በማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ከአጥኚ ኮሚቴውና ከቋሚ ሲኖዶሱ በአቋም የተለዩት ፓትርያርኩ፡- ‹‹በማኅበሩ ጉዳይ ርዱኝ፤ ብቻዬን ነኝ›› ሲሉ የጨለማውን ቡድን እገዛ ጠየቁ

 • ረቡዕ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በሚጀመረው የርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ላይ በንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ የሚመራውና አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያምና መዝገበ ጥበብ ቀሲስ ዮሐንስ ኤልያስ በዋናነት በሚያስተባብሩት የጨለማው ቡድን ድጋፍ ከጥቅምቱ ቅ/ሲኖዶስ ያደረው የደንብ ማሻሻያ ረቂቁ በአጀንዳነት ተይዞ እንዳይጸድቅ ለመከላከል ዝተዋል!
 • ፓትርያርኩ ዛቻ ያሰሙበትንና በስልታዊ መንገድ የተመረጡ የመምሪያዎችና ድርጅቶች ዋናና ምክትል ሓላፊዎች የተሳተፉበትን ድንገተኛ ስብሰባ ያስተባበሩት የፅልመታዊው ቡድን ቀንደኞች እነንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፡- ‹‹ቅዱስ አባታችን አይዞዎት፤ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንድንገኝ መድረክ ይፍጠሩ፤ እስከ መጨረሻው እንታገላለን›› በማለት አጋርነታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡
 • ማኅበሩ ማንኛውንም የጉባኤ መርሐ ግብሮቹን በቅ/ሲኖዶስ በጸደቀለት መተዳደርያ ደንብና በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ መመሪያ ከማከናወን ይልቅ ከልዩ ጽ/ቤታቸው በሚሰጥ ፈቃድ እንዲያካሒድ የሰጡት ትእዛዝ ተቃውሞ የቀሰቀሰባቸው ፓትርያርኩ፣ በደንብ ማሻሻያ ረቂቁ ውስጥ ያለአንዳች ማስተካከያ እንዲካተት ለአጥኚ ኮሚቴው የሰጡት ባለ24 ነጥብ የድንጋጌዎችና ግዴታዎች መመሪያ ‹‹ማኅበሩን የማያሠራና ከቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ጋራ የሚጋጭ›› በሚል ተቀባይነት አላገኘም፡፡
 • ቋሚ ሲኖዶሱ የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ በምልዓተ ጉባኤው ስብሰባ ላይ በአጀንዳነት እንዳይያዝ ፓትርያርኩ ያሰሙት ዛቻ የምልዓተ ጉባኤውን ውሳኔ እንደሚጋፋ በመጥቀስ የተቃወማቸው ሲኾን የጠቅ/ቤተ ክህነቱ ዋ/ሥ/አስኪያጅም ለኹለት ዓመት የዘገየው የደንቡ ማሻሻያ ረቂቅ በመጪው ምልዓተ ጉባኤ ሳይዘገይ ጸድቆ ማኅበሩ እንዲገለገልበት አሳስበዋል፡፡
 • ፅልመታዊው ቡድን በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ፣ በማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ እና በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሕግ ረቂቆች ጉዳይ ከፓትርያርኩ ጋራ የዶለተውን ምክር÷ ሊቃነ ጳጳሳቱን በማስፈራራትና የቅዱስ ሲኖዶሱን ኁባሬ(አንድነት) ለአደጋ በሚያጋልጥ አኳኋን አቋማቸውን በመከፋፈል ለማስፈጸም ዐቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡
 • ‹‹ጵጵስና አሾማችኋለኹ›› በሚል ለሹመት ካሰፈሰፉ ቆሞሳት እጅ መንሻ እየተቀበለ የሚገኘው ፅልመታዊ ቡድኑ÷ አካሔዱ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ሒደት ላይ የሚፈጥረውን ውጥረት በመጠቀምና ለውጥረቱ ማኅበሩንና አባላቱን ተጠያቂ በማድረግ በማኅበሩ አመራርና አባላት ላይ የታቀደውን ርምጃ ለማፋጠን ማሰቡ ተጠቁሟል፡፡nebureed-elias-abreha
 • ‹‹የሊቃነ ጳጳሳቱን ሥነ ልቡና ዐውቀዋለኹ፤ ከእግዚአብሔር ይልቅ የኢሕአዴግን ካድሬ ይፈራሉ፤ በራቸውን እያንኳኩ ማስፈራራት ነው፡፡›› /የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርን ኹለተኛ ቢሯቸው በማድረግ ከሚኒስትሩ ጋራ ግንኙነታቸውን ያጠበቁት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ/

‹‹ይህች ቤተ ክርስቲያን እኮ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ለዚኽች ታላቅ መንፈሳዊ ተቋም የሚመጥኑ ሰዎች መገኘት አለባቸው፡፡›› – ይህ ቃል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር መጠናከር አስፈላጊ ስለኾነው የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተከታታይ መመሪያ ሲሰጡ በነበሩባቸው የፕትርክና ሹመታቸው ወራት ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን ሰው በሰው ላይ በመደራረብ ሳይኾን ከመሠረታዊ ተልእኮዋ ጋራ የሚጣጣም ትምህርትና ችሎታ ባለው፣ ለተመደበበት የሥራ ደረጃ በሚመጥን የሠለጠነ ኃይል እንድትገለገል የማድረግ ምኞትና ፍላጎት እንዳላቸው በቃለ ምልልሱ የተናገሩት ፓትርያርኩ÷ ለውጡ ቀስ በቀስና ደረጃ በደረጃ የሚመጣ ቢኾንም ወደ ዕድገትና ሥልጣኔ የሚያደርሰው መንገድ ግን ዛሬ መጀመር እንዳለበት ለዚኽም ቅ/ሲኖዶስ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበው ነበር፡፡

ፓትርያርኩ በዚኽ ብቻ ሳይወሰኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ ከምንም በላይ በራሱ መተማመን እንዳለበት፣ ከእግዚአብሔር በታች እምነቱንና ትውክልቱን በቤተ ክርስቲያን ላይ አድርጎ ቤተ ክርስቲያኒቱን ነቅቶና ተግቶ መጠበቅ እንደሚገባው፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ህልውና፣ ለእግዚአብሔር ክብርና ለሃይማኖት ሲባል እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ኾኖ ተስማምቶና ተግባብቶ በሥምረት እስከሠራ ድረስ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያምኑ ከመግለጻቸውም በላይ ቅ/ሲኖዶሱን ከግለሰባዊና ቡድናዊ ተጽዕኖዎች እንደሚጠብቁትም ቃል ገብተው ነበር፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በመዋጋት አሠራሯን ለማጥራትና መዋቅሯን ለማጠናከር በምታደርገው ጥረት ፊት ተጋርጦባት ስለቆየው በመንደርተኝነትና በጥቅመኝነት የመሳሳብ በሽታም ‹‹ቤተ ክርስቲያናችን የእግዚአብሔር ቤት ኾና ስለተመሠረተች በዘረኝነት መበከል የለባትም፡፡ ማንኛውንም ሠራተኛ ልንወደውም ልንጠላውም የሚገባን በግብሩ፣ በጠባዩና በትምህርቱ እንጂ በዘሩ መኾን የለበትም፤›› እያሉ በተደጋጋሚ ሲመክሩ ነበር፡፡

ከዚኽ ቀደም በወረቀት የቀሩና በአፈጻጸም የተደፈቁ የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎችን በማስታወስና አማሳኞች፣ ጎጠኛና አድርባይ ፖሊቲከኞች ቅዱስነታቸው ዐውጀው ባስጀመሩት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ላይ በሚያሰሙት ዛቻ ሳቢያ ውጥኑ በከንቱ እንዳይቀር ለጠየቋቸው የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች፣ ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች ‹‹አስቀድሜ ሙስና፣ ብልሹ አሠራርና የመሳሰሉት ከቤተ ክርስቲያን ሊወገዱ ይገባል ብዬ የጮኹት እኔ ነኝ፤ ይኼ ነገር ሳይተገበር ቢቀር ጩኸቴን የምቀማው እኔው ራሴ ነኝ፤›› በማለት ልባቸውን አረጋግተውም ነበር፡፡

‹‹ፓትርያርክ ቢኾኑ ከአምስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ምን የተለየ ይሠራሉ?›› ተብሎ በፓትርያርክ ምርጫው ዋዜማ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱ ትክክለኛውንና ቀጥተኛውን መንገድ እንድትይዝ፣ በውስጧ ያለው ኹሉ መንፈሳዊነትን የተጎናጸፈ፣ እውነተኛነትን የተጎናጸፈ እንጂ እንደ ዓለማዊነት መደረግ የለበትም ባይ ነኝ፡፡ በተቻለ መጠን ይህን ወደ እውነተኛ መንገድ ለመመለስ ነው ተስፋ የማደርገው›› ሲሉ ምላሽ ሰጥተው ነበር፡፡

ከአንደኛ ዓመት የፕትርክና ዘመን በኋላ የኾነው ኹሉ ሲጤን ግን ፓትርያርኩ ከተግባር ይልቅ ንግግር ያበዙበት የለውጥ ተስፋ በውስጣዊ አሻጥሮችና በውጫዊ ተግዳሮቶች ሳቢያ በከባድ ዕግዳት(deadlock) ውስጥ የገባበት ኹኔታ ተስውሏል፡፡ የለውጥ ሒደት የራሱ ባሕርያዊ ፈተናዎች ያሉት ቢኾንም ነባሩን የቤተ ክህነት ጠባይና አሠራር ተገንዝቦ የለውጥ ሒደቱን ከቅርቃርና ከከላሾች ሤራ ለመጠበቅ ተገቢውን አመራር በመስጠት ረገድ ፓትርያርኩ በጉልሕ የታየባቸው አካላዊና አእምሯዊ ውሱንነት በቀዳሚ መንሥኤነት የሚጠቀስ ነው፡፡

ይህ የአካላዊና አእምሯዊ አቅም ውስንነት÷ ዓምባገነንነትና ቤተ ዘመዳዊ አሠራር ሰፍኖበት የነበረውን የቀድሞውን ፓትርያርክ ሥልጣን ለመግራት የተደረገውን ጥረትና ጥረቱ ያሳደረውን የለውጥ ተስፋ ጭፍለቃ ሊባል በሚችል የኃይል ርምጃ በማምከናቸው ምክንያት የጨለማው/ፅልመታዊ ቡድን የሚል ግብራዊ ስም የተሰጣቸውን ግለሰቦች አሻጥር፣ እነርሱን መሸጋገርያ ያደረገውና ፓትርያርኩ አለተጨማሪ ጥያቄ የሚያስተናግዱትን ውጫዊ ተጽዕኖ በአግባቡ ለመረዳትና ለመቋቋም እንዲሳናቸውና በቀላሉም እንዲቆጣጠራቸው ምክንያት ኾኗል፡፡

አቡነ ማትያስ ከኤጲስ ቆጶስነታቸው አንሥቶ ከሦስት ዓሥርት ዓመታት በላይ በውጭ መቆየታቸው ከፓትርያርክነት ሢመታቸው በኋላ ሓላፊነታቸውን በበቂ ላልተወጡባቸውና ድክመት ላሳዩባቸው ኹኔታዎች ‹‹እንግዳ ነኝ›› ለሚል ሽሽት ያገለገለ ቢኾንም ቢያንስ ከዓመት በኋላ እንግድነቱ ተወግዶ በቤተኛነት ስሜት የለውጥ እንቅስቃሴው ለሚፈልጋቸው ሊቃውንትና ባለሞያዎች ቦታ ሰጥቶና ተግባብቶ መሥራት ይገባ ነበር፡፡ ያም ኾኖ እንግድነቱ ቢኖር ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በአንደኛ ዓመት የፓትርያርኩ በዓለ ሢመት መርሐ ግብር ላይ እንደተናገሩት፣ ቅ/ሲኖዶሱ ‹‹አዲስ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና አዲስ የጠቅ/ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ›› ሾሞላቸዋልና ከእነርሱ ጋራ ቋሚ ሲኖዶሱን ይዘው እየተመካከሩ መሥራት ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ከዚህም ባሻገር የግንቦት ፳፻፭ ዓ.ም. የቅ/ሲኖዶስ የተቋማዊ ለውጥ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱ የአበው ሊቃነ ጳጳሳት – ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን – ምሁራን ምእመናን መማክርት ጉባኤ በየሞያ ዘርፉ በማቋቋም የአማካሪነት መዋቅሩን መሠረት ለመጣልና ለማጠናከር የሚቻልበትን ዕድል የሚፈጥር ነበር፡፡ የቅዱስነታቸው የኹልጊዜ ምርጫዎች ግን መንፈሳዊነትም ሞያዊነትም የራቃቸው፣ በቃል የተናገሩለትን ቀጥተኝነት፣ እውነተኛነትና መንፈሳዊነት በተግባር ለቤተ ክህነታችን ማጎናጸፍ የማያስችሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተፃራሪ ኃይሎች ኾነዋል፡፡

ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያናችን ለመንፈሳዊ ተቋምነቷ የሚመጥኑ ሰዎች ሊመደቡላት እንደሚገባ ቢናገሩም ከቅዱስነታቸው ጀምሮ በየመድረኩ የሚታየው አቋም የለሽነትና አቅመ ቢስነት ከፍቶ ዐደባባይ ወጥቶ አሸማቃቂ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ጥቂት በማይባሉ ሠራተኞችና አገልጋዮች ዘንድ ደግሞ አቅመ ቢስነቱና አቋመ ቢስነቱ ንቀትና ጥላቻን ከማስከተሉም በላይ የቀድሞውን ፓትርያርክ በደል አስረስቶ አቡነ ማትያስ ሳይቀር በይፋ ያደነቁላቸውን ዓለም አቀፍ ሰውነት እንዲሁም ብዙዎች የሚስማሙበትን አእምሯዊ ብልጠትና ቅልጥፍና (እንግሊዞች ‘too clever for your own good’ እንደሚሉት ቢታይም) ያስናፈቀ ኾኗል፡፡

Holy Synod in session

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ዓመታዊ ስብሰባ (ፎቶ፡ አንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት መጽሔት ፳፻፮ ዓ.ም.)

‹‹በባዮሎጂና ኬሚስትሪ እንቀድስ ይላሉ›› የሚለው የፓትርያርኩ ክሥና ወቀሳ የሐቅ መሠረት የሌለው ተርታ ንግግር ብቻ አይደለም፤ ከመንፈሳዊነትና ሞያዊነት ይልቅ በጥቅመኝነትና ጎሰኝነት የተሳሰሩ አማሳኞች በፓትርያርኩ አስተሳሰብ ላይ የፈጠሩት የፀረ መንፈሳዊነትና የፀረ ምሁርነት ተጽዕኖ የተጋለጠበት ነው፡፡ በሌላ ገጹ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱን በሠለጠነና በተማረ ኃይል አንቀሳቅሳለኹ፤ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በቆራጥ የእርምት ርምጃዎች አስተካክላለኹ፤ ታማኝነት፣ ሐቀኝነትና ተጠያቂነት አሰፍናለኹ›› ዓይነቱና የመሳሰለው ንግግራቸውም ‹‹ሥር በሰደደ ችግር መፍትሔ አማጭ መስለው ራሳቸውን ያስተዋወቁበት፣ ከውስጥ እምነታቸው ያልመነጨና የተጫነባቸው›› ለመኾኑ ዘግይቶም ቢኾን ብዙዎች የተስማሙበት እውነት ኾኗል፡፡

‹‹ቅ/ሲኖዶስ ከምንም በላይ በራሱ መተማመን አለበት፤ ከእግዚአብሔር በታች እምነቱና ትውክልቱ በቤተ ክርስቲያን ላይ መኾን አለበት፤ ቤተ ክርስቲያኒቱንም ነቅቶና ተግቶ የመጠበቅ ሓላፊነት አለበት›› ብለው በዕለተ ሢመታቸው የመከሩት ቅዱስነታቸው፣ ራሳቸውን ለአላስፈላጊ ተጽዕኖ ያጋለጡበት ፈቃደኝነትና ዝግጁነት ቄሣራዊው ወገን ያልጠበቀውና የሚያሳፍረው ጭምር ኾኗል፤ በርእሰ መንበርነት ለሚመሩት ቅ/ሲኖዶስና ከኀምሳ ሚልዮን ለሚልቁ አገልጋዮችና ምእመናን በርእሰ አበውነት የተሠየሙበትን መንበረ ተክለ ሃይማኖት ከውስጣዊና ውጫዊ ግለሰባዊና ቡድናዊ ጣልቃ ገብነት ተከላክለው መመሪያውንና ውሳኔውን በማስፈጸም ልዕልናውን ማስከበርም ተስኗቸዋል፡፡

ቅ/ሲኖዶሱ ለተቋማዊ ለውጥ ጥናቶች የሰጠውን ይኹንታና የአፈጻጸም አቅጣጫ በአማሳኞች ምክር ማገት ሳይበቃቸው ይባስ ብለው እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ ኾኖ ተስማምቶና ተግባብቶ በሥምረት እንዳይሠራ የቤተ ክርስቲያኒቱን የተቋማዊ ለውጥ ዕድሎችና ተስፋዎች ሲያመክን ከኖረው ፅልመታዊ ኃይል የድጋፍ መሠረትና ርዳታ ጠይቀዋል፡፡

ጥያቄው የቀረበው ባለፈው ሳምንት ኃሙስ፣ ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ቀትር ላይ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር መምሪያ ዋና ሓላፊ በጠሩት የመምሪያዎችና ድርጅቶች ዋናና ምክትል ሓላፊዎች ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በዋና ሓላፊው ‹መዝገበ ጥበብ› ቀሲስ ዮሐንስ ኤልያስ አማካይነት በድንገት በተጠራውና ከቀኑ 9፡00 በፓትርያርኩ ጽ/ቤት በተካሔደው ስብሰባ÷ አማሳኞች፣ ጎጠኛና አድርባይ ፖሊቲከኞች እንዲሁም የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኞች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ በየመድረኩ የሚያዘንቡትን ክሥ አቡነ ማትያስ በቀጥታ እየተጠቀሙ በመወንጀል ዘልፈውታል፡፡

በማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ ውስጥ የሚካተት ባለኻያ አራት ነጥብ አንቀጽ ለአጥኚ ኮሚቴው መስጠታቸውን ፓትርያርኩ በስብሰባው ላይ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ማኅበሩ ወደደም ጠላም በሕግ ሥር ይውላል›› በማለት ደንቡን ለሚያሻሽለው ኮሚቴ የሰጡት ‹‹የድንጋጌዎችና ግዴታዎች›› አንቀጻቸው አንዳችም ማሻሻያ ሳይደረግበት እንዲካተት፣ አንቀጹ የማይካተት ከኾነ የማኅበሩ ማሻሻያ ደንብ ረቂቅ ኃሙስ በሚጀመረው የርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ በአጀንዳነት እንዳይያዝና እንዳይጸድቅ ለመከላከል ዝተዋል፤ ‹‹በማኅበሩ ጉዳይ ብቻዬን ነኝ፤›› በማለት በቅ/ሲኖዶስ ከተሠየመው የመተዳደርያ ደንብ አጥኚ ኮሚቴና ለቅ/ሲኖዶሱ አጀንዳ ከሚቀርፀው ቋሚ ሲኖዶሱ በአቋም መለየታቸውን ያመለከቱት አባ ማትያስ ‹‹ርዱኝ›› ሲሉም እገዛ ጠይቀዋል፡፡

ስብሰባው በመምሪያዎችና ድርጅቶች ሓላፊዎች ስም የተጠራ ይኹን እንጂ ለፓትርያርኩ የእገዛ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት አጋርነታቸውን ያሳዩት ዋነኛ ተሳታፊዎች የጨለማው ቡድን ቀንደኞች ናቸው፡፡ ፅልመታውያኑ በንግግራቸው ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ማኅበር እንዳልተሳተፈባቸው የሚታወቁ ጥናቶችን ሳይቀር እየጠቀሱና ማኅበሩን ለቤተ ክርስቲያኒቱ ባዕድ እያደረጉ ‹‹ቤተ ክርስቲያኗ በቂ ባለሞያዎች አሏት፤ ኹሉም ጥናት ለምን በማኅበሩ አባላት ይካሔዳል?›› የሚል ቅናት አይሉት ምቀኝነት ዝናና ጥቅም ፈላጊነት የሚገፋቸውን ክሦች በስፋት አሰምተዋል፡፡ እነርሱ በሚጠቅሷቸው ጥናቶች ከማኅበሩ ጋራ አብረው ሠርተዋል ያሏቸውንና በተቋማዊ ለውጥ ጥረታቸው የሚታወቁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን በሥልጣን ፈላጊነት አምተዋል፤ ዘልፈዋል፡፡ ማኅበራት አያስፈልጉም ሲሉም በማኅበሩ ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በጡረታ ካገለላቸው በኋላ ተመልሰው በገቡበት የኮንትራት ቅጥር ከአሠራር ውጭ የካህናት አስተዳደር መምሪያ ዋና ሓላፊ የኾኑት መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም፡- ‹‹የኢሕአዴግ አባልና ደጋፊ የኾኑ መነኰሳት ለኤጲስ ቆጶስነት መመረጥ የለባቸውም፤›› የሚል ቅስቀሳ እየተካሔደ እንደኾነ በመጥቀስ ማኅበሩን ከሠዋል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ በማይታወቅ መዋቅር ‹የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ› በመኾን የቀድሞውም የወቅቱም ፓትርያርኮች ለፈጸሟቸው ስሕተቶች ቀዳሚ ተጠያቂ የሚደረገው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፡- ‹‹ቅዱስ አባታችን አይዞዎት፤ እስከ መጨረሻው እንታገላለን፤›› በሚል ‹ቁርጠኝነት› አጋርነቱን ገልጧል፡፡

በትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊነታቸው÷ አብነት ት/ቤቶችን፣ የካህናት ማሠልኛዎችንና መንፈሳዊ ኮሌጆችን በተመለከተ ከያዟቸው ዕቅዶቻቸው አንዳቸውንም እንዳላሳኩ፣ የመምሪያውም ሥራ ሙሉ በሙሉ መዳከሙንና ለውጥ ለማምጣት እንዳልቻሉ በመንፈቅ ዓመት ሪፖርታቸው ላይ በግልጽ ያመኑት አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ በስብሰባው የአካሔድ ችግር እንዳለ በማመልከት ማኅበረ ቅዱሳንንና የሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ረቂቅ በተመለከተ በስፋት ረግጦ በመወያየት ጠበቅ ያለ ውሳኔ እንዲተላለፍ ጠይቀዋል፡፡

Advertisements

41 thoughts on “በማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ከአጥኚ ኮሚቴውና ከቋሚ ሲኖዶሱ በአቋም የተለዩት ፓትርያርኩ፡- ‹‹በማኅበሩ ጉዳይ ርዱኝ፤ ብቻዬን ነኝ›› ሲሉ የጨለማውን ቡድን እገዛ ጠየቁ

 1. ግእዝ በመሥመር-ላይ May 10, 2014 at 2:29 pm Reply

  እናንተ ሰዎች ግን መቼ ነው የሚገባችኍ? ፓትርያርክ ተብየው’ኮ የጨለማው ቡድን አባል ናቸው–ሲጀመር! ሲያበቃ ምን እንደሚኾኑ እሱ ይወቅላቸው። ከዛሬ ዓመት ሦስት ሳምንት ቀደም ብሎ፤ “ፓትርያሪኩ በጨለማው ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ መደምደሙ ከጊዜው የቀደመ ይመስላል” የሚል ነገር ስታስነብቡን የሚከተለውን አስተያየት ሰንዝሬ ነበር፦

  ምን ማለት ነው? አዬ ሐራ! እናንተም ቀልድ ዘመም መኾናችኍ ነው ወይስ “ከጊዜው የቀደመ” የሚለው ዳኅፀ ታይፕ ነው (“የዘገየ” ለማለት ዐስባችኍ በታይፕ ስሕተት “የቀደመ” ብላችኹት ነውን)? ርሳቸውን መልምሎ የሾማቸው ማን ኾነና! ደግሞስ የጨለማው ቡድን ርስ በርሱ ቢፈረካከስ አንዱ ፍርካሽ ብርሃን የሚኾን መሰላችኍ? ከእሾኽ ወይን እንደማይለቀም ኹሉ ከኵርንችትም በለስ እንዳይገኝ እያወቅነው፦ ከንቱ ድካም። እሊህን እሾኾች እና ኵርንችቶች መንቀል ቢያቅት ባይኾን ውሃ ማጠጣት አይገባም። ይድረቁ።

  ታዲያ እኔ እንዲኽ እያልኍ ብወተውትም፤ ጕረሮየ ደርቆ ቀረኍ እንጂ፤ እናንተ ጆሮ ዳባ ልበስ ብላችኍ፤ ውሃ ማጠጣት በቻ ሳይኾን ማዳበሪያ ስታስታቀፉ ቆያታችዃል። ውጤቱ ግን ያው የሚታየው ነው።

  ረ ንቁ!!!

  https://haratewahido.wordpress.com/2013/04/19/%E1%88%B0%E1%89%A0%E1%88%AD-%E1%8B%9C%E1%8A%93-%E1%88%88%E1%8D%93%E1%89%B5%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%AA%E1%8A%A9-%E1%88%98%E1%88%98%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%88%88%E1%88%98%E1%88%B5/

  • Anonymous May 14, 2014 at 2:15 pm Reply

   ምን ማለት ነው? አዬ ሐራ! እናንተም ቀልድ ዘመም መኾናችኍ ነው ወይስ “ከጊዜው የቀደመ” የሚለው ዳኅፀ ታይፕ ነው (“የዘገየ” ለማለት ዐስባችኍ በታይፕ ስሕተት “የቀደመ” ብላችኹት ነውን)? ርሳቸውን መልምሎ የሾማቸው ማን ኾነና! ደግሞስ የጨለማው ቡድን ርስ በርሱ ቢፈረካከስ አንዱ ፍርካሽ ብርሃን የሚኾን መሰላችኍ? ከእሾኽ ወይን እንደማይለቀም ኹሉ ከኵርንችትም በለስ እንዳይገኝ እያወቅነው፦ ከንቱ ድካም። እሊህን እሾኾች እና ኵርንችቶች መንቀል ቢያቅት ባይኾን ውሃ ማጠጣት አይገባም። ይድረቁ።

   ታዲያ እኔ እንዲኽ እያልኍ ብወተውትም፤ ጕረሮየ ደርቆ ቀረኍ እንጂ፤ እናንተ ጆሮ ዳባ ልበስ ብላችኍ፤ ውሃ ማጠጣት በቻ ሳይኾን ማዳበሪያ ስታስታቀፉ ቆያታችዃል። ውጤቱ ግን ያው የሚታየው ነው።

   ረ ንቁ!!!

 2. Anonymous May 10, 2014 at 4:24 pm Reply

  If they can’t take care of the church and the followers, we should say , to the reverse, Egziabher Yiftachew!!!!!!!!!

 3. የቅርብ ታዛቢ May 10, 2014 at 4:49 pm Reply

  ወይ ጉድ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ይልቅ ለማኅበሪቱ ቅድሚያ ሰጥታችሁ የቄሳሮቹን መመሪያ በማክበር በአቋም ታግላችሁ ያሾማችሁት ሹም <> በናንተዉ ላይ አርጩሜ /ዱላ/ አነሣ ይገርማል የአምላክ ሥራ ። አቡንም መፍትሔው ዋልድባን እርቀ ሰላሙን የሹመቱን ወቅት የት እንደነበራችሁ አስቦ ንስሐ መግባት የሚሻል ይመስለኛል ። በቃሌ የነገርኳችሁን በጽሑፍ ደገምኩላችሁ እኛ ሥጋዊያን የሥጋን ነገር እናስባለን አንተ ግን የመንፈስን መንገድ ምራን ።

 4. የቅርብ ታዛቢ የውነት አሽከር May 10, 2014 at 4:58 pm Reply

  ወይ ጉድ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ይልቅ ለማኅበሪቱ ቅድሚያ ሰጥታችሁ የቄሳሮቹን መመሪያ በማክበር በአቋም ታግላችሁ ያሾማችሁት ሹም “• ፓትርያርክ •” በናንተዉ ላይ አርጩሜ /ዱላ/ አነሣ ይገርማል የአምላክ ሥራ ። አሁንም መፍትሔው ዋልድባን እርቀ ሰላሙንና የሹመቱን ወቅት የት እንደነበራችሁ አስቦ ንስሐ መግባት የሚሻል ይመስለኛል ። በቃሌ የነገርኳችሁን በጽሑፍ ደገምኩላችሁ እኛ ሥጋዊያን የሥጋን ነገር እናስባለን አንተ ግን የመንፈስን መንገድ ምራን አለ ደራሲው ታላቅ ልመና ።

 5. Seni May 10, 2014 at 6:38 pm Reply

  What happen to the patriarch? Any hidden agenda?

 6. Anonymous May 10, 2014 at 11:05 pm Reply

  ድሮስ በዘር ፍቅር ከተለከፈ ሰው ምን ይጠበቃል የያዛቸው ሰይጣን እስኪለቃቸው ደሞ ዘመናት ይፈጃል ስለዝዝ እነዚህን መናፍቃን ጠራርጎ ማስወጣት ነው ::ይህንን ለማድረግ ደሞ የ አባቶቻችን አንድነትና ፀሎት ያስፈልጋል ::
  እግዚአብሔር አባቶቻችንን ይርዳቸው :ሀገራችንንና ቤተክርስቲያናችንን ሊያጠፉ የተነሱትን ያስታግስልን ::

 7. Anonymous May 11, 2014 at 5:22 am Reply

  ‹‹ቅዱስ አባታችን አይዞዎት፤ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንድንገኝ መድረክ ይፍጠሩ፤ እስከ መጨረሻው እንታገላለን›› መታገሉ ባልከፋ ግን በቦታው ሲሆን ያምራል ….
  በእውነት ለእንደነዚህ አይነት ሰዎች ልንጸልይላቸው ብቻ ሳይሆን መካሪ ካላቸው ሊመከሩም ይገባል።
  ፖለቲከኞች እንኳ ዝቶ አለመሄድን እየተማሩ ባለበት! ….እንደው “እግዚአብሔር በፈቀደ” ን ምን ገደለው? እንደው ላፋቸው! ያውም ከአንድ አባት/

  አሜሪካ

 8. esayas May 11, 2014 at 6:05 pm Reply

  እግዚአብሄርን ተስፋ የሚያደርጉ እያፍሩም

 9. esayas May 11, 2014 at 6:08 pm Reply

  እረ ለኤልያስ አብርሃ የሚሆን ስው ይጥፋ!!!!!!

 10. worku May 12, 2014 at 6:08 am Reply

  እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸዉ!!! ከእጅ አይሻል ዶማ!!!!

 11. Anonymous May 12, 2014 at 7:36 am Reply

  ያለምንም ይሉኝታ የአንድ ብሄር አባላትን ለይቶ “የጨለማ ቡድን” በሚል የፍረጃ ቅጥያ ማሳደድ በራሱ የጨለመ ዐይን እይታ ያሰኛል፡፡ጉዳዩ ወደ ግራ ሲነበብም የተመልካቹን ሌላ ከፋፋይና ዘረኛ ጽልመታዊ እይታ ያሳያል፡፡
  እንግዲህ ምን እንላለን!! የቤተክርስቲያን አምላከ በአባቶቻችን አድሮ ለልጆቹ የሚበጀውን እንዲያደርግ ከመጸለይ በቀር የምንለው የለንም፡፡

  • Anonymous May 12, 2014 at 4:20 pm Reply

   If the darkness group is from one ethnic, it is not we group them in the group of challenging the church. They are given this name not by their ethnic identity but by their action, action of similarity.

   Therefore, you must stop thinking like this. Think towards the church.

   • Seni May 13, 2014 at 7:07 am

    “If the darkness group is from one ethnic, it is not we group them in the group of challenging the church. They are given this name not by their ethnic identity but by their action, action of similarity.”……Very good observation. Thanks!!!

   • Anonymous May 13, 2014 at 8:52 am

    I swear!! u have no sufficient info about the fact on the ground except swallowing w/o chewing gossips tuned with fanatic pro-MK bloggers who are blinded with anti-Tigray motive!!any way most of the commentators can be labeled as ‘gim le gim abreh azgim!!’ atleast you should have questioned the overall image of MK around the clergy instead of searching for escaping goat!!
    We are not as such fool, to expect balanced news and comment from a blog that works for cheap popularity mixing religion and politics in the name of defending MK and addressing its LOYAL READERS who has deafen themselves. go ahead, if you can resolve your internal problem by externalizing towards your-singled out one ethnic members!!

 12. Mesfin Dubale May 12, 2014 at 7:52 am Reply

  ማ/ቅ እዉነትን ብቻ ያዙ እዉነትንም ተከተሉ ልኡል እግዚአብሂር ለሁሉም ነገር ጊዚ አለዉ፤ ቢተ-ክ/ያንን ለደላሎች አሳልፎ አይሰጣትም፤ ድካማችሁንና ፍረያቸችሁን አገር አይደለም አለም ያዉቀዋል ዋጋችሁም በሰማያት ታላቅ ነዉ-ነገር ግን በርቱ ጠንክሩ ሁሉ በእናንተ ዘንድ በፍቅር ይሁን !!!

 13. Anonymous May 12, 2014 at 9:31 am Reply

  k hulem belay maheberachenen mahebere kedusanen keduse egeziabehere y tebekelene hulum yalefale esu gene ayalefem,

  k 12 tu hawariyatoch 1ndu yhudaa Getawene kerestosene be 30 birr endeshetew hulu zarem betekerestianen lishetu y tezegaju hailochene eskemecireshaw Amelakachene Kiduse Egeziabehere y tagesale enjii zeme aylem.

  be tselote metsenate befetena metsenate ke Mahebere Kidusane Ameraroch ena Abalate y tebekebenale !

 14. Anonymous May 12, 2014 at 12:31 pm Reply

  እግዚአብሄርን ተስፋ የሚያደርጉ እያፍሩም

 15. Anonymous May 12, 2014 at 12:40 pm Reply

  EGZIABHER ABATOCHEN LEBONA YESETELEN BETEKERESETIYANACHENENE YETEBEKELEN..

 16. Anonymous May 12, 2014 at 2:55 pm Reply

  Be Jimma Hagere Sebekete Be Beshasha Sele ewenetenyawa Haymanotachew sele anegetachene le gejeraa sewetew haymanotene y sebekulene y 2tu kesoch ena y 4tu abatoch ena enatoch besu asetemerewenale be ewenete le haymanotachene besu mesewatene lenekefele endemigeba temerenale

 17. Anonymous May 12, 2014 at 2:56 pm Reply

  Eskemecireshaw y mitsena eresu y denale

  • በዛብህ ተወከል May 13, 2014 at 3:46 am Reply

   ማህበሩን ማፍረስ የረፈደ ጉዞ፣ ማህበሩን መንካት የፖለቲካ ኪሳራ ማስከተል፣ ማህበሩ መከፋፈል ህልም ሆነ። እኛ ግን የማህበሩን በጐ ስራ ዲያብሎስ እያከረረ በሚፈትለው ፈትል እናየዋለነ። እናም ወዳጀ ጠላት ጨለማን ባበረታው ቁጥር ማህበሩ የሚበራቸው ችቦወች ይበራከታሉ። ቸቦው ግን ብርሀን ብቻ ሳይሆን ሙቀትም እንዳለው መረዳት ያስፈልጋል።

 18. Anonymous May 12, 2014 at 8:21 pm Reply

  We will see the real and final change from the stand of synodose in this decision result , unless its last hope we expect and no need up to the date of GOD .

 19. Anonymous May 13, 2014 at 4:40 am Reply

  They took the Church resources and become rich in flesh; they divided us on our ethnicity; they knocked the door and beat our Fathers; they completely forget God and run for their flesh. We know that they have done many other evils but we prefer to be silent. I think, hard time is coming. They have challenged our faith to much. May be, the end of this hard time is coming soon! “Linega sile yichelimale”. Let’s all stand together for our Church. God is always with the truth. With God every thing is possible. God bless Ethiopia and our people. Yabatochachine bereket ayileyen Amen!!!

 20. Seni May 13, 2014 at 7:12 am Reply

  “ሐራ ዘተዋሕዶ – የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደር፣ የተዋሕዶ ጭፍራ ማለት ነው፡፡ ሐራ – ሐርነት፣ ነጻነት ያለው ማለት ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ትምህርትና ሥርዐት፣ ትውፊትና ታሪክ ለማጥፋት በውስጥና ከውጭ የሚንበለበሉትን የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ፍላጻ ለመመከት የእምነትን ጋሻ አንሥተን እንጦምራለን፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ብሔራዊ ክብርና ተቋማዊ ነጻነት በማንበር ሐዋርያዊ አገልግሎቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጠናከርና እንዲስፋፋ የመረጃንና የዕውቀትን ሰይፍ በመያዝ እንጦምራለን፡፡ በአገልጋዮችና ምእመናን አዎንታዊ ተግባቦት ለተጨባጭ ለውጥ የሚያበቃ የመንፈስና የተግባር ተናሥኦት (Uprising) እንዲፋፋም እንጦምራለን፡፡ ስለዚህም ሐራውያን ለተዋሕዶ – የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደሮች፣ የተዋሕዶ ጭፍሮች ነን፡፡” Bravo Harawoch, bertu. We are all with you and and Let God bless your service.

 21. Anonymous May 13, 2014 at 7:49 am Reply

  We will show our deep heart feeling and commitment to our church (Mahebere Kidusan) honestly and devotedly to fight our church enemies . Any way it is better to wait Sinodose meeting and decisions hopefully , My the Grace of God with as in to over come all issues through peace and secured way !

 22. ms May 13, 2014 at 9:09 am Reply

  ለራሳችሁ ጨለምተኛ ስትሆኑ ሌላውን የጨለማ ብዱን ትላላችሁ!! ችግራችሁ የሃይማኖት ኣይመስልም የከረረ የብሔር ጥላቻ ያላችሁ ነው የምትመስሉ። ኣንደበታችሁና ጽሑፋችሁ ክርስትያናዊ ቃና የለውም የስርዓት ኣልበኛና ስድ ኣነጋገር ነው።

  • weg May 14, 2014 at 1:32 am Reply

   Aye anegager!! Aye Christna !! Endih ende ms new enji. Do you think your words have “ክርስትያናዊ ቃና”? Yigermal.

 23. Anonymous May 13, 2014 at 12:00 pm Reply

  ማህበሩን ማፍረስ የረፈደ ጉዞ፣ ማህበሩን መንካት የፖለቲካ ኪሳራ ማስከተል፣ ማህበሩ መከፋፈል ህልም ሆነ። እኛ ግን የማህበሩን በጐ ስራ ዲያብሎስ እያከረረ በሚፈትለው ፈትል እናየዋለነ። እናም ወዳጀ ጠላት ጨለማን ባበረታው ቁጥር ማህበሩ የሚበራቸው ችቦወች ይበራከታሉ።

 24. Anonymous May 13, 2014 at 12:01 pm Reply

  “ሐራ ዘተዋሕዶ – የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደር፣ የተዋሕዶ ጭፍራ ማለት ነው፡፡ ሐራ – ሐርነት፣ ነጻነት ያለው ማለት ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ትምህርትና ሥርዐት፣ ትውፊትና ታሪክ ለማጥፋት በውስጥና ከውጭ የሚንበለበሉትን የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ፍላጻ ለመመከት የእምነትን ጋሻ አንሥተን እንጦምራለን፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ብሔራዊ ክብርና ተቋማዊ ነጻነት በማንበር ሐዋርያዊ አገልግሎቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጠናከርና እንዲስፋፋ የመረጃንና የዕውቀትን ሰይፍ በመያዝ እንጦምራለን፡፡

 25. Anonymous May 13, 2014 at 12:05 pm Reply

  ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያናችን ለመንፈሳዊ ተቋምነቷ የሚመጥኑ ሰዎች ሊመደቡላት እንደሚገባ ቢናገሩም ከቅዱስነታቸው ጀምሮ በየመድረኩ የሚታየው አቋም የለሽነትና አቅመ ቢስነት ከፍቶ ዐደባባይ ወጥቶ አሸማቃቂ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ጥቂት በማይባሉ ሠራተኞችና አገልጋዮች ዘንድ ደግሞ አቅመ ቢስነቱና አቋመ ቢስነቱ ንቀትና ጥላቻን ከማስከተሉም በላይ የቀድሞውን ፓትርያርክ በደል አስረስቶ አቡነ ማትያስ ሳይቀር በይፋ ያደነቁላቸውን ዓለም አቀፍ ሰውነት እንዲሁም ብዙዎች የሚስማሙበትን አእምሯዊ ብልጠትና ቅልጥፍና

 26. gedamualebachew May 13, 2014 at 12:48 pm Reply

  E/R tewahido hayimanotachen titebqln ketafiw beztuwalna.

 27. gedamualebachew May 13, 2014 at 1:11 pm Reply

  የአህዛብ ዱለታ የተጀመረኡው አሁን አዪደለም የኦርቶዶክስ ተዋሂዶን እምነት ለማጥፋት ከቆሙ ቆዪተዋል ግን እራሳችዉ ዪተፋሉ እንጂ አያተፉዋትም፤ በሰይፍ የሚገድል በሰይፍ ይገደላል፤ ኢትዮፕያ የእግዚአብሂር ሃገር ናትና እግዚአሂር ይተብካታ እነዳኒ አይⶋህችሁ እግዚአብሂር ከነአንተጋር ይሁን።

 28. Anonymous May 14, 2014 at 5:55 am Reply

  egziabehar yezemenun hawareya maheberachen yetbek ,

 29. Anonymous May 23, 2014 at 1:37 pm Reply

  በእግዚአብሔር የሚታመን ሁሉ ምህረት ይከበዋል: የማይታመን ግን መቅሰፍት ይከበዋል::

 30. Anonymous May 29, 2014 at 10:36 am Reply

  ማህበሩን ማፍረስ የረፈደ ጉዞ፣ ማህበሩን መንካት የፖለቲካ ኪሳራ ማስከተል፣ ማህበሩ መከፋፈል ህልም ሆነ። እኛ ግን የማህበሩን በጐ ስራ ዲያብሎስ እያከረረ በሚፈትለው ፈትል እናየዋለነ። እናም ወዳጀ ጠላት ጨለማን ባበረታው ቁጥር ማህበሩ የሚበራቸው ችቦወች ይበራከታሉ። ቸቦው ግን ብርሀን ብቻ ሳይሆን ሙቀትም እንዳለው መረዳት ያስፈልጋል።

 31. meash June 1, 2014 at 7:20 am Reply

  Egeziabehare yiker yibelen…yih mekfafel ye hatiyat kefati min yahil endebeza yemiyasayi new egziabehare yiker yibelen!!!!!!!!!!!

 32. T October 12, 2014 at 5:28 am Reply

  Oh god! egna sewech malet: betam, betam, beetam……..I don’t have words to say it

 33. K. DANIEL G/SELASSIE October 13, 2014 at 6:28 am Reply

  K. DANIEL
  SELAM HARAWOCH BETEKIRSTIAN ZARE KEBAD FETENA LAY MEHONWA HULUM KIRSTIAN LIYAWKEW YEGEBAL . BEMAHIBERACEN MK LAY EJACHEWN YANESUT ABAT NEN BAYOCH BIZUWOCHU BEATBIYA BETEKIRSTIAN BEMIZBERA .BEZEREFA BEGIL HIYWOTACHEW DEMO LEARAYANET YEMAYBEKU NACHEW. BEMEHONUM KEMAHIBERU GON ENIKOMALEN.

 34. kasa January 13, 2016 at 7:43 pm Reply

  ለአባቶቻችን እግዚአብሔር አንደበተ ርቱዕ ያድርግልን፡፡

 35. Anonymous October 26, 2017 at 12:53 pm Reply

  what is the need of patryark abune matyas——–God or what——

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: