ወቅታዊ ተግዳሮቶቼን የምፈታው በምክክርና በጸሎት ነው – ማኅበረ ቅዱሳን

 • ማኅበሩ ትውልዳዊ ተልእኮውን ለአባቶች በመታዘዝና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመወሰን የመፈጸም አሠራሩና ፍላጎቱ እንደጸና መኾኑንና ከዚኽ ውጭ በሌላ መንገድ የሚመጣ መፍትሔ ይኖራል ብሎ እንደማያምን የሥራ አመራር ጉባኤው አስታውቋል፡፡
 • መንግሥት አካሒዳለኹ ከሚለው የፀረ አክራሪነት ትግልና ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ወስና የአፈጻጸም አቅጣጫ ከሰጠችበት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ አፈጻጸም ጋራ በተያያዘ በተለያዩ አካላት የሚሰነዘሩበትን የስም ማጥፋት ዘመቻዎችና መሠረተ ቢስ ክሦች ከአባቶች፣ ከአስተዳደር ሓላፊዎች፣ ከሰንበት ት/ቤቶች፣ ከመንፈሳውያን ማኅበራትና ከመላው ምእመናን ጋራ ተቀራርቦ በመረዳዳትና በጸሎት ፍትሐ እግዚአብሔርን በመጠየቅ የመፍታት የወትሮ ጥረቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፵፫፤ ቅዳሜ ሚያዝያ ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

Admas logoበከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ወጣቶችን አደራጅቶ የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነት፣ ሥርዓትና ትውፊት እንዲማሩና የአበው ተተኪ እንዲኾኑ በቅ/ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት የሚያገልግለው ማኅበረ ቅዱሳን÷ በየመድረኩ ከሚሰማው የአክራሪነት ፍረጃና ከቤተ ክርስቲያኒቱ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ እንቅስቃሴ ጋራ በተያያዘ የገጠሙትን የስም ማጥፋትና የማኅበሩን አገልግሎት የማሰናከል ወቅታዊ ተግዳሮቶች ተቀራርቦ በግልጽ በመመካከርና በጸሎት መፍትሔ ለማስገኘት ሲያደርግ የቆየውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ገለጸ፡፡

Mahibere Kidusan Sira Amerar Gubae

የሥራ አመራር ጉባኤው ፩ኛ የመንፈቅ ዓመት ስብሰባ በአቡነ ጎርጎሬዎስ የትምህርትና ሥልጠና ማዕከል
(ፎቶ: ማኅበረ ቅዱሳን)

የማኅበሩ የሥራ አመራር ጉባኤ ከመጋቢት 27 – 28 ቀን 2006 ዓ.ም በአቡነ ጎርጎሬዎስ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል አዳራሽ ባካሔደውና ከ45 የሀገር ውስጥና የውጭ ማእከላት የተውጣጡ 160 ያህል አመራሮች በተሳተፉበት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት መደበኛ ስብሰባ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ህልውናና በማኅበሩ አገልግሎት ቀጣይነት ላይ ተጋርጧል ያላቸውን ወቅታዊ ተግዳሮቶች በዝርዝር በመገምገም ቀጣይ የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጡ ተጠቁሟል፡፡

የሥራ አመራር ጉባኤው ያለፉትን ስድስት ወራት የአገልግሎት ዕቅድ ክንውን ሪፖርት በማዳመጥና በስፋት ቀርቧል በተባለው የወቅታዊ ኹኔታዎች ግምገማ ላይ በጥልቀት በመምከር ባስቀመጠው የመፍትሔ አቅጣጫ÷ ማኅበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት ትውልዳዊ ተልእኮውን ለአባቶች በመታዘዝና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመወሰን የመፈጸም አሠራሩና ፍላጎቱ እንደጸና መኾኑንና ከዚኽ ውጭ በሌላ መንገድ የሚመጣ መፍትሔ ይኖራል ብሎ እንደማያምን አስታውቋል፡፡

በተዛባ አመለካከትና በሐሰተኛ ክሥ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶችና የመንግሥት አካላትን ግራ በማጋባትና በማሳሳት የማኅበሩን አገልግሎት ማስተጓጎል ዋነኛ አጀንዳ አድርገዋል ባላቸው ግለሰባዊና ቡድናዊ ቅስቀሳዎች ላይ የሥራ አመራር ጉባኤው በትኩረት መወያየቱ ተነግሯል፡፡mahibere kidusan

መንግሥት አካሒዳለኹ ከሚለው የፀረ አክራሪነት ትግልና ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅ/ሲኖዶስ ወስና የአፈጻጸም አቅጣጫ ከሰጠችበት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ አፈጻጸም ጋራ በተያያዘ በተለያዩ አካላት የሚሰነዘሩበትን የስም ማጥፋት ዘመቻዎችና መሠረተ ቢስ ክሦች ከአባቶች፣ ከአስተዳደር ሓላፊዎች፣ ከሰንበት ት/ቤቶች፣ ከመንፈሳውያን ማኅበራትና ከመላው ምእመናን ጋራ ተቀራርቦ በመረዳዳትና በጸሎት ፍትሐ እግዚአብሔርን በመጠየቅ የመፍታት የወትሮ ጥረቱ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን አቅጣጫ ማስቀመጡን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የማኅበሩ ዓላማና ፍላጎት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሐዋርያዊ ተልእኮ የሚነሣና ጥቅሙም ለቤተ ክርስቲያኒቱ በመኾኑ ከቤተ ክርስቲያኒቱና ከሀገሪቱ ህልውና የሚቀድም የተለየ የማኅበር (ቡድናዊ) ዓላማና ጥቅም እንደሌለም የሥራ አመራር ጉባኤው ውሳኔ ገልጦአል፡፡

የማኅበሩ አባላት በመተዳደርያ ደንቡ በሰፈረው የአባላት መብትና ግዴታ መሠረት በቤተ ክርስቲያኒቱ የአገልግሎት መዋቅሮች ውስጥ ታቅፈው ቤተ ክርስቲያኒቱ በምታዛቸው ማንኛውም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግዳጆች በመሳተፍ ሐዋርያዊ ተልእኮዎቿን የማጠናከር፣ መብቶቿንና ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላትና አገልጋዮች ጋራ በመደጋገፍ የመቆም ድርሻቸውን በላቀ መንፈሳዊና ሞያዊ ብቃት መወጣታቸውን እንዲቀጥሉ በአጽንዖት አሳስቧል፡፡

ኢትዮጵያ የተለያዩ እምነቶችና ባህሎች ሀገር መኾኗን በቅጡ እንደሚገነዘብ የገለጸው ውሳኔው፣ የማኅበሩ አባላት እያንዳንዳቸው ሕጋቸውና መመሪያቸው ያደረጉትን የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ወራሽና ተቀባይ የኾኑለትን ሥርዓትዋንና ክርስቲያናዊ ይትበሃሏን በመንፈሳዊና አእምሯዊ መንገድ ከመጠበቅና ከማስከበር በቀር ሌላው አይኑር በሚል በአመለካከትና በአስተሳሰብ የተለዩ ወገኖችን አጥርና ቤት በኃይልና በጫና የመነቅነቅና የመጋፋት ባሕርያዊ መገለጫ ይኹን ድርጊታዊ ተሞክሮ እንደሌላቸውና እንደማይኖራቸው ጠቅሷል፡፡

አባላቱንና ተቋማዊ አሠራሩን በተመለከተ በማስረጃ ተደግፈው የሚቀርቡለትን ችግሮች ከመተዳደርያ ደንቡና ከውስጣዊ አሠራሩ አኳያ ያለማመንታት ለማረም ምንጊዜም ዝግጁ እንደኾነ የመከረው የሥራ አመራር ጉባኤው፣ እንደ ምእመንነታቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን ከመከባከብ ባሻገር እንደ ዜግነታቸው ለሀገራቸው ልማታዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለማበርከት የሚበቃ ሞያዊ አቅምና ሥነ ምግባር ያላቸውን ከ30ሺሕ መደበኛና ከግማሽ ሚልዮን በላይ ደጋፊ አባላት ያቀፈውን ማኅበር በማበረታታት የድርሻውን እንዲወጣ ከማድረግ ይልቅ፣ በተለያዩ ክሦችና ውንጀላዎች ለማሸማቀቅ ያለዕረፍት የሚደረገው ሐሰተኛ ቅስቀሳና የክሥ ዘመቻ አግባብነት እንደሌለውና ውጤትም እንደማያመጣ አስገንዝቧል፡፡

Advertisements

8 thoughts on “ወቅታዊ ተግዳሮቶቼን የምፈታው በምክክርና በጸሎት ነው – ማኅበረ ቅዱሳን

 1. maru April 13, 2014 at 5:17 pm Reply

  Egziabher Hulgizem ke mahiberu gar new. Amlakachin dink newna. Mechem Aytewenmna. Simu lezlalemu yetemesegene yihun.

 2. Anonymous April 14, 2014 at 6:27 am Reply

  Hulem Egziabheren Agaze Adredge kegonachehu alehu.

 3. Anonymous April 14, 2014 at 7:18 am Reply

  የማኅበሩ አባላት በመተዳደርያ ደንቡ በሰፈረው የአባላት መብትና ግዴታ መሠረት በቤተ ክርስቲያኒቱ የአገልግሎት መዋቅሮች ውስጥ ታቅፈው ቤተ ክርስቲያኒቱ በምታዛቸው ማንኛውም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግዳጆች በመሳተፍ ሐዋርያዊ ተልእኮዎቿን የማጠናከር፣ መብቶቿንና ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላትና አገልጋዮች ጋራ በመደጋገፍ የመቆም ድርሻቸውን በላቀ መንፈሳዊና ሞያዊ ብቃት መወጣታቸውን እንዲቀጥሉ በአጽንዖት አሳስቧል፡፡

 4. yibra son of king April 14, 2014 at 4:52 pm Reply

  egziabher yetemesegene yhun

 5. Anonymous April 14, 2014 at 8:21 pm Reply

  የማኅበሩ አባላት በመተዳደርያ ደንቡ በሰፈረው የአባላት መብትና ግዴታ መሠረት በቤተ ክርስቲያኒቱ የአገልግሎት መዋቅሮች ውስጥ ታቅፈው ቤተ ክርስቲያኒቱ በምታዛቸው ማንኛውም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግዳጆች በመሳተፍ ሐዋርያዊ ተልእኮዎቿን የማጠናከር፣ መብቶቿንና ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላትና አገልጋዮች ጋራ በመደጋገፍ የመቆም ድርሻቸውን በላቀ መንፈሳዊና ሞያዊ ብቃት መወጣታቸውን እንዲቀጥሉ በአጽንዖት አሳስቧል፡፡
  የዚህ ዓለም ናፋቂ መናፈቃንና የመናፍቃን ጉዳይ አስፈፃሚዎች በቤተ ክህነት የተደበቁ ተኩላ ጳጳሳትና ካህናት ድብን ቅጥል ይበሉ ሰይጣንም አናቱ ይቀጥቀጥ ወዮልን ለነሱ ::

 6. Anonymous April 15, 2014 at 7:01 am Reply

   ማኅበረ ቅዱሳን የአባቶቻቸውን ፈለግ የሚከተሉ በመሆኑ እኝ ክርስቲኖች እንኮራባችኋለን…… ግን ሀሰተኞች ስለበዙ ተጠንቀቁ.

 7. Anonymous April 15, 2014 at 7:04 am Reply

  ማኅበሩ የሚሰራቸውን ሥራዎች በሙሉ ሰይጣን ስለማይወደው መልካም የማያስቡ በሙሉ ይጠሉታል የኦርቶዶክስ ልጆች ልንነቃ ይገባናል

 8. WOLET MARIAM April 16, 2014 at 5:59 am Reply

  Tikekle alu, egziabher Yestewo, Btam tirue new. Maheber Kidusan Bmelkam Seraw, Bagelelotu, Behulentenawi Bego fekadu, malete Beteklala Befriew Yetawkal. Kefwoch Yaluten Belem Hulu Bejue, Hulu Bedeju Yalewn ,Mnem Yemisanewn Medehen Alem Kirstosen Kenatu Kemebetachen Kendengel Weladite Amlak Gar Bemhon Ahunem Bertu Engme Kegonachehu Alem. Yemebetachen Milja Hulem Lezelalem Kemhber Kidusan Gar Ayle!!! AMEN, AMEN, AMEN…!!!…!!!…!!!…!!!…!!!…!!!…!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: