ሰበር ዜና – ባልተጠናቀቀው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ መግለጫ ተሰጠ፤ ጋዜጠኞችን አደናግሯል

Holy Synod00

ከግንቦት ፭ – ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ለ16 ቀናት የተካሔደውን የምልዓተ ስብሰባ ውሳኔዎች በ17 ነጥቦች የዘረዘረውና ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በፓትርያርኩ ቢነበብም የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ላይ የተጀመረው ውይይት ቀጥሎ ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ተናግረዋል፡፡

በመግለጫው ተ.ቁ.(12) ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ በተመለከተ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ወጥቶ የነበረው ደንብ እንዲሻሻል በአጥኚ ኮሚቴው የተዘጋጀው 34 ገጽ ረቂቅ መቅረቡ ተጠቅሷል፤ አያይዞም ‹‹ምልዓተ ጉባኤው ከተመለከተ በኋላ በስፋት ውይይት ተደርጎበታል›› ከማለት በቀር ስለውሳኔ ያመለከተው ነገር የለም፡፡

የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ ለምልዓተ ጉባኤው ቀርቦ በንባብ የተሰማው ትላንት ጥዋት ሲኾን ውይይቱ ግን ከቀትር በኋላ 9፡00 ላይ ተጀምሮ በፓትርያርኩ ተቀባይነት የሌላቸው አቋሞች ሳቢያ ወደ ዝርዝር ጉዳይ ሳይገባ ለዛሬ በይደር ቆይቶ እንደነበር የስብሰባው ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ መግለጫው በፓትርያርኩ ንባብ ከተሰማ በኋላ ጥያቄ ለማቅረብ ባለመፈቀዱ ጋዜጠኞች እንዲወጡ ቢደረግም፣ የቤቶችና ሕንፃዎች አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም ባልተመለሱ ቤቶችና ሕንፃዎች ጉዳይ አሟልተው እንዲያቀርቡ የታዘዙትን ሪፖርት ለማሰማት ተጠርተው ሲገቡ መታየታቸውና የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ስለ ማኅበሩ አጀንዳ ቀጣይነት መናገራቸው የስብሰባው ሒደት በአንዳች ምክንያት ዕግዳት ውስጥ እንደገባና በወጉ እንዳልተጠናቀቀ አመላክቶ አልፏል፡፡

ይኹንና ምልዓተ ጉባኤው በመግለጫው፡-

 • የቤተ ክርስቲያኒቱ ቋሚ ንብረቶች ኾነው በመንበረ ፓትርያርክ አካባቢ የሚገኙት እስከ አኹን ድረስ ያልተመለሱ አራት ሕንፃዎች በሚመለሱበት ኹኔታ አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግ ከስምምነት ላይ መድረሱን ጠቅሷል፡፡
 • በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመኾን ለመላው አህጉረ ስብከት በአርኣያነት የሚጠቀሰውን የመዋቅር የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት በቅድመ ግንባር የመሩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጥያቄአቸው መሠረት ከሓላፊነታቸው ለቀዋል፡፡
 • በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የተዘጋጀው የሚዲያዎች ስርጭት ደንብ ጸድቋል፡፡ በደንቡ መሠረት የብዙኃን መገናኛ ቦርድ በቋሚ ሲኖዶሱ ተቋቁሞ ሥራውን ይጀምራል፡፡
 • ገዳማትን መልሶ ማቋቋምና ማጠናከር እንዲቻል የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ሰፋ ያለ ጥናት ተጠንቶ እንዲቀርብ በጥቅምቱ ምልዓተ ጉባኤ ብፁዓን አበው ያሉበት አንድ ኮሚቴ በሠየመው መሠረት ተዘጋጅቶ በቀረበው ጥናት ላይ ጉባኤው ተነጋግሮ፣ በ40 ገዳማት ላይ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለማከናወን የቀረበውን ጥናት ጉባኤው አጽድቆ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
 • ቤተ ክርስቲያናችን ሥራዋን በመሪ ዕቅድ እንድታከናውን የተዘጋጀው የመሪ ዕቅድ ዘገባ ለምልዓተ ጉባኤው ቀርቦ በስፋት የተገለጸ ሲኾን የመጨረሻው መሪ ዕቅድ በጥራዝ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብና በቋሚ ሲኖዶስ ታይቶ አስፈላጊው እንዲፈጸም ጉባኤው ተስማምቷል፡፡
 • የሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ረቂቅ ምልዓተ ጉባኤው በንባብ አዳምጦ በአብዛኛው ነጥቦች ላይ ማሻሻያ በማድረግና በማረም ለተጨማሪ እርማት ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ባለሞያዎች ያሉበት ኮሚቴ ቅ/ሲኖዶሱ ሠይሟል፤ ለጥቅምቱ ምልዓተ ጉባኤ እንዲያቀርቡም ተወስኗል፡፡
 • ወደፊት ለኤጲስ ቆጶስነት ስለሚመረጡ ቆሞሳት እንዲዘጋጅ ተደርጎ የነበረውን መመዘኛ ጉባኤው በንባብ ካዳመጠ በኋላ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ረቂቅ ከተዘረዘረው መመዘኛ ጋራ ተገናዝቦ ለወደፊቱ እንዲቀርብ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
 • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቦርድ ደንብ በተመለከተ አንዳንድ መሻሻል የሚገባቸው ነጥቦች በመኖራቸው ይህንኑ ደንብ ተመልክተውና መሻሻል የሚገባውን አሻሽለው ለጥቅምት ፳፻፯ ዓ.ም. የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሚያቀርቡ ከሊቃነ ጳጳሳትና ከሕግ ባለሞያዎች ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
 • በቤተ ክርስቲያናችን በቅዱስ ሲኖዶስ ማእከላዊነት የሚደረገው የሜሮን አወጣጥ ዝግጅት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሥራውን የሚከታተሉ ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተመደቡ ሲኾን በጀትም እንዲያዝ ተወስኗል፡፡
 • በእንግሊዝ ለሚኖሩ አገልጋዮችና ምእመናን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ለብድር ያቀረቡትን የገንዘብ ጥያቄ ጉባኤው ተነጋግሮ ከጠየቁት 4‚800‚000.00 (ዐራት ሚልዮን ስምንት መቶ ሺሕ ብር) ውስጥ 2‚400‚000.00 (ኹለት ሚልዮን አራት መቶ ሺሕ ብር) በስጦታ እንዲሰጣቸው ኾኖ የገንዘብ አሰባሰቡም በቋሚ ሲኖዶስ ታይቶ ውሳኔ እንዲያገኝ ምልዓተ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡
 • ፓትርያርኩ በሀገር ውስጥና በውጭው ዓለም ባሉ አህጉረ ስብከት የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በእጅጉ ጠቃሚ በመኾኑ ለሐዋርያዊ ጉዞው በሚያስፈልገው በጀት ላይ የማሻሻያ ጥናት ተደርጎ ለቀጣዩ በጀት ዓመት እንዲቀርብ ተወስኗል፡፡
 • በመንበረ ፓትርያርክ ቅጥር ግቢ ለብፁዓን አበው ወደ ሕክምና ቦታ ማመላለሻ፣ በውጭ አህጉረ ስብከት የሚኖሩ ብፁዓን አበው ከውጭ ሲመጡና ሲመለሱ መቀበያና መሸኛ የሚኾን መኪና በማስፈለጉ ለቀጣዩ በጀት ዓመት በጀት እንዲያዝ፣ ከበጎ አድራጊዎች ርዳታ እንዲፈለግ ተወስኗል፡፡
 • ለሕዳሴ ግድብ ቤተ ክርስቲያናችን ቀደም ሲል ካደረገችው የገንዘብ አስተዋፅኦ በተጨማሪ ብፁዓን አበው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ የየወረዳውና የየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፣ መንፈሳዊ ኮሌጆች፣ ገዳማትና መንፈሳውያን ት/ቤቶች፣ ሠራተኞች በበጎ ፈቃደኛነት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለቦንድ ግዥ እንዲያውሉ ተወስኗል፡፡

Holy Synod Ginbot 2006 Meglecha

Advertisements

14 thoughts on “ሰበር ዜና – ባልተጠናቀቀው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ መግለጫ ተሰጠ፤ ጋዜጠኞችን አደናግሯል

 1. Berhanu Y.berhan May 27, 2014 at 4:21 pm Reply

  Thank you Hara tewahedo keep it up God bless you.

 2. Anonymous May 27, 2014 at 4:22 pm Reply

  yegibagne lekirestose——————–
  emenugne egiziabher ke egna gar new ke eneresu kalut ke egna ga yalut yebeletalu Mk enidezih tefeteneh ketsenah ewunet yemekeraw zemen alefe3 malet new emenugngne egiziabher hayal new minim ayametum sihon egziabeher eneresun lemekdem ayezegeyem!!!!!!!!

 3. Anonymous May 27, 2014 at 4:52 pm Reply

  Harawoch kale hiwot yasemalin. bezihu ketlu

 4. Anonymous May 27, 2014 at 6:05 pm Reply

  betekerstiyanene kezerafi lenadenat yegebebanal

 5. Anonymous May 27, 2014 at 6:40 pm Reply

  Hi Harawiyan,

  በመግለጫው ተ.ቁ.(12) ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ በተመለከተ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ወጥቶ የነበረው ደንብ እንዲሻሻል በአጥኚ ኮሚቴው የተዘጋጀው 34 ገጽ ረቂቅ መቅረቡ ተጠቅሷል፤ አያይዞም ‹‹ምልዓተ ጉባኤው ከተመለከተ በኋላ በስፋት ውይይት ተደርጎበታል›› ………………….”ከማለት በቀር ስለውሳኔ ያመለከተው ነገር የለም”፡፡ what do you want to share us ? As you read it in the first paragraph of the Synod letter, it says ” THE HOLY SYSNOD HAS PREPARED AN AGENDA ITEMS WHICH ARE VERY CRUCIAL FOR THE NATION’S PEACE AND DEVELOPMENT, AND HOLY SYNOD HAS MADE THE NECESSARY DISCUSSION AND PASSED THE FOLLOWING DECISIONS.”

  PERIOD! SO WHAT DO YOU WANT NOW? I THINK YOU GUYS BETTER TO RECONCILE AND WORK WITH YOUR FATHERS AND BROTHERS IN CHRIST. AFTER ALL, THIS IS SPIRITUAL SERVICE NOT POLITICS. I LOVE YOU GUYS AND APPRECIATED YOUR COURAGE AND FINALLY I WISH ALL THE BEST FOR YOUR FUTURE SPIRITUAL ENDEVOUR!

  MAY GOD GIVE ALL OF US HIS WISDOM AND MORE BLESSINGS TO SERVE OUR MOTHER CHURCH, EOTC.

  BE EWINET YITAYAL

  • Anonymous May 27, 2014 at 10:30 pm Reply

   ምን እየተደረገ እንደሆነ ታውቀዋለህ::

   • Anonymous May 28, 2014 at 3:04 am

    Ahun antem yebetekirstian lij negne til yihon endezih ayinet yewerede e-christianawi konko eyetetekemih. Endeante ayinetu eko new yemahiberun ageligilot yazegawwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwww!!!!

 6. abebe May 28, 2014 at 1:57 am Reply

  betekrstiyann be ewqetachn, begenzebachn enagelgl, yabatochachnn feleg enketel yemilutn eyegefu, musegnochn na yebetekrstiyan telatochn beguya aqfo ewnetegnoch yebeterkstiyan ljochn meqawem na gefto maswtat beswm be egziabherm zend yemiyasweqs sra now. Egziaher awaqi now. hulum yalfal.

 7. WOLET MARIAM May 28, 2014 at 6:26 am Reply

  YEMENTEBEKEW KEEGZIABHERE BICHA NEW. AYE ABA MATIAS ENDEH ADEREGUNE KEFETARIACHEN ENAGEGNEW ENDGE LELA MINE YEBALAL, YALEFUTEN ABATOCHACHENEN ARAYA ENADERG ENGE.YACHE BSEW LAYE YEFERDENW AHUN BERASACHEN SIDERESE MNDEN LENEL NEW?????

  .

 8. Nakachew Getnet May 28, 2014 at 7:18 am Reply

  hulu neger le-bego newu . EGZEABHER betun yetebekal . yewust telatoch ena seytan legizewu des bilachewum ashenafi gen bemechereshaw ewunete ena ewunet becha newu.

 9. Anonymous May 28, 2014 at 2:57 pm Reply

  በእንግሊዝ ለሚኖሩ አገልጋዮችና ምእመናን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ለብድር ያቀረቡትን የገንዘብ ጥያቄ ጉባኤው ተነጋግሮ ከጠየቁት 4‚800‚000.00 (ዐራት ሚልዮን ስምንት መቶ ሺሕ ብር) ውስጥ 2‚400‚000.00 (ኹለት ሚልዮን አራት መቶ ሺሕ ብር) በስጦታ እንዲሰጣቸው ኾኖ የገንዘብ አሰባሰቡም በቋሚ ሲኖዶስ ታይቶ ውሳኔ እንዲያገኝ ምልዓተ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡
  What does it mean? A number of churches in rural and small towns have huge problems even to make KIdase once in a month. Whereas those who are capable to get service with short distance getting this amount of money as free? I know that building a chuch wherever it is completely incomparable than those who steal the money of us with corruption! But who need more support is the question. Sorry our fathers forgetting the base where the majority of EOTC follower are found and their strangle to pass through a dark valley in every devastating day and situation seems forgetting yourself where you came. God and Our Mother St.Virgin Mary help you our fathers who are honestly struggling for the strong Orthodox.

  • weg May 29, 2014 at 12:53 am Reply

   I agree with you. They supposed to give priority for rural churchs

 10. habte May 28, 2014 at 3:24 pm Reply

  ከአቡነ ማቲያስ ኋላ የመንግስት እጅ አለበት፡፡ከመንግስት ኋላ ደግሞ ንቡረ ዕዶች እና ተሀድሶዋች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ከቤተክርስቲያን ኋላ አለ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ይጠብቃታል፡፡ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡

 11. Anonymous May 29, 2014 at 6:37 pm Reply

  SELAM !
  ASTEYAYET LEMESTET SELETEFEKEDELEGN EGZIABHERE YAKBERELEGN !
  1/ SEDEB AZELE ASTEYAYETOCHE BE ETIHOPIAWIAN ZENDE ATSEYAFI KEMEHONACHEW BASHSGERE YEBELOGUN DEREJA ZEKE SELAMIADERGU : SIHON BATAWETUACHEW ALFEW KEWETUM TOLO BETANESUACHEW !
  2/ LOLE LEGETAW TESHUAMI LE SHUAMIW METAMENU YENORE NEGERE SELEHONE LIGERMEN AYEGEBAM, YELEKUN YEHE HULU ENDIHON EYANDANDACHEN YABEREKETNEW ASTEWATSEO MENORUN TEGENZEBEN FETARI BEYEKERTAW TEMELKETON BETUN ATSEDETO MENGAWEN YENE BALACHEW BETAMENU EREGNOCH YASTEBEKE ZENDE ENETSELEY.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: