ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን በጥንታዊ የብራና መጻሕፍት አያያዝና አጠባበቅ ላይ ለዛሬ የጠራውና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት የተፈቀደው ጥናታዊ ጉባኤ በፓትርያርኩ ውሳኔ ተከለከለ

mahibere kidusan

 • ዛሬ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 – 11፡00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዝየም አዲሱ አዳራሽ ‹‹ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዓይነትና የይዘት ትንተና እንዲሁም አያያያዝና አጠባበቅ›› በሚል ርእስ የተጠራው የጥናት ጉባኤ ክልከላ መንሥኤ ‹‹የሥልጣን ተዋረድንና የዕዝ ሰንሰለትን ባልተከተለ መልኩ በቀጥታ የአድባራትንና የገዳማትን አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች እንዲሁም በቤተ ክርስቲያኒቱ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ስብሰባ መጥራት›› የሚል ነው፡፡
 • ለጥናታዊ ጉባኤው የተጠሩት የገዳማትና አድባራት አለቆች ቤተ መዘክር ያላቸው ሦስት አብያተ ክርስቲያን ብቻ መኾናቸውን የገለጹት የጉባኤው አስተባባሪዎች በበኩላቸው÷ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለድርሻዎች፣ ምሁራንና እንግዶች ጥሪ ያደረገው ዕቅዱና አስፈላጊነቱ ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ቀርቦ ከተመከረበትና ከተፈቀደ በኋላ መኾኑን አስታውቀዋል፡፡
 • ፓትርያርኩ ማኅበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ የኾነበትን አሠራር በመሻር ማንኛውንም ስብሰባዎቹንና ጉባኤዎቹን ኹሉ ያለልዩ ጽ/ቤታቸው ፈቃድ እንዳያካሒድ ከሕጉ ውጭ በቀጥታ ለማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት በላኩት የልዩ ጽ/ቤታቸው ደብዳቤ አሳስበዋል፡፡
 • የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የጥናታዊ ጉባኤውን መከልከል በተመለከተ በቀጥታ ለማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት ደብዳቤ ለመጻፍ የተገደደው፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ስለጉባኤው እንደሚያውቁና ዝግጅቱም የአሠራር ክፍተት እንደሌለበት ለልዩ ጽ/ቤቱ የበላይ ሓላፊ በማሳወቅ ሊታገድ እንደማይገባው በመከራከራቸው ነው፡፡
 • ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የዋናውን መሥሪያ ቤት ማለትም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን መምሪያዎችና ድርጅቶች ጨምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚገኙትን የሥራ ዘርፎች ኹሉ በበላይነት የማስተዳደር ሥልጣንና ተግባር የሚሰጠው ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ነው፡፡ በዚኽ ረገድ የፓትርያርኩ ሓላፊነት በቅዱስ ሲኖዶስ የሚወጡ ሕጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በፊርማቸው የማስተላለፍ፣ በተግባር ላይ መዋላቸውንም መከታተልና መቆጣጠር ነው፤ ፓትርያርኩ የሚፈጽሟቸው ተግባራት ካሉም ዓበይትና የቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ ያረፈባቸው መኾን እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡
 • በፓትርያርኩና በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሥራ አለመግባባቶች እየተባባሱ የመጡ ሲኾን መንሥኤውም÷ በአማሳኞችና ጎሰኞች የሚመከሩት ፓትርያርኩ የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት ጨምሮ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የሥራ ዘርፎች በቀጥታ የመምራትና የማስተዳደር ሓላፊነት ያለባቸውን ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን በመጋፋት የጀመሩት አካሔድ ነው፡፡
 • ፓትርያርኩ የሚመለከታቸውንና የማይመለከታቸውን ዐውቀውና ለይተው በብቃት የመምራት አቅም ያጡትን ያኽል በዙሪያቸው የከተሙ አማሳኞችንና ጎጠኞችን መሸጋገርያ ያደረገውን ውጫዊ ተጽዕኖ በቀጥታ ተቀብሎ ለማስፈጸም የሚታይባቸው ፍጥነትና ታዛዥነት በእጅጉ እንዲናቁና እንዲጠሉ እያደረጋቸው ይገኛል፡፡

*                           *                              *

 • ጥናታዊ ጉባኤው÷ ማኅበረ ቅዱሳን በመተዳደርያ ደንቡ መሠረት ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማት፣ ዕድገት፣ ታሪክ፣ ቅርስና መሰል አርእስተ ጉዳዮች ጥናት የሚያደርጉ ሰዎችን በተለይም ወጣት ምሁራንን ለማበረታታትና በተቻለው ኹሉ ለመርዳት፤ ሃይማኖታቸውን የሚጠብቁ፣ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚከባከቡና ሀገራቸውን የሚወዱ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት በተጣለበት ሓላፊነት መሠረት ከቤተ ክርስቲያን ጋራ ተያያዥነት ባላቸው ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ለማከናወን ባቋቋመው የጥናትና ምርምር ማእከል በየኹለት ወሩ የሚካሔድ መደበኛ መርሐ ግብር ነው፡፡
 • የማኅበሩ የጥናትና ምርምር ማዕከል በየኹለት ወሩ የሚያካሒደው መደበኛ ጥናታዊ መድረክ አካል የኾነውና የሚመለከተው የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጽ/ቤት ዝርዝር ይዘቱን ከአንድ ወር በፊት በጋራ ውይይት ጭምር እንዲያውቀው ተደርጎ የተጠራው ጥናታዊ ጉባኤ፣ በጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዓይነትና የይዘት ትንተና እንዲኹም ጥበቃ ላይ ያተኮረ መኾኑ የመርሐ ግብሩ መግለጫ ያመለክታል፡፡ms1971
 • ሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ ‹‹ዜና መጻሕፍተ ብራና›› በተሰኘውና በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም. በተካሔደው ሦስተኛው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጥናት ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ጽሑፋቸው እንደገለጹት÷ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍታችን ገበታቸው የወርቅ የኾነ፣ የብርዓቸው አጣጣልና የብራናቸው ንጽሕና፣ የቅርፃቸው ማማርና ውበት ሲመለከቱት በእውነት የእነርሱን መልክና ቅርፅ የኑሮ ቤት አድርጎ መኖር እንጂ በዚኽ ዓለም በሥጋዊ ኑሮ ታስሮ መኖርን አያስመኙም፡፡
 • ከቅዱሳን ገድላትና ድርሳት ባሻገር አያሌ ‹የቴዎሎጊያ እና ፊሎሶፊያ› ሀብት ያካበቱት ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት በይዘታቸው ‹‹እግረ ኅሊና ያልደረሰበት፣ የአእምሮ ክንፍ ያልበረረበት የተሸሸገ ጥበብና ያልተሞከረ ስውር ፍልስፍና›› የተካበተባቸው ናቸው ያሉት ሊቁ÷ ያልተከፈተውን የዕውቀት ጎዳና፣ ዓይን ያላየውን ዦሮ ያልሰማውን በጥበበኞች ያልታሰበውን ብልሃትና ሥነ ጥበብ መፈለግና መሻት ፈልጎም ማግኘትና አግኝቶም በፍሬውና በመልኩ መጠቀም ከአኹኑ ትውልድ የሚጠበቅ አዲስ አለኝታ፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ የምሥራች መኾኑን አመልክተዋል፡፡Ge'ez 1
 • የተማረው ትውልድ የጠፋባትን የወርቅ ቀለበት ለማግኘት ባጡ፣ ቆጡ፣ ማዘንቱ፣ ማቶቱ ሳይቀር ኹሉንም በጥንቃቄ እያገላበጠች የምትፈልገውን ልባም ሴት መምሰል እንዳለበት ሊቁ በጽሑፋቸው መክረዋል፡፡ የበሬ ቆዳው በገዛ ሞራው እንዲለፋና እንዲለሰልስ የሀገራችን መልክና ቅርፅ በገዛ ሥነ ጽሑፋችንና ቅርፃችን ማሣመር እንድንችልና በዝግ ቤት ከየቤተ መቅደሱ ምህዋርና ከዋሻ ውስጥ ወይም ከመንደርና ደንበኛ ካልኾነ ዕቃ ቤት ተደብቆ ትውውቁ ከሌሊት ወፍና ከአይጥ መንጋ ጋራ የኾነውን የአባቶቻችንን ሥነ ጽሑፍ እያሠሥንና እየመረመርን ለተከታዩ ትውልድ እንድናቆይም በጥናታቸው አደራ ብለው ነበር፡፡
 • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎች የበጀት እጥረትንና የሰው ኃይል ውሱንነትን በመጥቀስ ተግባራቸውን ማከናወንና የታሰበውን ለውጥና ውጤት ማምጣት እንደተሳናቸው ሰሞኑን በአስተዳደር ጉባኤው ላይ ቀርቦ ከተገመገመው የስድስት ወር ዕቅድ ክንውን ሪፖርታቸው በተረዳንበት ኹኔታ ያልነበሩና የሌሉ ለመኾን የተቃረቡትን ጥንታዊ የብራና መጻሕፍታችን ላይ ያተኮረው ጥናታዊ ጉባኤ የተከለከለበት ዋነኛ ምክንያት ታድያ፣ በልዩ ጽ/ቤቱ ደብዳቤ እንደተመለከተው ዝግጅቱን ካለማወቅ አልያም የዝግጅት ሒደቱ የሥልጣን ተዋረድንና የዕዝ ሰንሰለት አልተከተለም ከሚለው የተለመደ የማሰናከያ ስልት ጋራ በርግጥም የተያያዘ እንዳልኾነ ግልጽ ነው፡፡
 • የልዩ ጽ/ቤቱ የክልከላ ውሳኔ ከታወቀበት ከትላንት ቀትር ጀምሮ ደብዳቤውን እያሰራጩ የሚገኙት በፓትርያርኩ ዙሪያ በአማካሪነትና ረዳትነት ስም ከተጠጉት እነንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋራ የዓላማና የጥቅም ግንኙነት ፈጥረው የሚንቀሳቀሱት አማሳኞቹ እነኃይሌ ኣብርሃ መኾናቸው ሲታይ የክልከላ ውሳኔው ምንጭ፣ የአብነት መምህራን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ከታገደበት የካቲት ወር ጀምሮ የተጠናከረውና ማኅበሩን ብሎም ቤተ ክርስቲያኒቱን የማዳከም ልዩ ተልእኮ ባላቸው ባለሥልጣናት ጭምር ተደግፎ የቀጠለው ጫና ስለመኾኑ ግልጽ ያደርገዋል፡፡
 • የማኅበሩ አመራር ስለፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የክልከላ ደብዳቤ ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጋራ መምከሩ የተገለጸ ሲኾን በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አማካይነት የጽሑፍ ምላሽ እንደሚሰጥ ተመልክቷል፤ የጎሰኝነት ሰለባ በመኾንና ለአማሳኞች ሽፋን በመስጠት በበታች ሠራተኞች ዘንድ ሳይቀር ክፉኛ እየተናቁና እየተጠሉ በመጡት ፓትርያርክ ዙሪያ የተኮለኮሉትን ጥቅመኞች የማጋለጥ እንቅስቃሴም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እየተገለጸ ይገኛል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ዓመታዊ ስብሰባው የማኅበሩን ተጠሪነት ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር አውጥቶ በጊዜያዊነት ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ያደረገበት ውሳኔ፤Holy Synod 2004 Ginbot annual meeting decision on Mahibere Kidusan

የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ በመተላለፍ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የፈቀዱትን የማኅበሩን ጥናታዊ ጉባኤ የከለከሉበትና ለወደፊቱም ማኅበሩ የልዩ ጽ/ቤቱን ፈቃድ ሳያገኝ ስብሰባ ማካሔድ እንደማይችል ያሳሰቡበት ደብዳቤ፤pat ban

Advertisements

57 thoughts on “ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን በጥንታዊ የብራና መጻሕፍት አያያዝና አጠባበቅ ላይ ለዛሬ የጠራውና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት የተፈቀደው ጥናታዊ ጉባኤ በፓትርያርኩ ውሳኔ ተከለከለ

 1. maru May 1, 2014 at 6:33 am Reply

  Egzio meharene kirstos!

 2. Anonymous May 1, 2014 at 8:09 am Reply

  yasaznal

 3. sim May 1, 2014 at 8:18 am Reply

  ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማን ግብ ያለው በመሆኑ በጊዜው በሚታዩ ጥቅመኞችና አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሁከት ሳንዘናጋ የወንጌል ተልእኳችንን በጥበብና በትዕግስት ከግብ ማድረስ ይገባናል እንላላን፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ያዕቆብ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ እወቁ፡፡ ያዕ.1፡2 እንዳለ ስለ እምነታችንና ስለቤተ ክርስተያናችን የምናደርገውን አገልግሎት ፈታኙ ዲያብሎስ ሊያደናቅፍ ሠራዊቶቹን ቢያሰማራም እግዚአብሔር አምላካችንን ትዕግስትንና ጽናትን እንዲሰጠን ፈተናውንም እንዲያሳልፍልን በጽናት እንለምነው፡፡- እርሱ በሰው ዘንድ የማይቻለውን እንድንችል ማድረግ ያውቅበታልና፡፡ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

 4. Anonymous May 1, 2014 at 8:53 am Reply

  God is Great!!!!!!!!!!!!!!!!

 5. Anonymous May 1, 2014 at 8:55 am Reply

  yebase atamta

  • Anonymous May 2, 2014 at 6:43 pm Reply

   Amennnnnnn!!! Yakedosan Amelak yerdan kedset Batkeresetanen yetabekelen

 6. Seni May 1, 2014 at 10:25 am Reply

  Min nekachew abatachin? yih tsom tselotina subae yifeligal

 7. መስፍን May 1, 2014 at 11:55 am Reply

  ቆይ ግን……እንደ ዛሬ ዘመናዊ ትምህርት ባልተስፋፋበት ወቅት ለሀገሪቷ እንደ ትምህርት ሚኒስቴር በመሆን ብዙ ሊቃዉንትንና ነገሥታት ያፈሩትን የአብነት ት/ቤቶችን እናስተዋውቅ፣ እናክብር፣ እንጠብቃቸዉ ሲባል ፤ አይቻልም የሚሉ…….እንደ ዛሬ የወረቀት ፋብሪካዎች ሳይስፋፉ፣ ምንም የኬሚስትሪ ትምህርት ሳይኖር አባቶቻችን ቀለም በጥብጠው፣ ብራና ዳምጠው ለሀገራችን ያስቀመጡት፣ የማይለኩ ጥበባት የሚገኝባቸው የብራና መጻሕፍትን እንጠብቃቸው ሲባል፤ “በውሃ ቀጠነ ” ምክንያት አትችሉም የሚሉ እነዚህ ወገኖች ከወደየት ናቸው???……..ይህ ነገር ማኅበረ ቅዱሳንን በማሰላቸት ማዳከም ብቻ ሳይሆን ሌላ ተልዕኮም ያለው ይመስላል፡፡

 8. ashebir.G May 1, 2014 at 1:13 pm Reply

  Seytan Yetateknewun Menfesawi Tor liyasfetan bitatarim Yastateken AMLAK Keigna gar silale Yitebikenal !!!!! Mahiberachinin Egziabher Yitebik !!! Leabatochachinim Lib-yistilin!!!!

 9. በአማን ነጸረ May 1, 2014 at 1:18 pm Reply

  ወቆመ በፍኖት እንተ በኩሉ ኢኮነት ሠናይተ!!
  1. እባካችሁ፡ወደ ውስጣችሁ ተመልከቱ፣ማኅበር ላይ የሚኖርን አመለካከት እንደ ቤ/ክ ጥቅም መለኪያ አድርጋችሁ አትውሰዱ፣ካለአዋቂ ሳሚ ሚዲያዎች እንራቅ፣ይሄን ካላደረግን ማኅበሩ በቤተክህነቱ ያለው አመኔታና ተቀባይነት እንዲሁም መደራደር አቅም ይቀንሳል፡፡ይሄን ነው ላለፉት ወራት የለፈፍነው፡፡ግን የሰማን የለም፡፡ጭራሽ ውሉደ-ጥምቀት መሆናችን ጥያቄ ውስጥ ገባ፡፡አሁን ስታለቃቅሱም….ሶበ ትረክቦ ኃጢኣቱ ይጸልአ… እያልን እባካችሁ አካሄዳችሁንና ከበላይ አካላትም ሆነ ከሌሎች የቤ/ክ አካላት ጋር ያላችሁን ግንኙነት በመተማመን ላይ ለመስረት የሚያስችል ብልሃት ፈልጉ ስንል እንለምናችኋለን፡፡ራሳችሁን የኦርቶደክስ ብቸኛ አርበኛ እያደረጋችሁ ጉዳዩን የኃጥአንና የጻድቃን ልዩነት አታስመስሉት!!
  2. ዘረኝነትና ጉቦኝነት የማይናቅ ሚና በሚጫወቱበት የቤተክህት ፖለቲካ ውስጥ የእናንተ አጉል ማኅበርን ከሃይማኖት ያምታታ አካሄድ አባቶችን ከፋፍሎ ወደ አልሆነ መስመር እንዳይከተን ጥንቃቄ አድርጉ፡፡እሱን አስነዋሪ ተግባር ላለመፈጸም ኳሱ በእናንተ እጅ ነው፡፡ስለዚህ አጉል ቡድናዊነትን ፕሮሞት በማድረግ ብፁዕ ስ/አስኪያጁንና ፓትርያርኩን ሊያጋጩ ከሚችሉ ተግባራት ታቀቡ፡፡
  3. በፓትርያርኩ ውሳኔ ደስ ካልተሰኛችሁ ሥርዐቱን ጠብቆ ለቅ/ሲኖዶስ ይግባኝ ማለት ነው፡፡ከዚህ ውጭ አዲሱን አባት በማኅበር ሚዛን እየለኩ ስማቸውን ቆርጦ ለመቀጠል መጣር ለማናችንም አይጠቅምም!!እነ ሀይሌም ላይ ማስረጃ ካላችሁ አውጡት፡፡ዝም ብሎ ከርሞ ማኅበሩ ላይ ጥያቄ ባነሱ ቁጥር ዘራፍ ማለት ግን የተአማኒነት ጥያቄ ያስነሳል፡፡
  4. የወያኔ/ኢህአዴግ ፖለቲካ፣የመናፍቃን ዘመቻ፣የአማሳኞችና ዘረኞች ግንባር….እያሉ ቃላትን አጋኖ በማሽሞንሞን የራስን ያልተገባ አካሄድ መሸፈኛ ማድረግ ሊበቃ ይገባል፡፡የችግሮቹን መኖር እናንተ በምታጋንኑት መጠን ባንቀበለውም መኖራቸውን አንክድም፡፡የሰከነና በቅንነት ላይ የተመሰረተ መድረክ ከፈጠራችሁ እኛም የምናውቀውን የቤተክህነት እንከን ከመናገር ወደ ኋላ አንልም፡፡ነገር ግን ማኅበራችን እነዚህን ችግሮች ብቻውን እየተዋጋ ስለሆነ ውስጥህን ፈትሽ አትበሉት ማለት “የሹም ዶሮ ነኝና እሺ አትበሉኝ”ን ያስተርትባችኋል፡፡መመጻደቅ የሚለውን ቃል እዚህ ላይ እንመዘዋለን!!
  5. ስለ ኢህአዴግ አንድ ነገር ልጨምርላችሁ፡፡ከሙስሊሞች እንቅስቃሴ እንደተረዳሁት ኢህአዴግ በአንድ የሃይማኖት ውስጥ አንድ የአስተዳደር ተቋም ነው እንዲኖር የሚፈልገው፡፡ለዛ ነው ኢህአዴግ የምርጫ ጊዜው ያልተጠናቀቀውን መጅሊስ ሸፍነው የሙስሊሙ ወኪል እኛ ነን ሲሉ የነበሩ የአንዋር የሙስሊሙ ማኅበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ በሚል የተቋቋሙ ሰዎች ላይ ሰይፉን የመዘዘው፡፡የመንግስትን አካሄድ ስታዘበው ለአንድ ሃይማኖት፣አንድ የሃይማት አስተዳደር የሚል መርህ ያለ ይመስለኛል፡፡በተለይ በኦርቶዶክስና በእስልምና፡፡ተቋማቱም ቢሆኑ ይህ መርህ ይስማማቸዋል ብየ አስባለሁ፡፡በተለይ እኛ እንደ ኦርቶዶክስ በአንድ ሲኖዶስ ስር በሚተዳደር የአስተዳደር መዋቅር ማደራችን ግድም ነው፡፡እንደነ-ስም-አይጠሬ ዝርው መሆን አይቻልም፡፡ወደ ነጥቡ ስመጣ፡ ማኅበሩ በአንድ ሃይማኖት ተቋም ውስጥ ያለ ሌላ ተቋም ሆኖ እየታየ ነው፡፡ይሄ እይታ ከቤተክህነቱ አልፎ የመንግስትም እይታ ወደ መሆን ካደገ የአንዋር ችግር ወደ ራጉኤል ተጋባ ማለት ነው-መንግስት መበርበሪያውን አስቀድሞ ከነቆመጡ ይመጣል፡፡
  6. ያ እንዳይሆን እንስከን!!ቢያንስ ማኅበሩ በልሳናቱ ማለት የሚገባውን ይበል!!አንባብያንም ዘለን ወያኔ/ኢህአዴግ እያሉ የኖረ ቂም ያለ በሚያስመስል መልኩ ስሜታዊ ሆነን ማኅበሩን ለመከላከል መሞከር ቀድሞውኑ በመንግሥት አይን…አንዳንድ የማኅበረቅዱሳን….አባላት ተብሎ ለተቀመጠው የአክራሪነት መለኪያ ሚዛን ራስን በማስረጃነት መቁጠር ወይም ክሱን አምኖ የተከሳሽነትን ቃል እንደመስጠት የሚቆጠር ነው፡፡ስለዚህ ቁጣችንን በልክ እናድርገው፡፡
  ወነአምን በአሀቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላእለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት!!

  • Anonymous May 1, 2014 at 11:31 pm Reply

   አንተ መናፍቅ ምን እያልክ ነው ?ደደብ

   • Anonymous May 2, 2014 at 11:02 am

    በጣም ጥሩ ምክር ነው የሰጠው። በምክሩ ባትስማማ አንኳን መሳደብ ትክክል አይደለም። መሳደብ የስሜታዊነት ምልክት ነው። ስሜታዊነት ደግሞ ከመንፈሳዊ ሰው አይጠበቅም። ማህበራችን ችግር ውስጥ እንዳይገባ መደማመጥ ጥሩ ነው።

  • ልብ ይስጠው May 2, 2014 at 7:27 am Reply

   ይሁን እሲ፡፡ የቤተክርስቲያን አምላክ ሁሉንም ልብ ይስጠው፡፡

  • Anonymous May 2, 2014 at 10:10 am Reply

   ኦርቶዶክሳዊ ለመምሰል ያደረከዉ ጥረት አልተሳካም…..እዛዉ ባዶ አዳራሽህ ሄደህ ብትጮህ ይሻልሃል……ዉሾች ይጮሀሉ…ግመሎችም ይሄዳሉ፡፡

  • Annonyname May 2, 2014 at 11:18 am Reply

   በአማን ኢነፀርከ አንተ ውዕቱ ማኅጎሊ!!!!!

  • የገሀነም ደጆች አይችሏትም! May 6, 2014 at 10:17 am Reply

   – የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!
   የተባለች ቅድስት ቤክርስቲያናችን ግን እስከ አለም ፍፃሜ ትኖራለች፡፡
   – አንተ ተረፈ አሪዎስ ተስፋ ቁረጥ!!!
   – አንተ ይሁዳ ተስፋ ቁረጥ!!!
   – አንተ ሙሰኛ ተስፋ ቁረጥ!!!
   – አንተ ከሀዲ ተስፋ ቁረጥ!!!
   – አንተ የመስቀሉ ስር ቁማራተኛ ተስፋ ቁረጥ!!!
   ….

 10. Anonymous May 1, 2014 at 1:33 pm Reply

  abet

 11. ግእዝ በመሥመር-ላይ May 1, 2014 at 3:22 pm Reply

  ስም አጠራራቸው የተመሰገነው አለቃ አያሌው፤ አባ ጳውሎስን የተቃወሙበት ዐይነተኛ ምክንያት፤ በኦርቶዶክስ አስተምህሮ የሲኖዶስ የበላይ መንፈስ ቅዱስ ሲኾን፤ አባ ጳውሎስ ያንን ሽረው ሲኖዶሱ ተጠሪነቱ ለእኔ ነው ማለታቸው ነበር። አባ ጳውሎስ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ቦታ ልውረስ ባሉ መጠን ራሳቸውን ጣዖት ማድረጋቸው ነውና ወይ ሊመለሱ አለያም ሊወገዙ ይገባል ያሉት አለቃ ለጊዜው ሰሚ ቢያጡም ዃላ ግን እነ አባ ገብርኤልን ጨምሮ ኹሉም የሚጮኸው ጩኸት ኾኖ ነበር። [በዚኽ አኳዃን “ዘኢተግብረ ተገብረ” የሚያሰኝ ነገር፦ በቦሌ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከጣዖት ጋራ መኖር ጀምሯል ማለት ነው። እስከ መቼ ይቆያል? ባለቤቱ ይወቅ!]

  አባ ጳውሎስ ሲያልፉም ሲኖዶሱ ለፓትርያርክ እንኳ ሳይኾን ጭራሽ ለይቶለት ለዐላውያን ተጠሪ የሚኾንበት መንገድ “ልዩ ጽ/ቤት” በሚባል እልፍኝ በኵል እንዲዋቀር ተደርጎ፤ አባ ማትያስ ስንኳን በጥምቀት እና በሢመተ ክህነት ያገኙትን መንፈስ፤ ልባቸውንም ኾነ አእምሯቸውን የሚያስቀምጡበት አስቀምጠው ለዚኹ አገልግሎት አስፈላጊ የኾነውን መልካቸውን ብቻ አሳምረው በለስላሳ አንደበታቸው ምእመናንን እያታለሉ እንዲቀመጡ ኾኗል። ስንኳን ይቺን የዝንብ ጠንባራ የሚያውቀው ማኅበርም፤ ችግሩ እንዲኽ ራሱ ላይ እስኪመጣ ድረስ የርሳቸውን “መንፈሳዊነት” በጋዜጣው እና በቴሌቫንጄሊዝሙ እያወዳደሰ ዋና አቀማማጭ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ባጭሩ ማኅበሩም በግብረ ዐበርነት አጥፍቷል።

  ስለዚኽ ማኅበሩ ባለፈው ጥፋቱ ተጠጥቶ፤ አኹንም በልዩ ጽ/ቤት ተብየው በኩል እየተላተመ ያለው ካማንም ከማን ጋራ ሳይኾን፤ አገሪቱን ለመበተን፤ ቤተ ክሲያኗን ለማጥፋት ቈርጠው ከተነሡት ዐላውያን ጋር እንደኾነ በምር ሊረዳና፤ ይኽንኑም “የእግዚአብሔር ፈቃድ” ነው እያለ ተዘናግቶ ማዘናጋቱን በማቆም የሚገባውን ለማድረግ መወሰን ይኖርበታል።

  • Anonymous May 2, 2014 at 11:27 am Reply

   አባ ጳውሎስ ሲያልፉም ሲኖዶሱ ለፓትርያርክ እንኳ ሳይኾን ጭራሽ ለይቶለት ለዐላውያን ተጠሪ የሚኾንበት መንገድ “ልዩ ጽ/ቤት” በሚባል እልፍኝ በኵል እንዲዋቀር ተደርጎ፤….ብለህ ስትሳሳት ያዝኩህ፡፡ተሳስተሀል፡፡የፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ድሮም ነበር፡፡አዲስ አይደለም፡፡አጣራ፡፡
   ቅስቀሳህን ግን ጥሩ ነው፡፡ለአንድነት ፓርቲ የእሪታ ቀን የሰልፍ ጥሪ ይሆናል፡፡ከቻልክ ፓምፕሌቱንም ጨምረህ ለጥፍ፡፡ወይ ግእዝ፣ እንዲህ መስመርሽ ይጥፋ!!

   • ግእዝ በመሥመር-ላይ May 5, 2014 at 1:30 pm

    ይዘኽ ሙተኻል። በአስተያየቴ፤ ልዩ ጽ/ቤት “ድሮም” ስለመኖር አለመኖሩ፤ ወይም “አዲስ”ስለመኾን አለመኾኑ በግልጥ የተቀመጠ ነገር የለም። ደግሞ አንተ “ድሮ” ያልከው የትናንቱን የአባ ጳውሎስን ዘመን ነው። ይኹንልኽና ወዳጄ፤ በቀድሞ ጽ/ቤትስ ዐዲስ የተንኮል መንገድ ማዋቀር አይቻል ይመስልኻልን? ልብ በል፤ በንግግሬ ዐዲስ ኾኖ የሚታየው በቤተ ክህነቱ የተሰገሰጉ ወሮ በሎች በቤተ መንግሥቱ ከመሸጉት ዐላውያን ጋራ እየተናበቡ ፓትርያርኩ ፈቀዱም አልፈቀዱ መርዛቸውን የሚረጩበት መሥመር ነው። ዐውቀኽ የምታደናቁር ካልኾንኽ በቀር፤ ይኽንን ማየት አይሳንኽም። መሥመር የጠፋኽ አንተ ነኽ!

 12. Anonymous May 1, 2014 at 5:38 pm Reply

  በቃ በደከመ ላይ በትር አይብዛ! ሰው ያለውን ያቀብላል፤ በመሰለው ባደረበትና በዋለበት ይመዘናል፤ ያለውንም ነው የሚመነዝረው!!
  ነገር ግን የሚያሳዝነው
  ከላይ አማን ነጸረ እንዳለው፡ ብፁዕ አባታችን የማስተዳደር ችሎታም ብቃቱም ከሌላቸው መፍትሔው ምንድር ነው? የሚለውን መመለስ ያስፈልጋል።
  (1) መሰረታዊና basic የሆነውን የአስተዳደር ስርአት አጠናክሮ ከየሀገሩ-ስብከት አባቶች፤ ከቋሚ ሲኖዶሱና፤ ከሲኖዶሱ ጋር መስራት መቻል።
  (2) በቤተ-ክህነቱ አስተዳደር ላይ በተለይ በጎጠኞችና በጥቅመኞች ላይ ዘመቻውን አጠናክሮ መቀጠል፤ ግለሰቦቹን ለይቶ ማውጣትና ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ መጣር
  (3) ተበዳዮ ማኅበሩ ብቻ ሳይሆን በየሃገረ ስብከቱ ያሉ አባቶች፤ ስራ አስኪያጆችና መዕመናን በአጠቃላይ ስለሆኑ ይህንን በተቀናጀና መልክ ባለው መስራት
  (4) በመጪው የሲኖዶሱ ስብሰባ ቢቻል የፓትርያርኩን እንደዚህ የተዝረከረከ አሰራር እንዳይቀጥል ማስቻል፤ የፓትሪያርኩ ልዩ ጽህፈት ቤት የተባለውን፤ ልዩ ጸሃፊዎቻቸውንና አማካሪዎቻቸውን (ከአባቶች በስተቀር) ጭምሮ ሀላፊዎቹንና ሀላፊነታቸውን መጎብኘት (ለእኔ ሸዋንግዛው ስም ተሰጥቶት ተወልደ መሆኑ ሲገኝ ያሳፍራል። ያውም ቤ/ክ..ክህነት)

  በፈተና ጥንካሬን ያመጣል። እግዚአብሔር በሁሉም ነገር ይጨመርበት።

 13. Anonymous May 1, 2014 at 5:54 pm Reply

  I returned, and saw under the sun, that the race is not to the swift, nor the battle to the strong, neither yet bread to the wise, nor yet riches to men of understanding, nor yet favour to men of skill; but time and chance happeneth to them all. Eccles. 9:11

 14. Anonymous May 1, 2014 at 7:52 pm Reply

  GUYS, TECHICALLY MAHIBER ERIKUSA IS CLOSED ABUNE MATHIAS I, THE 6TH PATHRIARCH OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH, ON MAY 1ST 2014…PERIOD!!!

  OUR LORD, GOD IS GREAT!

  EWINETU SIGELET

 15. tobiaw21 May 2, 2014 at 5:57 am Reply

  Reblogged this on tobiaw211712.

 16. Anonymous May 2, 2014 at 5:59 am Reply

  ስም አጠራራቸው የተመሰገነው አለቃ አያሌው፤ አባ ጳውሎስን የተቃወሙበት ዐይነተኛ ምክንያት፤ በኦርቶዶክስ አስተምህሮ የሲኖዶስ የበላይ መንፈስ ቅዱስ ሲኾን፤ አባ ጳውሎስ ያንን ሽረው ሲኖዶሱ ተጠሪነቱ ለእኔ ነው ማለታቸው ነበር። አባ ጳውሎስ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ቦታ ልውረስ ባሉ መጠን ራሳቸውን ጣዖት ማድረጋቸው ነውና ወይ ሊመለሱ አለያም ሊወገዙ ይገባል ያሉት አለቃ ለጊዜው ሰሚ ቢያጡም ዃላ ግን እነ አባ ገብርኤልን ጨምሮ ኹሉም የሚጮኸው ጩኸት ኾኖ ነበር። [በዚኽ አኳዃን “ዘኢተግብረ ተገብረ” የሚያሰኝ ነገር፦ በቦሌ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከጣዖት ጋራ መኖር ጀምሯል ማለት ነው። እስከ መቼ ይቆያል? ባለቤቱ ይወቅ!]

 17. Anonymous May 2, 2014 at 6:10 am Reply

  mengst beketeta betekerstiyanachenen eyemerat selhon hulum ortdox crstian menkat aleben …

 18. Anonymous May 2, 2014 at 6:41 am Reply

  Abetu Maren!!!! Hulum beseferebet kuna yiseferal. His Holyness Aba Matias need to return to his own heart. He is doing wrong, not on MK but on the church as a whole. Hulum yalifal, gin tizibit new!!!!!! Eyebase hede eyebase. liasegn new,alemetadelachin!!!!!!!!!

 19. Anonymous May 2, 2014 at 7:16 am Reply

  do not say “ስም አጠራራቸው የተመሰገነው አለቃ አያሌው” ለፍጡር ይህ ቃል አይገባም

  እኔ የምለው ማቅ ለመሆኑ የእዝ ስንሰለት የማትጠብቊት ለምንድን ነው ? ከአባቶ ች ጋር እየተመካከራችሁ ያማትሰሩት ለምንድን ነው ?

  • Anonymous May 3, 2014 at 6:46 am Reply

   አንተ ድንጋይ ለመሆኑ የእዝ ስንሰለት ምን ማለት እንደሆነ ተረድተሃል?ደሞስ የማህበሩንስ ያለበትን መዋቅርስ ታውቀዋለህ?

  • Anonymous May 3, 2014 at 6:50 am Reply

   መናፍቅ ገና ስትነሳ ከ አነጋገርህ ያስታውቃል ወይም መፅሐፍ እንኩአን ያነበብክ አይመስልም ወይንም ብታነብም ሰይጣን ስለሸፈነብህ ምንም ነገር አይታይህም

  • Minyidereg Minyiderg May 7, 2014 at 10:39 am Reply

   አንተ አዋቂ ከሆንክ፣ ማኅበሩ በቤተክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ቅርጽ (organizational structure) የት እንደሚገኝ በማሳየት በዚህ ጉዳይ የእዝ ሰንሰለት (chain of command) ያላከበረዉ ማን እንደሆነ አስረዳን፡፡ ያን ጊዜ ማን የእዝ ሰንሰለት እንዳልገባዉ እናያለን፡፡ ጉዳዩን በቅንነት ለመረዳት ግን ከጽሁፉ ጋር በማስረጃነት የተለጠፉትን ደብዳቤዎች ማየት ብቻ በቂ ነዉ፡፡

 20. Anonymous May 2, 2014 at 11:05 am Reply

  ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማን ግብ ያለው በመሆኑ በጊዜው በሚታዩ ጥቅመኞችና አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሁከት ሳንዘናጋ የወንጌል ተልእኳችንን በጥበብና በትዕግስት ከግብ ማድረስ ይገባናል እንላላን፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ያዕቆብ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ እወቁ፡፡ ያዕ.1፡2 እንዳለ ስለ እምነታችንና ስለቤተ ክርስተያናችን የምናደርገውን አገልግሎት ፈታኙ ዲያብሎስ ሊያደናቅፍ ሠራዊቶቹን ቢያሰማራም እግዚአብሔር አምላካችንን ትዕግስትንና ጽናትን እንዲሰጠን ፈተናውንም እንዲያሳልፍልን በጽናት እንለምነው፡፡- እርሱ በሰው ዘንድ የማይቻለውን እንድንችል ማድረግ ያውቅበታልና፡፡ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

 21. Anonymous May 2, 2014 at 11:48 am Reply

  የተፃፈዉ የእግድ ደብዳቤ ቅንነት የጎደለዉ እና ሌላ ተልዕኮ ያለዉ መሆኑን ከአፃፃፋ ያስታዉቃል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠዉን መመሪያ ወደጎን ትቶ በጠቅላይ ቤ/ክህነት ኃላፊነት ላይ እንደቀድሞዉ ጣልቃ በመግባት ማህበሩን እነዳይሰራ እንቅፋት መሆን ተገቢነት የለዉም፡፡ ማህበሩ ማሳወቅ ያለበት ተጠሪ ለሆነለት አካል ወይስ ለልዩ ጽ/ቤቱ? ይህ አይነት አካሄድ በእዉነት ከሃይማኖት መሪ የሚጠበቅ አይደለም፡፡በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ የነበሩ ሰወች በልዩ ጽ/ቤቱ ተሰግስገዉ አሁንም እንቅፋት እየሆኑ ነዉ እና ቅ/ሲኖዶስ መፍትሄ ሊሰጠዉ ይገባል፡፡ እባካችሁ አዝመራዉ እጅግ እጅግ ብዙ ነዉ የሚቅበዘበዝ እና የሚሰበስበዉ የሚፈልግ! ቤ/ክርስቲያንም ብዙ ስራ የምትሰራዉ አለ ባለመስራቱዋ ያጣችዉም የትየለሌ ነዉ፡፡ እንዲህ የተማረ በማህበር ተደራጅቶ ቤ/ክርስቲያኑን ላልማ ላገልግል ያለን አካል ተደስቶ እልል ብሎ ማሰማራት ሲገባ በቢሮ ተቀምጦ ይህን አታድርግ ብሎ ማገድ በእዉነት ኃላፊነት እና መንፈሳዊነት የጎደለዉ ተግባር ነዉ፡፡ ወይ ስሩ እና አሳዩን ወይ ሰሪን አሰሩ፡፡ አይ ቤ/ክርስቲያን ከጉድ ወደ ሌላ ጉድ
  አቤቱ መንፈሳዊ መዓዛችን ጠፍቷል እና መልስልን

 22. sim May 2, 2014 at 11:49 am Reply

  የተፃፈዉ የእግድ ደብዳቤ ቅንነት የጎደለዉ እና ሌላ ተልዕኮ ያለዉ መሆኑን ከአፃፃፋ ያስታዉቃል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠዉን መመሪያ ወደጎን ትቶ በጠቅላይ ቤ/ክህነት ኃላፊነት ላይ እንደቀድሞዉ ጣልቃ በመግባት ማህበሩን እነዳይሰራ እንቅፋት መሆን ተገቢነት የለዉም፡፡ ማህበሩ ማሳወቅ ያለበት ተጠሪ ለሆነለት አካል ወይስ ለልዩ ጽ/ቤቱ? ይህ አይነት አካሄድ በእዉነት ከሃይማኖት መሪ የሚጠበቅ አይደለም፡፡በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ የነበሩ ሰወች በልዩ ጽ/ቤቱ ተሰግስገዉ አሁንም እንቅፋት እየሆኑ ነዉ እና ቅ/ሲኖዶስ መፍትሄ ሊሰጠዉ ይገባል፡፡ እባካችሁ አዝመራዉ እጅግ እጅግ ብዙ ነዉ የሚቅበዘበዝ እና የሚሰበስበዉ የሚፈልግ! ቤ/ክርስቲያንም ብዙ ስራ የምትሰራዉ አለ ባለመስራቱዋ ያጣችዉም የትየለሌ ነዉ፡፡ እንዲህ የተማረ በማህበር ተደራጅቶ ቤ/ክርስቲያኑን ላልማ ላገልግል ያለን አካል ተደስቶ እልል ብሎ ማሰማራት ሲገባ በቢሮ ተቀምጦ ይህን አታድርግ ብሎ ማገድ በእዉነት ኃላፊነት እና መንፈሳዊነት የጎደለዉ ተግባር ነዉ፡፡ ወይ ስሩ እና አሳዩን ወይ ሰሪን አሰሩ፡፡ አይ ቤ/ክርስቲያን ከጉድ ወደ ሌላ ጉድ
  አቤቱ መንፈሳዊ መዓዛችን ጠፍቷል እና መልስልን

 23. Solomon May 2, 2014 at 12:48 pm Reply

  May God bless Ethiopia!

 24. በአማን ነጸረ May 2, 2014 at 3:41 pm Reply

  1. ቆይ ቆይ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች ተጠሪነታቸው ለማን ነው ??
  2. ማኅበሩ በቀጥታ ለእነዚህ አለቆችና አስረዳዳሪዎች የጥሪ ደብዳቤ የማድረስ ስልጣን አለው??
  3. ካለፈው ስብሰባ ወዲህ በየአህጉረ ስብከቱ ያለበላይ አካል እውቅና በማኅበሩ ስም ብቻ ቀጥታ ማንኛውንም አለቃ፣መምህር ወይም ካህን ለስብሰባ መጥራት የሚከለክል ሰርኩላር ስለመበተኑ አልሰማችሁም ??
  4. ምርጥ ሆኖ በብራና መጻሕፍትና በማይክሮ የተደራጀው የመንበረ ፓትርያርክ ቤ/መጻሕፍት የጎብኝ ድርቅ መመታቱን ሰሎሞን ቶልቻ ሲናገር አልሰማችሁም??ወይስ የቤ/ክ ችግር የምትሉት ማኅበሩ ሲቸገር ብቻ ነው??
  5. የስብሰባው መሰረዝ ይሄን ያህል የሚያስጮህ ነው??የተሰረዘው እኮ በሸሪኣ ቃል አይደለም፡፡ በራሳችን ፓትርያርክ አይደለም እንዴ፡፡ታዲያ የእሳቸውን ምክንያት በገለልተኛ ስሜት ሳንመረምር የምን ደርሶ መደምደም ነው??
  6. ለወደፊቱ እንዴት ብናረግ ነው ቅዱስነታቸው ስብሰባውን የሚፈቅዱልን ብሎ መጠየቅ ይሻላል ወይስ ብሶትን ይዞ በየሶሻል ሚዲያው ማማረር እና ርግማን ማዝነብ??
  7. እስከ መቼ ነው ጳጳሳቶቻችንና ፓትርያርኮቻችን በእናንተ ሚዛን እየተመዘኑ የሚብጠለጠሉት??
  8. ሌሎቹ የቤ/ክህነት መምሪያዎች ችግር ቢኖር እንኩዋ በውስጥ ይፈቱታል እንጅ እንዲህ በየአደባባዩ በዓለማውያን ፊት ሲያዝረከርኩት አናይም::የእናንተ ችግር ያለ ባእዳን ተሳልቆ የማይፈታው ለምንድን ነው??
  9. ሰው እንዴት 22 አመት ሙሉ ተመሳሳይ ምሬት ይማረራል??
  10. በዚህ ጊዜ ውስጥ ስንት አመራር፣ስንት መመሪያ ተቀይሮላችኋል፡፡በኢኮኖሚም በአባላትም አድጋችኋል፡፡ግን ምሬታችሁ ያው ነው፡፡አታመሰግኑም፡፡እስኪ እየተዛዘብን ከልብ እናውራቸው!!እውነት ችግሩ ከላይኛው ቤት ብቻ ነው??ማኅበሩ እንከን የለበትም ነው ምትሉት??ወይስ የማኅበሩን እንከን መናገር መናፍቅነት ነው ብላችሁ ደምድማችኋል??

  • Misikir May 2, 2014 at 8:46 pm Reply

   በአማን ነጸረ, I see you are trying to convince everyone that you are working on the dark side of the church. What is wrong with you?

  • Anonymous May 3, 2014 at 6:52 am Reply

   አንተማ ስራህን እየሰራህ ነው ይሄው ቤተክርስትያኗን ለማጥፋት መልፋት ከጀመራችሁ ሁለት ሺ ዓመት ሆናችሁ አይደለ እንዴ ?
   መናፍቅ

  • Minyidereg Minyiderg May 7, 2014 at 10:50 am Reply

   በዚህ መልኩ በሚደረግ ጥናት ላይ ተመስርቶ ለመወያየት ጥሪ ማድረግ የተጠሪነት ጉዳይን አያሳይም ፤ የመረጃ ልዉውጥን እንጂ፡፡ ማንም መረጃዉ ይጠቅመኛል የሚል አካል ይሳተፋል፡፡ እንዲሳተፍ ግዴታ የጣለ አካል የለም፡፡ የዘረዘርካቸዉ ነጥቦች በሙሉ ፍላጎትህ ምን እንደሆነ የሚያሳዩ ናቸዉ፡፡ የምትጠላዉን ማኅበር የምትቆረቆርለት በማስመሰል መጻፍ ለምን አስፈለገ?

  • ኃይል የእግዚአብሔር ነው!!! May 7, 2014 at 3:08 pm Reply

   ኃይል የእግዚአብሔር ነው!!! ኃይል የእግዚአብሔር ነው!!! ኃይል የእግዚአብሔር ነው!!!

   አንተ ተረፈ ይሁዳ!
   ያች ሴት ለጌታ ያቀረበቸውን ሽቶ፣ ይሁዳ ለምን ተሸጦ ብሩ ለካህናቱ ገቢ አይደረግም ሲል እኮ አዝኖ ይመስል ነበር፡፡ በኋላ ግን ጌታውን በ30 ብር ሸጦ፣ የንስሃም እድል ቢሰጠው እንቢ ብሎ! ለዘላለም አሸለበ! አንተና መሰሎችህ ከዘመኑ ይሁዳ አንዱ ናችሁ፡፡
   ማኅበረ ቅዱሳን እንኳን ምቼም ምንም አይሆንም!!! የቤ/ክ አምላክ የት ሄዶ! የቤ/ክ እራስ እኮ እርሱ ክርስቶስ ነው! የማኅበረ ቅዱሳንን መስራች እኮ እሱ የቅዱሳን አምላክ! የገዢዎች ገዥ! የአለቆች አለቃ ! የድንግል ልጅ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እስከ ዛሬ አታውቅም እንዴ? ወይስ እንደ ሳጥናኤል የፈጠርኳችሁ፣ የማስተዳድራችሁ… እኔ ነኝ ብለህ ትክድ ይሆን!!! ኃይል የእግዚአብሔር ነው!!!

 25. Anonymous May 2, 2014 at 3:55 pm Reply

  የተፃፈዉ የእግድ ደብዳቤ ቅንነት የጎደለዉ እና ሌላ ተልዕኮ ያለዉ መሆኑን ከአፃፃፋ ያስታዉቃል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠዉን መመሪያ ወደጎን ትቶ በጠቅላይ ቤ/ክህነት ኃላፊነት ላይ እንደቀድሞዉ ጣልቃ በመግባት ማህበሩን እነዳይሰራ እንቅፋት መሆን ተገቢነት የለዉም፡፡ ማህበሩ ማሳወቅ ያለበት ተጠሪ ለሆነለት አካል ወይስ ለልዩ ጽ/ቤቱ? ይህ አይነት አካሄድ በእዉነት ከሃይማኖት መሪ የሚጠበቅ አይደለም፡፡

 26. Anonymous May 2, 2014 at 10:13 pm Reply

  በአማን ነጸረ MALET America Denver Colorado yemigegne ” Like Gubae” Dn Kinefe new (KIFU SEW NEW ) – KEZIH BEFIT YE ADDIS ABABA HAGERESIBIKET TSEHAFI BEMEHON HAGERESIBIKETUN ZERIFO AMERICA MIST GEZITO YEGEBA SEW NEW. WEDI TIGIRAY KINEFE KEBEREHA JEHIMIRO ABIREN NEW YEMETANEW BEMALET YEMITAWEK NEW. YOU HAVE TO KNOW THIS DANGER GUY…

  ABUNE MATHIAS PATHRIARCH ENDEMIHONU YEBEREHA EKID NEW MANIM LIHON AYICHILIM BEMALET YASIWERA ENDENEBER KEZIH HUNEN SEMITENAL…BE AGATAMI YIHUN BETAKEDEW MESERET PATHRIARCH SIHONU DEGIMO ALALIHUACHIHUM BEMALET YASIWERAL ALU…ANYWAY, AMERICA YALACHIHU ABALAT TETENIKEKUT…TAKE CARE!

  “YEGETA FEKAD YIHUN BILEN ZIM ALINE”

 27. Anonymous May 2, 2014 at 10:44 pm Reply

  እስቲ እኝህ በ አማን ነጸረ የተባሉ መናፍቅ ምን አይነት ሰው እንደሆኑ እንመልከት :የገዢው ፓርቲ ደደብ አገልጋይ ለመሆናቸውና ቤተክርስትያን ፈርሳ ለመናፍቃን መሰጠት አለባቸው ከሚሉት እንዲሁ በ ጎሳ ፍቅር ከታወሩት ጎራ እንደሆኑ ከፈስቡክ ገፃቸው መመልከት ይቻላል::
  https://www.facebook.com/firdna.kunene/about

 28. Anonymous May 2, 2014 at 11:33 pm Reply

  “በአማን ነጸረ” በሚል የምታቀርበውን ሀሳብ በሀሳብ ደረጃ ብቀብለውም አሁንም ልነግርህ የምፈልገው ነገር ቢኖር መንጽርህን እንድታጸዳውና በአንተ ደረጃ በዚህም በዚያም ያለውን ማለት ነው በትክክል እንድታየው ነው። ምክንያቱም ለመተራረም ከሆነ እውነተኛነትና የነገር ተአማኒነት ያስፈልጋል። ይህንን ካልያዝክ ግን አካሄድህ በጣም የህሳብ መንሸዋረሩ የበለጠውኑ ከመነጽሩ ዘልቆ እየታየ ነውና በደንብ አጢነው። በኔ ህሳብ በዚህ ድረ ገጽም ሆነ በዲ/ን ዳንኤል አይቼአለሁ ለአንድ ወገን መልስ ሰጪ እንጂ የራስህን አእምሮ በትክክል የተጠቀምክበት አይመስለኝም። አሁንም ቢሆን በገንቢ የሀሳብ ልዩነት አምናለሁ። አሁንም የአንተን ሀሳብ እንደተከታተልኩት ምርቅና ፍትፍት ዓይነት ነው። የማኅበሩ አባላት ቢበዙ ለትሩፋት ሥራ በመሆኑ ያስደስታል አንጅ አያስከፋም። ምሬቱ እኮ የቀጠለው በቤተ ክህነቱ ዙሪያ ያለው ፖለቲካዊ ጎጣዊ ዘመቻዎች ለሥራ እንቅፋቶች አሁንም ከበዋት ስለአሉ ነው አንተ ከፈራህው እኔ ልናገርልህ። ያንን አካባቢ ቀድም ብዬ ስለማውቀው ነው እንዲህ የምልህና አስብበት። ለምተሰጣቸው ሀሳብ ነጥብ በነጥብ መሥጠት ይቻል ነበረ ነገር ብዙው ነገር ቁም ነገር ስለሌለው እንዲሁ በተራ መልኩ አቅርቤዋለሁ።

 29. Anonymous May 3, 2014 at 6:46 am Reply

  ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማን ግብ ያለው በመሆኑ በጊዜው በሚታዩ ጥቅመኞችና አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሁከት ሳንዘናጋ የወንጌል ተልእኳችንን በጥበብና በትዕግስት ከግብ ማድረስ ይገባናል እንላላን፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ያዕቆብ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ እወቁ፡፡ ያዕ.1፡2 እንዳለ ስለ እምነታችንና ስለቤተ ክርስተያናችን የምናደርገውን አገልግሎት ፈታኙ ዲያብሎስ ሊያደናቅፍ ሠራዊቶቹን ቢያሰማራም እግዚአብሔር አምላካችንን ትዕግስትንና ጽናትን እንዲሰጠን ፈተናውንም እንዲያሳልፍልን በጽናት እንለምነው፡፡- እርሱ በሰው ዘንድ የማይቻለውን እንድንችል ማድረግ ያውቅበታልና፡፡

 30. ኢታርየነ ሙስናሃ ለቤተክርስቲን! May 3, 2014 at 9:35 am Reply

  ወንድሜ አሰተያየተህን ብዙ ጊዝ አነባለው አንዳንዴ ቅነነት የለው ይመስላል አንዳንዴ ደግሞ ሴራ ይሆን ካለማወቅ ትክክል ያልሆኑ እይታወችን ትሰጣለህ ለሁሉም እግዜር የወቀው ምን ብትል ምን የማለት መብት የሰጠህ ፈጣሪህ እሰከሆነ ደረስ የማለት መብት አለህ የሄን ሀሳብ ስለሠጠህ ልትሰደብ አየገባም ተሳዳቢወችን እኔም አለደገፍካቸውም ፡፡ ነገር ግን ቅን ልቦና ካለህ እሰኪ እንደስመህ እወነቱን መርምር ማኅበሩ አይሳሳትም አይባልም ሊሳሳት ይችላል እኔ ስመለከት የማኅበሩ ስህተት ከቅንነት የመነጨ እንጅ ከክፋት አይደለም ቤተክርስቲያንን የሚጠቅም ነገር ከማደረግ ነው ደግም ከዚህ ማንነቱ ካልተወቀ አስተያየት ሰጭ የተነሳ ማኅበሩን የሚወቅሱ በሙሉ መናፍቃን ናቸው ትላላቹ ብለህ መደምድምህ መሳሳት ነው፡፡ ያልበሰለ ግልፍተኛ(ደም ፍላተኛ) የሆነ ጠባይ ያለው ወይንም ደግሞ ሌላ ሴራ የያዘ አስመሳይ እንደሚሆንም መጠርጠር አይገባምን? ለሁሉም ግን በእውነት የምትመለከት ከሆነ በቅንነት የሚሳሳትንና ሆን ብሎ ለጥፋት አስቦበት የሚሳሳትን ብታይ መልካም ነው፡፡ ደግሞ የማኅበሩ ችግር ቤተክረሰቲያኗ መፍታት ትችላለች ነገር ግን እንደው በእውነት ከነፀርክ ማን ነው ግልባጭ እያደረግ ለማይመለከተው አካል ወደ ውጭ የሚያወጣው ? አባቶችን ስላከበረ ይመስለኛል አታድረጉ አታካሂዱ ሲባል እሽ ብለው የተውት ክብር ባይኖራቸው ሁለቱ የታገዱትን ጉባኤያት ማካሄድ አይችሉም ነበርን? የአሁኑስ ጉባኤ የሚመለከተው አካል አለፈቀደምን አላሳወቁምን? የተጠሩት አስተዳዳሪወችስ ቢሆኑ መዘክር ያለቸውና ቢገኙ ከጥናቱ አንጻር ጥቅም ላይ ሊያውሉት ይችላሉ ከማለት እንጅ መገኘት አለባቸሁ ብለው አሰገደዱ? የሚወራው ርዕሰ ጉዳይስ ቢሆንስ ግልፅ አይደለምን? አባቶች ከሰጡት የስራ ድረሻ አንዱን ነው፡፡ ውድ ወንድሜ ቀርቦ ማየት በአማን ለመነፀር ይጠቅማልና የቤተክርስቲያን ቅን ልጃ ከሆንክ ቀርበህ እይ መቸም አትይ የሚልህ እንደለለ 100% እርግጠኛ ነኝ፡፡ ብሌላም በኩል የሉትንስ የቤተክረስቲናችን ችግሮች ልምን አልነፀርክም ለምንስ ችግሩ ባንድ አቅጣጫ ብቻ እንዳለ ታያለህ እውን ይሄ በዓማን የሚነፅር ሰው መገለጫ ነውን ? የቤተክርሰቲያን አምላክ ፍረዱን የሰጣል ለሁሉም፡፡

 31. Anonymous May 3, 2014 at 8:36 pm Reply

  Kenefe
  Kenefe Rigib liwoded bilo tsafe enji

 32. Anonymous May 4, 2014 at 8:36 am Reply

  Sawochi Yichi Betakiristiyan indititafa lamin yifaligalu. Mahibaru yemisarawu larasu sayihon lebetakiristiyan naw iko. Yesawoch kinat ignan kawadakinibata ansiton Ye Igiziabiher liji silaragan nawu way. Yihi iwunat yesetan sira naw. Mehibaru hulem yinoral be abatoch tsalot.

 33. Anonymous May 4, 2014 at 12:55 pm Reply

  Wodajoch,

  As one of the blogger said, this and previous letters of the patriarch “technically close MK’s Office”. Unless MK gets permission from Patriarch’s special office, they are not allowed to have “ANY MEETINGS related to the church affairs”. By the way, the patriarch copied the letter to Federal Affairs Minister, Police Commission and Holy Synod – This implies that the state and the church are the same page against MK. Now, the big deal of this letter is the government gets an amazing entry door to fully control the MK’s movement (Take this analysis as a important analysis). Because, the pathriarch officially invites the government to help the church direction against MK. BTW, where is Abune Mathios and other holy synod members reply for the patriarch letter…That is why the blogger said “Technically MK is Closed” – If MK reacts against this circular, the government will take official actions…

  Where is Abune Mathios, Abune Kostos, Abune Kirlos, Abune Estifanos, Abune Abrham, Abune Gebriel, Abune Elias and so on………………………………………………………………..

  Cher Were Yaseman

 34. Anonymous May 4, 2014 at 3:05 pm Reply

  እኔ የምለዉ ፓትሪያሊኩ ምን ነካቸዉ? ከአንድ የሀይማኖት መሪ የሚሰራዉ ስራ ለቤተክርስቲያን ይጠቅማል? ወይስ ይጎዳል? የሚለዉ እንጅ የስልጣን ተዋረድ ተከተለ አልተከተለ ምን ይጠቅመዋል? እንኳን አካሄዱን ያልጣሰ ሥራ፡፡ በጣም የሚያሳዝን ንዉ፡፡ እግዚያብሄር ልቦና ይስጥል፡፡ አሜን!!

 35. Anonymous May 5, 2014 at 9:47 pm Reply

  Beaman Netsere manim sayihon CIA, EPRDF,…New. Becouse enihin Geltu “Abat” Kewoyane gar agafari bemehon yaskemete, yashome silehone ahun beminim bihon silesachew dikam mesimat silemayifelig yihin litsif yichilal. Kenefe endezih yemetsaf akim yelewim.

 36. mulugeta May 6, 2014 at 7:00 am Reply

  በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ አሉ አበው ሲተርቱ። አባ ማትያስ ስልጣኗን እንጅ ከባዷን ሃላፊነት ያሰቧት አይመስልም። በየቀኑ በሙስና በኑፋቄ እና በመሳሰሉት የሚገቡት ቃል የት ገባ? ሙሰኛው ኑረዲን ማለትም ያ መሪጌታው አማካሪ ሆኖ ሙስናን ሲዋጉ አይታያችሁም። እንዳው መጨረሻቸውን ማየት ነው። ማቅ ከቆመለት አላማ አኳያ ይህን ፈተና ማለፍ ይሳነዋል ብየ አልገምትም። ነገር ግን ቤተ ክህነቱ በመናፍቃን የበለጠ እየተጠናከረ መሆኑን እናያለን። እነ አባ ቃለ ጽድቅ ከካሊፎርኒያ ከአባ መልከ ጸዴቅ ተጣልተው ሌላ ስደተኛ ቤተ ክርስቲያን ካቆሙ በኋላ እንደገና በስነ ምግባር ችግር ምዕመናኑ አባሯቸው ሳለ አዲስ አበባ ሄዶ የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ ተዓምረ ማርያም አንባቢ እኔ ነኝ እያለ እየደሰኮረ ወደ ብስራተ ገብርኤል ተመድቧል አሉ። በዛ ያሉ ወጣት እህቶቻችንን እርሱ ይጠብቃቸው። ዋናው ነገር መናፍቃኑ የልባቸውን ከሰሩ በኋላ ከውጭ ወደውስጥ እየገቡ ሹመቱን ተያይዘውታል። ይሄ ደግሞ በውጭም በውስጥም ሲታገላቸው የነበረውን ማኅበረ ቅዱሳንን ለማጥቃት እንድቻል በአሰማሪ ድርጅቶ ቻቸው የተሰጣቸውን ለማስፈጸም እንደሆነ አትጠራጠሩ። ይህ የጠቀስኩት ቀሳጭ የአባ ሰላማን ብሎግ ያዘጋጃል እየተባለም ይታማል። ፓትርያርኩ ድሮ አሜሪካ ብቻቸውን በነበሩበት ጊዜ አብረዋቸው ብዙ መከራ የተቀበሉ ወንድሞችንና እህቶችን ለትልቅ ስልጣን ሲበቁ ያንገላቷቸው ጀመር ያ ሁሉ ትግል ምናልባት ስልጣን ላይ ለመወጣጫ ነበር እንደ ያስብላል።
  ለማንኛውም ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ከውጭ ብቻ አይደሉም። መልካም አስተዳደር ከመነኩሴ ላይገኝ ይሆን? ይህ ነው የሚያስፈራው። ከሱ ደግሞ እርሱ አንድዬ ይሰውረን።

 37. ethiopia May 6, 2014 at 10:07 am Reply

  የገሀነም ደጆች አይችቷትም!!! የተባለች ቅድስት ቤክርስቲያናችን ግን እስከ አለፍ ፍፃሜ ትኖራለች!!!

  – ተረፈ አሪዎስ ተስፋ ቁረጥ!!!
  – ይሁዳ ተስፋ ቁረጥ!!!

  – … አሁን በሹመት ላይ ያሉት ‹‹ፓትርያሪክ›› ተብዬ እኮ ይህችን ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናን፣ … የመምራትም፣ የማስተዳደርም፣ የመጠበቅም፣ የማገልገልም፣ … አካላዊም፣ ሞራላዊም፣ ስነ-ልቦናዊም … ብቃት እንደሌላቸው በአደባባይ በተግባራቸው እየመሰከሩ ነው፡፡
  – ለቤተክርስቲያም፣ ለሀገርም ፣ ለምዕመንም … አይበጁም!!!

  – ቤተክርስቲያኒቷን እየመሩት ያለው እኮ ቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ቅዱስ ሲኖዶስ… በሰጣቸው ተልዕኮ፣ ደንብ፣ መዋቅር፣ መመሪያ … ሳይሆን ፍጹም – በዘረኝነነት በተላበሰ !!!
  – በዘረኝነነት በተከተለ !!!
  – በመሀይምንት !!!
  – በአላዋዊነት !!!
  – ምንፈሳዊንት በጎደለው !!! ….. አካሄድ ብቻ ነው፡፡
  ባይሆንማ ኖሮ ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ትዕዛዝ ውጭ ለመናፍቅ፣ ለከሃዲ ካድሬ ባለጎበደዱ ነበር፡፡

  – የአንድ አመት ተግባራቸው ቁልጭ ብሎ እንደሚያሳየው ከሆነ ቤተክርስቲያኒቷን እየመሩት፣ እያስተዳደሩ፣ እያገለገሉ … ያለው
  – ከአንዳንድ ከጸረ-ኦርቶዶክስ የመንግስት ‹‹ካድሬዎች›› ጋር፣
  – ከሙሰኞች ጋር፣ ከመናፍቃን ጋር….፣
  – ከጸረ-ኢትዮጵያ አካላት ባንዳዎች ጋር … ህብረትና ቅንጅት በመፍጠር ነው፡፡
  ይህ ደግሞ የአንድ ዓመት ሥራቸው፣ ተግባራቸው… ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፣ ይመሰክራል፣ … ፡፡

  – ነገር ግን እኚህ አባት በዚች ምድር ላይ ዘላለም እንደማይኖሩ በጣም እርግጠኖች ነን፡፡
  – በስጋ ይሞታሉ!!
  – የጎሳቸውን ዝና ይዘው ይሞታሉ!!
  – በዙሪያቸው የከበቧቸውን ካድሮዎች ፣ ሙሰኞች ፣ መናፍቃን … ትተው ብዙም ሳይቆዩ ሞተው እናያቸዋለን፡፡
  ‹‹የነፍቻቸው ነገር ግን የፈጣሪ ጉዳይ ቢሆንም››፤
  – የስጋቸው ፍጻሜ ግን ብዙም ሳይቆይ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሞትና ሞት ብቻ ሆኖ እናየዋለን፡፡

  የንስሃ ህይወት ይስጣቸው!!

  ሌላ ምን ይባላል፡፡ ምንም፡፡

  የገሀነም ደጆች አይችቷትም!!! የተባለች ቅድስት ቤክርስቲያናችን ግን እስከ አለፍ ፍፃሜ ትኖራለች፡፡

  – ተረፈ አሪዎስ ተስፋ ቁረጥ!!!
  – ይሁዳ ተስፋ ቁረጥ!!!

 38. Anonymous May 7, 2014 at 6:21 am Reply

  አቢቱ ልኡል እግዚአብሂር ሆይ ቢተ-ክርስቲያንና ምእመናን እዉነትን በሚጋፉ አባቶች የምትመራዉ እስከ መቺ ድረስ ነዉ?

 39. Mesfin Dubale May 7, 2014 at 7:11 am Reply

  አቢቱ ልኡል እግዚአብሂር ሆይ ቢተ-ክርስቲያንና ምእመናን እዉነትን በሚጋፉ አባት መሳዮች የሚመሩት እስከ መቺ ድረስ ነዉ ?

 40. hgfsaaas May 7, 2014 at 1:42 pm Reply

  ግን መቸነው እዉነተኛ አባት የምናገኘዉ ፓትሪያሪኩ ወደ መንበረጵጵስና ሲመጡ የተናገራቸው 5 ነጥቦች ለምን እና እንደት እረሶቸው አረኒስ እውነተኛ አባትናፈቀኝ

 41. Anonymous October 26, 2014 at 10:13 pm Reply

  Ebakachihu wegenoch kelay endayenew ye’ez senseletu begizeyawinet le K/Sera askiyaju Ts/bet enji le liyu yepatriaric Ts/bet alemehonun bemasreja yetedegefew debdabe yasayal. Yihen manibeb kakatachihu weyim meredat kalchalachihu teyiko meredat enji yalhone neger menager leman litekim? lebete kiristian; Aymeslegnim, yewust meslo yeteleye hasabin yemawenabed teliko yalew kalhone beker. Ende bi’er simih beaman menetser yemiyawatah yimeslegnal. Le’ewnet bitmesekir ewnet netsanet yawetahal. Ye Kidusan Amlak Bete Kiristiananchinin Yitebik.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: