የአ/አበባ ሀ/ስብከት የመዋቅር የአደረጃጀትና የአሠራር መመሪያ ጥናት ሰነድ ርክክብ ተካሔደ፤ የባለሞያ ቡድኑ÷ ጥናቱን ዳግመኛ ለማየት በተቋቋመው የምሁራንና ሊቃውንት ኮሚቴ ላይ አከራካሪ ሐሳቦችን የማብራራት ዕድል እንዲሰጠው ጠይቋል

Expertsየባለሞያ ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ፡-

 • ለባለሞያ ቡድኑ ይህ ታሪካዊ ዕድል ተሰጥቶን ችግር ፈቺ ጥናት እንድናጠና በመደረጋችን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፡
 • የጥናት ቡድኑ ወደ ዋናው የመዋቅርና የአሠራር መመሪያዎች ጥናት ከመግባቱ በፊት ሥራው የተቃና ይኾን ዘንድ በአባቶች ጸሎት እንዲታሰብ መብዓ አሰባስቦ ወደ ገዳማት በመላኩ፣ ለጥናት ቡድኑ ብርታት እንዲኹም ለሥራው መጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

???????????????????????????????

 • የጥቅምት ወር ፳፻፮ ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ባስተላለፈው ውሳኔ የጥናት ሰነዱ በየደረጃው ካሉ ሓላፊዎች ጀምሮ እስከ አጥቢያ ምእመናን ድረስ ወርዶ ውይይት እንዲደረግበት በወሰነው መሠረት ውይይቱ ተከናውኗል፡፡
 • በሀ/ስብከቱ አዳራሽ ለ14 ቀናት በተካሔደው ውይይት÷ የጥናት ሰነዱ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎች፣ የሀ/ስብከቱ የዋና ክፍል ሓላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ሥራ አስኪያጆች፣ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የካህናት፣ የምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች ተወካዮች ሐሳብ የተካተተበትና 96 በመቶ ተቀባይነት ያገኘ በመኾኑ ከአኹን በኋላ የመላው የቤተ ክርስቲያኒቱ አማኞች ሰነድ ነው ብለን እናምናለን፡፡
 • ለዝግጅቱ መሳካት አስተዋፅኦ ያደረጉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችና አገልጋዮች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሓላፊዎች፣ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ ከምንምና ከማንም በላይ ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው ድረስ በኹሉ ነገር ያልተለዩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
 • መታሰቢያነቱ የለውጥ እንቅስቃሴውን ላስጀመሩት ለብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ለካህናት፣ ለሰንበት ት/ቤቶችና ለምእመናን እንዲኾን እንመኛለን፡፡
 • በመዋቅርና መመሪያዎች ጥናት ሒደት በርካታ ተግዳሮቶች የገጠሙን ቢኾንም በእግዚአብሔር ቸርነት አልፈናቸዋል፡፡ ሳንጠቅስ የማናልፈው ግን፣ በሰነዱ ይዘት ላይ ሳይኾን በአጥኝው አካል ላይ ቅሬታ ያላቸው አካላት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ ከጥናቱ ጋራ ምንም ግንኙነት የሌለው አካል እንዳዘጋጀው ተደርጎ ሥራውን ውድቅ ለማድረግ የሥራው ባለቤቶች የኾን እኛን ሳያነጋገሩ ወደ ውሳኔ የተኼደበት መንገድ አግባብ ነው ብለን አናምንም፡፡
 • ጥናቱን ዳግመኛ ለማየት የተቋቋመው ኮሚቴ በሥራው ሒደት የማይቀበለውን ሐሳብ በቀጥታ ከመጣ ይልቅ ለምን በሰነዱ እንደተካተተ ለማብራራት ዕድሉን እንዲሰጠን እንጠይቃለን፡፡
 • ጥናቱ በቅ/ሲኖዶስ ታምኖበት ሲጸድቅ ዝርዝር የትግበራ ስልቱን ከእያንዳንዱ መመሪያና ፖሊሲ በርካታ ቅጻቅጾችና አባሪዎች ጋራ ሠርተን ለማቅረብ ዝግጁዎች ነን፡፡
 • ይህ ሰነድ የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር በኹሉም ዘርፍ በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመኾኑ፣ በቅዱስ ፓትርያርኩ በአንድ ወቅት እንደተነገረው፣ ከሌሎች አህጉረ ስብከት ነባራዊ ኹኔታ ጋራ እየተጣጣመ ለእነርሱ በሚኾን አግባብ እንዲዘጋጅላቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተመክሮበት አቅጣጫ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን፡፡

የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን፡-

 • ቅዱስ አባታችን÷ ሀ/ስብከቱና ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ናቸው ይህን ጥናት ያስጀመሩት፤ ብፁዕነታቸው ከሀ/ስብከቱ ጋራ ተረካክበው ያምጡልኝ ብለዋል፤ በብፁዕነታቸው ሲቀርብላቸው ቅዱስነታቸው ለሚመለከተው አካል ያስረክባሉ፡፡Handing over ceremony of the A.A Dioceses Change mgt doc00
 • ሊቃውንት ይዩት መባሉ በኹሉም አቅጣጫ ታይቶ ዕንከን የለሽ ሕግ ለማውጣት ያስችላል፤ ለአንድ ዓላማ እየተነጋገርን የአስተሳሰባችን ደረጃና አካሔዳችን ሊለያይ ይችላል፤ ኹሉም ግን ቤተ ክርስቲያን እንድታድግ ነው የሚፈልገው፤ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅመውን ነገር ደግሞ እግዚአብሔር አያስቀረውም፡፡

በሀ/ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፡-

 • በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደ መነሻ የሚኾን፣ እንድናስብ የሚያስችል ጥናት በእናንተ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ተረቆ ለቤተ ክርስቲያን እንዲሰጥ አድርጋችኋል፤ ከቅዱስ አባታችን ጋራ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ባሉበት እንደምትወያዩ እንደሚባርኳችኹ ተነጋግረናል፤ የምስጋና ደብዳቤ በቅዱስ አባታችን እንዲደርሳችኹ እናደርጋለን፡፡ የሰዎችን ድካም የማያስቀር አምላክ ድካማችኹንን ይቀበልላችኹ፡፡ በጎ አገልግሎታችኹን እግዚአብሔር አያጉድልባችኹ፡፡

His Grace Abun Estifanos recieving the doc

 • ቅዱስ አባታችን ሰነዱ ለመጪው ርክበ ካህናት እንዲቀርብ አኹን ለምን አታመጡም ይሉን ነበር፤ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰነዱ ሥራ ላይ የሚውልበትን ሒደት እየቀየሱ ነው፤ አስረከባችኹ እንጂ ሥራችኹ አላበቃም፤ ተጠርታችኹ ጥያቄ ሊቀርብላችኹ ስለሚችል ማስተካከያ በሚያስፈልግበት ጊዜ ኹሉ ተሳትፎ ይኖራችኋል ብዬ አስባለኹ፡፡
 • አዲስ ነገር መጣ ሲባል ተቃዋሚም ደጋፊም መፈጠሩ ቅር የሚያሰኝ ነገር አይደለም፤ ከተነጋገሩ በኋላ የደከሙበት ነገር መና ሲቀር ነው የሚያሳዝነው እንጂ፡፡ ቃለ ዐዋዲው በወጣበት ወቅትም ብዙ ውጣ ውረድ እንደነበረበት ይታወቃል፡፡ ቃለ ዐዋዲው አዲስ ስለነበር ሰበካ ጉባኤ ይቋቋማል፤ ምእመናን ይገባሉ ሲባል መባዕ የሚቀበሉ ገበዞስለነበሩ ‹ይኼ የሌሎች አሠራር ነው› በሚል ይቃወሙት ነበር፤ ጥሩ ነው የሚሉ ደጋፊዎችም ነበሩት፡፡
 • ዛሬም በሰነዱ ዙሪያ እያየነው ያለነው ነገር በመዋቅር ጥናቱ ላይ ያተኮረ ከኾነ መደገፍም መቃወምም መብት ነው፤ ቅዱስ ሲኖዶሱም ሰነዱ ወደ ታች ወርዶ የሚቀነሰው ተቀንሶ የሚጨመረው ተጨምሮ በውይይት ዳብሮ የተስማሙበትን ሐሳብ ይዛችኹ ቅረቡ ነው የተባልነው፡፡ ሰይጣን ሰዎችን አጣልቶ ራሱ ይሥቃል ይባላል፤ መነቃቀፉ መተቻቸቱ ለጠላት ጥሩ ነው፤ ለቤተ ክርስቲያናችን ግን ጎጂ ነው፤ መደማመጡ መከባበሩ ነው የሚበጀን፡፡ ሲቃወምም ሲደግፍም የነበረ በመጨረሻ ወደ አንድ መጥቶ ለትግበራ ሲሰለፍ ደስ ያሰኛል፤ ኹላችንም ወደ አንድ መጥተን ቤተ ክርስቲያናችንን እንድንታደጋት ነው የሚያስፈልገው፡፡
 • ብጣሽ ወረቀት ከኛ ሳትጠየቁ እኛም አንዳች ነገር ሳንሰጣችኹ ለቤተ ክርስቲያን ቋሚ አገልግሎት ሊሰጥ በሚችል መንገድ ሌት ተቀን ደክማችኹ አዘጋጅታችኹ ያስረከባችኹንን ሞያዊ ዐሥራታችኹን በነገው ዕለት ለቋሚ ሲኖዶሱ እናስረክባለን፡፡

the team with his grace abune estifanos

 • ነገ የጥናት ሰነዱን ለቋሚ ሲኖዶስ ካስረከብን በኋላ የራሳችንን ሓላፊነት ተወጥተናል ማለት ነው፤ ከዚያ በኋላ ባለቤቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያናችን የሚሠራ በቂ ሕግ ነው ብሎ ሲያምን ጸድቆ ይተገበራል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: