የፓትርያርኩ የለውጥ ተስፋዎች ወዴት ገቡ?

Your Holiness Listening the quest for change mgt

ቤተ ክርስቲያን ለተቋማዊ ለውጥ ትጣራለች፤ መልስም ትጠብቃለች!!

  • አቡነ ጳውሎስን ሲያሳስቱና ሲያጋጩ የነበሩ ጎሰኛ እና አማሳኝ ግለሰቦች አኹን ምናልባት ከዚያ ቦታ ሳይነሡ እርስዎንም ወደዚያ የጥፋት ሣጥን አስገብትዎት መውጫ አሳጥዎት ከኾነ እባክዎ ወደ ልቡናዎ ተመልሰው ቃል የገቡባቸውን የለውጥ ተስፋዎች ለመተግበር ይነቃቁ፡፡
  • የመንግሥት ፖሊቲካዊ ጫና ሳያስፈራዎ፣ መንፈሳዊ የለውጥ አባትነትዎን በተግባር ያሳዩን፡፡ የለውጥ ሥራዎ አብቦና ፍሬ አፍርቶ ለማየትና ለመጠቀም ጉጉት አለን፡፡

(ሪፖርተር፤ ይድረስ ለሪፖርተር፤ ቅጽ 19 ቁጥር 1448፤ እሑድ፣ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም.)

reporter-issue-1448በመጀመሪያ የአክብሮት ሰላምታዬን ለቅዱስ ፓትርያርኩ በማቅረብ የተሰማኝን ለመግለጽ እወዳለኹ፡፡ ቅዱስነትዎ በመጀመሪያ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አባት ኾነው ወደ መንበሩ በመምጣትዎና አንድ ዓመትዎን በማክበርዎ እንኳን ደስ አልዎ በማለት መልእክቴን አስተላልፋለኹ፡፡

ወደ ሓላፊነት ሲመጡ ብዙ የለውጥ ተስፋዎችን በብዙኃን መገናኛዎች አስተላልፈዋል፤ ‹‹አይዟችኹ፣ ለውጥ ይመጣል›› ሲሉ ተናግረውም ነበር፡፡ እኔም በቤተ ክርስቲያናችን የተስፋፋውን ጎሰኝነትና አማሳኝነት በአጠቃላይ ያለው ብልሹ አሠራር ይለወጣል ብዬ እጅግ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ እርስዎም በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣሉ ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር፤ ነገር ግን ከተወሰኑ ወራት በኋላ ድምፅዎን መስማት፣ እርስዎንም ማየት ባለመቻሌ ፍርሃት አደረብኝ፡፡

በርግጥ ቀደም ሲል የነበረው የዘረኝነትና የአማሳኝነት ሰንሰለት አዲስ ለውጥ ለማምጣት ከባድ ሊኾንብዎ እንደሚችል እገምታለኹ፡፡ አቡነ ጳውሎስን ሲያሳስቱና ሲያጋጩ የነበሩ ጎሰኛ እና አማሳኝ ግለሰቦች አኹን ምናልባት ከዚያ ቦታ ሳይነሡ እርስዎንም ወደዚያ የጥፋት ሣጥን አስገብትዎት መውጫ አሳጥዎት ከኾነ እባክዎ ወደ ልቡናዎ ተመልሰው ቃል የገቡባቸውን የለውጥ ተስፋዎች ለመተግበር ይነቃቁ፡፡

ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ሲነሡ መሰናክሉ ብዙ እንደኾነ ይሰማኛል፡፡ ይኹንና በአገራችን የተፈጠረው የዘር በሽታ ሳያደናቅፍዎና ለአሉባልታ ወሬ ጆሮ ሳይሰጡ ለመሥዋዕት እንደመጡ ተናግረዋል፡፡ የመንግሥት ፖሊቲካዊ ጫና ሳያስፈራዎ፣ መንፈሳዊ የለውጥ አባትነትዎን በተግባር ያሳዩን፡፡ የለውጥ ሥራዎ አብቦና ፍሬ አፍርቶ ለማየትና ለመጠቀም ጉጉት አለን፡፡

በፈጣሪም በሰውም በታሪክም እንዳይወቀሱ ቃል ከገቡበት የለውጥ ጎዳና ወደ ኋላ እንዳይሉ አስተያየት ለማቅረብ እወዳለኹ፡፡

መብራቱ መረሳ

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ

Letters to the reporter

Advertisements

2 thoughts on “የፓትርያርኩ የለውጥ ተስፋዎች ወዴት ገቡ?

  1. Anonymous March 19, 2014 at 7:26 am Reply

  2. […] የፓትርያርኩ የለውጥ ተስፋዎች ወዴት ገቡ?With 1 comment […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: