በተጠርጣሪ የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አራማጆች ላይ ዛሬ ምስክሮች ይሰማሉ

holy trinity building

 • ከሓላፊነታቸው ውጭ የሚንቀሳቀሱ ፕሮቴስታንትና ጉዳዩን ፖሊቲካዊ ያደረጉ የደኅንነት አባላት ነን ባዮች የኮሌጁን ሓላፊዎች በመጫን ተጠርጣሪዎቹን ከተጠያቂነት ለማዳን እየሠሩ ነው፤ ተጠርጣሪዎቹ በኮሌጁ አስተዳደር የተከለከለ ስብሰባ በግቢው እንዲያካሒዱ ረድተዋቸዋል፡፡
 • በ‹ደኅንነት አባላቱ› የሚደገፉትና ‹‹የኢሕአዴግ ተወካዮች ነን›› የሚሉት ተጠርጣሪዎቹ፣ ለሃይማኖታቸው የቆሙትን ብዙኃኑን የኮሌጁን ደቀ መዛሙርት በስለትና በፌሮ ብረት የታገዘ ዛቻና ማስፈራራት እያደረሱባቸው ነው፤ ደቀ መዛሙርቱና የኮሌጁ አስተዳደር ጉዳዩን ለጸጥታ አካላት አስታውቀዋል፡፡
 • ተጠርጣሪዎቹ÷ ‹‹ጽንፈኝነትን ታስፋፋለች›› በማለት ቤተ ክርስቲያንን የከሰሱ ሲኾን ዋና ዲኑን ጨምሮ አንዳንድ የኮሌጁን ሓላፊዎች ደግሞ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችኹ›› በሚል ውንጀላ በምርመራው ሒደት እንዳይሳተፉና ከቦታቸው ለማስነሣት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡፡
 • ኅቡእ የኑፋቄ አንቀሳቃሾችን በመመልመልና በማደራጀት የሚታወቁ ግለሰቦች (አሳምነው ዓብዩ፣ ደረጀ አጥናፌ እና ታምርኣየሁ አጥናፌ) ተጠርጣሪዎቹ ጥፋታቸውን እንዳያምኑ ከመገፋፋት ጀምሮ ደቀ መዛሙርቱን በጎጠኝነት በመከፋፈል አንድነታቸውን ለማሳጣትና ክሡን ለመቀልበስ እያሤሩ ነው፡፡

 

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር ጉባኤ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ መጋቢት ፳፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጠዋት፣ የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አንቀሳቃሾች ናቸው በሚል በተጠረጠሩ ዐሥር ደቀ መዛሙርት ላይ የጀመረውን ማጣራት ዛሬም ቀጥሎ ይውላል፡፡

በሦስት የኮሌጁ መምህራንና የሕግ ባለሞያ የሚታገዘው የአስተዳደር ጉባኤው በመጀመሪያ ቀን ውሎው፣ ዐሥሩ ተጠርጣሪዎች በተናጠል እንዲቀርቡ በማድረግ በኻያ ነጥቦች በተደራጁና በየስማቸው አንጻር ተለይተው በሰፈሩ ክሦች ላይ የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ጠይቋቸዋል፤ ኹሉም ተጠርጣሪዎች ‹‹እንዲኽ አልተናርንም፤ እንዲኽም አላደረግንም›› በሚል የቀረቡባቸውን ክሦች እየተማሉና እየተገዘቱ መካዳቸው ታውቋል፡፡

የኅቡእ እንቅስቃሴው መጋለጥና የአስተዳደር ጉባኤው ለጉዳዩ የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ድንጋጤም ብስጭትም እንዳሳደረባቸው በግልጽ የታየባቸው ተጠርጣሪዎቹ እንደተለመደው፣ ‹‹ክሡ ፖሊቲካዊ ነው፤ ከሣሾቻችን ማኅበረ ቅዱሳን የኾኑት እገሌና እገሌ ናቸው፤›› በማለት መደናገር ለመፍጠር ሞክረው የነበረ ቢኾንም በአስተዳደር ጉባኤው አባላት እየተመከሩና እየተገሠጹ አደብ እንዲገዙ መደረጋቸው ተሰምቷል፡፡

የአስተዳደር ጉባኤው ዛሬ ከቀትር በኋላ ለኹለተኛ ጊዜ በሚሠየምበት ስብሰባ፣ የተጠርጣሪዎቹን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ኅቡእ እንቅስቃሴ የሚያስረዱ የ፵፭ የሰው ምስክሮችን ቃልማዳመጡን እንደሚቀጥል ተገልጦአል፡፡

የኮሌጁን የቀን መደበኛ የዲግሪ መርሐ ግብር የሚከታተሉት ከ፩ኛ – ፬ኛ ዓመት ያሉት ደቀ መዛሙርት አጠቃላይ ቁጥር ፻፶ ነው፤ ከእኒህም ውስጥ የድምፅ፣ የጽሑፍና የሰው አስረጅዎች የቀረቡባቸውን ተጠርጣሪዎች ጨምሮ ክትትል የሚደረግባቸው ከኻያ የማይበልጡ በመኾኑ ብዙኃኑ ደቀ መዛሙርት ለሃይማኖታቸው መጽናት የቆሙ ርቱዓን እንደኾኑ ግልጽ ነው – ‹‹ዐሥሩንም ተጠርጣሪዎች ከንግግራቸው እስከ ግብራቸው ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን፤›› ብለዋል በማስረጃቸው ሐቀኝነት ላይ ስላላቸው ርግጠኝነት የተናገሩ ኹለት የደቀ መዛሙርት ም/ቤት አባላት፡፡

ብዙኃኑ ጽኑዓን ኦርቶዶክሳውያን ደቀ መዛሙርት በተጠርጣሪዎቹና አደራጆቻቸው ‹‹ያልበራላቸው የጌታ ጠላቶች፣ በጨለማ ጫካ የሚኖሩ፣ ደንቆሮዎችና ግንዞች›› የሚሉ ስድቦችና ዘለፋዎች የሚደርሱባቸው ሲኾን ይህም በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአበው መነኰሳትና ቀሳውስት እንዲኹም በአኃው ዲያቆናት ላይ ሳይቀር የሚሰነዘር እንደኾነ በክሡ መግለጫ ላይ ተመልክቷል፡፡

አራተኛ ዓመት ደቀ መዛሙርት ተራ ገብተው በሚያስተምሩበት ጸሎት ቤት በተለይ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ትኩረት ሰጥተው ሲያስተምሩ ‹‹ተረታ ተረትኽን ተውና ውረድ›› በሚል ግልጽ ተቃውሞ እንደሚደርስባቸው ተገልጦአል፡፡ የክሡ መግለጫ ጨምሮ እንደሚያስረዳው፣ ትኩረታቸውን በአንደኛ ዓመት ደቀ መዛሙርት ላይ አድርገው የሚንቀሳቀሱት የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አንቀሳቃሾቹ፣ አዲስ ገቢ ደቀ መዛሙርቱን ‹‹ቴዎሎጂ መማር ከፈለግኽ የበላኸውን ትፋ!›› በማለት በኦርቶዶክሳዊ ማንነታቸውም ያሸማቅቋቸዋል፡፡

ከኮሌጁ ውጭ በሚሰጣቸው አስተምህሮና ተልእኮ ፕሮቴስታንታዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ የፕሮቴስታንት አስተምህሮን ለማሰራጨት የሚሠሩት ተጠርጣሪዎቹ፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አትሰብክም፤ የምትሰብከው ፍጡራንን ነው›› ከማለት አልፈው ‹‹ጽንፈኝነትን ታስፋፋለች፤ የተወሰነ ጎሳ ናት፤›› በሚልም በትምክህተኝነት ይከሷታል፡፡

ይህን የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ጠባብ ፖሊቲከኞች ክሥ የሚያስተጋቡት የስም ደቀ መዛሙርት ራሳቸውን ‹‹የኢሕአዴግ ተወካይ ነኝ›› ለማለት የማያፍሩ ሲኾኑ ጉዳያቸው መታየት ከጀመረበት ካለፈው ኀሙስ ምሽት ጀምሮ የስለት መሣርያዎችና ፌሮ ብረት ይዘው በመኝታ ክፍል ኮሪዶሮች ላይ በመንቆራጠጥ ኑፋቄአቸውንና ክሕደታቸውን ያጋለጡ ደቀ መዛሙርትን ‹‹ፖሊቲከኞችና የማኅበረ ቅዱሳን አጫፋሪዎች›› በማለት እየዛቱባቸውና እያስፈሯሯቸው መኾኑ ተገልጦአል፡፡

ጠብ አጫሪ አካሔዳቸው ግጭት ቀስቅሶ ወደ ደም መፋሰስ ከማምራቱ በፊት የኮሌጁ አስተዳደር እኒኽን ግለሰቦች እንዲቆጣጠር ደቀ መዛሙርቱ በዚያው ዕለት ምሽት ለኮሌጁ አስተዳደር ኹኔታውን ከግለሰቦቹ ስም ዝርዝር ጋራ አያይዘው የገለጹ ሲኾን አስተዳደሩም በበኩሉ ለሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ማስታወቁ ተነግሯል፡፡

ከዚኹ ጋራ በተያያዘ ራሳቸውን በደኅንነት አባልነት ያስተዋወቁ ግለሰቦች፣ የቀረቡት ክሦች ሃይማኖታዊ ሳይኾን ፖሊቲካዊ ናቸው በሚል በኮሌጁ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትና የአስተዳደር ሓላፊዎች ላይ ጫና በመፍጠር ክሡን ለማዳፈንና ተጠርጣሪዎቹን ከተጠያቂነት ለማዳን እየሠሩ እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡ ከቀኑ መደበኛ መርሐ ግብር ሓላፊነት ተወግዶ ከኮሌጁ የተባረረው ዘላለም ረድኤትን፣ ተጠርጣሪዎችን በመመልመልና በማደራጀት የሚታወቁ ሦስት ግለሰቦችን በአስተባባሪነት የጠቀሰው የመረጃ ምንጩ÷ ጫናው በኮሌጁ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣ በኮሌጁ ሊቀ ጳጳስ፣ በአካዳሚክ ዲኑና በቀን መርሐ ግብር ሓላፊ ላይ ያተኮረ መኾኑን አስረድቷል፡፡

የኮሌጁ አስተዳደር በቅጽሩ ምንም ዓይነት ስብሰባ እንዳይካሔድ በከለከለበት ሰሞናዊ ኹኔታ ችግሩን በማባባስ የሚወቀሱና ተጠርጣሪዎችን በኅቡእ በማደራጀት የሚታወቁ ግለሰቦች የደኅንነት ነን ባዮቹን አይዞኽ ባይነት ተገን በማድረግ በአንድ በኩል ‹‹በዕርቅ እንፈታለን›› በሚል ጉዳዩን በሽምግልና ኮሚቴ ለማድበስበስ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ጉዳዩን ከተወላጅነትና ክልላዊነት ጋራ በማገናኘትና የኾነ ወገን በማንነቱ እንደተፈረጀ በማስመሰል ደቀ መዛሙርቱን በጎሰኝነት የሚከፋፍል ዘመቻ በግቢው እያካሔዱ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡

የደኅንነት አባላት ነን በሚል በኮሌጁ ሓላፊዎች ላይ ጫና ለመፍጠርና ተጠርጣሪዎችን ከተጠያቂነት ለማዳን ከሚሠሩት ግለሰቦች የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እንደሚገኙበት የገለጹ የጉዳዩ ታዛቢዎች፣ የግለሰቦቹ ተልእኮ ከጸጥታ አንጻር ብቻና ስምሪታቸውም ሕጋዊ ስለመኾኑ መረጋገጥ እንደሚገባው ያሳስባሉ፡፡ የግለሰቦቹ ስምሪት በርግጥም ሕጋዊ ከኾነ ደግሞ የተልእኳቸው አፈጻጸም የእምነታቸውን ተጽዕኖ በጣልቃ ገብነት ከማሳረፍ የጸዳና የቤተ ክርስቲያኒቷን ሉዓላዊነትና የትምህርት ተቋሞቿን ነጻነት ያከበረ ሊኾን እንደሚገባው ይመክራሉ፡፡

Advertisements

11 thoughts on “በተጠርጣሪ የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አራማጆች ላይ ዛሬ ምስክሮች ይሰማሉ

 1. Ribkah April 7, 2014 at 4:27 pm Reply

  Enezih menafikan badebaby yisekelulin!!!!

 2. Anonymous April 8, 2014 at 9:36 am Reply

  አንቺን እራሱ ጠረጠርኩሽ?ለምን ይሰቀላሉ ከቤተክርስቲያናችን ጠራርገን ማባረር እንጂ!!!

 3. Anonymous April 9, 2014 at 6:26 am Reply

  እኔ ደግሞ ሁለታችሁንም ጠረጠርኳችሁ፡፡ ስለምን ይሰቀላሉ፣ይጠረጋሉ መጀመሪያ ወሬው ተመርምሮ እውነት ከሆነ ይገሰጻሉ ፣ይመከራሉ፣ቀኖና ይቀበላሉ፣በመጨረሻ ካልተመለሱ ተወግዘው ይለያሉ፡፡እውነት ካልሆነም ከሳሾች በተራቸው ስለሐሰተኛ ውንጀላቸው ይጠየቃሉ፡፡የተጠረጠረ ሁሉ ይሰቀል፣ይጠረግ ብሎ ሥርዓት የለም፡፡

 4. Anonymous April 10, 2014 at 3:01 pm Reply

  ke kessate brihan enema nachew simachew biggalet melakam new

 5. Anonymous April 11, 2014 at 8:58 am Reply

  ‹‹ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አትሰብክም፤ የምትሰብከው ፍጡራንን ነው›› true or false … my question is why don’t they leave the church and establish another? If their clam is true and if they are truly based on bible, they will definitely get followers..

 6. temesgen April 11, 2014 at 9:38 am Reply

  ለሁሉም ነገር እግዚያብሄር መልስ ኣለው። ቤተክርስቲያንን ከጅቦች መንጋ የሚጠብቃት እና እዚህ ያደረሳት ኣኢትዮጵያ የቃል ኪዳኑ ሃገር ስለሆነች እንጂ እንደመናፍቃን በዌጽጤርን የሸሚዝ ድጋፍ ኣይደልም።

  • temesgen April 11, 2014 at 9:41 am Reply

   ይቅርታ-በዌስተርን ይባል -በዌጽጠርን የሚለው

 7. Anonymous April 13, 2014 at 5:17 pm Reply

  please ere tewooo kesasoch memenun atadenagreu

 8. Tesfay April 17, 2014 at 12:07 pm Reply

  እስከ አሁን ብዙ ስታደናግሩ ቆይታችኋል፣ አሁን ግን ዓላማችሁ ታውቋል የፖለቲካ ነው፣ ስለዚህ እንኳን ለእናንተ ለደርግም አልፈራም፤፤ ኢህአዴግ

 9. yetayali ewunetu April 20, 2014 at 7:13 am Reply

  ታላቁ አደናገሪ የፈተና ወቅት በቤተክርስቲያን
  የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በቅድስት ሥላሴ መ/ኮሌጅ ተመረቆ በስራ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለዚህ ጽሑፍ ሃላፊነትን ለመውሰድ የተዘጋጀ ነው፡፡ በጣም አሰልቺ ከሆነው የተሃድሶ አቀንቃኞች አባባል ለማምለጥ ሳይሆን ስለእውነት የማንኛውም ማህበር አባል አይደለም፡፡ ከማንኛውም የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቀኖና እና ዶግማ ጠባቂ ማህበራት ጋር አይተባበርም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለዛውም “የተሃድሶ አረም አራማጅ ከሆኑት ጋር አብሯል” ከመባል እንደተለመደው በእምነትና በስርዓት ከቤተክርስቲያን ካልራቁት ማኅበረ ቅዱሳንና ሌሎችም ጋር ስሙ መያያዙ ያኮራዋል፡፡
  ከተሃድሶ ፕሮቴስታንቶች እስከ መዝባሪዎች፣ ከዘረኞች እስከ የስነ ምግባር ስንኩሎች ብዙ ተብሏል፡፡ ዋናው ችግር የቤተክርስቲያናችን መሪ ማጣት ነው፡፡ በቀድሞ ጊዜ መሪዎች ከገዳማት ይወጡ ነበር፡፡ የሀገርም የቤተክርስቲያንም መሪዎች፡፡
  በገዳማት ትህትናን፣ መታዘዝን፣ ጸሎትን፣ ትሩፋትን፣ጸሊዓ ንዋይን፣ ፍቅረ ቢጽን፣ታማኝነትን፣ ራስን ለክርስቶስ አሳልፎ መስጠትን፣ ማኅበራዊ ኑሮን፣ መንፈሳዊ የቀለምም ሆነ የቃል ትምህርትን፣ ማንኛውንም ፈተና ተቋቅሞ ማለፍን ሌላም ብዙ ዕውቀትን ይገባያሉ፡፡ በስራቸው ግብር ገብተው ጣዕም ከቀመሱ አበው ጸሎት ይቀበላሉ፡፡ ከራሳቸው ትጋት ጋር የአበው በረከት ተዳምሮ በሄዱበት ሁሉ የመጣውን ሁሉ ለማለፍ የሚችሉበትን ታላቅ ኃይል ይጎናጸፋሉ፡፡ ይኼ ነበር የአባቶች ለመሪነት መታጫ፡፡ በትምህርት ብሎም በቅድስና፡፡
  ዛሬ ዛሬ ገዳማት ታናጉ፡፡ ተመልካች አጡ፡፡ ገዳማዊ ህይወት ተናቀ፡፡ ገዳም እንደ መኪና ታርጋ “የዕለት” ተባለ፡፡ አበው ያለፉበት ከተቃራኒ ጾታ ርቆ ንጽሕ ጠብቆ የመኖር መንገድ እንዲሰናከል ይሆነኝ ተብሎ ከወንዶች ገዳማት ሴትች ከሴቶች ገዳም ወንዶች አብረው ይኖሩ ዘንድ ግፊት በረከተ፡፡ በገዳም ስርዓት አጥብቆ የሚከለከለው ወደከተሞች በመሄድ የማደር ጉዳይ ተረስቶ ይባስ ብሎ ያለስራ በከተሞች በሕጋውያን መሃል ቤት ተከራይቶ መኖር ተስፋፋ፡፡ በየከተማው የመነኮሳትን ልብስ ለብሶ በሚደረግ አስነዋሪ ተግባር ቤተክርስቲያን በአሕዛብ ፊት ተሰደበች፡፡ ምዕመናን ልባቸው ደማ፡፡ እግዚአብሔርም መናኝ አጣ፡፡ “ገዳም ብንሄድም እነ እገሌ ተመልሰው መጥተው ከኛ የባሰ ስራ እየሰሩ ነው፡፡ ለምን ወደ ምናኔ እንሄዳለን?” አሉ ለማለት ነው፡፡
  ስለዚህ የነገ መሪዎቻችንም ማንነት ሲታሰብ አሳሳቢው ነገር ይሰቀጥጣል፡፡ አንድ የቤተክርስቲያን መሪ በመዳራት፣በሌብነት፣በዘረኝነት፣ በምንፍቅና፣ ተርመጥምጦ እንዴት ከላይ የተጠቀሱትን ነውሮች ከቤተክርስቲያን ለማጽዳት ይተባበራል? የቅብጥ መሪዎች ወርሓዊ ደመወዝ የላቸውም፡፡ ማንኛውንም ነገር ከቤተክርስቲያን ይሟላላቸዋል፡፡የባንክ አካውንት፣ቤት አይታሰብም፡፡ ገዳማቶቻቸው የመሪዎች ምርትን ያፈልቃሉ፡፡ ገዳማቱን በአበምኔትነት የሚመሩት ጳጳሳት ናቸው፡፡ አንድ የግብጽ ጳጳስ በሀገራችን በየከተማው ያለስራ የሚቅበዘበዙ መነኮሳትን በአድናቆት ተመልክቶ ለራሱ የግብጽ ፓትርያርክ ለቅዱስነታቸው አቡነ ታዎድሮስ አመለከተ፡፡ እርሳቸውም የወቅቱን ፓትርያርክና የፓትራርኩን ዋና ጸሐፊ “አንድ ገዳም ስጡንና እንደሞዴል ስርዓት አስይዘን እናስረክበችሁ” ብለው ሲጠየቁ የእኛ አባቶች “የእናንተና የእኛ ሀገር የገዳማት ስርዓት የተለያየ ነው” በማለት ነበር የተቃወሙት፡፡ ስርዓተ ምንኩስና በግብጽ እንደተጀመረ፤ የገዳማት ስርዓት መጽሐፍ ከእነርሱ ቋንቋ ወደእኛ እንደተመለሰ አለማወቃችው በዚህ ተገለጸ፡፡
  ስለዚህ መሪ የሌላት ቤተክርስቲያን ማንም ተነስቶ የፈነገው ስርዓት ሲቀርጽላት “ተው!” ባይ ሊኖር አይችልም፡፡ ቢኖርማ እነዚያ ጥቂት የማኒና የማልኮስ ልጆች ቤተክርስቲያን ራስዋ ባቋቋመችው ኮሌጅ ላይ የልብ ልብ ተሰምቷቸው የቤተክርስቲያንን ልጆች ለማሸማቀቅ ድፍረት አይኖራቸውም ነበር፡፡ ስለቅ/ሥላሴ የተሃድሶ እፉኝቶች ብዙ ሰው ያልተረዳው ነገር ሁሉም ከመናፍቅነት አልፈው “ለዚህ ዓለም ሰራዒ መጋቢ የለውም” እስከ ማለት የደረሱ የማኒ ልጆች መሆናቸውን ነው፡፡ በእነዚህ ጉዶች አንደበት በአካዳሚክ ነጻነት ስም በክፍል ውስጥ ክብር ይግባውና አምላክ ይሰደባል፡፡ የቅዱሳንና የእመቤታችንማ አይነገርም፡፡ ሰው “እምነት አለኝ” እያለ እንዴት አምላኩን ይሰድብ ዘንድ አፉን ይከፍታል? “ክርስቶስን አላወቃችሁም እናንተ ጨለማ ውስጥ ናችሁ” የሚል ሰው እንዴት በየካፍቴርያው፣ በየቢሮው ከሴተኛ አዳሪዎች፣ ከራሱ ጓደኛ ሚስቶች ጋር ጭምር ይማግጣል? እንዴት በየመሸታ ቤቱ በስካር ናውዞ በየዶርሙ ያሉ ሰላማዊ ተማሪዎችን ሰላም ይነሳል? በምንስ መንገድ ተማሪዎች በረሃብ አድማ ጊዜ ከዚያው ከፈረደበት “አልበራለትም” ከሚባለው ምዕመን ከተለመነ መክሊት በቀዳዳ ቀልቀሎው ገንዘብ አከማችቶ ሱፍ፣ ሞባይል…… ከመሸመት አልፎ በታላላቅ የመዝናኛ ስፍራዎች የቀን ውሎው ይሆናል?
  የፕሮቴስታንት ቡችሎች ከባህር ማዶ በተማሪ ስም ከተሰበሰበ ገንዘብ ላይ በየአደባባዩና በብዙኀን ጭምር “ሙስናን እንቃወማለን” እያሉ ቀን መፈክር እያሰሙ ማታ ግን ከሐዋርያት ከረጢት ብር ሲሸልግ የነበረውን ይሁዳን ነበሩ፡፡ ብዙ ተሃድሶያዊያን ከትምህርት ይልቅ በፌስ ቡክ ቻት ላይ ተጥደው ከተለያዩ የባህር ማዶ ኮረዶች በተለይ ከስቃይ ጋር ግብግብ ገጥመው ከሚታትሩ የዓረብ ሀገር ሴቶች ጋር በመጻጻፍ ጊዜያቸውን ማሳለፍ ተግባራቸው ነው ፡፡ ስንቶቹ እህቶች በእነዚህ መሰሪዎች ቃል እንደሚታለሉ ተታለውም ከቤተክርስቲያን እንደሚርቁ የፌስ ቡክ መስኮቶች ይቁጠሯቸው፡፡
  አብዘኛዎቹ የተሃድሶ ምልምሎች ኮሌጅ ውስጥ ሲገቡ ወይ የቤተክርስቲያን ወይ የዘመናዊ ትምህርት ፍላጻ ያቆሰላቸው ገመምተኞች ናቸው፡፡ ስለዚህ ዘመናዊ ሰው ሲጠይቃቸው የመንፈሳዊው ትምህርት ባለሞያዎች መንፈሳዊ ትምህርት የተማረ ሲጠይቃቸው የዘመናዊ ትምህርት ኤክስፐርቶች ናቸው፡፡ይህም በኮሌጁ ካሉ የውጭ ሀገር ዜጋ መምህራን ጋር በሚያደርጉት የዕለት ተዕለት ግንኙነት ይገለጻል፡፡ ያለአስተርጓሚ መግባባት ዳገታቸው ነው፡፡ በኮሌጁም “አሳይመንትና ሪሰርች ጻፉልኝ” እያሉ ከዶርም ዶርም ሲራወጡ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ በአጠቃላይ ማንነታቸውን ከግሬድ ሪፖርታቸው ማናበብ ይቻላል፡፡ ለዚያውም ከመሰል ተሃድሶ መምህራን የተበረከተላቸውን ዳረጎት ተጨምሮ ማለት ነው፡፡ምዕመናኑ የሚደግሙትን ውዳሴ ማርያም፣በቅዳሴ ጊዜ ስርዓተ ቅዳሴን ለመቀበል ያልቻሉ በመሆናቸው ተምረው ከማወቅ ይልቅ የዚህ አገልገሎት ደመኛ መሆንን መረጡ፡፡ ከምረቃ በኋላም ባለሶስት ጎማ መጓጓዣ ማሽከርከር ምርጫቸው ሆነ፡፡ ክርስቶስ እኮ ሰውን” ለእምነት እንዲያጓጉዙ፤ ካለማመን ወደማመን እንዲያመጡ መርጧቸው ነበር፡፡
  ተሃድሶ ተማሪዎች በኢሕዴግ አባልነት ለመመልመል ብዙ ደክመው የተሳካላቸው በፓርቲ አባልነታቸው ሌላውን ለማሰፈራራት መሞከር በግቢው የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ አቅራቢ አእምሮ የገዢውን ፓርቲ ውድቀት መፋጠን ከዚህ ተነስቶ ማሰላሰል ተጀመረ፡፡ ለኮንዲምየም መመዝገቢያ የመታወቂያ ካርድ ለማግኘት እና በመዲናችን የስራ ዕድል ፍለጋ ፓርቲውን የተቀላቀሉና የፓርቲ ደብተር ከወንጀል ነጻ መሆኛ ሳይሆን ህዝብን ማገልገያ መሆኑን ያልተረዱ አባላት፣ ላሳደገቻቸውና ለምትመግባቸው ቤተክርስቲያን ባላንጣ የሆኑ፣ ለህዝቡ ባህል ከበሬታ የሌላቸው አባላት ፓርቲን መበከላቸው አይቀሬ መሆኑ ያለግዜው ናፍጣውን ጨርሶ ፋኖሱን ካጨለመውና ከጠፋው ከኢሠፓ የታየ በመሆኑ ነው፡፡
  በኮሌጁ የሚሰጠውን ትምህርት አብረን ከተሃድሶች ጋር ተማርን፡፡ያውም ከእነርሱ በላይ ካላስ አቴንድ አድርገን፡፡ ሁሉንም ኮርሶች ወሰድን ፡፡ አንድም ቦታ የእነርሱን ዶክትሪን “ትክክል ነው” የሚል የለም፡፡ ታዲያ ለምን በስመ ሥላሴ የተጠመቁት ሰዎች በተሃድሶ ስም እንደገና ተጠመቁ ቢባል መልሱ ቀድመው ሲመጡ ምንም ቤዝ የለም፡፡ መንፈሳዊ ጥንካሬ የለም፡፡ የሚመጡትም የስራ ዕድል ፍለጋ ነው፡፡ ስለዚህ “ይህ የእምነት ክፍል ይህን ይላል” ሲባሉ መደናገጥ ይጀምራሉ፡፡ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ስለተለያዩ የእምነት ተቋማት አስተምህሮ ትምህርት ይሰጣል፡፡ፍልስፍናው ክህደቱ ከጥንታዊው እስከዘመናዊው ፡፡ አውቆ ራሱንም የሚያስተምረውንም ከተጠቀሱት ኑፋቄዎች እንዲጠብቅ ለማድረግ ነው፡፡ ታዲያ ተሃድሶች በዚህ ተጠልፈው ወደቁ፡፡
  ለተጠቀሱት ችግሮች መፍተሔ
  የቤተክርስቲያን መሪን ለማፍራት ገዳማትን ማጠናከር ፡፡ ገዳማት የስቃይና የመከራ ቦታዎች ብቻ ተደርገው ከማሰብ ለስጋም ለነፍስም አማካይ ስፍራ እንዲሆኑ ማብቃት፡፡ ስርዓትን ሳይለቅ ዘመናዊነትን በገዳማት ማስረጽ፡፡ የትራንስፖርት፣መብራት፣ንጹሕ የመጠጥ ውሃ፣ ሌሎችም ዘመናዊነትን ሊወክሉ ይችላሉ፡፡ይህ ከሆነ የንጽሕናን ኑሮ በምናኔ ላይ ያከሉ አባቶችን ከገዳማት ማፍራት ይቻላል፡፡
  የሌሎች ኮሌጆች ይቅርና በቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ለሆነው ሁሉ ግንበር ቀደም ተጠያቂዎቹ መሪዎቻችን ናቸው፡፡ሀ/ስብከቶቻችንም በመቀጠል ኃላፊነትን ይወስዳሉ፡፡ የቤተክርስቲያን አምላክ ክርስቶስ እና በየጊዜው ምላሳቸው ባልተገረዘ ተሃድሶዎች የሚሰደቡት ውዱሳን ቅዱሳን፣ ራሳቸውን አስርበው “ለእምነታችን ማጠናከርያ” እያሉ ሃብታቸውን የምመጸውቱ ምዕመናን በጌታ መንበር ፊት ይፋረዱዋቸዋል፡፡
  ከፓትርያርኩ ሲጀመር ዓይና ጆሮን፣ጥርስና ፣እግሩን ጨርሶ ሌላ ምትክ ያስገጠመ ሰው ከጡረታ ይልቅ ይህን ታላቅ ተቋም መምራት እንደማይችል እየታወቀ መሪ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ በፓትርያርክነት ምርጫው ያደረገውን ወረታ ከመክፈል ውጭ ሌላ ተልዕኮ አይኖረውምና ያስፈርዳል፡፡ የኮሌጁ የበላይ ኮሌጁን የራሳቸው ሀብት አድርገው የሚቆጥሩ በግል ትምህርት ቤቶች እንኳን የማይደረገውን በቤተክርስቲያን ሀብት ላይ ከተማሪ ሞግዚት እስከ ጥበቃ፤ ከመምህር እስከ ቢሮ ሰራተኛ፤ ከጽዳት እስከ ተላላኪ ብሎም እስከ ሾፌር እርሳቸው ከተመዘዙበት ብሔር ከዚያም አልፎ ከቅርብ ዘመድ በማድረግ፤ ሙሉ የኮሌጁን የገንዘብ ዝውውር በርሳቸው በኩል እንዲያልፍ በማድረግ በሌላም ለጽሑፍ ፍጆታ ሊውሉ በማይችሉ ነውሮች ያደረሱት በደል ምን ዓይነት ንሰሐ ገብተው ይሰረይላቸው ይሆን?
  ስለዚህ ለኮሌጁ ትንሣኤ የበላይ ጠባቂው መነሳት ብቻ ሳይሆን ጭራሽ እዚያ አለመድረስ ወሳኝነት አለው፡፡ ከዚያ ውስጥ ያሉትን ነቀዞችም ማንነት ተጣርቶ ከስፍራው ማስወገድ ብቻ ሳይሆን በኃላፊነት ማስጠየቅ ነው፡፡
  ሀ/ስብከቶች በተማሪ ምልመላ ጊዜ የሚመርጡዋቸውን ተማሪዎች ማንነት መመርመር፣ በክረምት ወደ ሀ/ስብከታቸው ሲመለሱ አስተምህሮታቸውን መከታተል ነው ፡፡ በመድረክ ላይ ካመለጣቸው ኑፋቄ የተነሳ የታገዱ ደቀመዛሙርት አሉ፡፡ ለዚህ የሀ/ስብከት ኃላፊዎች ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ በተቃራኒው በህዝብና በኮሌጅ ተወግዘው የተለዩ ተማሪዎችን “እኔ ኃላፊ እሆናለሁ” ብለው በጠርሙስ ቢራ እና የትራንስፖርት ወጪ ከተባረረበት ያስገቡ ስራ አስኪያጆችም አሉ፡፡ የም/ሸዋ ሀ/ስብከት ዋና ስራ አሰኪያጅ ከኮሌጅ ተባሮ የነበረውን አሳምነው አብዩን ቦታው ድረስ አምጥቶ ዋስ ሁኖ አስገብቶ ነበር፡፡ ይኼው ሲመረቅ በኮሌጁ ዙርያ እየተመላለሰ በጎችን ከበረታቸው የሚነጥቅ ተኩላ ሆነና አረፈው፡፡ ለነገሩ ዘጠና ከመቶ ከዚህ ሀ/ስብከት የሚመጡ ተማሪዎች ምን እንደሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ከዘላለም ረድኤት እስከ ወንድሰን፣ አሳምነው፣…… ቢባል ማን ጤነኛ አለ? ስለዚህ የስራ አሰኪያጁንም ማንነት ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡ ከሚጥለውና ከሚቀፈቅፈው የእባብ እንቁላልና ልጅ፡፡……………… ይቀጥላል፡፡

 10. Hailemariam May 2, 2014 at 1:27 pm Reply

  guys teregagu

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: