ቅ/ሲኖዶስ በመንግሥት ተወርሰው ስላልተመለሱ ቤቶችና ሕንፃዎች የተሟላ መረጃና ሪፖርት እንዲቀርብ አስመላሽ ኮሚቴውን አዘዘ፤ የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፹ ቀን የቅ/ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት ይዘከራል

Arat Kilo twins tower

 • በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ሐረር ከተሞች ከ310 ያላነሱ የተወረሱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቪላ ቤቶችና ሕንፃዎች አልተመለሱም፤ ለተመለሱት ቤቶችና ሕንፃዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለማውጣት የተያዘው ዕቅድ በተሟላ ኹኔታ ተሳክቷል፡፡
 • ለቤተ ክርስቲያኒቱ የተመለሱት 16 ሕንፃዎች፣ 12 መጋዘኖች፣ 110 ቪላ ቤቶች ዓመታዊ የኪራይ ገቢ ከ23 ሚልዮን ብር በላይ ደርሷል፤ የኪራይ ተመን ማስተካከያ ለማድረግ ጥናት እየተካሔደ ነው፡፡
 • የአራት ኪሎውን የኢሕአዴግ ዋና ጽ/ቤት ጨምሮ ለኦሮሚያ ሲቪል ሰርቪስ፣ ለፊንፊኔ የምግብ አዳራሽ እና ለተወካዮች ምክር ቤት ሕንፃዎች በካሳነት የታሰበው 70 ሚልዮን ብርና በምትክነት ይሰጣል የተባለው የግንባታ ቦታ እያነጋገረ ነው፡፡

The Freedom Tower

 • በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. ተቋቁሞ በርካታ ይዞታዎችን ያስመለሰውና በአኹኑ ወቅት አምስት አባላትን ይዞ በመጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም ሰብሳቢነት የሚመራው የቤቶችና ሕንፃዎች አስመላሽ ኮሚቴ፣ ስለ ካሳ ክፍያውና የአራት ኪሎ ‹መንትዮች ሕንፃ›ን ለማስመለስ ከመንግሥት አካል ጋራ ውይይት እያደረግኹ ነው በሚል ያቀረበው ሪፖርት ‹‹አጥጋቢ ያልኾነና ያልተሟላ›› በሚል ተገምግሟል፡፡
 • የአስመላሽ ኮሚቴው፣ ሪፖርቱ፣ ቤቶቹና ሕንፃዎች ከከተማው የልማት ፕሮግራም አኳያ የሚገኙበትን ወቅታዊ ኹኔታ አካቶና በመረጃ ተደግፎ ለሰኞ የምልዓተ ጉባኤው ስብሰባ እንዲቀርብ በቅዱስ ሲኖዶሱ ትእዛዝ ተሰጥቶታል፡፡
 • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የምሕንድስና ዘርፍ ዋና ሓላፊ የነበሩትና ከግንባታዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ጋራ ተያይዞ ሲነሡ ለቆዩ የከፉ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች ተጠያቂ የኾኑት አቶ ሰሎሞን ካሳዬ ከዋና ሓላፊነታቸው ተባረዋል!! ዘርፉ በባለሞያዎች የቴክኒክ ኮሚቴ በጊዜያዊነት እየተመራ ነው፡፡፡

***

 • በመንግሥት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መሠረት በማድረግ ተጠንተው የተጠናቀቁና ዋጋ የወጣባቸውን ሕንፃዎችና ቪላ ቤቶች ከከተማው የፕላንና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመነጋገር የተጠናቀቁ የግንባታ ፕላኖችን በመውሰድ ቤተ ክርስቲያንን ከከፍተኛ ወጪ ለማዳን ጥረት ተደርጓል፡፡
 • አህጉረ ስብከት እንዲሁም ታላላቅ አድባራትና ገዳማት በአክስዮን እንዲሳተፉ በማድረግ ባሉን ክፍት ቦታዎችና ሰፋፊ መሬቶች ላይ ለእንግዶች ማረፊያ፣ ለመኖሪያ፣ ለሆስፒታል፣ ለቢሮ ወዘተ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ሕንፃዎችን በመገንባት ለቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የሚያግዝ አቅም ለመፍጠር በቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የረጅምና የአጭር ጊዜ የልማት ዕቅዶች ተይዘዋል፡፡
 • የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በቴክኒክና በፋይናንስ ድጋፍ ረገድ የጂ.ቲ.ዝድ፣ የቻይናና የቱርክ ኩባንያዎችን ሰብስበው ያነጋገሩ ሲኾን በተለይም የቻይናና የቱርክ ኩባንያዎች ጊዜና ወጪ ቆጣቢ ሕንፃዎች መገንባት የሚቻል መኾኑ ከኩባንያዎቹ ከተገኙት ዶኩመንቶች አንጻር ታምኖበታል፡፡

Piyassa Bete Yordanos and Zewditu building

 • በመሀል ፒያሳ ዘውዲቱ ሕንፃ ጀርባ በሚገኘው 749 ካሬ ሜትር ክፍት ቦታ ላይ በማስተር ፕላኑ መሠረት ለቦታው ታሪካዊነት በሚስማማ አኳኋን ኹለት ባለአራት ደርብ ሕንፃዎችን በ48 ሚልዮን ብር ወጪ ለመገንባትና በማልሚያ ፕላን ስምምነት የግንባታ ፈቃድ ከተገኘባቸው አምስት ቦታዎች መካከል በአንድ ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ አንድ ኹለገብ ሕንፃ ከቻይናው ሲ.ጂ.ሲ.ኦ.ሲ ጋራ በመተባበር በ3 ቢልዮን ብር ለማሠራት የቀረበው የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ዕቅድ በቅ/ሲኖዶሱ ጸድቋል፡፡
 • የኹለቱን የግንባታ ፕሮጀክቶች ዲዛይኖች ሥራ ከክፍያ ነጻ በበጎ ፈቃድ አግልግሎት የሠሩትና በምልዓተ ጉባኤው ፊት ቀርበው ከቦርዱ ሊቀ ጳጳስ ጋራ ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ባለሞያዎች በቅዱስ ሲኖዶሱ ተመስግነዋል፤ ፓትርያርኩ በምልዓተ ጉባኤው ማብቂያ ዕብነ መሠረት በማስቀመጥ የግንባታ ሥራውን ያስጀምራሉ ተብሏል፡፡

***

Alemayehu-atomsa-source-ERTA

ነፍስ ኄር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ወስመ ጥምቀቱ ገብረ እግዚአብሔር

 • የቀድሞው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ወስመ ጥምቀቱ ገብረ እግዚአብሔር የ፹ ቀን መታሰቢያ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በዛሬው ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል፡፡
 • በፀረ ሙስና አቋማቸው የሚታወቁት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ወስመ ጥምቀቱ ገብረ እግዚአብሔር፣ በአንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደተናፈሰው፣ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ተከታይ አልነበሩም፡፡
 • በኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሕግ ባለሞያና በምዕራብ ወለጋ ሀ/ስብከት ግምቢ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አባልና የአገልግሎቱ ፍሬ የኾኑት ባለቤታቸው ወ/ሮ ፀሐይ በንቲ እንዲሁም ቤተሰዎቻቸው ብፁዕ አቡነ ኄኖክ ኖላዊ ኄር ኾነው የሚመክሯቸው፣ በቅዱሳን ወዳጅነታቸውና በጽኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ ምግባራቸው የሚታወቁ ናቸው፡፡
 • የዐደባባይ ሰዎችንና የፖሊቲካ ባለሥልጣናትን ፕሮቴስታንታዊ በማድረግና ፕሮቴስታንታዊ ናቸው በሚል ፕሮቴስታንታዊነት ማስፋፋት፣ በኵላዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ላይ በፈጠራ ታሪክ የሚገፋ ጎሳዊ ጥላቻን በማጠናከር ሀገራዊ አንድነትን ለአደጋ ለማጋለጥ አድርባይ ፖሊቲከኞችና ጎጠኞች በስፋት የተያያዙት የብተና ፕሮጀክት ነው፡፡
 • ከነፍስ ኄር አቶ ዓለማየሁ የፖሊቲካ አቋም ጋራ ፍቅር ባይኖረንም በዚህ መንፈስ በሐዋርያዊቷ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚሰነዘረውን የአድርባዮችና ጎጠኞች ሤራና ስልት ማጋለጥ ግን ኦርቶዶክሳዊነታችን ግድ ይለናል፡፡
 • ሐራዊ ምንጮች እንደተረጋገጠው፣ ነፍስ ኄር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ በሓላፊነት በሠሩባቸው አካባቢዎች ኹሉ በአጥቢያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በአባልነት ተመዝግበው አስተዋፅኦ በማድረግ የምእመንነት ግዴታቸውን የተወጡ ኦርቶዶክሳዊ ነበሩ፡፡
 • በአዲስ አበባ የመካኒሳ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ አባል የነበሩት የቅዱሳን ወዳጅ አቶ ዓለማየሁ፣ በስፋት ከሚነገረው መመረዝ ጋራ በተያያዘ በታመሙበት ወቅት በጥያቄአቸው መሠረት የደብረ ሊባኖስ ገዳም አበው መነኰሳት በመኖርያ ቤታቸው እየተገኙ ጸሎት ያደርጉላቸው፣ ጠበልም ያጠምቋቸው ነበር፡፡
 • ሥርዓተ ቀብራቸው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መከናወኑ መንግሥታዊ የቀብር ሥርዓትን ለማሳመር ሳይሆን በሃይማኖታቸው ኦርቶዶክሳዊ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ስለኾኑ ነው!!
Advertisements

4 thoughts on “ቅ/ሲኖዶስ በመንግሥት ተወርሰው ስላልተመለሱ ቤቶችና ሕንፃዎች የተሟላ መረጃና ሪፖርት እንዲቀርብ አስመላሽ ኮሚቴውን አዘዘ፤ የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፹ ቀን የቅ/ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት ይዘከራል

 1. Senait May 26, 2014 at 3:47 am Reply

  “የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፹ ቀን የቅ/ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት ይዘከራል”…abo endezih ayinet news batinegiruns? I heard z guy is not member of Tewahido thogh i am not sure

  • Anonymous May 26, 2014 at 1:29 pm Reply

   @Senait read the details

 2. Anonymous May 26, 2014 at 9:33 am Reply

  LET US BREAK THE SYSTEM OF PRTOTESTANT . PLEASE ANNOUNCE FOR ALL ORTHODOX TEWAHIDO FOLLOWERS TO KNOW THE TRUTH.

 3. Senait May 26, 2014 at 1:05 pm Reply

  Wow Harawoch, God bless you for the quick elaboration about Ato Alemayehu. I was confused with the rumor that he was protestant, but now you told us the truth. Good job!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: