አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት የፈረጁበት ስብሰባና መግለጫ ሊቃነ ጳጳሳቱን አስቆጣ

 • ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል
 • የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉና በጀቷን አውጥታ እያስተማረቻቸው የሌላ እምነት በሚያራምዱ የስም ደቀ መዛሙርት ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፵፩፤ መጋቢት ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

Admas logoየኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ በማስተባበር ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት በመፈረጅ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ጠቅላላ ሀብቱና ንብረቱ የሚታገድበት ውሳኔ እንዲተላለፍ በመንግሥትም በኩል እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአድባራት አስተዳዳሪዎች መግለጫ አውጥተውበታል በተባለው ስብሰባ ጉዳይ ኹለት ሊቃነ ጳጳሳት ለከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ፡፡

የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን በስም የጠቀሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች እንደኾነ ቢገልጹም የሓላፊዎቹን ስም ከማሳወቅ ተቆጥበዋል፡፡

Lukas

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በክልል ትግራይ የምዕራብ ሰቲት ሑመራ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ቤተ ክርስቲያኒቱ በፀረ ሙስናና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከመንግሥት ጋራ የተጠናከረ ሥራ ለመሥራት በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መወሰኗን ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰው፣ በዚህም መሠረት ለሙስናና ብክነት የተጋለጡ አሠራሮችን ለማረምና ለማስተካከል ጥረት እያደረገች ቢኾንም ባለሥልጣናቱ ከማን ጋራ መሥራት እንዳለባቸው በትክክል አለመለየታቸውንና ግንኙነቱም አማሳኞችን በአይዟችኹ ባይነት የሚያበረታታ እንደኾነ መናገራቸው ተጠቅሷል፡፡

ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን በዚህ መልኩ ለባለሥልጣናቱ ለማቅረብ ያስገደዳቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎቹ፣ ‹‹ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ለአድማ ያነሣሣል፤ በሀገርና በቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከትና ሽብር እንዲፈጠርና ሰላም እንዲደፈርስ ያደርጋል›› ባሉት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊ ርምጃ በፀረ ሽብር ሕጉ መሠረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁበት መግለጫቸው ነው፡፡

የመንግሥት የተለመደ እገዛ እንዳላቸው በአጽንዖት የጠቀሱት አስተዳዳሪዎቹ በዚኹ መግለጫቸው፣ መንግሥት በፀረ ሽብር ሕጉ ታሳቢነት ገለልተኛ ኦዲተር መድቦ በማኅበሩ ላይ የሀብትና ንብረት ቁጥጥር የማካሔድ ድጋፉ እንዳይለያቸው ያስተላለፉት ጥሪ በሌላቸው ሕጋዊነትና ውክልና የቀረበ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በራስዋ መንገድ ማከናወን በሚገባት ተግባር ላይ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነትን የሚጋብዝና ለውጭ ተጽዕኖ አሳልፎ የሚሰጥ እንደኾነ ተመልክቷል፡፡

በመንበረ ፓትርያርኩ ከተገኙት የመንግሥት ሓላፊዎች ጋራ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እንደተካሔደ በተገለጸው የኹለትዮሽ ውይይት፣ ማኅበረ ቅዱሳንን በመቃወም አድርጎ (በመቃወም ሰበብ) የወጣው የአስተዳዳሪዎቹ መግለጫ ዋነኛ ዓላማ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ወስና የምታካሒደውን የመዋቅር የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ሒደት መጋፋት ነው ተብሏል፡፡

መላውን የሀገረ ስብከቱን አድባራት ለመወከል የማይበቁ ጥቂት ግለሰቦችን በመያዝ ይደረጋል የተባለው ይኸው ተቋማዊ ለውጡን ኾነ ብሎ የመጋፋት እንቅስቃሴም ‹‹የት እንደሚያደርስ እናየዋለን!›› የሚሉ ንግግሮች ጭምር ከሊቃነ ጳጳሳቱ የተሰሙበት እንደነበር ምንጮቹ አስታውቀዋል፤ ጉዳዩም በመጪው ግንቦት በሚካሔደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዓቢይ መነጋገርያ መኾኑ እንደማይቀር ጠቁመዋል፡፡

ከሀገረ ስብከቱ አድባራት የተውጣጡ ናቸው የተባሉ አስተዳዳሪዎች ያደረጉት ስብሰባ፣ አስተባባሪዎቹ ከፓትርያርኩ ተሰጥቶናል ከሚሉት ፈቃድ በቀር በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ዘንድ በይፋ የታወቀና የተፈቀደ እንዳልነበረ ምንጮቹ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳንን በሁከትና ሽብር ለሚከሱ በቂ ሕጋዊነትና ውክልና የላቸውም ለተባሉ አካላት ፓትርያርኩ የሰጡትን የስብሰባ ፈቃድ፣ በቅርቡ ማኅበሩ ከፍተኛ ፋይዳ ያለውን ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ እንዳያካሒድ ከተጣለበት እገዳ ጋራ ያነፃፀሩ ታዛቢዎች፣ ኹኔታው የፓትርያርኩን ርምጃዎች መርሕ አልባነት የሚያጋልጥ ነው ይላሉ፡፡ ከዚኽም ባሻገር መተዳደርያ ደንብ ያለውና ግልጽ ተልእኮ ይዞ የሚንቀሳቀሰው ማኅበር ህልውናና አገልግሎት በግልጽ አስተዳደራዊ ጫና ውስጥ መግባቱን እንደሚያመለክት ታዛቢዎቹ ያምናሉ፡፡

ከመዋቅር፣ ከሀብትና ንብረት ቁጥጥር ጋራ በተያያዘ በማኅበሩ ላይ የሚቀርቡት ውንጀላዎች፣ በፀረ አክራሪነት ስም የሚናፈስበትን ፕሮፓጋንዳ በማጠናከር ፖሊቲካዊ ርምጃ እንዲወሰድበት ፍላጎት ያላቸውን አካላት ምኞት በጉልሕ እንደሚያሳይ አስረድተዋል፡፡ ማኅበሩ ሃይማኖቱን የሚጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያኑን የሚከባከብና ሀገሩን የሚወድ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ያለውን ዓላማ የሚረዱ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናንና የመንግሥት አካላትም የተቃዋሚዎቹን አቋምና መግለጫ በጥንቃቄ እንዲመለከቱትም አሳስበዋል፡፡

Emblem of Holy Trinity Theological collegeበሌላ በኩል፣ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖናና ትውፊት ውጭ ነው በተባለ የሌላ እምነት አስተምህሮ ምክንያት በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት መካከልና በደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት አባላት ውስጥ ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ እንደገባ እየተገለጸ ነው፡፡

ከኮሌጁ ውጭ ከሚገኙና በቅ/ሲኖዶስ ከተወገዙ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋራ የዓላማና የጥቅም ግንኙነት መሥርተዋል በተባሉ ጥቂት ደቀ መዛሙርት አማካይነት በኮሌጁ ውስጥ ከመንጸባረቅ አልፎ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው የተባለው ይኸው የኑፋቄ አስተምህሮ፣ አስተዳደራዊ መፍትሔ እንዲበጅለት የደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት ጥር 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ለኮሌጁ አስተዳደር ያቀረበው ጥያቄ እስከ አሁን ምላሽ አለመሰጠቱ ውጥረቱን የበለጠ እንዳባባሰው ለአዲስ አድማስ የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡

የአስተምህሮው ውዝግብ አፋጣኝ መፍትሔ አለማግኘቱ ከደቀ መዛሙርቱ አልፎ የደቀ መዛሙርቱን ምክር ቤት አባላት ለሁለት እንደከፈለ ተገልጧል፡፡ ኮሌጁንና ደቀ መዛሙርቱን በቅንነትና በትጋት ለማገልገል በደቀ መዛሙርቱ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠውና ከፍተኛ ሓላፊነት የተጣለበት የደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት ‹‹ከልማቱ ጥፋቱ አመዝኗል›› ያሉት ጸሐፊውና አንድ የአመራር አባሉም ራሳቸውን ማግለላቸው ታውቋል፡፡

‹‹ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናና ትውፊት ውጭ የኾነ የኑፋቄ ትምህርት ሲዘራ ድምፀ ተዓቅቦ ከማድረግ ባሻገር ችግር አለባቸው ከሚባሉት ደቀ መዛሙርት ጎን ተሰልፈው ኮሌጁንም ኾነ ሓላፊነት የሰጠንን ደቀ መዝሙር በቅንነት እንዳናገለግል የአንዳንድ መማክርት አባላት ተግባር አግራሞትን ፈጥሮብናል›› ያሉት ሁለቱ አባላት፣ በዚህ ሳምንት ለኮሌጁ ዋና ዲን ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣ ምክር ቤቱ የችግሩ ተባባሪ በመኾኑ ከሓላፊነቱ ታግዶ ጉዳዩ እንዲጣራና እምነታቸውና ሥነ ምግባራቸው በተመሰከረላቸው ደቀ መዛሙርት እንዲተካ ጠይቀዋል፡፡

‹‹የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉና በጀቷን አውጥታ እያስተማረቻቸው የሌላ እምነት የሚያራምዱ›› ያሏቸውን አጥብቀው እንደሚቃወሙ የገለጹ የደቀ መዛሙርት ተወካዮች በበኩላቸው፣ ኮሌጁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ለመጠበቅና ለማስፋፋት ከየአህጉረ ስብከታቸው ተልከው የመጡበት በመኾኑ አስተዳደሩ ኹኔታውን አስመልክቶ በቃል፣ በድምፅና በጽሑፍ የሚቀርቡለትን ማስረጃዎች መርምሮ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል፡፡Letter of Holy Trinity Theological college disciple's council to the adminLetter of Holy Trinity Theological college disciple's council to the admin00

Advertisements

38 thoughts on “አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት የፈረጁበት ስብሰባና መግለጫ ሊቃነ ጳጳሳቱን አስቆጣ

 1. Anonymous March 31, 2014 at 8:45 am Reply

  በአይናችን ያየነውና የምናየው፤ በታሪክም የምናውቀው ፤ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ፤ በአላማም ሆነ በሌላ… የቤተክርስቲያኗ ነቀርሳ የሚሆኑ /የመንግስት ሹመኛ፣ ‘የእኛ’ና የሌላ አምላኪ/ መኖራቸው ምንጊዜም ሃቅ ነው። …. በፈተናው መጽናት እንጂ አያስረብሽም!

  ከሁሉ ግን፤ ለመንግስት የመረጋጋትና ማስተዋል (7x)ልብን ይስጥልን።

  ለቤ/ክርስቲያናችን የሚቆሙላት አባቶችን፤ ወንድሞችንና፤ እህቶችን እግዚአብሔር አያሳጣን::

  ዳላስ፣ ቴክሳስ

 2. Lemlem March 31, 2014 at 11:52 am Reply

  እመቤታችን ማርያም ማህበራችንን ጠብቂልን በምልጃሽ . . . .

 3. Anonymous March 31, 2014 at 12:39 pm Reply

  እግዚአብሔር አባቶቻችንንነ ያበርታልን ቤተክርስቲን ከነ ሥርዓቷ እንድትቀጥል ሁላችንም ልንፀልይ ይገባለናል…

  • Anonymous April 1, 2014 at 12:34 am Reply

   አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት የፈረጁበት ስብሰባና መግለጫ ሊቃነ ጳጳሳቱን አስቆጣ

   Brother, would you please read these letters from sunday school department website? http://www.eotcssd.org/ .

   Your brother “Abune Mathious ” is also collaborating and running against MK.PERIOD!

   He wrote and circulate three important letters against MK, Read it please and tell us now the reason why Mathios wrote these letters.

   DONOT HIDE THE TRUTH, NO ONE FROM THE CHURCH WILL STAND IN YOUR SIDE, BELIEVE ME. Your members including ” Your archbishops’ email and phone conversation are under the controlled.

   A very strong intelligence work has already done. WHO IS DOING WHAT WITH WHOM AGAINST THE CHURCH AND THE GOVERNMENT OF ETHIOPIA WILL BE DISCLOSED IN THE UPCOMING WEEKS, AND OFCOURSE MK AND MAFIYA GROUP WILL PAY FOR IT.

   You KILLED our church’s FATHERS (ABUNE PAULOS, ABUNE MEREHAKIRSTOS, MEGABIBILUY SEIFESELASSIE & A BUNCH OF CLERGIES.

   Ewinetu Sigelet

   • Anonymous April 1, 2014 at 9:55 am

    ፈሳም መናፍቅ ልብ ይስጥህ

   • WEB April 1, 2014 at 7:53 pm

    I never read http://www.eotcssd.org/ .when I follow your link, I see that it is direct copy of Abaselama.org. Yigermal.

   • Anonymous April 3, 2014 at 1:44 pm

    hey Mr WEB, the issue is not where it was discovered!!just focus on the truthfulness of the content!!sometimes even the devil tells the truth,as he witnessed JESUS CHRIST as a SON OF GOD!!denying the fact by resorting 2 z evilness of z link is fallacious!!

 4. Teshale March 31, 2014 at 5:51 pm Reply

  የባሰ አታምጣ ከዚህ በላይ
  አሳልፈናል ብዙ ሳቃይ
  ያየነው ይብቃን አምላካችን
  ለሌላው ሸክም አቅም የለን።

 5. Anonymous March 31, 2014 at 7:03 pm Reply

  Aba Lukas and aba Estifanos! we know you very well than you know yourself. enough is enough. you have been misleading our people by wearing the holy dress of our real fathers. Mk is a number one enemy of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church and he has been killing a lot of innocence scholars ,no one can pay any attention for your cry. if you really need to scab from this you have to admit your mistake and surrender to the church. and you have obey to the church and abide by the law of the church. let me tell you this, maybe you can run for a while but you cannot get any bush to hide yourself, time for repentance is running out please repent and return to the truth.
  Abba LUKAS ! Abba Estifanos shame on you, wait you will get your wage \

  • Anonymous March 31, 2014 at 7:22 pm Reply

   አሜሪካ ተደብቀህ አትጩህ መናፍቅ

  • Anonymous March 31, 2014 at 7:29 pm Reply

   seem stupid,

  • Anonymous March 31, 2014 at 9:40 pm Reply

   What a shameful comment!

  • aslvis April 1, 2014 at 6:28 am Reply

   Hhe : Krstiyan yemaymesl sewu :Anonymous: bemil sm yetsafe hulu Krstiyan aydelem : mnalbatm enem bhon ::: So you don’t need to replay back unnecessary words. Cos you make your own ensconce dirty. please, forget the negativity, which has not enough evidence for his / her negative thoughts.

  • Anonymous April 1, 2014 at 8:31 am Reply

   You are stupid !It doesn’t surprise to hear such a stupid and idiot idea from Menafik!!!!

 6. Anonymous March 31, 2014 at 9:22 pm Reply

  ende anteee demo maneh bakihhhh…..,mk endew atefa enkuwan bibal deg siraw silemibelit minim tifat yelebetim,,,,manew tiwulidun hayimanotun tenkikko endiyawuk yaderegew..esti wetat ehit ena wendimochin teyikachew university kegebahu new bedenib silehaimanote yawekut eko new yemilihhhh endee……esti sra bota hid musina yemayibelu lijochi yemanachew’???????????esti muslim bewererachew yegeter abiyatekrstiyanat hid manew yaskefetachew ere manew manew eza yalutin tikit chrsstianochi alen ayizuachu bilo yasinanaw,,,,,ante tegadimeh afihin tikefitaleh ende eee mejemerya mk manew bileh meteyek alebihhhh?????????

 7. Anonymous March 31, 2014 at 10:12 pm Reply

  Egziabher Amelake mehaberachenen yetebekelen le kerstyanoch hule geze kenu Areb new selzeh befetena yesena ersu yesenale.

 8. Anonymous April 1, 2014 at 5:27 am Reply

  Abatochin yemizelfe andebet kewedet endehone bezihe nigigre yastawikal. yeseyitan ashker kemehone nisiha megibatina memelese yemigebahe yihine yetenagerke sew nehe. Fetari libona yisthe!

  • Anonymous April 1, 2014 at 3:01 pm Reply

   Ke MK temiro yihonala, Ke Ahiya gar yewale fes yilemidal

 9. Anonymous April 1, 2014 at 6:51 am Reply

  you know them more than they know themselves??????? …. what an embarrassment are you? … better if you go and take your meds!!

 10. Anonymous April 1, 2014 at 7:20 am Reply

  theis is the real sound of diabilos.

 11. በአማን ነጸረ April 1, 2014 at 7:32 am Reply

  ዘሱቱኤል የተባለ የጥንት ባለቅኔ በድምጸ-ብዙኃን መታገት ቢያንገበግበው እንዲህ አለ፡
  ማእከለ አራዊት ንኬልህ ወአልቦ ዘይሰምአነ፣
  እስመ አራዊት ይበዝሁ እምኔነ!!
  1. እናንት የማኅበረቅዱሳን አመራሮች፡ ኢቲቪን ለመክሰስ አደባባይ ስትወጡ ይገርመኛል፡፡በቤ/ክ ዙሪያ በሚሰሩ የኢቲቪ ዶክመንተሪዎች እኮ ከእናንተ አባላት ውጭ ሰው አይተን አናውቅም፡፡ስለባህላዊ እጸዋቱም፣ስለአብነት ትምህርት አሰጣጥም፣ስለበዐላትም፣ስለታሪክም፣ስለመቻቻልም ቤ/ክ ሊቃውንት የሌሉዋት እስኪመስል ድረስ በግቢ ጉባኤ ቆይታ ቅዳሜና እሑድ የወሰዳችሁዋቸውን ኮርሶች ስትናገሩ እየሰማን እንዳልሰማን፣እያየን እንዳላየን አለፍን፡፡የኢቲቪ ጋዜጠኞችን ምነው ሰው ታጣና የስንት ሊቃውንት እናት ቤ/ክ በየጊዜው በነዲያቆን እከሌ ብቻ የምትወከል ብንል ሊቃውንቱ ሚዲያ አይወዱም፤እነዲያቆን እከሌ ግን በቀላሉ ማግኘት ስለሚቻል ነው አሉን፡፡ዝም አልን፡፡ሁኔታው ቀጠለ፡፡ዝም አልን፡፡መጨረሻ ቀና ብንል ማሊያ ቀይራችሁ ከማኅበረቅዱሳን አመራር ወዲያ ሊቅ ላሳር፣ቤ/ክ ያለማኅበሩ ኦና ናት፣ማኅበሩ ባልተፈጠረበት ዘመን ቤ/ክንን ያን ሁሉ መከራ ተሸክሞ ለዚህ ማብቃቱ ተረስቶ ቤተክህነቶቹማ ሊሸጡዋት ሲደራደሩ ነበር እየተባለ ይዘፈናል፡፡ግሩም!!የግሩም ግሩም!!
  2. በአናቱም ጳጳስ እንጅ ሃይማኖትና ስርዐት ያላዋሰችን የግብጽ ኮፕት ቅኔና ዜማ ስለሌላት እሱን ትተን ልክ እንደሷ በግቢ ጉባኤ ኮርስ ቤ/ክ መምራት ማለት ዘመኑን መዋጀት ነው ተባልን፡፡እና ሰው እንደቤቱ እንጅ እንደጎረቤቱ አይኖርም፤በዚህ ላይ ያለ ዝማሬ-ያሬድና ያለ ምስጢረ-ቅኔ ቤ/ክ ምኑን ቤ/ክ ሆነች፤እንደገና በዚህም ላይ ግብጾች እንደእናንተ አድገው ጎልመሰው ዲግሪ ከጫኑ በሁዋላ በ30 እና በ40 አመታቸው ዲቁና እየተቀበሉ ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ ጎን ለጎን መንፈሳዊ ት/ት ሲማሩ ከቆዩ በኋላ በትንሹ 10 አመት በቲዎሎጅ ትምህርትና ገዳም ወርደው በትህርምት ካሳለፉ በሁዋላ ነው የቤ/ክ አመራር ላይ የሚወጡት፣በዚህ መስፈርት ከሄድን ደግሞ በ20 አመት ከአንድ እጅ ጣት የማይበልጡ ግለሰቦች ስላፈነገጡ ብቻ በሺህ የሚቆጠሩ ትጉሃን ምሩቃንን ደምራችሁ በመናፍቅ መፈልፈያነት የምትከሱዋቸው መንፈሳዊ ኮሌጆች ናቸው አመራሩን ይረከቡ ቢባል የሚያምርባቸው ብንልም ማን ሰምቶ!!ሆ በል ሲሉ ሆ ማለት ሆነ!!
  3. ማኅበራዊ ሚዲያ ከግል ፕሬስ ገጥሞ ጨሰ አቡዋራው ጨሰ ይላል!!አሁንም ልድገምላችሁ ከባዮሎጅ እና ኬሚስትሪ ጎን ለጎን በትርፍ ጊዜያቸው ቅዳሜና እሁድ በወሰዱት ኮርስ ቤ/ክ እንምራ የሚሉ ካሉ ተሳስተዋል፡፡ባይሆን እንደ ምዕመን ወኪል ወይም እንደ ሰ/ተማሪ ሰ/ጉባኤ ተመርጠው በዛ በኩል በውሳኔ ሰጭነት ይሳተፉ ቢባል ያስኬዳል፡፡ከዚህ ውጭ እንሁን ማለት ግን አንድም በዲያስፖራው ቤ/ክ ህግና ስርዐት ጥሶ ዐውደምህረቱን የፖለቲካ መናኸሪያ ያደረገውን ቦርድ የሚባል ካድሬያዊ አደረጃጀት ለማምጣት መጣር ነው እንዲያም ሲል እንደመናፍቃኑ ሽማግሌ ተብየ ተነታራኪዎች በየቀኑ እየተነታረከ ቤ/ክ እንደ መርካቶ ሽንሽን ሱቅ የሚከፍል ቡድን መፍጠር ነው፡፡በነገራችን ላይ ቤ/ክ ምትመራበት ቃለዐዋዲ ለሰ/ት/ቤት ካልሆነ በቀር ለማኅበር ተብሎ የወጣ ድንጋጌ የለውም፡፡ማኅበረቅዱሳን የተቋቋመው በመመሪያ እንጅ በቃለዐዋዲ አይደለም፡፡እዚህ የምንሰማው ግን ሌላ ነው፡፡
  4. በወዲያኛው ወገን ያለው ድምጽ እንዲሰማ አይፈለግም፡፡ምክንያቱም ይህ የሳጥናኤልና የሚካኤል ሰራዊት ጦርነት ነው ተብሎ ታውጇል፡፡ነገር ግን ትግሉ ከሕግና ከሥርዐት በታች ማደር አለበት በሚሉ ወገኖችና የለም ለሌላው ሕግ አወጣለሁ እንጅ ለኔማ ምን የቆረጠው ነው በሚል አካል መሀል የሚደረግ ነበር፡፡በጥፋታቸው ይወዳደሩ ከተባለም አማሳኞች ተብለው ከፍርድ በፊት ስም የወጣላቸው ወገኖች የፈጸሙት ጥፋት ከማኅበሩ ቡድናዊ ጥፋቶች አይብስም ነበር፡፡ለዚህ ሳይሆን ይቀራል መጽሐፍ “ወክልኤቱ ይሰድድዎሙ ለእልፍ” እንዳለው በጥቂት ግለሰቦች ማኅበሩ እንዲሕ የሚሸበረው!!ግዴለም ልሳን አለን ብላችሁ አባቶችን በጽርፈት አታንሱ፣ወደላይ አያድጣችሁ አልን፣ሚዛናዊ ዘገባ አቅርቡ ያለበለዚያ ውሸታሙ እረኛ መሆን ይመጣል አልን፣ማን ሰምቶ!!ማን አጣርቶ!!ጠረፍና ጠረፍ፣ዳር እና ዳር፣አንዳንዴም ከባህር ወዲህና ባህር ማዶ ሆኖ ባላዩት ባልሰሙት ማኅበሩ ያለውን ብቻ ይዞ ማስተጋባት ሆነ!!ይሄው አሁን የፈለጋችሁትን ዶሴ በየኢንተርኔቱ ብትለቁ ቁብ የማይሰጠው ልቡ የደነደነ ቤ/ክህነት በራሳችሁ ላይ አቆማችሁ፡፡አሁንም እናርም ካልን ግን አልረፈደም!!ሁሉም ይደርሳል!!

  • Anonymous April 1, 2014 at 9:58 am Reply

   ስምህን አሳምረህ ግብርህ የዳቢሎስ

  • Anonymous April 1, 2014 at 2:21 pm Reply

   I am ashamed on u. Do not see short duration benefit from the church. U are running for benefit and power by the name of church.

  • WEB April 1, 2014 at 7:59 pm Reply

   በአማን ነጸረ, I thought you are the truth chirstian, but no happy with MK for some reason. Now I see you are from the other side. Please do something to save your church not to distroy your religion. Forget about MK. It is just one ‘mahiber’ which is doing its part. The church can survive without MK, and MK members are just doing their part for their just donating their money and time. Who is doing this kind of sacrification nowdays, except critizing. MK members take all those critics because they are doing something. Nobody critize me and you because we are not doing anything. Let me say it again, if you are a true christian think about your church and your religion!!!!

 12. በአማን ነጸረ April 1, 2014 at 7:38 am Reply

  5. የማኅበሩን አመራር በዘረኝነትና ለተቃዋሚ በመወገን አዝማሚያ እንዳየው የሚያደርጉኝ ተጨማሪ ምክንያቶች፡
  ሀ – እንደ ተቋም የሚተላለፉ የቤ/ክህነት ውሳኔዎችን የጥቂት ገዢው ፓርቲ ድጋፍ ያላቸውና የአንድ አካባቢ ተወላጅ ግለሰቦች በማስመሰል ቲተራቸውን ያሳረፉትንና ከቢሯቸው ደብዳቤው ተፈርሞ የወጣውን የጠ/ቤ/ክህነት ስ/አስኪያጅ የሆኑ ብጹእ አባት አብዛኞቹ የማኅበሩ ስ/አስፈጻሚ አባላት ከተገኙበት ሀገር ስለተወለዱ ብቻ ይመስላል በጠባብ መድፌ አሾልኮ ለማሳለፍ የሚካሄደው ጥረት ጉዳዩ ሌላ አጸፋዊ ዘረኝነት በውስጡ እንዳለ ያሳያል፡፡በማኅበሩ ብዙ ማስታወቂያ በተሰራለት የአ/አ/ሀ/ስብከት መዋቅራዊ ጥናት የሽግግር ወቅት ስ/አስኪያጅ በነበሩት ግለሰብ ከ50 በላይ አባወራዎች ከስራቸው ላይ ተፈናቅለው በአየር ላይ ሲንሳፈፉ ሁሉም እንዳላየ አለፈ፣በጥናቱ መቅድምነት የመጡት የወረዳ ስ/አስኪያጆች በጠራራ ፀሀይ ካህኑን አሰልፈው ሲዘርፉት ከአንድ በላተኛ ወደ 7 በላተኛ ካለው ዳንኤል ክብረት ውጭ ሀይ ያለ የለም፣ከዛ በፊት ደግሞ ንቡረዕድ ገ/ማርያም የተባሉ አባት ሙስናን ለመዋጋት ጉረሮ ለጉረሮ የመያያዝ ያህል ትንቅንቅ ሲያደርጉ ማኅበሩ እንዳላየ ነበር ያለፋቸው ምንአልባት መወለድ የሌለባቸው ቦታ ስለተወለዱ ይሆናል፣ማኅበሩ አቀረብኩት ለሚለው ጥናት እንደመሸጋገሪያ አገልግሏል በተባለውና ሊቀአእላፍ በላይ መኮነን ከመምጣታቸው በፊት የነበረው ጊዜ ካህናት እንደባሪያ ተፈነገልንበት ያሉበት ወቅት ነበር፡፡ሆኖም ያንን ገሀድ ማውጣት የማኅበሩን ዐላማ ያሰናክላል፣ለማኅበሩ ሽፋን የሰጡትንም አባት ያስወቅሳል በዚያውም ላይ የተነካው የምስኪን ካህናት የስራ ዋስትና እንጅ የማኅበሩ ጥቅም አይደለም ተብሎ ነው መሰለኝ ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሎ ታልፎ ይሄው እነ ቀሲስ በላይ አንዴ በኮሚቴ ሌላ ጊዜ በአጣሪ ቢሉ የማያልቅ መዝገብ ሆኖባቸው መከራ ያያሉ፡፡የሚያሳዝነው ያንን ውዥንብር ለማጥራት ደፋ ቀና የሚሉት እነ ቀሲስ በላይ የሚነገርላቸው ለቤ/ክ መልካም አስተዳደር ያደረጉት አስተዋጽኦ ሳይሆን የኦህዴድ አባል መሆናቸው ነው፡፡
  ለ – ከመንግሥት አይስማማም ያሉትን ሁሉ ዓላማው ምንም ይሁን ምን ዘለው ማቀፍ ከሚቀናቸው የስመ – ነጻ ሚዲያዎች ማኅበሩ ያለው አጉል ቁርኝት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡አይጠቅምም፡፡ፕሬሶቹ ፌስቡክ ላይ እንጅ መሬት ላይ እግራቸውን አልተከሉም፡፡ስለዚህ ማኅበሩ እነሱን ለመመርኮዝ ከመጣር ቀጥተኛውን የቤ/ክህነት መስመር ተጠቅሞ ያለመታከት ለማስረዳት ቢሞክር ጥሩ ነበር፡፡አልሆነም፡፡በትህዝርቱ ታውሮ ራሱን ድመት ሌላውን አይጥ ማለት ጀምሯል፡፡ከ40 ሚሊዮን በላይ ምዕመናን እና ከ500ሺህ በላይ ካህናት ባሏት ቤ/ክ ራሷ ቤ/ከ ስመወልድና ሀብተ ክርስትና የሰጠቻቸውን ታዳጊ ከተማ ቀመስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተይዞ ሕዝብ ሆነናል እየተባለ ቤ/ክህነትንና መንግስትን ለማስፈራራት ሲሞከር እያየን ነው፡፡ዳሩ የፈራ ባይኖርም!!
  ሐ. በዚህ መሀል ማኅበሩ ውስጥ እረ ተው እንስከን እናስተውል የሚል መጥፋቱ ሌላው አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ለስንት የጠበቅናቸው ነባር አባላቱ ጉዳዩን ከፖለቲካ አቅጣጫ ብቻ በማየት ሃይማኖት እና አይማኖት እያሉ በቃላት ጨዋታ ራሳቸውን ያሞኛሉ፡፡ከፊሉም በመጽሐፋቸው የአሁኑ ደቡቡ የኢ/ያ ክፍል ወደ ሌላ ሃይማኖት ሂዶ ቀረው የግብጽ ጳጳሳት መምጣት በተቋረጠበት ዘመን ካህን ስለጠፋ መሆኑን ነግረውን ሲያበቁ ተገልብጠው ደግሞ ያለ ኢ/ዊ ጳጳስ የኖርንበትን ጊዜ መናፈቅ ጀምረዋል፡፡አዳዲስ የዋሃን አባላቱም ከእነሱ የተለየ ሀሳብ በሰሙ ቁጥር የሚወረውሩት ስድብ ማኅበሩ ሲያስታጥቅ የኖረው እውቀትንና ትህትናን ነው ወይስ ስድብና ትእቢትን እንድንል እያደረገን ነው፡፡በዛኛው አንጻር ስላለው ቅሬታ ጋዜጦቹም አያነሱም፤ አባላቱም መስማት አይፈልጉም፡፡አበሳውን ሁሉ እንደ ኦሪቱ የማስተስረያ ፍየል በቤ/ክህነትና በመንግስት ላይ መደፍደፍ ብቻ!!
  መ – ከማኅበሩ አገልግሎታቸውን ጨርሰው የተሰናበቱ የአመራር አባላት በብዛት በየግል ፕሬሱ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጽሁፎችን በማበርከት ሲሳተፉ እናያለን፡፡እሱ መብታቸው ነው፡፡ግን እኛም ከእነሱ አቋም ተነስተን ማኅበሩ አሸባሪ ነው ብለን ማስረጃ ያልቀረበበት ወሬ ባናወራም የማኅበረቅዱሳን አመራር አባላት መንግሥትን የመቃወም አዝማሚያ አላቸው የማለት መብት አለን፡፡በየማኅበራዊ ሚዲያው ያለው አንባቢም እረ እስኪ ጋዜጦችንና ብሎጎችን ትተን የራሱን የማኅበረቅዱሳንን ገጸ-ድር እንይ እንዳይል በዋናው ገጸ-ድር መረጃዎችን ማውጣት ያስመታናል ተብሎ ነው መሰለኝ ማኅበሩ በእጅ አዙር መንግስትንና ቤ/ክህነትን በአንድ ድንጋይ ለመምታት ያሥችለኛል የሚለውን ነውጥ አንጋሽ ሚዲያ ለመጠቀም እየሞከረ ነው፡፡በየጋዜጣው አምድና የባለቤትነት ድርሻ የያዙት ነባር የማኅበሩ አመራሮች ይሄን ዘመቻ ለማስፈጸም ተልእኮአቸውን የወሰዱ ይመስላሉ፡፡ከወትሮም አሰፍስፈው የሚጠብቋችው የከተማ አናብስቱ የተቃዋሚው ጎራ ሰዎች ገና ከወዲሁ ለአቀባበል የተዘጋጁ እስኪመስሉ ድረስ አታሞ እየደለቁ ነው፡፡
  ሠ – ቤ/ክህነቱን አንድ ብሄር የተንሰራፋበት ማስመሰል፣በፖለቲካ ወገንተኛነት መክሰስ፣ከማኅበሩ አባል ውጭ በኢቲቪ የታየ የቤ/ክህነት ሰው ሁሉ ካድሬ ነው ብሎ ማስወራት፣የሙስሊም አክራሪነት አለ ብሎ ቀድሞ ጽፎ አክራሪነቱን ለመቃወም ሰልፍ ሲጠራ አይ መንግስት ለፖለቲካው ያደረገው ነው ማሰኘት፣በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቤ/ክህነቱ የመሀይምናንና የካድሬዎች ስብስብ እንደሆነ በመስበክ የምዕመኑን አመኔታ ለማሳጣት መሞከር፣እንደዋልድባ አይነት ቤ/ክህነቱንና መንግስትን የሚያገናኙ ጉዳዮች ሲፈጠሩ ቤ/ክህነቱ እንደተቋም ያለውን አቋም እስኪገልጽ ከመጠበቅ ይልቅ ጉዳዩን እያጎኑ ራስን ማሻሻጫ ማድረግ፣የቤ/ክህነት ሰዎች ከመንግስት መቀራረብን ለቤ/ክ ከሚያመጣው ጥቅም ይልቅ ሁሌ እኔ ላይ እያሴሩ ነው ብሎ በስም ማጥፋት ዘመቻ ማሳደድ፣በቤተክህነት በራሱና ከሌሎች መንግስታዊ የሆኑና ያልሆኑ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ተጠቃሚ የሆነባቸውን ፕሮጀክቶቹን ትተን 6ሺህ ህጻናትና አረጋውያንን በቋሚነት የሚረዳውን የተራድኦ ኮሚሽንና የ300 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ሆነውን የአክሱም ወመዘክር እንዲሁም በአዲስአበባና በየክልሉ የሚካሄዱ ዘርፈብዙ የልማት ተግባራትን እንዳልተደረጉ ቆጥሮ የማኅበሩን ስራዎች ግን ከጣራ በላይ በማጮህ በልማቱ ዘርፍ ከቤ/ክንም አልፈን ከመንግሥት ጋር እንወዳደራለን እስከማለት የደረሰ በተርእዮ የተሞላ እብሪት ማኅበሩን በጠዋቱ ወደመቀሰፊያውና ወደ መሰዊያው እየጎተተው ነው፡፡የማያድግ ልጅ ካንገቱ ይረዝማል እንደሚባለው መሆኑ ይሆን!!
  ረ – አሁንም ከልቤ እላለሁ!!የማኅበሩን ክፉውን አያሳየኝ፡፡በየጋዜጣው የሚወራውንም ውሸት ያድርገው፡፡ነገር ግን ጉዳዩ ከዚያ አልፎ አደጋ ቢከሰት ጣቴን በ1ኛ ደረጃ የምቀስረው ወደ ማኅበሩ አመራር ነው፡፡አሁንም እናንተ የምትንጫጩትን ያህል እየሆነ አይደለም፡፡እኔ የምፈራው ይሄ መስመር የለቀቀ ጫጫታ ወደፊት ከመንግስትና ከቤ/ክህነት ኃላፊዎች ጋር ተቀምጦ ለመነጋገር አመኔታ እንዳያሳጣችሁ ነው፡፡ስለዚህ እላለሁ፡፡እናገራለሁ፡፡ካለአዋቂ ሳሚው የግል ፕሬስ ራሳችሁን አርቁ፡፡አባላቱም ማኅበሩን ቅዱስ ቅዱስ ከማለት ቀድመን ቤታችንን እንፈትሽ ማለትን ብታስቀድሙ መልካም ነው፡፡በነገራችን ላይ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የአ/አ/ሀ/ስብከት ስ/አስኪያጅ እንጅ የጠቅላይ ቤ/ክህነት ስላልሆኑ ተቃዋሚ የተሰኙት ሰዎች በጠ/ቤ/ክህነት አዳራሽ ለመሰብሰብ የእሳቸውን ፈቃድ መጠየቅ የሚያስፈልጋቸው አይመስለኝም፡፡

  • ም.ክ.ረ. April 1, 2014 at 11:59 am Reply

   በአማን የተባልክ … የነውረኞች ትፋትም ቢሆን በቃ ሰምተንሃል የተላከልህን በደንብ ነው ፔስት ያደረከው… ጎበዝ ተላላኪ ነክ … አሁን ለምን ውልቅ ብለክ ወደ አደራሽክ ወይም ወደ ክድርናክ አትሄድም? እርግጥ ነው ግዕዝ ተናጋሪና አደናጋሪ ካድሬዎች እንዳላችሁ እኮ እናውቃለን…. አንተን የሚመስሉ ተረፈ-አይሁዶች የናት ጡት ነካሾች በቅ/ቤተ ክርስቲያን ተሰግስጋችሁ በሁለት ቢላዎ ስትበሉ ስታባሉን በሃሰት ስትከሱን ስታካስሱን የኸው ዘመን ተቆጠረ… ደግሞም መንግስታችን ቸር ነው ካባረሩንም ወጥተን የራሳችንን ቤ/ክ እንሰራለን አይደል ያላችሁት….? እናንት የማኅበሩ ከሳሾች ዲያብሎስ የተጣባችሁ ህሊናችሁን ለፍርፋሪ የሸጣችሁ….

  • WEB April 1, 2014 at 8:01 pm Reply

   Do you think everyone should support the government? You may support your self, others have a right to support or oppose; why you are trying to relate people’s personal opinion with MK. MK is responsible for things have done as MK.

 13. Anonymous April 1, 2014 at 10:51 am Reply

  ante kehadi yemanawkeh meseleh

 14. Anonymous April 1, 2014 at 11:08 am Reply

  egziabher leabatochachin tsinatun yistilin lebetekristianachinim selam!!

 15. Anonymous April 1, 2014 at 11:17 am Reply

  በዚህ መሀል ማኅበሩ ውስጥ እረ ተው እንስከን እናስተውል የሚል መጥፋቱ ሌላው አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ለስንት የጠበቅናቸው ነባር አባላቱ ጉዳዩን ከፖለቲካ አቅጣጫ ብቻ በማየት ሃይማኖት እና አይማኖት እያሉ በቃላት ጨዋታ ራሳቸውን ያሞኛሉ፡፡ከፊሉም በመጽሐፋቸው የአሁኑ ደቡቡ የኢ/ያ ክፍል ወደ ሌላ ሃይማኖት ሂዶ ቀረው የግብጽ ጳጳሳት መምጣት በተቋረጠበት ዘመን ካህን ስለጠፋ መሆኑን ነግረውን ሲያበቁ ተገልብጠው ደግሞ ያለ ኢ/ዊ ጳጳስ የኖርንበትን ጊዜ መናፈቅ ጀምረዋል፡፡አዳዲስ የዋሃን አባላቱም ከእነሱ የተለየ ሀሳብ በሰሙ ቁጥር የሚወረውሩት ስድብ ማኅበሩ ሲያስታጥቅ የኖረው እውቀትንና ትህትናን ነው ወይስ ስድብና ትእቢትን እንድንል እያደረገን ነው፡፡በዛኛው አንጻር ስላለው ቅሬታ ጋዜጦቹም አያነሱም፤ አባላቱም መስማት አይፈልጉም፡፡አበሳውን ሁሉ እንደ ኦሪቱ የማስተስረያ ፍየል በቤ/ክህነትና በመንግስት ላይ መደፍደፍ ብቻ!!

 16. Anonymous April 1, 2014 at 12:19 pm Reply

  Nothing will happen.

 17. GETAYE MEHARI April 1, 2014 at 1:44 pm Reply

  ENANTE YEBEG LEMID YELEBESACHIHU TEKULOCHE LEMIN ATEWINIM

 18. Anonymous April 1, 2014 at 4:27 pm Reply

  God makes every thing good….on his time now which is the time that “mahbere kidusan” destroyed……we all orthodox Christians stands for change by taking part on destroying this bad norms holder team…

 19. welde Dawit April 1, 2014 at 5:05 pm Reply

  long life for MK ye Ortodox eyen nachehu enaneta ke semaye selahonachu
  mederaweyen hule geze yemeyeschnekechaw yemedrawe neger new betekersteyen
  demo abatochachen endeserakebun lalegeochachen enasetelalefalen Ortodox atetadesem!!!

 20. Anonymous April 4, 2014 at 8:35 am Reply

  mk wongel endisfafa ena sewch endidnu yemisera mahber sayhon leesu haymanot sewech hone leleloch sewech metfat ,memot blom wed siol endihedu yemiaderg yewengeln ber yemizega new.

  • Anonymous April 5, 2014 at 12:54 pm Reply

   ohh
   I can read but ican’t reply on b/c of generalization

 21. Anonymous April 8, 2014 at 4:38 pm Reply

  Hulet papasat kemahbere kidusan ekuy tegbar ga mewesenachew min yasdenikal? mahberu eko beseytan menfes eyetemera new

 22. Anonymous June 13, 2014 at 7:48 am Reply

  who you are ? are you a devil? tell us what is the mistakes or heresy of MK? do you have any evidence? at least try to convince us by making the false true. we know what and who is the father of false. by the way I am not the member of MK, but admire and wonder their commitments and determination they have for orthodox tewahdo churches.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: