‹‹ፓትርያርኩ ይደግፉናል መንግሥት ያግዘናል›› ያሉ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ሀብትና ንብረቱ ታግዶ በፀረ ሽብር ሕጉ መሠረት እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት ጠየቁ

 • በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ያልታወቀውና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት የአዳራሽ ፈቃድ የተነፈጋቸው አማሳኞቹ ትላንት መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ረፋድ ላይ ተጀምሮ እስከ እኩለ ቀን በዘለቀው ስብሰባቸው፣ በሌላቸው ሕጋዊነትና ውክልና ‹‹የአዲስ አበባ አገልጋዮች ማኅበር›› መሥርተው ማኅበረ ቅዱሳንን መቃወማቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
 • ‹ውሳኔያቸውና የአቋም መግለጫቸው› ተቀባይነት አግኝቶ ተፈጻሚ ካልኾነና የማስወጣት ርምጃ ከተወሰደባቸው የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ተቃውሟቸውን ለማጠናከር የዛቱ ተሰብሳቢዎችም አሉባቸው! – ‹‹ከዚኽ እንኳ ቢያስወጡን መንግሥታችን ቸር ነው፤ ቦታ ተቀብለን የራሳችንን ቤተ ክርስቲያን ሠርተን ለምን አንቀጥልም?››
 • የአቋም መግለጫቸውን በተለያዩ መሸኛዎች አዘጋጅተው ከሚያደርሷቸው አካላት መካከል÷ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት፣ የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ የመ/ፓ/ጠ/ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ለየብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚገኘበት ሲኾን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይገኙበታል፡፡
 • ፓትርያርኩየተዘጋባቸው አዳራሽ እንዲከፈትላቸው ከማዘዝ ጀምሮ በተቃውሟቸው ሳቢያ ከሥራቸው እንደማይፈናቀሉና መፍራት እንደሌለባቸው በመግለጽ አበረታተውናል ያለው ኃይሌ ኣብርሃ፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያን በፊዚክስና ኬሚስትሪ አትመራም›› በማለት በአንድ ስብሰባ ላይ መናገራቸው እነርሱን ለማበረታታት መኾኑን በመጥቀስ አወድሶላቸዋል፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ደብዳቤ ለመጻፍ በመድፈራቸው ‹‹ልናደንቃቸው ይገባል›› ብሏል፤ ደብዳቤዎቹም በንባብ ተሰምተዋል፡፡

*   *   *

 • ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹በሀገር አቀፍ ደረጃ ንጹሕ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ለአድማ በማነሣሣት በሀገርና በቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከትና ሽብር እንዲፈጠር ሰላም እንዲደፈርስ ያደርጋል›› ያሉትና የደኅንነቱ ኃይል በእጃቸው እንደኾነ የተናገሩት አማሳኞቹ እርስ በርሱ በሚምታታውና በሚገባ ባልተደራጀው መግለጫቸው፣ ‹‹መንግሥት ለሽብር ተግባር እንደሚውል ዐውቆ በፀረ ሽብር ሕጉ ታሳቢነት ማኅበሩ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ስም ከምእመናን በሚሰበስበው ዓሥራት በኩራት ያፈራውን ጠቅላላ ሀብትና ንብረት ቁጥጥር በማድረግ የተለመደ እገዛው እንዳይለየን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤›› ብለዋል፡፡
 • አማሳኞቹ በቅ/ሲኖዶስ በኩል ለሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲተላለፍላቸው የጠየቁት የጠቅላላ ሀብትና ንብረት እገዳ ደብዳቤ ደግሞ÷ ት/ቤቶች፣ ሕንፃዎች፣ የንግድ ተቋማት፣ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች፣ የንዋያተ ቅድሳት ማምረቻዎችና ማከፋፈያዎች፣ የአክስዮን ተቋማትና የባንክ አካውንቶች የሚመለከት ነው፡፡ አማሳኞቹ ከቀደመው ንግግራቸው ጋራ በሚጋጭ አኳኋን እንደተናገሩት፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሀብቶችና ንብረቶች ምንጭ አይታወቅም፤ ባለቤትም የላቸውም፤ ኦዲት ተደርገውም አያውቁም፤ ዓመታዊ ሪፖርት አቅርቦ አያውቅም፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሞዴልም ተገልግሎ አያውቅም፡፡
 • በቅ/ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት ለዓላማው ተግባራዊነት በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸውና በጉልበታቸው የሚራዱ አባላት ያሉት ማኅበረ ቅዱሳን እንደየገቢያቸው መጠን በየወሩ ቢያንስ ከመቶ አንድ እጅ(1%) የአባልነት አስተዋፅኦ የሚያደርጉ አባላት አሉት፤ ለማኅበሩ አገልግሎት አስፈላጊ የኾኑ አዳዲስ የልማትና ተራድኦ ተቋማት እንዲቋቋሙ ወይም እንዲዘጉ የመወሰን ተግባርና ሓላፊነት ያለው የሥራ አመራር ጉባኤ አለው፡፡
 • ማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ዕቅድ ዝግጅቱንና የአፈጻጸም አጠቃላይ ዘገባውን በየስድስት ወሩ አንድ ጊዜ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ያቀርባል፤ በዘመናዊ የፋይናንስ አሠራርና የንብረት አስተዳደር መመሪያ የያዘውን የአባላቱን ሀብት አጠቃቀም በተመሰከረለት የውጭ ኦዲተር ያስመረምራል፤ የኦዲት ሪፖርቱንም በየዓመቱ ያቀርባል፤ መመሪያም ይቀበላል፡፡
 • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የነጠላ ሒሳብ ሥርዓት አዝማናት የተሻገሩትና ከማንኛውም የአካውንቲንግ ሶፍትዌሮች ጋራ የማይጣጣም ከሊትሬቸሩም የጠፋ ነው፤ ለቁጥጥር የሚያመች የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መመሪያ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አልተተከለም፤ ሞዴላሞዴሎቹ ምስጢራዊ ኅትመት (security features) የሌላቸው፣ የሀብት፣ ንብረትና ዕዳ መጠን በተመለከተ ተፈላጊውን መረጃ የማይሰጡ በምትኩ ለአማሳኞች ማጭበርበርያ አመቺ ኾነው እንዳሉ በተለያዩ መድረኮች ሲገለጽ የቆየ ነው፡፡
 • ከዚኽ አኳያ የማኅበሩ ጥያቄ ቤተ ክህነቱ አይቆጣጠረኝ ሳይኾን ለቁጥጥር አመች(audit-able) የኾነ ነባራዊ ኹኔታ(ለምሳሌ፡- ጠቅ/ቤተ ክህነቱ ኅትመቱን የፈቀደውና ቁጥሩን የመዘገበው፣ ከሒሳብ ሥርዐቱ ጋራ የሚስማሙ ደረሰኞች ኅትመት) የመፍጠር ጥያቄ እንደኾነ በየጊዜው እንደሰጣቸው የሚታወቁ ገለጻዎች ሰሚ ጆሮ አስተዋይ አእምሮ ቢያገኙ መልካም ነው፡፡
 • በስተቀር የማኅበሩ አባላት በድካማቸው ያፈሩትን ሀብት ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ እንጂ የማይቀበሉ (አማሳኞቹ እንዳሉት የዓለም የኑሮ ውድነት አባሯቸውና መንግሥት የሚከፍላቸው ደመወዝ አላረካ ብሏቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሰርገው የገቡ) እንዳልኾኑ፣ ማኅበረ ቅዱሳንም በማዕከላዊ የቤተ ክህነት መዋቅር ውስጥ ኾኖ የድርሻውን በመወጣት ላይ የሚገኘው፣ በአባቶች የታመነበትን ክፍተት የመሙላት አገልግሎቱን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ለመከታተል እንደኾነና ይህን የአገልግሎት ድርሻውን ለመወጣት በበጎ ፈቃድ የተሰበሰቡ አባላቱ ማኅበር በመኾኑ ለሥራው የሚመደብለት በጀት ይኹን ከእርሱም የሚጠበቅ የገቢ ፈሰስ እንደሌለ ሊያዝ ይገባል፡፡

*   *   *

 • መንግሥት ባጋመስነው የ፳፻፮ ዓ.ም. በጀት ዓመት በትኩረት እረባረብበታለኹ በሚል በያዘውና በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር አስተባባሪነት እንደሚመራ በገለጸው የፀረ አክራሪነት ዕቅድ፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በማኅበራት ጥላ ሥር ይካሔዳል ያለውን ‹የአክራሪነት አመለካከትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ› የምዝገባ፣ የክትትልና የመረጃ ሥርዐቱን አጠናክሮ የፋይናንስ ዝውውራቸውንና አጠቃቀማቸውን ግልጽነት በማረጋገጥ እንደሚፈተሽ አስፍሯል፡፡
 • የፀረ አክራሪነት ትግል አስተዳደራዊና የጸጥታ ሥራ ብቻ ሳይኾን ቁልፍ ፖሊቲካዊ ትግልም እንደኾነ የሚገልጸው መንግሥት፣ ፖሊቲካዊ ትግሉ የሴኩላር መንግሥትን ሚና ጠብቆ በንቃት ሊመራ እንደሚገባውና ከዚኽ አኳያ በገዛ መዋቅሩ ውስጥ መሽገው የትግሉን አቅጣጫ የሚያስቱ፣ የሚያደበዝዙና ሽፋን የሚሰጡ፣ የሕዝብን እይታ የሚያዛቡና ለተለያዩ ጥርጣሬዎች መንገድ የሚከፍቱ ያላቸው የመንግሥትና የድርጅት አካላትና አባላት ቁመና መፈተሽ እንደሚገባው ያሳስባል፡፡
 • እናስ? የቤተ ክርስቲያናችን ማኅበራት አፈራረጅ ይቆየንና ከእነ ንቡረ እድ ኤልያስ ጋራ ጥብቅ ቁርኝት ፈጥረው በመንቀሳቀስ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናቱ የሚሰናከልበትን አሻጥር እየሠሩ የሚገኙት አማሳኞቹ እነ ኃይሌ ኣብርሃ ‹‹በእጃችን ናቸው›› ያሏቸው ‹‹የቤተ ክህነት ደኅንነቶች›› የትግሉ አያያዝና የቁመና ጥራት መፈተሽ አይኖርበትምን?

*   *   *

 • አማሳኞቹ ተጽዕኖ ለመፍጠር አልመው እንዳስወሩት፣ ፓትርያርኩ በስብሰባው ላይ ባይገኙም ቅዱስነታቸው የቅ/ሲኖዶሱን ጽ/ቤት እና የሌሎች ብፁዓን አባቶችን ምክር ወደ ጎን በማለት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አዳራሽ ሓላፊ ቀጥተኛ የቃል ትእዛዝ በማውረድ ለአማሳኝ ተቃዋሚዎች ቁልፍ እንዲሰጥ በማድረግ ነበር ስብሰባው በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የስብሰባ አዳራሽ የተካሔደው፡፡
the corrupt parish head haile abreha

በልማታዊነት ስምና በእልቅና ካባ በሚልዮኖች የተመዘበሩባቸው አብያተ ክርስቲያናት ሀብት (ከደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ብቻ 13.3 ሚልዮን ብር መኾኑ ተጠቁሟል) ፣ የግል ሚኒባስ፣ የግል መኖሪያ ቤቶች ይዞታና ድልብ የባንክ ተቀማጭኽ ጉዳይ ይቆየንና በ1.3 ሚልዮን ብር የተገዛውና በወር 70‚000 ብር የኪራይ ገቢ የሚገኝበት ሲኖ ትራክ ገልባጭ መኪና ባለቤትነትኽ ምንጩ ምን ይኾን?

 • እነኃይሌ ኣብርሃ ባስተባበሩትና በዘካርያስ ሐዲስ በተመራው ቅጥፈትና ያላዋቂነት እብሪት (arrogance of ignorance) በተሞላበት ስብሰባ ከተገኙት በደግ ግምት 200 ያኽል በሚኾኑ ተሰብሳቢዎች መካከል ኹለቱን ቀንደኛ አማሳኞች ጨምሮ አስተዳዳሪዎቹ ስምንት ብቻ ናቸው፡፡
 • ከ169 በላይ በኾኑ የሀገረ ስብከቱ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ካሉ 14 ሺሕ ያኽል ሠራተኞች መካከል አማሳኞቹ በጎጥና ጥቅም ከሳቧቸውና በሥልጣናቸው ካስፈራሯቸው በቀር የተገኙት አስተዳዳሪዎችና አጠቃላይ ተሳታፊዎች ቁጥር ማነስ አማሳኞቹን ክፉኛ አሳስቧቸዋል፡፡
 • ኹኔታውም አንዱ ተናጋሪ ‹‹ሴት ያወጣውን ሕግ አንቀበልም›› እንዳለው ሳይኾን የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ትግበራው እንዲፋጠን እየተጠየቀ ያለውና 96 በመቶ የሀገረ ስብከቱን ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች የተረጋገጠ ድጋፍ ያስገኘው የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት ሰፋኒነትና ኃያልነት የተመሰከረበት ኾኗል፡፡
 • የሕግና የሥርዓት ምንጭ የኾነችውን ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የሚመራው ቤተ ክህነታችን ባለቤት የሌለው ይመስል የግለሰቦችና ቡድኖች መፈንጫ መምሰሉ በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ተሻሽሎ ማየት የማይሹ አማሳኞች መንበረ ፓትርያርኩን ከበው የፓትርያርኩን የለውጥ ተነሣሽነት ሲያግቱት ማየቱም ያስቆጣል፡፡ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔዎች የማስፈጸም ሓላፊነት ያለበት ቋሚ ሲኖዶስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአጠቃላይ እየኾነ ያለውን ነገር በዝምታ ሊያዩት አይገባም፡፡ በሃይማኖት ተቋማት ለልዩነት፣ ግጭትና ቅስቀሳ ምቹ ኹኔታዎች እንዳይፈጠሩ እሠራለኹ የሚለው መንግሥትም ነገሩን በጥንቃቄ ሊያጤነው ያስፈልጋል፡፡
Advertisements

35 thoughts on “‹‹ፓትርያርኩ ይደግፉናል መንግሥት ያግዘናል›› ያሉ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ሀብትና ንብረቱ ታግዶ በፀረ ሽብር ሕጉ መሠረት እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት ጠየቁ

 1. ገብረ ማርያም March 24, 2014 at 5:54 am Reply

  አምላክሰ ኢያረም………
  እባካችሁ በቤተ ክርስቱያን አንጡራ ቦርጫችሁን ለማሳደግ አትሩጡ። ሙስናም ይቀራል……
  የተቀደፈ መዋቅርም ይሰራበታል። አምላክ ዝም አይልምና።

 2. kidanemariama March 24, 2014 at 7:25 am Reply

  የሕግና የሥርዓት ምንጭ የኾነችውን ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የሚመራው ቤተ ክህነታችን ባለቤት የሌለው ይመስል የግለሰቦችና ቡድኖች መፈንጫ መምሰሉ በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ተሻሽሎ ማየት የማይሹ አማሳኞች መንበረ ፓትርያርኩን ከበው የፓትርያርኩን የለውጥ ተነሣሽነት ሲያግቱት ማየቱም ያስቆጣል፡፡ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔዎች የማስፈጸም ሓላፊነት ያለበት ቋሚ ሲኖዶስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአጠቃላይ እየኾነ ያለውን ነገር በዝምታ ሊያዩት አይገባም፡፡ በሃይማኖት ተቋማት ለልዩነት፣ ግጭትና ቅስቀሳ ምቹ ኹኔታዎች እንዳይፈጠሩ እሠራለኹ የሚለው መንግሥትም ነገሩን በጥንቃቄ ሊያጤነው ያስፈልጋል፡፡

 3. habtamu dessie March 24, 2014 at 8:05 am Reply

  አቤቱ ይቅር በላቸው ለሰጋዊ ትቅማቸ

  ው ተበሎ ይህን ታከል ተገል

 4. Anonymous March 24, 2014 at 11:05 am Reply

  እኔ በእናንተ ላይ በሚፈርድ ሰው አዝናለሁ፡፡ የሚፈርድባችሁ ምን ስላደረጋችሁ ነው፤
  1) ለዘመናት እንደልብ ከምታፍሱት የገንዘብ ካዝና አንርቅም በማለታችሁ ነውን፤
  2) አይደለም ለራሳችሁ በዘር በቋንቋ ተጠራርታችሁ ልትጠቅሙት ሊጠቅማችሁ ቀጠሮ የያዛችሁለትን ሳትፈጽሙ ላለመውጣት በመጠየቃችሁ ነውን፤
  3) ገና ቆብ ስትደፉ ጀምሮ ቤ/ክንን እጅግ ውል የጠፋባት ለማድረግ ቃል ገብታችሁና ተማምላችሁ ገብታችሁ አሁን ገና ከመጀመራችሁ እንቅፋት የቤ/ክ አምላክ ስደረሰባችሁ ነውን፤
  4) ወይንስ ሚኒባስ፣ ሲኖትራክ፤ ጂ ፕላስ 2 ቤት፤ … ገዝታችሁ ክፍያውን እጃችን ላይ ካለው ከምንከፍል እንደሌለን እንዲቆጠር በብድር እናድርገው ብላችሁ ተበድራችሁ የእጃችሁን ለጵጵስና ለመታጨት፤ ፓትርያርኩን ለማማለል፤ የመንግስት ባለስልጣናትን ለምደዋልና እጅ መንሻ ለመስጠት ሰጥታችሁ ሰትታችሁ በመጨረሳችሁ የባንኩ ደግሞ ለክፉ ቀን አሜሪካ መውጫ ብላችሁ የመኪናና የቤት ዕዳ ከቤ/ክ ሙዳየ ምጽዋት አንክፈል ተውን በማለታችሁ ነውን፤
  5) ወይንስ የሚከሷችሁ እግዚአብሔር ይይለትና ከአባላቱም ከምዕመናንም ሽራፊ ሳንቲም አሰባስቦ እናንተ ያልተማራችሁባቸውን አብነት ት/ቤቶች የሚያቋቁመውን፤መምህራን አይሰደዱ፤ ተማሪዎች አይበተኑ የሚለውን፤ ወጣቱ ከልጅነቱ ተምሮ ቤ/ክንን ያልግል የሚለውን፤ ገንዘብ በፈረንጅ ማሽን ይመዝገብ፤ ማቅ የተባለ ማኅበረ ቅዱሳንን ስለተዋጋችሁ ነውን፤
  ኸረ አይገባም፡፡ እናንተንማ መሾም መሸለም እንጂ፡፡ እኛ ጸሎታችን እናንተን የቤ/ክንን በሮች (ላልቶ ይነበብ) ‹ አቁሞ ያሂድልን › ነው፡፡ ለዚህም ረጅም የምድር ላይ ዕድሜ ለመልአከ መንቅራት ሃይሌ አብርሃ ፣ለአባ ሰረቀ እና ለነብረ ዕድ ኤልያስ ይሁንልን፡፡ ለማንኛውም ብዬ ነው፡፡ ደግሞ በሰማይም የማኅበረ ቅዱሳን አጫፋሪዎች መንግሰተ ሰማያት አናስገባም ቢሏችሁ የምድሩን ጠገብ በሉት ብዬ ነው፡፡
  ተስፋዬ ከዳር አገር

 5. Anonymous March 24, 2014 at 11:56 am Reply

  እኔ በእናንተ ላይ በሚፈርድ ሰው አዝናለሁ፡፡ የሚፈርድባችሁ ምን ስላደረጋችሁ ነው፤
  1) ለዘመናት እንደልብ ከምታፍሱት የገንዘብ ካዝና አንርቅም በማለታችሁ ነውን፤
  2) አይደለም ለራሳችሁ በዘር በቋንቋ ተጠራርታችሁ ልትጠቅሙት ሊጠቅማችሁ ቀጠሮ የያዛችሁለትን ሳትፈጽሙ ላለመውጣት በመጠየቃችሁ ነውን፤
  3) ገና ቆብ ስትደፉ ጀምሮ ቤ/ክንን እጅግ ውል የጠፋባት ለማድረግ ቃል ገብታችሁና ተማምላችሁ ገብታችሁ አሁን ገና ከመጀመራችሁ እንቅፋት የቤ/ክ አምላክ ስደረሰባችሁ ነውን፤
  4) ወይንስ ሚኒባስ፣ ሲኖትራክ፤ ጂ ፕላስ 2 ቤት፤ … ገዝታችሁ ክፍያውን እጃችን ላይ ካለው ከምንከፍል እንደሌለን እንዲቆጠር በብድር እናድርገው ብላችሁ ተበድራችሁ የእጃችሁን ለጵጵስና ለመታጨት፤ ፓትርያርኩን ለማማለል፤ የመንግስት ባለስልጣናትን ለምደዋልና እጅ መንሻ ለመስጠት ሰጥታችሁ ሰትታችሁ በመጨረሳችሁ የባንኩ ደግሞ ለክፉ ቀን አሜሪካ መውጫ ብላችሁ የመኪናና የቤት ዕዳ ከቤ/ክ ሙዳየ ምጽዋት አንክፈል ተውን በማለታችሁ ነውን፤
  5) ወይንስ የሚከሷችሁ እግዚአብሔር ይይለትና ከአባላቱም ከምዕመናንም ሽራፊ ሳንቲም አሰባስቦ እናንተ ያልተማራችሁባቸውን አብነት ት/ቤቶች የሚያቋቁመውን፤መምህራን አይሰደዱ፤ ተማሪዎች አይበተኑ የሚለውን፤ ወጣቱ ከልጅነቱ ተምሮ ቤ/ክንን ያልግል የሚለውን፤ ገንዘብ በፈረንጅ ማሽን ይመዝገብ፤ ማቅ የተባለ ማኅበረ ቅዱሳንን ስለተዋጋችሁ ነውን፤
  ኸረ አይገባም፡፡ እናንተንማ መሾም መሸለም እንጂ፡፡ እኛ ጸሎታችን እናንተን የቤ/ክንን በሮች (ላልቶ ይነበብ) ‹ አቁሞ ያሂድልን › ነው፡፡ ለዚህም ረጅም የምድር ላይ ዕድሜ ለመልአከ መንቅራት ሃይሌ አብርሃ ፣ለአባ ሰረቀ እና ለነብረ ዕድ ኤልያስ ይሁንልን፡፡ ለማንኛውም ብዬ ነው፡፡ ደግሞ በሰማይም የማኅበረ ቅዱሳን አጫፋሪዎች መንግሰተ ሰማያት አናስገባም ቢሏችሁ የምድሩን ጠገብ በሉት ብዬ ነው፡፡
  ተስፋዬ ከዳር አገር

 6. Mesfin Dubale March 24, 2014 at 12:27 pm Reply

  ቅዱስ አባታችን በተመረጡ እለት ስለ ቢተ-ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ ለዉጥ አስፈላጊነት ያደረጉትን ንግግር መቺም ቢሆን አልረሳዉም- እባክዎን ቃልዎን ያክብሩ፤ ከእዉነተኛ አባቶች ጋር ብቻ ይተባበሩ-አደራ ፤የቢተ-ክርስተቲያናችንን ትንሳኢ ያፋጥኑ—የቢተ-ክርስቲያናችን መሪ ከሆኑበት ጊዚ ጀምሮ ለልማትም ይሁን ለጥፋት በቅድሚያ የሚነሳዉ የእርስዎ ስም መሆኑን አይዘንጉ-ልዑል እግዚአብሂር ሁል ጊዚ ከእዉነት ተናጋሪዎችና ሰሪዎች ጋር ነዉና.

 7. Anonymous March 24, 2014 at 12:52 pm Reply

  ye patryariku akm manes new yemiyasayewu zekariyas hayile yetaweku mezbariwechi nachew lmn yakerbochew yimeslchihal leba slehonu bchia new esachewum akm slelelachew bcha new

 8. Anonymous March 24, 2014 at 2:12 pm Reply

  Abo cher yasenbitih!!! Yedar ageru wgnei, egna mehal hager honen tekatelin. Bicha, yebet kirsitian amlak aytewenim. Enaliks. aby tsom huleim fetena yistenagedibetal. Me, since my job is in the church, understand and facing what you said. His holyness Abune Matyas must confirm the implementation of the new structure and reform. Otherwise, yeshomachew Leul Amlak Yiferdal. I have no even certificate in any spritual and modern education. But I need the Re-emerging of the Church. Yebetekirsiyanen tinsaei yasayen!!!!!!!!!!!!!!

 9. በአማን ነጸረ March 24, 2014 at 2:57 pm Reply

  በእነ መልአከ መንክራት ኃይሌ አካሄድ ደስ አለኝ!!ምነው ቢሉ….
  1. ስብሰባቸውን በዓለማዊ አዳራሽ ከማድረግ ይልቅ እንደ ማኅበረቅዱሳን የራሳቸው ሕንጻ እንደለሌላቸው አውቀው በእናት ቤ/ክ ስር ያለውን የጠ/ቤ/ክህነትን አዳራሽ ማስፈቀዳቸው፣በዚህም ቤ/ክንንም ሆነ ራሳቸውን ካላስፈላጊ ትችት ለመከላከል በመቻላቸው፣
  2. ከ13 አጥኚ ውስጥ ከአንድ ጸሐፊ በቀር አንድም አስተዳዳሪ እና ቋሚ የቤ/ክ ተቀጣሪ ሰራተኛ ሳይሳተፍበት በማኅበረቅዱሳን የገሀድና የስውር ጫና በቤ/ክ አገልጋዮች ላይ ሊጫን የነበረውን ጥናት ‘የለም እስኪ ከመጽደቁ በፊት እኛም ያገባናል በሊቃውንቶቻችን ይታይ’ ብለው ሁሉም ብሶቱን ባመቀበት ወቅት የታመቁ ካህናት ድምጽ ሆነው በዐደባባይ በመቆማቸው፣
  3. መላውን ካህን ለማንቀሳቀስ ያለውን አስቸጋሪነት ተረድተው ከየአድባራቱ ኮሚቴ አዋቅረው አላማቸውን ለማሳካት ለሁሉም ወገን ግልጽ በሆነ ሁኔታ በመንቀሳቀሳቸው፣ይሄ አካሄድም ወደ አንድ ወገን ባጋደለው የግል የህትመት ሚዲያና ማኅበራዊ ሚዲያው የሚያመጣባቸውን አሁን እየቀረበ ያለውን ማስረጃ ያልቀረበበት የውንጀላና ፍረጃ ጫና ጨምሮ ብዙ ዋጋ ሊከፍሉ እንደሚችሉ አስቀድመው ተረድተው ለጫናው መዘጋጀታቸው፣
  4. ብዙዎች ያልደፈሩትን ማኅበረቅዱሳን ፐርሰንት መክፈል አለበት፣ ንብረቶቹን በቤ/ክ ስም እያስመዘገበ ገቢውን ይጠቀም፣ሕጋዊውን የቤ/ክን ደረሰኝ ይጠቀም የሚሉ ከቃለ ዐዋዲው ጋር የሚጣጣሙና እስካሁን በቅ/ሲኖዶስ በአጀንዳነት ከመቅረብ ባለፈ ተግባራዊ ያልተደረጉ ጥያቄዎችን ደፍረው በማንሳት ማኅበሩ በነቢብ ብቻ ሳይሆን በገቢርም ከሕገ – ቤ/ክ በታች እንዲኖር ግፊት ማሳደራቸው፣
  5. እስካሁን ባላቸው እንቅስቃሴ በተቻለ መጠን ለዐለማዊ ሚዲያም ሆነ ለተሀድሶ ብሎጎች ቀጥተኛ መረጃ ባለመስጠት ጉዳዩ በቤ/ክ አስተዳደር ሊፈታ የሚችል መሆኑን አምነው መንቀሳቀሳቸው፣በተለይም የኢንተርኔት ዘመቻዎችን “ለመናፍቃን መዘባበቻ” የሚያደርጉ ብለው በአደባባይ ታህሳስ 9/2006ዓ.ም በማውገዝ ግራና ቀኝ ሆነው ጠርዝ የወጡ ዜናዎችን በሚያራግቡ ብሎጎች ላይ በግልጽ አቋም መውሰዳቸው አስደስቶኛል!!

  ከመጋቤ ምስጢር ኩልክሙ ልዋስማ….ሊቁ እንዲህ ነበር ያሉት…
  …ወቤቴል አሀቲ ኢትኩን ዝርወተ፣
  አኃዝ ማኅበራተ
  መዋግደ ብዙኅ ጸጋከ ወአስተናድፍ ስርዓተ….
  ይሄን ሲያብራሩትም ‘አኃዝ’ ማለት ‘እሰር ዝጋ ማለት አይደለም ሁሉ በስርዓት ይሁን ማለት እንጅ’ ሲሉ አብራርተውት ነበር!!ሀሳባቸው ሀሳቤ ነው!!ቤ/ክንን ከውስጥ ቀሳጥያንም ሆነ ከውጭ በስመ-ተሃድሶ ከሚጮኸው ዓለማዊነት መራሹ ፕሮቴስታንቲዝም ታድገን አኃቲ በሚል ስያሜዋ እንድትቀጥል በሥርዓት እንራመድ!!የሃይማኖታችን መለኪያ ማኅበር በመደገፍና ባለመደገፍ ባይሆን ጥሩ ነው!!
  ወነአምን በአሀቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላእለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት!!

  • Anonymous April 11, 2014 at 7:04 am Reply

   atachiberbir yemaygenagn neger !!!

 10. Anonymous March 24, 2014 at 2:58 pm Reply

  ሕግና የሥርዓት ምንጭ የኾነችውን ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የሚመራው ቤተ ክህነታችን ባለቤት የሌለው ይመስል የግለሰቦችና ቡድኖች መፈንጫ መምሰሉ በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ተሻሽሎ ማየት የማይሹ አማሳኞች መንበረ ፓትርያርኩን ከበው የፓትርያርኩን የለውጥ ተነሣሽነት ሲያግቱት ማየቱም ያስቆጣል፡፡ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔዎች የማስፈጸም ሓላፊነት ያለበት ቋሚ ሲኖዶስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአጠቃላይ እየኾነ ያለውን ነገር በዝምታ ሊያዩት አይገባም፡፡ በሃይማኖት ተቋማት ለልዩነት፣ ግጭትና ቅስቀሳ ምቹ ኹኔታዎች እንዳይፈጠሩ እሠራለኹ የሚለው መንግሥትም ነገሩን በጥንቃቄ ሊያጤነው ያስፈልጋል፡፡

 11. Anonymous March 25, 2014 at 6:45 am Reply

  ጌታውን አሳልፎ በ 30 ብር የሸጠው ይሁዳ በባህሪው ሌባ ነበር: ከሙዳየ ምጽዋትም ይሰርቅ ነበር: በመጨረሻው ግን አንጀቱ ተዘርግፎ ሞተ::እግዚአብሔር ጅራፉን እስከሚያነሳም ድረስ መጠበቅና መታገስ ያሻል::

 12. Anonymous March 25, 2014 at 7:50 am Reply

  ይገርማል እኮ በጥናቱ ሰነድ እንደተረጋገጠው የለውጡ ተቃዋሚዎች በብዛት 4በመቶ ነው፡፡ ከ169 አብያተክርስቲያናት 8 ተቃዋሚ አማሳኝ አስተዳዳሪዎች፡፡ ድንቄም ቀፎ፡፡

 13. SAMUEL FASIL March 25, 2014 at 8:32 am Reply

  የመንፈስ ቅዱስን ስራ መታገል አይቻልም አንልም ታገሉ ንኩት ግን አታጠፉትም የመንፈስ ቅዱስን ስራ ሊያቁአርጡ የሞከሩ ሁሉ አሰፉት አበዙት እንጂ አላሳነሱትም

 14. SAMUEL FASIL March 25, 2014 at 8:34 am Reply

  የቅዱስ እስጢፋኖስን ሞት ብቻ ተመልከቱ

 15. Anonymous March 25, 2014 at 11:50 am Reply

  እባካችሁ ተያይዘን ገደል አንሁን፣ አንዳችን ካንዳችን በምን እንሻላለን ; ቢያንስ አንሰዳደብ እርሱ ባለቤቱ ምፍትሄ እስኪጠን ተግተን እንፀልይ፡፡

 16. DANIEL ARAYA March 25, 2014 at 2:20 pm Reply

  EGZIABHER BETEKIRSTIANIN YITEBIK KETEMA EGZIABHER KALTEBEKE TEBAKIW BEKENTU YIDEKIMAL AYDELLLLLLLLLLLL!

 17. በአማን ነጸረ March 25, 2014 at 3:37 pm Reply

  ካንድ ወገን በሚመነጭ አድሏዊ ዜና ከሚዋከቡት እነ መልአከ መንክራት ኃይሌ አብርሃ ጎን የምቆምባቸው 6 ምክንያቶች…
  1. ስብሰባቸውን በዓለማዊ አዳራሽ ከማድረግ ይልቅ እንደ ማኅበረቅዱሳን ቤ/ክህነት የማያዝበት የራሳቸው ሕንጻ እንደለሌላቸው አውቀው በእናት ቤ/ክ ስር ያለውን የጠ/ቤ/ክህነትን አዳራሽ ማስፈቀዳቸው፣በዚህም ቤ/ክንንም ሆነ ራሳቸውን ካላስፈላጊ ትችት ለመከላከል በመቻላቸው፣
  2. ከ13 አጥኚ ውስጥ ከአንድ ጸሐፊ በቀር አንድም አስተዳዳሪ እና ቋሚ የቤ/ክ ተቀጣሪ ሰራተኛ ሳይሳተፍበት በማኅበረቅዱሳን የገሀድና የስውር ጫና በቤ/ክ አገልጋዮች ላይ ሊጫን የነበረውን ጥናት ‘የለም ለውጥ ባንጠላም እስኪ ከመጽደቁ በፊት እኛም ያገባናልና በሊቃውንቶቻችን ይታይ’ ብለው ሁሉም ብሶቱን ባመቀበት ወቅት የታመቁ ካህናት ድምጽ ሆነው በዐደባባይ በመቆማቸው፣
  3. መላውን ካህን ለማንቀሳቀስ ያለውን አስቸጋሪነት ተረድተው ከየአድባራቱ ኮሚቴ አዋቅረው አላማቸውን ለማሳካት ለሁሉም ወገን ግልጽ በሆነ ሁኔታ በመንቀሳቀሳቸው፣ይሄ አካሄድም ወደ አንድ ወገን ባጋደለው የግል የህትመት ሚዲያና ማኅበራዊ ሚዲያው የሚያመጣባቸውን አሁን እየቀረበ ያለውን ማስረጃ ያልቀረበበት የውንጀላና ፍረጃ ጫና ጨምሮ ብዙ ዋጋ ሊከፍሉ እንደሚችሉ አስቀድመው ተረድተው ለጫናው መዘጋጀታቸው፣
  4. ብዙዎች ያልደፈሩትን ማኅበረቅዱሳን ፐርሰንት መክፈል አለበት፣ ንብረቶቹን በቤ/ክ ስም እያስመዘገበ ገቢውን ይጠቀም፣ሕጋዊውን የቤ/ክን ደረሰኝ ይጠቀም የሚሉ ከቃለ ዐዋዲው ጋር የሚጣጣሙና እስካሁን በቅ/ሲኖዶስ በአጀንዳነት ከመቅረብ ባለፈ ተግባራዊ ያልተደረጉ ጥያቄዎችን ደፍረው በማንሳት ማኅበሩ በነቢብ ብቻ ሳይሆን በገቢርም ከሕገ – ቤ/ክ በታች እንዲኖር ግፊት ማሳደራቸው፣
  5. እስካሁን ባላቸው እንቅስቃሴ በተቻለ መጠን ለዐለማዊ ሚዲያም ሆነ ለተሀድሶ ብሎጎች ቀጥተኛ መረጃ ባለመስጠት ጉዳዩ በቤ/ክ አስተዳደር ሊፈታ የሚችል መሆኑን አምነው መንቀሳቀሳቸው፣በተለይም የኢንተርኔት ዘመቻዎችን “ለመናፍቃን መዘባበቻ” የሚያደርጉ ብለው በአደባባይ ታህሳስ 9/2006ዓ.ም በማውገዝ ግራና ቀኝ ሆነው ጠርዝ የወጡ ዜናዎችን በሚያራግቡ ብሎጎች ላይ በግልጽ አቋም መውሰዳቸው፣
  6. በ15/07/06 ዓ.ም በጠ/ቤ/ክህነት ባደረጉት ስብሰባ ተልእኳቸው ሊሳካ የሚችለው ሁሉም ካህን የፓ/ርኩን ጸረሙስና አቋም ሲደገፍ በመሆኑ ሁሉም ተሰብሳቢ ቤ/ክንን ከሚያስነቅፍ ተግባር እንዲታቀብና ለመልካም አስተዳደር መስፈን እንዲተጋ ብርቱ ማሳሰቢያ መስጠታቸው ሰማዕት ዘእንበለ ደም የሚያሰኝ ተግባር ነው!!!!

  ከመጋቤ ምስጢር ኩልክሙ ልዋስማ….ሊቁ እንዲህ ነበር ያሉት…
  …ወቤቴል አሀቲ ኢትኩን ዝርወተ፣
  አኃዝ ማኅበራተ
  መዋግደ ብዙኅ ጸጋከ ወአስተናድፍ ስርዓተ….
  ይሄን ሲያብራሩትም ‘አኃዝ’ ማለት ‘እሰር ዝጋ ማለት አይደለም ሁሉ በስርዓት ይሁን ማለት እንጅ’ ሲሉ አብራርተውት ነበር!!ሀሳባቸው ሀሳቤ ነው!!

  • WEB March 25, 2014 at 4:58 pm Reply

   በአማን ነጸረ, your stand is confusing. Do you blieve framing MK as ‘terrerist’ good for the church??? Do you think this is going to stop with just MK??? Do you support the corrupt group? Are you part of them??? please answer my questions, thank you.

   • በአማን ነጸረ March 26, 2014 at 9:08 am

    @WEB: ለጥያቄህ አመስግኘ ብጀምር ደስ ይለኛል፡፡አመሰግናለሁ፡፡
    1. ማኅበረቅዱሳን አሸባሪ ነው ብየ ትናንትም ዛሬም አላምንም፡፡አመራሩ የማኅበሩን ይፋዊ ልሳናት ከመጠቀም ይልቅ ማኅበራዊና የግል ህትመት ሚዲያዎችን ወደ መጠቀም ማዘንበሉን፣ “ለሃይማኖታቸው ሳይሆን ለማኅበረቅዱሳን እንሞታለን” የሚሉ አስተያየት ሰጭዎችም መረጃ ሳያጣሩ የማኅበሩ ስም በተነሳ ቁጥር ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንዲሉ(እኔ እንኳ ሆድ ያባውን ፌስቡክና ብሎግ ያወጣዋል ነው የምለው!!) ዘለው ኢህአዴግ ላይ መውጣታቸው “ኃጥዕ ሳያባርሩት ይሸሻል” እንድል እያደረገኝ ነው፡፡ቢሆንም ይህን አመለካከት የቅሬታ መጠቆሚያ እንጅ የአሸባሪነት ምልክት አድርጊ አላየውም፡፡ “ማኅበሩ እንደማኅበር አሸባሪ ነው ማለት በሬ ወለደ የማለት ያህል ነው” ካሉት እስማማለሁ፡፡
    2. በእኔ በኩል ቅ/ሲኖዶስ፣ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ጠ/ቤ/ክህነት፣አህጉረ ስብከቶች በየተዋረዳቸው ከሚሰጡት መመሪያ ውጭ የሚሄድ ሁሉ ስርዓታዊ አይደለም፡፡እንዲህ አይነት አካሄድ ሲኖር ቤ/ክ ከቻለች በራሷ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ስልጣን፣ ጉዳዩ ሀይል የተቀላቀለበት ሆኖ ጉልበት ከጠየቀም በሐዋ ስራ ም19 ቁ 39 እስከ40 መሰረት ሕግ ለማስከበር የተቀመጠውን መንግሥት እርዳታ ተጠቅማ ቤቷን የማስተካከል ሙሉ መብት አላት፡፡ችግር የሚመስለኝ በሰላም ሀገር መንግሥት ሳይጠራ እከሌ ዐይነውሃው ስላላማረኝ ላጥፋው ብሎ ደጀሰላሙን ከተራመደ ነው፡፡ እስካሁን እንደማየው መንግሥት በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ እኛ ወደ እሱ የምንሄደውን ያህል እሱ ወደ እኛ አልመጣም፡፡ስለዚህ ቢመጣም ችግር ፈጣሪ ስለመሆናቸው ማስረጃ ከያዘባቸው ግለሰቦች አልፎ መላዋን ቤ/ክ ላጥቃ ይላል ብየ አላምንም፡፡
    3. ማኅበረቅዱሳን ላይ ቅሬታ እንዳነሳ የሚያደርገኝ ሌላው ነጥብ ሁሌም ግለሰቦችን ስም እየሰጠ መክሰስ የሚጀምረው ቤ/ክንን የበደሉ እለት ሳይሆን ማኅበሩን የተቃወሙ እለት ነው፡፡በእነኚህ “ለምን ለእኛ ብቻ ለማኅበረቅዱሳንም ሕግ ይውጣ” የሚሉ ወገኖችም ላይ እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ሰዎቹ በቤ/ክ አስተዳደር ዙሪያ በትንሹ ከ10 አመት በላይ ቆይተዋል፡፡ነገር ግን ዘራፊነታቸው የሚነገረን ቤ/ክንን መዝረፍ በጀመሩ በ10ኛው አመት ነው፡፡ይሄ ደግሞ አሁንም ከማኅበሩ ጎን በመቆማቸው ብቻ ያልተጋለጡ ተተርጣሪ ሙሰኞችን ሁኔታ ሳይና በእነኚህ ለጊዜው ማስረጃ ያልቀረበበት የአሉባልታ ክስ ሰለባ የሆኑ ሰዎች ላይ የሚቀርቡትን ፍጹም ሚዛናዊነት የጎደላቸው ዘገባዎች ሳይ ጉዳዩ ለቤ/ክ ከመቆርቆር የመነጨ ሳይሆን የማኅበር ጥቅም ካለመ ቡድናዊ አካሄድ ሆኖ ነው የሚታየኝ፡፡
    4. ስለዚህ ለቤ/ክ ጥቅም ተብሎ ሳይሆን ለማኅበር ጥቅም ተብሎ የኢንተርኔት አክሰስ የሌላቸው አባቶቼ እንዲያው በየሜዳው ሲዘለፉ እያየሁ እንዳላየሁ ከማልፍ ገና ሳይከሰሱና ማስረጃ ሳይቀርብባቸው በማኅበራዊ ሚዲያው ስቅላት ከተፈረደባቸው አባቶቼ ጋር ብሰቀል ይሻለኛል፡፡አቋሜ ነው፡፡ይሄን ለማለት ሙሰኛ መሆን አይጠበቅብኝም፡፡በቤ/ክ ያደኩ የቤ/ክ ልጅ መሆኔ በቂ ነው፡፡ስለሆነም the right to be presumed innocent until proved guilty according to the law ከሚለው ዓለማዊ ሕግ በፊት ከመ ኢመፍትው ንገሥጽ ወኢመነኒ ዘእንበለ ያቅሙ ሎቱ ስምዐ ከመ አበሰ(እንደበደለ ሳያስመሰክሩ ማንንም እንቀጣ ዘንድ እንዳይገባ) የሚለውን ከ81ዱ አንዱ የሆነውን መጽሀፈ ዲስስቅልያ አንቀጽ 7 ገጽ 72 ማንበቤ በቂ ነው፡፡በይፋ ማስረጃ ቀርቦ በቤ/ክ አስተዳደርም ሆነ በፍ/ቤት የተፈረደባቸው ቀን ግን እንደእናንተ እኔም ሙሰኛ፣ጉቦኛ እላቸዋለሁ፡፡እስከዛው አባትነትና ወንድምነታቸውን እይዘዋለሁ፡፡

    በነገራችን ላይ በዲ/ዳንኤል ክብረት 4ቱ ኃያላን መጽሐፍ ውስጥ ካህናተ ደብተራ የተባሉ ህገ እ/ርን ሳይሆን ገጸ-ንጉሥን አይተው የሚናገሩ ሰዎች ስላሉ መጽሐፉን አንብበን ስድቦቻችንን በዛ መልኩ እንኳ ከዓለማዊነት እናውጣቸው!!

    መጽሐፉ ከመ ኢመፍትው የሚለውን በመንጋ ከመጣስ ይሰውረን!!እኛም ስለ ቤ/ክ ያገባናል ብለን ሀሳባችንን እንድንገልጽ መድረክ የሆነችንን ሐራ ተዋሕዶ ብሎግ በአቀራረቧ ኢ-ሚዛናዊነት ቅር ቢለኝም ልሳናችን ናትና ያሰንብታት!!

  • Anonymous March 26, 2014 at 5:38 am Reply

   Abet Nitsitsir ena digaf. Betekristyanin enawedim yemil meseri alama yalachewn bmrtut yesibseba adarash memezen?! Denkem maberariya Musinan enetseyefaln belwe yemifekru gin musegna yehonu Ato Alemayehu Atomsan endegedelu setesma min tesemah? Musinan tekawmu belhe atadenekachew. Musinan alesrume blena tekerakre

 18. Anonymous March 25, 2014 at 4:30 pm Reply

  ማኅበረ ቅዱሳን ከመንግስትም ሆነ ከሌሎች የእምነት ድርጅቶች ጋር ምንም ዓይነት ግጭት ሳይኖረው አክራሪነት የሚለው ብያሌ አልገልጠው ቢል በጽንፈኝነት አቋም በመበየን ለሕወሃት የስጋት ቀጠና ተብሎ ተፈረጀ፡፡ ለምን፤ የማኅበሩ አቋም ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ መሆን ነው፡፡ በሕገ መንግስቱም ቢሆን ፖለቲካና ሃይማኖች የተለያዩና አብረው የማይሄዱ መሆናቸው ተደንግጓል፡፡ የማኅበሩም አቋም ይሄው ነው፡፡ አመራሮቹ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አመራርነት ወይም አባልነት እንዳይሳተፉም ይደነግጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሕገ መንግስቱን ማክበርና መተግበር ነው እንጂ ጽንፈኝነት አይደለም፡፡
  አንድ መዘንጋት የሌለበት እውነት አለ፡፡ ሕወኃት/ኢህአዴግ ፖሊቲካዊ አቋሙን የሚነቅፍና የሚተች ተቃዋሚ ሰውን እንደማይወደው ሁሉ፤ ማንም ሰው ከሃይማኖቱ አስተምህሮ ጋር የማይስማማ ርዕዮተ-ዓለም የሚያራምድ የፖሊቲካ ፓርቲን/ድርጅትን ላይደግፍ ይችላል፤ አይደግፍምም፤ ይህ ደግሞ የብዙ ታጋዮች ደም የፈሰሰበትና ሕይወታቸውን ሁሉ ሳይቀር የሰውበት ዴሞክራሲያዊ መብቱ ነው፡፡ ያም ባይከበር ሰብዓዊ የእምነት ነጻነት መብቱ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔን አመለካከት/አይዲዮሎጂ፣ የእኔን ርዕዮት፣ የእኔን ፖሊሲና ስትራቴጂ ለምን አልተከተልክም ተብሎ ሊወቀስ፣ ሊከሰስ፣ ሊታሰር ወይም ሊገደድ አይገባውም፡፡ ለዚህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶም ዘጋቢ ፊልም ማዘጋጀት አያስፈልግም፡፡ ይልቅስ ዘጋቢ ፊልሙ በባሕልና ሃይማኖት አጠባበቅ ላይ፣ በአባይ ወንዝ ላይ፣ በአገር ፍቅር ላይ፣ በዕድገትና ብልጽግና ላይ፣ … ቢሆን መልካም ይሆናል፤ ሁሉንም ያስማማል፡፡ አንዱን ነጥሎ ለመምታት ታልሞ የሚዘጋጅ ከሆነ ግን ምናልባት “ከጥቅሙ” ጉዳቱ ሊብስ ይችላል፡፡ ያላሰቡትና ያልጠበቁት የፖሊቲካ ኪሳራና ውድቀትም ሊያስከትል ይችላል፡፡ የንብ መንጋ ካልደረሱበት አይደርስም፤ ከነካኩት ግን ሆ ብሎ ይነሳል፡፡ ኃይለኛ የዱር እንስሳትም እንዲሁ ናቸው፡፡ ክርስቲያኖችም እንዲሁ፡፡
  እኔም እንደግሌ ምንም እንኳን የማኅበረ ቅዱሳን አባል ባልሆንም በሚሰራው በጎ ሥራ ደጋፊና አድናቂ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ከግቢ ጉባኤ ጀምሮ አሁን እስካለሁበት የመንፈሳዊ ሕይወቴ መሠረት ከመጣል ጀምሮ በእምነቴ እንድጸና አድርጎኛል፡፡ በኅትመትና በኤሌክትሮኒክስ የብዙሃን መገናኛ ዘዴዎችም እያስተማረኝ ነው፡፡ እውነት ለመናገር ከንስሃ አባቴ ይልቅ ብዙ የሚመክረኝና የሚያስተምረኝ ይህ ማኅበር ነው፡፡ ምናልባት ይህ ማኅበር በሥነምግባር ባያንጸኝ ኖሮ አሁን ከምሰራበት መስሪያ ቤት “በኪራይ ሰብሳቢነት” ሥራ ተዋናይ እሆን ነበር፤ ደባል ሱስን ጨምሮ በመጥፎ ሥነምግባር ውስጥ እገኝ ነበር፤ ለተገልጋዮች ተገቢውን ክብር ባለመስጠትና በመልካም አስተዳደር እጦት መንግስትን እንዲያማርሩ አደርግ ነበር፤ መንግስትን የሚያስመሰግን መልካም ሥራ ላልሰራ እችል ነበር፡፡

 19. mulugeta March 26, 2014 at 5:13 am Reply

  መንግሥት ለመሆኑ አለ እንደ። መንግሥት ለዓላማው ተፈጻሚነት እስከረዱት ድረስ ሌባ ሆነ ጉቦኛ ሆነ ዘራፊ ጉዳዩ አይደለም። እነዚህ በመንግሥት ዘንድ ኃጢአት የሚሆኑት ሠዎቹ በመንግሥት ዘንድ የማያስፈልጉ ሲሆኑ ነው። የቤተ ክርስቲያናችን ችግር እኮ መንግሥት ራሱ ነው። መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን የአንድነት ምልክት በመሆኗ አይዎዳትም። ለምን አንድነትን እንደሚፈሩ አይገባኝም። እነርሱ ይፍሩት እንጅ መጽሐፉ ግን እኛ አንድ ብንሆን ጸጋውን እንዲያበዛልን እናምናለን። የአንድነት አምላክ ደግሞ ለክፉዎች አሳልፎ አይሰጠንም።

 20. Anonymous March 26, 2014 at 5:34 am Reply

  hulum be tewahido ashenafinte yifetsemale. Hodame hodun, woregnam afun yizo yikeral. Mahibere Kidusan Geta bekah kalew yifersal. Gin wyolacwe chel bilew mnegawen lemiyasbelu!!!!!!!

 21. Anonymous March 26, 2014 at 6:01 am Reply

  መስቀልንም አይቀበሉም ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ንግስት ኢሌኒ ወንድ አይደለችምና፡፡

 22. Anonymous March 26, 2014 at 6:48 am Reply

  ማኅበረ ቅዱሳን ከመንግስትም ሆነ ከሌሎች የእምነት ድርጅቶች ጋር ምንም ዓይነት ግጭት ሳይኖረው አክራሪነት የሚለው ብያሌ አልገልጠው ቢል በጽንፈኝነት አቋም በመበየን ለሕወሃት የስጋት ቀጠና ተብሎ ተፈረጀ፡፡ ለምን፤ የማኅበሩ አቋም ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ መሆን ነው፡፡ በሕገ መንግስቱም ቢሆን ፖለቲካና ሃይማኖች የተለያዩና አብረው የማይሄዱ መሆናቸው ተደንግጓል፡፡ የማኅበሩም አቋም ይሄው ነው

 23. Desta March 26, 2014 at 12:19 pm Reply

  Yemigerm new !!Ewnetegna abat metalin senil bedifret bechemistry ena bebiology yetemereku aymerunim malet minmalet new?Ene wedezih mahibere kidusan abal sihon betechristianin bemageligele destaye etif dirib new ;desyemilew degimo beminserabet office endihum belela bota bemenafikanina betehadiso endaninetek telek yale ewiket endinoren adergual mahibere kidusan begedamatina ene zerzirie bemalcherisew ageligilot tesemarten eyeseran new !menafikan yehone kalihone mahibere kidusanin yemikawem manim yale ayimesilegnim !minim bihon min be ageligilotachin tsenten eninoralen
  cher were yaseman!!

 24. WEB March 26, 2014 at 1:01 pm Reply

  በአማን ነጸረ March 26, 2014 at 9:08 am

  Thank you for your response. We will see who is in the right truck. I personally do not believe that MK is ‘akrari or thinfegna’. Of course I dont have detail knowledge about those group. I can see the trand of the government from the involvement of the “Federal Afairs..” whenever the letter is written to MK gets CC. I don’t undertand why this is happening. I don’t understand when you give order for your children the neighbor have to know. So I don’t agree with you that “…እስካሁን እንደማየው መንግሥት በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ እኛ ወደ እሱ የምንሄደውን ያህል እሱ ወደ እኛ አልመጣም፡፡ስለዚህ ቢመጣም ችግር ፈጣሪ ስለመሆናቸው ማስረጃ ከያዘባቸው ግለሰቦች አልፎ መላዋን ቤ/ክ ላጥቃ ይላል ብየ አላምንም፡፡..” for me, it seems that the government involve in the church affairs or the people in the church makes the government to be involved. This was said that “and hager and haimanot” which never said in their T-shirt (I don’t think they are members of mk). I don’t know how you explain this.

 25. Anonymous March 27, 2014 at 11:08 am Reply

  Mr.Corrupter,time for corruption is lapsed,Please Bring back the money that you have stolen from God.

 26. TEMESGEN KIBRU March 27, 2014 at 4:28 pm Reply

  Bzu gize yemahbere kidusan alamana telko yalgebachew ena tkm felagi sewoch betekrstianachnn kepoletika gar bemayaz lemeshersher leteken eyetegu ygegnalu. mabere kiduan lebetekirstianachnn yekome bekidusan sm yeteseyme baber nw. bergt tikit sgawe tikm yalachew bemahberu sm yemingdu shokakawoch ena swr sera yalachew alu .slezih enezih nachew yemiyanagut . Betechale meten enegnih mentro mawtat alebn.

 27. Anonymous March 27, 2014 at 7:08 pm Reply

  ማኅበረ ቅዱሳን ከመንግስትም ሆነ ከሌሎች የእምነት ድርጅቶች ጋር ምንም ዓይነት ግጭት ሳይኖረው አክራሪነት የሚለው ብያሌ አልገልጠው ቢል በጽንፈኝነት አቋም በመበየን ለሕወሃት የስጋት ቀጠና ተብሎ ተፈረጀ፡፡ ለምን፤ የማኅበሩ አቋም ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ መሆን ነው፡፡ በሕገ መንግስቱም ቢሆን ፖለቲካና ሃይማኖች የተለያዩና አብረው የማይሄዱ መሆናቸው ተደንግጓል፡፡ የማኅበሩም አቋም ይሄው ነው፡፡ አመራሮቹ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አመራርነት ወይም አባልነት እንዳይሳተፉም ይደነግጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሕገ መንግስቱን ማክበርና መተግበር ነው እንጂ ጽንፈኝነት አይደለም፡፡
  አንድ መዘንጋት የሌለበት እውነት አለ፡፡ ሕወኃት/ኢህአዴግ ፖሊቲካዊ አቋሙን የሚነቅፍና የሚተች ተቃዋሚ ሰውን እንደማይወደው ሁሉ፤ ማንም ሰው ከሃይማኖቱ አስተምህሮ ጋር የማይስማማ ርዕዮተ-ዓለም የሚያራምድ የፖሊቲካ ፓርቲን/ድርጅትን ላይደግፍ ይችላል፤ አይደግፍምም፤ ይህ ደግሞ የብዙ ታጋዮች ደም የፈሰሰበትና ሕይወታቸውን ሁሉ ሳይቀር የሰውበት ዴሞክራሲያዊ መብቱ ነው፡፡ ያም ባይከበር ሰብዓዊ የእምነት ነጻነት መብቱ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔን አመለካከት/አይዲዮሎጂ፣ የእኔን ርዕዮት፣ የእኔን ፖሊሲና ስትራቴጂ ለምን አልተከተልክም ተብሎ ሊወቀስ፣ ሊከሰስ፣ ሊታሰር ወይም ሊገደድ አይገባውም፡፡ ለዚህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶም ዘጋቢ ፊልም ማዘጋጀት አያስፈልግም፡፡ ይልቅስ ዘጋቢ ፊልሙ በባሕልና ሃይማኖት አጠባበቅ ላይ፣ በአባይ ወንዝ ላይ፣ በአገር ፍቅር ላይ፣ በዕድገትና ብልጽግና ላይ፣ … ቢሆን መልካም ይሆናል፤ ሁሉንም ያስማማል፡፡ አንዱን ነጥሎ ለመምታት ታልሞ የሚዘጋጅ ከሆነ ግን ምናልባት “ከጥቅሙ” ጉዳቱ ሊብስ ይችላል፡፡ ያላሰቡትና ያልጠበቁት የፖሊቲካ ኪሳራና ውድቀትም ሊያስከትል ይችላል፡፡ የንብ መንጋ ካልደረሱበት አይደርስም፤ ከነካኩት ግን ሆ ብሎ ይነሳል፡፡ ኃይለኛ የዱር እንስሳትም እንዲሁ ናቸው፡፡ ክርስቲያኖችም እንዲሁ፡፡
  እኔም እንደግሌ ምንም እንኳን የማኅበረ ቅዱሳን አባል ባልሆንም በሚሰራው በጎ ሥራ ደጋፊና አድናቂ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ከግቢ ጉባኤ ጀምሮ አሁን እስካለሁበት የመንፈሳዊ ሕይወቴ መሠረት ከመጣል ጀምሮ በእምነቴ እንድጸና አድርጎኛል፡፡ በኅትመትና በኤሌክትሮኒክስ የብዙሃን መገናኛ ዘዴዎችም እያስተማረኝ ነው፡፡ እውነት ለመናገር ከንስሃ አባቴ ይልቅ ብዙ የሚመክረኝና የሚያስተምረኝ ይህ ማኅበር ነው፡፡ ምናልባት ይህ ማኅበር በሥነምግባር ባያንጸኝ ኖሮ አሁን ከምሰራበት መስሪያ ቤት “በኪራይ ሰብሳቢነት” ሥራ ተዋናይ እሆን ነበር፤ ደባል ሱስን ጨምሮ በመጥፎ ሥነምግባር ውስጥ እገኝ ነበር፤ ለተገልጋዮች ተገቢውን ክብር ባለመስጠትና በመልካም አስተዳደር እጦት መንግስትን እንዲያማርሩ አደርግ ነበር፤ መንግስትን የሚያስመሰግን መልካም ሥራ ላልሰራ እችል ነበር፡፡

 28. Anonymous March 27, 2014 at 10:38 pm Reply

  በተለይ በአማን ነጸረ በሚል የምታቀርበው ሀሳብ ምንም ገንቢ ያልሆነ በደንብ ላጤነው ደግሞ የመሠርይ አካሄድ ነው። ምክንያቱም ሁለት ሶስት ጊዜ ያስነበብከው አንተም አቋም ይዘህ እንጂ ከራስህ የመነጨ እንዳይደለ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ማኅበሩ የመላአክት ስብስብ አይደለም ባለመሆኑም ስተቶች ሊታዩ ይችላሉ የሆኖ ሆኖ ማህበሩ በቤተ ክርስቲያን ዙሪይ ጉልህ አገልግሎት አለው እኔም ራሴ እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነት የማውቀው ብዙ ነገር አለ። ነግር ግን የአንተ አገላለጽ ግን አንዳንድ ጥቃቅን ነገሮችም እያነሳህ በዚህ አልስማማም ትላለህ ይህ ራሱ በማኅበሩ ላይ ያለህን ጥላቻ አለባብሰህ እያውራህው ነው። ለመሆኑ ለውጡን ለመቃወም የተነሱት እነማናቸው? በግልጽ እንደሚታወቀው አንድም የአንድ ጎሣ አባላትና ከፖለቲካው አመራር ይሁንታ ያገኙና የዚችን ቤተ ክርስቲያን አንድነት የማይሹ መሆናቸው ግልጽ ሆኖ እየታየ ነው። የአንተ አስተያየት እንደውም ከዛም የተሻገረ የሸር አካሄድ እንጂ አንድም የሚረባ አመለካከት የለውም። ለመሆኑ በተለይ በሃያ አመታት የታየው ቅሌት መቼም ታይቶ የማይታወቅ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ሳለ አንተ ስለአንድ ማኅበር ሥርዓት አለመያዝ ታውራለህ። በቤተ ክህነቱ ዙሪያ ያለው የጎሳ ሁኔታ ብዙውን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ከአካባቢው እንዲርቁ አድርጎአል። እንደውም አሁን ያሉት ካህናት እንደገና መፈተሽ የሚገባበት ወቅት ነውና አንተም ስታወራ መሠረታዊውን ነገር እየደፈጠጥክ የማይረባውን እንደ እውቀት ማሳያ እያደረግህ አታቅርበው።

 29. b sinegio April 4, 2014 at 7:22 pm Reply

  yemahberu achberbarinet D/n Mulugeta W/Geb. “mahbere kdusan weys mahbere seytan” betebalew meshafu bemigeba tegeltsoal yihem GUDACHEW endaynekabachew bzu tret madregachew behulu zend yetaweke new! Gn ahunm Egzi. Amlak beDemu yewajatn yihchn K/Bete K. /Mahbere Memenann/ ayitewenm weyolachu yebete krstiyan meslachu lemtamtatu!!! “Ewnet ewnet elach’huwalehu wede begoch beret/ Bete K. /beberu yemayigeba belela menged gn yemiweta ersu leba wembedem new….lebaw liserkna, liyard, liyatefam enji sl’lela aymetam ” Yohans wengel=10:-1-16

 30. nanucha April 7, 2014 at 2:54 pm Reply

  ማህበሩ ራሱን እንደሃይማኖት አድርጎ እየወጣ ያለ ተቋም ሆኗል….. የትምህክተኛ ፖለቲከኞችም መናከሪያም ሆኗል …. የትግሬ ሚካኤል የአማራ ሚካኤል የኤረትራው አቡነአረጋዊ….. እያለ በፖለቲካ አቋምና በዓለማዊ ትምህርት ደረጃ ሰዉ እንዲለያይ እያደረገ ያለ ድርጅት ነው……መስራቾቹንም እያጣ የመጣበት የአካሄድና የሙስና ችግር ተንሰራፍቶበታል…. ይህን ዶክመንት በደንብ አንብቡት ከዓመታት በፊት የተፃፈ ነው፡፡http://salsaywoyane.files.wordpress.com/2013/10/assocaition-of-saints-or-association-of-the-davil.pdf

 31. Anonymous April 11, 2014 at 7:11 am Reply

  Long Live MK!! Down with the enemy of the EOTC!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: