የአብነት መምህራኑ የምክክር ጉባኤ እገዳ የስልታዊ ጫና ማሳያ ነው

(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፬ የካቲት ፳፻፮ ዓ.ም.)

FACT Magazine cover,Yekatitማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ላይ በፓትርያርኩ ደብዳቤ የተጣለው እገዳ በማኅበሩ ላይ ይደረጋል ለሚባለው ስልታዊ ጫና ማሳያ እንደኾነ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለፋክት መጽሔት ገለጹ፡፡

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሚጠራቸው አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን የተመለከቱ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር መድረኮች ላይ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካላት ይኹንታ የተቋቋሙ የወጣት ማኅበራት አደረጃጀቶች የአክራሪዎች ምሽግ እንደኾኑ በግልጽ የሚቀርቡ ክሦች መኖራቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአመራር አካሏ በኾነው በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ መተዳደርያ ደንብ አጽድቃ የአገልግሎት ይኹንታ የሰጠችው ማኅበር ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ የኾነው ማኅበረ ቅዱሳን መኾኑን ምንጮቹ አረጋግጠው፣ ሚኒስቴሩ በዚኽ ማኅበር ውስጥ መሽገዋል የሚላቸውንና ለይቶ የማይጠቅሳቸውን አካላት እየተጠቀመና ማኅበሩ ለፀረ ዴሞክራሲ ፍላጎቶች ከለላ እንደኾነ በመክሠሥ፣ ዕውቅናና ይኹንታ ከሰጡት የሃይማኖት አባቶች ጋራ ‹‹ውጦአችኋል፤ መቆጣጠር አልቻላችኹም፤ ከአቅማችኹ በላይ ኾኗል፤ መሥመር አላስገባችኋቸውም›› በሚል ፍጥጫ ውስጥ እንዲገባ ስልታዊ ጫና እተየፈጠረበት ነው ብለዋል፡፡

An Accomplished Scholars of the Ethiopain Orthodox Tewahido Church Traditional Schools

ማኅበሩ ከየካቲት 7 – 9 ቀን 2006 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል፣ በብሔራዊ ሙዝየም አዳራሽ እና በኢትዮጵያ ባህል የስብሰባ ማእከል ያዘጋጀው ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ ከቀትር በኋላ ፓትርያርኩ ለዋና ሥራ አስኪያጁ በጻፉት ደብዳቤ መታገዱ ተዘግቧል፡፡

በዐሥራ አንደኛው ሰዓት የተጻፈው ደብዳቤ ለእግዱ የሰጠው ዋናው ምክንያት፣ ማኅበሩ የጉባኤውን መካሔድ ለሚመለከተው አካል ካለማሳወቅ ጋራ የተያያዘ ቢኾንም የማኅበሩ አመራሮች ጉባኤው ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በሚያውቀው የማኅበሩ ዓመታዊ ዕቅድ የተካተተና መምህራኑ የተጋበዙባቸው አህጉረ ስብከት ከአንድ ወር በፊት እንዲያውቁት ተደርጎ መምህራኑ በየአህጉረ ስብከቱ ዕውቅና ለጉባኤው የተጋበዙ መኾናቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል፡፡

በመሀል ለተፈጠረው የተግባቦት ክፍተት የማኅበሩ ጽ/ቤት ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን በደብዳቤ ይቅርታ መጠየቁ ተገልጧል፡፡ ይኹንና ለጉባኤው ተዘጋጅተው የነበሩት የአብነት ት/ቤቶችን ወቅታዊ ተቋማዊ ኹኔታ የተመለከቱ አጀንዳዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ በመኾናቸው የማይደራደርባቸውና ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ጋራ በመነጋገር መከናወናቸው አይቀሬ መኾኑን የማኅበሩ አመራሮች ማስታወቃቸውን ምንጮቹ ለፋክት መጽሔት ገልጸዋል፡፡

slide presentation by Dr. Shiferaw000

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነት ማብራሪያዎቻቸውና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ በሐዋሳ – ሌዊ ሪዞርት ጥር ፴ እና የካቲት ፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ለተካሔደው የሃይማኖት ተቋማት ምክክር ጉባኤ ካቀረቡት ስላይድ

Advertisements

6 thoughts on “የአብነት መምህራኑ የምክክር ጉባኤ እገዳ የስልታዊ ጫና ማሳያ ነው

 1. Anonymous February 23, 2014 at 4:05 pm Reply

  MAHIBERU HULEGIZEM YENORAL MAHIBERUN LEMATEFAT YEMITERU GENE WOLADITE AMELAKEN ELACHIHUALEHU YETEFALU

 2. በአማን ነጸረ February 24, 2014 at 12:18 pm Reply

  የአብነት መምህራኑ የምክክር ጉባኤ እገዳ የስልታዊ ጫና ማሳያ ሳይሆን በማኅበረቅዱሳን የተግባቦት ክፍተት ምክንያት የሚመለከተው የቤ/ክ አካል ሥርዓት ለማስጠበቅ ሲል የወሰደው እርምጃ ነው!!
  1. የተመስገን ደሳለኝ ፋክት ‘የቤ/ክህነት ምንጮች’ የምትላቸውን ተውት!! እናውቃቸዋለን!! የመረጃ ምንጩ ፍሰት ሁሌ የተቃውሞ ድምጽ ወደሚያስታጋቡ የህትመት ሚዲያዎች ብቻ ማዘንበሉም የአመራሩን የፖለቲካ ገለልተኛነት ለማሳየት እንደሚረዳ እንቆጥርላችሁዋለን!!ይሄ ነው እንጅ ገለልተኛነት!!ጎበዞች!!ለነገ ቀጣሪዎቻችሁ ዛሬ ምንጭ መሆን ከሲቪ በላይ ዋጋ አለው!!ደግሞም ፖለቲካ ማለት መንግስትን መደገፍ ብቻ እንጅ ከተቃዋሚዎች እና ከተቃዋሚ ሀሳብ አራማጆች ማበር ማለት እንዳልሆነ በቅጡ እያሳያችሁን ነው!!ይበል!!
  2. እናንተ የማኅበረቅዱሳን መራህያን፡ ብታውቁ ጫናው ሁሉ የሚመነጨው ከእናንተ መስመር ያልተከተለ አካሄድ ጭምር እንጅ ከቤ/ክህነቱ ብቻ አልነበረም!!ባይሆንማ ነጋ ጠባ ቁምስቅላቸውን ስታሳዩአቸው የኖሩት አባት ሲያርፉ ጫናውም ይጠፋ ነበር!!ግን አልጠፋም!!ድሮም ከእሳቸው አልመነጨማ!!ስለዚህ ንቁ!!መስመር ጠብቁ!!መፍትሄው እሱ ነው!!በተረፈ ለተፈጠረው የተግባቦት ችግር ይቅርታ መጠየቃችሁና ለወደፊቱም ከሚመለከታቸው የቤ/ክ አካላት ጋር በመነጋገር ለመስራት መወሰናችሁ እሰየው ነው!!እንዲህ ተዋረዱን ጠብቃችሁ በሥርዐት ስትራመዱ ከጎናችሁ ለመቆም አናመነታም!!
  3. “አንደራደርም” የሚለውን ፉከራ ይሁን ዛቻ ግን ተውት!!ይሄ ጉዳይ በአግባቡ ይሁን ተባለ እንጅ የሊቃውንትን ነገር በመርህ ደረጃ ማንም ወገን ለድርድር አላቀረበውም!!ባልተጀመረ ጦርነት ጥይት አታባክኑ!!ሲጀመር እናንተን ተደራደሩ ያለ ሰው የለም!!ምክንያቱም አጋዥ-ንዑስ ክፍል ናችሁ!!ቤቱን ወክሎ የመደራደርና ያለመደራደር ስልጣንና መብት ያለው ለተግባቦት ችግራችሁ ይቅርታ የጠየቃችሁት ክፍል ነው!!አህጉረ ስብከቶች ናቸው!!ጠ/ሚኒስቴር እያለ የዞን አስተዳደር ለድርድር ተልኮ አያውቅም!!በእናንተና በጠቅላይ ቤ/ክህነት መሀል የዞን አስተዳደርና የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት የሚያህል ልዩነት አለ!!
  4. ደግ ለመስራት-ለትሩፋት ተነሳን ካላችሁ ከልጅ የሚጠበቀውን እያደረጋችሁ አባቶችንና ቤ/ክንን ተራዱ!!ከዛ ውጭ ለስንትና ስንት አመታት ካለእናንተ እርዳታ ከነሊቃውንቱዋ የኖረችው ቤ/ክ እናንተ ከሌላችሁ እሱዋም ሆነ ሊቃውንቱዋ እንደሚጨልምባቸው በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለማስረዳት መለፈፋችሁን ለመቀበል ያዳግተናል!!ግዴላችሁም ይቺን የተርእዮ አባዜ አሸንፉዋት!!አባቶቻችን ብሶታቸውን እንደናንተ በህቡእ ሳይሆን በአደባባይ “አታስቆጡን” እያሉ መንግስትን ፊትለፊት የሚሞግቱ ናቸው እኮ!!በእነሱ አናፍርም!!እናምንባቸዋለን!!ስለዚህ እነሱ የሚሉዋችሁን ስሙ፣የሚያዙዋችሁን ፈጽሙ!!ያንጊዜ አብረናችሁ እንጮሀለን!!ያለበለዚያ ‘አይ ልማዳቸው ነው’ እያልን እናልፋችሁዋለን!!

  ሁለት ጊዜ እንቅፋት የመታው ሰው አካሄዱን እንጅ እንቅፋቱን መወንጀል የለበትም!!

  • WEB February 25, 2014 at 3:18 pm Reply

   Why do you extrimely hate MK? You know all your saying is not true, right? be honest for yourself.

   • በአማን ነጸረ February 27, 2014 at 8:16 am

    sorry, I’m not a hate agent!! What i want to see is a respect for rules and regulations of our beloved EOTC!!Most of the time MK management try to externalize all obstacles towards our beloved church administration!! For me, that is not acceptable!!They have their own stake for the mess!!
    But most of them are not willing to take the responsibility!! Rather than resolving differences sitting with our fathers, roaring through the so called private print media and prosecuting fathers using social media became their manifestation!!In my opinion, this kind of making oneself a saint at the cost of exposing and blaming fathers for all misdeeds is hard to swallow!!
    So as an ardent child of EOTC, i began to express my view about the relation of MK and our fathers!! If GOD permits i will continue until they review their approach towards private and social media!! Specially, unless they follow the guidance of HOLY SYNOD and its supremacy with full hearts, i will continue being hesitant!!
    Mind,many clergy members are suspicious not only on MK, but on any event for which MK is a participant!!However, many of the members turned deaf ear!!
    Answering;why many of the priests watch us in suspicion? what should we do to establish a good relation with the priesthood? are we ding enough to be a good medium b/n the EOTC administration and its beloved followers? are we going in line of due respect for assigned administration and laws of the EOTC??,is a parameter to criticize or appreciate MK!!
    ANY WAY, DON’T WORRY, I’M ONLY AGAINST APPROACHES OF MK IN ITS RELATION WITH THE HIERARCHY OF EOTC AND IT’S MEDIA RELATION!!STILL I BELIEVE, WE ARE ALL CHILDREN OF THE SAME MOTHER EOTC!!STILL I RECOGNIZE THE LAST 20 YEARS ACHIEVEMENTS OF MK IN MANY AREAS!!AND MY WISH IS TO SEE, IN THE FUTURE, A BETTER MK W/O THE ABOVE MENTIONED DRAWBACKS!!
    LET THE ALMIGHTY, SON OF ST.MARY HELP US!!

 3. Anonymous February 26, 2014 at 9:07 am Reply

  MAHIBERU HULEGIZEM YENORAL MAHIBERUN LEMATEFAT YEMITERU GENE WOLADITE AMELAKEN ELACHIHUALEHU YETEFALU

  • amhea February 26, 2016 at 1:59 am Reply

   We will to see all power and judgment from our God only. Amalagent kembetachen news.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: