የፓትርያርኩ የግብፅ ጉብኝት ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈው ‹‹በመንግሥት ውሳኔ ነው››

 • የአቡነ ማትያስ የመነጋገርና የመደራደር አቅም ለጉብኝቱ መሰረዝ በምክንያትነት ተጠቅሷል
 • የግብፁ ፓትርያርክ በስድስት ወራት ውስጥ ሦስት ጊዜ የጉብኝት ጥያቄ አቅርበዋል
 • የአቡነ ታዎድሮስ ተደጋጋሚ ውትውታ ጉዳዩ ከሕዳሴው ግድብ ጋራ መያያዙን አመላክቷል
 • የጉብኝቱ መሰረዝ በአቡነ ታዎድሮስ ጥያቄ እንደኾነ መዘገቡ ከመቅለል መጥቅለል እንዲሉ ነው
 • ‹‹መንግሥት የግብፆችን ያህል ቤተ ክርስቲያኒቱን የዲፕሎማሲው አካል አላደረገም››

(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፵፫፤ ፳፻፮ ዓ.ም.)

His hHoliness00

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 118ኛ ፓትርያርክ ፖፕ አቡነ ታዎድሮስ ባቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄ መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከትላንት ጀምሮ በግብፅ ሊያካሒዱት የነበረው የጉብኝት መርሐ ግብር የተሰረዘው በመንግሥት ክልከላ መኾኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለፋክት መጽሔት ገለጹ፡፡

ፖፑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጋራ ሲላላኩ የቆዩት ከመስከረም ወር 2006 ዓ.ም. አንሥቶ እንደኾነ የገለጹት ምንጮቹ፣ እስከ ጥር ወር ድረስ ኹለት ጊዜ የጉብኝት ጥያቄ መቅረቡንና ይዘቱም ቅዱስነታቸው (ፖፕ አቡነ ታዎድሮስ) ወደ ኢትዮጵያ ይመጡ ዘንድ ይፋዊ ግብዣ ከኢትዮጵያው መንበረ ፓትርያርክ እንዲቀርብላቸው የሚጠይቅ ነበር ብለዋል፡፡

250px-Tawadros_II_of_Alexandria

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ

 

 

 

 

 

 

 

የፖፑን የጉብኝት ጥያቄ የመንግሥት አካል እንዲያውቀው ተደርጎ በመንበረ ፓትርያርኩ እየተጤነና መደረግ ስለሚገባውም ቅድመ ዝግጅት በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃና ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋራ እየተመከረበት ሳለ ፖፑ ከጥር ወር በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ መጻፋቸው ተጠቅሷል፤ በዚኽ ወቅት የቀረበው ጥያቄም ‹‹እኔ ልምጣ›› ከሚለው ይልቅ ‹‹እናንተ ኑ›› በሚል የኢትዮጵያው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ግብፅን እንዲጎበኙ የቀረበ ጥሪ/ግብዣ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ኹለቱ ጥንታውያንና ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት በትምህርተ ሃይማኖት አንድነታቸውና በጠበቀ ታሪካዊ ቁርኝታቸው እኅትማማች ቢኾኑም በብሉይ – ኢየሩሳሌም – የዴር ሡልጣን – የቅድስናና የታሪክ ይዞታ በመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሳቢያ ከፍተኛ ልዩነት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የኹለቱ እኅትማማች አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮች ሌላ ተጨማሪ የመነጋገሪያ ነጥብ እንደሚኾን ከፖፕ አቡነ ታዎድሮስ ‹‹ተደጋጋሚና የተቻኮለ›› ውትወታ ለመረዳት መቻሉ ተነግሯል – ‹‹ውትወታው አንድ የሚፈልጉት ነገር እንዳለ ያሳያል፡፡››

ኹለቱም ፓትርያርኮች በጉዳዩ ላይ የታወቀውን የመንግሥቶቻቸውን አቋም ጠብቀው በፍትሐዊ ክፍፍል ላይ ለተመሠረተ የአገሮቻቸው ብሔራዊ ጥቅም ከመነጋገር በቀር የተለየ አቋም ይኖራቸዋል ተብሎ እንደማይጠበቅ ምንጮቹ ገልጸው፣ በዚህ ረገድ በቂ ዲፕሎማሲያዊ ሥራ እንደተሠራና የፓትርያርኩ የካይሮ ጉብኝትና የኹለቱ የሃይማኖት አባቶች ንግግር የሚጨምረው ምንም ዓዲስ ነገር አይኖርም የሚል እምነት በኢትዮጵያ መንግሥት በመያዙ ሳቢያ ጉብኝቱ መሰረዙን ለፋክት ተናግረዋል፡፡

እንደምንጮቹ ገለጻ÷ የግብፅ መንግሥት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋራ ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ተጠቅሞ የውጭ ዲፕሎማሲው እንቅስቃሴ አካል ለማድረጉ የፖፕ አቡነ ታዎድሮስ ውትወታ የሚያሳይ ሲኾን፣ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት ተመሳሳይ ጥረት እንደማይታይና ደካማ መኾኑን ተችተዋል፡፡

ይህም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከፓትርያርኩ የዐደባባይ ንግግር ክህሎትና መስብሕነት ደካማነት* እንዲኹም እንደ ሕዳሴው ግድብ ባሉ ስሱ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላቸው የመደራደርና የማሳመን አቅም አስተማማኝ አለመኾን ጋራ ተያይዞ ከሚሰነዘርባቸው የከፋ ትችት ጋራ በቀጥታ እንደሚያያዝ አስረድተዋል፡፡

ለሕዳሴው ግድብ የቅስቀሳ ኃይል ኾኖ ተቋቁሞ ወደ ግብፅ ለማምራት ተዘጋጅቶ በነበረው የሕዝባዊ ዲፕሎማሲ ቡድን ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶችና ሓላፊዎች እንደሚገኙበት ያወሱ ሌሎች አስተያየት ሰጭዎች በበኩላቸው መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን በውጭ ዲፕሎማሲው ሚና ነፍጓታል የሚለውን ትችት አይቀበሉትም፡፡

ይኹንና የፓትርያርኩ የግብፅ ጉብኝት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከውጭ አብያተ ክርስቲያናት ጋራ ያላትን ግንኙነት የማስፋፋትና የማጠናከር፣ የፓትርያርኩንም የውጭ ጉብኝት የመፍቀድ የመጨረሻ ሥልጣን ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነና በዚኹም መሠረት ይኸው ጉብኝት ለመንግሥት ተገልጦ በቋሚ ሲኖዶሱ በኩል ዝግጅት ሲደረግበት እንደቆየ በመጥቀስ ጉብኝቱ በመንግሥት ውሳኔ ተከልክሏል መባሉ በታሪካዊቷ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረግ ግልጽ ጣልቃ ገብነት እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

‹‹እኛም በጉብኝቱ ልናስተላልፍ የሚገባውን የራሳችንን በጣም አስበንበት ነበር፤›› ያለው ሌላ ምንጭ፣ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ እና ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (አስቀድሞ በተመረጡት በብፁዕ አቡነ ገብርኤል ምትክ) በልኡክነት ለመጓዝ ተዘጋጅተው እንደነበር አስታውቋል፡፡ የጉብኝቱ መሰረዝ ከጸጥታ ጉዳዮችና ከፓትርያርኩ ደኅንነት ጋራ በተያያዘ ምክንያት ሊኾን እንደሚችል የጠቀሰው ምንጩ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የበዓለ ትንሣኤውን መልእክት ለብዙኃን መገናኛ ከሰጡበት ቀን ማግስት (ከኀሙስ ሚያዝያ ፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ) እንደሚያውቁ ጠቅሷል፡፡

ይኹንና የኹለቱ ፓትርያርኮች ግንኙነት በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የሰሞኑ የቪ.ኦ.ኤ ቃለ ምልልስ እንደተመለከተው ‹‹ኹሉም ነገር ተስተካክሎ የተጋበዙበት›› በመኾኑና ከሕዳሴው ግድብ ውጭ በሃይማኖት አንድነት የመደጋገፍና የቆየውን ግንኙነት አጠናክሮ የመቀጠል ወቅታዊ ጉዳይ** ያለበት እንደመኾኑ መጠን በመንግሥት ውሳኔ ተከልክሏል መባሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ነጻነትና ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው ተብሏል፡፡

በዴሞክራሲው መንገድ የተመረጡ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት እንደኾኑ የሚነገርላቸውን ሞሐመድ ሙርሲን ከሥልጣን መወገድ ተከትሎ በተነሣው ቀውስ በግብፅ ክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲያናት ላይ በደረሰው መከራና ጥፋት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የግብፁን አቻቸውን በወቅቱ በስልክ ውይይት አጽናንተው እንደነበር በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በሚያዝያ ወር ፳፻፭ ዓ.ም. ታትሞ ከወጣው ዜና ቤተ ክርስቲያን መጽሔት ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሡልጣን የታሪክና ቅድስና ይዞታችን ከማርጀቱ የተነሣ በአደጋ ላይ መኾኑና ያለው አማራጭ ‹‹የኢትዮጵያው ሲኖዶስ ከግብጽ ሲኖዶስ ጋራ ተወያይቶ ችግሩን ለመፍታት መሞከር ነው›› ማለታቸውን በመጥቀስ ፓትርያርኩ ግብጽን ሊጎበኙ እንደሚችሉ በወቅቱ በጡመራ መድረኩ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

************************
* ‹‹ቅባት ቀንሱ፤ ተልባ ጠጡ፤ አትክልት ብሉ፤›› በሚል የስቅለት ዓርብ ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በቅድስት ውስጥ ተቀምጠው ኢ.ቴቪ የቀረፀውንና በበዓለ ትንሣኤ የዜናው አካል አድርጎ ያስተላለፈው ‹ምክር› በበርካታ ምእመናንና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ዘንድ ‹‹የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ደረጃ አይመጥንም፤ ቅዱስነታቸውንም አይመለከትም›› በሚል በስፋት መነጋገርያ ኾኗል፡፡

ቃለ አቀባይ በሚል በውል በማይታወቅ መዋቅር ሓላፊነት ተይዞ የፓትርያርካዊ ጉብኝቱ በሌለ ሰበብ መሰረዙን ለማስታወቅ የተጋውና ሚዲያዊ ጉዳዮች የሚመለከተው አካል በአጠቃላይ፣ ይህንና ይህን በመሳሰሉና ሌሎችም ጉዳዮች የፓትርያርኩ አስተያየቶች፣ ንግግሮችና መግለጫዎች በተገቢው ጉዳይ ላይ ደረጃቸውንና ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲሰጡ ማድረግ አይገባውምን?

** ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሪፖርት፡-Abune Pawlos and Assam Sherif

 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከኅዳር ፫ – ፭ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በግብጽ ሐዋርያዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ ግብጽ አኹን ስላላቸው ግንኙነት ከግብፁ ጠቕላይ ሚኒስትር ከዶ/ር አሳም ሸሪፍ ጋራ ተወያይተዋል፡፡P1040881
 • ቅዱስነታቸው መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ የግብጽ እኅት ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ላይ ተገኝተዋል፡፡ በአጋጣሚው ለተገኙት የሃይማኖት መሪዎችም ስለ ሰላምና ስለ ሰብአዊ መብት መከበር ሰፊ ንግግር አድርገዋል፡፡
 • ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የግብጽ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሞሐመድ ሙርሲን ስለጋራ የሀገር ጉዳይ አነጋግረዋል፡፡
 • ኅዳር ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ቤተ ክርስቲያናችን ለምታካሒደው ኹለንተናዊ የልማት ሥራ የተጠናከረ እገዛ እንደሚደረግ፣ ይልቁንስ በቅዱስ ማርቆስ ስም ለሚሠራው ሆስፒታል የግብጽ እኅት ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቤ መንበር ለተመራው የቤተ ክርስቲያናችን ልኡካን ቡድን ማረጋገጣቸው ተገልጦአል፡፡
 • በ፮ኛው ፓትርያርካችን ምርጫ ተገቢው መረጃ ለዓለም ተላልፏል፤ በተለይም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን አምስት የልኡካን ቡድን በመላክ በምርጫው ተሳትፋለች፡፡
 • ግንቦት ፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ከግብጽ የመጡ ከፍተኛ የሕክምና ባለሞያዎችን በጽ/ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡

  Abune Mathias_President Mursi

  ፓትርያርኩና ሞሐመድ ሙርሲ በኢትዮጵያ የግብጽ ኤምባሲ (ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

 • ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በኢትዮጵያ የግብጽ ኤምባሲ ተገኝተው የግብጽ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሞሐመድ ሙርሲን ስለ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት መጠናከር አወያይተዋል፤ በውይይቱም ከመልካም መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
Advertisements

5 thoughts on “የፓትርያርኩ የግብፅ ጉብኝት ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈው ‹‹በመንግሥት ውሳኔ ነው››

 1. Anonymous April 26, 2014 at 4:23 pm Reply

  ድሮስ መናፍቅ እንደፈለገ የሚዘውረው ቤት እንዴት አይደፈር መጀመሪያ ቤተክርስቲያንቱን አባቶችን ከ መናፍቃን ያፅዱ ከዛ እስቲ መንግስት እንደፈለገ ሲፈነጭበት ታያላችሁ ?መጀመሪያ መናፍቁን ንቡረዕድ ተብየው ኤልያስንና ‘ሠረቀ’ን እንዲሁም ሳዊሮስን እና ሌሎች መናፍቃን ጳጳሳትን አባሩ ከዛ ቤቱ ማንም አይፈነጭበትም::

  እግዚአብሔር ሀገራችንንና ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን

 2. Anonymous April 27, 2014 at 2:31 am Reply

  ወይ መስተዳደር~
  አባቶቻችን ከጸሎታቸው፤
  …..፤ ከመንፈሳዊ ሥራቸውና
  …………ከመባረካቸው ውጭ …..
  ማለት ፤ የቀዶ ስራ/ ዶክተርነት ጉዳይን በተመለከት … ለበቁ/ ለተሻሉ የቤ/ክ ልጆቿ/ መእመኗ ቢተው ወይም ቢያማክሩ! ምናለ?!!
  ማለት፤ የኢንጅነሪንግን/ ምህንድስና »……….» …… » …………..» ……………» ምናለ?!!
  ምናለበት?፤ የፖለቲካ ጉዳይን……….»………………»……………..»….!!
  ማለት፤ የዲፕሎማሳዊ ጉዳይን …..»……………»…………..»…. !!… ምናለበት ቢመከሩ?!!!
  ማለት፤ ለዓለማዊ ጉዳይም እናውቃለን ባይባል!
  …. መንግስት ምን ያድርግ? …. (እሱም በአቅሙ ~“)
  … አቦይ ስብሓት በሚገባቸው ቋንቋ ‹አባቶች አይረቡም› ሲሉ…. ‘ሊቃውንተ አስተዳዳሪዎች’ በደነገጡ ነበር ~~~~ ወይ መተዳደር!!
  ያለ ማወቅን የሚያሳውቀን ኧእምሮ እግዚአብሔር ይስጠን!
  የሚተዳደሩ ሳይሆን የሚያስተዳድሩ አባቶችን/ መዕመንን ቤ/ክርስቲያናችን አያሳጣት!!

 3. adonay April 28, 2014 at 7:00 am Reply

  batame yamegaremawe ato tamasegan ahune ahune alamahene semalakatawe kaalekayeda besahe eyamatahe yemaselagale mekeneyatume alamahe kamaneme yatadabaka selalehona ewenate ba gata tebaka yalace selahona enge anta ena masaloche meker behon ayehoneme enge yehane yahele hezebune endate betegametute naw yeha lahezebu yalacehune nekate badambe yamalaketale yehezbe yananta kumare macawaca endalehona yamasekalu melase babakachu nabare sekatle ya patereyrku negeger kasente geza bawehala tagalatalachu wana amasegage enanta alenabarachu enda ahune enanta lay selazoru mekeneytu eko gata bagezawe selananta galatalacawe ahune sela amagagabe managare men kefate alwe aba pawelose yamemasaganubate geza mata esacawe hulune bahodacawe naber eghe dagemo endehe nacawe.baka men yedaragal,,,,,,,[,yeha asetayayate latamaseganeme m/k] yehunelge…….gata lebe yesetane amane;

 4. Anonymous April 29, 2014 at 3:04 pm Reply

  Check this website for the future to benefit from true sources. Take this message as step 1 to disclose state documentation against KK…ETV and other medias will continue,,,the next few days.
  የቀለም አብዮትን -በ ሃይማኖት የማይቻለውን መሻት – የማይደፈረውንም መድፈር
  http://aigaforum.com/articles/religion-and-color-revolution.pdf

 5. Anonymous April 30, 2014 at 3:56 am Reply

  “Check this website for the future to benefit from true sources” hah,, huuu,, hehehe….
  you make laugh.
  Aiga; stay in your kilile. Go_segna, Z_erenga.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: