በኢሕአዴግ የአዲስ አበባ አደረጃጀቶች ስለ አክራሪነት በተካሔደ ውይይት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረው ፍረጃና ክሥ ተሳታፊዎችን አስቆጣ

 • ውይይቱ ቀጣዩ የአሰላለፍ ስልትና የምት አቅጣጫ የሚወሰንበት ሊኾን ይችላል
 • ተሳታፊዎች ፍረጃዎችንና ክሦችን በመረጃና በሐሳብ የበላይነት ማጋለጥ ይገባቸዋል

AFRO TIMES TUESDAY EDITION

(አፍሮ ታይምስ፤ ቅጽ ፩ ቁጥር ፯፤ ማክሰኞ እና ረቡዕ፤ ሚያዝያ ፲፬ – ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

ገዥው ግንባር ኢሕአዴግ በሃይማኖት ይኹን በማንኛውም ሽፋን የሚደረግን የፖሊቲካ ግጭት ለመመከት በሚል በአዲስ አበባ በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ ከታቀፉ አባሎቹ ጋራ ውይይት በማካሔድ ላይ መኾኑ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ዐሥር ክፍለ ከተሞች 116 ወረዳዎች ካሉት ሰባት የግንባሩ አደረጃጀቶች ማለትም የሴቶች፣ ወጣቶች፣ መምህራን፣ የመንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች ሠራተኞች፣ የአነስተኛ ጥቃቅን ተቋማት ከእያንዳንዳቸው የተውጣጡ ስድሳ፣ ስድሳ አባላትን ያሳተፈና ሦስተኛ ሳምንቱን የያዘ ውይይት በመካሔድ ላይ ይገኛል፡፡

‹‹የሃይማኖት ተቋማትና ተከታዮች በሰላም አብሮ የመኖር ወርቃማ ተሞክሮና የማስቀጠል ፋይዳው››፣ ‹‹አዲሲቷ ኢትዮጵያና የሃይማኖት ብዝኃነት አያያዝ››፣ ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነት ከሕገ መንግሥታችን ጋራ ያለው የማይታረቅ መሠረታዊ ቅራኔና መፍትሔው›› በሚሉ ርእሶች በቀረቡ ጽሑፎች ላይ የተመሠረተው ውይይቱ ለአራት ተከታታይ ዙሮች እንደሚካሔድ ተመልክቷል፡፡

‹‹የመደማመጥ መድረክ›› የተሰኙት የመጀመሪያዎቹ ኹለት ዙሮች፣ ከቀረቡት ጽሑፎች ጋራ በተያያዘ የተዘጋጁ የመወያያ ነጥቦችን አስመልክቶ የተሳታፊዎች ግንዛቤና አቋም ምንድን ነው የሚለውን ለማወቅ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና አቋሞች በስፋት እንዲነሡና በዚህም ስልት በአባላት ውስጥ ያለውን ስሜት በቀጥታ ለማዳመጥ የታቀደበት መኾኑ ተገልጦአል፡፡

ባለፈው ሳምንት በተከናወኑት የውይይቱ ኹለተኛ ዙር መድረኰች÷ በአወያይነት በተመደቡት የወረዳ ጽ/ቤት ሓላፊዎች አማካይነት በየፈርጁ ተጠቃለው ለበላይ አመራር (ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር) ቀርበዋል ለተባሉት የተሳታፊዎች ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና አቋሞች የግንባሩና የመንግሥት አቋሞች፣ መረጃዎችና ዕቅዶች በምላሽነት እንደተሰጡ ታውቋል፡፡

በቀጣይ በሚካሔዱት ኹለት ዙሮች፣ በተናጠል ሲወያዩ የቆዩት የሰባቱ አደረጃጀቶች ስድሳ፣ ስድሳ ተሳታፊዎች በጋራ በመገናኘት በሥልጠና አመለካከታቸውንና ግንዛቤያቸውን ያስተካክሉበታል ተብሎ የሚጠበቅ የማጥራትና የመግባባት መድረክ እንደሚኾን ተጠቁሟል፡፡

በዚኽ መልኩ የሠለጠኑት የየወረዳው 420 የግንባሩ ‹‹የልማትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ አደረጃጀቶች›› በቀጣይ በተመሳሳይ አጀንዳ ላይ እንደሚጠራ በሚጠበቀው የብዙኃን መድረክ ከሕዝቡ ጋራ ተቀላቅለው በተለያዩ ስልቶች በመሳተፍ መድረኰቹ በታቀደው አቅጣጫ እንዲመሩና ወደተፈለገው መደምደሚያ እንዲደርሱ በማድረግ ድርጅታዊ ተልእኮዎቻቸውንና ስምሪቶቻቸውን እንደሚወጡ ተመልክቷል፡፡

‹‹ጠባብነት፣ ትምክህትና አክራሪነት›› የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከቶች እንደኾኑና ከሕዝብ አቅም ግንባታ አኳያ ዋናው ርብርቡ በእነዚህ ላይ እንደኾነ መንግሥታዊ ጽሑፎች ይገልጻሉ፡፡ ሙስሊሙ ከጠባብነት፣ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ከትምክህት ርእዮት ጋራ የመዳበል ባሕርያት እንደሚታይባቸው የሚገልጹት የመንግሥት ሰነዶች÷ በእኒኽ ባሕርያት በተቃኙ ‹‹ሃይማኖታዊ ርእዮቶች›› ላይ የተመሠረተ ሽብርተኝነትና ሃይማኖታዊ ግጭት ሊፈጠር እንደሚችል ታሳቢ አድርጎ ርእዮቶቹን ‹‹በትምህርትና ሥልጠና፣ በዴሞክራሲያዊ አኳኋን›› መታገልና የለዘብተኝነትና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር የተጠናከረ ሥራ መሠራት እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡

mahibere kidusanየመንግሥት የመልካም አስተዳደርና ልማት ጉዳዮች ተያይዘው በተነሡባቸው ባለፉት ኹለት የውይይት ዙሮች አንዳንድ የመድረክ አወያዮች ለስብሰባው አካሔድ ተቀምጧል ከተባለው ድርጅታዊና መንግሥታዊ አቋምና አቅጣጫ በተፃራሪ በኦርቶዶክሳዊው ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያሰሙት ገለጻ፣ የውንጅላና የፍረጃ መንፈስ የተጠናወተው ከመኾኑም በላይ ያልተፈለገ አደገኛ ውጤት ሊያስከትልም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

በየካ፣ በቦሌ እና በልደታ ክፍላተ ከተማ የተለያዩ ወረዳዎች የተሳተፉ የአፍሮ ታይምስ ምንጮች ስምና ሓላፊነታቸውን ለይተው የጠቀሷቸው አወያዮች÷ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን መዋቅሩን አጥንቶ ፋይናንሱን እኔ ካልያዝሁትና ካልተቆጣጠርሁት ብሏል፤ ስለዚህ አክራሪ ነው››፤ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሰጠችው ደንብ ውጭ ይንቀሳቀሳል፤ ስለዚህ አክራሪ ነው››፤ ‹‹መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ለመኾኑ አስገራሚ አስገራሚ መረጃዎች አሉት›› የሚሉና የመሳሰሉ ክሦችንና ፍረጃዎችን መሰንዘራቸውን አስረድተዋል፡፡

የት/ቤት(መምህራን) አደረጃጀት አባላት እንዲሁም የስብሰባው ተሳታፊ ካህናት በበኩላቸው፣ በቅርበት ጠንቅቀው የሚያውቋቸው በርካታ የማኅበሩ አባላት መኖራቸውንና ፍረጃውና ክሡ በማስረጃ መደገፍ እንዳለበት አለበለዚያ ማኅበሩን ይኹን አባላቱን ይገልጻቸዋል ለማለት እንደሚያዳግት በመጥቀስ ተቃውመዋል፡፡

አወያዮቹ ማስረጃ እንዲያቀርቡና አነጋገራቸውን እንዲያርሙ በጥብቅ ያስጠነቀቁት ተሳታፊዎቹ፣ ውይይቱ በዚህ መንፈስ የሚካሔድ ከኾነ በተሳትፎ ለመቀጠል እንደሚቸገሩ በማሳወቅ ስብሰባውን ጥለው ለመውጣት ተነሣስተው እንደነበርና አወያዩ አካል መድረኩን መሪዎች በሌሎች በመተካት አስቸኳይ እርማት በማደረጉ በተሳትፏቸው ለመቀጠል እንደቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ሌሎች የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያኒቱ አጽድቃ በሰጠችው መተዳደርያ ደንብ መሠረት እንደሚንቀሳቀስና የፈጸማቸውን ዐበይት ማኅበራዊና የልማት ተግባራት፣ የአገልግሎቱ ዕሴቶችና ትሩፋቶች ያስገኙትን አገራዊ ጠቀሜታዎች በመዘርዘር አስረድተዋል፤ በተሰነዘሩት ፍረጃዎችና ክሦች አንጻርም እውነታውን በመግለጽ ፍረጃውና ክሡ ሕገ መንግሥታዊውን ሃይማኖት ነክ ድንጋጌ የሚጥስ ጣልቃ ገብነት ነው በሚል ኮንነውታል፤ በሕግ አውጭነት ሉዓላዊ ሥልጣኗ አገልግሎቱን የፈቀደችለት ቤተ ክርስቲያ እንኳ ያላለችውን ሕዝብን ሰብስቦ ማኅበሩን በአክራሪነት መወንጀል የማኅበሩን ገጽታ በማጠልሸት ከሕዝቡ ለመነጠልና ሕዝቡን በማኅበሩ ላይ ለማዝመት ተይዟል ብለው የሚጠረጥሩት ዘመቻ አካል ነው ብለው እንደሚያዩትም አመልክተዋል፡፡

‹‹ከመቻቻል በላይ በፍቅር እየኖርን ነው፤ ከሕጋዊነትም በላይ በፍቅር እየኖርን ነው፤›› በማለት በመድረኩ ‹መቻቻል› እና ‹የሕግ የበላይነትን ማስከበር› በሚል ከተገለጸው ባሻገር ሕዝቡ በሰላም አብሮ የመኖር ዕሴቶቹን ጠብቆ በፍቅርና በመገናዘብ እየኖረ መኾኑን ይልቁንም በዚህ ረገድ ከአክራሪነትና ጽንፈኝነት ጋራ በተያያዘ የሚሰጡ ማብራሪያዎች አንዱን የድህነትና ኋላቀርነት ሌላውን የሥልጡንነት መለዮ የሚያስመስል ትርጉም እንዳያሰጡ ማስተዋልና ጥንቃቄ ሊደረግባቸው እንደሚገባ ተመክሯል፡፡

በተያያዘም ‹‹ታሪካችን ረዥም ነው የሚለውን ትምክህት መዋጋት›› በሚል ከመጀመሪያው ምእት ዓመት (34 ዓ.ም.) አንሥቶ የሚቆጠረው የቤተ ክርስቲያኒቱ ብሔራዊ ታሪክ በቅ/ሲኖዶስ አባላት ሳይቀር የመንግሥት ሓላፊዎች የተተቹበትና እንዲታረሙም የተጠየቁበት ኾኖ ሳለ ለውይይት በቀረቡት ጽሑፎች ውስጥ በአግባቡ አለመስፈሩ የመጽሐፍ ቅዱሱን እውነታ መቆነጻጸልና ጥንታዊነቷን የማደብዘዝ ውጥን እንዳለ የሚጠቁም ነው ተብሏል፡፡

እስልምና በሰላም ገብቶ እንዲስፋፋ ምክንያት ኾነዋል የተባሉትን ንጉሥ አርማህ ‹‹በወቅቱ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ›› ከማለት በቀር ስማቸውንና ክርስቲያናዊነታቸውን በመግደፍ የቀድሞዎቹ ነገሥታት በአጠቃላይ ብዝኃነትን እንደ አደጋ የሚመለከቱና የአንድ ሃይማኖት ፖሊሲ የሚያራምዱ ነበሩ ማለትም በአነስተኛው አነጋገር ቅንነት የጎደለው እንደኾነ ተሳታፊዎቹ ለአፍሮ ታይምስ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የመድረኩ አወያዮች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ለሰነዘሯቸው ክሦችና ፍረጃዎች ቅሬታ አቅራቢ ተሳታፊዎችን በግልጽ ይቅርታ መጠየቃቸው ተገልጦአል፡፡ ፍረጃውና ክሡ ለውይይቱ ከተሰጣቸው ተሰብሳቢውን የማዳመጥ አቅጣጫ አልፈው የተናገሩት መኾኑን በማመን መሳሳታቸውን የገለጹትም ‹‹ማንንም እንዳትፈርጁ፣ ‘specific’ እንዳታደርጉ ተብለናል፤ የመላእክት ስብስብ አይደለንም፤ ሰዎች ነንና እንሳሳታለን›› በማለት ነበር፡፡

ይኹንና ይህ ነው የተባለ ማስረጃ ባይጠቅሱም መንግሥት በሕግ የሚጠይቃቸው አንዳንድ ግለሰቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ ሳይጠቁሙ አላለፉም፤ መንግሥት በልዩነትና ግጭት ወቅት ሰላምና ጸጥታን ለማስጠበቅ በሚል ካልኾነ በቀር በሃይማኖት ጣልቃ እንደመግባት ተደርጎ የቀረበውን አስተያየትም አልተቀበሉትም፡፡

የውይይቱ ዓላማ ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ከአባሉና ከአጠቃላይ ሕዝቡ አቋምና ግንዛቤ በመነሣት በትምክህትና ጠባብነት የሃይማኖት አክራሪነት ርእዮት አራማጅነት በሚፈርጃቸው ወገኖች ላይ በቀጣይ የሚይዘውን አሰላለፍና የምት አቅጣጫ ለመወሰንና ይኹንታ ለማግኘት የሚጠቅምበት ሊኾን እንደሚችል ብዙዎች ያምናሉ፡፡

በቀጣዮቹ ኹለት ውይይቶችና ከዚያም በኋላ በታቀዱ የሕዝብ መድረኮች የስብሰባ ጥሪ የተደረገላቸው ኹሉ እስከ አኹን እንደታየው መዘናጋት ሳይሆን በስብሰባ እየተገኙ አካሔዱን በሐሳብና የመረጃ የበላይነት ማጋለጥና ተገቢው አቋም ላይ እንዲደረስ መትጋት እንደሚገባቸው ያሳስባሉ፡፡

Advertisements

21 thoughts on “በኢሕአዴግ የአዲስ አበባ አደረጃጀቶች ስለ አክራሪነት በተካሔደ ውይይት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረው ፍረጃና ክሥ ተሳታፊዎችን አስቆጣ

 1. MINILIK SALSAWI April 23, 2014 at 10:03 am Reply

  Reblogged this on MINILIK SALSAWI (ምንሊክ ሳልሳዊ) and commented:
  በኢሕአዴግ የአዲስ አበባ አደረጃጀቶች ስለ አክራሪነት በተካሔደ ውይይት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረው ፍረጃና ክሥ ተሳታፊዎችን አስቆጣ

 2. በአማን ነጸረ April 23, 2014 at 10:10 am Reply

  ህማም እንተ በአማን!!
  ስለማኅበረቅዱሳን ጉድለቶች በጻፍኩ ቁጥር ህሊናየ በነውጥ ውስጥ እንደሚወድቅ አልደብቃችሁም፡፡ስለ 3 ነገር፡(1ኛ)ቅንና ትጉሃን መስራቾቹ ባለፉት 22 አመታት ያበረከቱትን ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ የመረዳት እድል ስላለኝ፡፡የእነ ብርሃኑ ጎበናን ዓምደ ሃይማኖት፣የነሕብረት የሺጥላን ህይወተ ወራዙት፣የነዳንኤል ክብረትን ከኦርቶዶክስ መልስ አላት እስከ ሰሞኑ ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ አራቱ ኃያላን ሳሰስብ፣የሐመርን፣የስምዐ ጽድቅን፣የሐመረተዋሕዶ ጆርናሎችን እና ሌሎች የማኅበሩ የህትመት ውጤቶችን ስከታተል እንደመኖሬ ማኅበሩን ስወቅስ እነሱ እየመጡብኝ እሰቀቃለሁ፡፡(2ኛ)የዋሃን እና የቤቱ ቅናት የሚበላቸው ነበልባላዊ የግቢ ጉባኤ ኮርሰኞችን እያየሁ ስለማኅበሩ ስናገር እጨነቃለሁ፡፡(3ኛ)የማኅበሩ አመራር በትርፍ ጊዜ ለትሩፋት የሚሰሩ ብዙ ቅን ኦርቶዶክሳውያን እንዳሉበት ሳስብ እነሱን ደባልቄ እንዳልሰልቅ እየፈራሁ እታወካለሁ፡፡
  እናም ያለኝ አማራጭ 2 መጥፎ አማራጭ ነበር/ነው፡፡አንድም ከላይ የተጠቀሱትን ሰዎች በማሰብ አሁን አሁን በማኅበሩ ላይ የማስተውልን ክፍተት ሰዎቹ እንደእኛው ሰዎች እንጅ የቅዱሳን ስብስብ ስላልሆኑ ቢሳሳቱም ከስህተታቸው መልካም ግብራቸው ስለሚበልጥ ብየ እንደአብዛኛው ሰው እንዳላዩ ማለፍ፡፡ይሄ ካልሆነም የምናገረው ነገር ከላይ በጠቀስኳቸው ከማኅበሩ አልፈው ለሀገርም ለሃይማኖታችንም መትረፍ የሚችሉ ሰዎችን ስሜት እንደምጎዳ እያወቅሁት ስለ አማናዊቷ እና እምላእለ ኩሉ ስለምንላት ቤ/ክ ዘላቂ ጥቅም እንደግለሰብ ይበጃል ብየ የማምንበትን በተለይም በአንጻረ ማኅበረቅዱሳን የሚሰማኝን ሁሉ በግልጽ መናገር፡፡ምርጫየ 2ኛው አሳማሚ መንገድ ነበር፡፡አሁንም ነው፡፡እስኪ ስለመፍትሄው እናውራ!!
  ተምኔታት 10ቱ እንተ በአማን(በእንተ ማኅበረቅዱሳን)
  1. ማኅበረቅዱሳን በመምሪያ ደረጃ ተዋቅሮ እንደ ሌሎቹ 18 መምሪያዎች ሁሉ እሱም በ19ኛነት ተደምሮ ተጠሪነቱ በቋሚነት ለጠቅላይ ቤተክህነት ቢሆን፣
  2. የየእለት ተግባራቱን የሚያስተባብር በቤተክህነት ፔሮል ተቀጣሪ የሆነ መሪ ቢኖረው፣
  3. ስልጣንና ተግባሩ ዝርው እየመሰለ ስለሆነ የሌሎችን መምሪያዎች ስልጣንና ተግባር ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ተሰፍሮና ተቆጥሮ ቢደነገግለት፣
  4. የማኅበሩ አስተባባሪነት እንዳለ ሆኖ ግቢ ጉባኤ ተጠሪነቱ ባለበት አካባቢ ላሉ ሀገረስብከቶች ቢሆን፣
  5. ቦርዱ ተዋጽኦው የቤ/ክህነት አመራሮችንና ሊቃውንትን ቢያካትት እና ምርጫው በጠ/ቤ/ክህነት ወይም በቋሚ ሲኖዶስ እንዲጸድቅ ቢደረግ፣
  6. ማኅበሩ ፐርሰንት እንዲከፍልና የቤ/ክህነት ደረሰኞችን እንዲጠቀም ቢደረግ፣
  7. ሁለንተናዊ የአባላት ስነምግባር ቢቀረጽ፣በተለይ ሀገር በቀል ኦርቶዶክሳዊ እሴቶችን ማጎልበትን፣አባቶችን ማክበርን፣ህዝባዊ ውግዘቶችን ማስወገድን፣ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን፣ሃይማኖትንና ማኅበርን አለማምታታትን የሚያስገነዝብ የአባለት ስነምግባር መመሪያ ቢደነገግ፣
  8. የማኅበሩ ልሳናት የቤ/ክህነቱን አቋም ባገናዘበ መልኩ እንዲንቀሳቀሱ መርሆዎች ቢቀመጡ፣
  9. በማኅበሩም ሆነ በአባላቱ ለሚፈጸሙ ግድፈቶች ያለው ኃላፊነትና አስተዳደራዊ እርምጃ በዝርዝር እና በደረጃ ቢቀመጥ፣በእርምጃው ቅሬታ ካለም እስከ ሲኖዶስ ሊደርስ የሚችል የይግባኝ መብት ቢዘረጋ፣
  10. መንግስትን ጨምሮ ከማንኛውም ውጫዊ አካል በማኅበሩ ላይ የሚሰነዘሩ ክሶችንም ሆነ ፍረጃዎችን ቤተክህነቱ እንደ ተቋም በማንኛውም መልኩ የመከላከል ግዴታ እንዳለበት ቢደነገግ፣በተመሳሳይ መልኩ ማኅበሩ ስለማንኛውም ውጫዊ አካል ጠ/ቤተክህነትን ሳያሳውቅ መግለጫ የመስጠትም ሆነ ግንኙነት የመመስረት መብት እንደሌለው ቢደነገግ ምኞቴ ነው፡፡
  ከላይ ያነሳሁዋቸው ነጥቦች አሁን ባለው የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብም ሆነ በቃለ ዐዋዲው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ካሉ ወደ መሬት ወርደው እንያቸው፡፡ከሌሉ ቢካተቱ እመኛለሁ፡፡ይህ የአንድ ኦርቶዶክሳዊ ምኞት ነው፡፡ ምኞት ደግሞ አይከለከልም፡፡

  • Mamo April 23, 2014 at 5:16 pm Reply

   አስመሳይ መናፍቅ!!!
   ለሚያይህ አዛኝ ኦረቶዶክሳዊ ትመስላለህ፤ አንተን በሎ ባለምኞት

   • Annonyname April 28, 2014 at 7:41 am

    ‹‹ አረ በፍቅር በስመ አብ ይቅር፡፡ ›› አለ ሰይጣን ፡፡ በአማን ኢነፀርከ አንተ ውዕቱ ወልደ ማኅጎሊ/ወልደ ኃጎል/ ወግድ!!!! አንተ ሰይጣን!!!!! ያልከው ሀሳብ የአንተ መናፍቁና የግብረ አበሮችህ ነውና እስከ ሀሳባችሁ ጥፉ፤ ይሆን መሰለህ?

  • Anonymous April 24, 2014 at 1:02 am Reply

   ውሻ መናፍቅ አንተ ብሎ መካሪ በደንብ ስለምናውቅህ እዛው አዳራሽህ ብትጨፍር ይሻልሃል

  • ማሙሽ April 24, 2014 at 8:45 am Reply

   በአማን ነጸረ ምኞትህ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን………..
   ማህበረ ቅዱሳን ማለት የሜዳ አህያ እኮ ነው፡፡……….እንደ ልቡ መፈንጨት የለመደን የሜዳ አህያ እጅ እግሩን አስረህ ለኢህአዴግ ልትሸጠው/በነጻ ልትሰጠው ማሰብህ ይገርማል፡፡
   ለማንኛውም እኔም እንደ አንተ የማህበሩን መፍረስ አልደግፍም፡፡ ነገር ግን ማህበሩ ስረዓት መያዝ አለበት፡፡
   የማህበረ ቅዱሳን ትልቁ ስህተት ቅዱሳን አባቶቻችንን ሌቦች ሙሰኞች እያለ መስደቡ ነው፤ አባቱን እየሰደበ የሚያድግ ልጅ መጨረሻው ጥፋት ወይም ውድቀት ነው፡፡
   እኛ እስከምናውቀው አባቶቻችን ሌቦች አይደሉም ምክንያቱም፡- “……..የእስራኤል ህዝብ ለእኔ የሚያመጡትን አስራት ሁሉ የሌዋውያን ድርሻ እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ፤ ይህም እኔ በምመለክበት ድንኳን ውስጥ ለሚሰጡት አገልግሎት ደመወዝ ይሆንላቸዋል፡፡” ዘሌዋውያን 18፡21
   ስለዚህ የማህበረ ቅዱሳን አባላት አባቶቻችንን አትስደቡ፤…..እምቢ ካላችሁ ግን ትጠፋላችሁ
   በአማን ነጸረ ማህበሩ ስርዓት እስኪይዝ ድረስ ማረም፣ መቃወም የሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ድርሻ ነው፡፡ሀሳብ መስጠትህን ቀጥልበት፡፡

 3. Anonymous April 23, 2014 at 5:05 pm Reply

  ወያኔ አሁን ገና ልቡ አበጠ

 4. Anonymous April 24, 2014 at 4:10 am Reply

  ሐሳብህ አይነፋማ በለምድ የተሸፈነ መርዝ አለበት ለማንኛውም ለመልካም አስተያየትህ እግዚአብሔር ይስጥህ

 5. ሸዋ April 24, 2014 at 6:43 am Reply

  በቅዳሴው በወንጌሉ የሚነግሩን አንድ አምላክ እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ እግዚኦ ማሀረነ ክርስቶስ እያልክ ለምን የዝችን ሀገር ጥፋት ትመኛለህ

 6. Anonymous April 24, 2014 at 8:44 pm Reply

  ማህበረ ቅዱሳን አባቶችን ይሳደባል የምትል አንተማነህ? በእውኑ ያሳደገችህን ቤ/ያን ትነክሳለህ?

 7. Senait April 25, 2014 at 4:11 am Reply

  በአማን ነጸረ…This guys idea is divisive and poisonous, appreciating old leaders of MK and condemning the current leaders which is well known TPLF/EPRDF strategy, and generally there is enough reason to say በለምድ የተሸፈነ መርዝ….We need to take care of this guy, i guess he is a Menafik sponsored and highly available on different social medias.

  • በአማን ነጸረ April 25, 2014 at 10:07 am Reply

   1. Sorry, sister Senait!!U r attacking me, personally, not my idea!!Even, i can say, u didn’t read what i wrote!!B/c, i also gave a credit 2 z current leaders saying(3ኛ)የማኅበሩ አመራር በትርፍ ጊዜ ለትሩፋት የሚሰሩ ብዙ ቅን ኦርቶዶክሳውያን እንዳሉበት ሳስብ እነሱን ደባልቄ እንዳልሰልቅ እየፈራሁ እታወካለሁ፡፡
   2. While speaking or writing about my religion i am not obliged to follow any political strategy, i don’t need sponsorship of MENAFIK, even i have no duty 2 appreciate all approaches of MK!! Being baptized and get grown in mother EOTC is more than enough 2 forward my idea concerning my religion!!U and ur fellows r not entitled 2 take or give my orthodox Christian identity!!I hope; ur problem shall b solved if my wish of (7)ሁለንተናዊ የአባላት ስነምግባር ቢቀረጽ፣በተለይ ሀገር በቀል ኦርቶዶክሳዊ እሴቶችን ማጎልበትን፣አባቶችን ማክበርን፣ህዝባዊ ውግዘቶችን ማስወገድን፣ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን፣ሃይማኖትንና ማኅበርን አለማምታታትን የሚያስገነዝብ የአባለት ስነምግባር መመሪያ ቢደነገግ is fulfilled!!Any way,being with or against MK ‘s some approaches is not a parameter 2 b named as an orthodox!!
   3. I appreciate u 2 disclose z reasons that convinced u 4 labeling me as a በለምድ የተሸፈነ መርዝ….!! If u can’t, i will consider u as a character assassin and one of blind fanatic followers of MK, who make EOTC and MK as synonymous and interchangeable despite z latter is a subset of z former!!!
   4. YES!! i am available on d/t social medias!!So what??

   • Anonymous April 25, 2014 at 11:43 pm

    አንተ አሰመሳይ መናፈቅ ወግድ ውሻ

 8. Anonymous April 25, 2014 at 1:41 pm Reply

  mengest arfeh betekemet yeshalehal..

 9. Anonymous April 25, 2014 at 7:42 pm Reply

  Guys, TEREGAGU! Hulum Ende Egziabher Fekad Hunual Yihonalim…..!!!

  I really appreciate በአማን ነጸረ idea. Indeed, you know MK and the mother church. The major problems of MK blind fanatic followers are they hastily generalize everything. They don’t appreciate different ideas that comes from non- MK followers. As you clearly indicated “Being baptized and get grown in mother EOTC is more than enough 2 forward any idea concerning EOTC”.

  MK and its blind fanatic followers are not entitled to give and /or take the identity of orthodox Christians!!I Anyway, “THROUGH HIM ALL THINGS WERE MADE. BUT, WITHOUT HIM NOTHING WAS MADE” JOHN 1:3

  Neither the government nor the state have this strong power to destroy MK rather MK’s unspiritual way of doing business (mixing of politics with orthodox Christianity) diminish the association. Moreover, the association acts as an umbrella and considering the church as a subset of the association. This really the most bad leadership quality. Any way, ” jib kehede wisha chohe” endilu abew…MK stands now in the red line of the state and the church. We want to save the church by eradicating this anti-gospel evil association.

  Thanks በአማን for your your genuine and timely idea for the association (i.e., የአባላት ስነምግባር ቢቀረጽ፣አባቶችን ማክበርን፣ህዝባዊ ውግዘቶችን ማስወገድን፣ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን፣ሃይማኖትንና ማኅበርን አለማምታታትን የሚያስገነዝብ የአባለት ስነምግባር መመሪያ ቢደነገግ ). However, MK is not ready to take any idea whether it comes from በአማን or from anegel of God! TRULY, SPEAKING ALL ARE DONE AND HERE AFTER NOBODY GONNA PROTECT MK ( PATHRIARCH. ARCHBISHOP, EDUCATED SCHOLARS..BLA BLA…). WE WILL SEE WHO WILL BE IN JEL AND WE WILL SEE “HOW MK HIDDENLY AFFECT THE CHURCH AND STATE WHILE TH GOVRNMENT DISCLOSES IT IN MEDIA”,

  SELIFU KELAYNEW !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

 10. TD April 26, 2014 at 5:17 am Reply

  በአማን ነጸረ ምኞትህ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ….
  i. ይህ ሃሳብህ መርዝ የተሞላበት የእባብ ተንኮል ነው። ተቀጣሪ መሪ አያስፈልገውም። የበጎ ፈቃድ አገልግሎት (like community service) ነገር ግን ለጽድቅ የተቋቋመ ማኅበር ስለሆነ በቤተክህነት ፔሮል ተቀጣሪ የሆነ መሪ አያስፈልገውም። ስለዚህ አሁን አንተ ያልከው ዘዴ ማኅበሩን ለማቀጨጭና እንደፈለጋችሁት ለመዘወር ያሰብከው ዘዴ ነውና እርሳው።
  ii. ስልጣንና ተግባር ተሰፍሮና ተቆጥሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ተደንግጎለታል፡ ደግሞም ሰው ከሚጠበቅበት በላይ ቢሰራ ቢወደስ እንጂ ሊከሰስ አይገባውም አንተ ግን እንደ አይሁድ ለምን በሰንበት እውራንን አበራችሁ እያልክ ነው
  iii. የማኅበሩ አስተባባሪነት እንዳለ ሆኖ ግቢ ጉባኤ ተጠሪነቱ ባለበት አካባቢ ላሉ ሀገረስብከቶች ቢሆን ያልከው ደግሞ አሰራሩ ወጥነት እንዳይኖረውና የማ/ቅ ምንጭ የሆነውን ግቢ ጉባኤ መሰረቱን ለመናድ ያሰብክ ትመስላለህ። እንዲያው በከንቱ ትደክማለህ እንጂ የማ/ቅ ዓላማ ከምዕመናን ውስጥ አየጠፋም
  iv. ቦርዱ ተዋጽኦው የቤ/ክህነት አመራሮችንና ሊቃውንትን ቢያካትት እና ምርጫው በጠ/ቤ/ክህነት ወይም በቋሚ ሲኖዶስ እንዲጸድቅ ቢደረግ ላልከው ደግሞ አሁንም ቢሆን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽንሰ ሃሳብን አልተረዳህም (ለነገሩ አንተ ትቀበለኛለህ ብዬ ሳይሆን ያንተን መርዝ ያለበት ሃሳብ አይተው እንዳይሳሳቱ መልስ ለመስጠት ነው)።ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ለተጨማሪ ትሩፋት (በአጥቢያው ወይንም በቤተ ክህነት ከተመደበበት በተጨማሪ)የማ/ቅዱሳንን ዓላማ ከደገፈ ውስጥ ገብቶ ማገልገል ይችላል። ከዚያ ውጭ ግን ማኅበሩ ዘወትር ልቃውንትን እያማከረ ይሰራል፤ ይታዘዛልም።
  v. ማኅበሩ ፐርሰንት እንዲከፍልና የቤ/ክህነት ደረሰኞችን እንዲጠቀም ቢደረግ ላልከው ደግሞ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደዚህ ዓይነት የፐርሰንት ክፈል ነገር ተሰምቶ አይታወቅም። እያንዳንዱ አባል በአጥቢያው የሚከፍለው አስራትና አገልግሎት እንዳለ አትርሳ። ከዚያ ውጭ አባላት በማ/ቅ ስም የሚያደርጉት አገልግሎት ከሚጠበቀው በላይ ተጨማሪ የትሩፋት ሥራ ነው።

  vi. ማኅበሩ በአጠቃላይ ዘወትር የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ነው የሚያንጸባርቀው፤ ቤተ ክሀነት ውስጥ ካሉ ተሃድሶዎች ሳይሆን ከአባቶች ጋርም አብሮ ይሰራል፤ እሰራም ነው።

  • በአማን ነጸረ April 28, 2014 at 1:52 pm Reply

   አመሰግናለሁ ወንድሜ TD!!ሌሎች ጩዋሂዎች ምኞቴ ከቅ/መጻህፍትም ሆነ ከቃለ ዓዋዲው ስለመጣረሱ ካስረዳችሁኝ ወይም ከመናፍቃን መርሆዎች ጋር የሚገናኝ ስለመሆኑ ካለመከታችሁኝ ንስሐ እገባለሁ፡፡በተረፈ “መናፍቅ የሚለውን ቃል ተሞልታችሁ እንደ ውሃ ወፍጮ ስለተንደቀደቃችሁ” በአማን ነጸረ አንገት ይደፋል ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል፡፡በጭፍኖች መሰደብ አዲሳችን አይደለም፡፡እንኳን እኔ ታናሹ፡ ፓትርያርኩ፣ጳጳሳቱ፣የ2 ጉባኤው ባለቤት ሊቁ ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ፣ሌሎችም ስልጣነ ክህነት ያላቸው የቤ/ክ ሰዎች ብዙ ተብለዋል፡፡ስለዚህ ጩኸታችሁን “ወይገብዕ ጻማሁ ዲበ ድማሁ” ብየ አልፈዋለሁ፡፡እንደ በለዓም ሀብተ መርገም ተሰጠን ካላችሁም ፍጻሜውን እናያለን፡፡ወደ ወንድሜ ነጥቦች……
   ኑ!!አንቀጽ በአንቀጽ እንዋቀስ!!
   ሀ. ማኅበረቅዱሳን ፐርሰንት መክፈል አለበት የምልባቸው ምክንያቶች፡
   (1)በቃለ ዓዋዲው አንቀጽ 56(2)(ሰ) መሰረት የሰ/ት/ቤት ገቢ ለአጥቢያው ይውላል፡፡ማኅበሩ በአጥቢያ ደረጃ ሳይሆን በጠ/ቤ/ክህነት ደረጃ ከመዋቀሩ በቀር 2ቱም የፈቃድ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ስለዚህ ከገቢው 20% የማይከፍልበት ምክንያት የለም፡፡(2) ማኅበሩ በቃለዓዋዲው አንቀጽ 12(12) ማምለጥ ከፈለገም የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን ከንግዱ ይለይና ቢያንስ ከንግዱ ፐርሰንት ይክፈል፡፡በዚያውም ቤ/ክህነቱ ስለማኅበሩ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ትክክለኛ መረጃ ይኖረዋል፡፡ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ በቤ/ክ ስም እንዳይንቀሳቀስም ይረዳል፡፡(3)በሌላም በኩል ፐርሰንት መክፈልን የታዛዥነት ምልክት አድርጌ እወስደዋለሁ፡፡(4)ነገ ሌሎች ማኅበራትም በበጎ አድራጎት ስም እንደፈለጉ ቤ/ክንን ከለላ አድርገው ቤቱን የሸቀጥ ቤት እንዳያደርጉት ይረዳል፡፡
   ለ. ማኅበሩ የቤ/ክህነት ደረሰኞችን ይጠቀም የምልባቸው ምክንያቶች፡
   (1)ቃለ ዓዋዲው በግልጽ በአንቀጽ 56(4)(5)ከቤ/ክ ውጭ የሆነ ደረሰኝን መጠቀም ስለሚከለክል፣(2)በቤ/ክህነት የሚታተሙ ደረሰኞችን ጉድለት ከአሰራሩ በመሸሽ ሳይሆን ራሳቸውን እየተጠቀሙ ነገር ግን እንዲሻሻሉ በውስጥ ሆኖ ግፊት ማድረግን ስለምመርጥ፣(3)ሌብነትን ደረሰኝ በመቀየር ብቻ መቋቋም ይቻላል ብየ እንዳልደመድም ካሽ ሬጅስተር እያለም VAT የሚያጭበረብሩ ብዙ ነጋዴዎች ስለመኖራቸው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ምስክር ስለሆነች ደረሰኝን እያመሀኙ አጉል ከማእከላዊነት ሽሽት አሳማኝ አይሆንልኝም፡፡
   ሐ. የቦርዱን ተዋጽኦ በሚመለከት
   (1)የቤ/ክ አመራሮችንና ሊቃውንትን ተሳትፎ በማግለል በእንግሊዝኛ ተናጋሪዎች የተሞላ ቦርድ ሙሉ ነው ለማለት ይከብደኛል፡፡(2)እንደ ቤ/ክህነትም በዚህ መልኩ ለተዋቀረ ቦርድ ውሳኔዎች ኃላፊነት ለመውሰድ አስቸጋሪ ነው ብየ አስባለሁ፡፡ቤ/ክህነት ከመንግስት ጋር ስለማኅበሩ አፉን ሞልቶ እንዳይሙዋገት የሚያደርገው አንዱ ም/ትም የቦርዱ ቅርብ መስሎ ሩቅ መሆን ነው፡፡(3)የቋሚ ሲኖዶሱ ወይም የጠ/ቤ/ክህነቱ ቦርዱን ተቀብሎ ማጽደቅ አንድም ቡራኬ ነው፣አንድም መተማመንን ይፈጥራል፣አንድም አሰራሩ በኢኦተቤክ ተራድኦ ኮሚሽንም ስለሚሰራበት አዲስ አይደለም፡፡
   መ. በቤ/ክህነት ፔሮል የተቀጠረ የማኅበሩ መሪ ይኑር የምለው
   (1)የተራድኦ ኮሚሽንን ተሞክሮ ተመልክቼ ነው፡፡(2)መሪው የቤ/ክህነት ተቀጣሪ ከሆነ በጠ/ቤ/ክህነት የአስተዳደር ጉባኤ ውስጥ ማኅበሩን ወክሎ የመቀመጥ መብት ስለሚያገኝ የጠ/ቤ/ክነቱንና የማኅበሩን ግንኙነት ለማቀላጠፍ ይረዳል ብየ አምናለሁ፡፡
   ሠ. የማኅበሩ ሚዲያዎች ከቤ/ክህነት ይናበቡ የምለው የተግባር ችግር ስለማይ ነው፡፡ማሳያ ልጥቀስ ያውም በ6 ወራት ውስጥ ብቻ ያየኋቸውን፡
   የአብነት መምህራን ጉባኤ የተጠራበት መንገድና የቤ/ክህነቱ የእግድና የይቅርታ ጠይቁ ትእዛዝ፣የማኅበሩ ሲኖዶስን የቀደሙ ውግዘቶችና የእነበጋሻው የስብከት ፈቃድ ማግኘት ፣የአ/አ/ሀ/ስብከት የመዋቅር ጥናትና የማኅበሩ ልሳናት ውጥንቅጥ አካሄድ ተደማምረው የማኅበሩን ከቤ/ክህነቱ መናበብ ሳይሆን የማኅበሩን መቅለብለብ ነው የሚነግሩኝ፡፡ “አፍ ይጼውኦ ለሞት” ነውና ያ ከመሆኑ በፊት ለአፉ ጠባቂ ማኖር ካልቻለ በቤ/ክህነቱ በኩል ሊቀመጥለት ግድ ነው፡፡የሚዲያ መርህ ይቀመጥለት!!
   ረ. ስልጣንና ኃላፊነቱ ተቆጥሮና ተመትሮ ይሰጠው ስል
   (1)ስራን ቆጥሮና ተካፍሎ መስራት መጽሐፋዊም ነው፣ስልጣኔም ነው፡፡በቤ/ክ ስርዐት ቅኔ መቀኘት የቻለ ሁሉ መወድስ አያደርገም፣አቋቋም የተማረ ሁሉ አንገርጋሪ አይመራም፣ድጓ ያወቀ ሁሉ እስመለዐለም አይቃኝም፣መቀደስ ስለ ቻለ ብቻ መቅደስ ገብቶ እንቡ ማለት የለም፡፡ሁሉም ስርዓቱን፣ተራና ተርታውን ጠብቆ ነው የሚደረገው፡፡ያውም የአጋፋሪው፣የቄሰ ገበዙና ሊቀ ዲያቆኑ፣የአስተዳዳሪውና የመምህሩ ፈቃድ እየተጠየቀ፡፡(2)በዐለማውያኑም ቢሆን በእጓለማውታን ዙሪያ እሰራለሁ ያለ በጎ አድራጎት ድርጅት የሚመለከተውን አካል ሳያስፈቅድ ስለቻለ ብቻ በአንዴ ተገልብጦ ቅርስ ተንከባካቢ መሆን አይችልም፡፡በጎ ፈቃደኝነትም የራሱ አካሄድ እንዳለው እናውቃለን፡፡ለነገሩ በኢኦተቤክ ስር የሚል መጠሪያን ከላይ ደርቦ ለመብትና ግዴታ ሲሆን ዐለማዊውን የበጎ ፈቃድ መርህ መጥቀስ መቀላቀል ነው፡፡አለዚያም ጃርገን እየፈጠሩ ማወናበድ ነው፡፡የትምህርትና ማሰልጠኛው መምሪያ ሳያውቅ እና ሳይጋበዝ በእሱ የስልጣን ወሰን ውስጥ የሚገኙ ሊቃውንትን እየሰበሰቡ ሆድ ማስባስ መቼም ቢሆን በሰንበት እውራንን የመፈወስ አይነት ትሩፋት ሊሆን አይችልም፡፡ለነገሩ የቤ/ክህነት ዐይን ማየት የጀመረው ከ22 አመት ወዲህ አይመስለኝም፡፡ድሮም ይደብዝዝ እንጅ “ለዘእውሩ ተወልደ” የሚባል አልነበረም፡፡እሱን ከእናንተ ነው የምንሰማው፡፡ግዴለህም 500ሺህ ካህናት የሚመሩት በእውራን አይደለም፡፡ቃለዓዋዲውን አንብቡት!!!
   ሰ. የማኅበሩ አስተባባሪነት እንዳለ ሆኖ የግቢ ጉባኤ ተጠሪነቱ ለአካባቢው ሀ/ስብከት ይሁን ስል፡
   አስተባባሪነቱ የትምህርቱን ወጥነት ያስጠብቃል ብየ በማመን ሲሆን ተጠሪነቱ ለአካባቢው ሀ/ስብከት መሆኑ ደግሞ(1)በቅርበት ለመቆጣጠር(2)ጉባኤው ለአካባቢው ሰ/ት/ቤቶችና ለሀ/ስብከቱ መጠናከር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ(3)ከዩኒቨርሲቲ አካባቢ የሚመነጩ የግቢ ጉባኤ ችግሮችን በሀ/ስብከት ባሉ ሊቀ ጳጳሳት ደረጃ ኃላፊነት ወስዶ ተነጋግሮ ለመፍታት(4)የግቢ ጉባኤን የተለየ ደሴት አድርጎ ከመመልከት ይልቅ ከአባቶችና ከስር ጀምሮ ካሉት የቤ/ክ አስተዳደር መዋቅሮች ጋር ለማለማመድ ይረዳል፡፡

 11. Anonymous April 26, 2014 at 4:34 pm Reply

  “በአማን ነጸረ” በሚል የምታቀርበው ሀሳብ የግል ቢሆንምና ምንም ምን ይሁን ሀሳብን በነጻነት የማንሸራሸሩ መብትም እንደተጠበቀ ሆኖ በትክክል አየሁት ከምትለው አነጋገር እንኳን ለመገመት ቢቻል ፍጹም ተአማኒነት እንደሚጎድለው ያሳያል። ይህንንም ስል በተለያዩ ጊዜ ያስነበብካቸውን እንደተመለከትኩት በትክክል የአንድ ወገን አቋም ይዘህ የማኅበሩን አንተ እንደምትለው ችግሮች ብለህ የምትጠቅሳቸውን ጥቃቅን ጉዳዮች ስታመለክት በአለፉት ሃያ ዓመታት የታዩትን ከፍተኛ ጉድለቶችና የቤተ ክርስቲያኗን እርምጃ አንቀው የያዙትን የውስጥና የውጪ ኃይሎችን መሠርይ አካሄድ “በአማን መነጽር” ደፍረህ እንኳን አለመመልከትህ የመነጽሩ አገልግሎት በቂ ሳይሆን እንዳልቀረ በግምት ውስጥ አካትቺዋለሁ። እንዲሁ ግእዙን “በአማን ነጸረ” ብለህ ቃላትን ለማስዋብ ከሆነ የተጠቀምክበት በዚህ እንስማማለን። በተረፈ ግን የቤተ ክርስቲያኗን የውስጥ አስተዳደር ችግሮችን ማለት በቤተ ክህነቱ ዙሪያ ያለውን ማለቴ ነው አብረህ ብታቀርበው ምናልባት ሚዛናዊ ሆኖ ነገሮችን በትክክለኛው ለማሳየት ይቻል ይሆናል። አለበለዚያ ግን “መነጽርህ” ምርመራ ያስፈልገዋል ማለት ነውና ይህንንም በጥንቃቄ ተመልከተው። ከዚህ ካለፈ ግን የመነጽሩ ሳይሆን የሀሳብ መንሸዋረር ስለሚሆን ሰው ነህና የኅሊና ሚዛንም እንዲኖርህ ጥረት አድርግ። ይህን የምለው ግን የቤተ ክህነቱንም ሆነ የማኅበሩን ጉዞ በቅርብ ስለማውቀው ነው። ለአስተያየት ሰጪዎች ግን የማስተላልፈው መልእክትቢኖር ከመስመር የወጣ ስድብ ሳይሆን የሚያስፈልገው ጠንካራ ትችት ነውና እንታረም።

  • በአማን ነጸረ April 28, 2014 at 1:59 pm Reply

   @Anonymous April 26, 2014 at 4:34 pm ቤተክህነትን ያማልተችባቸው ምክንያቶች
   (1)ችግሩን በይፋ ስላመነ፡፡ሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት የቤ/ክ ፈተናዎች መሆናቸውን ቅዱስ ፓ/ክ አቡነ ማትያስ በይፋ ስለተናገሩና ዜና ቤ/ክ ጋዜጣም ዘወትር ስለሚጽፍበት እሱን መደጋገም አያስፈልገንም፡፡በአንጻሩ ማኅበረቅዱሳን ችግሩን በይፋ ሲያምን አይተነው አናውቅም፡፡ይልቅስ ከየመምሪያው ሲላተም ይቆይና ሁሉም ፊቱን ሲያዞርበት በጎ የሰራ ይፈተናል እያለ ነው የሚመጻደቀው፡፡በእነሱ ቤት ያለ እነሱ በቤ/ክህነት ውስጥ ሰራተኛ መምሪያ የለም፡፡ስራ ፈት ብቻ ነው፡፡ይሄ ትክክለኛ ያልሆነና ቤ/ክህነትን እንደተቋም በማሳጣት(ሳ’ን አጥብቀህ ጣ’ን አላልተህ አንብብ) ላይ የተመረኮዘ ርካሽ ተወዳጅነት አይመቸኝም፡፡እታገለዋለሁ!!ማኅበረቅዱሳንና ቤተክህነት ለንጽጽር የማይቀመጡ ተቋማት ናቸው፡፡ቤተክህነት ማለት እኮ እንደ ማኅበረቅዱሳን አይነት ወደ 20 የሚጠጉ መምሪያዎችን ያቀፈ ግዙፍ የእግዚአብሄር መንግስት በምድር እንደራሴ ነው፡፡እናስተውል!!
   (2)ቤ/ክህነት ችግሩ የትችት ማነስ ሳይሆን ከትችትም አልፎ ፍጹም እንደተቋም እንዳይኖር በግራቀኙ የሚካሄድበት ዘመቻ ልቤን ስለሚነካው ለጊዜው ቀና ብሎ እንዲሄድ ከትችት ይልቅ የተጫኑበትን እቡያን ስርዓት ለማስያዝ መወትወት ይገባል ብየ አምናለሁ፡፡
   (3)ገና የ55 አመት ጎልማሳ የሆነው መንበር በ3 መንግስታት ውስጥ ሆኖ ያየውን ውጣ ውረድ ስለምረዳ እና በዚህ አጭር እድሜው ከእስክንድርያ ካልተወዳደርክ ተብሎ ከእውቀታቸው ስሜታቸው በሚጎላ ፈልተው ያልሰከኑ ለቅ/ጴጥሮስ አደራ የተሰጡ ጠቦች የሚደርስበት ወከባ ስለሚያቆስለኝ አንደበቴን እየተገፋ ነው ብየ በማስበው ተቋም ላይ ማላቀቅ አልፈልግም፡፡
   (4) የቤ/ክ ጸሐፍት ነን ብለው የሚነሱ ወገኖችም ሆነ ባለሻርፓ ታጋይ መሰል ጋዜጠኞች የተቆጣጠሩት መድረክ አጀንዳው ቤ/ክህነት ላይ ቀድሞ የደመደመ በመሆኑ ሰብሮ ገብቶ አጀንዳ ለማስያዝ መጀመሪያ የእነሱን ብሎን ማላላት ግድ ነው ብየ ስለማምን የቤተክህነቱን ትችት አቆይቸዋለሁ፡፡
   (5)ቤተክህነትን መተቸት የሸዋ ዳቦን ሙልሙል የመቅደድ ያህል ቀላል እየሆነ ስለመጣ ለጊዜው መከላከሉ ላይ ማተኮሩ ግድ ነው፡፡ማኅበሩም ቤ/ክህነት ማለት የሊቃውንት ጉባኤን፣ ቅርስ ምዝገባና ጥበቃ መምሪያን፣ትንሳኤ ዘጉባኤ ድርጅትን፣ወዘተ…የሚያካትት ተቋም መሆኑን ረስቶ አባ ሰረቀ ባጣደፉት ቁጥር መላውን ቤተክህነት ጠቅልሎ ፈርጆ ዘመቻ ማካሄድ መምረጡ ስለሚያበሳጨኝ የቅኝት ለውጥ እስኪመጣ በእድሜም ሆነ በእውቀት ከእኔ ጋር ተቀራራቢ በሆኑ ወንድሞቼ የተሞላው ማኅበርና ማኅበርተኞቹ ወደ ትክክለኛው ቅንና ታዛዥ ልጅ የመሆን ባህርይ ቀልባቸው እስኪመለሱ ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ቅሬታየን ልገልጽ ለራሴ ቃል ገብቻለሁ፡፡አልመለስም!!!

 12. Anonymous April 27, 2014 at 2:22 pm Reply

  ወይ ጉድ! ወሬ በዛ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: