መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት አልፈረጅኹም አለ

 • እንደ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ገለጻ በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ በአክራሪነት የተፈረጁት ‹አንዳንድ ግለሰቦች›÷ ‹‹አንዲት ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት›› የሚሉቱም ናቸው፡፡ ታዲያ ምን ይበሉ?!
 • ‹‹በይፋ አክራሪ ናችኹ ያለን አካል የለም፡፡›› /ተስፋዬ ቢኾነኝ፤ የማኅ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ/
 • ‹‹በጉዳዩ ላይ የጠራ ነገር የለም፤ ነገር ግን ጢስ አለ፡፡ ከጢሱ በስተጀርባ ያለው እሳት ይኹን እሳተ ገሞራ ባይታወቅም ለጊዜው ግን ማኅበሩን በተመለከተ ግልጽ የኾነ ነገር የለም።›› /ዲ.ን ዳንኤል ክብረት/

/ሰንደቅ፤ ፱ ቁጥር ፬፻፵፰፤ ሚያዝያ ፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም./Sendek Miyazeya 2006

ዘሪሁን ሙሉጌታ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት የተቋቋመውን ማኅበረ ቅዱሳንን የኢትዮጵያ መንግሥት በአክራሪነት አለመፈረጁን አስታወቀ፤ ማኅበረ ቅዱሳንም በበኩሉ በይፋ በአክራሪነት የፈረጀው አካል እንደሌለ ገልጦአል።

በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ አበበ ወርቁ እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ አቶ ተስፋዬ ቢኾነኝ÷ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንን መንግሥት በአክራሪነት ፈርጆ ሊያፈርሰው ነው፤›› የሚለውን አስተያየት በተመለከተ ተጠይቀው እንደመለሱት፣ ማኅበሩ በአክራሪነት በይፋ መፈረጁን እንደማያውቁ ተናግረዋል።

‹‹የአክራሪነት ፍረጃው ጉዳይ ከምን አንጻር እንደተነሣ ግልጽ አይደለም። በየትኛውም መድረክ ላይ ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ነው ተብሎ የተነሣበት ኹኔታ የለም። ማኅበረ ቅዱሳንን የማሳደግ፣ የመደገፍ ሓላፊነት የራሱ የሃይማኖቱ ተቋም እንጂ የመንግሥት ጉዳይ አይደለም፤ የማፍረስ ዓላማ አለው የተባለውም ስሕተት ነው፤›› ያሉት አቶ አበበ፣ ‹‹መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ ሕገ መንግሥቱም አይፈቀድለትም፤ የመንግሥትም ባሕርይ አይደለም፤›› ብለዋል።

‹‹የመንግሥት ፍላጎት ሃይማኖት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ተከትሎ በአግባቡ በዚህች ሀገር ላይ ሰላማዊ የአምልኮ ሥርዓት እንዲፈጸም እንጂ በሲኖዶሱ የተደራጀን ተቋም ሊያፈርስ የሚችልበት ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን የለውም፤›› ሲሉ አቶ አበበ ጨምረው ገልጸዋል።

‹‹መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳንን ሊያፈርስ ነው፤›› የሚለው ጉዳይ የተለያየ መነሻ እንደሚኖረው የጠቀሱት የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው፣ ጉዳዩ ከግንዛቤ እጥረት ወይም ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የአክራሪነት አስተሳሰብን የማስፋፋት ፍላጎት ባላቸው አካላት የተነሣ ሊኾን እንደሚችል ገምተዋል።

‹‹ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ የሚካሔድን እንቅስቃሴ ሊሸከም የሚችል ትከሻ እንደሌለው በተደጋጋሚ አሳይቷል፤ ትልቅ ትግልም አካሒዷል፤›› ያሉት አቶ አበበ፣ የአሉባልታው ምንጭ አክራሪነትን በማስፈንና አክራሪነትን በመዋጋት መካከል ባለው ፍልሚያ የተቀሰቀሰ አሉባልታ ነው ብለዋል።

‹‹ጉዳዩ በሬ ወለደ ነው፤›› የሚሉት ሕዝብ ግንኙነቱ፤ ‹‹ከዚኹ አካባቢ[ከማኅበረ ቅዱሳን] አክራሪነትን ሊደግፉ የሚችሉ ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ፤›› ብለዋል። ‹‹የሰላማዊው አምልኮ ሥርዓት እየጠነከረ በሄደ ቁጥር የአክራሪው መድረክ እየጠበበ ስለሚመጣ ከሕዝብ ልንነጠል ነው በሚል ፍራቻ ልክ በሕዝበ-ሙስሊሙ አካባቢ የሐሰት ወሬ ተዘርቶ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ ገብቷል እንዳሉት ኹሉ አሁን ደግሞ ወደ ሕዝበ-ክርስቲያኑ በማሰራጨት በባዶ ጩኸት ሕዝቡን ለማሳሳት የታለመ ነው፤›› ብለዋል።

‹‹መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ምንም ዓይነት ስጋት የለውም፤›› ያሉት አቶ አበበ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከመንፈሳዊ ሥራው ጎን ለጎን እያካሄደ ያለው የልማት፣ የሰላም፣ የዴሞክራሲ ሥራ ስለሚሠራ፣ መንግሥት ከያዘው አጀንዳ ጋር ስለሚጣጣም በአጋዥነት ስለሚያየው ይደግፈዋል እንጂ አያፈርሰውም ብለዋል። ይህ ሲባል ግን እንደ ማንኛውም ተቋም የተቀደሰውን ዓላማ የሚያራክሱ፣ ማኅበሩን ወዳልኾነ አቅጣጫ የሚወስዱ ግለሰቦች አይኖሩም ማለት እንዳልኾነ ጠቅሰዋል። በተለይም ‹‹አንድ ሃይማኖት! አንድ ሀገር! አንድ ጥምቀት!›› እያሉ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ። እንደዚህ ዓይነቶቹ ግለሰቦች በአክራሪነት ሊፈረጁ ይችላሉ ብለዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ አቶ ተስፋዬ ቢኾነኝ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው፣ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና አግኝቶ መተዳደርያ ደንብ ተቀርፆለት የሚተዳደር ማኅበር እንደኾነ አስታውሰው፤ ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያኗ ሥር የሚያገለግል ማኅበር በመኾኑ ከአክራሪነት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፤›› ብለዋል።

‹‹ክርስትናችን አክራሪነትን የሚያስተምር አይደለም። የማኅበሩም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ከአክራሪነት ጋር ምንም የሚያገናኝ ሥራ የለውም። የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እየሰጠ ያለ ማኅበር ነው፤ በጉዳዩም ላይ በይፋ የደረሰን የተጻፈ፣ በቃልም የተባልነው ነገር የለም። ካለም ልንወያይ፣ አስፈላጊውን ነገር ልንተባበር እንችላለን፤›› ሲሉ አቶ ተስፋዬ ከአክራሪነት ፍረጃ ጋር በተያያዘ በይፋ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፤ ማኅበሩም የተለመደ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።

ማኅበሩን በተመለከተ እየተነሣ ያለው የፍረጃ ሐሳብ ምንጩ ምን እንደኾነ አናውቅም ያሉት አቶ ተስፋዬ፣ ምንጩን ሊያውቁ ይችላሉ ብለን የምንገምተው ሚዲያዎቹ ናቸው። እኛ ምንም የምናውቀው ነገር የለም። እንደማንኛውም ጉዳዩን እንደሚከታተል አካል ነው የምናየው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ በወጡ ሰነዶች ላይ ማኅበሩ መጠቀሱን በተመለከተ አቶ ተስፋዬ ተጠይቀው፣ በማኅበር ደረጃ በይፋ በግልጽ የተጠቀሰ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ማኅበሩን በቀጥታ የሚመለከት በደብዳቤም ኾነ በሌላ መንገድ የተባለ ነገር የለም ብለዋል።

Dn. Daniel Kibretአንዳንድ የማኅበሩ ምንጮች በመጋቢት ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የፀረ አክራሪነት ትግል የወቅቱ ኹኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች››* በሚል ርእስ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና መድረክ የአክራሪነት አደጋ ያለው በሃይማኖት ሽፋን በሚንቀሳቀሱና የከሰሩ ፖሊቲከኞች ምሽግ በመኾን ያገለግላሉ በተባሉ ማኅበራት ውስጥ ነው መባሉ፤ በቅርቡም በሐዋሳ ከተማ ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነት ችግሮቹና መፍትሔዎቹ››** በሚል ርእስ በቀረበ ጽሑፍ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአክራሪዎች ምሽግ የኾኑት የወጣት ማኅበራት አደረጃጀቶች መኾናቸውንና እኒህም ማኅበራት በሃይማኖት ተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ይኹንታ ያላቸው ከመኾኑም በላይ ማኅበራቱ ከጽንፈኛ የፖለቲካ ኃይሎች ጋራ ግንኙነት እንዳላቸው መጠቀሱ እንዲሁም ከፓትርያርክ ምርጫው፣ ከቀድሞ ፓትርያርክ ጋር ዕርቅ ለመፍጠር የተደረገውን ጥረት ማኅበሩን ከከሰሩ ፖለቲከኞች ጋር ለማስተሳሰር መሞከሩና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች የማኅበሩ አባላት መንግሥትን በጥርጣሬ እንዲያዩት መደረጉን ይገልጻሉ።

በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ከነበራቸው አመራሮች አንዱ የነበሩት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በግል ስለ ኹኔታው ተጠይቀው፣ በጉዳዩ ላይ የጠራ ነገር አለመኖሩን፣ ነገር ግን ጢስ መኖሩን ገልጸዋል። ከጢሱ በስተጀርባ ያለው እሳት ይኹን እሳተ ገሞራ ባይታወቅም፤ ለጊዜው ግን ማኅበሩን በተመለከተ ግልጽ የኾነ ነገር የለም ብለዋል።

በግላቸው መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳንን በማፍረስ ስሕተት ይሠራል ብለው እንደማይገምቱና ምናልባትም ለማኅበሩ ያሰቡ ሰዎች መስለው ለማኅበሩ የተሳሳተ መረጃ ያቀበሉ እንዲሁም በመንግሥት በኩል ማኅበሩን በተመለከተ አፍራሽ አቋም ሊያንጸባርቁ የሚችሉ አንዳንድ ግለሰብ ባለሥልጣናት ሊኖሩ እንደሚችሉ ያላቸውን ጥርጣሬ ተናግረዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም በዋናነት በእምነቱ ተከታዮች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የተመሠረተ ሲኾን፤ የአባልነት መዋጮ በመክፈልና ከፍተኛ አገልግሎት በማበርከት ተሳትፎ ያላቸው ከ፴ ሺሕ በላይ አባላትና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተባባሪ አባላት አሉት፤ ማኅበሩ በስብከተ ወንጌል ረገድ ከሚያከናውነው ዓበይት መንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር ገዳማትና የገጠር አብያተ ክርቲስያናት በልማት ራሳቸውን እንዲችሉ፣ የአብነት ት/ቤቶች እንዲጠናከሩና እንዲጎለብቱ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ላይ የሚገኝ ማኅበር ነው።

>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>> 

በኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ማኅበራት የአክራሪነትና የከሰሩ ፖሊቲከኞች ምሽግ በመኾን መገልገል ከጀመሩ ውሎ አድሯል፡፡ ከ፮ው ፓትርያርክ ምርጫ ጋራ በማያያዝ የየራሳቸው ፍላጎት የሚያሳኩ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍና አሜሪካ ከሚገኘው ስደተኛው ሲኖዶስ ከሚባለው ቡድን ጋራ የዕርቅ ኹኔታ በሚል እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ፡፡

በዚኽ በራሳቸው በፈጠሩት ትርምስ ውስጥ መንግሥት እጁን አስገብቷል ወዘተ እያሉ የኦርቶዶክስ አማኞችን ለማወናበድ ይሞክራሉ፡፡ በራሳችንም እንደሌላው ኃይል ሰልፍ ልንወጣ ይገባል በሚል የዐመፅና የሁከት ቅስቀሳ ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡

በተለይም ሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ራሱን ስደተኛው ሲኖዶስ ብሎ የሚጠራው አካል ሰላማዊ፣ አሳታፊና ግልጽ ኾኖ የተካሔደውን የ፮ው ፓትርያርክ ምርጫ አውግዘናል በማለት መግለጫ ሲሰጥ የሰነበተ ቢኾንም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዩ ሕዝብ ጆሮውን ሳይሰጠው አልፏል፡፡ በሒደትም ይህ ኃይል ሰላም እንዳልኾነ፣ የሰላም ጥረቶችን በሙሉ ሲያሰናክል የሰነበተ፣ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ሳይኾን የከሰሩ ፖሊቲከኞች እንቅስቃሴ መኾኑን ግንዛቤ ይዟል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ የመሸጉ የትምክህት ኃይሎች ጽንፈኛ የፖሊቲካ ኃይሎች አካል በመኾን በጋዜጣና በመጽሔት ሕዝባችንን ለዐመፅና ሁከት ለማነሣሣት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በስደተኛው ሲኖዶስ በመሸፈንም እያንዳንዱ ሌላ ቀን ኢትዮጵያ የምትባል አገር የሌለች አስመስለው የግንቦት ሰባትን ከበሮ ሲመቱ ከርመዋል፡ (የፀረ አክራሪነት ትግል የወቅቱ ኹኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች፤ መጋቢት ፳፻፭ ዓ.ም.)

** slide presentation by Dr. Shiferaw000

 

 

 

 

 

 

 

 

Advertisements

41 thoughts on “መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት አልፈረጅኹም አለ

 1. Anonymous April 9, 2014 at 3:35 pm Reply

  አንችው ታመጭው፤አንችው ታሮጭው፡፡

 2. Anonymous April 9, 2014 at 4:13 pm Reply

  eski enayalen……….gen mazenagiya enidayehon

 3. ግእዝ በመሥመር-ላይ April 9, 2014 at 5:06 pm Reply

  ጥቂት ሐረጎችን እንምዘዝ፦

  …‹‹ከዚኹ አካባቢ[ከማኅበረ ቅዱሳን] አክራሪነትን ሊደግፉ የሚችሉ ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ፤›› ብለዋል።
  ይህ ሲባል ግን እንደ ማንኛውም ተቋም የተቀደሰውን ዓላማ የሚያራክሱ፣ ማኅበሩን ወዳልኾነ አቅጣጫ የሚወስዱ ግለሰቦች አይኖሩም ማለት እንዳልኾነ ጠቅሰዋል። በተለይም ‹‹አንድ ሃይማኖት! አንድ ሀገር! አንድ ጥምቀት!›› እያሉ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ። እንደዚህ ዓይነቶቹ ግለሰቦች በአክራሪነት ሊፈረጁ ይችላሉ ብለዋል።

  …በጉዳዩም ላይ በይፋ የደረሰን የተጻፈ፣ በቃልም የተባልነው ነገር የለም። ካለም ልንወያይ፣ አስፈላጊውን ነገር ልንተባበር እንችላለን፤››

  …መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳንን በማፍረስ ስሕተት ይሠራል ብለው እንደማይገምቱና ምናልባትም ለማኅበሩ ያሰቡ ሰዎች መስለው ለማኅበሩ የተሳሳተ መረጃ ያቀበሉ…

  [ከዚኽ በመነሣት ሲታይ፤ አኹን የሚያሰጋው፦]

  ያገጠጠ ኹሉ ሳቂ እየመሰለን
  ጠላትን ስጠብቅ ወዳጅ እንዳይገድለን! ነው።

  [ወንጌሉ የሚለው፦]

  …ግብር ይመጽእ መንሱት
  ወባሕቱ አሌ ሎቱ ለዘያመጽኣ ለመንሱት እምኀቤሁ!

  (ይኽም፦ መከራ ግድ የመጣል፤ ላምጪው ሰው ግን ወዮለት! ማለት ነው። አያይዞም “ከእኒኽ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያስት የወፍጮ ደንጊያ ባንገቱ አስረው ከጥልቅ ባሕር ቢያሰጥሙት ይሻለው ነበር” ይላል። )

  • ግእዝ በመሥመር-ላይ April 9, 2014 at 5:26 pm Reply

   [ከላይ ለማለት የፈለግኹት፦]

   ከወዲያ የሚሰማው የጠላት ድንፋታ አንድ ወገን ነው። እንዳመጣጡ ለመመለስ አያስቸግርም። ነገር ግን እስኪ ከወዲኽ የተባሉትን ተራቸውን ብቻ አገላብጠን እንያቸው።

   – “…ምናልባትም ለማኅበሩ ያሰቡ ሰዎች መስለው ለማኅበሩ የተሳሳተ መረጃ ያቀበሉ…”
   – “…ካ[ሉ]ም ልንወያይ፣ አስፈላጊውን ነገር ልንተባበር እንችላለን፤”

   “አይመጣምን ትተሽ…” በሚለው ምክር ለአንድ አፍታ ተመርተን ኹለቱን ብናያይዛቸው ምን ሊያሰሙ ይችላሉ?

   “…ምናልባትም ለማኅበሩ ያሰቡ ሰዎች መስለው ለማኅበሩ የተሳሳተ መረጃ ያቀበሉ…ካ[ሉ]ም ልንወያይ፣ አስፈላጊውን ነገር ልንተባበር እንችላለን፤” መኾኑ አይደለም?

   ኾነም ቀረም፤ እነማን ላይ እንደኾነ ገና አልተገለጠልንም እንጂ ከወዲያ ስይፍ እንደተመዘዘ ከወዲኽም የገናኛ ሰማዕታትን ቸብቸቦ አመቻችቶ ለመስጠት (ወይም ቸብቸቧቸው ሲቆረጥ ዝም ብሎ ለማየት) ዝግጅት እንዳለ ይታያል። እሱ ባለቤቱ ከወዲያም ያለውን ሰይፍ ይስበርልን፤ ከወዲኽም ያለውን ልቡና ይመልስልን።

 4. ጥናት April 10, 2014 at 5:15 am Reply

  ቀብሮ ለቀባሪ ለመስጠት የተሰነዘረች መግለጫ መሆኗ ነውን? እንዴት አንድ “ዋና ጸሐፊ” አንዳንድ የማኅበር አባላት የሚለውን አባባል መግለጫ ሳይሰጥበት በዝምታ ያልፋል? ነገሩ እንዴት ነው? ወዴት ወዴት ጃል! በገደምዳሜው ሜዳ ላይ መሮጥ ምንኛ ፋወል ናት በል! መውጫው በር ጠፍቶበት ይሆንን?……ያነጋግራል፡፡

 5. Annonyname April 10, 2014 at 6:10 am Reply

  በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ የመሸጉ የትምክህት ኃይሎች ጽንፈኛ የፖሊቲካ ኃይሎች አካል በመኾን በጋዜጣና በመጽሔት ሕዝባችንን ለዐመፅና ሁከት ለማነሣሣት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በስደተኛው ሲኖዶስ በመሸፈንም እያንዳንዱ ሌላ ቀን ኢትዮጵያ የምትባል አገር የሌለች አስመስለው የግንቦት ሰባትን ከበሮ ሲመቱ ከርመዋል፡፡ (የፀረ አክራሪነት ትግል የወቅቱ ኹኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች፤ መጋቢት ፳፻፭ ዓ.ም.)ይህ ምን ማለት ይሆን? የመንግስት አካላቱ ታጥቀው ሲራወጡና በተለይም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎችና ለዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች ይህንን ስልጠና ሰጥተውናል፡፡ በግልፅ በጋዜጣና በመፅሔት ህዝቡን ለዓመፅ እየቀሰቀሱ ነው የሚለው አባባል ማንን ሊሆን ይችላል ብላችሁ ትገምታላችሁ፡፡ እኔ አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ በሰጠው ሀሳብ በፍፁም አልስማማም፡፡ መንግስት ማኅበሩን አክራሪ ብሎ መፈረጅ ምን ያክል የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ እንደሚከተው ስላወቀና ስልቱን ስለቀየሰ እንጂ በይፋ ሲናገረው የነበረውን ዲስኩር እንዴት ይዘነጋል?‹‹ አልሸሹም ዘወር ›› ወገኔ ለቤተ ክርስቲያናችን ጠባቂዋ እግዚአብሔር አለ እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ አይደለም አጠቃላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ በመንግስት ጥርስ ውስጥ መግባቷን አጥርተን እናውቃለን፡፡ ለዚህ ስኬት ደግሞ እንቅፋት ይሆንብኛል ብሎ መንግስት ያሰበው ማኅበረ ቅዱሳንን የመጀመሪያው ሰለባ መሆኑን እናውቃለን፡፡ የመንግስት ውሸት ከደሙ ጋር የተዋሃደው ስለሆነ ቢዋሸን አይገርመንም፡፡ እናንተ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ግን እውነቱን በግልፅ ልትናገሩ ይገባል እንጂ መሸፋፈን ተገቢ መስሎ አይታየኝም፡፡ በእርግጠኝነት ማኅበሩን መንግስት ለማፍረስ በአዲሱ ስልት/ስትራቴጂ/ በቤተ ክህነት ውስጥ በሰገሰጋቸው መናፍቃን፤ ካድሬዎቹ እንዲሁም አድር ባይ አገልጋዮች ስላደረገ ብቻ እንጂ የመንግስት በማኅበሩ ላይ ያለው አቋም ከላይ አቶ አበበ የሰጡት ሀሳብ ሆኖ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡

  • Anonymous April 10, 2014 at 2:13 pm Reply

   Alemesmamat mebteih newu. Mahiber Kidusan yeteferawin hulu jas aylim, gin yiketatelal. Be meselegn aytenakosim. Yemeselewin gin gizei setito yiketatela. Yitseliyal. Mahiberu sayinager Egziabher Melse yisetal, bizu bizu aytenal. Silezih, Ato Tesfaye Tikikil nachew. Meglechaw Yemiwekilew, btikikil setitew kehone, mahiber kidusanin new. Ato tesfayen Aydelem!!!!

  • Anonymous April 11, 2014 at 10:44 am Reply

   Highly acceptable comment!! But Ato Tesfaye is also right as he is speaking on behalf of Mahibere-Kidusan – It is not his personal opinion.

 6. Anonymous April 10, 2014 at 6:16 am Reply

  ሚዲያዎች ለምትሰጡት መረጃ ጥንቃቄ ብታደርጉ!
  የሙያ ሥነምግባርም ቢከበር!!!

 7. Mesfin Dubale April 10, 2014 at 6:43 am Reply

  አንድ ጊታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት ያለዉ የእግዚአብሂር ቃል የተፃፈበት መፅሃፍ ቅዱስ ነዉ-እንጂ በሰዉ የተፃፈ ህገ መንግስት ስላልሆነ መቀየር አይቻልም!!!

  • Yeshiwas April 10, 2014 at 3:12 pm Reply

   “እንደ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ገለጻ በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ በአክራሪነት የተፈረጁት ‹አንዳንድ ግለሰቦች›÷ ‹‹አንዲት ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት›› የሚሉቱም ናቸው፡፡ ” ታዲያ መንግስት ማህበሩን በአክራሪነት አልፈረጅኩም የሚለው ከዚህ በላይ ምን ሊለን ፈልጎ ነበር ‹‹አንዲት ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት›› የሚለውን ቃል እኮ አምላካችን ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በታላቁ መጽሃፍ በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ በግልጽ ያስቀመጠው ክቡር ቃሉ ነው እንጂ የአሁኑ ትውልድ የፈለሰፈው መፈክር አይደለም ይህንን መንግስት ሊያውቀው እና ሊያምንበት ይገባል ፡፡

   • Anonymous April 11, 2014 at 10:46 am

    Perfect comment!!! So is the Government saying any body using the Bible is terrorist?

 8. gebire eyesus Atnaf April 10, 2014 at 10:15 am Reply

  we go always at right road, this is personal attitude.

 9. Ewnet April 10, 2014 at 10:42 am Reply

  The individuals in the different Government Organs with hidden individual religious sectarian agenda (” Re-evengalization “of the whole Ethiopia) shall be careful and responsible when addressing religious issues. Every religion is apologetic to its dogma. St Paul wrote ” One Baptism, One Lord and One religion ” it is found in the Bible and every Christian believe in it. While I believe that your religion is the true one and the unrevised one and defend it from those it says false., I have also peacefully co-exist with fellow country people of other beliefs. We shall not imposed forceful our religion on others ! Can you accuse St Paul as extremist? This wrong interpretation has to be corrected.

 10. Anonymous April 10, 2014 at 10:49 am Reply

  ene yemimeslegn mengset gize selaterew mazenagiya endayehon new……………………………….tegeten entseleye

 11. Annonyname April 10, 2014 at 11:06 am Reply

  ትናንትናም ዛሬም ነገም ሁልጊዜም እንላለን እንዲህ አንድ ጊታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት ኤፌሶን አንብብ

 12. Anonymous April 10, 2014 at 12:34 pm Reply

  ሆን ተብሎና የተጠና በሚመስል ሁኔታ መንግሥት በተለያዬ መድረኮችና ይፋ ባደረጋቸው ስነዶች ሳይቀር ማኀበረ ቅዱሳን እንደ ማኅበር በአክራሪነት መፈረጁን እያወቁ፣ ይህን ተከትሎ የማኀበሩ ሚዳያዎች እነዚህኑ ይፋዊ ስነዶች እየጠቀሱ ማህበሩ አክራሪ አይደለም መጻፋቸው እየታወቀ፣ የማኀበሩ አመራር አካላት መግለጫ መስጠታቸውን እየታወቀ፣ ‹‹ ከዚህ ቀደም ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ በወጡ ሰነዶች ላይ ማኅበሩ መጠቀሱን በተመለከተ፣ በማኅበር ደረጃ በይፋ በግልጽ የተጠቀሰ ነገር እንደሌለ መናገር ምን ይሉታል? አንዳንድ የተባሉ ወንድሞችን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ ወጥመድ ስለመኖሩ ከመጠቆም በቀር፡፡

 13. lema April 10, 2014 at 1:41 pm Reply

  አንድ ጊታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት ያለዉ የእግዚአብሂር ቃል የተፃፈበት መፅሃፍ ቅዱስ ነዉ-እንጂ በሰዉ የተፃፈ ህገ መንግስት ስላልሆነ መቀየር አይቻልም!!!

 14. Anonymous April 10, 2014 at 1:59 pm Reply

  don’t misquote him!!read carefully z content,not the headline!!it says….በተለይም ‹‹አንድ ሃይማኖት! አንድ ሀገር! አንድ ጥምቀት!›› እያሉ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ። እንደዚህ ዓይነቶቹ ግለሰቦች በአክራሪነት ሊፈረጁ ይችላሉ ብለዋል።why dear commentators evasively denied z word አንድ ሀገር!??

  • weg April 10, 2014 at 6:08 pm Reply

   “አንድ ሀገር” Ato meles yetenagerut new enji manim alalem. He had wrong information from his security or they add it in purpose to give political figure. I wonder why every body quote this “አንድ ሀገር”.

 15. Anonymous April 10, 2014 at 2:23 pm Reply

  አንድ ጊታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት ያለዉ የእግዚአብሂር ቃል የተፃፈበት መፅሃፍ ቅዱስ ነዉ-እንጂ በሰዉ የተፃፈ ህገ መንግስት ስላልሆነ መቀየር አይቻልም!!!

 16. Besemayat April 10, 2014 at 4:03 pm Reply

  “Doron sideliluat….. ” Endayihon negeru!

 17. መይሳው ካሳ April 10, 2014 at 5:59 pm Reply

  ማሕበረ ቅዱሳን ላይ አንድ ነገር ይድረስና የዚያኔ እንተያያለን !!!

 18. Anonymous April 10, 2014 at 6:12 pm Reply

  ሕገ መንግስትን በማለት ያጸደቀውን ሕገ አራዊት (ሕገመፈጽመ ወንጀል) ማኅበረ ቅዱሳን ላይ መተግበር ማለት ምን ማለት እንደሆነ አእምሮ ላለው ሁሉ አይጠፋውም (እጅግ ዉድ የሆነ ዋጋ ያስተፋል!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

 19. Anonymous April 10, 2014 at 8:55 pm Reply

  1, mengist yihen biyaderg <> / behageritua yehaymanot torinet tenesa malet new. silehonem anqets 11ena 27 aywqum lemilachew zegoch bicha sayiho lerasu shumamint liyastena yigebal!

  2, endetewaredu ke’qidus sinodos ena bsnbet timhert betoch maderaja memiriya sir be’meqetel yalew egziabher be’rasu gize yazegajew widu mahiberachinim awqew qidisina yegodelachew qidsinan markes yemiwedu yeseyitan wirajoch beiru <> beguyaw sheshigo kale beziya betelemedew menfesawi gimgemw liyabetirachew yigebal.

 20. ታሪክ እንማር April 10, 2014 at 9:15 pm Reply

  ውሸት ለወያኔ ቀሚሱ ነው ። ካለፈው እንማር እርቀ ሰላሙን ለመቅበር ወስኖ ቀባሪ ከመደበ ከጨረሰ በኋላ የለሁበትም መብቱ የቤተ ክርስቲያኗነው ሲል የሰጠውን መግለጫ ልብይሏል ።

  • Anonymous April 11, 2014 at 1:08 am Reply

   Tru new

  • ግእዝ በመሥመር-ላይ April 11, 2014 at 1:17 pm Reply

   ድንቅ ብለኻል፤ ወዳጄ። ዐላውያኑ አኹንም ሊያደርጉ የሚችሉት ይኸው ነው። ከዚኽ ቀደም ለሃይማኖታቸው በጥብዓት የቆሙትን አኹንም ሊቆሙ የሚችሉትን አሳልፈው እንዲሰጧቸው ጥቂት ብልጣብልጦችንከዚያው ከማኅበሩ አመራር ያዘጋጁና፤ ራሳቸው በነገሩን መሠረት “ለማኅበሩ ጭምር ያስቸገሩትን አሰርን ቀጣን እንጂ እኛ የለንበትም” እንደሚሉን አይጠረጠርም። ስለዚኽ አንዳንድ ወዳጅ የሚመስሉ ባንዶች እንዳያስጠቁን ከወዲኹ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

 21. xxxxxx April 11, 2014 at 2:47 am Reply

  befederalism wuyiyit lay mahibere kidusan sitekes neber mahiberu yan semto zim maletu atirun sineku zim kalu afrso yigebal new mibalew

 22. xxxxxx April 11, 2014 at 2:49 am Reply

  DR shiferaw the protestant one ……………

 23. Anonymous April 11, 2014 at 5:02 am Reply

  ሕገ መንግስትን በማለት ያጸደቀውን ሕገ አራዊት (ሕገመፈጽመ ወንጀል) ማኅበረ ቅዱሳን ላይ መተግበር ማለት ምን ማለት እንደሆነ አእምሮ ላለው ሁሉ አይጠፋውም (እጅግ ዉድ የሆነ ዋጋ ያስተፋል—————

 24. Anonymous April 11, 2014 at 5:30 am Reply

  መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት አልፈረጅኹም አለ

  ይቺ አባባል ”ስልታዊ ማዘናጊያ” ናት በርታ ማኀበረ ቅዱሳን ሥራህን ሥራ፡፡

 25. Anonymous April 11, 2014 at 6:06 am Reply

  አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት ያለዉ የእግዚአብሂር ቃል የተፃፈበት መጽሐፍ ቅዱስ ነዉ።እንጂ በሰዉ የተፃፈ ህገ መንግስት ስላልሆነ መቀየር አይቻልም!!! እና እኛስ ምን እንበል? ይህ እኮ ዶግማ ነው።አይቀየርም። የድሮ ነገስታት በሃይማኖታቸው የጸኑ ነበሩ የዛሬወቹስ?

 26. Anonymous April 11, 2014 at 7:09 am Reply

  Long Live Mahibere Kidusan!! Down with the hypocrite so called “monks’

 27. Anonymous April 11, 2014 at 11:58 am Reply

  ብራቮ ከሪፖርተር፣ፎርቹንና ካፒታል ውጭ ያላችሁ የግል ጋዜጦችና መጽሄቶች!!
  1. መንግሥት መቀየር ባትችሉም ስም የሌለው ምንጭ ጠቅሳችሁ በሰራችሁት ዜና ጥቂት የማይባሉ ምዕመናንን ፕሮፋይል ፒክቸርና ስክሪን ሰቬር ማስቀየር ችላችኋል!!
  2. አሜሪካ ከከተመ ዲያቆን እስከ ፓርላማ አባል በገደምዳሜ ማኅበርና ሃይማኖት አንድ ሲሆኑ ሁለት፣ሁለት ሲሆኑ አንድ ብለው እንዲናገሩ አድርጋችኋል!!
  3. ካህናት በቤተክህነት አዳራሽ መታደም ለፈለገ ሁሉ ክፍት በተደረገበት መንገድ አስፈቅደው መሰብሰባቸውን ጠቅሳችሁ የጻፋችሁት ሀተታ ጥብቅ ምስጢሮችን ፈልፍሎ የማውጣት አቅማችሁ የት እንደደረሰ ያሳያል!!ብራቮ!!
  4. የፓርቲ መታወቂያ ሳታዩ 16 የቤ/ክህነት ኃላፊዎች የህወሀት አባላት መሆናቸውን ማረጋገጣችሁ በፓርቲው ውስጥ ምን ያህል የረቀቀ የመረጃ መረብ እንዳላችሁ ያሳያል!!
  5. በተለይ የድጓ፣የአቋቋም፣የዝማሬ መዋሥዕት፣የትርጓሜ መጻህፍት መምህራን ያሉበትን ስብስብ በካድሬነት መፈረጃችሁ በቤ/ክ እውቀት መበልጸጋችሁን ያመላክታል!!ጎሽ!!
  6. ችግሩ፡ ስለመንግሥት በማኅበሩ ጣልቃ መግባት ስትናገሩ ማስረጃ ሳይጠይቁአችሁ ያመኗችሁ ሰዎች በማኅበሩ ስም ስለጠራችሁት የስቅለት ሰልፍ ሲሆን መልሰው አንፈልግም የራሳችን ድምጽ ሐመር እና ስምዓ ጽድቅ ነው ብለው ፊት መንሳታቸው ነው፡፡ጥሪያችሁ ከብረት ጋር ስለምታላትም እሷ ትቆየን ማለታቸው እናንተንም እኛንም አታስገርመንም፡፡ይልቅስ የምስል ቀያሪዎችን የdouble standard አካሄድ እናይባታለን!!

 28. ms April 11, 2014 at 1:04 pm Reply

  ኣቤት ውሸት! ኣሁን “ኣንዲት ኣገር ኣንዲት ሃይማኖት” የሚለውን ጠምዝዛቸሁ “ኣንዲት ጥምቀት ኣንዲት ሃይማኖት” ትላላችሁ! ዉይ ውሸት በክርስትና ስም ለምን ትዋሻላችሁ ኣረ ተዉ ሃይማኖታችንን ኣታሰድቡ ሐራዎች??? እሱም ትምህርተ ሃይማኖት እኮ ነው? ወንጀል የሚሆነው “ኣንዲት ኣገር ኣንዲት ሃይማኖት” ሲሆን ነው !

 29. Anonymous April 11, 2014 at 9:06 pm Reply

  mahbere kdusan berta ende abath grgorewos kale ”srahn zm bleh sra…..eske mot dres.

 30. ጥናት April 12, 2014 at 5:43 am Reply

  ወዳጄ ግእዝ በመሥመር ላይ፡
  ጉዳዩ የገባዎት ይመስላል፡፡ ግን ማን ጀግና ይመልስልዎት ዘንድ ቻለ? እንዲሁ እያድበከበኩት (እንዳልሆን እንዳልሆን እያደረጉት) ለወንድሞቻቸው የማይራሩ (በሌላ ያምኑ እንደሆነ እንጂ…በክርስትና ማመናቸው እስኪያጠራጥር ድረስ) ቸብቸቦ ቆርጠው ሊሰጡ የተቃረቡ መሆናቸውን ማን ተረዳ?
  ግን ኖላዊ ትጉህ ወኄር ዘኢይትነውም የሚሠራው እንዳለ ማን ያውቃል? ለ”አንደንዶችም” በረከት ለእነዚያም ሙስና (ጥፋት)

 31. Endalkachew Nefso April 14, 2014 at 6:49 am Reply

  በተለይም ‹‹አንድ ሃይማኖት! አንድ ሀገር! አንድ ጥምቀት!›› እያሉ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ። እንደዚህ ዓይነቶቹ ግለሰቦች በአክራሪነት ሊፈረጁ ይችላሉ ብለዋል። This is not in any way related with Ephesians.

 32. Anonymous April 22, 2014 at 11:03 am Reply

  ብዙ ነገሮችን ጫንቃችን እስኪጎብጥ ድረስ ቻልን አሁን ግን በሃይማኖታችን ከመጣችሁ አንገታችንን ለመስጠት ዝግጁ ነን!!!! ሃይማኖታችን ለእኛ የህልውናችን መሰረት ናትና!!! በርታ ወገኔ ከየትኛውም ሰዓት ይልቅ ሃይማኖትህን ነቅተህ የመጠበቂያ ጊዜህ አሁን ነው!!!

  ብዙ ነገሮችን ጫንቃችን እስኪጎብጥ ድረስ ቻልን አሁን ግን በሃይማኖታችን ከመጣችሁ አንገታችንን ለመስጠት ዝግጁ ነን!!!! ሃይማኖታችን ለእኛ የህልውናችን መሰረት ናትና!!! በርታ ወገኔ ከየትኛውም ሰዓት ይልቅ ሃይማኖትህን ነቅተህ የመጠበቂያ ጊዜህ አሁን ነው!!!

 33. belew abiye mwu goba health campus May 13, 2014 at 4:59 pm Reply

  mahibere kidusan yewengel ing yepoletica sebaki ayidelem kirstina befetena yetekebebe newna upto the last drop ofour blood ……………………..!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: