የመቐለ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መ/ኮሌጅ ኹለት የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አንቀሳቃሾችን አባረረ፤ ለሰባት ተጠርጣሪዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ በቅ/ሥላሴ መ/ኮሌጅ በዐሥር የኑፋቄው ኅቡእ አቀንሳቃሾች ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ዛሬ መመርመር ይጀምራሉ

HOLY TRINITY THEOLOGICAL COLLEGE LOGO

 • የኮሌጁ የደቀ መዛሙርት ም/ቤት ችግሩ በአስቸኳይ እንዲጣራ ከኹለት ወራት በፊት ያስገባው ደብዳቤ ለተጠርጣሪ ደቀ መዛሙርት ሽፋን በሚሰጠውና ተጠርጣሪዎችን በቢሮው እየጠራ በሚያበረታታው የአስተዳደር ዲኑ ያሬድ ክብረት ተቀብሮ መቆየቱ ተገልጦአል፡፡
 • በቅ/ሲኖዶስ ከተወገዙ ግለሰቦችና ፕሮቴስታንታዊ ድርጅቶች የኑፋቄ አስተምህሮና ተልእኮ የሚሰጣቸው ኅቡእ አንቀሳቃሾች ትኩረታቸውን በአዲስ ገቢ ደቀ መዛሙርት ላይ አድርገዋል፤ በመምህራን ምደባ ተጽዕኖ እስከመፍጠር፣ በነግህ ጸሎት ቤት ተራ ወጥቶላቸው ለስብከተ ወንጌል የሚመደቡ ቀናዒ ደቀ መዛሙርትን በማሸማቀቅ መርሐ ግብሩን እስከማስተጓጎልና መደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜዎችን በጋጠ ወጥነትና በአካዳሚያዊ ነጻነት ስም እስከማወክ የደረሱት ኅቡእ አንቀሳቃሾቹ፣ ከየአህጉረ ስብከቱ ተልከው የመጡበትን የኮሌጁን ትምህርት በክፍል ተገኝተው በመደበኛነት አይከታተሉም፤ ቤተ መጻሕፍቱንማ ጨርሶ አያውቁትም!!
 • በተጠርጣሪነት ክትትል ከሚደረግባቸው ኻያ ያህል የስም ደቀ መዛሙርት መካከል የድምፅ፣ የጽሑፍና የሰው ምስክሮች የቀረቡባቸው ዐሥር ተማሪዎች፡- ጥበቡ ደጉ(፬ኛ ዓመት ከደብረ ማርቆስ)፣ መለሰ ምሕረቴ(፬ኛ ዓመት ከራያና ቆቦ)፣ ያሬድ ተስፋዬ(፫ኛ ዓመት ከሃላባ)፣ ኤርሚያስ መለሰ(፫ኛ ዓመት ከባሌ)፣ ታቦር መኰንን(፫ኛ ዓመት ከወሊሶ)፣ በኃይሉ ሰፊው(፫ኛ ዓመት ከቤንች ማጂ)፣ ተመስገን አዳነ(፪ኛ ዓመት ከሐዋሳ)፣ ይስፋ ዓለም ሳሙኤል(፫ኛ ዓመት ከሰቆጣ)፣ ገብረ እግዚአብሔር ተስፋ ማርያም(፫ኛ ዓመት ከአሶሳ)፣ ሀብታሙ ወልድ ወሰን(፫ኛ ዓመት ከወለጋ) ናቸው፤ የኑፋቄ ተልእኳቸውና ማስረጃዎቹ ከየስማቸው ዝርዝር በአንጻሩ ሰፍሯል፡፡
 • ከተጠርጣሪ ደቀ መዛሙርት መካከል የአጫብር አቋቋም ዐዋቂ ነው የተባለው መሪጌታ ጥበቡ ደጉ የደቀ መዛሙርት ም/ቤት አባል ሲኾን በፈረንሳይ ለጋስዮን ገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በስብከተ ወንጌል እያገለገለ እንደሚገኝ ተዘግቧል፤ ግለሰቡ በግልጽ በሚናገረው ኑፋቄው፣ ‹‹እያንዳንድህ የበላኸውን ትፋ! ያለነው በጫካ ውስጥ ነው፤ ክርስቶስን ለማወቅ ካለንበት ጫካ መውጣት አለብን፤ መስቀል ዕንጨት ነው፤ ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ለመልአክ የምሰግደው ተገልጦ ሲታየኝ ብቻ ነው፤ ለማርያም የጸጋ ስግደት የሚለው በመጽሐፍ ቅዱስ የቱ ላይ ነው፤›› በሚል ግልጥ ኑፋቄ የቤተ ክርስቲያንን የነገረ ድኅነትና ክብረ ቅዱሳን አስተምህሮ በመጋፋት ይታወቃል፡፡
 • በኤቲክስና ሶሲዮሎጂ መምህሩ ተሾመ ገብረ ሚካኤል ‹‹ታዲያ ለምን ኤቲክስ ትማራለኽ?›› በሚል የተጠየቀው መለሰ ምሕረቴ፡- ‹‹ኢየሱስ አማላጅ ነው፤ በጸጋው ድነናል፤ ሥራ(ምግባር) አያስፈልግም፤›› በማለት ይታወቃል፡፡ ያሬድ ተስፋዬ፡- በነግህ ጸሎት ቤት ነገረ ማርያምንና ክብረ ቅዱሳንን ማእከል አድርገው የሚያስተምሩ ቀናዒ ደቀ መዛሙርትን ትምህርት አስቁሞ ከመድረክ እንዲወርዱ በማስገደድ፤ ተመስገን አዳነ፡- አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ‹‹የተሻለ ሥልጠና የምታገኙበት ቦታ አለ›› በሚሉ የጥቅም ማባበያዎች እየመለመሉ በመውሰድ፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ትራክቶችንና መጽሐፎችን በኅቡእ በማሰራጨት፤ ‹‹እኔ የመንግሥት የደኅንነት አካል ነኝ፤›› የሚለው ታቦር መኰንንና ገብረ እግዚአብሔር ተስፋ ማርያም ቀናዒ ደቀ መዛሙርትን ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችሁ›› እያሉ በማስፈራራት፣ መምህራን በምደባቸው እንዳያስተምሩ በውጤት አሰጣጥ ያኮረፉ ተማሪዎችን ለዐመፅ በማነሣሣት፣ በክፍል እያስተማሩ በሚገኙ መምህራን ላይ ከውጭ በር በመቀርቀርና በማንጓጠጥ፣ ዋናው ዲን የኮሌጁን ማኅበረሰብ በመንፈስ ለማስተሳሰር የጀመሯቸውን ጥረቶች (በጋራ እንደማስቀደስና እንደመመገብ ያሉ) በመቃወም በተለያዩ ስልቶች ወንጅሎ ለማስነሣት በሚፈጽሟቸው ሤራዎች ይታወቃሉ፡፡
 • ኅቡእ አንቃሳቃሾቹን እየመለመሉና ከኮሌጁ ውጭ በተለያዩ መንደሮች እያደራጁ ተልእኮና ጥቅም በመስጠት ወደ ኮሌጁ መልሰው ከሚያሰማሩት ግለሰቦች መካከል፡- በ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. በቅ/ሲኖዶስ ተወግዞ ከሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተባረረው ግርማ በቀለ፣ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወገዘው አሸናፊ መኰንን፣ የታገደው ጥቅመኛና ጥራዝ ነጠቅ ተላላኪ አሰግድ ሣህሉ በዋናነት ተጥቅሰዋል፤ ከኮሌጁ ተመርቀው ምደባ ቢሰጣቸውም በአዲስ አበባ ተቀምጠው የማደራጀት ሥራውን የሚመሩትም አሳምነው ዓብዩ፣ ታምርአየኹ አጥናፌ፣ አብርሃም ሚበዝኁ፣ ጋሻው ዘመነ፣ ‹አባ› ሰላማ ብርሃኑ፣ እሸቱ ሞገስና በድሬዳዋ የሚገኘው በረከት ታደሰ እንዲኹም በኮሌጁ የድኅረ ምረቃ ትምህርት በመከታተል ላይ የሚገኙት አእመረ አሸብርና ደረጀ አጥናፌ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡
 • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር በጽሑፍ፣ በድምፅና በሰው ምስክሮች ተደግፈው የቀረቡ ማስረጃዎችን ከቅዱሳት መጻሕፍት፣ ከትምህርተ ሃይማኖትና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ለመመልከት የሚያግዙትን ሦስት መምህራን መርጦ ዛሬ ምርመራውን ይጀምራል፤ የተመረጡት መምህራን፡- የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ታሪከ ሃይማኖት መ/ር ፍሥሓ ጽዮን ደመወዝ፣ የሥርዓተ ቅዳሴ መ/ር ሐዲስ ትኩነህና የትምህርተ ሃይማኖትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መ/ር ዶ/ር ሐዲስ የሻነህ ናቸው፡፡

 

Kesis_Sayefa_Photo

ቀሲስ ሰይፈ ገብርኤል(ኸርበርት) ጎርደን
የቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲን

 • ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስና ዋና ዲኑ ቀሲስ ኸርበርት ጎርደን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ተላላኪዎች ጉዳይ ተጋልጦ እንዲመረመር በጽናት የተንቀሳቀሱ የደቀ መዛሙርት ም/ቤት አባላትንና ብዙኃኑን ደቀ መዛሙርት በከፍተኛ አባታዊና የሓላፊነት ስሜት ተቀብለው እያበረታቱ ናቸው፡፡
  *                               *                               *

 

 • ‹‹በጣት የሚቆጠሩ ውሱን ተማሪዎች ከኮሌጁ ውጭ በሚሰጣቸው ተልእኮ ፕሮቴስታንታዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ በአካዳሚያዊ ነጻነት ስም የፕሮቴስታንት አስተምህሮ እያሰራጩ ይገኛሉ፡፡ በዚኽም ተባባሪ ለማግኘትና በፕሮቴስታንት ሳንባ የሚተነፍሱ ደቀ መዛሙርት ለማብዛት በተለይም አዲስ በሚገቡ የመጀመሪያ ዓመት ደቀ መዛሙርት ላይ መደናበር በመፍጠር ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱ ናቸው፡፡ ከዐሥር በማይበልጡ ተማሪዎች የተነሣ አንጋፋው ኮሌጃችን ‹የፕሮቴስታንት ኾኗል፤ መናፍቃንን እያፈራ ነው› እየተባለ ሲሰደብና ቤተ ክርስቲያናችን ኪሳራ ሲደርስባት በዝምታ መመልከት ጉዳቱ የከፋ ነው፡፡›› /ጥያቄዎቻቸው ለኹለት ወራት በአስተዳደር ዲኑ በየሰበቡ የታገተባቸው ደቀ መዛሙርቱና የም/ቤት አባላቱ ለዋና ዲኑ ያስገቡት የአቤቱታ ደብዳቤ/
 • ‹‹ኮሌጁ የሚቀበላቸውን አዳዲስ ተማሪዎች አመላመል በጥብቅ ዲስፕሊን መመሪያውን ጠብቆ በጥራት ቢኾን፤ ከመተዳደርያ ደንቡ ውጭ የሚንቀሳቀሱ መምህራንና ሠራተኞች ኹኔታ በማጣራት የዲስፕሊን ርምጃ ቢወሰድ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የኮሌጁን አጠቓላይ የሥራ ሪፖርት በማዳመጥ ለደካማ ጎን መስተካከልና ለጠንካራ ጎኑ ማበረታቻ የሚሰጥበት የክትትል ሥርዓት ቢኖረው፤›› /የ፳፻፭ ዓ.ም. የአስተዳደሩንና የደቀ መዛሙርቱን ውዝግብ የመረመረው አጣሪ ቡድን ለፓትርያርኩ በመፍትሔነት ካቀረበው ሪፖርት/
 • ‹‹ለቤተ ክርስቲያኒቱ ኮሌጆችና የካህናት ማሠልጠኛዎች የመምህራን አመራረጥና አመዳደብ፣ የደቀ መዛሙርት አመራረጥና አቀባበል ላይ ብርቱ ጥንቃቄ አለመደረጉና በየጊዜውም የትምህርት ክትትልና ቁጥጥር ማነስ ለችግሩ መከሠት ምክንያት ይኾናል ተብሎ ይገመታል፡፡ ስለኾነም ወደፊት በቤተ ክርስቲያናችን ኮሌጆችና የካህናት ማሠልጠኛዎች የመምህራን አመዳደብና የደቀ መዛሙርት አቀባበል ላይ ብርቱ ጥንቃቄና ትኩረት እንዲደረግ፤›› /8 የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ድርጅቶችና 16 ግለሰቦች የተወገዙበትን ጉዳይ ያጣራው የሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት ጥምር ጉባኤ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. ለቅ/ሲኖዶስ አቅርቦት የነበረው የውሳኔ ሐሳብ/
 • ‹‹የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በኮሌጆቻችን የሚገኙትን ተማሪዎች መቆጣጠርና መከታተል አስፈላጊ መኾኑን በአጽንዖት በመወያየት ደቀ መዛሙርቱ ከየአህጉረ ስብከታቸው ተመርጠው ሲላኩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መኾናቸውና የሃይማኖታቸው ጥንካሬ ታይቶ ወደ ኮሌጆቻችን ሊላኩ ይገባል በማለት እያንዳንዳቸው አህጉረ ስብከት ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጉባኤው ተነጋግሯል መምህራንም የሚሰጡት ትምህርት በኮሌጆቻችን ሓላፊዎች እየተገመገመ ትምህርቱ እንዲሰጥ ኾኖ ትምህርቱ ኑፋቄ ያለበት ከኾነ ደረጃውን ጠብቆ ለምልዓተ ጉባኤው እንዲቀርብ ጉባኤው ወስኗል፡፡›› /በ8 የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ድርጅቶችና 16 ግለሰቦች ላይ ውግዘት ያስተላለፈው የግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ/

ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ

Advertisements

22 thoughts on “የመቐለ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መ/ኮሌጅ ኹለት የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አንቀሳቃሾችን አባረረ፤ ለሰባት ተጠርጣሪዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ በቅ/ሥላሴ መ/ኮሌጅ በዐሥር የኑፋቄው ኅቡእ አቀንሳቃሾች ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ዛሬ መመርመር ይጀምራሉ

 1. Mesfin Dubale April 3, 2014 at 10:30 am Reply

  እባካችሁን የቢተ-ክርስቲያናችን የበላይ አባቶች ሆይ በቢተ-ክርስቲያን ዉስጥ እንክርዳድ እየበዛ ስለሆነ በጉባዒ በምትወስኑት አፈጻጸም ላይ ትኩረት ስጡበት !!!

 2. Anonymous April 3, 2014 at 11:07 am Reply

  ሚጥሚጣ በእጅ ተተክላ ቃጠሎዋ መከራ ነው እንዲባል የኮሌጁ አስተዳደር ለቤተ ክርስቲያን መጠበቅ ብሎም ለኮሌጁ ስም ሲል ድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል፡፡ የእውነተኞቹ መምህራን እና ደቀመዛሙርት ስም በጥቂት ስሑታን እንዳይታወክ ጥንቃቄ ያሻዋል፤ ያ ካሆነ ግን ነገ ከዚህ ኮሌጅ መመረቅ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ትርጉሙ በምእመናን ዘንድ ተዛብቶ የተዛባውን አመላከት ለማቅናት እንዳንደክም እላለሁ ተቀምጠን ሰቅለን ቆመን ለማውረድ እንዳንቸገር፡፡ እነዚህ ሰዎች የቀን ተማሪዎች ውስጥ ብቻ አይደለም ያሉት የማታዎችም ውስጥ ራሳቸውን ደብቀው ይገኛሉና ልብ ማለት ያሰፈልጋል፡፡ ለማንኛውም ሐዋርያት እንዳሉት ወዕቀባ ለቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት እንተ ሣረርካ በእንተ ሳረርካ በእንቲአሆሙ ጉዳዩን በችሎት ብቻ ሳይሆን በጸሎትም ማየት ተመራጭ ነው፡፡

 3. Anonymous April 3, 2014 at 11:53 am Reply

  ka mahibere kidusan gar ya tayazewun gibgib ba metekem la betekristiyan yamayetenyu PROTRSTANTOCH bazih bekul endaygebu kefetenya tenekake madereg yasfelegal.
  (WELDEYESUS)

 4. Anonymous April 3, 2014 at 12:44 pm Reply

  Though it seems late, any way, our true fathers and brothers, be strong, be committed, be careful for you are assigned there with great responsibility and accountability from above.

  I may be wrong, but feels that these theology colleges must be closed for at least two years. We are not looking satisfactory result for the church. Sorry, we know true and committed graduates who are working at country side areas. Closing for two years and totally re-designing the overall system. Other wise, at the expense of the church, I am afraid we are training protestant leaders.

  Tesfaye Ze tewahido.

 5. Anonymous April 3, 2014 at 12:57 pm Reply

  eshi uyegna yebete krstian asabiwoch asbachihulat motachuhal yehew yenatachin gemena eyalachu kemisuan gelbachu masayet lenante tilk tsidkna yebetekrstuian asabinet new aydel sijemer ewnetna fithawinet yemigodlachu yebete krstianua telat nachu kenezih wendmoch andu kebetekrstian biweta betekrstianua yemtitekemewn neger eski ngerugn agil eweket alu chifn tilachana admegninetachu meche yhon milekachu yegd 1 deke mezmur krstian lemebal yemahiber abal mehon alebe????? eski melsulign lemanignawm bewendimh hatyat yemtferd ante maneh yemilewn yefikr kal anbbu esun btawku endih betilacha bahir wst atwagnum neber libona ystachu yedingil lij

 6. Anonymous April 3, 2014 at 1:08 pm Reply

  በ ኮሌጁ ውስጥ በቀንም በማታም ተማሪዎች እንዲሁም በመምህራን እና በስታፍ ሰራተኞች ውስጥ የተሐድሶ መንፈስ ያላቸው አሉ እውነት ነው።እኔ ኮሌጅ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ በአይኔ አይቻለሁ።እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።

 7. hiruy April 3, 2014 at 1:24 pm Reply

  ወንጀል እንደ ወንጌል!!
  በየማኅበራዊ ሚዲያው በአባቶች፣ በሰባክያን እና ደቀመዛሙርት ላይ የሚለጠፉት ክሶች ቢያንስ ለሚመለከተው አካል ከመቅረባቸው በፊት ይፋ ባይደረጉ፣ተከሳሾቹ የማስተባበል እድል ስለሌላቸውና አንባቢውም ይህን ያልተስተባበለ ክስ እንደወረደ ተቀብሎ ግለሰቦችን ወደመፈረጅ ስለሚገባ አቀራረባቸው ደምዳሚ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ቢደረግ፣ መጽሀፉ በ1ኛጢሞ5-19 “ሁለት ወይም ከሶስት ምስክር በቀር በሽማግሌ(ካህን)ላይ ክስ አትቀበል” እንደሚል ብናስተውል፣አንባብያንም ለሚቀርቡ ክሶች በቂ ማጣራት ሳናደርግ ‘ወይኔ ቤ/ክ’ እያልን በችኮላ ለስም ማጥፋቱ ተባባሪ ለመሆን ባንፋጠን፣ትችቶች ሁሉ ለመጥረግና ለማሳደድ ብቻ ሳይሆን መክሮና ገስጾ መመለስና ማነጽም እንደ አማራጭ ቢያዙ ፣ከቡድናዊ አጀንዳ(motive)ሳይሆን ከቤ/ክ ጥቅም ብቻ ተነስተን ብንጽፍ/ብንናገር፡፡ ስለዚህ ብሎገሮች እናስተውል!!!በእናንተ ሊደርስ የማትፈልጉትን የስም ማጥፋት ወንጀል እንደ ወንጌል አትስበኩት፡፡

 8. Anonymous April 3, 2014 at 1:39 pm Reply

  ante mk kenh kerbewal

 9. Anonymous April 3, 2014 at 1:57 pm Reply

  Yih zena ejeg asdengach new selezizeh yadere gubet yiwetawal enam sayikatel beketel.yemenar mastemar sera bemakom matarat.lemed lebsew teqorquari yemimesluten betinekake meleyet tegebi yimeselegnal.

 10. Anonymous April 4, 2014 at 12:01 am Reply

  Guys, please don’t be silly. This is a strategy of MK to divert the attention of the followers, Holy Synod and the government. Here is the step that most scholars and responsible bodies are agreed;
  1. First, we have to clean the bad structure of MK from the church, because this structure facilitate corruption, and has hidden cell structure to facilitate the agenda of opposition parties (mainly GINBOT 7). Of course, the killer of our Holy Synod members and church scholars.
  2. Secondly, as the patriarch announced, we will stand in the side of the government to fight corruption and extremism which are the obstacles of national peace and development agenda.
  3. Thirdly, we , the true scholars of the church will use our device (Gospel) to preach the kingdom of God and plant our followers by the true word of GOD.

  AFTER WE GET RID OF THIS EVIL AND TERRIORIST ASSOCIATION, ALL US WILL FOCUS ON THE THIRD AGENDA (I.E; PREACHING GOSPEL TO EXPAND THE KINGDOM OF GOD) AND ALL WILL KNOW THE TRUTH, THE LIGHT, AND THE LIFE (THE SON OF GOD – JESUS CHRIST THE LORD) AND THEN HULUM WODEBERETU YIGEBAL, AMEN!

  I WANNA ASK MY BROTHERS AND SISTERS WHO ARE THE MEMEBERS OF THIS CONROVERSIAL ASSOCIASATION: AS MK SAID, ASSUME THAT “MK WAS WORKING DAY AND NIGHT FOR THE LAST 20 YEARS”, SO WHY THE CHURCH LOST ABOUT 20 MILLION FOLLOWERS WHO ARE CONVERTED INTO PROTESTANTISM?

  IF MK WAS PREACHING THE GOSPEL, AS THE APOSTLES WERE DOING, THE NUMBERS OF THE FOLLOWERS OF THE CHURCH SHOULD BE INCREASED. I HOPE THIS THIS IS SIMPLE LOJIC FOR YOU “ACADAMICIANS”, AND ALWAYS TRUE FOR WE THEOLOGIAN.THE WORD OF GOD IS POWERFUL THAN ANYTHING TO CHANGE THE LIFE OF HUMANBEINGS. BUT, TO THE CONTRARY, THE CHURCH LOST 20 MILLION AND THUS IF MK CONTINUES ITS ANTI-GOSPEL TEACHING, THE CHURCH WILL LOSE ALMOST ALL LATIES IN THE UPCOMING 10 YEARS (POWER CALCULATION – THIS IS SIMPLE FOR MK ACADEMICIANS” LOL).

  FOR MOST OF US WHO ARE WORKING TRULY FOR THE CHURCH, FOR THE LAST 20 YEARS;
  a. MK WAS FOCUSED ON ANTI-GOSPEL TEACHING AND WAS RUNNING AGAINST TRUE SCHOLARS OF THE CHURCH WHO WERE DEDICATED TO PREACH GOSPEL
  b. MK INTERST WAS FUNDRAISING FOR ITS HIDDENLY POLITICAL AGENDA TO INTERUPT THE PEACE AND DEVELOPMENT AGENDA OF THE NATION
  c. MOBILIZE FOLLOWERS TO STAND AGAINST THE CHURCH AND STATE LEADERS, BECAUSE ACCORDING TO MK BOTH THE STATE AND CHURCH LEADERS SHOULD BE AMHARA INSTEAD OF TIGRAIE
  d. WE ARE REALLY SORRY FOR GENUINE FOLLOWERS OF THE CHURCH WHO ARE MEMBERS OF THIS EVIL ASSOCIATION. WE BELIEVE THAT YOU KNOW VERY LITTLE FOR YOUR ASSOCIATION. MK IS A POLITICAL PARTY NOT A FAITH-BASED ASSOCIATION.
  e. SHOW US YOUR FRUIT FROM YOUR CROP FOR THE LAST 20 YEARS. WE WILL SEE YOUR ACCOUNT WHILE THE CORRUPTION COMMISSION DISCLOSED….

  HULUM WODEBERETU YIGEBAL/YIMELESAL, AMEN!

  Wodajachihu Ewinetu Sigelet

  • Anonymous April 4, 2014 at 6:11 am Reply

   ደሮን ሲያታልልዋት…አንተ ማንነተህን በግልፅ አስታዉቀሃል ኑፋቄን ለማስፋፋት የዘመኑን ሁኔታ በመከተል አሸባሪ ምናምን ማለት አያስፈልግም ሌባ ሙሰኛ ማን እንደሆነ የደባባይ ምስጢር ነዉ

  • Anonymous April 4, 2014 at 11:01 am Reply

   You may be one of those tehadiso followers in the theology colleges. Please, hear and read the fruit of MK. You cannot bring a single evidence about the corruption of MK. Try, and try. You feel happy by writing all this. You cannot test the fruit of MK, of course, of the church. Ask peoples in the church not in the Adarash, ask the new generation, ask Abinet memhiran, ask Monastries, ask remote areas that we called them but now baptized, ask your self.

  • Anonymous April 4, 2014 at 5:00 pm Reply

   You the silly man, are you confirming that Mk can all these power and capacity for diverting what ever it likes?? Egziabher Yimesgen, antew endalkew yihunena yemesereten, yaberetan, haile yeseten Leul Amlak yimesgen, Be MK sire asebasebo gena bizu yaseranal. Essey. Essey. Gin yigermal, BeMahibere Kidusan laye yaltelakeke tifat ye September 11 Ye America hintsawoch wedemet bicha yimeslegnal. Hulum tatun tekumual. Antem Jegnaw tehadiso yedershain belhale. Gin Lib yistih!!!!

  • yetayali ewunetu April 6, 2014 at 6:58 pm Reply

   we know every thing about reformers, about the college student who said about them self as they are the messengers of gospel in paper. in ground they intoxicates, on the way of adultery, who find in the street to do evil relation with the street girls, stolen of money . for example the who who are against the who graduated last year took the which was gathered from the believers during the boy cot last year. when they need money and other things they are orthodox after that they are the only the preachers of the word of God. most of them are the victims of ESLE and liturgical education. p/s don’t wast you time to describe about MK and the rest . we know every

  • Anonymous November 5, 2015 at 1:55 pm Reply

   ‹‹ እውነቱ ሲገለጥ ›› አውነቱ ሲገለጥማ በእውነትም አንተ ተኩላ ነህ፡፡ እኛ ማኅበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን፡፡ አንተ ግን ማነህ? የእኛ እውነት ገላጭ!!!! ‹‹ አረ በፍቅር በስመ አብ ይቅር ›› አለ ሰይጣን፡፡ ዝም አንልም፡፡ እንጮሃለን መናፍቃን ሳንነቃ የዘረፋችሁን ይብቃ!!! አሁን ግን እናንተን እሺ ካላችሁ በመፀሐፍ እምቢ ካላችሁ በወንችፍ ከቤተ ክርስቲያናችን እናስወጣችኋለን፡፡

  • Anonymous November 7, 2015 at 5:31 pm Reply

   U r best missionary & “preaching us very well’ I would like to say much more, but…”Empty vessel has a nice voice” Aristotle… Enough 4 u as qoutin from z bible may be ” senseless”

  • Belay April 12, 2016 at 3:10 pm Reply

   this justification shows you are the follower of tehadiso orthodox,please please ask and visit what MK has done for the past 24 years

 11. Tehadiso-nufakie Nehasie Has Coming April 4, 2014 at 12:38 am Reply

  Nehasie – Musho

 12. readers April 4, 2014 at 10:46 am Reply

  pls let us try to think again and again before writing any thing on this public site
  pls dont forget as we have enemies around us so dont expose the church for unbelievers before the exact decision of the committee and opposites
  pls let us try to pray if we are spiritual than writing poach a poach or from using some qualiqual expressions

 13. Anonymous April 10, 2014 at 4:32 pm Reply

  The information under this topic is totally wrong. I’m one of the cursed individuals. Let God Judge everything around

 14. Anonymous November 6, 2015 at 8:37 am Reply

  ሐራዎች በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ለቤተ ክርስቲያን የቆመች እውነተኛ የመረጃ ምንጭ እንደሆነች በግሌ አምናለሁ፡፡ ምክንያቴ ደግሞ በአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ያለውን እውነታ ስለማውቅና የዘረዘራችኋቸው ሰዎች በደንብ የሚጠረጠሩና ኮሌጁ ቢታረሙ ብሎ ለረጅም ጊዜ የታገሳቸው ናቸው፡፡
  ቀጥሉበት በብሎጋችሁ ላይ የዘረዘረቻችኋቸው ግለሰቦች በንሰሐ እስካልተመለሱ ድረስ ቤተ ክርስቲያኗ በብላክ ሊስት ይዛቸው በስሯ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ለሚገኙ አስተዳደራዊም ሆነ መንፈሳዊ ተቋማቶቿ የምታሳውቅበት አሠራር ቢኖር፡፡ ስማቸውንም ቀይረው ቢመጡ የምታውቅበትን መንገድ በዘመኑ ቴክኖሎጂ በተደገፈ መልኩ ከነገጽ ምስላቸው ለሕዝብ ይፋ ቢደረግ፡፡
  ተመሳሳይ ችግሮች ያሉባቸውን ግለሰቦችንም ሆነ ተቋማት የምትጠይቅበት ሕጋዊ ህልውና እንዲጠበቅላት ቤተ ክርስቲያኗ እራሷ ጠንክራ ብትሰራ፣ ከጅምሩ የሷ ያልሆኑትን ሰርገው የገቡትን አካላት በ2004 ዓ/ም አውግዛ እንደለየቻቸው በንሰሐ ካልተመለሱ ጠራርጋ ብታስወጣ ምክንያቱም ከጅምሩ የሷ ስላልሆኑ! በነሱ ጉዳይና በሙሰኞች ጉዳይ ታውከናል! በቤተክርስቲያናችን የወንጌል አገልግሎት ተስተጓጉሏል፡፡
  መድረክ የሚገባቸው ቢያስተምሩ አገልጋዩንም ሆነ ምዕመናኑን በማነጽ ኢ አማኙንም ለመማረክ የሚያስችል መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ ቅድስና ያላቸው በሥነ ምግባር የታነጹ የወቅቱ ችግሮቻችን በደንም የተገነዘቡ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች ታፍነዋል፡፡ አሁን መድረኩ በቀማኞች ተይዟል፡፡ አምላክ ምሕረቱን ይላክልን!
  አሁን ዓለም ያለበት ሁኔታ ወደመመሳሰልና አንድ ወደመሆን እንጠጋጋ ወደሚል እሳቤ እየተኬደ ይመስለኛል፡፡ በዚህም አካሄድ ከቀጠልን ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም የበደለ ቢኖር ንሰሐ ይግባ የሚለውን የአምላክ ትዕዛዝ ይጣሳል፡፡ ምክንያቱም ብንበድልም፣ ብናጠፋም የኛ ጥፋት ከሌሎች ጥፋት ጋር አንድ ወደመሆንና መመሳሰል ደረጃ እንዲሁም ኃጢያት ሰርተን እንዳልሰራንና ምንም እንዳልተፈጠረ ስለሚሰማን ከቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት አንዱና ዋነኛው የንሰሐ አገልግሎት የሚፈጽማት ስለማይኖርና በስተመጨረሻ የአምላክ መኖር ጥያቄ እንዲገባና የማናውቀውን አካል ወደማምለክ እንጓዛለን፡፡ ግብረ ሰዶማውያን እንቅስቃሴ ለዚህ ዘመን ማሳያ ይሆናል፡፡
  ይኽን እኩይ ተግባር በየአገሩ ለማዳረስ የያስችል ዘንድ የፕሮቴስታንታዊ ሃይማኖት እሳቤ ሕዝቡን ማጥመቅ የመጀመሪያ እንቅስቃሴ መሆኑ ከዚያም የኟዋን ጠንካራ መሠረት ያላትንንና ለአገር ብቻ ሳይሆን ለዓለም የምትጸልይ ቤተ ክርስቲያን እንቅፋት ስለሆነችና ወደፊትም ስለምትሆን መበታተን፣ አቅማን ማዳከም ብሎም ሙሉ በሙሉ በመውረስ የራስ ማድረግ፣ ተሐድሶን እንደአማራጭ መውሰድና ማስፋፋት ሳይታለምለት የተፈታ ነው፡፡
  ይኽ አካሄድ ደግሞ በምራባውያን ተጠንስሶ ዳጎስ ያለ ገንዘብ የሚቀርብባትና በመስመራቸው ላይ ያለ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም በዚህ ዓለም የሚከብርበት ይሆናል፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳን በየብሎጋቸው በመጥፎ ስላነሱት እንዲሁም ከቤተክርስቲያኗና ከመንግሥት ጋር ለማጣላት መጣራቸው የዕቅዳቸው አንዱና ዋነኛው አካል አድርገው ስለሚያስቡት እንዲበታተን ከተቻለም እንዲፈርስ መሥራታቸው ለዚሁ እንደሆነ መረዳት ይኖርባችኋል፡፡ በየመድረኩ ቤተክርስቲያኒቷ የሚያሸማቅቅ ማኅበሩን የማዳከም እንቅስቃሴ እንደሚቀጥልና ለዛ ወገብን ታጠቅ ብሎ መጠበቅና ድርሻን መወጣት ያስፈልጋል፡፡ መድከም አያስፈልግም! የቤተክርስቲያናችን ታሪክ ይኽን አያሳይም፡፡ በስተመጨረሻም ውሾችም ይጮሀሉ፤ ግመሎችም መንገዳቸውን ቀጥለዋል! የቆሎ ተማሪ ላይ በእነተ ስሟለማርያም ሲለምኑ፤ ማነው የሚጮኽባቸው ሰጪዎቹ ሰዎች እኮ አይደሉም! ውሾች ናቸው፡፡ ለምን እንደሆነ ታውቃላቸውሁ ለእኛ ይሰጥ የነበረውን ፍርፋሬና የሻገተ እንጀራ ይቀራመቱናል ብለው ነው!! ስለዚህ የቆሎ ተማሪውም ብልጥ አይደል በእነተስሟለማርያም ሲወጣ ውሻ ማባረሪያ አሪፍ ዱላ ይዞ ይወጣል፡፡ አሪፍ ዱላ መያዝ አለብን በየመንገዱ የሚገጥሙ ውሾች አይጠፉምና!
  ስለሆነም መረጃችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉበት፡፡ እኛ ደግሞ በተቻለን አቅም ቤተክርስቲያናችንን ከወራሪዎች ለመጠበቅ አምላክ በፈቀደ መጠን እንንቀሳቀሳለን፡፡
  የድንግል ማርያም ልጅ ይጠብቀን፣ይርዳን!!!

  • Anonymous April 12, 2016 at 11:53 pm Reply

   WooooooW! የድንግል ልጅ አብዝቶ ይባርክህ+++

   በእርግጥም የቆሎ ተማሪው ላይ አብዝቶ የሚጮኸው ውሻው ነው። እኛ ደግሞ አንተ እንዳልከው እንደ ቆሎው ተማሪ ደህና ዱላ(ትምህርተ ሃይማኖትን፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን፣ ትውፊትን) ይዞ መዞር ነው። ለውሾቹ ማባረሪያ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: