የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት ተካሔደ

Holy Synod opening prayerዛሬ፣ ረቡዕ ግንቦት ፮ ቀን የሚጀመረው የ፳፻፮ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት በትላትናው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሒዷል፡፡

በትላንትናው ዕለት ከቀኑ ፲ ሰዓት ጀምሮ በተከናወነው በዚኹ የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ከሀገር ውስጥና ከውጭ አህጉረ ስብከት የተሰበሰቡ ከሠላሳ በላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል፤ በሥርዓተ ጸሎቱ መክፈቻና መዝጊያ የቤተ ክርስቲያኑ የደወል ድምፅ ለደቂቃዎች ተሰምቷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ‹‹ሑሩ ወመሀሩ›› በሚል ርእስ በጽሑፍ የተዘጋጀ ትምህርት የሰጡት የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ናቸው፡፡

His Grace Abune Garima‹‹ኹላችንንም ከየአህጉረ ስብከታችን ሰብስቦ ስሙን በመቀደስ፣ ቃሉን በመስማት ዓመታዊ ስብሰባችንን በጸሎት ለመጀመር ላበቃን አምላካችን እግዚአብሔር ‹ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት› ብለን እናመሰግነዋለን›› በማለት ትምህርታዊ ጽሑፋቸውን የጀመሩት ብፁዕነታቸው÷ በቅዱስ ሲኖዶሱ እየተጠናና እየተመከረበት የሚወጣው ሕግና ደንብ ለእምነታችን ህልውና፣ ለኅብረተሰባችን ማኅበራዊ አገልግሎት ዋስትና የሚሰጥ ስለኾነ ለሕጉ ተገዥዎች መኾን እንደሚጠበቅብን አሳስበዋል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስን ምንነትና አጀማመር፣ ቤተ ክርስቲያንን በመምራትና በመጠበቅ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ በየዘመኑ ስላሳለፋቸው ውሳኔዎችና የሥልጣን ልዕልናው እንዲሁም ከወቅቱና ከመጪ ኹኔታዎች አንጻር የሚጠበቅበትን አባታዊ ሓላፊነትና ውሳኔዎቹን በማስፈጸም ረገድ ካህናትና ምእመናን ያላቸውን ድርሻ ብፁዕነታቸው በትምህርታዊ ጽሑፋቸው በስፋት አብራርተዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት በፓትርያርክ ሰብሳቢነት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ለመወሰን የሚደረግ የሊቃነ ኤጲስ ቆጶሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤ መኾኑን ብፁዕነታቸው ገልጸው፣ ከጥንት ጀምሮ ጸንቶ የመጣውን የአበው ሐዋርያት፣ የአበው ሊቃውንት ትምህርተ ሃይማኖት ያለምንም ለውጥ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ሓላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን የሥልጣነ ክህነት ባለሥልጣን መኾኑንና ውሳኔውም የመጨረሻና ይግባኝ እንደሌለው ብፁዕነታቸው አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከ50 ሚልዮን በላይ ተከታይ ምእመናን፣ ከ500‚000 በላይ ካህናት፣ መዘምራንና ዲያቆናት፣ ከ60‚000 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያንና ከ1000 በላይ ገዳማት እንዳሏት የጠቀሱት ብፁዕነታቸው÷ ሃይማኖትና ምግባር እንዲጸና፣ አገር እንዲቀና፣ የተቸገረ ወገን እንዲረዳ ቅዱስ ሲኖዶሱ በየጊዜው እየተሰበሰበ የሚያስተላልፋቸውን ውሳኔዎች በሥራ ለመተርጎም የኹሉንም ጥረት እንደሚጠይቅና ለዚኽም ክህነታዊ አገልግሎቱ ወቅቱን የዋጀ እንዲኾንና የቅ/ሲኖዶሱ አባላት በግንባር ቀደምነት አባታዊ ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

Advertisements

11 thoughts on “የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት ተካሔደ

 1. Anonymous May 14, 2014 at 10:57 am Reply

  ከሠለሥቱ ምዕት ጋር የተገኘት አመ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም አሥራት ሀገሯን የኢትዮጵያን ቤ/ክ ከሚመሩት ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተገኝታ ለቤ/ክ በሚመችና በሚበጅ ሃሳብ አንድ ታድርግልን፡፡ ደግሞም ታደርጋቸዋለች፡፡
  የግል ጥቅምና ድብቅ የጥፋት ሤራ እጆችን ገስጻ ታሳፍራለች፡፡ ልጇ ወዳጇ መድኅን ዓለም ክርስቶስም እንደቀድሞው ሁሉ ዝም አይልም፡፡ እኛ በየኣላማችን ጎራ ብንለይም ለቤ/ክ በሚበጀው ጎራ ውስጥ ያስባናል፡፡ እኔ በፊት ያልገቡኝ ብዙ ነገሮች አሁን የገቡኝ ይመስኛል፡፡ ግን ዝም ብዬ (በአንደበቴ) በልቤ ተስፋ የድንግል ማርያምን፤ የቅዱሳንን የረድኤት ውጤት የአማኑኤልን የጥበቃ ፍሬ አያለሁ፡፡ የአባቶቼን ጉባኤ ትክክለኛ መረጃ ግን በየቀኑ መስማት እፈልጋለሁ፡፡
  እኔ ለተስፋ ትንሣኤ ቤ/ክ የቤ/ክ ጠላቶች ደግሞ ለማፈር እንዘጋጅ፡፡ የተዘጋጁበት ነገር አይከፋም፡፡

 2. Anonymous May 14, 2014 at 1:50 pm Reply

  ለአባቶቻችን እግዚአብሔር አምላክ በአንድነታችው ፅናትና ማስተዋልን ይስጥልኝ እኛም ምዕመናን በፀሎት መርዳት አለብን በጎች የሏቸው ዕረኞች እንዳይሆኑ እነሱም መትጋት አለባቸው
  ::

 3. HABTAMU May 14, 2014 at 5:32 pm Reply

  Egziyaber kenante gar yihun

 4. Ye Tewahido Lij May 15, 2014 at 6:02 am Reply

  Ye kidusan amlak ke abatochachin gar yihun. Emebete be dokimas bet tegegnita ye godelewin yemolach ahunim be abatochachin mehakel tegegnita godelowin timulalin.

 5. Anonymous May 15, 2014 at 6:02 am Reply

  B NIKIYA YETEGEGNE AMLAK ZAREM K ABATOOCHACHIN GAR YIHUN.

 6. Seni May 15, 2014 at 8:27 am Reply

  Let us all pray for our fathers to strong and bring church’s interest first than other earthy thing.

 7. Anonymous May 15, 2014 at 1:55 pm Reply

  egzeabhar lbatkerstein ymebjawun ngar yadrg

  • walda yohanis May 16, 2014 at 11:28 am Reply

   abatochachin yerasachon hasab sayhon ye igziabiherin hasab indiyastanagidu igzibiher yirdachow

 8. Anonymous May 16, 2014 at 5:05 am Reply

  Let us all pray for our fathers to strong and bring church’s interest first than other earthy thing.

 9. seyoum@frehymanot May 16, 2014 at 8:06 am Reply

  we ne’amen be ahati kidist bete kirstiyan ente la’ele gubae ze hawaryat!

 10. korabanchi April 4, 2016 at 4:46 pm Reply

  በድንብ ብሉ ስለተ ባሉ ይብሉ ሃይ ባይ የሌለው ገብስ ውፍ ይጨርስዋል

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: