የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነትአ እና ሕገ ወጥነት የሚወነጀልበትን መሠረተ ቢስ ክሥ የሚያዳብር የአቋም መግለጫ የሚያወጡበትን ስብሰባ ቅዳሜ ለማካሔድ እየቀሰቀሱ ነው

ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳን

 • አማሳኞቹ ‹‹በግንቦቱ ሲኖዶስ ለውሳኔ ይቀርባል›› ያሉት የአቋም መግለጫ ከፖሊቲከኞችና ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞች ጋራ ግንባር የፈጠሩበትና የማኅበሩን መዋቅር እና አገልግሎት አዳክሞ ለመቆጣጠር አልያም አካቶ ለማፍረስ ለተያዘው የአስተዳደራዊ ርምጃ ውጥን ግብዓት የሚኾን ነው፡፡
 • የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር እና ሥራ አስፈጻሚ አባላት በደጅ ጥናትም ቢኾን ከፓትርያርኩ ጋራ በግንባር የመነጋገር ዕድል ካገኙና ፓትርያርኩም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ይዘው ሌላ ዙር ሰፊ ምክክር እንደሚያካሒዱ በገለጹሳምንት ጊዜ ውስጥ÷ ‹‹በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ለግንቦት ሲኖዶስ ውሳኔ ግብዓት የሚኾን የአቋም መግለጫ እናውጣ›› ለሚሉ አማሳኞች የስብሰባ ፈቃድ መሰጠቱና ፓትርያርኩም በስብሰባው ላይ ለመገኘት መስማማታቸው፣ ሰሞኑን የሚታየው የማኅበሩን እንቅሰቃሴ በአስተዳደራዊ ርምጃዎች የማሰናከልና አገልግሎቱን የማዳከም ርብርብ ውጫዊ ፖሊቲካዊ ግፊትም እንዳለበት አመላካች ኾኗል፡፡
 • ፓትርያርኩን በግንባር ያነጋገረው የማኅበሩ አመራር በአጠፌታው፣ የሚሰነዘርበትን ማንኛውንም ውንጀላ በፍትሕ አካል በሕግ አግባብ ከመፋረድ ጀምሮ በጥቅመኝነት፣ በፖሊቲከኝነትና በኑፋቄ ዓላማዎች የሚገፋውን የቀንደኛ አማሳኞች ክሥ በዐደባባይ ለመፈተንና ለማጋለጥ እንደሚሠራ ይጠበቃል፡፡

*                               *                              *

NebureEd Elias Abreha

ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ

 • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከሰጠው አቅጣጫ በተፃራሪ ‹‹የአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱን ዳግመኛ መገምገም›› በሚል በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስም ተሠይመው የጥናት ሰነዱን በተጽዕኗቸው ሥር ካስገቡት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ እና አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ጋራ ጥብቅ ቁርኝት ፈጥረው የሚንቀሳቀሱት አማሳኞቹ እነ ኃይሌ ኣብርሃ እና ዘካርያስ ሐዲስ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ሀብትና ንብረቱን ያስረክብ›› በሚል በጠሩት ስብሰባ ላይ የማይሳተፉ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችን በመፈረጅና የሓላፊነት ቦታቸውን በማስነጠቅ ጭምር ለማስመታት እየዛቱ ናቸው፡፡
 • ‹‹ድምፃችን አልተሰማም›› የሚሉ የተቋማዊ ለውጥ ደጋፊዎች በበኩላቸው፣ በአማሳኞቹ የተጠራውን ስብሰባ÷ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱ የደረሰበትን ለማወቅ እና በማኅበሩ ላይ አላግባብ የሚደረገው ተጽዕኖ እንዲቆም ወደሚጠይቅ ትዕይንት ለመለወጥ እየተዘጋጁ ናቸው፡፡
 • ፓትርያርኩ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞችን ለአማካሪነትና ለረድእነት ባቀረቧቸው ግለሰቦች አሳላፊነት በየዕለቱ ለማለት በሚቻል ኹኔታ እየተቀበሉ ከመማከር ባሻገር በስብሰባቸው ላይ ለመገኘት ፈቅደዋል መባሉ ለመልካም አስተዳደር፣ ፍትሕና ርትዕ ከሚናገሩበት ሞራላዊ ሥልጣን እንደሚያሰናብታቸው እየተነገረ ነውውጤቱም ቤተ ክርስቲያናችንን የርስ በርስ ትርምስ ውስጥ በመጨመር ተቋማዊ ህልውናዋን ለከፋ አደጋ እንዳያጋልጠው አስግቷል፡፡
Advertisements

10 thoughts on “የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነትአ እና ሕገ ወጥነት የሚወነጀልበትን መሠረተ ቢስ ክሥ የሚያዳብር የአቋም መግለጫ የሚያወጡበትን ስብሰባ ቅዳሜ ለማካሔድ እየቀሰቀሱ ነው

 1. TIRSIT March 21, 2014 at 7:24 am Reply

  አባታቶቻችን እባካችሁን የጥቅምት ሲኖዶስ ላይ ያሳያችሁንን ቁርጠኝነት ድገሙልን አባታችን ቃልዎት አክባሪ ያድርግልን፣ አፅራረ ቤተክርስትያንን ልብ ይስጥልን ጌታ ከእኛ ጋር ይሁን

 2. Anonymous March 21, 2014 at 7:32 am Reply

  ይህ ዓይነቱ ችግር ያለጸሎት አይጠፋምና ሁሉም በያሉበት እንዲጸልዩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

 3. Anonymous March 21, 2014 at 8:40 am Reply

  ቤተ ክርስቲያናችንን ሊያጠፉ ከተነሱት ግለሰቦች ብዙዎቹ የቤተክርስቲያን እውቀት የሌላቸው ፤ በጉቦና በሙስና የሚታወቁ ና አስመሳይ ፖለቲከኞች ናቸው ከነዚህ መሀከል የሰዓሊተ ምህረት ቤ/ክ ጸሀፊ የሆኑት ዲያቆን ሩፋኤል የማነብርሀንና ሂሳብ ሹም የሆኑት አቶ ዘርዐብሩክ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
  ግን ደግሞ መቼም ቢሆን እግዚአብሄር ከጥፋት ሀይሎች ቤቱን ይጠብቃል ለዚህም የቤተክርስቲያን ታሪክን ማንበብ በቂ ነው፡፡ ወራትን እየጠበቁ ለማውገዝ ቢሞክሩም እውነትን እስካልያዙ ድረስ የትም አይደርሱም ምክንያቱም የእውነት አምላክ ቤቱን ይጠብቃል፡፡

 4. በአማን ነጸረ March 21, 2014 at 10:30 am Reply

  ንቁም በበህላዌነ!! መልእክቱ ለማኅበረ ቅዱሳን ነው!!

  ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት 22 አመታት ለቤ/ክ ፈጸማቸውን መልካም ተጋድሎዎች የሚክድ አእምሮ የለኝም፡፡በተለይ በግቢ ጉባኤና አጽራረ ቤ/ክንን በመዋጋት ረገድ ጉልህ ተጋድሎዎችን ፈጽሟል፡፡በዚህ ተጋድሎው ውስጥ ማኅበሩ የሰዎች ስብስብ ነውና የፈጸማቸው ስህተቶችም ነበሩ፡፡በተለይ ለቤ/ክህነቱ አስተዳደር ያለው አመለካከት ሊሆን የሚገባውን ነው ለማለት አልችልም፡፡በማኅበሩ አመራር ዙሪያ ባሉ ሰዎች በአጥቢያ ደረጃ ካለው የቤ/ክ አስተዳደር ጀምሮ ላዕላይውን መዋቅር እንደሽፋን ሰጭ እንጅ እንደ አጋርም ሆነ እንደ ራስ አካል ተቀብሎ ያለመሄድ አዝማሚያ ነበር፡፡ስለዚህ አሁን ወደ አደባባይ እየወጣ ያለው አለመግባባት የ22 አመት የዞረ ድምር ነው፡፡እስካሁን እንዲህ አፍጥጦ ያልመጣው ሊቃነጳጳሳቱን ጨምሮ በብዙሀኑ የካህናት ወገኖች ነገሩን ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ብቻ የሚያያዝ አድርጎ የመረዳት የተሳሳተ ግንዛቤ ስለነበረ ነው፡፡ችግሩ በእሳቸው ማለፍ አለማለፉን ሲረዳ የችግሩን ስር ለመረዳት ሁሉም እድል አገኘ፡፡
  አሁንም እላለሁ፡፡የማኅበሩን ክፉ አያሰማኝ፡፡እ/ር ዐላማውን በትክክለኛው መንገድ እንዲያሳካ አብሮት ይሁን፡፡የነዛ የየግቢ ጉባኤው ንጹሀንና ትጉሃን የቤ/ክ ልጆች ጸሎት ይጠብቀው፡፡በአባቶች እግር ስር ሆኖ ከሕግ በታች ለአገልግሎት የመፋጠን ተልእኮውን እንዲወጣ አምላከ ቅዱሳን ይርዳው፡፡ጸሎቴ ነው፡፡
  አሁን ቅሬታየን እናገራለሁ፡፡
  1. በፍትሕ አካል በሕግ አግባብ መፋረድ፣በዐደባባይ መፈተንና ማጋለጥ፣ድምጻችን ይሰማ የሚል ትእይንት ማካሄድ…የሚሉት አካሄዶች ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ለማኅበሩም አይጠቅሙም፡፡በዚህ አይነት ድርጊት ማኅበሩ ራሱን ያስከብራል ማለትም ‘ያለ አዋቂ ሳሚ’ ምክር ነው፡፡ማኅበሩ ተጠሪነቱ ለጠ/ቤ/ክህነት ይመስለኛል፡፡ስለዚህ ይህ አካል ማኅበሩ አካሄድ ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ የማሳረፍ መብት አለው፡፡ማኅበሩ በውሳኔው ቅር ከተሰኘ ለቅ/ሶኖዶስ ይግባኝ ማለት ነው፡፡ከዚህ ውጭ ማኅበሩ በፌደራል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተመዘገበ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሳይሆን በቅ/ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመ ሃይማኖታዊ ማኅበር ስለሆነ በዓለማዊ ሕግ መብቱን ሊያስከብርበት የሚችል መሰረት ያለው አይመስለኝም፡፡ ስለሆነም አለማዊ ሕግን እንደ አማራጭ ማየቱ አዋጭ አይደለም፡፡ቤ/ክ የራሷ ፍርድ ቤት ይቋቋምላት እያለ ብዙ ከተናገረና ከጻፈ ማኅበርም ይሄ ችግር ወደ ዓለም ይዞ መፍትሄ ፍለጋ የመሄድ አዝማሚያ ያስተዛዝባል፡፡
  2. በዐደባባይ መፈተንና ማጋለጥ የምትሉትም ከመደጋገሙ የተነሳ እየቸከ ነው፡፡ቢሆንም በቂ ማስረጃ ካለ አደባባይ መውጣት ሳያስፈልግ ለሚመለከተው የቤ/ክህነትም ሆነ የቤ/መንግሥት አካል በማቅረብ መፍትሄ ማግኘት ይቻል፡፡በ2ቱም መንገዶች ተስፋ መቁረጥ አይገባም፡፡ድምጻችን ይሰማ…የሚለው የአደባባይ ትእይንት አካሄድ ላይ ማስተዋል ይገባል፡፡ቃሉ ራሱ ‘የአወሊያ’ ቅጅ ስለሚመስል ለመንግሥት ፍረጃ እና እርምጃ ራስን አመቻችቶ ሰማዕት ዘበከንቱ መሆን ነው፡፡ ኋላ ትእይንቱ ወደ አልሆነ መስመር ቢቀየር ማኅበሩን እንደ ማኅበር ቤ/ክንን እንደ ሃይማኖት ተቋም ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡እናስተውል፡፡በዚህ ትእይንታዊ አካሄድ ተጠቃሚ የለም፡፡አስቀድሞ …የርስ በርስ ትርምስ ሊፈጠር ይችላል… እያሉ ሙዋርት የተጫነው ቅስቀሳ ማካሄድም ትንቢት ሳይሆን እንደ ድሮው ዘመን ‘አትነሳም ወይ’ አይነት መፈክር ሆኖ ነው የሚሰማኝ፡፡ይህ መልእክት ገንቢ አይደለም፡፡
  3. ሌላ ቅር ያለኝ ነገር አለ፡፡በእናንተ ተቃዋሚ የተሰኙ የቤ/ክ ወገኖች ‘ማኅበሩ ሀብትና ንብረት ያስረከብ’ ብለዋል ተብሎ እንደ ክስ የቀረበው ጉዳይ አላሳመነኝም፡፡ምናልባት ሰዎቹ ማኅበሩ የንብረቶቹን ገቢ መጠቀም አይችልም ቢሉ እኔም እንደእናንተ እቃወማቸው ነበር፡፡ነገር ግን ንብረቶቹ ባለቤትነታቸው በቤ/ክህነት ስር ሆኖ ማኅበሩ ለቤ/ክህነት በቃለ አዋዲው መሰረት ከገቢው 20 በመቶ እየከፈለ ሌላውን አገልግሎቱን ለማፋጠን እንዲጠቀም የሚል አቋም እስካራመዱ ድረስ በምንም መልኩ አማሳኝ እና ፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ የሚል ከሲኖዶስ የቀደመ ህዝባዊ ውግዘት ሊሰነዘርባቸው አይገባም፡፡ አሁንም መደረግ ያለበት ነው፡፡ማንኛውም የማኅበሩ ንብረት ስመ-ንብረቱ (ownership title) በቤ/ክህነት ስር ሆኖ ነገር ግን ገቢው በማኅበሩና በሚመለከተው የቤ/ክህነት ኃላፊ ጥምር ፊርማ እየወጣ በማኅበሩ ለተቀረጹ ፕሮጀክቶችና አገልግሎቶች ማስፈጸሚያ ይዋል ቢባል ደስታየ ነው፡፡
  4. እንረጋጋ፡፡በተለይ ኦርቶዶክሳዊ ቀናኢ ወጣቶች እናስተውል፡፡ማኅበር የሚኖረን ቤ/ክ ስትኖረን ነው፡፡እስካሁን ማኅበሩ ይፍረስ ብሎ የተነሳ የቤ/ክህነት ወገን የለም፡፡በዚህ ላይ አባታችን የማኅበሩን አመራር ተቀብለው ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡እሱ ቀጠሮ አልተሰረዝም፡፡ስለዚህ ድምጻችን በማኅበሩ አመራር በኩል እንዲሰማ ማድረግ ትልቅ እድል ነው፡፡ለባእዳን ሀሜት የሚያጋልጠውን የአደባባይ መጋፈጥና ትእይንት ወደ ጎን ብለን ከጾሙ ጋር የሚሄደውን የተረጋጋ ምክክር ማካሄድ አንድም ስርአታዊ ነው አንድም ህጋዊ ነው፡፡ፓትርያርኩ እነ እከሌን ለምን አነጋገሩ እያሉ ሰልፍ መውጣት ከማን ጋር መነጋገር እንዳለባቸውም እኛ ነን የምንወሰነው ወደ ማለት ስለሚመራ ከፍትህም ከህሊና ፍርድም ውጭ ነው፡፡እናስተውል፡፡እኛም ሆነ ማህበሩ የሚጠቀመው በሕገ ቤ/ክ እስከተመራን ድረስ ነው፡፡እሱ ካልገዛን ያው የወታደር ቆመጥ ይመዘዛል፡፡ በእሱ ማንም ሳያሸንፍ ሁላችንም እንወድቃለን፡፡ቅ/ቤ/ክንንም እናስነውራለን፡፡በተለይ አመራሩ፡ ቅን የሆኑና ማኅበሩ የተናገረውን ሁሉ በማንኛውም አማራጭ እናስፈጽማለን የሚሉ ብሩሃን ተከታዮቹን መንፈሰ-ቀሊልነት ተጭኗቸው ወደ አልሆነ መስመር እንዳይገቡ አግባብነት ያለው መልእክት የማስተላለፍ ኃላፊነት አለበት፡፡ካለአዋቂ ሳሚ የህትመት ውጤቶችና ‘ወደቀ ሲባል ተሰበረ’ ከሚሉ ብሎገሮችም ራሱን አግልሎ ማለት የሚገባውን በልሳናቱ ብቻ ቢል ጥሩ ነው፡፡
  ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድህነነ እመዐተ ወልዳ!!

 5. Anonymous March 21, 2014 at 11:57 am Reply

  mehabere kidusan zarem negem yenoral mareyamine!!!!!

 6. ms March 21, 2014 at 12:54 pm Reply

  ማኅበሩ ስነ ስርዓት ቢያደርግ ይበጃል! ሰለጀመር ለቤተ ክርስትያን ጥብቅና ብቻ የቆመ ኣይደለም! ጥሩ ስራ ሰርተዋል ብየ የማምነው በግቢ ጉባኤ ብቻ ነው! ከዛ ውጭ የፖሎቲካ ወገንተኝነት የሚያንጸባርቅና የቤተ ክርስትያኒቱን ተቋማዊ ሰውነት በጠራራ ጸሐይ የሚቃወምና የሚጥስ ሆኖ ተገኝተዋል! በሰዓቱ ራሱን ካላስተካከለ ኣደጋ ላይ ነው!

 7. Anonymous March 21, 2014 at 1:05 pm Reply

  “የርስ በርስ ትርምስ ውስጥ በመጨመር ተቋማዊ ህልውናዋን ለከፋ አደጋ እንዳያጋልጠው አስግቷል” እናንተ ያላችሁት ካለሆነ እንከፍላታለን ማለታቹ ነው? እንደ አባቶቻቹ? የተሰበሰባቹት ለመክፈል እንደሆነ ያሰያል በጣም ያሳዝናል

 8. andualem March 21, 2014 at 1:59 pm Reply

  betekrstiyan yetmolachiwu beleboch slehone yemitarubet gizewu kirb newu wanawu wede egziabher mechoh newu

 9. andualem March 21, 2014 at 2:03 pm Reply

  ቤተ ክርስቲያንን የከበቧት ክርስቶስንና እመቤታችንን የማያውቁ ለሆዳቸውና ለክብራቸው ያደሩ ስለሆነ ለሁሉም እንደስራው የሚከፈልበት ጊዜው ቅርብ ነው፡፡

 10. Anonymous March 21, 2014 at 10:38 pm Reply

  I appreciate በአማን ነጸረ comments and I also agree the contribution of MK in the universities. But, we tried to show you guys how you can change your strategy to move forward and contributing to mother church, EOTC. But, you kept insulting as TEHADISO and consider your selves as a guard for the church. We all born in and growing up for the church. We also told you that you are touching the RED LINE of the church and the government. As a result, you are facing now the cumulative results of what you did for the last 22 years. Truly speaking you guys deserve it and the church need to get red of this evil association as soon as possible.

  Believe me, if you are standing to fight the government and likawinte bête-Christian, you will pay more. Stop and see what GOD want to do our church. PLEASE, PLEASE, PLEASE stop your propaganda. You killed many scholars of the church including; Abune Paulos, Abune Mereha Kirstos, Abune MIchael….and Megabi Biluye Seife ( MK is anti-Tigray and Gojjam).

  “የርስ በርስ ትርምስ ውስጥ በመጨመር ተቋማዊ ህልውናዋን ለከፋ አደጋ እንዳያጋልጠው አስግቷል” እናንተ ያላችሁት ካለሆነ እንከፍላታለን ማለታቹ ነው? Who are you after all. We know you very well. you are nobody for the church. NOTHING WILL HAPPEN AS WE ARE READY TO CONTROL EVERYTHING IN A PROFESSIONAL AND A SPIRITUAL MANNER. WE WERE WORKING DAY AND TIME FOR THE LAST 3 YEARS.

  YES, “ABUNE PAULOS AND MELES ARE DEAD BECOUSE OF YOUR PRAYER/MERGEM”. BUT THEIR LEGACY AND DIRECTION WILL CONTINUE AS THE MOTHER CHURCH IS THE MAIN INSTITUTION WORKING WITH THE GOVERNMENT COLLABORATIVELY. NOW YOU CAN CRY, THIS IS YOUR TIME TO CRY….LOL!

  ሰጀመር ለቤተ ክርስትያን ጥብቅና የቆመ ኣይደለም! የፖሎቲካ ወገንተኝነት የሚያንጸባርቅና የቤተ ክርስትያኒቱን ተቋማዊ ሰውነትየሚቃወምና የሚጥስ ሆኖ ተገኝተዋል! ማኅበሩ ኣደጋ ላይ ነው! ማኅበሩ ስነ ስርዓት ቢያደርግ ይበጃል! Most of the MK council members will be in jail the near future and will pay for all. Those who are residing in USA and Europe will never come to Ethiopia as a citizen and follower of EOTC. We will see how your abroad politics will work.

  May the caring God gives you His wisdom to see His love and mercy!

  እ/ር ዐላማውን በትክክለኛው መንገድ እያሳካን ያለን ንጹሀንና ትጉሃን የቤ/ክ ልጆች የመፋጠን ተልእኮውን እንድንወጣ አምላከ ቅዱሳን ማኅበሩ ብዙ ዋጋ እንደከፍል እየእዳን ነው!፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: