በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ላይ ሲካሔድ የቆየው የቅ/ሲኖዶሱ ውይይት ተጠናቀቀ፤ ስብሰባው በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ቀጥሏል

His Grace Abune Samuel, Archbishop of DICAC

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፥የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ፣ የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ

 • በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሰብሳቢነት የተመራው ኮሚቴ በ80 አንቀጾችና በ99 ገጾች አዘጋጅቶ ያቀረበው የ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ለተከታታይ ቀናት ሲካሔድ የሰነበተው ውይይት የተጠናቀቀው፣ ምልዓተ ጉባኤው በሰጠው አስተያየትና ባደረገው ማስተካከያ መሠረት ከአርቃቂ ኮሚቴው ጋራ ሠርቶና አሟልቶ ለቀጣዩ ስብሰባ የሚያደርስ የሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ባለሞያዎች ኮሚቴ በማቋቋም ነው፡፡

***

Holy Synod04

 • የፓትርያርክ እንደራሴ ምደባ እንዳስፈላጊነቱ ሲሠራበት የቆየ መኾኑን በመጥቀስና ለወደፊቱም ሲያስፈልግ ሊመደብ እንደሚችል በመስማማት አንቀጹ ከማሻሻያው እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
 • የቅ/ሲኖዶሱን ዓላማ ለማስፈጸም እንደሚቋቋሙ በማሻሻያ ረቂቁ ከተገለጹት ተጨማሪ አካላት መካከል ‹‹ቋሚ ኮሚቴዎች››ን በተመለከተ፣ ኮሚቴዎች እንዳስፈላጊነቱ ጉዳይ ተኮር ኾነው ከሚቋቋሙ በቀር በቋሚነት መደራጀት የለባቸውም በሚል ማስተካከያ ተደርጓል፡፡
 • ‹‹የሊቃውንት፣ ካህናትና ምእመናን መማክርት ጉባኤ›› ለውጭ ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ በር ይከፍታል በሚል የምልዓተ ጉባኤውን ተቀባይነት ባለማግኘቱ ሐሳቡ ከማሻሻያ ረቂቁ ወጥቷል፡፡፡፡

***

Holy Synod03

 • ስለምንኵስና ደረጃዎች፣ መሥፈርትና አፈጻጸም፣ ለመነኰሳት ስለተከለከሉ ተግባራት(ያለፈቃድ ከገዳም ወጥቶ በከተማ መዋልና ማደርን፣ በመጠጥ ቤትና አልባሌ ቦታ መገኘትን፣ የግል ንብረት ማከማቸትንና ማቋቋምን፣ ለሴቶችና ባለትዳሮች በንስሐ አባትነት ማገልገልንና አለባበስን ጨምሮ) ሕግን ስለሚተላለፉ መነኰሳት ዝርዝር ደንብና መመሪያ እንደሚወጣ ተመልክቷል፡፡
 • የማስመስከሪያ የአብነት ት/ቤቶች መምህራን እንደየሞያቸው በጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም በየአህጉረ ስብከቱ አማካይነት ቋሚ ደመወዝ ይመደብላቸዋል፡፡ ከምስክር አብያተ ጉባኤያት የሚመረቁ ሊቃውንት በት/ቤቶቹ የምስክር መምህርና በሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በጋራ የተፈረመ የጽሑፍ ማረጋገጫ ይሰጣቸዋል፡፡ የአብነት ትምህርቶች ማረጋገጫ ከዶክትሬት እስከ ዲፕሎማ ድረስ ተመጣጣኝ ደረጃ ወጥቶላቸዋል፡፡
 • በቤተ ክርስቲያን በሓላፊነት ደረጃ ያሉ ካህናት የማንኛውም የፖሊቲካ እንቅስቃሴ አባል ወይም አራማጅ መኾን እንደማይችሉ የካህናትን መብትና ግዴታ በሚደነግገውና ለካህናት የተከለከሉ ተግባራትን በሚዘርዝረው የማሻሻያ ረቂቁ አንቀጽ በአከራካሪ ኹኔታ ውሳኔ አግኝቷል፡፡

***

Holy Synod01

 • ‹‹ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች›› በሚለው የማሻሻያ ረቂቁ ምዕራፍ÷ ስለ በዓለ ንግሥ (የክብረ በዓል ጊዜና የበዓለ ንግሥ አከባበር ሥርዓት)፤ ንዋያተ ቅድሳት ከቅጥረ ቤተ ክርስቲያን ውጭ አገልግሎት ላይ ስለሚውሉበት ኹኔታ፤ በቤተ ክርስቲያን ስም ስለሚታተሙ መጻሕፍት ምርመራ፣ ስርጭትና ተቀባይነት፤ ስለ መዝሙራት ዝግጅት፣ ኅትመት፣ ስርጭትና ተቀባይነት (ዜማ፣ የዜማ ይዘትና የዜማ መሣርያዎች)፤ በስመ አምላክና ስመ ቅዱሳን ስያሜ አጠቃቀምና ክልከላ (ለምሳሌ፡- በቅዱሳን ስም የንግድ ድርጅትን መሰየም ተከልክሏል)፤ ቤተ ክርስቲያን በዘመኑ ቴክኖሎጂ የተቃኙ ብዙኃን መገናኛዎች እንደሚኖሯት፣ ብዙኃን መገናኛዎቹን የሚመራ ተቋም (ድርጅት) እንደሚቋቋምና ተቋሙ (ድርጅቱ) የሚመራ ቦርድ በቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚሠየም፣ ደንብና መምሪያም እንደሚወጣለት የተመለከቱ አንቀጾች ተካተውበታል፡፡

***

Holy Synod06

 • የቤተ ክርስቲያንን የሥራ አስፈጻሚነትና የአስተዳደር ተግባራት የማከናወን ሥልጣን የተሰጠው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት መምሪያዎችና አገልግሎቶች፡- (ሀ) መንፈሳዊ ዘርፍ፣ (ለ) የፋይናንስ የሰው ሀብትና ልማት ዘርፍ በሚል ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ በኾኑ ኹለት ምክትል ሥራ አስኪያጆች ለመከታተል የቀረበው ሐሳብ ‹‹አስፈላጊ አይደለም፤ ሥራ የለውም፤ ኹሉም ሥራ መንፈሳዊና መንፈሳዊውን ተግባር የሚደግፍ ነው›› በሚል ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የቀረበውን ማብራሪያ መነሻ አድርጎ ጽ/ቤቱ በጠቅ/ሥ/አስኪያጁና በአንድ ምክትል ሥራ አስኪያጅ እንዲመራ ተወስኗል፡፡
 • የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አንድ እንዲኾንና የዘርፍ ክፍፍሉ እንዲቀር በመወሰኑ ከሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ውጭ በመዋቅር ሳይታወቅ ሲሠራበት የቆየው የንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ‹‹የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ›› ሥልጣን ተሽሯል!!!
 • የጉባኤው ርእሰ መንበር ፓትርያርኩ፣ ከዘርፉ መዋቅራዊ አስፈላጊነት ይልቅ ‹የመቀመጫቸውን› ላጡት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ‹‹ታድያ ሰውዬውን የት እናድርገው?›› በሚል ያነሡት ጥያቄ የብፁዓን አባቶችን ፈገግታ ሳያጭር አልቀረም፡፡
 • በርግጥም ለንቡረ እዱ ርእሰ መንበሩ ያሰቡላቸው ቦታ ባይገኝላቸውም የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቁን በምልዓተ ጉባኤው አስተያየትና ማረሚያ መሠረት አሟልቶ ለቀጣዩ ስብሰባ እንዲያቀርብ በተቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ በፓትርያርኩ ውትወታ እንዲካተቱ መደረጉ እያነጋገረ ይገኛል፡፡

***

Holy Synod05

የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቁ በጥቅምቱ የምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ወቅት ለቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ደርሶ ሲጠና የቆየ ሲኾን ለሚመለከታቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነትና የአህጉረ ስብከት የሥራ አስፈጻሚ አካላትም ተሰራጭቶ የተሰበሰበው ሐሳብ ለምልዓተ ጉባኤው ውይይት ግብዓት ኾኗል፡፡

በምልዓተ ጉባኤው በተሰጠው አስተያየትና እርማት መሠረት የማሻሻያ ረቂቁን ሠርተውና አሟልተው እንዲያቀርቡ በተቋቋመው የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ባለሞያዎች ኮሚቴ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት÷ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ገሪማ በአባልነት እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

ካለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ትላንት ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቁ ቀዳሚ ትኩረት ሰጥቶ ሲመክር የሰነበተው ምልዓተ ጉባኤው÷ በትላንትናው ዕለት ከቀትር በኋላ የቤተ ክርስቲያናችን የሕይወት ምንጭ የኾነው ስብከተ ወንጌል ‹‹በሰው ኃይልና በሚዲያ ጭምር እየታገዘ በመላው ዓለም ላሉ የቤተ ክርስቲያናችን ተከታዮች በጥራትና በጥልቀት ይሰጥ ዘንድ›› በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በቀረበው የተጠና ደንብ ላይ ተወያይቷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው በዛሬው፣ የግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ውሎው፡-

 • ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ስትራተጅያዊ ዕቅድ በግንቦት ፳፻፭ ዓ.ም. የተቋቋመው የመሪ ዕቅድ ጥናት ዓቢይ ኮሚቴ ስለሚያቀርበው የትግበራ ስልቶችና ቀሪ ተግባራት፤
 • ገዳማት እንዴት መልሶ መቋቋምና መልማት እንዳለባቸው በጥቅምቱ መደበኛ ስብሰባ የተቋቋመው ሦስት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የገዳማት መምሪያ ዋና ሓላፊ ጋራ በመኾን ስለሚያቀርቡት ጥናትና የመፍትሔ ሐሳብ፤
 • የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ከቻይናው ሲ.ጂ.ሲ.ኦ.ሲ ኩባንያ ጋራ በመተባበር ለማስገንባት ስላቀደው የሦስት ቢልዮን ብር ኹለገብ ሕንፃዎች፤ በመሀል ፒያሳ ከዘውዲቱ ሕንፃ ጀርባ በ48 ሚልዮን ብር ለማስገንባት ስላቀዳቸው ኹለት ባለአራት ፎቅ ትይዩ ሕንፃዎች በድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ ሊቀ ጳጳስና በባለሞያዎች የሚቀርበውን ገለጻ በተመለከተ በተቀረፁ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ እንደኾነ ተጠቅሷል፡፡
 • ለምልዓተ ጉባኤው መነጋገርያ እንዲኾኑ ከጸደቁት ኻያ ያህል አጀንዳዎች መካከል፡- የኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት የሚመለከተው ‹‹የአባቶች ምርጫ መመዘኛ ሕግ›› እና በጥቅምቱ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቆ እንዲቀርብ ትእዛዝ የተሰጠበት ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ›› እንደ ቅደም ተከተላቸው ቀጣይ ተራቸውን የሚጠብቁ ይኾናሉ፡፡
Advertisements

14 thoughts on “በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ላይ ሲካሔድ የቆየው የቅ/ሲኖዶሱ ውይይት ተጠናቀቀ፤ ስብሰባው በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ቀጥሏል

 1. Birhan Asfaw May 22, 2014 at 5:25 pm Reply

  Melkamun hulu yasasbachuh.

 2. Anonymous May 22, 2014 at 7:00 pm Reply

  lebetekerstiyanachen yemibejewen amlakachen yasasebachu

 3. Anonymous May 22, 2014 at 11:31 pm Reply

  አባቶቻችንን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር፥የእመቤታችን ምልጃ፥የቅዱሳን መላእክት ተራዳይነት ፃድቃንና የሰማዕታት ፀሎት ይርዳቸው ::ምዕመኑም በፀሎት ሊረዳቸው የግድ ነው ::

 4. Anonymous May 23, 2014 at 2:38 am Reply

  ሁሉም መልካም ነው።ግን የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ እንደት የመጨረሻ አጀንዳ ሆነ?ማለቴ ብዙ በአይን የሚታዩ ስራዎችን እየሰራ ስለሆነ ትኩረት ቢሰጥበት! ብቻ……………..,

 5. shewa May 23, 2014 at 8:00 am Reply

  አባቶቻችንን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር፥የእመቤታችን ምልጃ፥የቅዱሳን መላእክት ተራዳይነት ፃድቃንና የሰማዕታት ፀሎት ይርዳቸው ::ምዕመኑም በፀሎት ሊረዳቸው የግድ ነው ::

 6. Anonymous May 23, 2014 at 8:02 am Reply

  ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን እያደረገ ያለው ሥራ በጣም የሚያስደስት ነው፡፡ ነገር ግን ስትራቴጅክ ዕቅዱ እና ሌሎች የወጡት መመሪያዎች በተክክል የሚፈጽሙ ከሆነ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነታችን ለውጥ ያመጣል ብሎ እገምታለሁ ፣ከምን ባይ ደግሞ
  ቤተ ክርስቲያን ከተማ ላይ ብቻ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ብትሰራ ጥሩ ቢሆንም ገና ብዙ ያልተሰራ ስራ እንዳለ ያስታውቃል በገጠር አካባቢ በተለይም በኦሮሚያ ክፍል ፣ ቤንሻንጉል፣ እና ሌሎችም ክልሎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል፡፡ ከዛ አልፎ ተርፎ አሁን እየወጡ ያሉት መንፈሳዊ መዝሙሮች ከመንፈሳዊ መዝሙርነታቸው አልፎ ዜማቸው ወደ ዓለማዊ ዘፈንነት እየተቀየሩ መተዋል ይህም ቀስ በቀስ ችግር ስለሚያመጣ ምእመናኑን ትክክለኛውን ዜማ እንዲሰማ እና መዝሙሮች ሲወጡ የሚወጣው መንፈሳዊ መዝሙር በሊቃውንቱ ተመርምሮ ፣ ዕውቅና ተሰጥቶት መሆን አለበት፡፡ ይህም ብቻ አይደለም አዳዲስ በሚወጡ መንፈሳዊ መጽሐት ላይም እንደዚሁ ቁጥጥር ያስፈልጋል ግዜው በጣም አስቼጋሪ ወቅት ስለሆነ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል፡፡ በተረፈ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ በመሆኑና ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት ልዑል አምላክ የሆነ እግዚአብሔር አምላክ ያቀዱትን ፣ እንሰራዋለን ያሉትን ወደ ተግባር እንዲያስገበልን እርሱ ይርዳን፡፡

 7. Demeke Tilahun May 23, 2014 at 8:08 am Reply

  አባቶቻችንን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር፥የእመቤታችን ምልጃ፥የቅዱሳን መላእክት ተራዳይነት ፃድቃንና የሰማዕታት ፀሎት ይርዳቸው ::ምዕመኑም በፀሎት ሊረዳቸው የግድ ነው ::
  I always keep my eyes open to meetings of the St. Sinodos !!!
  It is very important to come up with CONSTRUCTIVE ideas to those meetings and address the result to the “Mi’Emenan “.

  Building Towers is very important too…. But It is the Most important thing is Building Human !!!
  I mean The Church Schools @ Remote Areas of , Ethiopian which are know for providing the many Scholars to the Church and for the Country as well are now days being closed . This is because we are not working to much on that …. We should Pay attention to on this issue .
  European churchs are converted into Muziums . This is because they don’t have the person to continue the lagacies of Saints …..
  Let Me End Up With What Megabie Hadis Eshetu Alemayehu Said !!!
  No Days , It is More Important To Build a student( In Church School ) than Building a Tower .

  Wo’ Sebe’At Le’Egziabher , Wo’Le’Woladitu Dingle Wo’Le’Meskelu Kibur !!!

 8. Anonymous May 23, 2014 at 9:58 am Reply

  <>

  Tesfa alegn Ze Dar Ager

 9. Yemariam May 23, 2014 at 12:43 pm Reply

  hulum neger be’Egziabher fekad yihonal. yemahiberum sira bihon lebetekiristian silehone hasab ayigban….

 10. Anonymous May 23, 2014 at 1:48 pm Reply

  Does anyone know the status of the case of Deacon Begashaw? He was supposed to appear in front of “YeLiqawunt Gubae”, and the Synod to determine whether he’s in heresy or not. Please let me know.

  • Anonymous May 23, 2014 at 4:23 pm Reply

   አዎ እኔ አውቃለሁ አንተ ራሱ ከሱ የማትሻል ድንጋይ ነህ ስለትልቅ ጉዳይ እየተወራ ስለ አንድ “ዲያቆን” ተብዬ የመንደር ዱርዬ ታወራለህ !!! ሃይማኖትህ እሱ ከሆነ ሂድና የመናፍቃን ቴሌቪዥን የሆነው ምንሎጎስ ላይ ሲወሻክት ታገኘዋለህ

   • Anonymous May 27, 2014 at 8:17 pm

    በማታዉቀው ነገር ገብተህ ለምን ትፈተፍታለህ ዎንድሜ:: አንተስ ከሱ መች ትሻላለህና::ተሳዳቢ ነህና:: የድሮ ደቀመርዝሙሩ ሳትሆን አትቀርም::

 11. SHB May 27, 2014 at 5:41 am Reply

  bedemi wajteh yatsenahatn tebikilin betkirstianen

 12. Frieda June 9, 2014 at 12:20 am Reply

  You can certainly see your enthusiasm within the work you write.
  The sector hopes for more passionate writers like you who are not afraid to
  say how they believe. Always go after your heart.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: