በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ኅቡእ እንቅስቃሴ ተማሪውን የርስ በርስ ግጭት ወደሚያስገባ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

 • በቅ/ሲኖዶሱ በይፋ ከተወገዙና በኑፋቄ አራማጅነት ከሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋራ ግንኙነት ያላቸውና በኅቡእ በሚንቀሳቀሱ ጥቂት ተማሪዎች የሚራመድ ነው
 • ‹‹ችግሩን በዝምታ ለመመልከት ኅሊናችም ሃይማኖታችንም አይፈቅድልንም›› /ብዙኃኑ ደቀ መዛሙርትና የደቀ መዛሙርት ምክር ቤት አባላት
 • ለእምነትና ሥርዓት የሚቆረቆሩ መምህራንና ተማሪዎች ‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችኹ› በሚል እንዲሸማቀቁ ይደረጋሉ

(ዕንቊ፤ ቅጽ ፮ ቁጥር ፻፲፬፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.)

Enqu magazine logoየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በዘመናዊ አቀራረብ ከሚሰጡት ሦስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱና አንጋፋ በኾነው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናና ትውፊት ውጭ ነው የተባለ አስተምህሮ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ተማሪውን የርስ በርስ ግጭት ውስጥ ወደሚያስገባ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የኮሌጁ ምንጮች አስታወቁ፡፡

በቅ/ሲኖዶሱ በይፋ ከተወገዙና በኑፋቄ አራማጅነት ከሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋራ ግንኙነት እንዳላቸውና በኅቡእ በሚንቀሳቀሱ ተማሪዎች የሚራመድ ነው የተባለው አስተምህሮ፣ በአስተዳደሩ ተመርምሮ አልያም በመድረክ ተጋልጦ እልባት እንዲሰጠው የደቀ መዛሙርቱ ም/ቤት በጥር ወር መጀመሪያ ላይ ለኮሌጁ አስተዳደር ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ ሳይሰጠው መቅረቱን የኮሌጁ ምንጮች ለዕንቊ መጽሔት ተናግረዋል፡፡

የም/ቤቱ አባላት ኮሌጁንና ደቀ መዛሙርቱን ለማገልገል በደቀ መዛሙርቱ ጠቅላላ ጉባኤ መመረጣቸውን ያስታወሱት ምንጮቹ፣ አገልግሎታቸውን በቅንነትና በትጋት እንዲፈጽሙ ከፍተኛ ሓላፊነት ከተጣለባቸው አንዳንዶቹ ሃይማኖትን ለማጽናትና ለማስፋፋት ቤተ ክርስቲያኒቱ በጀት መድባ አገልጋዮቿን በምታስተምርበት ተቋም ከአስተምህሮዋ ውጭ ኑፋቄ ሲዘራ ድምፀ ተዓቅቦ በማድረግ የጋራ አቋም እንዳይደረስበት ይሠራሉ ብለዋል፤ ለእምነታቸውና ሥርዓታቸው የሚቆረቆሩ መምህራንና ተማሪዎችን ‹ማኅበረ ቅዱሳን›ና ‹ፖሊቲከኞች› እያሉ በተለያዩ ስልቶች በማሸማቀቅ ከሚታወቁት ችግር ፈጣሪ ደቀ መዛሙርት ጎን ተሰልፈው የሚፈጽሟቸው ተግባራትም እንዳሳሰባቸው ምንጮቹ አስረድተዋል፡፡

ለኮሌጁ አስተዳደር ዲን ከኹለት ወራት በፊት የገባው ደብዳቤ ምላሽ ሳይሰጠው በመዘግየቱና የችግሩ አያያዝ በም/ቤቱ አባላት መካከል ሳይቀር የአቋም ልዩነት በመፍጠሩ ይህንኑ የሚያስረዳ ሌላ ደብዳቤ በዚሁ ሳምንት በኹለት የም/ቤቱ አባላት ለዋና ዲኑ ጽ/ቤት መቅረቡ ተጠቁሟል፡፡

‹‹ችግሩን በዝምታ ለመመልከት ኅሊናችም ሃይማኖታችንም አይፈቅድልንም›› ማለታቸው የተጠቀሰው እኒኽ የም/ቤት አባላት፣ በአቋም ተለይተናቸዋል ያሏቸው የም/ቤቱ አባላት ከእንግዲኽ በም/ቤቱ ስም ለሚያስተላልፉት ማንኛውም ውሳኔ ሓላፊነት እንደማይወስዱ፣ ከልማቱ ይልቅ ጥፋቱ አመዝኗል ያሉት ም/ቤትም ታግዶ ጉዳዩ እንዲጣራ፣ እምነታቸውና ሥነ ምግባራቸው በተመሰከረላቸው ደቀ መዛሙርትም እንዲተካ መጠየቃቸው ታውቋል፡፡

Advertisements

5 thoughts on “በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ኅቡእ እንቅስቃሴ ተማሪውን የርስ በርስ ግጭት ወደሚያስገባ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

 1. Anonymous March 29, 2014 at 3:47 pm Reply

  zelalem silemeleyayetna sile kis bicha taweralachi eski andande enkuan silefikr awru yeand mahber degafi bcha kemehonm wetavchu yebetekrstian degafiwoch hunu ers bers kemtikasesuna kemtebelalu silefikrna andinet atsebkum silemeleyayet bcha enante tifajalachu esilam demo mimenun yfejewal

 2. Berhanu Y.berhan March 30, 2014 at 11:06 am Reply

  Keep it up.

 3. Anonymous March 31, 2014 at 6:55 pm Reply

  yebete krstiann gemena asalifo letelat meshet yhe new lenante krstina malet? manm lij yenatun hafret gelbo lelela sew ayasaym yhe yenante sra gn yenatn hafret gelbo masayet new betam yasazinal egziabher libona ystachu

 4. Anonymous April 1, 2014 at 5:24 am Reply

  ewnetna nigat eyader yiteral

 5. Anonymous April 1, 2014 at 2:55 pm Reply

  ጐልያድም እኮ ዝቶ ነበር፡፡ ግን የሆነውን ይታወቃል አሁንም .ቢሆን ጎልያዶች ቢዝቱ አይገርምም ማኀበረ ቅዱሳን የሚሸበርና የሚፈራ አባል የለውምና የሚያምነው ኃያሉን እግዚአብሔር ነውና፡፡ . የሚያስገርመው የሀገርና የቤተክርስቲያን ጠላቶች፤ የሀገርና የቤተክርስቲያን ወዳጆችን ባይቃወሙና ዝም ቢሉ ነበር. ይሄ የምናየው ለኛ በረከት ነው የበለጠ ያነቃናል እንደኔ ለተኛን በስም ሳይሆን በደም ኢትዮጵያውያን ለሆን፣ በመምሰል ሳይሆን በእውነት ክርስቲያኖች ለሆን የንቁ ደወል ነው፡፡
  ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲየን እድገት አብረን እንሥራ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: