የጎልማሶችና ወጣቶች ማኅበራት ኅብረቱ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር መዘጋጀቱን አስታወቀ፤ በወጣቶቹ ዝግጅት የተደናገጡ የለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች የኅብረቱን እንቅስቃሴና አመራሮቻቸውን በሽብር ለመወንጀል እያሤሩ ነው

 • ቁጥጥር ከሚደረግባቸው ሕገ ወጥ ተግባራት መካከል÷ ያልተፈቀደላቸው ሰባክያን ስምሪትና የኅትመት ውጤቶቻቸው ሽያጭና ስርጭት፣ የአስመሳይ ባሕታውያንና መነኰሳት ነውረኛ ድርጊቶች፣ ሕገ ወጥ ልመና፣ የአጥቢያ አስተዳደር ሙስናና የወጣት ሱሰኝነት ይገኙበታል፡፡
 • ማዕተብ ያለው ኦርቶዶክሳዊ ምእመን በተለይም ወጣቱ ከሱስ ነጻ መኾን አለበት፤ መስቀሉን አንጠልጥሎ በየባንኮኒውና በየዳንኪራው ከመታየት መጠበቅ አለበት፤ ዶግማውን፣ ቀኖናውንና ትውፊቱን ያወቀና የጠነቀቀ፣ በኢኮኖሚያዊና ፋይናንሳዊ አቅሙም ጠንካራና እርስ በርሱ መደጋገፍ ይገባዋል፡፡
 • 102 ያኽል ማኅበራት አንድነት የፈጠሩበትና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አቅራቢነት የቅ/ሲኖዶሱን ዕውቅና ያገኘው ኅብረቱ ከ150,000 በላይ አባላት አሉት፡፡ የኅብረቱ አመራሮችና አባላት፣ ወቅቱ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነትና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ በፍቅር እስከ መጨረሻው የምንቆምበት ነው ብለዋል፡፡
 • ‹‹ቤተ ክርስቲያን ተጨንቃ ትጣራለች፤ የምትጣራው ወጣቱን ነው፤ ወጣት ዕውቀትና ጉልበት አለው፤ እኔ ሴቷን ጨምሮ ኹላችን እያንዳንዳችን ሓላፊነት አለብን፤ ወይ ግዴታችሁን ተወጡ ወይ ውረዱ የምንልበት ወቅት ነው!!›› /የማኅበራት ኅብረቱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ፌቨን ዘሪሁን/

(ኢትዮ – ምኅዳር፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፷፪፤ መጋቢት ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

Ethio Mihdar logoበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥና ዙሪያ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠርና ቤተ ክርስቲያኒቱን በማኅበረሰብ ልማት ለመደገፍ የሚያስችሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን መንደፉን አስታወቀ፡፡

የማኅበራት ኅብረቱ መጋቢት ፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ዳግሚት ጽዮን አዲስ ዓለም ማርያም ቤተ ክርስቲያን ባካሔደው የአባላት ጉዞ መርሐ ግብር ላይ እንደተገለጸው፣ ፕሮጀክቶቹ በአብዛኛው ‹‹የችግሩ ምንጮችም የመፍትሔው አካላትም እኛው ነን፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ውስጣዊ ችግሮች ማጽዳትና ተጨማሪ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በር መዝጋት ላይ ማተኮር አለብን፤›› በሚል አቅጣጫ የተቀረፁ ናቸው፡፡

ሃይማኖቱን ከውስጥ በመፃረር አስተምህሮውንና ሥርዓቱን በሚቃረን መልኩ የሚፈጸሙ ተግባራትን እንዲታረሙ ማድረግና አስቀድሞ መከላከል፤ የአስተዳደር መዋቅሩን ከሙስና፣ ብኩንነትና ምዝበራ መጠበቅ፤ የአገልግሎትና የአባቶች አልባሳትን ለብሰው እምነቱን በሚያስነቅፉ ድርጊቶች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን መቆጣጠር፤ በልማት ተነሽዎች ምክንያት የምእመናን ቁጥር በመቀነሱ አቅማቸው የተመናመኑ አጥቢያዎችን መደገፍና ወደማስፋፊያ ሰፈሮች የሔዱ ምእመናንን የአገልጋዮች እጥረት መቅረፍ ከፕሮጀክቱ ትኩረቶች መካከል በዋናነት ተጠቅሰዋል፡፡

ማኅበራቱ በየደብራቸውና በማኅበራቱ ኅብረት በኩል በተቀናጀ ኹኔታ የቀረፁዋቸውንና ከባይተዋርነትና ብሶት ከማሰማት ይልቅ ተግባርና መፍትሔ ተኮር ናቸው ያሏቸውን እኒህን ፕሮጀክቶች÷ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት፣ ከስብከተ ወንጌል ኮሚቴዎች፣ ከሰንበት ት/ቤቶች እና ከፖሊስ ጋራ በመተባበር እንደሚተገብሯቸው ገልጸዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን ችግር ለመፍታት የግድ የአስተዳደር አባል አልያም ካህናት መኾን የለብንም ያሉት የማኅበራቱ አባላት፣ በፕሮጀክቶቹ ትግበራ ሒደትና ፍጻሜ መፍትሔ ያገኛሉ ካሏቸው ችግሮች መካከል÷

 • ቅዱሳት ሥዕላትን ከዓለማውያን ሥዕሎች ጋራ ቀላቅሎና በጎዳና ላይ አንጥፎ መሸጥ፣
 • በገጠር አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ስም በተጭበረበሩ ደብዳቤዎችና ሙዳየ ምጽዋትን በየሆቴሉና ሬስቶራንቱ በማስቀመጥ ሕገ ወጥ ልመናን በማካሔድ የግል ጥቅምን ማካበት፣
 • በሞንታርቦ ቅሰቀሳዎች ማወክና የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልግሎት ማስተጓጎል፣
 • የመነኰሳትን ልብስ በመልበስ በየመንገዱና በየመሸታው ቤት ነውረኛ ተግባራትን መፈጸም፣
 • በሚመለከተው አካል ያልተፈቀደላቸውና በእምነት አቋማቸው ጥያቄ የሚነሣባቸው ሰባክያንና ዘማርያን ስምሪትና የኅትመት ውጤቶቻቸው ሽያጭና ሥርጭት ይገኙበታል፡፡

ከ፳፻፪ ዓ.ም ጀምሮ ለጥምቀት በዓልና በወርኃዊ ክብረ በዓላት ወቅት ባንዴራ በመስቀል፣ ምንጣፍ በማንጠፍ፣ ቄጤማ በመጎዝጎዝ፣ የተሳላማዊውን ሥርዓት በማስከበርና አጠቃላይ ሥነ በዓሉን በማድመቅ የሚታወቁ ወጣቶች መንፈሳውያን ማኅበራት አንድነት የኾነው የአዲስ አበባ ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት፣ የተለመደው የማኅበራቱ ወጣቶች አገልግሎት እንደተጠበቀ ኾኖ በወጣቱ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ኑሮ ላይም በጥልቀት መፈጸም ስለሚገባቸው ተግባራት የማኅበራቱ አባላት በጉዞ መርሐ ግብሩ ላይ መክረዋል፡፡

W.rt Feven Zerihun briefing the project proposalsየማኅበራት ኅብረቱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ፌቨን ዘሪሁን በፕሮጀክቶቹ ይዘት ዙሪያ በሰጠችው ማብራሪያ÷ ‹‹ማዕተብ ያሰረ ኦርቶዶክሳዊ ምእመን በተለይ ወጣቱ በሱስ ቦታዎች መገኘት የለበትም፤ መስቀሉን አንጠልጥሎ በየባንኮኒውና በየዳንኪራው ከመታየት መጠበቅ አለበት፤ ወጣቱ የሃይማኖቱን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት የተማረና የጠነቀቀ፣ በኢኮኖሚያዊና ፋይናንሳዊ አቅሙ ጠንካራና እርስ በርሱ የሚደጋገፍ መኾን ይገባዋል፤ ለዚህም ቤተ ክርስቲያን ማንንም የማያሳፍር የነጠረ ትምህርት ስላላት ኦርቶዶክሳዊው ወጣት ወደ ሰንበት ት/ቤቶች ገብቶ እምነቱን፣ ሥርዓቱንና ትውፊቱን መማር አለበት፤ በኅብረቱ ታቅፎ ደግሞ ለኑሮው የሚያስፈልጉትንና ቤተ ክርስቲያኑን የሚያገልግለበትን የክህሎት ሥልጠናዎች እንዲያገኝ እናደርጋለን፤›› ብላለች፡፡

የማኅበራት መብዛት ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ችግር የሚፈጥር በመኾኑ ወደ ኅብረቱ የመግባትን አስፈላጊነት ያስረዳችው ሰብሳቢዋ ወ/ሪት ፌቨን÷ ማኅበራቱን ከሰንበት ት/ቤቶችና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ለማጋጨት የሚጥሩ አካላት እንዳሉ በመግለጽ ወቅቱ ከስሜታዊነት ተጠብቆና ስልታዊ ኾኖ በርካታ የአገልግሎት ተሞክሮ ካላቸው ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋራ በፍቅርና በአንድነት እስከ መጨረሻው ቆመን የምናገለግልበት ነው በማለት አሳስባለች፡፡

የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኝ የአድባራት አስተዳዳሪዎች እንደሚሉት ምእመኑ ገንዘቡን ሰጥቶ ዘወር ማለት ያለበትና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጉዳይ የማያገባው ሳይኾን በቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ መሠረት በካህናትና ምእመናን አንድነት የተደራጀው የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አካል ነው፡፡

ከዚኹ ጋራ በተገናኘ በተለይ የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች በጥያቄና አስተያየት እንዳነሡት የምንገኝበት ወቅት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ፣ ሙስናና በአድርባይ ፖሊቲከኝነት የታገዘ ጎሰኝነት ተሳስረውና ተመጋግበው የቤተ ክርስቲያኒቱን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ብሎም አጠቃላይ ህልውናዋን የሚፈታተኑበት በመኾኑ የምእመኑ ትኩስ ኃይል የኾነው ወጣቱ የሚጠበቅበት ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ የኅብረቱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ፌቨን ይህን የገለጸችው፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያን ተጨንቃ ትጣራለች፤ የምትጣራው ወጣቱን ነው፤ ወጣት ዕውቀትና ጉልበት አለው፤ እኔ ሴቷን ጨምሮ ኹላችን እያንዳንዳችን ሓላፊነት አለብን፤ ወይ ግዴታችሁን ተወጡ ወይ ውረዱ የምንልበት ወቅት ነው፤›› በማለት ነበር፡፡

[በመርሐ ግብሩ ላይ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን ታሪካዊ አመጣጥ፣ ያለበትን ወቅታዊ መገለጫዎች ከዚኽም አንጻር የተወሰዱ የማጋለጥ ርምጃዎችና በቀጣይ በየደረጃው ኹሉም በየበኩሉ ሊወስድ ስለሚገባው ድርሻ በተመለከተ የመነሻ ጽሑፍ ቀርቦ የፓነል ውይይት ተካሒዷል፡፡ የጉዞ መርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች ከየአካባቢያቸው ተጨባጭ ኹኔታ በመነሣት ያደረጉት የሐሳብና መረጃ ልውውጥ ከፍተኛ ግንዛቤ ያስጨበጠ ከመኾኑም ባሻገር ከአዳራሽ ውጭም በመልስ ጉዞ ላይ የውይይቱ ግለት በምንተ ንግበር መንፈስ የቀጠለበትን መነሣሣት ፈጥሮ ነበር፡፡]

ከ150,000 በላይ ጠቅላላ አባላት ያሉት የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበራት ኅብረት ከአራት ዓመት በፊት የተቋቋሙና ከዚያም በኋላ እየተጨመሩ የመጡ 102 ያኽል የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ማኅበራት አንድነት ሲኾን በየካቲት ወር 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አማካይነት በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀለት መተዳደርያ ደንብ ዕውቅና ማግኘቱ ተገልጦአል፡፡

*******************************************

የአዲስ አበባ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥና ዙሪያ ኑፋቄን፣ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለመቆጣጠር እንዲህና እንዲህ ባለው ፍቅረ ቤተ ክርስቲያንና መንፈሳዊ ቅንዓት ላይ ብቻ ተመሥርተው የመከሩበት የአባላት ጉዞ መርሐ ግብር ዜና፣ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞችን ማደናገጡና ማሳሰቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አማሳኞቹ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የክሥ መግለጫ ባወጡበት የመጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ስብሰባቸው፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረቱን እንቅስቃሴና አመራሮቹን ጭምር ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ተመሳሳይ በኾነ አኳኋን በሽብር የመወንጀል ውጥን እንዳላቸው የሚያመለክቱ ንግግሮች ተደምጠዋል፡፡

ማንነቱ በሐራውያን ምንጮች በመጣራት ላይ የሚገኝ አንድ የስብሰባው ተሳታፊ ሲናገር እንደተደመጠው፣ የማኅበራት ኅብረቱ እንደ አዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ኹሉ ዕውቅና ተሰጥቷቸው በክፍላተ ከተሞች የተደራጁት በማኅበሩ[በማኅበረ ቅዱሳን] ተንኰል ነው፤ በጀትም በማኅበሩ ተመድቦላቸዋል፡፡

የማኅበራት ኅብረቱ ውይይት በአዲስ ዓለም ከተማ እንደተካሔደ የጠቀሰውና ሙሉ ውይይቱ የተቀረፀበትን ካሴት ቅጂ እንደሚያቀርብ የገለጸው ተናጋሪው፣ ‹‹በአዲስ አበባ ለምን አንድ ነገር አናደርግም፤ ቢሞትኮ ሦስትና አራት ሰው ነው›› የሚሉ የዐመፅ ዕቅዶች በመርሐ ግብሩ ላይ ተመክሮበታል ብሏል፡፡

በዩኒቨርስቲዎች መንግሥት ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ እንዳይካሔድ በተማሪዎች የአምልኮ፣ የአመጋገብና የአለባበስ ሥርዓት ረገድ ያስተላለፈውን መመሪያ አድንቆ በቃለ አጋኖ የተናገረው ይኸው የመረጃ ሰው ነኝ ባይ ግለሰብ፣ በዚኽ መመሪያ ምክንያት የማኅበሩ[የማኅበረ ቅዱሳን] የግቢ ጉባኤያት እንቅስቃሴ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ገልጦአል፡፡

በአኹኑ ወቅት በሠራተኛ ጉባኤ ስም እንቅስቃሴው የሚካሔድባቸው ተቋማት ‹‹ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ እና ኮርያ ሆስፒታል›› መኾናቸውንና እነዚኽም እንቅሰቃሴዎች ተደርሶባቸው ክትትል እየተደረገባቸው በመኾኑ ውጤቱን በቀጣይ እንደሚገልጽላቸው፣ እስከዚያው ድረስ ማኅበረ ቅዱሳንን እስከ ሞት ደርሰው እስከ ወዲያኛው ለመቃወም ያሰቡበትንና በመቃወማቸውም ሳቢያ ችግር የሚደርስበትን አባላቸውን በገንዘብ ይኹን በአስፈላጊው ነገር ለመደገፍ ወሳኝ ነው ያሉትን ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ማኅበር በአዲስ አበባ›› ምሥረታን እንዲያፋጥኑ አማሳኞቹን በተደጋጋሚ ሲያሳስብ ተሰምቷል፡፡

የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚዎች በስብሰባቸው ማኅበራቱን እንዲኽ ባለ አሥቂኝ፣ ዓይን ያወጣና ፍጹም የፈጠራ በኾነ ክሥ ለመወንጀል ውጥን እንዳላቸው ከመጋለጡ በፊት የማኅበራቱን ወጣት አባላት በመጀመሪያ ማርከው ከጎናቸው ለማሰለፍ ሞክረው የነበረው የአማሰኑትን የምእመናን ገንዘብ ማማለያ በማድረግ እንደነበር የጉዳዩ ተከታታዮች ይገልጻሉ፡፡ ይህም አልሳካ ሲላቸው በአንዳንድ አጥቢያዎች ወጣቶቹን ከሰንበት ት/ቤት አባላት ጋራ የማጋጨት ሙከራ ማድረጋቸውን፣ እስከ መታሰር የደረሱ ወጣቶችም መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የኾነው ኾኖ ያልተሳካው የገንዘብ መደለያም ይኹን ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ በማገናኘት ሊሰነዘር የተፈለገው የሽብር ፈጣሪነት ውንጀላ የአማሳኞቹን ዓላማ ፍንትው አድርጎ ከማሳየቱም ባሻገር የማኅበራቱ አባላትና የኅብረት አመራሮቹ አካሔድ ለአንዲት እናት ቤተ ክርስቲያን ዕድገት በመሥራት ማህቀፍ ውስጥ ክፍተት ሳይፈጥሩ እርስ በርስ በመደጋገፍ በቅርበት መጠባበቅና መከታተል በእጅጉ እንደሚያስፈል የሚያጠይቅ ነው፡፡

Advertisements

24 thoughts on “የጎልማሶችና ወጣቶች ማኅበራት ኅብረቱ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር መዘጋጀቱን አስታወቀ፤ በወጣቶቹ ዝግጅት የተደናገጡ የለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች የኅብረቱን እንቅስቃሴና አመራሮቻቸውን በሽብር ለመወንጀል እያሤሩ ነው

 1. Mesfin Dubale April 1, 2014 at 1:36 pm Reply

  ጊ/መ/ ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ቢተ-ክርስቲያንን/ምእመናንን/ መቺም አይተዋትም!

 2. Anonymous April 1, 2014 at 1:50 pm Reply

  Ethiopia as a whole, and Tewahido in particular, has never and ever lost their identity. Egziabher Yabertachu!!!!! Bertu!! EPRDF through Dr. Shiferaw T/mariam will definitely follow you and try to block your ways, but go on. We all r with you. Even forget our support, GOD the Almighty is alwyas with You, as you are with the church!!!!! Bertu!!!!! Musegna hodamoch Alkisu!!!!!

 3. ም.ክ.ረ. April 1, 2014 at 2:08 pm Reply

  ‹‹…ማኅበራቱን ከሰንበት ት/ቤቶችና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ለማጋጨት የሚጥሩ አካላት እንዳሉ /ስላሉ/ …ወቅቱ ከስሜታዊነት ተጠብቆና ስልታዊ ኾኖ በርካታ የአገልግሎት ተሞክሮ ካላቸው ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋራ በፍቅርና በአንድነት እስከ መጨረሻው ቆመን የምናገለግልበት ነው››

  ‹‹የችግሩ ምንጮችም የመፍትሔው አካላትም እኛው ነን፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ውስጣዊ ችግሮች ማጽዳትና ተጨማሪ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በር መዝጋት ላይ ማተኮር አለብን፤››

  ‹‹ቤተ ክርስቲያን ተጨንቃ ትጣራለች፤ የምትጣራው ወጣቱን ነው፤ ወጣት ዕውቀትና ጉልበት አለው፤ ወይ ግዴታችሁን ተወጡ ወይ ውረዱ የምንልበት ወቅት ነው፤››

  ‹‹ …የማኅበራቱ አባላትና የኅብረት አመራሮቹ አካሔድ ለአንዲት እናት ቤተ ክርስቲያን ዕድገት በመሥራት ማህቀፍ ውስጥ ክፍተት ሳይፈጥሩ እርስ በርስ በመደጋገፍ በቅርበት መጠባበቅና መከታተል በእጅጉ እንደሚያስፈልግ የሚያጠይቅ ነው፡፡›› ጆሮ ያለው ይስማ !!!!!

  ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን!

 4. Anonymous April 1, 2014 at 2:56 pm Reply

  egnam zem anlem ahune BETEKERSTIYAN yemtabebebat woyem yemtwodkebt gize new selzihe ahune endtabebena lejochuan endtetadeg merbareb alebin atefiwochuan maswoged.

 5. Anonymous April 1, 2014 at 3:27 pm Reply

  ቃለ ህይወት ያሰማልን!!! በእ/ር ቸርነት ሁሉን እናልፋለን፡፡ አንድነታችንንም እንጠብቃለን፡፡

 6. Anonymous April 1, 2014 at 5:15 pm Reply

  we r with u always. continue what u r doing God b with u.

 7. Anonymous April 1, 2014 at 5:46 pm Reply

  ‹‹…ማኅበራቱን ከሰንበት ት/ቤቶችና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ለማጋጨት የሚጥሩ አካላት እንዳሉ /ስላሉ/ …ወቅቱ ከስሜታዊነት ተጠብቆና ስልታዊ ኾኖ በርካታ የአገልግሎት ተሞክሮ ካላቸው ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋራ በፍቅርና በአንድነት እስከ መጨረሻው ቆመን የምናገለግልበት ነው››

  ‹‹የችግሩ ምንጮችም የመፍትሔው አካላትም እኛው ነን፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ውስጣዊ ችግሮች ማጽዳትና ተጨማሪ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በር መዝጋት ላይ ማተኮር አለብን፤››

  ‹‹ቤተ ክርስቲያን ተጨንቃ ትጣራለች፤ የምትጣራው ወጣቱን ነው፤ ወጣት ዕውቀትና ጉልበት አለው፤ ወይ ግዴታችሁን ተወጡ ወይ ውረዱ የምንልበት ወቅት ነው፤››

 8. Anonymous April 1, 2014 at 5:47 pm Reply

  egziabhere yabertan beandenete lebetkersiyanachen eneseralen

 9. Anonymous April 1, 2014 at 8:50 pm Reply

  yehe benante becha ayechalem bechachwen honachu yemetcheleten betadergeu ega degmo besedet yemnegege ye orthdox legoch behulum neger kegonachu nen

 10. haymanot April 2, 2014 at 4:31 am Reply

  Betekrstiyanitu bekehadyan temolach. yeEgziabher sim yebeg lemd hone. agelgayoch nen blew besew fit kemeten belay melkam yehonewn kal ynageralu. beguadagin wegenachewn yshetalu. ykdutal, ywashutal, ywashutal…ywashutal. Yewashowoch gora honech.

 11. መምሩ April 2, 2014 at 4:38 am Reply

  አይ አልቃይዳ ድብቅ ጦርሽን አወጣሽ እውነትም አልቃይዳ

  • Anonymous April 2, 2014 at 11:34 am Reply

   ሌባ መናፍቅ አርፈህ ተቀመጥ

 12. fikrte dingle April 2, 2014 at 5:47 am Reply

  የድንግል ልደ የተመሰገነ ይሁን ደስ የሚል ዜና

 13. Anonymous April 2, 2014 at 6:27 am Reply

  ፋክት መጽሔት መረጃ (መረጃቸው ትክክለኛ መሆኑን በሂደት እያየን) መሰጠታቸውን ብቻ ቢቀጥሉ ጥሩ ነው፡፡
  ዕለተ ዓርብን የስቅለት ዕለት ወይንም ምርጫ ዕለት ለዓመጽ ተነሱ የሚለው ጥሪው ግን ፍጹም ፍጹም አልቀበለውም፡፡ ብዙዎችም አንቀበለውም፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳንን የማያውቅ ወይንም የራሱ ዓላማ ያለው ሰው በስሜት የጻፈው ይመስላል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የዓመጽ ማኅበር አይደለም፡፡ ሕግና ደንብ ያለው፤ ምንም ችግርና ፈተና ቢመጣ በሕግ በሥርዓት በቤ/ክንም በሀገርም ህጋዊ መንገዶችና መንገዶች ብቻ የሚታገል ነው፡፡ አባላቱም እንዲህ የተቃኙ መሆናቸውን እኔ ለዓይን ጥቅሻ ሳልጠራጠር እናገራለሁ፡፡ በግለሰብ ደረጃ አንዳንድ ግላዊ እንዲህ ዓይነት ስሜት ሊኖራቸው ቢችል እንኳ ስሜታቸውን እንዳሳዩ ይታረማሉ፡፡ እነርሱም ይሰማሉ፡፡ ይህን እሴት የሰጠን የቅዱሳን አምላክ ይመስገን፡፡
  ይልቁንም በማኅበሩ ስምና ሽፋን አንዳች የዓመጽ ነገር እንዳይኖር ነቅተን እንጠብቃለን፡፡ የሰንበት ት/ቤት አባላትም በመሆናችን በየትኛውም ደረጃ ዓመጽን እንከላከላለን፡፡ ከየትኛውም ጻድቅ አባትና እናት አልተማርነውምና!!!! ስለዚህ ቤ/ክ ውስጥ ያውም በዕለተ ስቅለት ዓመጽ መጥራት ወንጀል ብቻ ሳይሆን ኃጢያትም ነው፡፡
  ምናልባት ፈሪ ትሉኝ ይሆናል፡፡ አዎ! ከቀደሙት አበው ያልወረስነውን መስራት ያስፈራል፡፡፡
  ኃይለ ሥላሴ

 14. Anonymous April 2, 2014 at 8:01 am Reply

  እጅግ በጣም የሚያስደስት ነው ሁላችንም እንተባበራለን በገንዘብ፣ በጉልበት በሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን

 15. Anonymous April 2, 2014 at 9:35 am Reply

  የት ይደርሳል የተባለ ዛፍ ቀበሌ ቆረጠው… ይባል ነበር ድሮ የማከብረውና የምወደው ዳንኤል ክብረት ማኅበራችን ክንፍ አላት ዛፉን ቤ/ክህነት ጥላ ትበራች የሚል ሰምና ወርቅ ቅኔ ጽፎ አስቀየመኝ!!
  እመኒ ሀለየት ከመዝ ወለት ማኅበረቅዱሳን በልዋ፡ ሁሪ ወተፈለጢ፤ወሕንጺ ቤተ ሀዲሰ፡፡አምጣነ ክልኤ አጋእዝት ኢይክሉ ነቢረ በዋህድ ማኅደር!!
  እንዲህ ባታስቡ ጥሩ ነው፡፡ዛፏ አሀቲ መባሉዋን መካድ ነውና፡፡አሀቲነቷም በቃለ ሲኖዶስ ይጸናል፡፡እንግዲህ ከዛፍ ዛፍ መዝለል ካዋጣ ጥሩ ነው፡፡እኛ እንኳ እንዲህ እስከመመካት አትደርሱም፣ትምክህታችሁም ከእምነትና ስርዐት ነው የሚመነጨው ብለን በስስት እያየናችሁ ነበር፡፡እምነት አጎደላችሁ፡፡ቅሬታ እንኳ ቢኖር ለቅ/ሲኖዶስ ይግባኝ ማለት እየተቻለ ፍሬዋን መግባ፣በቅጠሎቿ ጎጇችሁን እንድትሰሩ አድርጋ፣ነውራችሁን እንዳላየች የልጅ ነውር ነው ብላ ስታልፍ የቆየቸውን የ2ሺህ አመት ትክል ዛፍ እንደነ እንትና ክንፍ አውጥተናል ብላችሁ፣ካለእኛ አትኖርም ብላችሁ ታብያችሁ፣ የአባቶቻችሁን ገመና በየጋዜጣውና በየብሎጉ ስትረጩ ኖራችሁና በክንፌ እበራለሁ የማለታችሁ ድርጊት ክህደት ነው፡፡
  ቃል መብላት ነው፡፡በስርዐት ከህግና ከአስተዳደር በታች እደሩ መባል ይሄን ያህል የሚያንገበግብ መሆኑ የአበቃቀል ሳይሆን የአስተዳደግ ችግር ነው፡፡አበቃቀላችሁማ ከተዋሕዶው መዶሻ ከ20ኛው ክ/ዘመን የቤ/ክ መኩሪያ አቡነ ጎርጎርዮስ መሆኑን እናውቃለን፡፡አሁን ለአቅመ አዳም ደርሳችኋል፣ከፊሎቻችሁም ጎልምሳችኋል፡፡ስለዚህ ለድርጊታችሁ ሁሉ እናንተኑ እንሞግታለን እንጅ እኚያን 50 አመት ኖረው የ500 አመት ስራ ትተውልን ያለፉ አባት ስለ እናንተ ግብር አንወቅስም፡፡ስለ በዐላት አከባበርም ሆነ ስለአጽዋማት ቀኖና ቅ/ሲኖዶስ ለመወሰን ሙሉ መብት አለው የሚሉ፣ ቃለሲኖዶስን ትምክህት ያደረጉ አባት ነበሩ፡፡እኚህ አባት ሲኖዶስ ባለበት ምድር የልጆቻቸውን እንበራለን ማለትን ቢያዩ ልጆቼ የሚሏችሁ አይመስለኝም፡፡
  ይገባችኋል፡፡ በጣም እኮ ነው የሚያመው፡፡አባቶች ምንም አይነት የማስተባበል እድል በማያገኙበት ሚዲያ እኮ ነው መያዣ መጨበጫ በሌለው ሀሜት የሚደበደቡት፡፡ማን ሀይ አለ፡፡ባለትዳርና የልጆች አባት የሆኑ አስተዳዳሪዎችና ጸሀፊዎች በስማ በለው ሲብጠለጠሉ ሁሉም እንዳላየ አለፈ፡፡የቻለውም በአስተያየት ስም ጨምሮ አነወራቸው፡፡ዳንኤል አንተ በእንዲህ አይነት ሂደት ውስጥ አልፈሀልና በየብሎጉና ጋዜጣው የሚደረግ የስም ማጥፋት በተጎጂው ላይ የሚያደርሰው ስቃይ ይገባሀል ብየ አስባለሁ፡፡ለስቅለት ሰልፍ ውጡ ተብሎ ሲቀሰቀስ ማን ነውር ነው አለ፡፡ሃይማኖት ከማኅበር ተምታቶ ማኅበር በተነካ ቁጥር ሃይማኖት ተነካ ተብሎ ሲለፈፍ ማን ተግሳጽ ሰጠ፡፡ሲኖዶስ እየተቆረጠ በሚቀጠልባት ሀገር ማኅበርን አትተቹ ማለት እኮ ቅዱስ ነን ለማለት መቃጣት ነው፡፡ልናገር ብትል ውርጅብኝ ነው፡፡ተሀድሶ፣ሙሰኛ፣አማሳኝ፣ጉቦኛ፣መናፍቅ፣ዘረኛ….ስድብ እንደጥይት ጆሮህ እስኪግል ይተኮስብሀል፡፡ይሄ ያማል፡፡ባልሆንከው ሲጠሩህ ያማል፡፡ስያሜ መስጠት እኮ የማሳደድና የግድያ መጀመሪያ ነው፡፡
  ዛሬ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆነው ስለ እነ አቡነ ቶማስ ሊቅነትና መንፈሳዊነት የሚነግሩን ብሎጎች ትናንት እሳቸው በህይወት እያሉ ትንፍሽ አላሉም፡፡እንዲወራልህ ከፈለክ ማውሪያውን ከተቆጣጠሩት መወዳጀት ያልተጻፈ ህግ ስለሆነ እኮ ነው ቀብረን ገድላቸውን መቃብራቸው ላይ የምናወራው፡፡ይሄ ያማል፡፡ሁሌ አባት እንደሌለህ የሚነግርህ ሰው እያጽናናህ ሳይሆን እያሳዘነህ ነው፡፡እኛኮ ላለፉት 20 አመታት እንደዛ ነው የሆነው፡፡ስለ እነ አቡነ ቄርሎስ የድጓ እውቀትና ስብከት፣ስለ እነ አቡነ ያሬድ እና አቡነ እንድርያስ የትርጓሜ መጻህፍት እውቀት፣ስለ እነ አቡነ ማርቆስ ቅኔ በጉንጩ መሆን፣የአሜሪካው አቡነ መልከጼዴቅ በመንፈሳዊ መጻህፍት ህትመት ለኢተ/ቤ/ክ ስላበረከቱት አስተዋጽኦ፣ስለ እነ አቡነ ገሪማ የኢኦተቤክ የውጭ ግንኙነትን ከሩብ ክ/ዘመን በላይ በጫንቃ መሸከም ማን ነገረን፡፡ሰውን በቁሙ ሁለት ጊዜ መግደል ይቻላል፡፡አንድም የሌላውን ስም በመስጠት፣አንድም የሰራውን ሁሉ እውቅና ባለመስጠት፡፡አዝናለሁ፡፡ይሄ ትውልድ ሁለቱንም በደሎች በትጋት እየፈጸማቸው ነው፡፡
  ለማንኛውም ዛፉ ዋርካ ነው፡፡ሰፊ፡፡በግዙፍ ቅርንጫፎቹ ብዙ አእዋፋትን ማስጠለል ይችላል፡፡አሁንም አስጠልሏል፡፡ችግሩ አንዳንድ አእዋፋት የዛፍ እና ወፍ የግንኙነት ህግን ጥሰው ዛፍን በወፍ ህግ እንምራ ማለታቸው ነው፡፡እሱን እንንገራችሁ አይሆንም፡፡ አይደረግም፡፡ከፈለጋችሁ አንዴ ሳይሆን 7 ጊዜ ብረሩ እንጅ ፓትርያርካቸውን የደርግ ሰይፍ በበላበት፣ጳጳሳቱ በየከርቼሌው በታጎሩበት ወቅት በደርግ የይለፍ ወረቀት እየተንቀሳቀሱ ቤ/ክ ሲተክሉ ሲያስተምሩ የነበሩ ሰዎች አቁመው ያከረሙትን ዛፍ ገና ተብላልቶ፣ሰክኖ ላልጠራ የወጣቶች ማኅበር አስረክቡ ማለት ነውር ነው፡፡ባይሆን ተረዳድተን እናጠንክረው፣በቤ/ክ ኮሚቴዎች ተዋቅረን የድርሻችንን እናገልግል ማለት የአባት ነው፡፡
  ይልቅስ ትልቅ ሰው ጠፋ፡፡እውነት እውነት እላችኋለሁ ሰው ጠፋ፡፡አዝናለሁ ዳኒ፡፡ባስቀመጥኩህ ቦታ አላገኘሁህም፡፡የማኅበሩንና የቤ/ክህነቱን አለመግባባት አቀራርቦ ለመፍታት እና ለወደፊቱም ማኅበሩ በተሰጠውና በሚሰጠው መመሪያ መሰረት እንዲሰራ ታላቅ ሚና ይኖርሀል ብየ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ዳዊት ወሶበ እገብእ ሀጣእክዎ ያለውን አርዘሊባኖስ ሆንክብኝና ተሸማቀኩ፡፡እባክህ አሁንም እንዲህ የሚያቀራርብ ሳይሆን የሚያራርቅ ህብረቅኔ በመጻፍ ጉዳዩን ወደ አንድ ጽንፍ ወስዶ ሚዛን ከማሳጣት ካንተ የሚጠበቀውን አድርግ፡፡ቢያነስ አንተ ከሌሎቹ የተሻለ ክብርና ሞገስ በሁለቱም ወገን አለህና፡፡አሁን የምትለውን ተወው፡፡እንዲህ አይነት ጽሁፍ እኮ እንዳንተ በሰም ባይዋዛም በወርቁ እየቀረበ ቃር ቃር እስኪለን እያነበብነው ነው፡፡እሱን ለመድገም አትፋጠን!!ይልቅስ ኅስሳ ለሰላም ወዴግና ለሚለው ቃል ታምነህ የምትችለውን አድርግ፡፡

  • መኑ April 2, 2014 at 11:29 am Reply

   የሚያሳዝነው ደግሞ አንዳንዶቹን ማን እንደሚቆርጣቸውም እይታወቅ፣ ልክ እንደዚህ Anonymous ሰው …. አለመታደል ነው!

  • Anonymous April 2, 2014 at 12:32 pm Reply

   አባታችን ምንኛ እንደመረረዎ ያስታውቃል፡፡ ግን ልጆችዎ ነንና ቻሉን፡፡ እንደ ልጅነቴ አደራ የምልዎት ግን ዲ.ን ዳንኤል ክብረት፣ ወዘተ በግል የሚጻፍ ማንኛውም ነገር ውክልናው የግለሰቡ ነው፡፡ በጣም የሚጨንቀን ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ማኅበር የያዘው አቋም፤ የሰጠው መረጃና መግለጫ፤ የሄደበት ሂደት አስጠያቂ ከሆነ ለምን አይጠየቅም፤ ይጠየቃል እንጂ፡፡ አባቴ ሌሎችም አባቶች የግለሰብን አስተያየትና የማኅበሩን አቋም ግን ለዩ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በየትኛውም የመዋቅሩ ደረጃ እሱን ወክለው መግለጫ የመስጠት ሥልጣን ያላቸውን አካላት የለየና በእርሱ በኩል እንዲሁም በህጋዊ ሚዲያዎቹ ብቻ የሚናገር እንደሆነ ለእርስዎ መንገር አያስልገኝምና አባታችን ምሬትዎትን መለስ አድርጉት፡፡

 16. Anonymous April 2, 2014 at 12:47 pm Reply

  አባታችን ምንኛ እንደመረረዎ ያስታውቃል፡፡ ግን ልጆችዎ ነንና ቻሉን፡፡ እንደ ልጅነቴ አደራ የምልዎት ግን ዲ.ን ዳንኤል ክብረት፣ ወዘተ በግል የሚጻፍ ማንኛውም ነገር ውክልናው የግለሰቡ ነው፡፡ በጣም የሚጨንቀን ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ማኅበር የያዘው አቋም፤ የሰጠው መረጃና መግለጫ፤ የሄደበት ሂደት አስጠያቂ ከሆነ ለምን አይጠየቅም፤ ይጠየቃል እንጂ፡፡
  አባቴ ሌሎችም አባቶች የግለሰብን አስተያየትና የማኅበሩን አቋም ግን ለዩ፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳን በየትኛውም የመዋቅሩ ደረጃ እሱን ወክለው መግለጫ የመስጠት ሥልጣን ያላቸውን አካላት የለየና በእነርሱ በኩል እንዲሁም በህጋዊ ሚዲያዎቹ ብቻ የሚናገር እንደሆነ ለእርስዎ መንገር አያስፈልገኝምና አባታችን ምሬትዎትን መለስ አድርጉት፡፡

 17. Anonymous April 2, 2014 at 12:50 pm Reply

  አባታችን የዲ.ን ዳንኤል ክብረትን ጽሁፍ እርስዎ በተረዱት ተርጉመው የጻፈው ስለ ቤተ ክህነትና ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ነው ብለው መተርጎም ባይከለከሉም እንዲህ እንዲማረሩና በዳንኤል በኩል ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲህ አይረቤ ነውረኛ ማኅበር እስኪሉት መድረስ አልነበረብዎትም፡፡ እስከ ዛሬ አባቶች ተሰደቡ፤ ተዋረዱ፤ ሲኖዶስ ተዘለፈ ወዘተ ያሉት እርስዎም እኛም እርግጠኞች ነን በማኅበረ ቅዱሳን አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት አስተያየት የጻፈልዎ ሰው የሰጠውን ሃሳብ እኔም ስለምጋራው እንዳለ ወስጄ እኔም አስተያየቴ ነው ብያለሁ፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳንን የሚወክለውና የሚያስጠይቀው በደነገጋቸው በደንቡ መሠረት መግለጫ ሲሰጥ፤ በሚዲያዎቹ ሲያሳውቅ፤ በደብዳቤ ስጽፍ እንጂ የማኅበሩ አባልና አመራር የነበረ ግለሰብ በጻፈ ቁጥር ያንን ይዞ ማኅበረ ቅዱሳንን ማጥላላት አባቴ ለእርስዎ ማለት ቢከብደኝም አይገባም፡፡

  ‹‹ አባታችን ምንኛ እንደመረረዎ ያስታውቃል፡፡ ግን ልጆችዎ ነንና ቻሉን፡፡ እንደ ልጅነቴ አደራ የምልዎት ግን ዲ.ን ዳንኤል ክብረት፣ ወዘተ በግል የሚጻፍ ማንኛውም ነገር ውክልናው የግለሰቡ ነው፡፡ በጣም የሚጨንቀን ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ማኅበር የያዘው አቋም፤ የሰጠው መረጃና መግለጫ፤ የሄደበት ሂደት አስጠያቂ ከሆነ ለምን አይጠየቅም፤ ይጠየቃል እንጂ፡፡
  አባቴ ሌሎችም አባቶች የግለሰብን አስተያየትና የማኅበሩን አቋም ግን ለዩ፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳን በየትኛውም የመዋቅሩ ደረጃ እሱን ወክለው መግለጫ የመስጠት ሥልጣን ያላቸውን አካላት የለየና በእነርሱ በኩል እንዲሁም በህጋዊ ሚዲያዎቹ ብቻ የሚናገር እንደሆነ ለእርስዎ መንገር አያስፈልገኝምና አባታችን ምሬትዎትን መለስ አድርጉት፡፡ ››

 18. Girma Sintayehu April 2, 2014 at 3:48 pm Reply

  I agree on this idea

 19. aba berehane selassa asefewe April 2, 2014 at 6:40 pm Reply

  1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
  1፥10
  ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።

 20. aba berehane selassa asefewe April 2, 2014 at 6:41 pm Reply

  ወደ ገላትያ ሰዎች
  5፥21
  መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

 21. adonay April 9, 2014 at 9:34 am Reply

  aye yehece mahebare lanagaru yasumaleya gorabate ayedalachu alekayeda alesababene fatara enanetame gen esekamaca batame yamegaremawe hezebu hulune nagar gata selagalatalate masemeya yalaweme.ato tamasegane lala yaletamokara sestam falege manegest endahone antane yameyastawesebate time yalaweme macame matasare enedamarahe yekarale.hezeba keresteyanu enkuan yanetan alama leyasaka gatawen yameyamalkebate time ayebakaweme enedamarahe yekarale.;

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: