፣ዘርና አገር የለውም። ይህ መንፈሳዊ ሕግ ዛሬ ለኔቢጤው ብቻ ባገሩ ምድር ላይ ሆኗል። መንግስትና አንዳንድ ጥቅመኛ (ዘረኛ) ኣባቶች ስራቸው የኦርቶዶክስ ልጆችን እያፋጁ እምነቷን ገፍትሮ ለመጣል የሚደረግ ሴራ ነው።
  ዛሬ የተያዘው ቅኔ “አማራ ኦረቶዶክስ ነው” ሳይሆን የሚል “ኦርቶዶክሰ አማራ ነው” የሚል ነው።
  በዚህም ሆነ በዚያ እምነታችንን አባቶቻችን ባቆዩት ትውፊት እንጠብቃለን !!! እባካችሁ እንባየን ጥረጉልኝ?
  ኃይላችን አብ፣ ብርሃናችን ወልድ፣ መሪያችን መንፈስ ቅዱስ፣ አማላጃችን ድንግል ማርያም፣ ጀነራላችን ቅዱስ ገብርኤል፣ እና ተፋላሚያችን ቅዱስ ሚካኤል ናቸው፤ አንፈራም በእምነታችን ቀልድ የለም !!!

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር ።

 23. orthodoxtewahedo June 7, 2014 at 5:50 am Reply

  ከማንም አልበልጥም በሀጥያት ብዛት ግን አዎ እበልጣለሁ ። ይሔም ሆኖ እግዚአብሔአጥ አምላክ የክብር አክሊል ባስቀመጠበት ላይ አንዳች እንዳላደርግ አልፌም እንዳልዳፈር ቅዱስ ዳዊት አባታችን ያስተማረው ማህተቤተ ነ።: ታድያ ምነው እናንተስ ስማችሁን በቅዱሳኑ ስም ሸፍናችሁ ምግባራችሁ እና ደፍረታችሁ ግን አባቶችን፣ ዻጳሳትን ማዋረዳችሁ: መናፍቅ በሚል ማህተማችሁ እያተማችሁ እናንተኑ ናፋቂ አደረጋችሁ: የማይገባችሁን የዲያብሎስን የድፍረት ባህሪ አከናነባችሁ : በድፍረት ስለሁሉ ትናገራላችሁ፣ ትሳደባላችሁ:: እናንተ ለቤተክርስቲያን የምትሰጡት ጥቅም፣ እርዳታ እግዚአብሔር እንደሚውድ አገልጋዬቹን ከማክበር ጋር ስላልሆነ እነሱን ከብር እንደአሳጣዘችሁ ልፋታችሁ በእሱ ፊት ከንቱ ነው። የምእመናን እንባና ጭንቀት እሳት ሆኖ ከነ ሁከታችሁ ያጥፋችሁ:። ለቤቱ ከእናንተ በላይ እሱ ጠባቂዋ ነው።

 24. Anonymous May 27, 2016 at 6:54 am Reply

  Egziabher yichemeribet

 25. Anonymous May 27, 2016 at 2:06 pm Reply

  ይህን የምታነቡ ሁሉ እባካችሁ “የሰይጣን ጎል አትዮዽያ” የሚለውን መፅሐፍ አንብቡ እና ስለ ፓትርያሪካችን አስተያየት ስጡ፡፡ በቅድስት ድንግል ማርያም አንብቡት!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

 26. Anonymous May 27, 2016 at 2:09 pm Reply

  ይህን የምታነቡ ሁሉ እባካችሁ “የሰይጣን ጎል አትዮዽያ” የሚለውን መፅሐፍ አንብቡ እና ስለ ፓትርያሪካችን አስተያየት ስጡ፡፡ በቅድስት ድንግል ማርያም አንብቡት!!!!!!!!!!!!!!!!!!! Pray for God!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: